You are on page 1of 11

ወረዳ ------------- ደጋዳሞት

ቀበሌ------------------ ጉድባ ሰቀላ

የተሞክሮ ባለቤት የጉድባ ሰቀላ ክረምት የበጎ ፈቃድ አድራጎት ወጣቶች ማህበር

ቁጥር-------

ቀን/24/11/2010 ዓ. ም

ለ----------------------------------ቀበሌ

ጉዳዩ፡- ምርጥ ተሞክሮ ማሳወቅን ይመለከታል፣

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት
ቡድን ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደ ተለያዩ አካባቢዎችና ሴክተሮች ስናሰፋ መቀየታችን ይታወቃል፡፡
ስለሆነም በጉድባ ሰቀላ ቀበሌ የበጎአድራጎት ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮ ቀምረን የላክን ሲሆን
በቀበሌያችሁ ካሉ የበጎ ፈቃድ ማህበራት ጋር ለጋራ በማድረግ ለጋራ ለውጥ እንድትጠቀሙበት ከዚህ ሽኝ
ደብዳቤ ጋር ----------ገጽ አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

// ከሠላምታ ጋር //

አበባው ታደሰ

ግልባጭ፣

 ለደ/ዳ/ወ/አስ/ም/ቤት
 ለደ/ዳ/ወ/ብአዴን/ጽ/ቤት
 ለወ/ስ/ወ/ጽ/ቤት
 ለሚ/ል/ጥ/ም/ ቡድን

ፈ/ቤት፣

መግቢያ

በአሁኑ ጊዜ የሀገራችን ወጣቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲ በለፅግ ፣ በአካባቢያቸው የተሰሩትን
የልማትና መልካም አስተዳድር ስራዎችን በመገንዘብና በማስገንዘብ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና
በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ የመረዳዳት ባህል እንዲዳብር ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ወጣቶች የክረምት ወራትን ጊዜያቸውን በበጎፈቃድ ስራ ላይ የተበላሹ መንገዶችን


በመጠገን፣ችግኞችን በመትከል፣የደካሞችንና ድሆችን ቤት በመስራት መርዳት እና በሌሎች ማህበራዊና፣
ኢኮኖሚያዊ፣እንቅስቃሴዎች አካበቢያቸውን ለማልማት የበጎፈቃድ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ስለሆነም ይህንን ተግባር ግለቱን አስጠብቆና አጠናክሮ ለማስቀጠል የወረዳችን ወጣቶች በሁሉም ቀበሌዎች ላይ
የሚካሄዱ የልማትና መልካም አስተዳድር ስራዎች ላይ የተሻለ ምርጥ ተሞክሮ የሰሩትን ቀበሌዎች በመቀመር
ለሌሎች በማስፋት እና የተሟላ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስፈልጋል፡፡በዚህም ሁኔታ በጉድባ ሰቀላ ቀበሌ ከተለያዩ
ዩኒቨርሲቲዎች ፣ኮሌጆች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ለእረፍት የመጡ ወጣቶችና ሌሎች ወጣቶች
የቀበሌያቸውን አጠቃላይ ሁኔታ ተረድተው በቀበሌው ልማት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ያሉበት የበጎ ፈቃድ
ልማታዊ እንቅስቃሴ የስራ ውጤት ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ቢሰፋ ውጤት ያመጣል ብለን ስለ አመንበት ይህን ምርጥ
ተሞክሮ ቀምረን ለማስፋት አዘጋጅተናል፡፡

1 . ሀሳቡ እንዴት መነጨ?


 በአካባቢ ያቸው ያሉ አቅመ ደካሞችን ለመርዳት
 በአካባቢያቸው ያሉ የመሰረተልማት ችግሮችን በማየት መፍትሄ ለመፈለግ
 ተማሪዎችን ውጤታና ለማድረግ በማሰብ
 በዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ የነበራቸውን ጥሩ ልምድ ለማካፈል በማሰብ
 ተጨባጭና ችግር ፈች ስራዎችን ሰርቶ ስኬታማ ለመሆን በማሰብ
 የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሸሻል በማሰብ
 በጎ ስራን መስራት የህሌና እርካታ መሆኑን ለማሳየት

2 መነሻ እቅድ

 ከህብረተሰቡ ጋር ስለ መሰረተ ልማት መወያየት


 የወጣቶችን ደረጃጀት ለማጠናከር ግብና አላማ ይዞ መነሳት
 ከቀበሌው አመራር ጋር በጋራ ለመስራት መወያየት
 ጊዜና አቅምን አሟጦ ለበጎአድራጎት ስራ ለማዋል መወሰን
 ህብረተሰቡን በማግባባትና ግንዛቤ በማስጨበጥ ማንቀሳቀስ
 በራስ አቅም የአካባቢያቸውን ችግር ለመፍታት ማመቻቸት
 በልማት እንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ አርያ ለመሆን
3 የተጠቀሙበት ስልት

 ከእቅድ በፊት ለሚተገበሩ ተግባራት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ፣


 በአካባቢው ካሉ የሀይማኖት አባቶች ጋር መስራት በማሰብና የጋራ ሀሳብ በመያዝ ወደ ስራ
በመግባት፣
 ከወረዳና ከቀበሌ አመራሮች እንደግባት የሚያገለግሉ የአሰራር አቅጣጫዎችን መቀበል፣
 በየደረጃው ያሉ የወጣት አደረጃጀቶችን በማጠናከር መስራት መቻል፣
 ቤተክርስቲያን ላይና በቀበሌ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ሰፋ ያለ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣
 ከቀበሌው ተወላጅ ነጋዴዎች የበጎ አድራጎት ማህበሩ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻል፣
 ከቀበሌው ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ጋር የጋራ ልማታዊ ግንዛቤ ላይ በመድረስ የገንዘብ ድጋፍ
ማሰባሰብ መቻል፣
 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ከመጡ የቀበሌው ተወላጅ ተማሪዎችጋር የእንኳን
አደረሳችሁ ፕሮግራም በማዘጋጀት ገቢ በማሰባሰብ፣

የተገኘ ውጤት

 የሁለት አቅመ ደካሞች ቤት በቆርቆሮ መሰራት እና የአንድ አባውራ ጎጆ ቤት መጠገን መቻሉ፡፡


 በጋራ የመስራት ባህልን ማዳበር መቻሉ፡፡
 የተበላሹ መንገዶችን በድንጋይና በጠጠር መጠገን መቻሉ ፡፡
 ለሀይማኖታዊ ተቋማት በቀበሌው ላለ ቤተ-ክርስቲያን ለማሰራት በጉልበታቸው ድንጋይና ጠጠር
በማቅረብ ድጋፍ ማድረግ መቻሉ፡፡
 በ 2009 እና 2010 ዓ.ም የ 10 ሄክታር የወል መሬት ወረራን ማስቆም መቻላቸው፡፡
 በቀበሌው ባለ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት 600 ተማሪዎችን የማጠናከሪያ ትምህርት በክረምት ማስተማር
መቻላቸው፡፡
 ችግኞችን መትከል
 የቀበሌ ማእከላትን መጠገን እናየእንስሳት መታከሚያ(catle crash)በእንጨት መስራት
 የእርከን ስራን ማጠናከር
 ከሌላ ክልል የተፈናቀሉ የቀበሌው ነዋሪዎችን ለመርዳት ከያንዳንዱ ግለሰብ
የምግብ(ዱቄት)እርዳታ እንዲያገኙ ማድረጋቸው፡፡

የተጠገነ መንገድ የእንስሳት ማከሚያ(catle crash)


አዲስ የተተከለ ችግኝ

ገና የሚደረግለት የቀበሌ ማእከል በቆርቆ የተሰራ የድሀ ቤት
ያጋጠሙ ችግሮች

 ህብረተሰቡ ስለበጎ አድራጎት ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን


 የጊዜ እጥረትና የክረምት የአየር ፀባይ ለመስራት አስቸጋሪ መሆን
 የቁሳቁስ እጥረት መኖር
 የበጎ አድራጎት ማህበሩ ተገቢውን ድጋፍ አለ ማግኘት
 የተሰሩ ስራዎችን በወቅቱ ዕሪፖርት አለማድረግ
 ስራውን ማህበረሰቡ ለተማሪዎች ብቻ አድርጎ መተው
 ቶሎ ወደ ስራ አለመግባት
 የበጀት እጥረት መኖር

የተወሰዱ መፍትሄዎች

 የማህበረሰቡን የግንዛቤ ችግር በተመለከተ፡-በአካባቢው በሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን ሰዎች በሚሰበሰቡበት ጊዜ


ትምህርት በመስጠት እና የህብረተሰቡን አንገብጋቢ ችግር ፈትቶ በማሳየት ችግሩ ተፈቷል፡፡
 የቁሳቁስ እጥረትን በተመለከተ፡-ወረቀትና ስክርቢቶ በጎ አድራጊዎች ከኪሳቻው ብር በመግዛት የተሸፈነ
ሲሆን ሌላውን ቁሳቁስ በቀበሌው ያለው ት/ቤት ሸፍኖታል፡፡
 የሪፖርት ችግርን በግል ስልክ በመደወል በመስጠትና በአካል ሂዶ ለሚመለከተው አካል በመስጠት ችግሩ
ተፈቷል፡፡
 የጊዜ እጥረትን በተመለከተ ወረዳው ካስቀመጠው የጊዜ ገደብ ፈጥኖ በመጀመር ችግሩ ተፈቷል፡፡
 የበጀት እጥትን በተመለከተ ከቀበሌው ተወለጅ ነጋዴዎች ብር በመሰብሰብ የአቅመደካሞችንና ድሆችን ቤት
በቆርቆሮና በሳር ለመስራት ተችሏል፡፡
 ስራውን ለተማሪዎች ብቻ አድርጎ የመተው ችግርን ከቀበሌ አመራሮች እና ሀይማኖት አባቶች ጋር
በመተባበር ስራው የጋራ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
 ቶሎ ወደ ስራ ያለመግባት ችግርን በእቅድ ልክ ለመስራት መህበሩ በመወያየት ከተሰጠው ጊዜ ገደብ
በመፍጠን ወደስራ ተገብቷል፡፡

ማጠቃለያ

በደጋ ዳሞት ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አድራጎት ማህበራትን በመመስረት


አካባቢን በማልማት ለለውጥ ከሚሰሩ የበጎ አድራጎት ማህበራት የጉድባ ሰቀላ ዎጣቶች ግንባር ቀደም ናቸው፡፡
እንዲሁም መንግስት ለበጎ አድራጎት ስራ የሚያደርገውን እገዛ ሳይጠብቁ በራሳቸው ተነሳሽነት የሁለት ድሆችን
ቤት ከህብረተሰቡ ባገኙት ብር በቆርቆሮ በመስራት ፣ የአንድ ድሀ ጎጆ ቤት በመጠገን፣ 6 ሄክታር የወል መሬት
ወረራን በማስለቀቅ ፣ በቀበሌው በሚገኘው 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 600 ተማሪዎች ለክረምት የማጠናከሪያ
ትምህርት በመስጠት፣በቀበሌው እየተሰራ ለሚገኘው ቤተ-ክርስቲያን የጠጠርና የድንጋይ አቅርቦት እገዛ ማድረግ
ከሌላ ክልል ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ተፈናቅለው ለመጡ የቀበሌው ነዋሪዎች ህዝቡን በማስተባበር
የምግብ እርዳታ እንዲያገኙ በማድረግ፣ በርካታ የእግር መንገዶችን በመጠገን፣በርካታ ችግኞችን በመትከል፣በባላት
ቀን የእግር ኳስ ለመጫዎት ሜዳ በማዘጋጀት ለሌላው ቀበሌ የክረምት በጎ ፈቃድ አድራጎት ማህበራት አርያ
ሁነዋል፡፡

የቀበሌዉ ወጣቶች የእግር ኳስ ሜዳ የቀበሌዉ ወጣቶች ያስለቀቁት የወል መሬት ወረራ

በወጣቶች ጥገና የተደረገላት የድሀ ጎጆ ቤት

You might also like