You are on page 1of 19

የድሬዳዋ ከተማ ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ

የቀበሌ 06 የሥራ ዕድልፈጣራና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ምርጥ ተሞክሮ ሰነድ

ግንቦት 2010 ዓ.ም


ድሬዳዋ

ማውጫ
1.መግቢያ..........................................................................................2

2 ዓላማ፣............................................................................................3

3 ግብ...............................................................................................3

4 አስፈላጊነት.......................................................................................3

5. የምርጥ ተሞክሮው ዓይነት.......................................................................3


6. የቀበሌው ጂኦግራፊያዊና የስነ ህዝብ ሁኔታ.......................................................3

7. የቀበሌው ነዋሪ ማበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ....................................................4

7.1. ማበራዊ ሁኔታ................................................................................4

7.2. ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ............................................................................4

8. አንድ ማእከሉን በተመለከተ ያሉ ሀቆች፤..........................................................5

9. ቀበሌው ከነበሩበት ችግሮች ለመውጣትና ማነቆዎችን ለመፍታት ሲነሳ የተከተለው ስልት.........7

10. የቀበሌው አንድ ማዕከል አገልግሎት ስትራቴጂክ ግቦች.........................................7

9.1. በልማት ሰራዊት ግንባታ የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች .................................9

9.1.1. የድርጅት ክንፍ ሁኔታ....................................................................10

9.1.2. የመንግስት ክንፉ ያለበት ሁኔታ..........................................................11

9.1.3. የህዝብ ክንፍ.............................................................................15

10. በቀበሌው ያለው የድጋፍ፣ ክትትል፣ ግምገማና እና ግብረመልስ ሥርዓት......................21

10.1. ግምገማና ግብረመልስ.....................................................................21

10.2. ሪፖርትና ግብረመልስ.....................................................................21

10.3. ሱፐርቪዥንና ግብረመልስ................................................................21

10.1. ግምገማና ግብረመልስ.....................................................................21

10.2. ሪፖርትና ግብረመልስ....................................................................21

10.3. ሱፐርቪዥንና ግብረመልስ................................................................22

11. ቀበሌው አሁን ለደረሰበት ስኬት ዋናዋና የስኬት ሚስጥሮች..................................22

12. የቀበሌው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ........................................................26

1.መግቢያ

በአንድ አካባቢ ወይም አካል ምርጥ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ውጤት የተመዘገበባቸውን የልማት
ሥራዎች ተሞክሮ ቀምሮ ወደ ሌሎች ማስፋት የማስፈጸም አቅም ግንባታ አንዱ ስልት ነው፡፡ በሌላ
በኩል የአመራር የአፈጻጸም ዘይቤን ተከትሎ በሚመራ ማንኛውም የልማት ዘርፍ በማጠቃለያ ምእራፍ
ከሚሰሩ ሥራዎች አንዱና ዋናው በዝግጀትና በተግባር ምእራፎች በተሰሩ የልማት ሥራዎች ምርጥ
የአሰራር ስርዓት የዘረጉና ውጤት ያስመዘገቡ አካላትን መለየትና ተሞክሯቸውን ቀምሮ ለሌሎች ማስፋት
ነው፡፡ በመሆኑም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ በልማት ሰራዊት ግናባታ፣ በሥራ
እድል ፈጠራና በኢንተርፕራይዞች ልማት በዝግጅትና በተግባር ምእራፍ ባከናወኗቸው ሥራዎችና
ባመጡት ውጤት ልቀው ከተገኙ ቀበሌዎች መካከል ቀበሌ 06 አንዱ በመሆኑ ይህ ምርጥ ተሞክሮ
ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
2 ዓላማ፣
የዚህ ተሞክሮ ቅመራ ዋና ዓላማ በቀበሌ 06 በዘርፉ ልማት ሰራዊት ግንባታ፤ በሥራ እድል ፈጠራና
በኢንተርፕራይዞች ልማት ሥራዎች ማለትም በዘርፉ ቁልፍና ዓበይት ሥራዎች አፈጻጸም የተገኙ ምርጥ
ተሞክሮዎችን በአግባቡ ቀምሮ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ማስፋትና እንደ አስተዳደር በዘርፉ የማስፈጸም
አቅምን ማሳደግ ነው፡፡
3 ግብ
የቀበሌ 06 በጥ/አ/ኢ/ልማት ሰራዊት ግንባታ እና በዘርፉ የዓበይት ተግባራት አፈጻጸም የተገኙ ምርጥ
የአሰራር ስርዓት ተሞክሮዎች ተቀምረው ለሌሎች ይሰፋሉ፡፡
4 አስፈላጊነት

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ውስብስበና በርካታ ማነቆዎች የበዙበት ዘርፍ
በመሆኑ እነዚህን ማነቆዎች ፈትቶ ውጤት ያስመዘገበን አካል ተሞክሮ ወደ ሌሎችም ማስፋት በአነስተኛ
ወጪ እና በአጭር ጊዜ የዘርፉን የማስፈጸም አቅም የሚያሳድግ በመሆኑ፤
5. የምርጥ ተሞክሮው ዓይነት

የተለያዩ ምርጥ ተሞክሮ ዓይነቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ይህ የቀበሌ 06 ምርጥ ተሞክሮ በትግበራ ላይ
ያሉና ተስፋ ሰጪ ምርጥ ተሞክሮዎች /Promising best practices/ ከሚባሉት የምርጥ
ተሞክሮ ዓይነቶች ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡

6. የቀበሌው ጂኦግራፊያዊና የስነ ህዝብ ሁኔታ


ቀበሌው በአስተዳደሩ ካሉ 9 የከተማ ቀበሌዎች አንዱ ሲሆን በአንጻራዊነት ጠበብ ያለ የቆዳ ስፋትና
ከፍ ያለ የህዝብ ጥግግት ያለው ነው፡፡
ቀበሌው እንደ ቀፊራ፣ መጋላ፣ ደቻቱ እና አምስተኛ የመሳሰሉ የድሬዳዋ ስም ሲነሳ
አብረው የሚነሱ ታዋቂና ከተቆረቆሩ አንድ ክፍለ ዘመን ያስቆጠሩ ነባር

ቀጠና የቀጠናዎች መጠሪያ በየቀጠናው ያሉ መንደሮች ብዛት

ቀጠና 1 የቀድሞ ቀበሌ 13 (ቀፊራ) 6

ቀጠና 2 የቀድሞ ቀበሌ 14 (አምስተኛ) 3

ቀጠና 3 የቀድሞ ቀበሌ 15 (መጋላ) 3

ቀጠናበአጠቃላይ 4 0 የቀድሞአባወራናቀበሌእማወ 16 ራ( የቀበሌው 3 ነዋሪ


ከ 598 ደቻቱያለ )ሲሆን ብዛትም ከ 40,

የድሬዳዋ ሰፈሮችና ደቻቱ ወንዝ የሚገኙበት ነው፡፡ ቀበሌው 4 ቀጠናዎችና 15 መንደሮች ያሉት
ሲሆን ቀጠናዎቹ የቀድሞ 4 ቀበሌዎችን መሰረት አድርገው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
በሌው 202 (19842 ወንድ 20360 ሴት) በላይ ነው፡፡
7. የቀበሌው ነዋሪ ማበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ
7.1. ማበራዊ ሁኔታ
ቀበሌው ሁሉም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ማለትም ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ ወዘተ
የሚገኙበት ሲሆን ህብረተሰቡም ከድሬዳዋ መቆርቆር ጀምሮ በአብሮነትና በመቻቻል በፍቅር ተሳስቦ
የሚኖር ነው፡፡ ነዋሪው ከሌሎች አገሮች ነዋሪዎች (ህንዶች፣ አረቦች ወዘተ) ጋር በንግድ ተሳስሮ አብሮ
የመኖር፣ አብሮ የመሥራትና አብሮ የማደግ ባህልን የተላበሰ ደግ ህዝብ ነው፡፡ ከጥናት የተገኘ መረጃ
ባይኖርም የቀበሌው ነዋሪ ሶሽዮ-ኢኮኖሚዊ ሁኔታ ሲታይ አብዛኛው ነዋሪ በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ
የሚገኝ ሆኖ ሌላው የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖር ነው፡፡ በሌላ በኩል
አካባቢው መሸታ ቤቶች የሚበዙበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሴተኛ አዳሪነት የሚበዛበት ነው፡፡
በተጨማሪም ቀበሌው በአንጻራዊነት ማህበራዊ ጠንቆች የሆኑት ሱሰኝነት፣ ልመናና የጎዳና ኑሮ
የሚበዛበት አካባቢ ነው፡፡
7.2. ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ
የነዋሪውን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ስናይ አካባቢው ቀደም ሲል ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ የሚበዛበት
ስለሆነ የአካባቢው ነዋሪ በአብዛኛው በንግድና በአገልግሎት የሥራ መስክ የተሰማራ ነው፡፡ በተለይ
ረጅም እድሜ ያለው ቀፊራ የንግድ ማእከል ከከተማው ነዋሪ አልፎ ለአካባቢው ገጠርና ለአጎራባች
ነዋሪዎች የንግድ ማእከል ሆኖ ያገለግላል፡፡ በዚህም ቀፊራ ለገጠር-ከተማ የኢኮኖሚ ትስስር ትልቅ ሚና
እየተጫወተ ይገኛል፡፡ የገጠሩ ነዋሪ የግብርና ምርቶቹን (በተለይ አትክልትና ፍራፍሬ) እያመጣ በመሸጥ
ለኑሮው የሚያስፈልጉትን የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተለይ የጥቃቅንና አነስተኛ ምርቶችን የሚገዛው በዚህ
ገበያ ነው፡፡ በአጠቃላይ በቀበሌው ጥሩ የንግድ እንቅስቃሴ አለ፡፡
በቀበሌው የሥራ አጥና የኢንተርፕራይዞች ብዛት በ 2010 በጀት ዓመት በተደረገው የሥራ ፈላጊዎች
የቤት ለቤት ምዝገባ በቀበሌው በአጠቃላይ
1203 (486 ወንድና 717 ሴት) ሥራ ፈላጊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 123 (67
ወንድና 58 ሴት) የኮሌጅና ዩንቨርሲቲ ምሩቃንሥራ ፈላጊዎች ናቸው፡፡ከምዝገባ በኋላ እየመጡ
የተመዘገቡትን ጨምሮ በጥቅሉ 159 ምሩቃን ሥራ ፈላጊዎች ተለይተዋል፡፡
እስከ ግንቦት ወር ድረስ ባለው መረጃ በቀበሌው በአምስቱ የሥራ ዘርፎች 106 ኢንተርፕራይዞች
ተደራጅተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
8. አንድ ማእከሉን በተመለከተ ያሉ ሀቆች፤
የቀበሌው አንድ ማእከል አገልግሎት ቀደም ሲል አገልግሎት ይሰጥ የነበረው ለብቻው በተደራጀ ቢሮ
ሳይሆን ከንግድና ገቢዎች ጋር ተዳብሎ በጠባብና በተጨናነቀች ክፍል ውስጥ ነበር፡፡ በዚህም ማእከሉ
ለአገልግሎት አሰጣጥም ሆነ ለሥራ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በ 2006
በጀት ዓመት ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ በቀበሌው
የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ህንጻ እንዲገነባ አድርጓል፡፡ በድሬዳዋ ካሉ 9 የቀበሌ አንድ ማእከል
አገልግሎት ጣቢያዎች ውስጥ ስታንዳርዱን የጠበቀ የራሱ ህንጻ ያለው አንዱና ብቸኛው የቀበሌ 06
እንድ ማእከል ነው፡፡ ህንጻው ለሥራና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹና ተደራሽ በሆነ ሁኔታ የተገነባና ከሞላ
ጎደል በአግባቡ የተደራጀ በመሆኑ የተቀናጀ የአንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጡት 3 ቱ አካላት
ማለትም፡- የጥቃቅንና አነስተኛ፣ የማይክሮፋይናንስና የንግድና ገቢዎች ማስተባበሪያ ሰራተኞች በጥሩ
ሁኔታ እየሰሩበት፤ ተገልጋዮችም ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ቦታ እያገኙበት ይገኛል፡፡

10. የቀበሌው አንድ ማዕከል አገልግሎት ስትራቴጂክ ግቦች

1. የልማት ሰራዊት ግንባታ


2. የሥራ ዕድል ፈጠራ
3. የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ
4. ኢንተርራይዞች ማደራጀት
5. የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት
6. የገበያ ልማትና ግብይት ድጋፍ
7. የፋይናንስ አቅርቦት (ብድር ምችችት፣ ብድር ማስመለስና ቁጠባ ማስቆጠብ)
8. ዳታቤዝ ባለሙያ
9. የፋይናንስ አቅርቦት (ብድር ምችችት፣ ብድር ማስመለስና ቁጠባ ማስቆጠብ)
ዳታቤዝ ባለሙያ
9. የልማታዊ ሰፊቲኔት ባለሞያ II
10. የልማታዊ ሰፊቲኔት ባለሞያ II
11. የልማታዊ ሰፊቲኔት ባለሞያ
በ 06 ቀበሌ በ 2010 በሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ብዛት
በአካባቢ ልማት ---5219 በቀጥታ ድጋፍ 1070 ድምር 6289 ወንድ ሴት ድምር 1897
4392 6289
በአጠቃላይ በቀበሌ 06 በሴፍትኔት ፕሮግረአም ዙሪያ የተሰሩት ስራዎች እጅግ አመርቂና
ጥሩ ናቸው ይህንን ስል ስራው በጣም አድካሚና አሰልቺ ቢሆንም እንደሚታወቀው
በቀበሌያችን ያለው ቅንጅታው አሰራር ከአመራር እስከ መንደር ኮሚቴ በጋራ በመስራቱ
ሁኔታ በጣም ጥሩ ስለነበረ ከልየታ እስከ ተግባር ምራፍ በተሳለጠ ሁኔታ ተጠናቆ ወደ ስራ
ውስጥ ከተገባ 1 ወር ሆኖታል::
ቀበሌው የልማት ሰራዊት ግንባታ ሥራን ቁልፍ ሥራ አድርጎ የወሰደበት ምክንያት አንድም ሰራዊት
የመገንባትና የልማት ሥራዎችን በሰራዊት አግባብ መሥራት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አስተዳደር ቁልፍ
ሥራ ተደርጎ በመወሰዱ ነው፡፡ በሌላ በኩል ሥራው የዘርፉ ልማት ቁልፍ ችግር የሆነው የአመለካከትና
የኪራይሰብሳቢነት ችግር የሚፈታው በዋናነት በዘርፉ ልማታዊ ሰራዊት በመገንባት በመሆኑ ነው፡፡
ስለዚህ ቁልፉ ችግር ሲፈታ ሌሎች ዓበይት ችግሮችም ይፈታሉ የሚለውን በመያዝ በዘርፉ ልማታዊ
አስተሳሰብን የመገንባት ሥራ ቁልፍ ሥራ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ ሌሎች ለሥራ ፈላጊዎችና
ለኢንተርፕራይዞች የሚደረጉ መንግስታዊ ድጋፎች በዓበይት ተግባርነት ተቀምጠዋል፡፡
እነዚህ ዓበይት ተግባራት ሌሎች ከቁልፉ ችግር ቀጥሎ ያሉ ዓበይት ችግሮችን ለመፍታት የታቀዱ
ናቸው፡፡
ከላይ እንደተገለጸው የ 2009 በጀት ዓመት አፈጻጸምን፤ እንደ አደረጃጀት የሦስቱ ክንፍ አደረጃጀቶች
ያሉበትን ሁኔታ፤ እንዲሁም የአመራሩ፣ የፈጻሚውና የአንቀሳቃሾች ሁኔታን በአግባቡ በመገምገም የእቅድ
መነሻ ተደርገዋል፡፡ ይሄንን ግምገማ ተከትሎ ችግር ፈቺና ሦስቱን የስምሪት ምእራፎች መሰረት ያደረገ
የጠራ እቅድ በማቀድ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ እቅዱን የተግባር መመሪያ አድርጎ ለመጠቀምም ጠንካራ
አቋም ተይዞ ሥራዎች በእቅድ መሰረት እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡
በተለይም በዝግጅት ምእራፍ በእቅድ ለያዝናቸው የቁልፍ ተግባር ሥራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተን
ሰርተናል፡፡
በዚህ ምርጥ ተሞክሮ ሰነድ በቁልፍና በዓበይት ተግባራት የተሰሩ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን ከዚህ
እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡
የቀበሌ 06 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ

የቀበሌ 06 የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ባለሙያዎች


በተጨማሪም የቀበሌው የቆዳ ስፋት ጠባብ መሆን የአንድ ማእከሉን አገልግሎትና የመስክ ድጋፉን
በየትኛውም ቦታ ለሚገኙ ነዋሪዎችና ኢንተርፕራይዞች ተደራሽ አድርጎታል፡፡
"ተቋም ማንን ይመስላል? መሪውን" እንደሚባለው የአንድ ማእከሉ አመራር ለሰራተኞች ምቹ የሥራ
ሁኔታ በመፍጠርና ጥሩ ስምሪት በመስጠት የሥራ ተነሳሽነታቸውንና በቡድን የመሥራት ስሜታቸውን
ገንብቷል፡፡
በተጨማሪም ለሰራተኞች ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፡፡ በዚህም ማእከሉ ሁሌም የተረጋጋና
ሰላማዊ ምቹ የሥራ ቦታ ነው፡፡ አንድ ማእከሉ ከሞላ ጎዴል የተሟላ ሰራተኛ ያለው ሲሆን ሰራተኞችን
በሥራ በማቆየትም የተሻለ ከሚባሉት ነው፡፡ ከ 6 ቱ የማእከሉ ሰራተኞች 5 ቱ (83%) ሴቶች
ናቸው፡፡
9. ቀበሌው ከነበሩበት ችግሮች ለመውጣትና ማነቆዎችን ለመፍታት ሲነሳ የተከተለው ስልት
ቀበሌው በዘርፉ ልማት ሰራዊት ግንባታ እና በሌሎች የዘርፉ ዓበይት ተግባራት ማለትም በሥራ እድል
ፈጠራና በኢንተርፕራይዞች ልማት ሥራዎች ዙሪያ ያሉትን የአፈጻጸም ክፍተቶችና ማነቆዎችን
ለማስተካከልና ውጤት ለማምጣት ሲነሳ በቅድሚያ ከአፈጻጸም አንጻር ቀበሌው ያለበትን ሁኔታ
በዝርዝር በመገምገም መረዳትና ምን ላይ ማተኮር እንዳለበት የመለየት ሥራ ነው የሰራው፡፡ ይህንን
ለማድረግ በቅድሚያ በ 2009 በጀት ዓመት አፈጻጸሙን የተገኙ ውጤቶችን፣ የአፈጻጸም ክፍተቶችንና
ማነቆዎችን የመለየት ሥራ ነው የሰራው፡፡ ቀጥሎም በሦስቱም ክንፎች እያንዳንዱን አደረጃጀትና
አባላትን የመገምገምና የመፈረጅ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ከዚህ በመነሳት በ 2010 በጀት ዓመት ማስተካከያ
የሚደረግባቸውን አደረጃጀቶች የመለየትና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸውን ሥራዎች የመለየት ሥራ
ሰርቷል፡፡
በዚህም ሥራዎቹን ከሚፈቱት ችግሮች ዓይነትና ስፋት እና ለዘርፉ ስትራቴጂ መሳካት ካላቸው ፋይዳ
በመነሳት በሁለት ከፈላቸው ማለትም በቁልፍና በዓበይት ተግባራት፡፡
1. ቁልፍ ተግባር
የልማት ሰራዊት ግንባታ
2. ዓብይ ተግባር
የሥራ እድል ፈጠራና የኢንተርፕራይዞች ልማት ሥራዎች
እነዚህ ቁልፍና ዓበይት ሥራዎች በእቅዱ በጥቅሉ በ 8 ስትራቴጂያዊ ግቦች ተቀምጠዋል፡፡

9.1. በልማት ሰራዊት ግንባታ የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች፤

ከልማት ሰራዊት ግንባታ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል በቀበሌው አመራር በኩል የተለያዩ ማነቆዎች
በተለይም የአመለካከትና የክህሎት ችግሮች ይንጸባረቁ የነበረ በመሆኑ የሰራዊት ግንባታውን አስቸጋሪ
አድርጎት ነበር፡፡
ከነዚህ ውስጥ ዋናውና ገዥው የአመለካከት ችግር የነበረው በልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነት ላይ
ወጥ የሆነ እምነት አለመያዝና ትኩረት አለመስጠት ነው፡፡ በዚህም ሰራዊት ለመገንባት በቁርጠኝነት
አለመሥራትና የዘርፉን ሥራዎች በሰራዊት አግባብ ከመስራት ይልቅ በተለመደው አሰራር የመፈጸም
ሁኔታዎች ነበሩ፡፡
የአመለካከት ችግር ቁልፍ ማነቆ በመሆኑ በራሱ ችግር ከመሆን አልፎ ሌሎች ማነቆዎችን በተለይም
የክህሎት ማነቆን ይፈጥራል፡፡
በዚህም አመራሩ በሰራዊት ግንባታ ላይ የነበረበት የአመለካከት ማነቆ በሰራዊት ግንባታ አደረጃጀትና
አሰራር መመሪያ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዳይኖረውና በሙሉ እምነት ወደ ስምሪት ገብቶ በተግባር አፈጻጸም
ክህሎቱ እንዳይዳብር አድርጓል፡፡
አመራሩ የዘርፉ ልማት ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያውን በአግባቡ ተረድቶ ያለመስራትና
ለሌሎች የሰራዊቱ ክንፎች ውጤታማ በሆነ መልኩ ግንዛቤ መፍጠር፣ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
ያለመቻል ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ አመራሩ ለኢንተርፕራይዞች ችግር ፈቺና ውጤታማ ድጋፍ ለመስጠት
ስልት ቀይሶ አለመስራትና የጠራ እቅድ አቅዶ በመሥራት በኩል በአመራሩ የነበረው የክህሎት ክፍተት
ሌላው የሰራዊት ግንባታ ማነቆ ነበር፡፡
በተጨማሪም ቀደም ሲል ጀምሮ የቀበሌው አመራር የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ በተለይም የሥራ እድል
ፈጠራን ቁልፍ የከተማ አጀንዳና ቁልፍ የአመራር ሥራ አድርጎ በመቀበል በኩል ትልቅ የአመለካከት
ችግር የነበረበት በመሆኑ ለጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ትኩረት አለመስጠት ሌላው ማነቆ ነበር፡፡ ነገር ግን
በየደረጃው በሚዘጋጁ የስልጠናና የውይይት መድረኮች እንዲሁም የእርስ በርስ መተጋገሎች እነዚህ
ሁኔታዎች እየተሻሻሉ፤ አመራሩ በሂደት በአመለካከትም ሆነ በክህሎት እየተለወጠ ሊመጣ ችሏል፡፡
በዋናነት የዘርፉን ሥራዎች በሰራዊት አግባብ ከተሰራ የተሻለና ዘላቂነት ያለው ውጤት ማምጣት
እንደሚቻል አምኖ በመሥራት ትልቅ ለውጥ ታይቷል፡፡ በዚህም አመራሩ ወደ ተቀራረበ ደረጃ
በመምጣቱ በዘርፉ ልማት ሰራዊት ግንባታና በዓበይት ተግባራት ተሳትፎውና ቁርጠኝነቱ ጨምሯል፡፡
በመሆኑም መመሪያውን መሰረት አድርጎ በሚሰሩ የሰራዊት ግንባታ ሥራዎችና ሌሎች ዓበይት ተግባራት
ውጤታማ እየሆነ ይገኛል፡፡
በቀበሌው ያለውን የሰራዊት ግንባታ ሥራና የተገኙ ውጤቶችን በሦስቱ
ክንፎች ለይተን እንደሚከተለው እናያለን፡፡
9.1.1. የድርጅት ክንፍ ሁኔታ

የቀበሌው የጥቃቅንና አነስተኛ ግንባር


ግንባሩ 7 ወንድና 7 ሴት በድምሩ 14 አባላትን ያቀፈ ሲሆን አደረጃጀቱ ሁሉንም አካላት ያካተተና
የተሟላ ነው፡፡
በእቅድ ከመመራት አንጻር ግንባሩ እንቀበሌ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና ሦስቱ የሰራዊት ክነንፎች
ያሉበትን ሁኔታ በመገምገም ሦስቱን የስምሪት ምእራፎች ተከትሎ የጠራ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ
ገብቷል፡፡ ሥራዎችንም በእቅዱ መሰረት ይሰራል፡፡
በየምእራፉ የእቅድ አፈፃፀሙን ይገመግማል፡፡
የግንኙነት አግባቡን በተመለከተ በየ 15 ቀኑ ማክሰኞ እየተገናኙ በሰራዊት ግንባታና በዓበይት
ሥራዎች ዙሪያ ይወያያሉ፡፡
የውይይት ጊዜን ጠብቆ በመወያየት ረገድ ጥሩ ነው፡፡ ከቃለ ጉባኤው መረዳት እንደሚቻለው በ 6
ወር ውስጥ 12 ጊዜ መሰብሰብ ሲጠበቅባቸው 9 ጊዜ (75%) መሰብሰብ ችለዋል በተለያየ
ምክንያት ያልተሰበሰቡት 3 ጊዜ ብቻ ነው፡፡
የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ይለያሉ፡፡ ሲወያዩም በቀጣይ የሚከናወኑ ተልእኮዎችንና
ውሳኔዎችን እየሰጡ ቀደም ሲል የተወሰኑ ውሳኔዎችን አፈጻጸም እየገመገሙ ይሄዳሉ፡፡
ከድጋፍና ክትትል ጋር በተያያዘ አመራሩ አንድ እርከን ወርዶ አደረጃጀቶችን ይደግፋል
ይከታተላል፡፡ በተጨማሪም መሰረታዊ ድርጅቶችንና ህዋሶችን አመራሩ ተከፋፍሎ ይደግፋል፡፡
በግንባሩና በቴክኒክ ኮሚቴው መካከል ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ አሰራር አላቸው፡፡ የኮሚቴውን
ደካማና ጠንካራ ጎኖች እየለየ መፈታት ያለባቸውን እያየ ይፈታል፡፡
የግንባሩ ሰብሳቢ አልፎ አልፎ ከቴክኒክ ኮሚቴው ጋር አብሮ እየተሰበሰበ ይደግፋል፡፡
የቴክኒክ ኮሚቴው የሚያቀርብለትን የጽሁፍ ሪፖርት እየገመገመ የጽሁፍ ግብረመልስ ይሰጣል፡፡
ግንባሩ የተገመገመ የጽሁፍ ሪፖርት ለቀበሌው ኮማንድፖስትና ለማእከሉ ግንባር ያቀርባል፡፡
የቀበሌ 06 ግንባር ከሚለይባቸው ነገሮች መካከል ለማእከሉ ግንባርና ለኤጀንሲው ጥራቱንና
ወቅቱን የጠበቀ የተሟላ ወርሀዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርት ሳይጠየቅ
የሚያስገባ መሆኑ ነው፡፡
የአንቀሳቃሽ መሰረታዊ ድርጅቶች፣ ህዋሶችና አባላት ሁኔታ
ግንባሩ በ 2010 በጀት ዓመት 15 አባላትን በመመልመልና በ 1 ህዋስ በማደራጀት አባላቱን 180
አድርሷል፡፡
በ 2010 በቀበሌው ያለው የድርጅት አባላት፣ የህዋስና የመሰረታዊ ድርጅት ብዛት፡-
ተ.ቁ አደረጃጀትና አባላት እስከ 2009 የነበረ በ 2010 ያለ
1. መ/ድርጅት 2 2
2. ህዋስ 8 9
3. አባላት 165 180

የድርጅት ክንፉ የመሪነት ሚናውን ከመወጣት አንጻር አባላት በሥራቸው ተግቶ በመሥራትና ውጤታማ
በመሆን ለሌሎች ግንባር ቀደም እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
2 ቱም መሰረታዊ ድርጅቶችና ከ 9 ኙ ህዋሳት 6 ቱ እስከ ግለሰብ ድረስ እቅድ ያላቸው ሲሆን ሁሉም
አባላት ወርሃዊ ክፍያቸውን አጠናቀው መክፈላቸው አንዱ ጠንካራ ጎን ነው፡፡ በእቅዳቸው መሰረትም
15 ተጨማሪ አባላትን አፍርተዋል፡፡
9.1.2. የመንግስት ክንፉ ያለበት ሁኔታ

የመንግስት ክንፉ የዘርፉ ፈጻሚና ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት ፈጻሚው (ባለሙያው) ሲሆን
የአስፈጻሚነትና የድጋፍ ሰጭነት ሚና አለው፡፡
ይሄንን ሚናውን በተደራጀ አግባብ ለመወጣት በቀበሌው ከዘርፉ ፈጻሚና ባለድርሻ አካላት (ከጥቃቅን፣
ከቴ/ሙያ፣ ከማይክሮፋይናስ፣ ከንግድና ገቢዎችና ከሴቶችና ወጣቶች ማስተባበሪያዎች) የተውጣጣ
የቴክኒክ ኮሚቴ ተደራጅቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት ይህ የቴክኒክ ኮሚቴ 4 ወንድና 7 ሴት በድምሩ 11 አባላት አሉት፡፡
ፈጻሚው ይሄንን ሚናውን ከመወጣት አንጻር ቀደም ሲል በቀበሌው የነበሩ ማነቆዎችን ማየት በቀበሌው
የመንግስት ክንፉ ቁመና በምን ደረጃ እንደተገነባና የመጣውን ለውጥ ለማየት ያስችለናል፡፡
ቀደም ሲል በአመራሩ የነበሩ የአመለካከት ችግሮች ፈጻሚውም የሚጋራቸው ሲሆን ከነዚህ አንዱ
የነበረው ፈጻሚው የልማት ሰራዊት ግንባታ ስራን አስፈላጊነት አለመረዳትና አምኖበት ያለመስራት፤
ከማይክሮፋይናንስና ከቴክኒክና ሙያ ባለሙያዎች ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ በመሥራት በኩል
ከአመካከት የመነጨ ችግር በመኖሩ በቁጠባ፣ በብድር ምችችት እና በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን
አገልግሎት ዙሪያ በጋራ መስራት ያለመቻልና ያለመናበብ ችግር ነበር፤
በፈጻሚና ባለድርሻ አካላት በተለይም በጥቃቅን፣ በቴ/ሙያ እና በማይክሮፋይናንስ ድጋፍ ሰጪ
ባለሙያዎች የተቀናጀ ድጋፍ ለኢንተርፕራይዞች መስጠት አለቻል፤
ባለሙያው የዘርፉን ልማት ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር መመሪያውን በአግባቡ ተረድቶ
ያለመስራት ለሌሎች በተለይ ለኢንተርፕራይዞች ውጤታማ በሆነ መልኩ ግንዛቤ መፍጠር
ያለመቻል፤
በፈጻሚው በኩል የጠራ እቅድ አቅዶ በመሥራት በኩል የክህሎት ክፍተት አንዱ የነበረ ማነቆ
ነበር፡፡
የቴክኒክ ኮሚቴው ከጅምሩ ጥሩ እንቅስቃሴ የነበረው ቢሆንም በተወሰኑ አባላት (ፈጻሚዎች) ብቻ
ይንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በመሃል ከሰራተኛ መልቀቅ ጋር በተያያዘ ወደኋላ የተመለሰበትና
እንቅስቃሴ ያቆመበት ሁኔታ ነበር፤
ፈጻሚው ከአመራሩ የአመለካከትና የክህሎት ለውጥ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በፌዴራልና በአስተዳደር
ደረጃ በተዘጋጁ የከተማ ልማት ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ሌሎች የግንዛቤና የአቅም ግንባታ
ስልጠናዎች ያገኘውን እውቀት ተጠቅሞ በአመራሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ከነበሩበት ማነቆዎች
በአብዛኛው የተላቀቀበትና በአመለካከት፣ በክህሎት፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራርና በድጋፍና ክትትል ትልቅ
ለውጥ ያመጣበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ከአደረጃጀት አንጻር የቴ/ኮሚቴው የሁሉንም ፈጻሚና ባለድርሻ
አካላት ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ በአግባቡ ተደራጅቷል፡፡ ኮሚቴው የራሱን የጠራ እቅድ አውጥቶ ወደ
ሥራ በመግባት ተልእኮውን ይፈጽማል፡፡ የኮሚቴው አባላት ተልእኳቸውን ተረድተው ያለማንም ግፊት
ሥራቸውን በከፍተኛ ተነሳሽነት ይሰራሉ፡፡ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡትን የኮሚቴ አባላት እንደ አንድ
አካል ሆነው እንዲሰሩ ካደረጓቸው ሁኔታዎች መካከል የአንድ ማእከሉ ሰራተኞች ተግባብተው
መሥራታቸው፤ በቡድን መንፈስ መሥራታቸውና አነውበት በቁርጠኝነት መሥራታቸው ነው፡፡
በተጨማሪም ሁሉም ግንባር ቀደም መሆናቸው ነው፡፡ ይሄ ነው በቅድሚያ ሌሎቹንም ባለድርሻ አካላት
ወደ ሥራው እንዲሳቡና ተቀናጅተው እንዲሰሩ ያደረጋቸው፡፡
በመንግስት ክንፉ በተደረገው ግምገማ ሁሉም የማእከሉ ፈጻሚዎች ግንባር ቀደም (A ያገኙ) ሲሆኑ
በቴ/ኮሚቴ ደረጃ ከ 11 አባላት ውስጥ 9 ኙ ግንባር ቀደም (A ያገኙ) ናቸው፡፡ ከሌሎች
ማስተባበሪያዎች የተወከሉት 2 ቱ ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ (B ያገኙ) ናቸው፡፡
ኮሚቴው በየጊዜው የእቅድ አፈጻጸሙን ይገመግማል፤ ከእቅዳቸው ውስጥ የሰሩትንና ያልሰሩትን
ሥራዎች እየለዩ ይገመግማሉ ቃለጉባዔያቸውም ይሄን ያሳያል፤ መደበኛ የግንኙነት ጊዜውን ጠብቆ
ሳይቆራረጥ እየተገናኘ በተለይ ለኢንተርፕራይዞች በሚሰጡ ድጋፎች ዙሪያ ውይይት ያደርጋል፡፡
የውይይት ቃለጉባዔም ይይዛል፡፡ በተጨማሪም ከግንባሩ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ፈጥሮ ይሰራል፤
ለግንባሩ የጽሁፍ ሪፖርት ያቀርባል፤ ከግንባሩ የሚሰጠውን ግብረመልስ ወስዶ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
ኮሚቴው በዋናነት ኢንተርፕራይዞችን በልማት ቡድንና በ 1 ለ 5 የማደራጀት፣ እቅድ የማሳቀድ፤ አጀንዳ
እየቀረጸ የመስጠት፤ መደበኛ የውይይት ጊዜያቸውን ጠብቀው እንዲወያዩና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን
በሳምንት 1 ቀን በመስክ እየሄደ ይሰጣል፡፡
በበጀት ዓመቱ በቀበሌው የልማት ቡድኖችን ብዛት 27፤ የ 1 ለ 5 ቶችን ደግሞ 107 አድርሷል፡፡
በሰራዊት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ አንቀሳቃሾች ቁጥርም በ 2009 ከነበረበት 471 በ 2010 ወደ
568 አድጓል፡፡
ኮሚቴው ለኢንተርፕራይዞች የተለያዩ ስልቶችን እየተጠቀመ በቅንጅት ይደግፋል ያለባቸውን ማነቆዎች
በጋራ እየለየ እየተወያየ ይፈታል፡፡
ኮሚቴው ለኢንተርፕራይዞች የመስክ ድጋፍ ሲያደርግ ቸክሊስትን መሰረት አድርጎ ሲሆን
የኢንተርፕራይዞቹን ቁልፍ ችግሮች በደረጃ በማስቀመጥ በቅደም ተከተል ይፈታል፣ ግብረመልስም
ይሰጣል፡፡
የተለዩትን የኢንተርፕራይዝ ችግሮች በቴ/ኮሚቴው አባል የሆኑ ባለድርሻ አካላት ሁሉ
የሚመለከታቸውን ወስደው እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ፡- የሙያ/የክህሎት ክፍተት ከሆነ ቴ/ሙያ፤
የፋይናንስ ችግር ከሆነ ማይክሮፋይናንስ፤ ከቦታ ጋር የተያያዘ ከሆነ ደግሞ ጥቃቅን እንዲሁም ህጋዊነትን
የማስፈን ጉዳይ ከሆነ ንግድና ገቢዎች ይወስዳል፡፡
የቴ/ኮሚቴው በቸክሊስቱ መሰረት ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጠው ድጋፍ በዋናነት በሁለት ይከፈላል፡፡
አንደኛው በሰራዊት አግባብ ከመሥራት አንጻር ኢንተርፕራይዞቹን በልማት ቡድንና በ 1 ለ 5
የማደራጀት፣ የተደራጁትን የማጠናከር፤ እቅድ የማሳቀድ፣ አጀንዳ ቀርጾ በመስጠት ጊዜያቸውን ጠብቀው
እንዲወያዩና ልማታዊ አስተሳሰብ እንዲገነቡ የማድረግ ሥራ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የድርጅት አባላት
ሁኔታንም ያያል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የኢንተርፕራይዞቹን ምርት/አገልግሎት ጥራትና ምርታማነት
የሚያሳድጉ የምክር፣ የሙያ ክህሎት፣ የአሰራር፣ የፋይናንስ፣ የገበያ ትስስርና የቦታ ምችችት የመሳሰሉ
የቴክኒክና የግብዓት ድጋፎችን ማድረግ ነው፡፡ በቸክሊስቱ እንደሚታየው ይሄንን ድጋፍ ሲያደርግ
በቁጠባ፣ በካፒታል መጠን፣ በሰው ኃይል፣ በገበያ የመጡ ለውጦችን ያያል፡፡
ኢንተርፕራይዞችም የቴ/ኮሚቴው የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግላቸው ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ለምሳሌ፡ ድሬ አባይ ልብስ ስፌት፣ መለሰና ጉልላት ልብስ ስፌት፣ ዘይነባና ወርቁሃ የከተማ ግብርና፣
አጋዥ ሃይል ህ/ሥ/ማ፡፡
የማእከሉ ፈጻሚዎችም ሆኑ የቴ/ኮሚቴው ለኢንተርፕራይዞች የመስክ ድጋፍ ሲሰጡ በቸክሊስቱ ላይ
ለኢንተርፕራይዞቹ የተሰጠው ድጋፍና ግብረመልስ ተጽፎ ኢንተርፕራይዞቹ እንዲፈርሙ ይደረጋል፡፡
ይሄም የኢንተርፕራይዞችን ችግሮችና የድጋፍ ፍላጎት መረጃን አደራጅቶ ለመያዝ ከሚኖረው ፋይዳ
በተጨማሪ የመስክ ድጋፉን ለመከታተል ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት በመደበኛ
ፕሮግራማቸው ለድጋፍ ወደ መስክ ሲወጡ አንዱ የአንድ ማእከል ፈጻሚ ተረክቦ የሚደግፋቸውን
ኢንተርፕራይዞች ብቻ ለይተው የሚደግፉበት አሰራር ነው፡፡
ማለትም በአንዱ ቀን በአንዱ ባለሞያ የሚደገፉትን ኢንርፕራይዞች በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላው ባለሞያ
የሚደግፍቸውን ኢ/ዞች በማየትና በመደገፍ የባለሙያዎችን የድጋፍ አሰጣጥ ውጤታማትንና ችግር
ፈቺነትን በጋራ እየገመገሙና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ይሰራሉ፡፡ በዚህም በድጋፍ አሰጣጡ ችግሮችን
እየለዩና መፍትሄ እየሰጡ የሚሄዱበት አሰራር ነው፡፡
በየሳምንቱ ሀሙስ ጠዋት በመስክ ሄደው የኢንተርፕራይዞችን ችግር ለይተው ይደግፋሉ፡፡ ከሰዓት በኋላ
ደግሞ በቢሮ ተሰብስበው ለሚደግፈው ባለሙያ በድጋፍ አሰጣጡ ዙሪያ ግብረመልስ ይሰጣሉ፤ የቀጣይ
ሥራዎችንና አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣሉ፡፡
ከቴ/ኮሚቴው አቅም በላይ የሆኑና የአመራሩን ውሳኔ/እገዛ የሚፈልጉ
ጉዳዮችን ለግንባሩ አመራር ያቀርባሉ፡፡
በአንድ ማእከልም ሆነ በቴ/ኮሚቴ ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎች ኢንተርፕራይዞቹ
ያለባቸው ችግር (ለምሳሌ የመስሪያ ወይም የመሸጫ ቦታ) ከነሱ አቅም በላይ ሲሆንና አመራሩ
ካልደገፋቸውና መፍትሄ መስጠት ካልቻሉ ወደ ኢንተርፕራይዙ ተመልሶ ለመሄድና ለመደገፍ ድፍረት
አያገኙም፡፡
በኢንተርፕራይዞች በኩል ያላቸውን ተቀባይነት ያጡ ስለሚመስላቸው የሥራ ሞራላቸውም ይጎዳል፡፡
ነገር ግን በቀበሌ 06 ከባለሙያ አቅም በላይ በሆኑ ጉዳዮች ሁሉ አመራሩ በቅርበት ስለሚደግፍና
መፍትሄ ስለሚሰጥ ሁሌም በተነሳሽነትና በመግባባት ይደግፋሉ፡፡ ይሄ ነው የድርጅት (የአመራሩ)
ክንፍና የመንግስት ክንፍ መስተጋብር፡፡
በተጨማሪም በቀበሌው የለውጥ ሰራዊት ከልማት ሰራዊት ጋር ተደጋጋፊና ተመጋጋቢ ሆኖ እየሄደ
ነው፡፡ በድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ በጋራ የተለዩ ችግሮችን በመውሰድ የአንድ ማከል ሰራተኞች በ 1 ለ 5
ውይይታቸው በግለሰብ ደረጃ በጥልቀት እያዩ የእርስ በርስ መማማርና መተጋገል ያደርጋሉ፡፡
በበጀት ዓመቱም በብድር ምችችት፣ በቦታ ምችችት፣ በገበያ ትስስር ወዘተ ጥሩ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
በዚህም በኢንተርፕራይዞች ከፍተኛ የእድገት ሽግግርና የካፒታል እድገት እየታየ ነው፡፡ በአመራሩም ሆነ
በፈጻሚው በመጣው የአመለካከትና የክህሎት መሻሻል መሰረት ምንም እንኳን ቀበሌው ለቦታ ምችችት
የሚሆን ምቹ ሁኔታ ባይኖረውም አልችልም ብሎ ከመቀመጥ ይልቅ በ 2010 በጀት ዓመት ባለው
አቅም ለኢንተርፕራይዞች የመስሪያና የመሸጫ ቦታ አመቻችቷል፡፡
9.1.3. የህዝብ ክንፍ

የህዝብ ክንፍ ሁኔታ እንደሚታወቀው በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የህዝብ ክንፍ የሚባሉት በዋናነት
የዘርፉ ፈጻሚዎችና ተጠቃሚዎች የሆኑት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች ሲሆኑ
ሌሎች የህዝብ አደረጃጀቶች የሆኑት የቀጠናና የመንደር አደረጃጀቶችና አባላትም የዘርፉ የህዝብ ክንፍ
አካል ናቸው፡፡ በቀበሌው በበጀት ዓመቱ የአደረጃጀቶችንና የአባላትን ብዛት ለማሳደግ በታቀደው
መሰረት የተለያዩ ሥራዎች ተሰርተው ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በዚህ መሰረት በቀበሌው ያሉ የቀጠናና
የመንደር አደረጃጀቶችንና የኢንተርፕራይዝ የልማት ቡድኖችንና
1 ለ 5 ቶችን ብዛትና ያሉበትን ሁኔታ ከዚህ እንደሚከተለው በቅደም ተከተል እናያለን፡፡
የቀጠናና የመንደር አደረጃጀቶች ያሉበት ሁኔታ ቀደም ሲል የነበሩ ችግሮች አደረጃጀቶቹ ቀደም ሲል
በሁሉም ቀጠናዎችና በሁሉም መንደሮች የተደራጁ ቢሆንም በወረቀት እንጂ እንደ ሰራዊት በተደራጀና
በተጠናከረ መልኩ ተልእኮን ተገንዝቦ በመሥራት በኩል ሰፊ ችግሮች ነበሩባቸው፡፡ እቅድ አቅዶ
በመሥራት፣ የግንኙነት ጊዜ ጠብቆ በመወያየት፣ ቃለጉባዔ በመያዝና ሪፖርት በማድረግ ረገድ ሰፊ
ክፍተቶች የነበሩባቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም በቀበሌው አብዛኞቹ የቀጠናና የመንደር አደረጃጀቶች ዋና
ሥራቸው የሆነውን የስራ እድል ፈጠራ ሥራ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ላይ የአመለካከትና የክህሎት
ውስንነቶች ነበሩ፡፡
ሆኖም የችግሮቹ ምንጮች አንድም የመሪነት ሚና ካለው በየደረጃው ያለ አመራር ጋር የተያያዘ ሲሆን
በሌላ በኩል በዘርፉ ልማት ሰራዊት ግንባታ ዙሪያ በቂና ውጤታማ ስልጠናዎች ካለመስጠት የመነጩ
ነበር ማለት ይቻላል፡፡
በቀበሌው አመራር ከመጣው የአመለካከትና የክህሎት ለውጥ፤ ከድጋፍና ክትትል ሥርዓት መጠናከር
እንዲሁም በአደረጃጀቶቹ ከተደረገው የአደረጃጀት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች
በሂደት እየተሻሻሉ መጥተዋል፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ጊዜ በማእከልና በቀበሌ ደረጃ የሰራዊቱን
ፋይዳና የአደረጃጀቶቹን ተግባርና ኃላፊነት አስመልክቶ የተዘጋጁት መድረኮች ግንዛቤያቸው እንዲዳብርና
በአወቁት ልክ አመለካከታቸው እንዲቃና አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ባሉት 4 ቀጠናዎችና 15 መንደሮች በሁሉም አደረጃጀቶቹ የተዋቀሩ ሲሆን
በነዚህ 4 የቀጠና አደረጃጀቶች 50 አባላት ያሉ ሲሆን በ 15 ቱ የመንደር አደረጃጀቶች ደግሞ 115
አባላት ይገኛሉ፡፡ ሁሉም ቀጠናዎችና መንደሮች አደረጃጀቶቹ የራሳቸውን እቅድ አቅደው ይሰራሉ፤
የግንኙነት ጊዜን በተመለከተ ከሞላ ጎዴል ሁሉም መደበኛ ጊዜያቸውን አክብረው ይወያያሉ፤ በቀጠና
ደረጃ በየ 15 ቀኑ በመንደር ደግሞ በየሳምንቱ ይገናኛሉ፡፡ እንዳንዴም እንዳስፈላጊነቱ ከመደበኛ ውጪ
ይሰበሰባሉ፡፡ በውይይታቸውም በስራ እድል ፈጠራና በስልጠና በብድር ምችችትና በብድር ማስመለስ
ላይ ይወያያሉ፡፡ ቃለጉባዔ ይይዛሉ ነገር ግን ሪፖርት ማድረግ ላይ ገና ይቀራል፡፡ በተጨማሪም በቀጣይ
አደረጃጀቶቹን የማመጣጠን ሥራ መሰራት እንዳለበት ተገምግሟል፡፡
አባላቱ ለሥራ እድል ፈጠራ ሥራ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሥራ ፈላጊዎችን በተለይም
ምሩቃንን በቀጠናና በመንደር ለይቶ መረጃቸውን የማምጣትና በዘርፉ እንዲሰማሩና ሥራ ፈጣሪ
እንዲሆኑ ግንዛቤ የመስጠት ሥራዎችን ይሰራሉ፡፡ በተጨማሪም ወላጅ ለልጁ የሥራ እድል ፈጠራ
የድርሻውን አንዲወጣ ያስተምራሉ፡፡ ነባር ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የፋይናንስና ሌሎች ችግሮች
ለቀጠናው ከተመደበው ባለሙያ ጋር ሆነው በመለየት ድጋፉን የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ፡፡
በተለይ ሞዴል ቀጠና የሆነው ቀጠና 4 እና በሥሩ ያሉ መንደሮች ሥራ አጦችን ከመመልመልና
ከመመዝገብ ባለፈ ወጣቶችና ሴቶችን ወደ ስልጠና በማስገባት፣ ቁጠባ በማስቆጠብ፣ ብድር እንዲያገኙ
በማመቻቸትና ሌሎች የፋይናንስ፣ የማቴሪያልና የሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው የዘርፉ
አካላትና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ በቀበሌው በቀጠናና በመንደር
አደረጃጀቶች ከተከናወኑት ሥራዎች ውስጥ የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡
የቀጠና 4 የሥራ እድል ፈጠራ ሥራዎች የቀጠና 4 አደረጃጀት ከተለያዩ የመንግስትና የበጎ አድራጎት
ድርጅቶች ጋር ተቀናጅቶ በመንደሩ ለሚገኙ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች የተለያዩ የሥራ እድል ፈጠራ
ሥራዎችንሰርቷል፡፡እንዲሁም በሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የሚሆኑ የደሀደሀ የመለየት ስራ ተሰርቶ
ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተመቻችቷ ሥራውም ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን ይችላል፡፡ አደረጃጀቱ በየመንደሩ ያሉ
ሥራ አጥ ወጣቶችንና ሴቶችን በመለየት በራእይ የበጎ አድራጎት ማህበር የገንዘብ ድጋፍ ሥራ አጦችን
በተለያዩ የሥራ መስኮች በግልና በማህበር ኢን/ዝ በማደራጀት የሥራ እድል ፈጥሯል፡፡ ለዓብነት ያህል
የሚከተሉት ቀርበዋል፡-
11 ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን በቴ/ሙያ በዶሮ እርባታ ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም 19 ወጣጦችን በጂብሰም ስራ የቴ/ሙያ ስልጠና እንዲወስዱ አድርገዋል፡፡
በወጣት ተዘዋዋሪ ፈንድ ለ 11 ማህበር 55 አባላት የስልጠና የብድርና የቦታ ምችችት ተደርጓል፡፡
ለ 11 ኢንተርፕራይዝ የተሰጠ ጠቅላላ ብድር 1,420,000 ብር፡፡
በወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ ቁጠባ ቆጥበው ብድር ለመውሰድ
መጠባበቅ ላይ ያሉ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች
6 ማህበር 30 አባላት ቁጠባ እንዲቆጥቡ አድርገዋል፡፡
12 ወጣቶችን ከራእይ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የመንጃ ፈቃድ ስልጠና እንዲያገኙና
መንጃ ፈቃድ እንዲወስዱ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ይህ ድጋፍ በገንዘብ ሲለካ
92,000 ብር (ዘጠና ሁለትሺ ብር) ብር ነው፡፡
በወጣት ተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር ለወሰዱ ለ 12 ከስደት ተመላሽ ለሆኑ ኢንተርፕራይዞች የኮንቴነር
ማስቀመጫ ቦታ ምችችት ተደርጓ በተጨማሪም አንድ የቀበሌ ቤት ተሰጥቷል፡፡
ወጣቶች በኮብልስቶን ተደራጅተው 8 ማህበር 94 አባላት የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል በቀጠና 2 (የቀድሞው ቀበሌ 14-አምስተኛ) ሥራ ፈላጊዎችን የመለየትና የሥራ እድል
የመፍጠር ሥራ እየተሰራ ሲሆን ለአብነት ያህል 12 ሥራ ፈላጊ ሴቶችን በህብረት ሥራ ማህበር
በማደራጀት በልብስ አጠባ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም የመስሪያ ቦታ ችግር
ስለነበረባቸው ጉዳዩን ለኮማንድፖስት በማቅረብ የቀበሌ ቤት እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ የሥራ እድል ፈጠራ ኢንሸቲቭ ፕሮጀክቱን በመደገፍ በቀጠናው 1 የብረታብረት
ኢንተርፕራይዝ እንዲደራጅ አድርገዋል፡፡
የአንቀሳቃሽ የልማት ቡድንና 1 ለ 5 አደረጃጀቶች ሁኔታ እንደ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች
ልማት የህዝብ ክንፍ የሆኑት የዘርፉ ፈጻሚና ተጠቃሚ አንቀሳቃሾች
/ኢንተርፕራይዞች/ ናቸው፡፡
በቀበሌው ያለውን የአንቀሳቃሾች ሁኔታ ስናየው ቀደም ሲል እንደ ኢንተርፕራይዝ በሰራዊት አግባብ
ለመንቀሳቀስ የአመለካከት ችግርና የሰራዊቱን ፋይዳ ያለመረዳት ነበረ፡፡ ይህም ችግር የመነጨው አንድም
አመራሩም ሆነ ፈጻሚው በልማት ሰራዊት ግንባታ ፋይዳና በአሰራርና በአደረጃጀት መመሪያው ላይ በቂ
ግንዛቤ ይዞ በቁር ጠኝነት ያለመደገፍ ሲሆን በሌላ በኩል በቂ ስልጠናዎችን ካለመስጠት የመነጩ
ናቸው፡፡
ሆኖም በሂደት በአመራሩና በመንግስት ክንፉ በኩል የጠራ አመለካከትና ጥሩ ግንዛቤ እየተያዘ
ሲመጣ ደጋፊውም አካል በአግባቡ እየደገፈና አንቀሳቃሾችም የራሳችውን ጥረት
በመጨመራቸው በሰራዊት አግባብ የመሥራት ሁኔታው ሊሻሻል ችሏል፡፡
ተ.ቁ አደረጃጀትና አባላት እስከ 2009 የነበረ በ 2010 ያለ
የልማት ቡድን 25 27
2. 1ለ5 84 107
3. አባላት 471 568

እዚህ ላይ በሰራዊት ተደራጅተው የሚነቀሳቀሱ አንቀሳቃሾች ብዛትና አደረጃጀቶች ብቻ ሳይሆን


የጨመረው አደረጃጀቶቹ በአመለካከትም፣ አቅዶ በመሥራትም የግንኙነት ጊዜ ጠብቆ በመገናኘትና
በወሳኝ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይቶችንና ትግሎችን በማድረግ ረገድም ጥሩ ለውጥ መጥቷል፡፡ ተደራጅቶ
በመንቀሳቀስ አምኖ ለመስራት የተዘጋጀ አንድ አካል፣ የመጀመሪያው መገለጫው ተግባርና ኃላፊነቱን
በአግባቡ ማወቁ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በቀበሌው ያሉ አብዛኞቹ ኢንተርፕራይዞች በቴ/ኮሚቴው
የተጠናከረ ድጋፍ ከመደራጀት በዘለለ በሰራዊት የመደራጀት ፋይዳንና ተግባርና ኃላፊነታቸውን
በአግባቡ ተረድተው በተቀመጠው አሰራር መሰረት የሚሰሩ ናቸው፡፡ በዚህም 27 ቱም የልማት
ቡድኖች እቅድ አላቸው፣ ሁሉም (107 ቱም) 1 ለ 5 ቶች የጥራት ደረጃው የተለያየ ቢሆንም በእቅድ
ይመራሉ፣ 25 ቱ (92%) የል/ቡድኖችና 80 ው (95%) 1 ለ 5 ቶች መደበኛ ጊዜያቸውን
ጠብቀው ይሰበሰባሉ ይወያያሉ፡፡ ሁሉም (100%) የልማት ቡድኖችና 1 ለ 5 ቶች ቃለጉባዔ
ይይዛሉ፡፡ 14 ቱ (56%) የል/ቡድኖችና 70 ው (83%) 1 ለ 5 ቶች ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡
በሰራዊት አግባብ በመንቀሳቀሳቸው በኢ/ዞች ላይ ተጨባጭ ለውጦች መታየትም ጀምረዋል፡፡ ለምሳሌ
በበጀት ዓመቱ ቀበሌው 9 ሞዴል ኢን/ዞችን እፍርቷል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በቀበሌው የራሳቸውን ገንዘብ፣
ጊዜና ጉልበት ተጠቅመው ከራስ ጥቅም አልፈው ሌሎች ኢንተርፕራይዞችንና ሀገራቸውን ለመጥቀም
የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን የሰሩ ኢንተርፕራይዞች ይገኛሉ፡፡ ቀበሌውም እነዚህን ኢን/ዞች ልዩ ትኩረት
ሰጥቶ ይደግፋል ያበረታታል፡፡ ለምሳሌ ማሜ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራዝን ማየት ይቻላል፡፡ ማሜ የዶሮ
እርባታ ኢንተርፕራይዝ በ 2006 ዓ.ም በ 10,000 ብር የመነሻ ካፒታል በአንድ ግለሰብ ተመስርቶ
ሥራ የጀመረ የግል ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ ሥራ ፈጣሪው የራሱን ገቢ ፈጥሮ ራሱን ለመቻልና ኑሮውን
ለማሻሻል የመረጠው የጥ/አነስተኛ ዘርፍን በመሆኑ በመኖሪያ ቤቱ በ 200 ዶሮዎች በጀመረው ሥራ
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከራሱ አልፎ ለሌሎች 5 ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል፡፡
ንተርፕራይዙ ከምስረታው ጀምሮ በየጊዜው ሙያዊ እውቀትና ክህሎቱን እንዲሁም የገበያ አቅሙን
እያሳደገ በመምጣት በአሁኑ ወቅት ካፒታሉን ከብር 500,000 በላይ ማድረስ የቻለ ኢንተርፕራይዝ
ነው፡፡
ኢንተርፕራይዙ በዓንድ አመት ውስጥ ብቻ ከአነስተኛ ጀማሪ ወደ አነስተኛ የበቃ ኢንተርፕራይዝ
መሸጋገሩ ፈጣን ሽግግር ያደረገ ብቸኛ ኢንተርፕራይዝ ያደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢን/ዙ በተሰማራበት
የዶሮ እርባታ ሥራ ሁሌም ጥናትና ምርምር የሚያደርግ በመሆኑ ያለውን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም
የፈጠራ ችሎታውን ተጠቅሞ በአንድ ጊዜ 3000 እንቁላሎችን ማስፈልፈል የሚችል የዶሮ ማስፈልፈያ
ኢንኪውቤተር ማሽን መፍጠር ችሏል፡፡ ይሄም ማሽን በሚመለከተው አካል ውጤታማነቱ
ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም የመኖ ማቀነባበሪያና መፍጫ ማሽን መፍጠር ችሏል
ኢንተርፕራይዙ ስራውን ለማስፋፋት ሌላ አዲስ ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ትግበራ ጀምሯል፡፡
በኢንተርፕራይዙ የተፈጠረውና ውጤታማነቱ የተረጋገጠው የመኖ ማቀነባበሪያና
በተጨማሪም በከተማ ግብርና ለሚሰራ ኢንተርፕራይዝ ቀደም ሲል ቆሻሻ መጣያ የነበረን ቦታ አልምቶ
እንዲጠቀም የተደረገለት ድጋፍ ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል፡፡
ማነቆዎችን ለመፍታት ቆርጦ የተነሳ አመራር አደናቃፊ ሁኔታዎች በበዙበት ሁኔታም ጭምር ማነቆዎችን
መፍታት ይችላል፡፡
ዋናው ጉዳይ ማነቆው መፈታት እንዳለበት በቂ ምክንያት መያዝና መፈታትም እንደሚችል ጽኑ እምነት
መያዝ ነው፡፡
በተጨማሪም ከተደላደለ የሥራ ሁኔታ ውስጥ /ከ Comfort Zone/ ወጥቶ ለመሥራት ራስን
ማዘጋጀትና በቁርጠኝነት መሥራት ነው፡፡
በሦስተኛ ደረጃ ነገሮችን በተለመደው መልኩ ሳይሆን ከሳጥን ውጭ ሆኖ ማሰብ፣ ፈጠራን መጠቀምና
ኃላፊነት መውሰድ ነው፡፡
የኢ/ዞች የእድገት ደረጃ ሽግግርና የታዳጊ መካከለኛና የሞዴል ኢ/ዞች ቁጥር፤ በቀበሌው አንድ ማእከል
የሚሰጡ መንግስታዊ ድጋፎች ውጤታማነት የሚታየው ቀበሌው ባፈራቸውና የእድገት ደረጃ ሽግግር
ባደረጉ፣ ሞዴል በሆኑና ወደ ታዳጊ መካከለኛ በተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ነው፡፡ በ 2010 በጀት
ዓመትም እስከ ግንቦት ወር በተሰራ የእድገት ደረጃ ልየታ እስከ 2007 ከተደራጁት 86
ኢንተርፕራይዞች ውስጥ 16 (30%) ኢን/ዞች የእድገት ሽግግር ማድረጋቸው የተረጋገጠ ሲሆን
ሥራው ገና እየተሰራ ያለበት ሁኔታ ላይ በመሆኑ በዓመቱ መጨረሻ ከዚህ በላይ ሽግግር ያደረጉ
ኢንተርፕራይዞች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 9 ሞዴል
ኢንተርፕራይዞችንና 2 ወደ ታዳጊ መካከለኛ የተሸጋገረ ኢንተርፕራይዝ ማፍራት ተችሏል፡፡
የቀበሌው ውስጣዊና ውጫዊ ቅንጅታዊ አሰራር ውስጣዊ ቅንጅቱን በተመለከተ የቀበሌው አመራር
ዘርፉን የስበት ማእከል አድርጎ በመቀበሉ በዘርፉ የሚሰሩ ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ ተቀናጅቶና ተናቦ
ይሰራል፡፡ በዚህም በአመራርም ሆነ በፈጻሚ ደረጃ ከሌሎች ማስተባበሪያዎች ጋር ጥሩ ቅንጅት ፈጥሮ
ይሰራል፡፡
በተለይም ከቴ/ሙያ ተቋማት ጋር በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና በአጫጭር ስልጠናዎች ተቀራርቦና ተናቦ
በመሥራት ውጤት እያመጣ ይገኛል፡፡ ከማይክሮፋይናንስ ጋርም በመካከላቸው ያለውን ቅንጅታዊ
አሰራር በጋራ በመገምገም በአሁኑ ወቅት ካለፈው በተሻለ ሁኔታ ተቀናጅቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ቀበሌው
ከኤጀንሲውና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጥሩ ቅንጅታዊ አሰራር አለው፡፡
10. በቀበሌው ያለው የድጋፍ፣ ክትትል፣ ግምገማና እና ግብረመልስ ሥርዓት

ቀበሌው አመራሩን ሲገመግምና ውጤት ሲሰጥ አመራሩ ለተመደበበት አደረጃጀት ባደረገው ድጋፍና
ክትትል ባመጣው ውጤት/ለውጥ መሰረት ነው፡፡
ቀበሌው በአቅዱ ለዘርፉ ልማት ሰራዊት ግንባታና ለዓበይት ሥራዎች እቅድ ትግበራ በዋናነት ሦስት
የክትትልና ድጋፍ ስልቶችን አስቀምጧል፡፡
10.1. ግምገማና ግብረመልስ

10.2. ሪፖርትና ግብረመልስ

10.3. ሱፐርቪዥንና ግብረመልስ

10.1. ግምገማና ግብረመልስ

በዚህ ስልት በየደረጃው በሚዘጋጁ መደበኛ ወይም በሌላ የስብሰባ/የግምገማ መድረኮች ተጠሪ አካላት
ሪፖርታቸውን በመድረክ የሚያቀርቡበትና በመድረክ የሚገመገምበት ስርዓት ሲሆን በአፈጻጸማቸው
የቃል ግብረመልስ ይሰጣቸዋል፡፡ ቀበሌው በየምእራፉ የዘርፉን ልማት ሰራዊት ግንባታና
የኢንተርፕራይዞች ልማት ሥራዎችን በየደረጃው በቀበሌው ኮማንድፖስት፣ በቀበሌው የጥ/አ/ግንባር
እንዲሁም በቴክኒክ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባዎች የአፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገመገማል፤
ግብረመልስም ይሰጣል፡፡ በተለይ በ 2010 በጀት ዓመት የዝግጅት ምእራፍና የተግባር ምእራፍ
ሥራዎችን ገምግመናል፡፡
10.2. ሪፖርትና ግብረመልስ

በሪፖርትና ግብረመልስ የድጋፍና ከትትል ሥርዓት ተጠሪ አካላት ለሚመለከተው አካል /አደረጃጀት
በየጊዜው (በየሳምነቱ፣ በየ 15 ቀኑ፣ በየወሩ፣ በየሩብ ዓመቱ ወይም በየዓመቱ) በመደበኛነት ወይም
በተጠየቀ ጊዜ የጽሁፍ ሪፖርታቸውን የሚያቀርቡበትና በአፈጻጸማቸው እንዳስፈላጊነቱ በቃልም ሆነ
በጽሁፍ ግብረመልስ የሚሰጥበት አሰራር ነው፡፡
በዚህ መሰረት በቀበሌ 06 ያሉ የድርጅት፣ የመንግስትና የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች ለሚመለከተው
አደረጃጀት የጽሁፍ ሪፖርት የሚያቀርቡበትና ግብረመልስ የሚሰጡበት ጥሩ ጅምሮች አሉ፡፡ ከዚህ ጋር
በተያያዘ ቀበሌ 06 ን ከሌሎች ቀበሌዎች ለየት የሚያደርገውና ግንባር ቀደም የሆነበት ጥሩ ባህል
አለው፡፡ ይሄም የቀበሌው አንድ ማእከልም ሆነ የጥ/አ/ግንባር ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመትና
ሌሎች በመደበኛነት የሚቀርቡ ወይም አስቸኳይ የቁልፍና የዓበይት ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርቶችን
የማንንም ጥሪ/አስታዋሽ ሳይጠብቅ በጥራትና በዝርዝር አዘጋጅቶ ከሁሉም ቀድሞ ያስገባል፡፡ እነዚህን
ሪፖርቶች ሲያቀርብም በቅድሚያ በቀበሌው ኮማንድፖስት አስገምግሞ /የተገመገመ ሪፖርት/ ነው፡፡
በተጨማሪም የሚቀርበው ሪፖርት የተሟላ፣ መሬት ላይ ያሉትን ተጨባጭ ሁኔታዎች በትክክል
የሚያሳይ ገላጭ ሪፖርት ነው፡፡
በተጨማሪም ሪፖርቱ ሲቀርብ የተደራጁ ኢ/ዞች፣ ድጋፍ ያገኙ ኢ/ዞች፣ ወዘተ ዝርዝር መረጃ አባሪ
ተደርጎ ነው፡፡
የቀበሌው የጥቃቅንና አነስተኛ ግንባር በየወሩ ለቀበሌው ኮማንድፖስት በጽሁፍ የተደገፈ ሪፖርት
ያቀርባል፤ ኮማንድፖስቱም ሪፖርት ገምግሞ ግብረመልስ ይሰጣል፡፡
10.3. ሱፐርቪዥንና ግብረመልስ

የቀበሌው አመራር፣ የማዕከሉ ፈጻሚዎችና የቴ/ኮሚቴ አባላት በቅንጅት በየአደረጃጀቶች የመስክ


ምልከታ የሚያደርጉ ሲሆን ይሄም ቸክሊስትን በመጠቀም የሚከናወን ነው፡፡ የግንባሩ አመራር
ህዋሶችንና ኢንተርፕራይዞችን ተከፋፍሎ በመስክ ይደግፋል፡፡ በመስክ ምልከታው ለአደረጃጀቶች
ግብረመልስ ይሰጣል፡፡
11. ቀበሌው አሁን ለደረሰበት ስኬት ዋናዋና የስኬት ሚስጥሮች /Success Factors/

ስኬታማ በሆኑ ሰዎችና በሌሎች መካከል ያለው ልዩነት ወይም የስኬታማነት ልዩነቱን የፈጠረው ነገር
በመካከላቸው ያለው የእውቀትና የክህሎት መበላለጥ ወይም የችሎታ መለያየት አይደለም፡፡ ዋናው
ልዩነት የአመለካከት ልዩነት መኖሩ ነው፡፡ ስለዚህ የስኬታችን ወይም የውድቀታችን ቁልፉ
አመለካከታችን ነው፡፡ ምክንያም የእውቀትና የክህሎት ደረጃችንን የሚወስነውና ባህሪያችንን የሚገዛው
አመለካከታችን ነው፡፡ የአመለካከት ማነቆ ከተፈታ ሌሎቹን ማነቆዎች መፍታት ቀላል ነው፡፡ መልካም
አስተሳሰብና አመለካከት የመልካም ውጤት ዘር ነው ይባላል፡፡ አመለካከት ላይ ችግር ካለ ሁሉም ነገር
ላይ ችግር አለ፡፡
ቀበሌ 06 ቀደም ሲል ከጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ሥራዎች በተለይ ከልማት ሰራዊት ግንባታ ጋር
በተያያዘ ሰፊ የአፈጻጸም ክፍተቶች ነበሩበት፡፡ የነዚህ ክፍተቶች ምንጭ ደግሞ በቀበሌው የነበረው
የአመለካከት ችግር ነው፡፡ ከላይ እንዳልነው አመለካከት ላይ ችግር ካለ ሁሉም ነገር ላይ ችግር አለ፡፡
በተለይም የአመለካከት ችግሩ በአመራሩ ውስጥ ከሆነ ችግሩን ከባድ ያደርገዋል፡፡ በቀበሌው የነበረው
የአመለካከት ችግር ብቻ ሳይሆን የክህሎት፣ የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የድጋፍና ክትትልና ሌሎችም
ችግሮች የነበሩ ቢሆንም መነሻቸው የአመለካከት ችግር በመሆኑ የነበራቸው ተጽእኖ ቀላል የሚባል
ባይሆንም ቁልፉ ጉዳይ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ በዋናነት ሁለት ቁልፍ የአመለካከት ችግሮች ነበሩ፡፡
አንደኛው የዘርፉን ሥራ (የሥራ እድል ፈጠራና የኢ/ዞች ልማት ሥራን) ቁልፍ የከተማ አጀንዳ አድርጎ
አምኖ አለመቀበልና የሥራ አጥነት ችግር የሚያስከትለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አሉታዊ
ውጤት (ቀውስ) አቅልሎ የማየት ነው፡፡ ሁለተኛው በልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነት ላይ ሙሉ
እምነት አለመያዝና በቁርጠኝነት አለመሥራት ነው፡፡
በዚህም በልማቱ ቀጣይነት ያለው ፈጣን ለውጥ ለማምጣትና ውጤቱንም
ዘላቂ ለማድረግወሳኝ የሆኑትን የልማት ኃይሎች በተሟላና በተቀናጀ መልኩ የመጠቀም እድሉ
አልነበረም፡፡
ቀበሌው ቀደም ሲል ከነበሩበት የአፈጻጸም ችግሮች ተላቆ ውጤት ማምጣት የጀመረበት ዓብይ ምክንያት
በቀበሌው በተለይ በአመራሩ የነበሩት እነዚህና ሌሎች የአመለካከት ችግሮች አብዛኞቹ በመቃለላቸው
ነው፡፡ የመሪነት ሚና ያለው የአመራሩ በአመለካከት መለወጡ ክህሎቱንም እንዲያሳድግና ያለውንም
ብቃት እንዲጠቀም በር ከመክፈቱም በላይ በሌሎቹም የሰራዊት ክንፎች ማለትም በመንግስት
ፈጻሚውና በአንቀሳቃሾች እንዲሁም በቀጠናና በመንደር አባላት ላይ ስር ነቀል የሆነ የአመለካከት፣
የክህሎት፣ የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የክትትልና ድጋፍ ለውጥ እንዲመጣ አስችሏል፡፡ ስለዚህ የቀበሌው
ስኬታማነት ዋናው መነሻ በየደረጃው በተዘጋጁ የተለያዩ የስልጠናና የውይይት መድረኮች ከአመራሩ
ጀምሮ በፈጻሚውና በአንቀሳቃሾች የተገኘው የአመለካከት ለውጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ በህይወቱ ትልቅ
ለውጥ አመጣ የሚባለው የአመለካከት ለውጥ ያመጣ ቀን ነው፡፡ ምክንያቱም የሰውን ልጅ አመለካከት
መቀየር ከባድ ስለሆነ ነው፡፡ ቀበሌው ወደ ስኬት ጎዳና ለመግባት አመለካከት ላይ የሰራው ሥራ
መንገዱን ጠረገለት ቢባልም ይሄን ተከትሎ የተሰሩ ሥራዎችና ሌሎች ከዚህ በታች የቀረቡ ጉዳዮች
ቀበሌውን አሁን ለደረሰበት ደረጃ አብቅተውታል፡፡
ከሞላ ጎዴል ሁሉም የቀበሌው አመራር የዘርፉን ልማት ቁልፍ የከተማ ልማት አጀንዳ አድርጎ መውሰዱና
ተግባሩን በዚህ ቅኝት አስተካክሎ መምራት መቻሉ፤ ማለትም የከተማው ነዋሪ ቁልፍ ችግር ድህነትና
ሥራ አጥነት መሆኑን በአግባቡ መገንዘቡ፤ ይህንንም ወስዶ እንደ ከተማ አመራርነቱ በቀበሌ ደረጃ
ትርጉም ሰጥቶ መሥራቱ፤ እነዚህን የድህነትና የሥራ አጥነት ችግሮችን ለመፍታት
መንግስትያስቀመጣቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች
(በተለይም የጥ/አ/ኢ/ልማት ስትራቴጂ) ላይ የጠራ ግንዛቤ ይዞ መንቀሳቀሱ፤ ይሄን ተከትሎ የቀበሌው
አመራር ለዘርፉ ልማት በተለይም ለሥራ እድል ፈጠራና ለኢ/ዞች ልማት ሥራ እንዲሁም ለሰራዊት
ግንባታ ሥራ ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የቀበሌው አመራርና ማህበረሰብ የጋራ መግባባት
ፈጥሮ የዘርፉ ባለቤት፣ ፈጻሚና ደጋፊ (Supportive) ሆኖ እየሰራ ይገኛል፤
በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የቀበሌውን ነባራዊ ሁኔታ መገምገማችንና ለውጥ ለማምጣት ቆርጠን
መነሳታችን ለውጤት አብቅቶናል፤ ችግሩን በአግባቡ ማወቅ የመፍትሄው ግማሽ ነው ይባላል፡፡ እንደ
ዘርፍ ያሉትን ችግሮችና የችግሮቹን ምንጮች መለየትና መተንተን መቻሉ፤ መፍትሄዎቹንና መሰራት
ያለባቸውን ሥራዎች ግልጽ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ አመራሩ ችግሮቹ ባይፈቱ የሚከተለውንና ቢፈቱ
ደግሞ የሚገኘውን ውጤት መገንዘቡ በቁርጠኝነት ለመሥራት ጠንካራ ምክንያት ሆኖታል፤
የ 2009 በጀት ዓመት የቁልፍና የዓበይት ተግባራት አፈጻጸምን፤ እንደ አደረጃጀት የሦስቱ ክንፍ
አደረጃጀቶች ያሉበትን ሁኔታ፤ እንዲሁም የአመራሩ፣ የፈጻሚውና የአንቀሳቃሾች ሁኔታን በአግባቡ
ገምግመን የእቅድ መነሻ ማድረጋችን፤
ይሄንን ግምገማ ተከትሎ ችግር ፈቺና ሦስቱን የስምሪት ምእራፎች ተከትለን የጠራ እቅድ አቅደን
መሥራታችን፤ እንዲሁም እቅዱን የተግባር መመሪያችን አድርገን በመጠቀም ረገድ አቋም ይዘን ከሞላ
ጎዴል ሥራዎችን በእቅድ መሰረት መሥራታችን፤ በተለይም በዝግጅት ምእራፍ በእቅድ ለያዝናቸው
ሥራዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተን ሰርተናል፡፡ በዝግጅት ምእራፍ በሦስቱም ክንፎች ማለትም ከድርጅት
ክንፍ አደረጃጀቶች 100 ፤ ከመንግስት ክንፍ
100% እናከህዝብ ክንፍ 97% አደረጃጀቶችን እቅድ አሳቅደናል፡፡
እቅድ ማሳቀዱ ብቻውን ውጤት ስለማያመጣ በሦስቱም ክንፎች የእቅድ ኦረንቴሽን በመስጠት ፈጻሚው
አካል የሚሰራውን ሥራ እና ለምን እንደሚሰራ እንዲያውቅ ተደርጓል፤ በዚህም የጋራ መግባባት
መፍጠር ተችሏል፡፡
በሦስቱም ክንፎች በተዘጋጁ የእቅድ ኦረንቴሽን መድረኮች፡- ከድርጅት ክንፍ አባላት 99%፤
ከመንግስት ክንፍ አባላት 100% እና ከህዝብ ክንፍ አባላት 96% በእቅድ ኦረንቴሽን እንዲሳተፉ
ተደርጓል፡፡
በ 2009/2010 በጀት ዓመት ለአመራሩ፣ ለፈጻሚው፣ ለአንቀሳቃሾችና ለአደረጃጀቶች አባላት
በየደረጃው (ከፌዴራል እስከ ቀበሌ) የተሰጡት የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፤
7.በመንግስት ክንፉ በተለይም በአንድ ማእከል የዘርፉን ተልእኮና የልማት ሰራዊት ግንባታውን ዓላማ
ተረድተው የሚሰሩ፤ ሥራቸውን አክብረውና የአገልጋይነት ስሜት ተላብሰው የሚሰሩ ግንባር ቀደም
ፈጻሚዎችን መፍጠራችን ለስኬታችን ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ በመንግስት ክንፉ በተደረገው ግምገማ
ሁሉም የማእከሉ ፈጻሚዎች ግንባር ቀደም (A ደረጃ ያገኙ) ናቸው፡፡
8.በቀበሌው በተለያዩ አካላት የተደረጉ የሱፐርቪዥን ሥራዎችና የተሰጡ ግብረመልሶች፤
9.የከተማ ኮማንድፖስትና የጥቃቅንና አነስተኛ ግንባር የሚሰጧቸውን የሥራ አቅጣጫዎችን ተከትለንና
ትኩረት ሰጥተን ተናበን መሥራታችን፤
10.በየጊዜውና በየምእራፉ በሦስቱም ክንፎች ያለውን የሰራዊት ግንባታ ሥራንና ሰራዊቱ ያለበትን
ሁኔታ እየገመገምን ክፍተቶችን እየለየን በክፍተቶቻችን ላይ የምንሰራ መሆኑ፤ በተለም በዝግጅት
ምእራፍ ማጠናቀቂያ ላይ ሥራዎቻችንን በደንብ ገምግመን በሦስቱም ክንፎች ጠንካራና ደካማ ጎኖችን
ለይተን ወደኋላ የቀሩብንንና የተንጠባጠቡብንን ሥራዎች ለቅመን በተግባር ምእራፍ ሰርተናቸዋል፡፡
11.ለዓብነት ያህል በግምገማችን የድርጅት ክንፉ በሚፈለገው ደረጃ አለመጠናከሩን አይተን የክትትልና
ድጋፍ አግባባችንን አጠናክረናል፤ በዚህም እያንዳንዱ የግንባሩ አመራር ህዋሶችንና ኢ/ዞችን ተከፋፍሎ
እንዲደግፍ ተደርጓል፡፡
12.በተመሳሳይ መልኩ የሥራ እድል ፈጠራ ሥራንና ለኢንተርፕራይዞች የሚሰጡ ድጋፎችን
በመገምገም ችግሮችን እየለየን መፍትሄ እየሰጠን መሄዳችን፤
13. ቀበሌው ገና ይቀረናል የሚላቸው ነገሮች፤ በቀበሌው አሁን በጅምር ደረጃ የተገኙት ውጤቶች
እንዳሉ ሆነው ቀበሌው ገና ይቀረናል የሚላቸውና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራቸው እንደሚከተለው
ቀርበዋል፡፡፤
የድርጅት ክንፉ የመሪነት ሚናውን እንዲጫወትና ለሌሎች
ግንባር ቀደም ሆኖ በዘርፉ ያሉ የኪራይ ሰብሳቢነትና የተዛቡ አመለካከቶችን እንዲታገል
ማብቃት፤
በሦስቱም ክንፎች ያሉ አደረጃጀቶችን ወደ ተቀራረበ የሰራዊት ቁመናና የአፈጻጸም ውጤት ላይ
ማድረስ፤
የዘርፉን ሥራዎች ሙሉ በሙሉ በሰራዊት አግባብ መፈጸምና መላ የቀበሌውን ህዝብ በንቃት
በማሳተፍ የልማቱ ፈጻሚና ባለቤት ማድረግ፤
በቀበሌው በብድር ማስመለስ ዙሪያ ለተመዘገበው ዝቅተኛ አፈጻጸም ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን
መለየት፣ መፍትሄ መስጠትና አፈጻጸሙን ማሻሻል፤
በቀበሌው ያለው ወጣት አሁን አሁን በዘርፉ ተደራጅቶ ለመሥራት ፍለጎት እያሳየ ቢሆንም ወጣቱ
የእለት ገቢውን ብቻ ከማሰብ ተላቆ በአመለካከት ተለውጦ የራሱን ሥራ ፈጥሮ በዘላቂነት እንዲሰራ
ከማድረግ አንጻር ሰፊ የአመለካከት ግንባታ ሥራ መሥራት ናቸው፡፡
12. የቀበሌው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ (ይሄን ውጤት አጠናከሮ ከማስቀጠል አንጻር)፤

1.የድርጅት ክንፉን በማጠናከርና ልዩ ድጋፍ በመስጠት የመሪነት ሚናውን በአግባቡ የሚወጣበት


ቁመና ላይ ማድረስ፤
2.በአደረጃጀቶች መካከል የተመጣጠነ የሰራዊት ቁመናና እንቅስቃሴ ደረጃ ላይ ማድረስና እንደ ቀበሌ
ሙሉ ቁመና ያለው ሰራዊት መገንባት፤
3.በዘርፉ ልማት ሥራዎች በተለይም በሥራ እድል ፈጠራ ዙሪያ አሁን ካለው በተሻለ ደረጃ
ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሥራ፣ መስራትና ሥራዎችን በሰራዊት አግባብ መሥራት፤ ውጤት ላይ ማተኮር
ናቸው፡፡
4.ወጣቱ ወደ ጥቃቀቅንና አነስተኛ መጥቶ የራሱን ሥራ ፈጥሮ ዘላቂነት ያለው ሥራ እንዲሰራ ከማድረግ
አንጻር ሰፊ የአመለካከት ግንባታ ሥራ መሥራት እንዳለብን ገምግመናል፡፡

You might also like