You are on page 1of 44

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች

ልማት ኮርፖሬሽን የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት


የ2013 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

የካቲት 2013 ዓ.ም


ክፍል አንድ
መግቢያ
 የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ደንብ ቁጥር
143/2008 ከተቋቋመ በኋላ በክልሉ 8 ዋና ዋና ከተሞች ቅ/ጽ/ቤቶችን ከጥር/2009 ጀምሮ
በማቋቋም ተልዕኮውን ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ያለ የክልሉ የልማት ድርጅት ነው
 የኮምቦልቻ ከተማ ቅ/ጽ/ቤትም የኮርፖሬሽኑን ተልእኮ፣ ራዕይና እሴቶች ለማሳካት
የራሱን ዓመታዊ እቅድ በማቀድ ፤ እቀዱን ለፈጻሚ አካላት እና ባለድርሻ አካላት
በማስተዋወቅ የተደራጀ የተግባር ስምሪት በመስጠት አፈጻጸሙን እየገመገሙ
ጥንካሬዎችንና መልካም አጋጣሚዎችን በመለየት እንዲሁም ድክመቶችንና ችግሮችን
እየለየ እንዲፈቱ በግብረ መልስ መልክ ለሚመለከታቸው አካላት በመስጠት ያለንበትን
ሁኔታ ተመስርተው ድጋፍ እንዲሰጡ በአጫጭር ኢንፎርሜሽን ማስተላለፊያ መንገዶች
እና በመደበኛው የሳምንት የወርና የሩብ አመት ሪፖርቶችን በማድረግ ስራውን በማስተባበር
ላይ እንገኛለን
 በመሆኑም በ2013ዓ/ም በግማሽ አመት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ውጤቶች
የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ያጋጠሙ ችግሮችና የተፈቱባቸው አግባቦች አሁንም
ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች በመለየት ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርት ከዚህ በታች
በአጭሩ ይቀርባል
ክፍል ሁለት
የ2013 የበጀት አመት የግማሽ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
 2.1. በዝግጅት ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች
 የ2012 ዓ/ም የእቅድ አፈጻጸም በማኔጅመንት እና በጠቅላላ ሰራተኞች በጋራ ተገምግሞ
የቅ/ጽ/ቤታችን የአፈጻጸም ደረጃ እንዲሁም የነበሩ ጥንካሬዎችንና ድክመቶች
አጋጥመው የነበሩ ችግሮችና የተፈቱበት አግባብ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን
በመለየት የተጠቃለለ ሪፖርት ለሚመለከታቸው አካላት የተላለፈ ሲሆን ለ2013ዓ/ም
የእቅድ መነሻ ተደርጎ ተወስዷል
 የባለሀብቶች ፕሮፋይል በዝርዝር ተጠንቶ እያንዳንዱ ፕሮጀክት ያለበት የግንባታ ደረጃ
ለኮርፖሬሽኑ ተላልፏል
 ለቅ/ጽ/ቤቱ አስፈላጊው የካፒታል በጀት እና የመደበኛ በጀት ጥያቄ በዝርዝር ተሰርቶ
ለኮርፖሬሽኑ ጥያቄ ቀርቧል
 የ2013 ዝርዝር የፊዚካል ስራ እቅድ በማቀድ ለኮርፖሬሽኑ በወቅቱ ተልኳል

 በእቅዱ ላይ ማኔጅመንቱ መላው ሰራተኛ በተደራጀ የኦረንቴሽን መድረክ ግልጽነት


እንዲያዝበት የጋራ መግባባትና መተማመን ላይ የሚያደርስ ውይይት ተካሂዶ እቅድ
በመላ ሰራተኛው ጸድቆ መደ ትግበራ ተሸጋግሯል

 ከከተማ አስተዳደሩ እና ከልዩ ልዩ ተቋማት የሚያስፈልገውን ድጋፍ በመለየት
የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት ተደርጓል
 በዞኑ እና በከተማው የአመራር መድረኮች ላይ በመገኘት የኢንዱስትሪ
ልማቱን በተለይ የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆዎች እና መልካም
አጋጣሚዎች በማስረዳት በየደረጃው ያለ አመራር ለአምራች ኢንዱስትሪው
ትኩረት ሰጥቶ አመራር እንዲሰጥ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል
 በዝግጅት ምዕራፍ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት የማስፈፀሚያ ቼክሊስት
ተዘጋጅቶ በማኔጅመንት በሰራተኛው እየተገመገመ መመራት በመቻሉ
ለተግባር ምዕራፍ መነሻ የሚሆኑ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራትን ማከናወን
ችለናል በተለይ ሁሉም ቡድኖች በእቅድና በቼክሊስት ስራዎቻቸውን
እንዲመሩ፣ በማድረግ ተችሏል በተለይ ኮርፖሬሽናችን በአዲስ መልክ
የተከተለውን የየእለት የሰራተኛ እቅድ የማቀድና ሪፖርት የማድረግ የሳምንት
የቡድን እቅድና ሪፖርት የማድረግ አሰራር በእምነት ተይዞ እንዲተገበር ተደርጓል

 በሁለቱ የካይዘን ቡድኖች የአፈጻጸም ግምገማዎችን እያደረጉ የመማማርና ልምድ
የማዳበር ስራ እንዲሰሩ ማኔጅመንቱ በየሳምንቱ እየተሰበሰበ ውሳኔና አቅጣጫ
የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች እየወሰነ አመራር እንዲሰጥ፣ ጠቅላላ ሰራተኛው ደግሞ
በየወሩ ስራዎችን በጋራ እየገመገመና እየተሳተፈ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ
ጥረት ተደርጓል
 በአመቱ መጀመሪያ የቅ/ጽ/ቤቱ እቅድ በውጤት ተኮር መልክ በመዘርዘር/cascading/
በማድረግ ለሁሉም ቡድኖችና ሰራተኞች የተቆጠረ እቅድ በመስጠት ወደ ስራ
እንዲገቡ ተደርጓል አፈጻጸሙን በስራ በቡድንና በከይዘን ልማት ቡድን እየተገመገሙ
እንዲሄዱ ተደርጓል
 በዝግጅት ምእራፍ ውስጥ ሆነን ከባለሀብቶቻችን ጋር አጫጭር የውይይት መድረኮችን
በማደራጀት ሁሉም ባለሀብቶች በክረምቱ ማጠናቀቅ የሚገባቸውን የቅድመ ዝግጅት
ስራዎች/ የቅድመ ግንባታ ተግባራት/ አጠናቀው በተግባር ምዕራፍ ወደ ተሟላ ትግበራ
እንዲሸገገሩ በርካታ መድረኮች ተደራጅተዋል ውጤት ያላሳዩት ላይ ደግሞ አስተዳደራዊ
ርምጃዎች ተወስደዋል/ ማስጠንቀቂያዎች እና የማነቂያ ደብዳቤዎች/ተሰጥቷል በዚህም
አብዝሀኛዎቹ ባለሀብቶች በዝግጅት ምዕራፍ ማሟላት የሚገባቸውን በማሟላት
በፍጥነት ወደ ግንባታ መሸጋገር በመቻላቸው አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል
2.2. በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተግባራት
 የ2013 በጀት አመት የቅ/ጽ/ቤታችን ቁልፍ ተግባር የመፈጸም አቅምን ማሳደግ እንደሆነ
በእቅዳችን በግልጽ ተመልክቷል በዚህም የአመራሩን እና የባለሙያውን የመፈፀም አቅም
በማሳደግ የክህሎት የእውቀትና የውጤታማነት ደረጃውን ከፍ የማድረግ፣ የኮርፖሬሽኑን
አሰራርና አደረጃጀት በየጊዜው እየፈተሸ ለማሻሻልና ለማዘመን ጥረት በማድረግ
ተግባራትን በተሟላ መልኩ መፈፀም፣ ለእቅዱ ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን
በተሟላ መልኩ የማቅረብና የበጀት አጠቃቀማችንን ውጤታማነት ማሳደግ የቁልፍ
ተግባራችን ቁልፍ ገጽታዎች እንዲሆኑ በእቅዳችን በግልጽ በማስቀመጥ ወደ ተግባር
ገብተናል፡፡ ቁልፍ ተግባሩን ለማሳካት የትኩረት መስኮቻችንን ለይተናል የትኩረት
አቅጣጫዎቻችንንም ተመልክተዋል ልናሳካቸው የሚገቡ ግቦቻችንንም በግልጽ አስቀምጠን
ወደ ስራ ገብተናል የአፈጻጸም ደረጃዎችንም አመልክተናል፣ ተግባራቶቹም የሚፈፀሙበት
የድርጊት መርሀ ግብር ተዘጋጅቶላቸዋል ፈጻሚ አካላትም በግልጽ ተለይቶ ወደ ትግበራ
ተሸጋግረናል
 የክትትልና ድጋፍ ስርዓቱም ወቅታዊ ሪፖርት ግምገማዎችና የአካል ምልከታና በግብረ መልስ
መልክ ሳይንጠባጠቡ የሚተገበሩ እንዲሆኑ በእቅዶቻችን አመላክተን ወደ ስራ ገብተናል
ለስራው የሚያስፈልግ በጀትም በግልጽ ተመልክቷል ከዚህ በመነሳት በገማሽ አመት በየዘርፉ
ምን አቀድን? ምን አከናወንን? ምን ውጤት አገኘን? ምን ይቀረናል? የሚሉትን ጉዳዮች
በአጭሩ ከዚህ በታች ይቀርባሉ፡፡

1. በሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ታቅደው የተከነወኑ ተግባራትና የተገኙ
ውጤቶች
 የቅ/ጽ/ቤቱ መዋቅር 42 ሲሆን አሁን በስራ ላይ ያለ የሰው ሀይል

 ቋሚ ወ፡-11 ሴ፡- 3 ድ፡- 14

 ኮንትራት ወ፡- 2 ሴ፡- - ድ፡-2

 በጠቅላላው 16 የሰው ሀይል ወይም 38 % ይሸፍናል

 ሰራተኛው በእቅደ እንዲመራ ተደርጓል የ6 ወር ውጤት ተኮር እቅድ ተሰርቷል የየእለት


እቅድና የአፈጸጸም ሪፖርት በተከታታይ ይደረጋል በቡድኖች የሳምንት እቅድና ሪፖርት
የማደረግ አሰራር ተፈጥሯል
 የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም /የደንብ ልብስና የሙያ አበል/ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች
የኮርፖሬሽኑ መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት ተፈጻሚ ሆኗል
 የሰራተኛውን አቅም ለማጎልበት በሁለት የከይዘን ቡድኖች የስራ አፈጻጸም
ግምገማዎችና የመማማር ተግባራት ወቅቱን ጠብቀው ይከናወናሉ እስከአሁን
እያንዳንዳቸው 10 ጊዜ መወያየት ነበረባቸው 10 ጊዜ/100%/ የሚሸፍን ውይይት
አካሂደዋል

 በየሩብ አመቱ የከይዘን ቀን ሁሉም ሰራተኛው በተሳተፈበት ይከበራል እስከአሁን 1 ጊዜ
መካሄድ ነበረበት የመጀመሪያው ረብ አመት የተካሄደ ሲሆን የ2ኛው ሩብ አመት
በሚቀጥለው ሳምንት የሚካሄድ ይሆናል
 በቅ/ጽ/ቤታችን በአመቱ መጀመሪያ ግምገማ አዘል ስልጠና ተሰቶል/የ2012 የእቅድ
አፈጻጸምና የ2013 እቅድ መነሻወቸ ግቦችና የሚከናወኑ ተግባራትና የማስፈፀሚያ ስልቶቸ
ላይ ተመስርቶ ውይይት ተካሂዷል
 ይህም በሰራተኛው ውስጥ ተስፋ፤ የስራ መነቃቃት በከፍተኛ ደረጃ ፈጥሯል

 የቅ/ጽ/ቤቱ የስራ አካባቢ ለሰራተኞች የተመቸ እንዲሆን ቢሮው ሳቢና ማራኪ እንዲሆን
በሰራነው ስራ ሰራተኛው ደስተኛ ሆኖ ተግባሩን በማከናወን ላይ ይገኛል/የጽ/ቤቱ ግቢ አጥር
እንደታጠረና በገቢውነ ውስጥ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እንዲሰሩ በማድረግ የተሸለ የስራ
አካባቢ ተፈጠሯል
 በአጠቃላይ በቅ/ጽ/ቤታችን በኩል በስራ አመራሩ በሙያተኛውና በድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች
መካከል ስራን ማዕከል ያደረገ መልካም ግንኙነት እየተፈጠረና እያደገ መጥቷል የአገልግሎት
አሰጣጣችንም እያደገ መጥቷል
 የ6 ወር እቅድ አፈጻጸመ የመገምገምና የቀጣይ 6 ወራት ውቴት ተኮር እቅድ የማዘጋጀት
ስራ እየተከወነ ሲሆነ ተጠቃሎ ለኮፖሬሽኑ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል
2.3. የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ተግባራት
 በግማሽ አመቱ በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ ከክላስተር ማዕከላት ኪራይ እና ከልዩ ልዩ
አገልግሎቶች በአመቱ 1183341.63 ብር ለመሰብሰብ እንዲሁም በ6 ወሩ ገቢ
566,687.79 ሲሆን ተሰብስቦ ገቢ የሆነው 400,556.39 ብር ወይም ከአመቱ
33.85% ከ6 ወሩ 71% አፈጻጸም ማስመዝገብ ተችሏል
 አፈጻጸማችን ሊቀንስ የቻለው የክላስተር ህንጻዎቹ በወቅቱ ወደ
ኢንተርፕራይዞች በኪራይ አለመተላለፋቸውና በሁለገብ ኢንዱስትሪ
ፓርኮች ወደ ስራ ያልገቡ ባለሀብቶች በመኖራቸው ከአገልግሎት መሰብሰብ
ያለብንን ገቢ መሰብሰብ አለመቻላችን ነው የተወሰኑ ኢንተርፕራይዞች
ደግሞ ውዝፍ ገቢ በመፍጠራቸው ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ ህግ
የተመሩ በመሆኑ ነው
 በግማሽ አመቱ ለደመወዝና ስራ ማስኬጃ የተጠየቀው 1,373,352.33 ሲሆን
የተለቀቀልን 1,317,352 ነው አፈጻጸማችን ሲገመገም ለደመወዝ
1,073,226.82 ለስራ ማስኬጃ 272,453.19 በድምሩ 1,345,680.01 ስራ ላይ
ውሏል ይህም ከእቅዳችን 95% አፈጻጸማችን ያሳያል

 የገቢ አቅማችን እያነሰ የወጭ ፍላጎታችን እየጨመረ በመሄዱ ምክንያት
የተፈጠረውን ጫና ለማጣጣም ገቢያችንን አሟጠን ለመሰብሰብ ወጭን
በቁጠባ እና በውጤታማነት ለመጠቀም ጥረት አድርገናል ነገር ግን
ለወደፊቱም ቢሆን ስራችንን በተሟላ መንገድ ለመፈፀም የምንችልበት እና
መደበኛ ወጭያችንን የሚያካክስ በጀት ስላልተመደበልን ኮርፖሬሽኑu በልዩ
ሁኔታ አይቶ ችግሩ እንዲፈታ በወቅቱ የማሳወቅ ስራ ተስርቷል
 ለልማት ማስፈጸሚያ የተጠየቀው የካፒታል ወጭ በአመቱ ስላልተፈቀደ ስራ
ላይ የዋለ የለም
 የግዥ ስርዓቱ በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ መሰረት በተጠቃለለ ግዥ
እንዲፈፀም ተደርጓል
 በራሳችን አቅም ሊፈቱ የሚችሉትን አነስተኛ ወጨዎች ባለሀብቶችን ፤
ኢንተርፕራይዞችን በማስተባበር ጭምር እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩም
ድጋፍ እንዲደረግ በማድረግ የመፍታት አቅጣጫዎችን ተከትለን አበረታች
ውጤቶችን አስመዝግበናል
3.የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች
 ሀ/መሰረተ ልማት ማሟላት
 የኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት የሚያስተዳድራቸው አምስት ሁለገብ ኢንዱስትሪ
ፓርኮች ሲሆኑ/ ኮምቦልቻ ቁ.1፣ቁ2፣ ቁ.3 ቀ.4 /ጥጥ ሜዳ/እና የሀርቡ /አዲስ
መንደር/ ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ያሉባቸው የመሰረተ ልማት ችግሮች
በጥናት እንዲለይ ተደርጓል
 የመንገድ የውሀ የመብራት የውሀ መፍሰሻ ስትራክቸሮች የተሟላላቸው
አለመሆኑ በጥናት ተለይቷል
 ከዚህ በተጨማሪ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት አመታት በጀት ይዞ የሰራቸው መሰረተ
ልማቶች በኮንትራት ውላቸው መሰረት አለመጠናቀቅ ችግሮች ተለይተዋል
 ለኮምቦልቻ ቁ.2 ኢንዱስትሪ መንደር 7 MW የመብራት ሀይል አቅርቦት 8.42
km የሚውል 9,620,442.57 ብር ለመስመር ክፍያ ተጠንቶ ለክልሉ ቀርቦ
ከክልሉ ኢንዱስተሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በጀቱ የተለቀቀ ሲሆን ለማብራ
ሃይል ደሴ ዲስትሪክት ገቢ ተደርጓል፡፡ በቀሪ ጊዜ የፊዚካል ስራ አፈጻጸሙ
ክትትል እየተደረገ ሪፖርት የሚደረግ ይሆናል

 አሁንም ግን ከአቅም በላይ የሆነውና በመሰረተ ልማት ችግር /የውሀ፣
የመንገድ፣ የመብራት ሀይል/ መሰረተ ልማት ባለመሟላቱ የሀርቡ ሁለገብ
ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ ማስጀመር ያልተቻለ በመሆኑ በቀጣይም የክልሉን
ውሳኔ የሚጠይቅ ነው
 በቃሉ/ሀርቡ ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ/ ተከልሎ ወደ ባለሀብቶች የተላለፈው
50ሄ/ር መሬት ግን የ ውሀ መስመር 13.2 km 21,418,938.60 ብር፣ ለ 5.53
km መንገድ 45,598,567.68 ፣ ለመብራት ሀይል አቅርቦት 24,584,426.78
ብር ተጠንቶ ለኮርፖሬሽኑ የቀረበ ሲሆን እስከ አሁን ምላሽ ባለመሰጠቱ
ልማቱንም ማስቀጠል አልተቻለም ባለሀብቶቹም በከፍተኛ ደረጃ ቅሬታ
በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኮርፖሬሽኑም ጉዳዩን በባልተቤትነት ይዞች ችግሩ
እንዲፈታ በውይይተ መድረኮችም በሪፖፖታችንም ቀረብነ በመሀኑ አሁንም
ትኩረት ተሰጥተቶት መፍትሄ የሚሻው ችግራችን መሆነን በድጋሜ
እንገልጻለን


ለ/ መሬት ማስተላለፍና ማስተዳደር
 በነባርም በአዲስ የሚለሙ መሬቶችን ለባለሀብቶች ለማስተላለፍ በተሰራው ስራ ሀርቡ ላይ
3072 ካ.ሜ ለ1 ባለሃብት እና ኮምቦልቻ ቁ.2 እና ቁ.3 ኢንዱስትሪ መንደር ለ2 ባለሃበት
6751ካ.ሜ መሬት ተላልፎል ባጠቃላይ ለ3 ባላሀብቶች 9823 ካ.ሜ መሬት ማስተላለፍ
ተችሎል፡፡
 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቀጥር 2 በመሰረተ ልማት ምክንያት ያለማውን 24 ሄ/ር መሬት
ለማልማት ፍላጎት ያሳዩ ባለሀብቶች በመጠየቃቸው ለመሰረተ ልማቱ /ለመንገድ እና ለድልድይ
ግንባታ/ የሚያስፈልገውን ወጭ /ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት የዳሰሳ ጥናት እና የቅየሳ
ስራ ተሰርቶል ቀሪው ስራ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ፍላጎት ያላቸውን ባለሃብቶች መልምሎ
መላክ ነው፡፡
 ወደ ልማት ያልገቡ 3 ባለሀብቶች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ተጨባጭ ለውጥ
ባለማሳየታቸው 2.2ሄ/ር መሬት የማስመለስ እርምጃ ተወስዷል
 በሁ/ኢ/ፓርኮች ከባለሀብት የተመለሱና በክፍትነት የነበሩ ተጨማሪ መሬቶችን 197000 ካ/ሜ
ለ9 ባሀብቶች እንዲተላለፉ የከተማ አሰተዳደሩ በወሰነው መሰረት ወደ ተግባር ተገብቶ ነበር
ነገር ግን ከባሀብችም ምልመላ ጋር ተያይዞ በተነሳው ቅሬታና በቀረበ የሙስና ክስ ምክንያት
ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ እልባት እስከሚሰጠው ድረስ መሬት የማስተላለፍ ተግባር ባለሀብት
እንዲቆም ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን

 ሐ/ አገልግሎት አሰጣጣችንን ማሻሻል
 የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታችን በማሻሻል የደንበኞች እርካታን ለማሳደግ
በተሰራው ስራ ባለሀብቶች በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚያጋጥማቸው
ችግሮች በአብዝሀኛው ከቅ/ጽ/ቤታችን ውጭ ያሉ ችግሮች ናቸው
 ከፕላን ስምምነትና ዲዛይን ማጽደቅ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ከከተማው
ህንጻ ሹም ጋር በመቀናጀት የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል
 ከውሀ መስመር መቆረጥና የውሀ ስርጭት ችግሮች ከከተማው ውሀ
አገልግሎት ከከተማው አስተዳደርና የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀትና ችግሩ
ሲከሰት አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ በርካታ ጥረት ተደርጓል
 ከመብራት ሀይል መቆራረጥ እና የሀይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ አፋጣኝ ምላሽ
ያላገኙት አንድ የመሰረተ ልማት ባለሙያ በቋሚነት በመመደብ እና ከተቋማቱ
ጋር በመቀናጀት እንዲፈታላቸው ጥረት ተደርጓል
 የከንቲባ ኮሚቴ እና የማኔጅመንት ኮሚቴ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
ለሚመለከተው አካል እየቀረቡ እንዲፈቱላቸው ተደርጓል

 በባለሀብቶቹ በራሳቸው የሚፈቱ ችግሮች እንደየ ፕሮጀክታቸው የአፈጻጸም ደረጃ
ለባሀብቶች አጫጭር የውይይት መድረኮችን በተከታታይ በማደራት እንዲፈቱና
ወደ ተሟላ ስራ ውስጥ እንዲገቡ ጥረት ተደርጓል
 በቅ/ጸ/ቤታችን የሚሰጠ ሀሉም አገልግሎቶች በስንዳርዳችንና ከስታንንርዱ ባነሰ
ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል
 ከዚህ በተጨማሪ ባለፉት አመታት ከጅኤምቲ ኢንዱስትሪያል ሃ/የተ/የገ/ማህበር
የተነጠቀው 30,000ካ/ሜ ለ2 ባለሀብቶች ተላልፎ ግንባታ እየተካሄደበት ሲሀን
መሬት የተነጠኩት ያለ አግባብ ነው የንብረት ግምት አላግባብ ተሰርቶ ክትትል
ሌሎች ያወጣኋቸው ወጭዎች ሊሸፍንልኝ ይገባል በሚሉ ጉዳዮች ክስ የመሰረተ
ሲሆን በጠ/ፍ/ቤት በክርክር ላይ ይገኛል
 በሌላ በኩል በከተማው ለሁለገብ ኢንዱሰትሪ ፓርክ ለመከለል ባለመቻ እና መሰረተ
ልማት ለማሟላትና ለካሳ ክፍያ የሚሆን መሬት ባለመዘጋጀቱ በቅ/ጽ/ቤታችንም
በኩል መሬት ባልተዘጋጀበት የባለሀብቶች ፕሮጀክት ለመቀጠል እንቸገራለን
በማለትነና አንቀበልም በማለታችን ከ250 በላይ ባለሀብቶች ከ400ሄ/ር በላይ
መሬት ጠየቀው ማስተነገድ አልተቻለም
4.የክላስተር ማዕከላትን ማስተላለፍና ማስተዳደር
 የክላስተር ማዕከሎቻችን በደሴ ከተማ 4 ህንጻዎች በኮምቦልቻ ከተማ 4
ህንጻዎች በድምሩ 8 ህንጻዎችን ቅ/ጽ/ቤታችን ተረክቦ እያስተዳደረ ሲሆን
በግማሽ አመቱ በተሰራው ስራ ማዕከላቱ ያሉባቸው የመሰረተ ልማት/ የውሀ፣
የመብራት፣ የፍሳሽ ማስረጊያ መሰረተ ልማቶች/ ቀደም ሲል የተጠናው ጥናት
በመከለስ የስራ ዝርዝር እና የሚያስፈልገው ወጭ ተሰርቶ ለኮርፖሬሽኑ እንዲላክ
ተደርጓል/ለደሴ 1.6 ሚሊዮን፤ለኮምቦልቻ፣860 ሽህ ብር/ ያስፈልገናል ነገር ግን
በጀት መመደብ ባለመቻ ስራዎች መስራት አልቻሉም ህንጻዎችም ለተጨማሪ
ችገር እየተጋለጡ ይገኛሉ
 ትንንሽ ችግሮችን/የመብራት ቆጣሪና ትራንስፎርመር መበላሸት፣ የፍሳሽ
መስመር መበላሸት ወ.ዘ.ተ./ ኢንተርፕራይዞችን በማስተባበር እንዲሸፍን
ተደርጓል
 ያልተከራዩ ወለሎች ወደ ኢንተርፕራይዞች ወይም አነስተኛ መካከለኛ
ባለሀብቶች እንዲተላለፍ ከሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ኢንዱስትሪና
ኢንቨስትመንት ተቋማት ከቴ/ሙያ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤቶች እንዲሁም ከከተማ
አስተዳደሮች ጋር በመነጋገር በኪራይ የማስተላለፍ ስራ ተሰርቷል

 በዚሁ መሰረት
 ደሴ 828.26 ካ/ሜ የመስሪያ ቦታ ለ4 ኢንተርፕራይዝ የማስተላለፍ ስራ የተሰራ
ሲሆን በኪራይ የተላለፈው የመስሪያ ወለል በ2011 ከነበረበት 92% አሁን ወደ
94.73% ማሳደግ ተችሏል ቀሪው 511.69 ካ/ሜ ለማስተላለፍ የምልመላ ስራዎች
እንዲሰሩ ለሚመለከታቸው አካላት በስልክ እና በአካል የማሳወቅ ስራ ተሰርቶል
በሚቀጥለው ጊዜ አፈጻጸሙን ወደ 100% ለማሳደግ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር
በመቀናጀት እየሰራን እንገኛለን
 ኮምቦልቻ ላይ የቅ/ጽ/ቤታችን ለቢሮ አገልግሎት ከሚጠቀምበት ወለል ውጭ
ያልተከራየ ወለል የለንም ይህም ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት
የተሻለ ስራ መስራት ተችሏል
 በዘርፉ የሚታየው ችግር አቅም ያላቸውን ኢንተርፕራይዞች አለመመልመል ፣
ወርሀዊ ክፍያቸውን በወቅቱ አለመክፈል /ውዝፍ መፍጠር/ በኮርፖሬሽኑ በኩል
ደግሞ የክላስተር ማዕከላቱን መሰረተ ልማት ትኩረት ሰጥቶ ያለማሟላት ሲሆን
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በቀጣይም በሁሉም አካላት በኩል ትኩረት
የሚያስፈልጋቸው ናቸው
5. የፕሮሞሽንና የህዝብ ግንኙነት
 የፕሮሞሽን እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በተለያየ መልኩ ለመስራት ጥረት ተደርጓል
 የመጀመሪያው እቅዳችንን መሰረት ያደረገ የኦረንቴሽን መድረኮችን ለማደራጀት
ለውስጥ ሰራተኞቻችን ግልጽነትና የጋራ መግባባት የመፍጠር በየደረጃው በተደራጁት
የዞንና የከተማ አስተዳደር መድረኮች በመሳተፍ ተልእኳችንን ለማሳካት
የምንፈልጋቸው ድጋፎች በማብራራትና በመጠየቅ ቅ/ጽ/ቤታችን አቅዶ
የሚተገብራቸውን ተግባራት ለባለሀብቶች ለአመራሮች መረጃዎችን በመስጠት
በቅ/ጽ/ቤታች የማህበራዊ ድህረገጽ በየጊዜው መረጃዎችን በመልቀቅ እየተሰራ
ይገኛል፡፡ ከዚሀ በተጨማሪ የአዲስ አመት የዘመን መለወጫ ወቅትን ምክንያት
በማደረግ በኮርፖሬሽኑ ስም ማስታወሻ /አጀንዳ/ በማስተላለፍ በማሰራጨት
የኮርፖሬሽኑን አርማ የያዘ ቲሸርት ለሰራተኛውና ለልዩ ልዩ የስራ ሀላፊዎች አሳትሞ
በማሰራጨት እና መጽሄት አሳትሞ በመሰራጨት ሰፊ የፕሮጀክት ስራዎች
ተከናውነዋል
 ነገር ግን በዚህ ረገድ አሁንም የሚፈለው ስራ በቅንጅት ተሰርቶ ተፈላጊው ውጤት
መጥቷል የሚባል ደረጃ ገና አልደረሰም በመሆኑም የቀጣዩ የትኩረት አቅጣጫዎችን
ይሆናል
6. የአካባቢ ጥበቃና ልማት ስራ
 ሀ/አረንጓዴ ልማት ፤-የሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና የክላስተር ማዕከላትን ሳቢና
ማራኪ ለማድረግ ባለሀብቶችን በማስተባበር በተለይ ወደ ማምረት የተሸጋገሩ
ባለሀብቶች የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እንዲያከናውኑ ተደርጓል
 በራሳቸው ወጭ ችግኞችን በመትከል አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ
ጀምረዋል ባለሀብቶችበዲዛይናቸው መሰረት ከ10-20% በላይ መሬት ለአረንጓደ
ልማት የሚውል እንደሆነ ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል በፓርኮቹ ውስጥ
31.45ሄ/ር መሬት ወደፊት በአረንጓዴ ልማት የሚሸፈን መሆኑ ተለይቷል
 በፓርኩ ውስጥ ከ70ሄ/ር በላይ መሬት በጎርጅና ሸለቆ የተያዘ ሲሆን ከልሎ በመጠበቅ
ብቻ የወደፊቱ የኢንዱስትሪዎቹ መተንፈሻ አካባቢ በመሆኑ ከንክኪ ነጻ ለማድረግ
ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ማልማት የሚጠይቅ ነው ነገር ግን አሁን ከልሎ
ለማልማት በአካባቢው አ/አደሮች በኩለ ከካሳ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች የሚነሱበት
በመሆኑ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት ይጠይቃል
 ባለሀብቶችን በማስተባበር በክረምት ወራት 6258 ልዩ ልዩ ችግኞች የተተከሉ
ሲሆን በቅ/ጽ/ቤታችን የክላስተር ማዕከላት 142 ችግኞች ለማስተከል ተችሏል
ችግግችን የመረካከብና በዘላቂነት የመጠበቅ ስራ እየተካሄደ ይገኛል

 ለ/አካባቢ ጥበቃ፤-ወደ ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገቡ ባለሀብቶች
የፕሮጀክቶቻቸውን የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ /EIA/ እንዲኖራቸው ከፍተኛ
ጥረት ሲደረግ ቆይቷል አብዝሀኛዎቹ ነባር ፕሮጀክቶች የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ
ያልነበራቸው ሲሆን እስከአሁን በተሰራው ስራ ከጠቅላላው 144 ፕሮጀክቶች መካከል
58 ፕሮጀክቶች የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ሰነድ እንዲኖራቸው ተሰርቷል
 በስራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በተለይ በማምረት ተግባራት ከተሰማሩት 21 ፕሮጀክቶች
መካከል ከአካባቢ ተጽእኖ አንጻር የ10 ባለሃብቶችን የፕሮጀክቶች አፈጻጸም የመስክ
ምልከታና ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ቀሪዎቹ ባለሃብቶች ተገምግመው በጽሁፍ ግብረ
መልስ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 አንድ በድንጋይ ከሰል የሚሰራ ፋብሪካ /ሁአክሱ/ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ
እስከ 2012 ድረስ ብቻ በድንጋይ ከሰል እንዲሰራ እና ከጥቅምት 2012 በኋላ ወደ
ኤሌክትሪክ ሀይል እንዲዛወር ፍቃድ የተሰጠው ቢሆንም በመንግስት በኩል ያለውን
የሀይል አቅርቦት ችግር በመፍታት በድርጅቱ በኩል ደግሞ መሟላት የሚገባውን
አሟልቶ እንዲቀይር ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ን የሀይል መጠን የሚያቀርብበትነ ደረጃ
ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን በኮምቦልቻ ከተማ ያሉት ሰብስቴሽንe በቂ ሀይል የሌላቸው
በመሆኑ ባለሀብቱ የጠየቀው አይደለም
7. ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠር
 በዚህ ግማሽ አመት በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በክላስተር ማዕከላት በግል
ባለሀብቶች እና በመንግስት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እናሳካዋለን ብለን
ያስቀመጥነው አንዱ ግብ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር ነው ይህን ግብ ለማሳካት በአንድ
በኩል የቅድመ ግንባታ ተግባራቸውን አሟልተው ወደ ግንባታ ያልገቡ ባለሀብቶችን ወደ
ግንባታ በማስገባት በግንባታ ሂደት ላይ ያሉትና ግንባታ ያጠናቀቁት ደግሞ ወደ ማምረት
እንዲሸጋገሩ በማድረግ በማምረት ተግባር ውስጥ ያሉት ደግሞ ያሉባቸው ችግሮች
ተፈተው በሙሉ አቅማቸው ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ ድጋፍ በማድረግና በመንግስት
በጀት የሚሰሩ የመስረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ዜጎችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ
እንዲሳተፉ በማድረግ እንደሆነ ግልጽ አቅጣጫ አስቀምጠናል
 ከላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአመቱ በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ 1680 ዜጎች
የስራ እድል ለመፍጠር፤ በክላስተር ማዕከላት ቋሚ 180 ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር
እና በጠቅላላው 1806 ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ግብ በመያዝ ወደ ስራ ገብተናል
 ከዚህ በመነሳት በዚህ ግማሽ አመት ድረስ የተፈጠሩ የስራ እድል በኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን
ቋሚ 197 ጊዜያዊ 447 በድምሩ ለ644 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፣ በክላስተር
ማዕከላት ቋሚ 11 ጊዜያዊ 10 በድምሩ ለ21 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል በጠቅላላው
ቋሚ 208 ጊዜያዊ 457 በድምሩ ለ665 ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል 

 ነባሮቹን ጨምሮ እስከ አሁን ቋሚ ፡1640 ጊዜያዊ ፡1619 ድምር፡ 3259 ዜጎች
ኮርፖሬሽናችን በሚያስተዳድራቸው ሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና
የክላስተር ማዕከላት የስራ እድል ተፈጥሯል
 በዚህ አመት ለማሳካት ካቀድነው እቅድ አንጻር እቅዳችንን ለመፈጸም
እንቅፋት የሆነው ችግር ልማቱ በሚፈለው ደረጃ መራመድ ያለመቻሉ
በመሆኑ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታትና ልማቱን በማፋጠን
ያቀድነውን ግብ ለማሳካት በቀሪ ጊዜያት በትኩረት የምንቀሳቀስ ይሆናል ከዚህ
በተጨማሪ ባለሀብቶች እና ኢንተርፕራይዞች ባለፉት አመታት ከነበሩት
ሰራተኞች በዚህ አመት በከፈተኛ ደረጃ ቁጥሩ ቀንሷል ይህም ከኮቪድ 19
ወረርሽኝ እና ከግብአት ገበያ ትስስር ጋር ያሉ ችግሮቻቸው ባለመፈታቱ
እንቅስቃሴ እየቀነሰ መምጣቱን ማየት ተችሏል
8. ችግር ፈች ድጋፍና ክትትል ማድረግ
 በ2013ዓ/ም እቅዳችንን ስናቅድ
 በሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በክላስተር ማዕከላት ገብተው እያለሙ ያሉ
ባለሀብቶች ያሉበትን ደረጃ አውቆ ለመደገፍ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ችግር
ፈች ድጋፍና ክትትል በማድረግ በኩል ጉድለቶቸ እንደነበሩብን እና በዚህ አመት
ይህን ችግር ለመፍታት አቅደን መፈጸም እንዳለብን በግልጽ አመልክተናል
 በባለሀብቶቹ በኩል ያለው የመጀመሪያው ችግር የምልመላ ችግር ነው አቅም
የሌላቸው ባለሀብቶች እና ለአካባቢው የላቀ ፋይዳ የሌላቸው ፕሮጀክቶች
ተመልምለው ወስደዋል ተቀራምተዋል እነዚህ ባለሀብቶች መሬት ከወሰዱ
በኋላ በትንንሽ ምክንያቶች እያመካኙ ለረጅም ጊዜ አጥረው የመቆየት
ዝንባሌዎች በስፋተ ታይተዋል
 በመንግስት በኩል ደግሞ ያልተፈቱና ሰበብ የሚሆኑ ከመሰረተ ልማት እና
ከ3ኛ ወገን ጋር የተያያዙ ችግሮች አሉ፤ በመሆኑም በቅ/ጽ/ቤታችንና
በባለሀብቶቸች በኩል ያሉትን ችግሮችን ቢያንስ ተቀረርበን በመስራትና
በመፍታት ባሀብቶቹን ወደ ስራ ለማስገgባት ችለናል

በተደረገው ድጋፍም ከሀርቡ ባለሀብቶች /51 ባለሀብቶች/ እና ኮምቦልቻ ላይ አዲስ ከገቡ 2
ባለሃብቶች በስተቀር 91 ባለሀብቶች ሙሉ በመሉ ወደ ዋና ዋና ስራቸው እንዲገቡ ማድረግ
ተችሏል
የሁ/ኢ/ፓርኮቻችንና የባለሀብቶች የስራ አፈጻጸም በሚከተለው መልኩ ቀርቧል
ኢንዱስትሪ መንደር ጠቅላላ የተከለለ ለባለሃብቶች የተላለፈ የባለሃብት ብዛት
የቦታ መጠን በሄ/ር የመሬት መጠን በሄ/ር

ቁጥር 1 35.17 6.4676 4

ቁጥር 2 173.48 40.21 40

ቁጥር 3 71.62 42.39 48

ቁጥር 4 10 10 1
ሀርቡ 50.5 39.7072 51
ድምር 340.77 138.7748 144

 ከምናስተዳድራቸው 144 ባለሃብቶች መካከል 21 ባለሃብቶች በምርት ላይ ፣ 26 ባለሃብቶች
ግንባታ ያጠናቁ ፣ 31 ባለሃበቶች በተለያዩ የግንባታ ደረጃ ላይ ፣ 13 ባለሀብቶች (መሬት ጠረጋ
ቆረጣ እና የቅየሳ ስራ) ላይ እንዲሁም 53 ባለሃብቶች ባዶ ቦታ ሲሆኑ ባዶ ቦታ ላይ ካሉ
ባለሃብቶች 51 ባለሃብቶች ሃርቡ ሁለገብ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን
የመሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው፣ የአካባቢው አርሶ አደሮች በሚያነሱት የካሳና የመልሶ
ማቋቋሚያ ጥያቄ ምክንያት ወደስራ ያልገቡ ናቸው ቀሪዎቹ 2 ባለሃብቶች ኮምቦልቻ ላይ
የሚገኙ ሲሆን በ2013 በጀት አመት መሬት የተላለፈላቸው ናቸው፡፡
160

144
144
140
140 2010 2011 2012 2013

123
120

100
83
80

80
62

60
53

40
32

31

26
25

24
22

21
20
17
20
13
13

13
8
8

0
ባዶ ቦታ ቅድመ ግንባታ ግንባታ ላይ ግንባታ ያጠናቀቁ ምርት ላይ ድምር
የግንባታ ደረጃ በዘርፍ
60

ባዶ ቦታ ቅድመ ግንባታ ግንባታ ላይ ግንባታ ያጠናቀቀ በምርት ላይ ድምር

50 48

40
40

30 29

20 19 19

14
12 12
10
10 9
7 7 7
6 6
5 5 5
4 4
3 3
2 2 2 2 2
1 1 1 1
0 0 0 0 0
0
ምግብ እና ምግብ ነክ እንጨት እና ብረታ ብረት ኬሚካል ጨርቃ ጨርቅ የህክምና መገልገያ እቃዎች የግንባታ ግብአት

 ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን የባለሃብቶችን ክትትል እና ድጋፍ የሚያደርግ ቡድን
በማቋቋም ሁሌም በየሳምንቱ ማክሰኞ በመስክ የሚቀሳቀስ ሲሆን በወር አንድ
ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ከኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ባለሙያዎች
ጋር በመሆን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ የአፈጻጸም ደረጃቸውን በመለየት
ደካማ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሃብቶች እንደ ደረጃቸው የውይይት መድረክ
በመፍጠር ግንባታቸውን ለመጀመር፣ለማጠናቀቅ እና ወደ ምርት ለመግባት
ያለባቸውን ችግር እንዲያቀርቡ እና የሚሰሩትን ስራ የ3 ወር የድርጊት መርሃ
ግብር እንዲያቀርቡ በማድረግ ችግር ፈች የሆነ ድጋፍ እና ክትትል ሲያደርግ
ቆይቷል፡፡
 በዚህም መሰረት በዚህ ግማሽ 6 ባለሃብቶች የመሬት ጠረጋ ስራ ሰርተዋል፡፡ 8
ባለሃብቶች ወደ ግንባታ (የመሰረት ስራ) ፣ 7 ባለሃብቶች ወደ ኮለን ስራ ፣ 2
ባለሃብቶች ወደ ብሎኬት መደርደር 3 ባለሃብቶች ግንባታ ማጠናቀቅ እና 1
ባለሃብት ወደምርት ለማስገባት ተችሎል ባጠቃላይ 27 ባለሃብቶች ካሉበት
ደረጃ ለውጥ እንዲያመጡ ለማድረግ ተችሎል፡፡

 የአብዝሀኛዎቹ ባለሀብቶች ችግር እየሰሩ ያሉት ፕሮጀክት በበቂ የአዋጭነት
ጥናት ላይ የተመሰረተ ያለመሆኑ ሲሆን ወደ ስራ ከገቡ በኋላ ከጥሬ እቃ
አቅርቦት፣ ከቴክኖሎጅ አመራረጥና ከፕሮጀክት ማኔጅመንት ጋር የተያያዙ
ችግሮች ያሉባቸው ሲሆን በርካታ ባለሀብቶች የዘርፍ ለውጥ እየጠየቁ ይገኛሉ
ከብድር እና ከሀይል አቅርቦት ከውጭ ምንዛሬ ችግር እና ግንባታ ማቴሪያል
የዋጋ መናር እና አቅርቦት እጥረት ጋር (በተለይ የሲሚንቶ እና የብረት ዋጋ
መናር) የተያያዙ ችግሮች ናቸው በመሆኑም ግንባታ የጀመሩና እያጓተቱ ያሉ
ግንባታ አጠናቀው ወደ ማሽን ተከላ ሳይገቡ እያጓተቱ ያሉ የሙከራ ምርት
ጀምረው ያቆሙ ፕሮጀክቶች ምን ይሁኑ? የሚለውን ዝርዝር ጥናት
መስራትና የመፍትሄ አማራጮችን በማቅረብ ያሉባቸውን ችግሮች
ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የኮርፖሬሽኑን እና የሌሎች አካላትን የተቀናጀ
ድጋፍና የውሳኔ አቅጣጫ የሚፈልግ ችግር ነው፡፡ ከዚህ ከክትትልና ድጋፍ ጋር
በተያያዘ በከተማው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት በኩል እርምጃ
እንዲወሰድባቸው

የቀረቡ ፕሮጀክቶች ነበሩ ፕሮጀክቶች መጓተት ላይ ልዩነቶች ባይኖሩንም በሚወሰዱ
ርምጃዎች ላይ ግን በመሬቱ ላይ ያለው ግንባታ ምን ይሆን የባንክ ብድር/እግድ/ ያለባቸው
ምን ይሆኑ ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶችን ተመሳሳይ ችግር ውስጥ ያሉ
ፕሮጀክቶችን ተመሳሳይ የውሳኔ ሀሳብ ለምን አልቀረበም በማለት ላይ ልዩነቶች
በመኖራቸው እና ኮርፖሬሽኑ በተናጥል ውሳኔ ቢያሳልፍ በተናጥል ሀላፊነትና
ተጠያቂነትንየሚያስከትልበት መሆኑን በማመን ያቀረበውን ጥያቄ በቅ/ጽ/ቤታችን በኩል
ለመተግበር የምንቸገር መሆኑን ለሀሉም የማሳወቅ ስራዎችን ሰርተናል በእነዚህ ጉዳዮች
ላይ ኮርፖሬሽኑከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ተጨማሪ አቅጣጫዎችን
እንዲወርድ እንጠይቃለን
 በአጠቃላይ በሪፖርት በግምገማ በአካል ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ችግሮቹን እየለዩ
ተከታታይ ግብረ መልስ በመስጠትና ስራዎቹን የየሩብ አመት ቼክሊስት በማዘጋጀት
በማኔጅመንትና በአጠቃላይ እየገመገሙ ለመምራት ወቅታዊ ውሳኔዎችን እየወሰኑ
አመራር መስጠት በመጀመራችን በባለሀብቱም በአካባቢውም አመራርም
በቅ/ጽ/ቤታችንም ደረጃ ወደተሻለ መነቃቃት መፍጠሩና ወደ ተጨባጭ ተግባር
መግባታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መጀመራችን የሚያበረታታ ቢሆንም
ፕሮጀክቶችን ወደ ተሟላ ትግበራ ለመሸጋገር ቀጣይ ጥረት ይጠይቀናል
9. በራስ አቅም ችግሮችን መፍታት
 በ2012 ተጀምሮ የነበረው የኮምቦልቻ ቁ.2 ሁ/ኢ/ፓርክ የ1600ሜትር የውሀ
መስመር ዘርጋታ በ1,562,935.33 ብር በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በተደረገ
ድጋፍ የ17 ባለሀብቶች የውሀ አቅርቦት በዚህ ግማሽ አመት የማጠናቀቀ ስራ
ተሰርቷል፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ጊዜ በሁ/ኢ/ማዕከሉ ሙሉ በመሉ በሚባል ደረጃ
የውሀ አቅርቦት ያለ ሲሆን በተመሳሳይ በኮምቦልቻ ቁ.3 ሁ/ኢ/ማዕከል ቀደም
ሲል በተሰጠው የኮንትራት ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ መስመር ለ8 ባለሀብቶች
የሚሆን የ400ሜትር ቀሪ የውሀ መስመር ዝርጋታ ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ
ተደርጓል
 ለኮ/ቻ ቁ.2 ሁ/ኢ/ፓርክ የሚውል የ7 ሜጋ ዋት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሀይል
ተሸካሚ ርዝመቱ 8.42ኪ/ሜ የሆነ የግምት ዋጋው ብር 9,620,442.57 ጥናቱን
በአዲስ መልክ በማሰራትና ለክልሉ ንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በመቅረብ
በጀቱ እንዲለቀቅ አድርገናል የመሰረተ ልማት ዝርጋታው በዚህ አመት
የሚከናወን ይሆናል፡፡ ይህ የሀይል አቅርቦት በኮ/ቻ ቁ.2 አዲስ ለገቡ 17 ባለሀብቶች
የሚውል ሲሆን ከእነዚህ ኢንዱስትሪዎች የተረፈው ፓወር በኮምቦልቻ ቁ.3
ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች እንዲመግብ ተደርጎ ዲዛይኑ የተሰራ ነው

 በኮ/ቻ ቁ.2 ኢ/ፓርክ አዲስ ለተሰራው መንገድ በጎርፍ እየተጠቃ ያለ ሲሆን
ይህን ችግር ለማስወገድ ቀደም ሲል ከባሀብቶቹ ተሰብስቦ ከመንገድ ክፍያ
በተረፈ ብር 368,000.00 የፍሳሽ መቀልበሻና የአፈር መጠበቂያ ግንብ
እየተሰራ ይገኛል
 በደሴ መናፈሻ ክላስተር ማዕከል የተቃጠለ ትራንስፎርመር በአዲስ እንዲቀየር
የተደረገ ሲሆን በተመሳሳይ የሴፍቲክ ታንክ ፍሳሽ ማስተላለፊያ ቱቦ
ኢንተርፕራይዞችን በማስተባበር የማስጠገንና አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል
 በተመሳሳይ በደሴ 40 ቁጠባ የተበላሸ ባለ 315 ኪ/ዋት ትራንስፎመር በጥገና
ላይ ያለ ሲሆን በቅርቡ ለማስገባት አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ በዚህ
ክላሰተር ማዕከል ለ2 ኢንተርፕራይዞች የሀይል አቅርቦት ማስተካከያ
ተሰርቷል
 ለአንድ ባለሀብት ጀኔቭ ትራንስፎርመር እንዲገባ የተደረገ ሲሆን የሁለት
ኢንዱስትሪዎችና ደግሞ በቅርቡ ክትትል እያደረግን ነው

 በአንድ ባለሀብት ይዞታ ላይ የተተከለውን የኤሌክትሪክ የፖል እጨት ለማንሳት ከደሴ
ለመጡ ባለሙያዎች ፖሉ የሚተከልበትን ቦታ በማመላከት ፖሉ ከባለሀብቱ ይዞታ ላይ
ተነስቶ መቀመጥ ካለበት ቦታ ላይ እንዲተከል ተደርጓል
 በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቁ.2 አንድ ፋብሪካ /ኢት ውድ ማኑፋክቸሪንግ/ የፕሮጀክት
መንገድ ዳር የተከለውን የባህርዛፍ ተክል እንዲያነሱ በተነገራቸው መሰረት የባህርዛር
ችግኞች እንዲነቀሉ ተደርጓል
 በአንድ ባለሀብት ይዞታ ላይ የፋይበር ኦፕቲክ መስመር ዝርጋታ ዩታል እንጨቶች
ተተክለው የነበሩ ሲሆን ለኮምቦልቻ /ደሴ የሚገኙትን ባለሙያዎች/ እንዲነሱላቸው
በማነጋገር የፖል እንጨቶች እንዲነሱ ተደርጓል
 ኢንዱስትሪ መንደር ቁ.3 ሽፍት ያደረገ የሽንሻኖ ፕላን ለማስተካከል ከከተማ አገልግሎት
ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን የልኬታ ስራ ተሰርቶ የፕላን ክለሳና ማተካከያ ውሳኔ
በማስወሰን ባለሀብቱ የግንባታ ስራውን በነበረበት ሁኔታ እንዲያከናውኑ ተደርጓል፡፡
 በሁ/ኢ/ፓርኩ ለአምራች ኢንዱስትሪ መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች የግንባታ ሸዳቸወውን
ወደ መጋዘንነት ቀይረው ለማከራየት የያደርጉት ጥረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት
ጋር በመነጋገር እንዲቆሙ ጥረት እየተደረገ ነው
ክፍል ሶስት
የነበሩ ጥንካሬዎች
 ያለፉ አፈጻጸሞችን በጥልቀት በመገምገም የኮርፖሬሽኑን እና የመንግስትን እቅድ
በመነሻነት በመውሰድ የአመቱን እቅድ በወቅቱ ማቀዳችንና ወደ ስራ መግባታችን
 እቅዱን ለፈጻሚ አካላት መድረኮችን በማዘጋጀት የማሳወቅ የጋራ መግባባትና
መተማመን ላይ መድረሱና በኮርፖሬሽን ደረጃ ለሁሉም ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱ፤
 ስራዎቻችንን በየ15 ቀኑ በማኔጅመንት፤በየወሩ ከጠቅላላ ሰራተኛ ጋር በሚደረግ
ግምገማና ምክክር፤ በየሩብ ዓመቱ በሚደረግ ጥልቅ ግምገማ በማድረግ እንድሁም
በየደረጃው አመራር መፈታት ያለባቸው ችግሮች እንድፈቱ ጥረት ማድረጋችን
 በአመቱ ትኩረት ተሰጥቷቸው መፈታት ያለባቸውን ችግሮች በዝርዝር ጥናት ላይ
በመመስረት ለኮርፖሬሽኑ ከማቅረቡም በላይ የከተማው አስተዳደር በራሱ አቅም
የሚፈታባቸውን ለይቶ በማቅረብና እንዲፈቱ መተማመን ላይ በመድረሱ በርካታ
ችግሮችን በራስ አቅም መፍታት መጀመራችን
 የባለሀብቶች መረጃ፤ የመሬት መረጃ እንዲሁም ሁሉም ፕሮጀክቶች ያለበትን ደረጃ
በዝርዝር በማጥናት በየጊዜው ማስተካከያ ርምጃ መውሰድ በመቻላችን በርካታ
ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምረናል

ከእነዚህም መካከል የሚከተሉት በጉልሀህ የሚታየዩ ውጤቶች ናቸው
 6 ባለሃብቶች ወደ ቅደመ ግንባታ ስራ /መሬት ቆረጣና ድልደላ/
እንዲገቡማድረግ ተችሏል
 8 ፕሮጀክቶች ከቅድመ ግንባታ ወደ ግንባታ በአዲስ መልክ አስገብተናል

 9 ፕሮጀክቶች የግንባታ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል

 3 ፕሮጀክቶች ግንባታቸውን በዚህ ግማሽ አመት ውስጥ አጠናቀዋል

 1 ፕሮጀክቶች ወደ ሙከራ ምርት ማስገባት ችለናል/ ኢቲ ውድ


ማኑፋክቸሪንግ/
 በአጠቃላይ 27 ፕሮጀክቶች በዚህ ግማሽ ዓመት ብቻ ወደ ለውጥ የገቡ ናቸው

 እስካሁን ድረስ 31 /21.52%/ ፕሮጀክቶች በግንባታ ሂደት፤26 /18%/


ፕሮጀክቶች ግንባታ ያጠናቀቁ፤ 21/14.58%/ ፕሮጀክቶች ወደምርት
የተሸጋገሩ ሲሆን ቀሪዎቹ 13/9.02%/ ፕሮጀክቶች መሬት ቆረጣና አፈር
በማንሳት ላይ ያሉ እና 53/36.8%/ ባዶ ቦታ ላይ ይገኛሉ ይገኛሉ/

 828.26 ካ/ሜ የክላስተር ወለል ለ4 ኢንተርፕራይዞች ማስተላለፍ ችለናል
 ለ3 ባለሀብቶች በአዲስ መልክ 9823ካ/ሜ መሬት አስተላልፈን

 ከ3 ባለሀብቶች 22000ካ/ሜ መሬት እንዲነጠቅ አድርገናል ወደ መንግሰት


ተመላሽ እንደሆን ማድረግ ችለናል
 በክላስተር ማዕከላት ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ተከታታይ ድጋፍ በማድረግና
ያሉባቸው ችግሮች እንዲፈቱ በማድረግ ወርሀዊ ገቢ ወቅቱን ጠበቀ
እንዲሰበሰብ ጥረት ተደርጓል
 የኮርፖሬሽኑ አሰራር ተጠብቆ እንዲቀጥል በተሰራው ሰራ በተደረሰው
መተማመን ሁሉም ሰራተኛ የየአለቱን የሳምንት እቅድና ሪፖርት እንዲደረግ
ተደርጓል

የነበሩ ድክመቶች
 አሁንም አብዝሀኛዎቹ ተግባሮቻችን ገና በሂደት ላይ ያሉ ናቸው በውጤት
የተቋጩ አይደለም 26 ባሀብቶች የግንባታ ሸድ አጠናቀዋል 44 ባለሀብቶች
ሸደ እየገነቡ ነው 13 ባለሀበቶች በመሬት ቆረጣና ወደ ማጽዳት ገብተዋል
አነዚህን ወደ ማሽን ተከላና ማምረት ማሸጋገር ይቀራል
 አሁንም በርካታ ባለሀብቶች ወደ ተሟላ ትግበራ ገና አልገቡም 53
ፕሮጀክቶች ባዶ መሬት ናቸው
 አሁንም ከማስታመምና ባለሀብቶቹ በሚያቀርቡት ችግር ከመፍታት ገና
አልወጣንም በተለይ ደግሞ ከ24 በላይ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጀምረው ለረጅም
ጊዜ ወደ ማሽን ተከላና ማምረት ሳይሸጋገሩ እያዘገዩ ይገኛሉ ይህን ችግር
ፈጥነን መሻገር ካልቻልን አሁንም በየአመቱ የያዝነውን ግብ ማሳካት
አንችልም በመሆኑም ከዚህ ድክመት ለመውጣት የተለየ ትኩረት ሰትተን
መንቀሳቀስ ይጠይቀናል

 ወደ ኢንተርፕራይዝ ያልተሸጋገሩ የክላስተር ህንጻ ወለሎች አሉ የደሴ ከተማ
አስተዳደር በዚህ ግማሽ አመት የተሻለ ስራ የሰራ ቢሆንም አሁንም ከ511.69ካ/ሜ
በላይ የመስሪያ ቦታ አልተከራየም የሚመለመሉት ኢንተርፕራይዞች አቅም ያላቸው
አይደሉም የሚጎድላቸውን ደግፎ ከችግር በማውጣት በኩልም ጉድለቶች አሉ
 የቅንጅታዊ አሰራር ችግራችንን አሁንም ሙሉ በመሉ የተሻገርናቸው አይደለም
በተለይ ከዩንቨርስቲው ጋር ከሚዲያ ተቋማት ጋር እንዲሁም ከባንኮችና ከመብራት
ሀይል ተቋማት እና ከከተማው አስተዳደር ከሁሉም ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ ችግሮችን
በመፍታት አሁንም ይቀረናል አልፎ አልፎ የመገፋፋት ዝንባሌዎችም ይታያሉ
 ከጠባቂነት ሙሉ በመሉ ተላቀናል ማለት አይቻልም ሀርቡ ላይ ያሉ ባለሀብቶችን
በማሳመን በራሳቸው አቅም መሄድ የሚችሉትን ያህል ያለመግፋት ከፀጥታ እና
ከአርሶ አደሮች ጋር የተያያዘውን ቅሬታ የዞኑ አመራርና የአካባቢው አስተዳደር
እንዲፈታና ባለሀብቶቹ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ በኩል ጉድለቶች ይታያሉ
 በመሆኑም በቀጣዮቹ ወራት እነዚህን ጉድለቶች ለማረምና ከሚለከታቸው አካላት
ጋር ተቀናጅቶ የተሻለ ውጤት ለማምጣት መረባረብ ይጠይቃል
ክፍል አራት
ያጋጠሙ ችግሮችና የተሰጡ መፍትሄ
 ደሴ ላይ የክላስተር ማእከላት ትራንስፎርመር አለመስራት እና የቆጣሪ አቅም ከማሽኖች
ጋር አለመመጣጠን ይህን ችግር ለመፍታት ኮርፖሬሽኑ በጥናቱ መሰረት በጀት አለመመደብ
 ከዚህ በፊት የተነጠቁ መሬቶች ወደ ሌላ ባለሃብት አለመተላለፋቸው እና ቅሬታ ያላቸው
ባለሃብቶች ውሳኔ አለመሰጠት/ ለ9 ባለሀብቶች እንዲተላለፍ በተወሰነው ውሳኔ ላይ
ቅሬታና አቤቱታ በመነሳት መሬቱን ማስተላለፍ አለመቻላችን
 ደሴ ላይ የክላስተር ህንጻዎቹን የሚከራዩ ኢንተርፕራይዞችን የሚመለከታቸው አካላት
መልምለው ባለማምጣታቸው ምክንያት ህንጻዎቹ ሳይከራዩ ለረጅም ጊዜ መቆየታቸውና
ተመልምለው የሚላ ኢንተርፕራይዞች አቅም የሌላቸው በመሆኑ ቶሎ ቶሎ
 የ3ኛ ወገን ችግር ከካሳ ከፍያ እና ከትክ መሬት ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊፈቱ
ባለመቻላቸው ባለሀብቶቹ ግንባታ አቋርጠዋል EIA ማሰራትና ብድር ለመበደር
ተቸግረዋል ከከተማው በኩል ደግሞ የበጀት እጥረተ አለበት ያለባቸው 11 ባለሃብቶች
ችግር አለመፈታት
 የሃርቡ 51 ባለሃብቶች የመሰረተ ልማት አለመሟላት በጠናቱ መሰረት በጀት አለመፈቀድ
አ/አደሮች የሚያነሱት የካሳ ቅሬታ አለመፈታት

 የውጭ ምንዛሬ እጥረት በመኖሩ ግንባታ ያጠናቀቁ ባሀብቶች እና የማሽን ግዥ ችግር ወደምርት
አለመግባት፡፡
 በባለሃብቱ በራሱ መንገድ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ችግሮችን በመደርደር ግንባታ
አለማጠናቀቅ እና ወደ ምርት አለመግባት፡፡ ርምጃ ለመውሰድም በመሬቱ ላይ ስለጀመሩት
ግንባታ እና አልፎ አልፎ ከብድር እግድ ጋር ለተያያዙ ችግሮች ግልጽ አሰራር አለመውረዱ
 የክላስተር ማእከላት ተከራዮች በሙሉ አቅማቸው መስራት ባለመቻላቸው ወቅቱን ጠብቀው
የኪራይ ክፍያ አለመክፈል እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ
 በርካታ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ቦታ ጠይቀው ቦታ አለመቻቸት እና መሰረተ ልማት
አለመሟላት፡፡ በአሁኑ ሰአት 229 ባለሀብቶች 488.56ሄ/ር መሬት ጠይቀው ማስተናገድ
አልተቻለም
 በከፍተኛ ደረጃ የግንባታ ግብአት መወድድ እና አቅርቦት አለመኖር/ በተለይ የሲሚንቶ እና የብረት
ግብአት ችግር ማጋጠሙ/
 ግንባታ ያጠናቀቁ ባለሃብቶች አብዘሃኛዎቹ የዘርፍ ለውጥ መጠየቅ እና የሚመለከተው አካል
አፋጣኝ ምላሽ አለመስጠት በአሁኑ ሰአት ከ10 በላይ ባለሀብቶች ጥያቄ አቅርበዋል እነዚህን
ችግሮች ለመፍታት የቅ/ጽ/ቤቱ ማኔጅመንት ከባሀብቶቹ እና ከአካባቢው አስተዳደር ጋር
በመወያየት ጥረት የተደረገና ለማሻሻል የተሞከረ ቢሆንም አሁነም ሙሉ በመሉ ተፈተዋል
ማለት አየይለም ጥያቄያቸው በወቅቱ ምላሽ እያገኘ አይደለም
የበላይ አካላትን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
 የሀርቡ ሁ/ኢ/ፓርክ የመሰረተ ልማት ማሟላት ጉዳይ / መንገድ ውሀ፣ መብራት/ በጀትና
የአ/አደሮች ከካሳ ጋር የተያያዘ ቅሬታ አለመፈታት
 የ3ተኛ ወገን ችግር ያለባቸውን ባለሃብቶች ችግር መፍታት አለመቻል እና ከካሳ እና
ማቋቋሚያ ጋር የሚጠየቀው ክፍያ ከከተማው አቅም በላይ በመሆኑ የክልሉን ድጋፍ
እንፈልጋለን
 የክላስተር ህንጻዎች የመሰረተ ልማት ችግር መፍትሄ መስጠት(የመፋሰሻ፤ የጥገና፤
የኤሌክትሪክ መስመር ወ.ዘ.ተ.) የበጀት ጥያቄ ምላሽ ባለመሰጠቱ ህንጻዎች ለተጨማሪ
ጉዳት እየተዳረጉ ይገኛሉ
 የመደበኛ በጀት የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ስራ መስኬጃ በጀት የግዴታ
ወጭዎቻችንን/የጥበቃ ሰራተኞች ደመወዝና የጅአይኤስ መሳሪያ ካሊብሬት ማስደረጊያ
የደሴና ኮምቦልቻ ህንጻዎች የአገልግሎት አመታዊ ክፍያ የህግ ባለሙያ ከደብረ ብርሀን
ደሴና ኮምቦልቻ ሲመላለስ የሚከፍለው የውሎ አበል ክፍያ የስልክና የመብራት የነዳጅና
አጠቃላይ የውሎ አበል ክፍያ ወዘተ ደግሞ ታይቶ ተስተካክሎ እንዲመደብልን
 በድጋፍና ክትትል መስኩም በኮርፖሬሽኑ በኩክ የሙያተኛ እና የአመራር የመስክ ምልታ
እየተደረገ ድጋፍ ቢሰጠንና ከእኛ አቅም በላይ የሆኑ ችግሮች በቦርዱና በክልሉ መንግስት
እንዲሁም በኮረፖሬሽኑ በኩል እንዲፈቱልን ቢደረግ ከዚህ የበለጠ ውጤታማ
እንደምንሆን እናምናለን
“ስኬቶቻቻችንን አጠናክረን
በማስቀጠልናጉድለቶቻችንን በማሻሻል
የኮርፖሬሽኑን ተልዕኮዎች
በላቀ ደረጃ ለማሳካት እንረባረብ”

የካቲት 2013ዓ.ም


You might also like