You are on page 1of 13

ማውጫ

ክፍል 1
አርስት፤ ገጽ፤
1. መግቢያ------------------------------------------------------------------------------------------------------1
2. የጥናቱ ዳራ--------------------------------------------------------------------------------------------------1
3. የጥናቱ ዓላማ------------------------------------------------------------------------------------------------1
4. የጥናቱ አስፈላጊነት-----------------------------------------------------------------------------------------1
5. የጥናቱ ወሰን------------------------------------------------------------------------------------------------2
6. ጥናቱ ሲካሄድ የገጠሙ ችግሮች---------------------------------------------------------------------------2
ክፍል 2
1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ------------------------------------------------------------------------------------2
2. የጥናቱ ተሳታፊወች----------------------------------------------------------------------------------------2
3. የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ-------------------------------------------------------------------------------------2
4. መጠይቁ የተበተነላቸው ባለድርሻዎች---------------------------------------------------------------------2
5. የመረጃ አቀራረብና አተናተን ስርዓት--------------------------------------------------------------------3-9
ክፍል 3
1. የጥናቱ ማደማደሚያ--------------------------------------------------------------------------------------10
2. መፍትሄ ሀሳቦች-------------------------------------------------------------------------------------------10

I
ክፍል አንድ
መግቢያ /Introduction/
መንግስት የጀመረውን ብቁ ዜጋ የማፍራት ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለማስኬድ የሚሰጠውን ትምህርት ጥራቱን
በማስጠበቅ ዜጎች ጥራት ያለው ትት አግኝተው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ይሆኑ ዘንድ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ይህን ተግባር በአግባቡ ለማከናወንና ለመደገፍ በእውቀት ፣ በአመለካከትና በክህሎት የተሻለ ግንዛኔ ይዞ
በአገልጋይነት ስሜት መስራትን ይጠይቃል።በመሆኑም በቡድናችን ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ለመረዳትና
ያሉ ክፍተቶችን ከወዲሁ እያስተካከለ ለመሄድ ያመች ዘንድ ይህን የዳሰሳ ጥናት መስራት አስፈላጊ ሆኖ
ተገኝቷል።
የጥናቱ ዳራ /Back ground of the study/
መንግስት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን መሻሻል ዋነኛ የቅድሚያ ትኩረት ጉዳይ አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በትምህርት ቤቶች የሚካሄደውን የመማር ማስተማር ተግባር በሚፈለገው ደረጃ በማከናወን የተማሪወች
ውጤት ማሻሻልን እንደ አንድ ቁልፍ ጉዳይ አድርጎ በመለየት ከ 1999 ዓ.ም ጀምሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት
ማረጋገጫ መርሀ ግብር በመቅረጽ በሀገራችን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በትምህርት ጥራት ማጋገጫ መርሀ ግብሩ
ውስጥም የአጠቃላይ ትምህረት ኢንስፔክሽን እንደ እንድ እካል ተወስዶ እየተተገበረ ይገኛል። ይህን ተግባር
በውጤታማነት ለመፈጸም ደግሞ የአገልጋይነት ስሜት ተላብሶ መስራትና የደንበኞችን እርካታ ማረጋገጥ
ያስፈልጋል። በመሆነም በቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ክትትልና ግምገማ
ቡድን በቡድኑ የአገልግሎት አሰጣጡን ለመረዳትና የሚታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል ታሰቦ የተዘጋከጀ የዳሰሳ
ጥናት ነው።
የጥናቱ ዓላማ /Objective of the study/
በቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ትምህርት ኢስፔክሽን ክትትልና ግምገማ / ቡድን የአገልግሎት
አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ በመረዳትና የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት የአገልግሎት አሰጣቱን ለውጥ ሊአመጣ
በሚችል መልኩ ለመፈጸም ነው፡፡
የጥናቱ አስፈላጊነት /Significance of the study/
ይህ ጥናት በአጠቃላይ ትምህርት ኢስፔክሽን ክትትልና ግምገማ ቡድን ያገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ደረጃ
በመረዳት የሚታዩ ችግሮችን በማስተካከልና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ትምህርት ቤቶች ወደ ሚፈለገው
ደረጃ ለማድረስ በመታሰቡ ነው፡፡

የጥናቱ ወሰን /Scope of the study/

1
ይህ ጥናት በቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ክትትልና ግምገማ ቡድን
ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በመረዳት የሚታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ለዋጭነት ያለው አገልግሎት
መስጠት ትምህርት ቤቶችን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ በወረዳው ያሉትን ትምህርት ቤቶች ያካትታል፡፡
ጥናቱ ሲካሄድ ያጋጠሙ ችግሮች /Limitations/
 የመጠይሇን ፋይዳ አሳንሶ ማየት
 መጠይቁን በወቅቱ ሞልቶ አለመላክ
 መይቱን በትክክል አለመሙላት
 መጠይቁን በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ አለመሙላት
ክፍል ሁለት
የናሙና አመራረጥ ዘዴ /Sampling technique/
በቢቡኝ ወረዳ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮ 5 ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ርእሰ
መምህር 20 እና የመጀመሪያ ደረጃ መምህር 15 በድምሩ 40 መርሰወች በኢንስፔክሽን ስርዓቱ ያለፉ
በመሆናቸውና ዋነኛ የመረጃ ምንጭ በመሆናቸው በራንደም ሳምፕሊንግ አመራረጥ /Random Sampling/ ዘዴ
ተመርጠዋል።
የጥናቱ ተሳታፊወች /Population/
በዚህ ጥናት ከተሳተፉት ውስጥ ፣ የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች የትምህርት ቤት ርእስ መምህራንና መምህራን
ይገኙበታል::
የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴወች /Methods of data collecotion/
የተጠቀምነው የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ የጹህፍ መጠየቅ ሲሆን መጠይቁን በማዘጋጀትና በሃላፊነት ለጉድኝት
ሱፐርቫይዘሮች በመስጠትና መጠይቁን ሞልተውና አስሞልተው እንዲአመጡልን በማድረግ በቅንጅት የተሰራ
ነው፡፡
መጠይቁ የተበተነላቸው ባለድርሻወች፣

ሱፐርቫይዘር ርዕሰ መምህር መምህር ጠቅላላ ድምር


5 20 15 40

የመረጃ አቀራረብና አተናተን ስርዓት/Mothods ct data presentation and analysis


መጠይቅ 1

2
1. በአጠቃላይ ትም/ት ኢንስፔክሽን ስራ ላይ የወረዳ ትም/ት ኢንስፔክተሮች ት/ቤቱ የኢንስፔክሽን ስራ
ከመሰራቱ በፊት ተቋሙ ኢንስፔክት እንደሚደረግ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ይሰራሉ ወይ?
ሀ. ግንዛቤ ፈጥረው ወደ ተቋሙ ይመጣሉ
ለ. ምንም አይነት እውቅና ሳይፈጥሩ ወደ ተቋሙ ይመጣሉ
ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 5 /100%/
የሚሆኑት የወረዳ የትምህርት ኢንስፔክተሮች ት/ቤቱ የኢንስፔክሽን ስራ ከመሰራቱ በፊት ተቋሙ
ኢንስፔክት እንደሚደረግ ግንዛቤ ፈጥረው ወደ ተቋሙ ይመጣሉ የሚል ምላሽ የሰጡ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ ከመጠይቁ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ መጠይቁ ከተሰጣቸው 20 የት/ቤት አመራሮች
ውስጥ 19 /95%/ የሚሆኑት ግንዛቤ ፈጥረው ወደ ተቋም ይመጣሉ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪው 1
ርእሰ መምህር /5%/ መጠይቁን ያልሞላ ነው።
በሌላ በኩል ከመጠይቁ አኳያ መረጃ እንዲሰጡ ከተፈለጉት 15 መ/ራን መካከል 12 /80%/ የሚሆኑት የት/ት
ኢንስፔክተሮች ት/ቤቱ ኢንስፔክት ከመደረጉ በፊት ለተቋሙ ግንዛቤ ፈጥረው ይመጣሉ የሚል ምላሽ
መስጠት የቻሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 /20%/ የሚሆኑት መ/ራን ደግሞ የሰጡት መረጃ የወረዳ የት/ት
ኢንስፔክተሮች ተቋሙ የኢንስፔክሽን ስራ እንደሚሰራለት ምንም አይነት እውቅና ሳይፈጥሩ ወደተቋሙ
ይመጣሉ የሚል ምላሽ የሰጡ ናቸው፡፡
ከዚህ መጠይቅ አኳያ አጠቃላይ መረጃ እንዲሰጡ መጠይቅ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 36
/90%/ የሚሆኑት መርሱወች የወረዳ የት/ት ኢንስፔክተሮች ት/ቤቱ በበጀት አመቱ የኢንስፔክሽን ስራ
እንደሚሰራለት እውቅና ፈጥረው ወደ ተቋም የሚሄዱ መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው፡፡

2. የአጠቃላይ ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን ወቅት ት/ቤት እንደደረሱ በመጀመሪያ


ማድረግ የሚገባቸውን ነገሮች በመመሪያው መሰረት ይተገብራሉ ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አላምንም
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 4

3
/80%/ የሚሆኑት አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪው 1 ሱፐርቫይዘር /20%/ አላምንም የሚል
ምላሽ መስጠት የቻለ ነው፡፡
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 20 /100%/ አዎ የሚል
ምላሽ የሰጡ ናቸው፤
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መራን ውስጥ 14 93.33% እዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪው
1 መምህር /6.37%/ ደግሞ አላማንም የሚል ምላሽ የሰጠ ነው።
 በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ ለመረዳት እንደተሞከረው መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች
ውስጥ 38 /95% የሚሆኑት የወረዳ ትምህርት ኢንስፔክተሮች በኢንስፔክሽን ወቅት ት/ቤት እንደደረሱ
ማድረግ የሚገባቸውን ነገር በመመሪያው መሰረት እየተገበሩ መሆኑን ያሳዩ ናቸው፡፡
3. የአጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ስራው ከተሰራ በኋላ ኢንስፔክተሮች በት/ቤቱ የተለዩ ችግሮችን ለባለድርሻ
አካላት በማሳወቅ በኩል ያለውን አስተዋጽኦ በምን ይገልፁታል?
ሀ. እ.በጣም ከፍተኛ ለ. በጣም ከፍተኛ ሒ ከፍተኛ መ. መካከለኛ ሠ. ዝቅተኛ
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መይቱን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 2 /40%/
የሚሆነት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሚል ምላሽ የስጡ ሲሆን ሌሎች 2 /40% የሚሆኑት ደግሞ በጣም ከፍተኛ
የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ቀሪው 1 /20%/ ከፍተኛ የሚል ምላሽ የሰጠ ነው።
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 4 /20% እጅግ በጣም ከፍተኛ º 4
/20% በጣም ከፍተኛ 4 /0% ከፍተኛ፤ 6 /30% መካከለኛ፤ 17/5%/ ዝቅተኛ መሙላት የቻለ ሲሆን ቀሪው 1
/5%/ መጠይቁን መውላት ያልቻለ ነው፡፡
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መራን ውስጥ 2 /13.33%/ እጅግ በጣም ከፍተኛ፣ 5 /33.33%/ በጣም
ከፍተኛ፣ 3 /20%/ ከፍተኛ 2 /13.33%/ መካከለኛ፤ 2 /3.33%/ ዝቅተኛ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪው 1
/6..66%/ መጠይቁን መሙላት ያልቻለ ነው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ ለመረዳት እንደተሞከረው መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች
ውስጥ 27 /67.5%/ የሚሆኑት እጅግ በጣም ከፍተኛ፤ በጣም ከፍተኛ እና ከፍተኛ የሚል ምላሽ የሰጡ
ቢሆንም ቀጣይ በትኩረት መሰራት ያለበት መሆኑን መረጃው ይጠቁማል፡፡

4. የወረዳ የትም/ት ኢንስፔክተሮች አጠቃላይ በትሌት ደረጃ የኢንስፔክሽን ስራቸውን ጨርሰው ከአከናወነ
በኋላ የተለዩ ችግሮችን በመውጫ ኮንፈረንስ ላይ ሲያሳዩ ያላቸውን ተቀባይነት /ስምምነት/ ተግባቦት በምን
ልክ ይገልፁታል።
ሀ. እበጣም ከፍተኛ ለ. በጣም ከፍተኛ ሐ. ከፍተኛ መ. መካከለኛ ሠ. ዝቅተኛ
ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 2/40%/

4
የሚሆኑት እጅግ በጣም ከፍተኛ፣ 1 /20%/ ከፍተኛ፣ 1 /20%/ መካከለኛ፣ 1/20%/ ዝቅተኛ የሚል
ምላሽ ሰጥተዋል።
ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 4 /20%/ እጅግ በጣም
ከፍተኛ 5 /25%/ በጣም ከፍኛ፣ 10 /50%/ ከፍተኛ፤ 1 /5%/ መካከለኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 3/20%/ እጅግ በጣም ከፍተኛ፤ 5 /33.33%/ በጣም
ከፍተኛ፤ 1 /6.66% ከፍተኛ፤ 2 /13.33%/ መካከለኛ፤ 1 /6.66/ ዝቅተኛ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን
ቀሪዎቹ 3 /20%/ መጠይቁን መሙላት ያልቻሉ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ ከመጠይቅ አኳያ ለመረዳት እንደተሞከረው መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች
ውስጥ 31 /77.5%/ የሚሆኑት እጅግ በጣም ከፍተኛ፣ በጣም ከፍተኛ እና ከፍተኛ የሚል ምላሽ
ሰጥተዋል፡
5. የወረዳ ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች አጠቃላይ በት/ቤት ደረጃ የኢንስፔክሽን ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ
የፅሁፍ ግብረ መልሱን ከ 2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለተቋማት ያደርሳሉ ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አላምንም
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 4
/80%/ የሚሆኑት አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን 1 /20%/ አላምንም የሚል ምላሽ መስጠት የቻለ
ነው።
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 14 /70%/ አዎ ያሉ ሲሆን
ቀሪዎቹ 6 /30%/ አላምንም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡ ❖ በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን
ውስጥ 106666/ አዎ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 5 /33.37% የሚሆነት ደግሞ አላምንም የሚል ምላሽ
ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ ለመረዳት እንደተሞከረው መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች
ውስጥ 28 /70%/ የሚሆኑት አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ወይም የኢንስፔክሽን ግብረ መልሱ ከ 2 ሳምንት
ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መድረሱን ያረጋገጡ ናቸው።

6. የወረዳ ትምህርት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ከስጡት አስተያየቶች ውስጥ የተለዩ ችግሮችን ለቀበሌ ምክር
ቤቶች አቅርበው ችግሮችን እየፈቱ ከመሄድ አኳያ ያለዎት እንቅስቃሴ ሲታይ
ሀ. ከፍተኛ ለ. መካከለኛ ሐ. ዝቅተኛ
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 2
/40%/ ከፍተኛ 2 /40%/ መከለኛ፣ 1 /20%/ ዝቅተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 3 /15%/ ከፍተኛ፤ 11 /55%/
መካከለኛ፣ ዝቅተኛ 6 /30%/ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

5
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሎት 15 መሃራን ውስጥ 320% ከፍተኛ፣ 2 /13.33%/ መካከለኛ 10
/66.66%/ ዝቅተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በአጠቃላይ ከመጠይቁ አኳያ ለመረዳት እንደተሞከረው መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ
17 /42.5%/ የሚሆኑት ዝቅተኛ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀጣይ በትኩረት መስራት እንዳለበት
መረጃው ያመላክታል፡፡
7. የት/ቤት የኢንስፔክሽን ስራ በተደጋጋሚ ተቋማት መደረጋቸው ጥቅም አለው ብለው ያምናሉ ወይ?
ሀ. አምናለሁ ለ. አላምንም
ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 4
/80%/ የሚሆኑት አምናለሁ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪው 1 /20%/ አላምንም የሚል ምላሽ
የሰጠ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 16 /80%/ አምናለሁ ያሉ
ሲሆን ቀሪዎቹ 4 /20%/ አላምንም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 14 /93.33%/ አምናለሁ ያሉ ሲሆን ቀሪው 1
/6.67%/ ደግሞ መጠይቁን ያልሞላ ነው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ ከዚህ አኳያ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 34 መርሱወች
/85% የሚሆኑት አምናለሁ የሚል ምላሽ የሰጡ ወይም ትምህርት ቤቶች በተደጋጋሚ ኢንስፔክት
መደረጋቸው ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ያረጋግጡ ናቸው፡፡

8. በት/ቤት ደረጃ የሚደረገውን የትም/ት ኢንስፔክሽን ስራ ኢንስፔክተሮች በተቀመጠው መመሪያና የጊዜ


ገደብ መሰረት እያከናውነት ነው ብለው ያምናሉ? ሀ. አዎ ለ. አላምንም
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካክል 3
/60%/ የሚሆኑት አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ 2 /40%/ አላምንም የሚል ምላሽ መስጠት
ችለዋል፡፡
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 18 90% አዎ ያሉ ሲሆን
ቀሪዎቹ 2 /10%/ አላምንም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

6
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 12 /80%/ አዎ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 /20%/
የሚሆኑት ደግሞ አላምንም ያሉ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 33 /82.5%/
የሚሆኑት አዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ወይም በትምህርት ቤት ደረጃ የሚደረገው የኢንስፔክሽን ስራ
በተቀመጠው መመሪያና የግዜ ገደብ መሰረት እየተሰራ መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው::
9. በትም/ት ኢንስፔክተሮች የተለዩት ችግሮችን በመያዝ የወረዳ ትምህርት ፅ/ቤቱን የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን
በምን መልኩ ይገልፁታል?
ሀ. በክፍተኛ ለ. በመካክለኛ ሐ. በዝቅተኛ መ. በጣም ዝቅተኛ
 ከዚህ መይት አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 1 /20%/
ከፍተኛ፣ 2 /40%/ ዝቅተኛ፤ 2 /40%/ በጣም ዝቅተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መራን መካከል 1 /5%/ ከፍተኛ ፣ 8 /40%/
መካከለኛ፣ ዝቅተኛ 5 /25%/፣ በጣም ዝቅተኛ 6 /30%/ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 2 /13.33%/ ከፍተኛ፣ 9 /60%/ መካከለኛ፣ 3
/20%/ ዝቅተኛ፣ 1 /6.67%/ በጣም ዝቅተኛ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ከመጠይቁ ከዚህ መጠይቅ የሚወሰድለት ድምዳሜ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች
ውስጥ 19 /47.5%/ የሚሆኑት የጽ/ቤቱ ድጋፉ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በዚህ
ተግባር ለቀጣይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት መረጃው ይጠቁማል፡፡

10. የአጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችን አጠቃላይ ስለ ትም/ት ኢንስፔክሽን መመሪያዎች፣ አሰራሮች


ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በጥቅሉ በምን ልክ ይረዱታል?
ሀ. በጣም ከፍተኛ ሊ ከፍተኛ ሐ. መካከለኛ መ. ዝቅተኛ
ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 2
/40%/ የሚሆኑት በጣም ከፍተኛ፣ 1 /20%/ ከፍተኛ፣ 1 /20%/ መካከለኛ፣ 1 /20%/ ዝቅተኛ የሚል
ምላሽ ሰጥተዋል።
ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 3 /15%/ በጣም ከፍተኛ፣
9 /45%/ ከፍተኛ፤ 7 /35%/ መካከለኛ፤ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን 1 /5%/ ደግሞ መጠይቁን መሙላት

7
ያልቻለ ነው።
በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 4 /26.6%/ በጣም ከፍተኛ፤ 3 /20%/ ከፍተኛ፣ 5
/33.33%/ መካከለኛ የሞሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 /20%/ መጠይቁን መሙላት ያልቻሉ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 22 /55%/ የሚሆኑት
የሰጡት ምላሽ የወረዳ የት/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች አጠቃላይ ስለ ኢንስፔክሽን አሰራሮች
ያላቸው እውቅና ከፍተኛ እና በጣም ከፍተኛ ነው የሚል ቢሆንም እውቀትና ክህሎትን እያዳበሩ
መሰራት እንዳለበት መረጃው ይቁማል፡፡
11. በኢንስፔክሽን ወቅት ኢንስፔክተሮች መረጃ በሚሰበስበብት ጊዜ በተጨባጭ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ
ተመስርተው ይሞላሉ ብለው ያምናሉ? ሀ. አወ ለ. አይደለም
 ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 2
/40%/ የሚሆኑት እዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 /60%/ አይደለም የሚል ምላሽ መስጠት
ችለዋል፡፡
 ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 19 /95%/ እዎ ያሉ ሲሆን
ቀሪው 1 /5%/ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
 በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መራን ውስጥ 12 /80% አዎ ያሉ ሲሆን 2 /13.33%/ የሚሆኑት
ደግሞ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ቀሪው 1 /6.67%/ ደግሞ መጠይቁን ያልሞላ ነው፡፡
 በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 33 /82.5%/
በኢንስፔክሽን ወቅት ኢንስፔክተሮች መረጃ የሚሰበስቡት በተጨባጭ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ
ተመስርተው መሆኑን ያረጋገጡ ናቸው፡

12. በኢንስፔክሽን የተለዩ ችግሮች በት/ቤቱ አመታዊ እቅድ ላይ ተካተው ታቅደዋል ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አይደለም
ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁን እንዲሞሉ ከተበተነላቸው 5 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች መካከል 3
/60%/ የሚሆኑት እዎ የሚል ምላሽ የሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ 2 /40%/ አይደለም የሚል ምላሽ መስጠት
ችለዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪም መጠይቁን ከሞሉት 20 የት/ቤት ር/መ/ራን መካከል 18 /90%/ አዎ ያሉ ሲሆን
ቀሪዎቹ 2 /10%/ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሌላ መልኩ መጠይቁን ከሞሉት 15 መ/ራን ውስጥ 12 /80%/ አዎ ያሉ ሲሆን 2 /20%/ የሚሆኑት
ደግሞ አይደለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ከዚህ መጠይቅ አኳያ መጠይቁ ከተበተነላቸው 40 መርሱዎች ውስጥ 33 /82.5%/

8
በኢንስፔክሽን የተለዩ ችግሮችን ት/ቤቱ በአመታዊ እቅዱ ላይ አካቷል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ክፍል 3/ሶስት/
የጥናቱ ማደማደሚያና የመፍትሄ ሀሳቦች/Conclusion and Recommendation/
 የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በቢቡኝ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን
የአገልግሎት አሰጣጡን በመዳሰስ፣
 ክፍተት ወይም ውስንነት ያለባቸውን በማስተካከልና
 ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል እንደሚቻል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡
በዚህም መሰረት፤
 የአጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ስራው ከተሰራ በኋላ ኢንስፔክተሮች በት/ቤቱ የተለየ ችግሮችን
ለባለድርሻ አካላት ማለትም ወ.ተ.መ.ህ ቀተስቦ ሱፐርቫይዘር ወ.ዘ.ተ ሁሉንም ሰብስቦ በማሳወቅ
በኩል ያለውን እንቅስቃሴ ውስንነት ያለበት መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።
 የወረዳ ትምህርት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ከሰጡት አስተያየቶች ውስጥ የተለየ ችግሮችን
የትምህርት ተቋማት ለቀበሌ ምክር ቤቶች አቅርበው ችሣሮችን እየፈቱ ከመሄድ አኳያ መሰረታዊ
ችግር እንዳለ ጥናቱ ያሳያል።
 በትምት ኢንስፔክተሮች የተለዩት ችግሮችን በመያዝ የወረዳ ትምህርት ዕቤቱ የድጋፍና የክትትል
ስርዓት ውስንነት ያለበት መሆኑን ጥናቱ ያሳያል።
 የአጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችን አጠቃላይ ስለ ትምት ኢንስፔክሽን መመሪያዎች
9
አሰራሮች ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ውስንነት እንዳለበት ጥናቱ
የሚያሳይ ሲሆን
 እንደ አጠቃላይ ሲታይ የቡድናችን የአገልግሎት አሰጣጥ ያለበት ደረጃ 73.12% ላይ መሆኑን ጥናቱ
ያመላክታል፡፡
የመፍትሄ ሀሳቦች /Recommendation/
 እንደ ቡድናችን የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳሻልና ትምህርት ቤቶችን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ
የሚከተሉት የመፍትሄ ሀሳቦች ተወስደዋል።
 ኢንስፔክስን ስራ ከተሰራ በኋላ በትምህርት ቤቱ የተለየ ችግሮችን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ
ችግሮችን የማቅረብና ችግሮችን በባለቤትነት እንዲቀበሏቸው የማድረግ ስራ ቢሰራ
 ለአዳዲስ የትምህርት ቤት አመራሮች ስለ ኢንሰፔክሽን አስራር እና ጠቀሜታ ቡድኑ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ
መስራት ሲሻል
 በትምህርት ቤት ደረጃ በኢንስፔክሽን የተለዩ ችግሮች ቀበሌ ምክር ቤት ላይ እየቀረቡ ችግሮች እንዲፈቱ
ለትምህርት ቤት አመራሮችና ለቀበሌ ምክር ቤት አፉ ጉባኤወች የግንዛቤ የመፍጠር ስራ ስሰራ
 በቀበሌ ደረጃ ያልተጠናከረ የቀበሌ ምክር ቤት እንዲደራጅ የወረዳ ምክር ቤት አፈጉባኤወችን የመጠየቅ ስራ
ቢሰራ
 ትምህርት ጽ/ቤቱ ለትምህርት ቤት አመራሮች በተለይም ለጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች የተለዩ የኢንስፔክሽን
ችግሮችን በባለቤትነት በመያዝ ለቀበሌ ምክር ቤት እንዲአቀርቡ ጫና እንዲፈጥር ማድረግ ቢቻል
 እንደ ቡድን ፕሮግራም በማዘጋጀት የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን ማድረግ ቢቻል
 በትምህርት ጽ/ቤቱ መደበኛ የሆነ የሱፐርቪዥን ስራ ሲኖር የኢንስፔክሽንን ተግባር አንድ የቸክሊስት አካል
አድርጎ በማካተት ድጋፍና ክትትሉን ማጠናከር ቢቻል
 ትምህርት ጽ/ቤቱ ለድጋፍና ክትትል የሚሆን በጀትና ትራንስፖርት እንዲፈቅድ ከአስተዳደር ጽ/ቤቱነ ግፊት
የማድረግ ስራ ቢሰራ
 በእቅድና በማንዋል የተደገፈ የርዕስ በርዕስ መማማር ስራ በመስራት ሁሉም የቡድኑ ባለሙያወች
በአሰራሮች ላይ ጥልቅ ግንዛቤ መያዝ እና በቡድኑ የሚገኙ የኢንስፔክሽን ልዩልዩ መመሪያችን ጊዜ ሰጥቶ
ማንበብ ቢቻል

10
የዳሰሳ ጥናት መጠይቆች
ይህ መጠይቅ በቢቡኝ ወረዳ ትም/ፅ/ቤት በአጠ/ትም/ኢን/ቡድን የአገልግሎት አሰጣጥን በዳሰሳ ጥናት
ለማረጋገጥና የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ መጠይቅ ሲሆን መጠይቁን በትክክልና በጥንቃቄ
እንዲሞሉልን መልካም ትብብርዎን እንጠይቃለን፡፡
ፆታ ወ ሴ የት/ት ደረጃ ……... የስራ ድርሻ ሀ. ሱፐርቫይዘር ለ. ር/መ/ር ሐ. መ/ር
1. በአጠቃላይ ትም/ት ኢንስፔክሽን -ስራ ላይ የወረዳ ትም/ት ኢንስፔክተሮች ት/ቤቱ የኢንስፔክሽን ስራ
ከመስራቱ በፊት ተቋሙ ኢንስፔክት እንደሚደረግ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ይሰራል ወይ?
ሀ. ግንዛቤ ፈጥረው ወደ ተቋሙ ይመጣሉ
ለ. ምንም እይነት እውቅና ሳይፈጥሩ ወደ ተቋሙ ይመጣሉ
2. የአጠቃላይ ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን ወቅት ት/ቤት እንደደረሱ በመጀመሪያ
ማድረግ የሚገባቸውን ነገሮች በመመሪያው መሰረት ይተገብራሉ ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አላምንም
3. የአጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ስራው ከተሰራ በኋላ ኢንስፔክተሮች በት/ቤቱ የተለዩ ችግሮችን ለባለድርሻ
አካላት በማሳወቅ በኩል ያለውን አስተዋጽኦ በምን ይገልፁታል?
ሀ. እ.በጣም ከፍተኛ ለ. በጣም ከፍተኛ ሐ. ከፍተኛ መ. መካከለኛ ሠ. ዝቅተኛ
4. የወረዳ የትም/ት ኢንስፔክተሮች አጠቃላይ በትቤት ደረጃ የኢንስፔክሽን ስራቸውን ጨርሰው ከእከናወኑ
በኋላ የተለዩ ችግሮችን በመውጫ ኮንፈረንሱ ላይ ሲያሳዩ ያላቸውን ተቀባይነት /ስምምነት/ ተግባቦት በምን
ልክ ይገልፁታል።
ሀ. እ.በጣም ከፍተኛ ለ. በጣም ከፍተኛ ሐ. ከፍተኛ መ. መካከለኛ ሠ. ዝቅተኛ
5. የወረዳ ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች አጠቃላይ በት/ቤት ደረጃ የኢንስፔክሽን ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ
የፅሁፍ ግብረ መልሱን ከ 2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለተቋማት ያደርሳሉ ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አላምንም
6. የወረዳ ትምህርት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ከሰጡት አስተያየቶች ውስጥ የተለዩ ችግሮችን ለቀበሌ ምክር
ቤቶች አቅርበው ችግሮችን እየፈቱ ከመሄድ አኳያ ያለዎት እንቅስቃሴ ሲታይ
ሀ. ከፍተኛ ለ. መካከለኛ ሐ. ዝቅተኛ
7. የት/ቤት የኢንስፔክሽን ስራ በተደጋጋሚ ተቋማት መደረጋቸው ጥቅም አለው ብለው ያምናሉ ወይ?
ሀ. አምናለሁ ለ. አላምንም

8. በት/ቤት ደረጃ የሚደረገውን የትም/ት ኢንስፔክሽን ስራ ኢንስፔክተሮች በተቀመጠው መመሪያና የጊዜ


ገደብ መሰረት እያከናወኑት ነው ብለው ያምናሉ? ሀ. አዎ ለ. አላምንም
I
9. በትም/ት ኢንስፔክተሮች የተለዩት ችግሮችን በመያዝ የወረዳ ትምህርት ፅ/ቤቱን የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን
በምን መልኩ ይገልፁታል?
ሀ. በከፍተኛ ለ. በመካከለኛ ሒ ዝቅተኛ መ. በጣም ዝቅተኛ
10. የእጠ/ትም/ት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችን አጠቃላይ ስለ ትም/ት ኢንስፔክሽን መመሪያዎች፤ አሰራሮች
ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በጥቅሉ በምን ልክ ይረዱታል?
ሀ. በጣም ከፍተኛ ለ. ከፍተኛ መ. መካከለኛ ሠ. ዝቅተኛ
11. በኢንስፔክሽን ወቅት ኢንስፔክተሮች መረጃ በሚሰበስቡበት ጊዜ በተጨባጭ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ
ተመስርተው ይሞላሉ ብለው ያምናሉ? ሀ. አዎ ለ. አይደለም
12. በኢንስፔክሽን የተለዩ ችግሮችን ት/ቤቱ በት/ቤቱ አመታዊ እቅድ ላይ ተካተው ታቅደዋል ብለው ያምናሉ?
ሀ. አዎ ለ. አይደለም
መጠይቁን በትክክል ስለሞሉልን እናመሰግናለን!!!

II

You might also like