You are on page 1of 17

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ

ሚያዝያ 2015 ዓ.ም


ምስጋና
 በቅድሚያ ይህን የከተማችን ህዝብ 1/6 የህ/ሰብ ክፍል የሆነዉ የአካል
ጉዳተኞች(ማየት፣መስማት፣መራመድና ሌሎች) ተዛማጅ በሽታዎች ምክንያት የተለያዩ ጉዳት
ያለባቸዉና የተገለሉ የህ/ሰብ አካላት በጎንደር ዋና ዋና የአለም አቀፍ ቅርሶች መስህቦች ተደራሽ
እንዲሆኑ ታሪካቸዉን እና ባህላቸዉን ማየት መስማት እና በስሜት መጎብኘት እንዲችሉ
ለማድረግ ተነሳሽቱን ለወሰደዉየጎ/ከ/አስ/ባ/ቱ/መምሪያ ሃላፊ አቶ ቻላቸዉ ዳኘዉና
ለማኔጅመንት አባላት በሙሉምስጋና ይድረስ
 በመቀጠል ድንቅ እና የሚገርም ችሎታ የተካነችዉ እና ማየት ለተሳናቸዉ አገልግሎት የሚዉል
የምልክት ቋንቋ በመጠቀም ማየት ለተሳናቸዉ የብሬል ፅሁፉን በማዘጋጀት ትልቁን የአካቶነት
ቴክኖሎጅ ለመተግበር ስራ ለሰራች ለመምህርት ፀሃይ መከተ ምስጋና ይድረሳት
 የጎንደር ቅርሶች ታሪክ በአጭር ተረኩልን አስጎብኝ እና ደራሲ አሰግድ ተስፋየ እና የቪዲዮን
ቀረፃ እና ቅንብሩን ለሰሩት አቶ ታምሩ ጥላሁን ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
 በመጨረሻም የፅሁፉን ስራ እና ኤዲቲንግ ስራ በአጭር ጊዜ ላደረሰችልኝ ለወ/ሮ ትዘዘዉ ክንዴ
ምስጋና እያቀረብኩ
 በአጠቃላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለዚህ ተግባራዊ ስኬት ለተባበራችሁ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ
ነዉ፡፡

መማውጫ
መግቢያ.........................................................................................................................................................1
2. የምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራ ዋና አላማ........................................................................................................2

2.1. የምርጥ ተሞክሮዉ ዝርዝር አላማ.....................................................................................................2

3. የምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራዉ አሰራር ስልት.................................................................................................2

4. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ዉስንነት.............................................................................................................3

5- የተደራሽነት ችግር ትንተና...........................................................................................................................3

5. የተሞክሮዉ ቅመራዉ የተካሄደባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች......................................................................................4

6. በዋና ዋና መስህቦች በጎንደር አጭር ታሪክ ከዋና ዋና ቅርሶች ምስሎችና ፖስት ካርዶች በብሬል አዘጋጅቶ ማየት
ለተሳናቸዉ ተጠቃሚ ማድረግ..........................................................................................................................4

6.1. በዋና ዋና መስህቦች በጎንደር አጭር ታሪክ በግብረ ህንፃዎች አሰራር የተሰሩበት የቁሳቁስ እና በጎንደር አጭር
ታሪክ በምስል የተደገፈ የምልክት ቋንቋ ቴክኖሎጅን (DVD)ማዘጋጀት...............................................................4

6.2. አፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት ግቢ፣ ራስ ግንብ ሙዚየም፣አፄ ፋሲል መዋኛ ግቢዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽና
ምቹ እንዲሆኑ የመንገድ ድንጋይ ንጣፍና ከርብ ስቶን በማዘጋጀት እና ዊልቸር አጠቃቀም ቴክኖሎጅዎችን
ማስጠቀም.................................................................................................................................................5

7. ምርጥ ተሞክሮዉ የተካሄደበት ከተማ/ክ/ከተማ/ልዩ ቦታ...............................................................................5

7.1. የከተማችን አጠቃላይ ሁኔታ.............................................................................................................5

8. ምርጥ ተሞክሮዉ ከመቀመሩ በፊት ወይም አሰራሩ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የነበሩ ሁኔታዎች..........................6

8.1. የክ/ከተሞች ሁኔታ...........................................................................................................................6

8.1.1. ፋሲል ክ/ከተማ...........................................................................................................................6

8.1.2. ዞብል ክ/ከተማ............................................................................................................................7

8.1.3. ጃንተከል ክ/ከተማ.......................................................................................................................7

11. የወጭና የገቢ ዝርዝር.........................................................................................................................12

11.1. የወጭ ዝርዝር...........................................................................................................................12

11.2. ገቢን የሚተካ የዉልና መንግስታዊ ግዴታዎች ዝርዝር በተመለከተ..........................................................13

12. ምክረ ሃሳብ......................................................................................................................................13

13. ማደማደሚያ....................................................................................................................................14
አፅህሮተ ፅሁፍ
በጎንደር አለም አቀፍ ቅርሶች ዋና ግቢ በሆነዉ ይህን አካቶነት ቴክኖሎጅ ስራ ስንጀምር እና እንደምርጥ
ተሞክሮ እንዲስፋፋ ሲፈለግ የተጠቀምንባቸዉን ስልቶች በአጨር በዚህ መልክ ተዘርዝሯል
የአለም፣የኢትዮጵያ እና የከተማችን ህ/ሰብ የአካቶነት ቴክኖሎጅ ባለመጠቀም ምን ያህል የህ/ሰብ ክፍሎች
እንዳገለልን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነትና የተጠቃሚዎችን መገለል በተሰራጨዉ መጠይቅና
በቃለ-ምልልሱ የጋራ ዉይይት ተጠቅመናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የጉዳት መጠን ተግባሩ ከመጀመሩ በፊትና በኋላ ተተንትኗል፡፡በአካቶነት ቴክኖሎጅ
ያተኮረባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች ማለትም (ማየት ለተሳናቸዉ፣ መስማት ለተሳናቸዉ እና መራመድ ችግር
ላለባቸዉ)የህ/ሰብ ክፍሎች ያተኮረ ተሞክሮ መሆኑን ያሳያል፡፡ተሞክሮዉ የተቀመረዉ በጎንደር አለም አለም
አቀፍ ቅርሶች ዋና አካል በሆነዉ በአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት ግቢ ብቻ መሆኑ መስፋት እንዳለበት ያመለክታል፡፡
ተሞክሮ በተወሰነ ግብዓት የተተገበረ በመሆኑ በሰፈዉ እንዲሰራ አመላካች ነዉ፡፡በጥቅሉ ይህ ፓይለት ስራ
በአነስተኛ ወጭ በመለስተኛ ጊዜ እና በአዋጭ ፋይናንስ በማከናወን ከ 100 ሺ ህ/ሰብ በላይ ተጠቃሚ
የሚያደርግ ነዉ፡፡ሞራላዊና መንፈሳዊ እርካታ የሚያስገኝ መሆኑን በመጠየቁ ምላሽ ጸረጋገፀ በመሆኑ
የሚመለከተዉ አካል ተገቢ ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት የተሻለ ተደራሽነት ይኖረዋል፡፡
መግቢያ
አገራችን ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሆነ የተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ ሃብቶች ባለቤት ናት ሃገራችን በተባበሩት
መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) የመስህብ ሃብቶቻቸዉን ካስመዘገቡ ቀዳሚ
ጥቂት ሃገራት አንዷ ናት፡፡

በአፍሪካም ከቁጥር አንፃር 10 ቅርሶችን በመያዝ ኢትዮጵያ በ 2 ኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡ (ዩኒስኮ ሪፖርት 2022)
ይህ ሃብት ወደ ክልል ድርሻ ሲታይ የአማራ ክልል ከ 50% በላይ ይዞ ይገኛል፡፡(በቆጠራ ሪፖርት) ጎንደር ከተማም
ብዙ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ባለቤት ነች የዚህ ሃብት ባለቤት ከሆኑት አንዷና በታሪካዊነቷ
የምትታወቀዉ ጎንደር ከተማ ነች፡፡

ጎንደር ከአክሱምና ከዛግዎ ስርዎ መንግስታት በኋላ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ በመሆን ከ 200 አመታት በላይ
አገልግላለች፡፡

የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዱት በዚያ ወቅት በነገስታቱ ፍላጎትና በህዝቡ ተነሳሽነት የጎንደር ዘመን ግብረ
ህንፃዎች ጥናታዊ ድልድዮች እና አብያተ ክርስቲያናት የመጨረሻዉ የህንፃ ግንባታ ጥበብ በመጠቀም
ተገንብተዋል፤ አሻራቸዉም እስከ አሁን ድረስ ይገኛል በጎንደር ከተማ ዉስጥ ሰባት የአለም ቅርስ አካል የሆኑ
(የየራሳቸዉ ሴሪያል ቁጥር የተሰጣቸዉ) ቅርሶች ከመኖራቸዉ ባሻገር የጥምቀትናየመስቀል በዓላት
የሚከበሩበት የቅርሶች፣ የንግድ ፣የኪነ-ህንፃ፣ የኪነ-ጥበብ እና የእደ- ጥበብ ማዕከል ነበረች አሁንም ናት፡፡

ጎንደራችን ይህ ሁሉ ሃብት በጉያዋ አምቃ ይዛ ለሁሉም አለም አቀፋዊና አገራዊ ቱሪስቶች ተደራሽነቷ ቀላል
ሆኖ እያለ ለዜጎቿም ሆነ ለሌሎች ዜጎች አካል ጉዳተኞች እስከ አሁን ተደራሽ ባለመሆናቸዉ የፍትሃዊነት
ጥያቄ ለዘመናት አስተናግዳለች፡፡ በመሆኑም ጥያቄዉ እየተድበሰበሰ እስከ 2014 የስራ ዘመን የቆየ ቢሆንም
ተቋሙ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደ አንድ ችግር አድርጎ በመዉሰዱ መፍትሄ ማግኘት ካለባችዉ
ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለመፍታት ተግባሩ በአንድ ተቋም ብቻ
እንዳይታጠር ተሞክሮዉን በመቀመር እንዲሰፋ ይህን ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መሰረት የማስፋት
ስትራቴጅዉን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል በአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት ግቢ በጎንደር አጭር ታሪክ እና
በጎንደር ከተማ ዋና ዋና መስህብ ቦታዎች ተተግብረዉ ዉጤት ያስጎበኙ አሰራሮች ወደ ሌሎች የክልላችን
መስህብ ቦታዎች ትልልቅ የአገልግሎት ተቋማት ተደራሽ ሆነዉ በስፋት እንዲዳረሱ ለማድረግ እንዲቻል
ምርጥ ልምዶች ከመገኘታቸዉ አስቀድሞ የነበረዉ ነባራዊ ሁኔታ አሁን የተገኘዉዉጤት ዉጤቱ የተገኘበት
ዝርዝር ሂደት፣ ዉጤቱን በማስገኘት ሂደት የጋጠሙ ችግሮችና የተፈቱበት አግባብ እና ከዚህ ምርጥ ልምድ
የተገኙት ተሞክሮዎችን ተዘርዝረዉ ተቀምረዉ ተዘጋጅተዋል፡፡

1
2. የምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራ ዋና አላማ
አለም አቀፋዊ ይዘት ያላቸዉ የጎንደር ቅርሶች ለብዙ ሚሊዮን ቱሪስቶች ተደራሽ በመሆን ለብዙ መቶ
አመታት ቢቆዩም ለአካል ጉዳተኞች ግን ተደራሽ ባለመሆናቸዉ አካታች ተደራሽነትን ለማስፈን ነዉ፡፡

2.1. የምርጥ ተሞክሮዉ ዝርዝር አላማ


ወደ ጎንደር ከተማ የሚመጡ ማየት የተሳናቸዉን የህ/ሰብ ክፍሎች በዋና ዋና አለም አቀፍ ቅርሶች
መስህቦቻችን የአካቶነት ቴክኖሎጅ ብሬል በማዘጋጀት ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ
የጎንደር አለም አቀፍ ቅርሶች የሚጎበኙ መስማት የተሳናቸዉን የህ/ሰብ ክፍሎች መስህቦችን
በምልክት ቋንቋ እንዲገነዘቡ ማስቻል
የጎንደር አለም አቀፍ ቅርሶች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ አስፈላጊዉን እንቅስቃሴ ድንጋይ
ንጣፍና ከርብ ስቶን የስራ ቡድን በመስራት ለዊልቸር ሆነ ለሌሎች ጉዳተኞች ግብአቶችን በማሟላት
ተደራሽ ማድረግ
የጎንደር አለም አቀፍ ቅርሶች ለሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች ተደራሽነታቸዉን በተግባር በመፈፀም
የገፅታ ግንባታችን መገንባት
የአጋርነት ፣የአብሮነትና የአካታችነት አለም አቀፍ የሰዉ ልጅ መርህን መፈፀም

3. የምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራዉ አሰራር ስልት


 ለምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራዉ የሚያገለግል መነሻ ሃሳብ (TOR) ማዘጋጀት
 ለአንዳንድ ቴክኖሎጅ ለምርጥ ተሞክሮዉ ቅመራ የሚያገለግል መጠይቅ ማዘጋጀት
 ከቅርስ አስተዳደሩ ሙያተኞች፣ከአስጎብኝዎች ማህበርናከፎቶ አንሽ ማኅበራት ዉጤቱ የተገኘበትን
ዝርዝርሂደት መረጃ ማሰባሰብ በአካል ተገኝቶ መመልከት
 በአፄ ፋሲል ግቢ በመገኘት ተግባሩ እንዴት እንደተፈፀመ የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ስራዉን መስራት
በአካል ተገኝቶ መመልከት ተግባሩን በመፈፀም ሂደት የነበሩ አደናቃፊ አመለካከቶችና ችግሮችን
እንዲሁም የተወሰዱ መፍትሄዎችን ማሰባሰብ
 የአፄ ፋሲል ግቢ ዋናዉ የተሞክሮ ቅመራ ልዩ ቦታ በመሆኑ ተግባራት ሲከናዎኑ ፎቶ ግራፍ ማንሳት
የምስልና የድምፅ ቀረፃዎችን ማከናዎን ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረዉ ናሙና በፎቶ ፣በድምፅና በቃለ
መጠይቅ ማደራጀት
 በተዘጋጀዉ መጠይቅ መሰረት የተሰበሰበዉ መረጃ የተነሱትን ፎቶ ግራፎች የድምፅና የምስል
መረጃዎች ተሞክሮዉን ለመቅሰም /ለማስፋት/ በሚያስችል መልኩ መፃፍ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡

4. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ዉስንነት


ጎንደር ስንል በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ወረዳዎችንና ዞኖችን እንደሚያጠቃልል ይታወቃል ነገር ግን
የተሞክሮዉ ቅመራ እና አተገባበር ያተኮረዉ

 በጎንደር ከተማ ዉስጥ በሚገኙ ዋና ዋና መስህብ ሃብቶች በከፊል


 የጎንደር ከተማ ታሪክም ትልቅና ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያተኮረዉ ከአፄ ፋሲል ንግስና በኋላ
ከተማዋን እንደመዲናነት ከተመሰረተች በኋላ ያለዉን መሆኑ
 ከማቴሪያል ዉስንነት የተነሳ ተግባሩ የተዘጋጀዉ በዉስን ቅርሶች ብቻ መሆኑ

2
በአጠቃላይ የጊዜ፣ የፋይናንስ፣ የቦታ ዉስንነት ያለዉ በመሆኑ ይህን ስራ በቦታና በግብዓት በማስፋት ችግሩን
ማቃለል ይቻላል፡፡

5- የተደራሽነት ችግር ትንተና


ጎንደር በሃገራችንተወዳጅና ዘርፈ ብዙ መስህብ ሃብቶች ባለቤት ከሆኑ ከተሞች አንዷ ናት፡፡

እነዚህ የሰዉ ሰራሽ፣ የተፈጥሮና ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ በአላትን መመልከት ከመንፈሳዊ
እርካታ በተጨማሪየተለያዩ ፍላጎቶቻቸዉ በአንድወይም በተቀራራቢ ቦታ ማበርከት የምትችል ከተማ
ናት፡፡ ሆኖም ግን በአለም 15% በአፍሪካ እና በአገራችን ኢትዮጵያ 17.6% ቁጥር ያላቸዉ የህ/ሰብ
ክፍሎች ለእነዚህ መስህብ ሃብቶች ተደራሽሳይሆኑ ለብዙ መቶ አመታት ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም
ከተማችን ዉስጥ ዋናዉ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ቆይተዋል፡፡

 ሁሉም የቱሪስት መዳረሻ መስህቦቻችን ማየት ለተሳናቸዉ የህ/ሰብ ክፍሎች አመቺም


ተደራሽም አይደሉም
 ሁሉም የቱሪስት መዳረሻ መስህቦቻችን መስማት ለተሳናቸዉ የህ/ሰብ ክፍሎች አመቺና
ተደራሽ አይደሉም
 ሁሉም የቱሪስት መዳረሻ መስህቦቻችን መራመድ ለተሳናቸዉ የህ/ሰብ ክፍሎች አመቺም
ተደራሽም አልነበሩም፡፡

ስለሆነም አለም አቀፍ መዳረሻዎቻችን ቀላል ቁጥር ላልያዙት የህብ/ሰብ ክፍሎች አግሎ የቆየ ነዉ፡፡
በመሆኑም ይህን ችግር መፍታት የሰብዓዊ ድንጋጌዎች ግዴታዎችአንዱ በመሆኑ በአፋጣኝ መፍታት
ቅርሶች ለሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ የዘርፉ ግዴታ ነዉ፡፡

በመሆኑም ይህን ችግር ለመፍታት የአካታችነት ቴክኖሎጅ ዘዴ መጠቀም እንዲቻል ይህን ተሞክሮ
ሰነድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

5. የተሞክሮዉ ቅመራዉ የተካሄደባቸዉ ርዕሰ ጉዳዮች


ጎንደር የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የአለም ሃብት የሆኑ ቅርሶች ባለቤት ናት፡፡ እነዚህ ቅርሶች አቅሙ ለፈቀደና
ፍላጎት ላለዉ የአለም ህዝብ ተደራሽ በመሆን ለዘመናት በመቶ ሚሊዮን እንግዶች ተጎብኝተዋል፡፡ ሆኖም ግን
አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ ቢኖራቸዉም በከተማችን ዉስጥ ያሉ ቅርሶች ለሁሉም ሰዉ ተደራሽ ሳይሆኑ
ለመቶዎችአመታት ቆይተዋል፡፡ ይህን ምክረ ሃሳብ መነሻ በማድረግ የከተማ ቅርሶቻችን አካታችነት
እንዲኖራቸዉ ታስቦ የተሰራዉ ስራ ወደ ሌላአካባቢ ቢስፋፋ የቅርሶችን ተደራሽነት በማሳደግ ቀላል
የማይባል የህ/ሰብ ክፍል ቁጥር ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ የአካታችነትን ፅንሰ ሃሳብ ለመተግበር
የተጠቀምንባቸዉን ዘርፎችና የቴክኖሎጅ አይነቶች አጠቃቀምናምርጥ ተሞክሮ የተቀመረበትን ሰራ
በአግባቡ ተሰርቶ ሰነድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡በመሆኑም ለምርጥ ተሞክሮዉ የተመረጡት ርዕሶች
የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

3
6. በዋና ዋና መስህቦች በጎንደር አጭር ታሪክ ከዋና ዋና ቅርሶች ምስሎችና ፖስት ካርዶች
በብሬል አዘጋጅቶ ማየት ለተሳናቸዉ ተጠቃሚ ማድረግ
ጎንደር ከተማችን አፄ ፋሲል ግቢና አካባቢዋ ስም የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል
ድርጅት ዩኒስኮ የተመዘገቡ 9 ዋና ዋና ባህላዊ ቅርሶች ያላት ከተማ በመሆን በሃገራችን ካሉት ጥንታዊ
ከተሞች ለየት ያደርጋታል፡፡ እነዚህ መስህቦች 7 ቱ በከተማ አስተዳደሩ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ቢሆኑም
17.6% ለሚሆነዉ የከተማችን ነዋሪ ተደራሽ አይደሉም፡፡(የአለም ባንክ የ 2011 እ.ኤ.አ. ሪፖርት)
በመሆኑም እነዚህ የህ/ሰብ አካላት ተደራሽ ለማድረግ ማየት ለተሳናቸዉ የብሬል አገልግሎት ሰነዶች
እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡ለተጠቃሚዎች ተደራሽ መሆኑን ማስፋት በማስፈለጉ ይህ የተሞክሮ ሰነድ በአፄ
ፋሲል ግቢ በመጀመር ወደሌሎች የከተማዋ አለም አቀፍ ቅርሶች ወደ ሆኑት ማስፋት እንዲቻል ይህ
ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

6.1. በዋና ዋና መስህቦች በጎንደር አጭር ታሪክ በግብረ ህንፃዎች አሰራር የተሰሩበት የቁሳቁስ
እና በጎንደር አጭር ታሪክ በምስል የተደገፈ የምልክት ቋንቋ ቴክኖሎጅን
(DVD)ማዘጋጀት
ጎንደር ከተማችን አፄ ፋሲል ግቢና አካባቢዋ ስም የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና
የባህል ድርጅት ዩኒስኮ የተመዘገቡ 9 ዋና ዋና ባህላዊ ቅርሶች ያላት ከተማ በመሆን በሃገራችን ካሉት
ጥንታዊ ከተሞች ለየት ብላ እናገኛታለን፡፡ እነዚህ መስህቦች 7 ቱ በከተማ አስተዳደሩ ክልል ዉስጥ
የሚገኙ ቢሆኑም 15%ለሚሆነዉ የከተማችን ነዋሪ ተደራሽ አይደሉም(በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸዉ
ብሄራዊ ማህበር)፤በመሆኑም እነዚህ የህ/ሰብ አካላት ተደራሽ ለማድረግ መስማት ለተሳናቸዉ
የምልክት ቋንቋ በድምፅና በምስል አገልግሎት ለመስጠት ሲዲና ሌሎች ሶፍት ኮፒ ተዘጋጅቶላቸዉ
እናም ሌሎች ግብአቶችን እንዲሟሉ በማድረግ ሁሉንም ቅርሶች እና የጎንደር አጭር ታሪክ በምልክት
ቋንቋ ተዘጋጅቶ ተደራሽ ተደርጓል፡፡

6.2. አፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት ግቢ፣ ራስ ግንብ ሙዚየም፣አፄ ፋሲል መዋኛ ግቢዎች ለአካል
ጉዳተኞች ተደራሽና ምቹ እንዲሆኑ የመንገድ ድንጋይ ንጣፍና ከርብ ስቶን በማዘጋጀት
እና ዊልቸር አጠቃቀም ቴክኖሎጅዎችን ማስጠቀም
ጎንደር ከተማችን አፄ ፋሲል ግቢና አካባቢዋ ስም የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል
ድርጅት ዩኒስኮ የተመዘገቡ 9 ዋና ዋና ባህላዊ ቅርሶች ያላት ከተማ በመሆን በሃገራችን ካሉት ጥንታዊ
ከተሞች ለየት ያለች ናት፡፡ እነዚህ መስህቦች 7 ቱ በከተማ አስተዳደሩ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ቢሆኑም
20%ለሚሆነዉ የከተማችን ነዋሪ ተደራሽ አይደሉም፡፡(በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸዉ ብሄራዊ
ማህበር) በመሆኑም እነዚህ የህ/ሰብ አካላት ተደራሽ ለማድረግ ለመራመድ አመች እንዲሆን የአፄ
ፋሲል ግቢ፣ የራስ ግንብ ግቢ፣ የአጼ ፋሲል መዋኛ ግቢ፣የደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ግቢና
የደብረ ፀሃይ ቁስቋም ማርያም ቤተ-ክርስቲያንና የእትጌ ምንትዋብ ቤተ-መንግስት)ግቢዎች የድንጋይ
ንጣፍና ከርብ እስቶን ስራ በሙሉ ተነጥፏል፤ተሰርቷል፡፡

4
7. ምርጥ ተሞክሮዉ የተካሄደበት ከተማ/ክ/ከተማ/ልዩ ቦታ
7.1. የከተማችን አጠቃላይ ሁኔታ
ጎንደር ከተማ ከአዲስ አበባ በ 727 ኪ.ሜ ከባህርዳርከተማ 180 ኪ.ሜ ከሱዳን(ካርቱም)በ 250 ኪ.ሜ እንዲሁም
ከአክሱም ከተማ በ 300 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በመገኘቷ የቱሪዝም መዳረሻ ብቻ ሳትሆን የቱሪዝሙ ማዕከል ከተማ
እንድትሆን አስችሏታል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ከሲራራ ንግድ የጀመረዉ ጥንታዊ የንግድ ማዕከልነቷ አሁንም
እየቀጠለ ይገኛል፡፡የአየር ንብረቷ ወይና ደጋ በመሆኑ ለመኖርና ኢንቨስት ለማድረግ ምቹነቷን ይበልጥ
የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ ማንኛዉም የሰብል ምርት የሚበቅልባትና የሚገኝባት በተፈጥሮ የታደለች
ከተማ ናት፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር በምስራቅ ጎንደር ዙሪያ ወረዳና ወገራ ወረዳ በምዕራብ ጎንደር ዙሪያ ወረዳና ደንቢያ
ወረዳ በሰሜንላይ አርማጭሆ በደቡብ ጎንደር ዙሪያ የሚዋስናትናናበስሜን ምዕራብ ኢትዮጰያ የምትገኝ
ስትሆን የከተማዋ የቆዳ ስፋት 665.70 ሄክታር ነው፡፡ ከጠቅላላ ከፕላን ኮሚሽን በተገኘው መረጃ መሰረት
የህዝቡ ብዛት በከተማና በገጠር ወንድ 213917 ሴት 240528 ድምር 454445 እንደሆነ ይገመታል፡፡ የከተማ
አስተዳደር ነዋሪ ጥግግትን ስንመለከት ደግሞ ከፍተኛ ጥግግት እንደሚኖር ያሳያል ይህም እንደ ሀገር ሲታይ
ከፍተኛ የህዝብ ጥግግት ያለ መሆኑን የከተማ አስተዳደር ነዋሪ ቋሚ አሰፋፈር ያለው እና ማህበራዊ ትስስሩን
የሚያጠናከሩ ልዩ ልዩ ማህበራዊ፤ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ አደረጃጀቶችም ባለቤት ናት፡፡ የከተማዋ ህዝብ
ቁጥር ከላይ የተገለፀውን ቢሆንም ከገጠር ወደ ከተማ የሚገባው ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ከ 700 ሽህ
በላይ ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል፡፡ ከዚህ የህዝብ ቁጥር መካከል 17.6%ያህሉ አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ
ይገመታል›› ከዚህ ቁጥር አንፃርና አካል ጉዳተኞችን እንደማንኛዉም የህ/ሰብ ክፍል በማንኛዉም የልማትና
የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነተና ተሳታፊነት ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ተቋማችን አካቶነትን
እንደአንድ ተግባር ይዞ ሲሰራበት በመቆየቱ ሌሎች መሰል ተቋማት ተግባሩን እንዲከተሉት ስለሚፈለግ ይህ
ምርጥ ተሞክሮ ተቀምሯል፡፡

8. ምርጥ ተሞክሮዉ ከመቀመሩ በፊት ወይም አሰራሩ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የነበሩ
ሁኔታዎች
በጎንደር ከተማ ብቻ ሰባት የአለም አቀፍ ቅርሶች የዚህ አካል የሆነ በርካታ ጥንታዊ ድልድዮች እና በየአመቱ
በደመቀ ሁኔታ የሚከበሩ የጥምቀትና መስቀል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት በደመቀ የሀገር ዉስጥና የዉጭ
ሀገር ቱሪስቶች ታድመዉበት የምታከብር ከተማ ናት፡፡ይህን በአሃዝ ደረጃ ለማየት መረጃ ከተያዘበት 1981
እስከ ሰኔ 2012 ያለዉ የቱሪስት ቁጥር ስናይ የዉጭ ሃገር ቱሪስቶች 1,993,308,115 ሲሆን የሃገር ዉስጥ
ቱሪስቶች ደግሞ 1,416,177 ሲሆን በሁለቱም አይነት ቱሪስቶች በፆታ፣ በእንግዳዉ አይነት ተዘርዝረዉ
የተቀመጡ ቢሆንም የአካል ጉዳተኞች መረጃ ግን በአግባቡ አልተካተተም ይህ መሆኑ እነዚህ የህ/ሰብ ክፍሎች

5
ምንያህል ተገለዉ እንደነበሩ በቃለ መጠይቆች የተገኘ ቢሆንም ምን አይነት የአካቶነት ቴክኖሎጅ ስልት
አለመኖሩን መረዳት ችለናል፡፡ አንዳንዶቹ አቅሙም ፍላጎቱም ያላዉ የዉጭ ሃገር ቱሪስቶች ቴክኖሎጅዉን
ሆነ አስጎብኝዎችን ረዳቶች በከፍተኛ ወጪ ይዘዉ የሚጠቀሙ እንደነበር ጠቋሚ መረጃዎች ምልክቶች
ቢኖሩም ሁሉም በሚባል ደረጃ ከነዚህ መስህቦች ታሪካዊ፣ ትምህርታዊና ሁለንተናዊ ፋይዳ ተጠቃሚነት
ተገለዉ የቆዩ መሆናቸዉን አረጋግጠናል፡፡

8.1. የክ/ከተሞች ሁኔታ

8.1.1. ፋሲል ክ/ከተማ


ፋሲል ክ/ከተማ በሰሜን የሳቢያ ሳይና የገጠር ቀበሌ አስተዳደር፣ በደቡብ ዞብል ክ/ከተማ በምስራቅ
ፈንጠር የገጠር ቀበሌ አሰተዳደርና በምዕራብ የአንቸዉየገጠር ቀበሌ አስተዳደር ያዋስናታል
ክ/ከተማዋበ 3 የከተማ ቀበሌዎች ማለትም የመድሃኒአለም፣የአንገረብና የአርበኞች አደባባይ ቀበሌ
አስተዳደሮችን ያቀፈችስትሆን በከተማዋ ዉስጥ ካሉ ስድስት ክ/ከተሞች አንዷና የራስ ግንብ
ሙዚየምና አብዛኛዉ የመንግስት አስተዳደር ቢሮዎች የሚገኙባት ክ/ከተማ ነች፡፡

8.1.2. ዞብል ክ/ከተማ


ዞብል ክ/ከተማ በሰሜን ፋሲል ክ/ከተማ፣ በደቡብ ማራኪ ክ/ከተማ በምስራቅ መሃል አራዳና በምዕራብ
የአባ እንጦንስ የገጠር ቀበሌ ያዋስናታል ክ/ከተማዋ በ 4 ቀበሌዎች ማለትም የልደታ፣የቃሃ
እየሱስ፣የገብርኤልና የፋሲለደስ የከተማ ቀበሌ አስተዳደሮችን ያቀፈች ስትሆን ክ/ከተማዋ በከተማዋ
ዉስጥ ካሉ ስድስት ክ/ከተሞች አንዷና የአፄ ፋሲል መዋኛ፣የደብረፀሃይ ቁስቋም ቤተ-ክርስቲያንና
የእትጌ ምንትዋብ ቤተ-መንግስትና የሺናዋ አዳራሽ እንዲሁም የዮሃንስ መጥመቀ መለኮት ታሪካዊ
ቤተ-ክርስቲያን መገኛ ነች፡፡

8.1.3. ጃንተከል ክ/ከተማ


ጃንተከል ክ/ከተማ በሰሜን ፋሲል ክ/ከተማ፣ በደቡብ መሃል አራዳ ክ/ከተማ በምስራቅ ፈንጠር የገጠር
ቀበሌ በምዕራብ ዞብል ክ/ከተማ ሲያዋስኗት ክ/ከተማዋ በ 4 የከተማ ቀበሌዎች ማለትም የፒያሳ ቀበሌ
፣ አደባባይ ኢየሱስ ቀበሌ፣አባጃሌ ቀበሌና መገናኛ ቀበሌ አስተዳደሮችን ያቀፈች በከተማዋ ዉስጥ ካሉ
ስድስት ክ/ከተሞች ዉስጥ ስትሆን በስሯ ታላቁ የአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስትና ታሪካዊ ቤተ-ክርስቲያናት
ማዕከል ክ/ከተማ ነች፡፡

8.2. የልዩ ቦታዉ ሁኔታ


8.2.1. አፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት ግቢ

አፄ ፋሲለደስ ከአባታቸው ከአፄ ሱስንዮስ ስልጣን ከተረከቡበት ከ 1624 ጀምሮ ለአራት ዓመታት በደንቀዝና
አዘዞ አካባቢ ሲያስተዳድሩ ከቁዩ በኋላ ወደ ጎንደር በመምጣት እ.ኤ.አ 1636/1628 ዓ.ም ጎንደር ከተማን
ቆርቁረዋል ይህን ግቢም እንደ ቤተ-መንግስት አስገንብተዋል ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ጎንደር ከ 250 ዓመታት በላይ
የሀገሪቱ ዋና ከተማ በመሆን አገልግላለች፡፡ በዚህም ዘመን ጎንደር የኪነ-ህንፃ የኪነ-ጥበብ፣የቤተ-ክህነት
ትምህርትና ሌሎች የእደ-ጥበብ ውጤቶች መማሪያና መፍለቂያ ከተማ እንደነበረች አሁን ያሉት ቅርሶቿ

6
ምስክርነትን ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ አብያተ መንግስታት የቱሪስት መስህብ በመሆን ለከተማዋ ዕድገት ጉልህ
አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ስዕል. 01 የአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስት

8.2.2. .አፄ ፋሲል መዋኛ

አፄ ፋሲል በስልጣን በነበሩበት ወቅት ካስገነቧቸዉ ቅርሶች መካከል አንዱ የአፄ ፋሲል መዋኛ ሲሆን
በአሁኑ ወቅት በጎንደር በተንቀሻቃሽ ቅርስነት የተመዘገበዉ የጥምቀት በዓል በድምቀት የሚከበርበት
ቦታና እንዲሁም የአፄ ፋሲል ፈረስ(የዞብል) መቃብር እንደሆነ የሚነገርለት ግብረ ህንፃ Y ሚገኝበት
ታሪካዊ ቦታ ነዉ፡፡

7
ስዕል.02 የአፄ ፋሲል መዋኛ

8.2.3. ራስ ግንብ ሙዚየም

ራስ ግንብ ሙዚየም ለራስ ቢትወደድ ወ/ጊዮርጊስ(ለአፄ ፋሲል የጦር አዛዥና ለልጃቸዉ ልዕልት
እስክንድራዊት መኖሪያ ታስቦ በአፄ ፋሲል ዘመን እንደተገነባ የሚነገርለት ታሪካዊ ቅርስ ሲሆን ጣሊያን
በወረራ ወቅት የጦር ማዘዣ አድርጎት የነበረ በኋላም አፄ ሃይለስላሴ ወደ ሰሜን ሲመጡ ሚያርፉበት
ቤተ-መንግስት የነበረ ሲሆን ከ 2009 ጀምሮ እንደገና የተወሰነ እድሳት ተደርጎለት በሙዚየምነት
ተደራጅቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

8
ስዕል. 03 የራስ ግንብ ሙዚየም

ደብረ-ብርሃን ስላሴ

ደብረብርሃን ስላሴ አማካኝነት በ 17 ኛዉ ክ/ዘመን በትልቁ አፄ እያሱ የተገነባ በድርቡሽ ያልተቃጠለ


ብቸኛ ቤተ-ክርስቲያን መሆኑ የሚነገርለት በዓለም ደረጃ ልዩ የሆኑ የጣራ ላይ ስዕሎች ያሉት ቤ-
ክርስቲያን ነዉ፡፡

ስዕል.04 ደብረ-ብርሃን ስላሴ

9
ደብረ ፀሃይ ቁስቋም ቤተ-ክርስቲያን

በጎንደር አለም አቀፍ ቅርስ አስተዳደር ስር ካሉት ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነዉ የቁስቋም ቤተ-
ክርስቲያንና የእትጌ ምንትዋብ ቤተ-መንግስት በእትጌ ምንትዋብ የተገነባና የእትጌይቱ፣የልጇ አፄ እያሱና
የልጅ ልጇ የአፄ እዩአስ አፅምና የሺናዋ አዳራሽ የሚገኝበት የከተማዋ አንዱ ታሪካዊ ቦታ ነዉ፡፡

ስዕል.05 ደብረ ፀሃይ ቁስቋም ቤተ-ክርስቲያን

9. አሰራሩ ተግባራዊ በመሆኑ የተገኘዉ ዉጤት


ይህ አሰራር ተግባራዊ የሆነዉ ከጥር 2015 ጀምሮ በመሆኑ ፡-

ሀ- መንፈሳዊ እርካታ ፡- በአካል ጉዳተኞች ተፈጥሮ የነበረዉን የስነ-ልቦና ጫና ከጅምሩ መንፈሳዊ እርካታ
ማሳደሩ ማለትም

 ተገለናል ከሚለዉ ስሜት መላቀቃቸዉ


 አካል ጉዳተኞች በጉዳቱ መጠንና አይነት በቅርስ ቦታዎች ያወጡት የነበረ ተጨማሪ ወጭ መቀነስ
 እንደ አንድ የህ/ሰብ ክፍል ተቆጥረዉ የአካቶነት ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ መሆናቸዉ የተፈጠረዉ
እርካታ
 የከተማችን ሆነ የቅርሶቻችን ገፅታ በአለም አቀፍ ደረጃ መቀየር መጀመሩ
 የተጠቃሚዎች ቁጥር ከምንም ወደ 1000 መድረሱ
 ቅርሶቻችን ያለ ልዩነት ለሁሉም የሰዉ ልጅ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ መሆኑ

10
በአጠቃላይ የአካታችነት ቴክኖሎጅ በመጠቀማችን ለሰዉ ልጅ ሊሰጠዉ የሚችለዉ ክብር መስጠታችን
የከተማችን ገፅታ ግንባታ ከፍ ከማድረግ በላይ የቅርሶችን ተደራሽነት በማስፋት የከተማችን ኢኮኖሚ
ለማሳደግ የዘርፉን ሚና ከፍ ያደርገዋል፡፡

10. የምርጥ ተሞክሮዉ ዉጤት የተገኘበት ዝርዝር ሂደት

ይህ ምርጥ ተሞክሮ የተቀመረበት ከተማ እና ዘርፍ ተሞክሮዉ ለሌሎች መሰል የክልላችን የአለም አቀፍ
መስህብ ቦታዎች ማስፋፈት እንዲቻል ስኬቱ ተገኘበትን ዝርዝር ሂደት እንደሚከተለዉ ለመቀመር
ተሞክሯል፡፡

ዘርፉ በተለያዩ የአለም አገሮች የሚታዩ (የተገኙ) መልካም ተሞክሮዎችን በከተማችን ዉስጥ በሚገኙ ዋና ዋና
የመስህብ ሃብት ቦታዎች ለመጠቀም ከ 2009 ጀምሮ ብዙ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ አካቶነት ቴክኖሎጅ የመጠቀም ግንዛቤ እና ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት ማስረፅ
በመቀጠል ተሞክሮ የተቀመረበት ከተማ እና ልዩ ቦታዉ የያዘዉ እምቅ እዉቀት ተደራሽ ያልሆኑ
የህ/ሰብ ክፍሎች ቀላል አለመሆናቸዉና የፍትሃዊነት ጥያቄ መኖሩ የማስረፅ ስራ መሰራቱ
ይህን ችግር ለመፍታት መረጃ የማሰባሰብ ስራ በኮሚቴ መፈፀሙ ፣ መረጃዉ መደራጀቱና መተንተኑ
የአካቶነት ቴክኖሎጅ አሰራር ሲተገበር የሚጠየቀዉ ልዩ የሆነ ሙያ የቁሳቁስ ግብአት በመረጃነት
መኖሩ
 የምልክት ቋንቋ ባለሙያ
 የብሬል ፅሁፍ አዘጋጅ ባለሙያ
 የቪድዮና ፎቶግራፍ ባለሙያ
 የአካባቢ አስጎብኝ ባለሙያ
 የኢዲተር ባለሙያ
 መረጃ የሚያሰባበስብና የሚተነትን ባለሙያ እና
 ሌሎች ቁሳቁሶች ማዘጋጀት ማሟላት ቅድሚያ በማሟላት ወደስራ
መግባት

11. የወጭና የገቢ ዝርዝር

11.1. የወጭ ዝርዝር


ተ.ቁ የተግባሩ አይነት በቁጥር/በአይነት ገንዘብ መጠን/በብር ምርመራ
1 ማየት ለተሳናቸዉ ብሬል ማቴሪያል 5 25000 በትብብር የተገኘ

11
2 ለድምፅና ለምስል ቀረፃ ለሁሉም 2 20000 በአበል ተከፈለ
ቅርሶች
3 መራመድ ለተሳናቸዉ ዊልቸር 4 30000 በትብብር
4 ማየት ለተሳናቸዉ መራመጃ ዘንግ 4 10000 በትብብር
5 ለምልክት ቋንቋ ማሳያ 65 ኢንች 1 100000 በግዥ
ቴሌቪዥን
6 ዲሽና ዲኮደር 1 3000 በግዥ
7 ጠረጴዛና ወንበሮች 25 80000 በግዥ
8 የሎቪዉ ቤቱ ማሳመሪያ የባህል 10 15000 በግዥ
አልበሳት
አጠ.የወጭ ድምር 256000 በግዥ

11.2. ገቢን የሚተካ የዉልና መንግስታዊ ግዴታዎች ዝርዝር በተመለከተ


የጎንደር አለም አቀፍ ቅርሶች ተደራሽነታቸዉን ማሳደግ እንደመንግስት አንድ አገልግሎት ሰጭ ተቋም
ማድረግ ከገቢ በላይ የመንግስት ግዴታ በመሆኑ
ከጎንደር የህዝብ ቁጥር አንፃር በፕሮጀክሽን ከ 100 ሺ በላይ የህ/ሰብ ክፍልን ያገለለ የነበረዉ የመስህብ
ሃብቶችን ተደራሽ በማድረግ የመግቢያ ክፍያን በማስከፈል የገቢ ምንጮች ስለሚሆን
የሞራል ተጠቃሚነት በማሳደጉ ማለትም ቀላል የማይባል የህ/ሰብ ክፍል ተጠቃሚ ሆኖ እያለ
ለዘመናት ተገለዉ መቆየታቸዉ በህዝብህ ላይ ትኩረት ያለመስጠትን የሚመስልን በደል
የሚመልስ በመሆኑ

12. ምክረ ሃሳብ


ተሞክሮዉ በብዙ አካላት እገዛና ትብብር የተሞከረ በመሆኑ ወደሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች እንዲስፋፋ
ተሞክሮዉ ቀማሪዉ አካል የሚከተሉትን ምክረ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

1- የህ/ሰባችን 1/6 ህብረተሰብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነ እ.ኤ.አ. በ 2022
በአለም ባንክ እና በአለም ጤና ድርጅት የተጠና ጥናት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ይህን ያህል የህ/ሰብ ክፍል
ያገለለ ተግባርን ስንፈፅም መቆየታችን በመፀፀት የአካቶነት ተግባር ሜኒይስትሪንግ አድርጎ መስራት
ቢጀመር
2- እንደመምሪያ የተጀመረዉ መልካም ስራ ተገቢዉ ግብአት በማሟላት መሰል ትልልቅ ድርጅቶች
አርአያነቱን በመከተል ቢጠቀሙበት
3- ተቋማችን የአገር ዉስጥ ሆነ የዉጭ ሃገር ጎብኝዎች ስለሚያስተናግድ ቢያንስ በክልላችን ያሉ አለም
አቀፍ የቅርስ መስህቦች በአጭር ጊዜ ተሞክሮዉን ቢወስዱና ቢጠቀሙ
4- መምሪያዉ ለከተማ አስተዳደሩ የጉዳዩን አስፈላጊነት እና ተደራሽነት በማስገንዘብ በበቂ በጀት እና
በሰፊዉ ተሰርቶ እንደ አንድ የህ/ሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸዉን እና ተደራሽነቱን በግብአት ቢያሟላ

12
13. ማደማደሚያ
ይህን ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ከእኛ ጋር እየኖሩና እያሉ የማናዉቃቸዉ የህ/ሰብ ክፍሎች ተደራሽ ያደረገና
ተጠቃሚ ያደረገ ሰነድ ነዉ፡፡ በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ 2011 የአለም ባንክ እና የአለም ጤና ድርጅት
አመታዊ ሪፖርት ከአለም ህዝብ ቁጥር 15% እና በታዳጊ ሃገራት ደግሞ 17.6 % ያህሉ ህዝባችን
ተጋላጭ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህ የፐርሰንት ገለፃ ወደ ቁጥር ሲቀየር አንድ ቢሊዮንየአለም ህዝብ እና
ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 21 ሚሊዬን እና ወደ ከተማችን ስንቀይረዉ 116 ሺ ያህል ህዝባችን በዚህ
አካቶነት ተጠቃሚ መሆኑን በመረዳት የአካታችነትን ቴክኖሎጅ የመጠቀም ቁጭት አድሮብን
በየአለንበት ስለተግባራዊነቱ መነሳሳት ይገባል፡፡ጅምሩ በአንድ ዉስን ቦታ እንደ ፓይለት የተጀመረ እና
በቀላሉ የተማርንበት በመሆኑ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጅምሩን ማስፋት ቢችል
ተገቢ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

13

You might also like