You are on page 1of 52

የአፈፃፀም ምዘና ዕውቅና እና ሽልማት

አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ

ሚያዚያ 2015 ዓ.ም


ይዘት

መግቢያ

ክፍል አንድ፡-ጠቅላላ ድንጋጌዎች

ክፍል ሁለት፡- የምዘና አፈጻጸም ሂደት

ክፍል ሦስት፡-በምዘናው የሚሳተፉና መረጃ ሰጪ አካላት

ክፍል አራት፡- ዕውቅና አሰጣጥ

ክፍል አምስት፡-የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት


መግቢያ
ለተቋማት ራዕይና ተልዕኮ መሳካት ከሠራተኞች የሚጠበቁ
ውጤቶችን ማሳወቅ፤
ሠራተኞች የተቋማቸውን ራዕይና ስትራቴጂ ከየዕለት ሥራቸው ጋር
የሚያስተሳስሩበትን አግባብ መፍጠር፤
የሠራተኛውን አፈፃፀም በተጨባጭ የአፈፃፀም መረጃ ላይ
በመመስረት ለመለካትና ለማሻሻል የሚያስችል የመንግስት ሠራተኞች
የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሥርዓት መዘርጋት፤
ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ መማማርን እውን ለማድረግ ሠራተኞችን
ለተሻለ አፈፃፀም ለማበረታታት
መግቢያ…….
ተገቢ ድጋፍ ለመስጠት እና በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን

ለመፍታት የሚያስችል የአመለካከትና የአሰራር ብቃት መገንባት


የተቋሙን ውጤታማነት ለማሰደግ የመንግስት አገልግሎት በግልፅነት፣

በተጠያቂነትና በውጤታማነት እንዲሰጥ ማድረግ


የዜጎችን እርካታና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንዲቻል ይህ የአጋርፋ

ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም


ምዘናና ሽልማት ሥርዓት መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአጋርፋ ግብርና

ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ "የአፈጻጸም ምዘና


ዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 01/2015 ዓ.ም"
ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ጠቅላላ…
2.ትርጓሜ
በዚህ አንቀጽ ሥር የተመለከቱት ቃላት ወይም ሐረጎች ሌላ ትርጉም
እስካልተሰጣቸው ድረስ፡-

“አፈጻጸም” ማለት በመጨረሻ በሚጠበቀው ውጤት እና ለውጤቱ መንስኤ

በሚሆኑ ሊለኩ በሚችሉ አመልካቾች የሚገለጽ ክንውን ነው፡፡

“የመመዘኛ መስፈርት” ማለት የሥራ ክፍሎችና ግለሰቦች የስትራቴጅክ እቅድ

አፈጻጸም የሚለኩበት የታወቁና የተለዩ መስፈርቶች ናቸው፡፡

“የአፈጻጸም ምዘና” ማለት በየደረጃው የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎችንና የተገኙ

ውጤቶችን ከመመዘኛ መስፈርቶች ጋር በማነጻጸር የተቋም የስትራቴጅክ


ሥራዎች አፈጻጸም ውጤትን መመዘን ነው፡፡
ጠቅላላ…
 “የአፈጻጸም ውጤት” ማለት ለመመዘኛ መስፈርቶቹ በተሰጠው ነጥብ
መሰረት ተሰልቶ ለሥራ ክፍሎች የስትራቴጅክ እቅድ አፈጻጸም የሚሰጥ
ነጥብ ነው፡፡
 “የአፈጻጸም ደረጃ” ማለት በመመዘኛ መስፈርቶች መሰረት ተመዝኖ
የተቋማት የስትራቴጅክ እቅድ አፈጻጸም ደረጃ የሚገለጽበት ነው፡፡
 “መዛኝ አካል” ማለት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የስትራቴጅክ እቅድ
አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልጽና ተጨባጭ በሆኑ
መረጃዎች እና በመመዘኛ መስፈርቶች መሰረት የለውጥ ሥራዎች
አፈጻጸም ምዘና የሚያካሂድ አካል ነው፡፡
ጠቅላላ…
• “ተመዛኝ አካል” ማለት የሥራ ክፍሎች አመራሮችና ፈፃሚዎች ማለት ነው፡፡

• “አጽዳቂ አካል” ማለት የሚቀርብለትን የሥራ ክፍሎችን የስትራቴጅክ እቅድ


አፈጻጸም ምዘና ውጤት የሚያጸድቅ የኮሌጁ ማኔጅመንት ማለት ነው፡፡

• “ዕውቅና” ማለት የሥራ ክፍሎች/ግለሰቦች የስትራቴጅክ እቅድ አፈጻጸም


ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት የሚሰጥ የዓይነት ወይም የገንዘብ ማበረታቻ
ነው፡፡

• “
ጠቅላላ…

• ዕውቅና ሰጪ አካል” ማለት የሥራ ክፍሎችና ግለሰቦች የእቅድ አፈጻጸም


ምዘና ውጤት መሰረት ዕውቅና ማግኘት ላለበት በዚህ መመሪያ መሰረት
ዕውቅና የሚሠጥ አካል ነው፡፡

• “ቅሬታ” ማለት መዛኙ አካል አጠቃሎ ይፋ ባደረገው የምዘና ውጤት ላይ


የሥራ ክፍሉ/ግለሰቡ ውጤቱ አግባብ አይደለም ብሎ ሲያምን ቅሬታን
ለማየት ለተቋቋመው አካል ይታይልኝ ወይም ይመርመርልኝ ብሎ
የሚያቀርበው ጥያቄ ወይም አቤቱታ ነው፡፡
ጠቅላላ…

3. ዓላማ

በኮሌጁ የሚገኙ የሥራ ክፍሎችን፤ የአመራሮችን እና

የባለሙያዎችን አፈጻጸም በመመዘን ውጤታማ የሆኑትን


ማበረታታት የሚያስችል የዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ስርዓት
በመዘርጋት የስትራቴጅክ ግቦችን አፈጻጸም ለማሻሻል ነው፡፡
ጠቅላላ…

4. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በኮሌጁ በየደረጃው ባሉ የሥራ ሂደቶች ላይ

ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት
የምዘና አፈጻጸም ሂደት
5. የምዘና መርሆዎች
በመረጃ ላይ መመስረት፡- የእቅድ አፈጻጸም ምዘና ውጤቶች በመረጃዎች
ሊደገፉና መረጃዎቹም ተአማኒነት ሊኖራቸው ይገባል፣
ግልፀኝነት፡- የእቅድ አፈጻጸም ውጤቶች ግልጽ ወይም አሻሚ ያልሆኑ
በተጨባጭ የተቋሙን ግቦች ስኬት የሚያሳዩ መሆን አለባቸው፣
አሳታፊነት፡- በተቋሙ የሚከናወነው ምዘና በተቋሙ መሳተፍ የሚገባቸውን
አካላት በሙሉ ያሳተፈ መሆን አለበት፣
የምዘና መርሆዎች…….

4.ሚዛናዊነት፡- በተቋሙ የሚከናወነው ምዘና የተቋሙን የእቅድ አፈጻጸም


መሰረት በማድረግ ያለአድልዎ ሊፈፀም ይገባል፣

5.ተጠያቂነት፡- የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ አካላት የሚበረታቱበት፤ ዝቅተኛ


ውጤት ያስመዘገቡት የሚደገፉበት አግባብ ሊኖር ይገባል፣

6.ለውጤት ዕውቅና መስጠት፡- ለውጤት መስራት የተቋም ባህል ሊሆን


ይገባል፡፡
6. ተመዛኝ አካላት

በኮሌጁ እየተተገበረ የሚገኘው የስትራቴጅክ ዕቅድ አፈፃፀም

ተቋማዊ መሰረት እንዲኖረው የሚመዘኑ አካላት፡-


 ዳይሬክቶሬቶች
 ትምህርት ክፍሎች
 ቡድን መሪዎች
 አስተባባሪዎች
 ግለሰብ ፈፃሚዎች ናቸው፡፡
7. ምዘናው የሚያተኩርባቸው ጉዳዮችና መመዘኛ መስፈርቶች

7.1 ምዘናው የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች

ስትራቴጂ ተኮር አመራርና ሰራተኛ እየተፈጠረ ስለመሆኑ፣

በተቋሙ የስትራቴጅክ ግቦችን ለማሳካት የተከናወኑ ተግባራት፣


የተገኙ ውጤቶችና የግብ ስኬቶች፣

የለውጥ ሥራዎች ትግበራ ለአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና


ውጤታማነት ያደረገው አስተዋፆኦ፣
ምዘናው የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች……….

 በለውጥ ሥራዎች ትግበራ በሰው ኃይል ላይ የመጣ ለውጥ


/በአመለካከት፣ በዕውቀት፣ በክህሎትና በግብአት አጠቃቃም፣

 የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን በማበረታታት እና ድጋፍ


የሚያስፈልጋቸውን ለይቶ ድጋፍ ማድረግ በማስፈለጉ፣
ምዘናው የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች……….

ከተለያዩ ተቋማት መልካም ተሞክሮዎችን በተቋሙ ለመተግበር


እንዲሁም ከአንዱ የሥራ ሂደት ወደ ሌላ የሥራ ሂደት ልምድ
ለማሸጋገር፣ በተቋሙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመርና
ለማስፋፋት በማስፈለጉ፣
በአጠቃላይ በተቋሙ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በማክሰም
የልማታዊ አስተሳሰብን ለማረጋገጥ፣ ይህ የአፈፃፀም ምዘና
ዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ መመሪያ ወጥቷል፡፡
7.2 የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶችና የክብደት ነጥብ
ምዘናው ከዚህ በታች በተገለጹ ዋና ዋና መመዘኛ መስፈርቶች
መሰረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡ የሥራ ክፍል መመዘኛ መስፈርቶችና
የክብደት ነጥብ፡-
ሀ. የዕቅድ አፈፃፀም ውጤት..……..…...30 %
ለ. ተቋማዊ ባህል ግንባታ…..…..…....…20 %
ሐ. የአገልግሎት አሰጣጥ ………....……20 %

መ. የመረጃ አያያዝና ጥራት ……......…20 %


ሰ. የተገልጋይ እርካታ….……………....10 %
የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶችና የክብደት ነጥብ…….

የግለሰብ ፈፃሚ መመዘኛ መስፈርቶችና የክብደት ነጥብ


ሀ. የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ውጤት……...….30%
ለ. በቡድን የመሥራት ችሎታ……….…...…20%
ሐ. አገልግሎት አሰጣጥ…………..…………20%
መ. ተጨማሪ በኮሌጁ የሚሰጡ ተልዕኮዎች የመቀበልና የመፈጸም
ብቃት.…15%
ሰ.የተቋሙን ስትራቴጂ ተገንዝቦ የመፈፀመም ብቃት..15%
7.3 ዝርዝር የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶች
የስራ ሂደትና የግለሰብ ፈፃሚዎችን አፈጻጸም ለመመዘን
በተቀመጡ ዋና ዋና የስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸም መመዘኛ
መስፈርቶች ስር ዝርዝር መመዘኛ መስፈርቶችን ማስቀመጥ
ያስፈልጋል፡፡
8. ለምዘናው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመስጠት ድርሻ ያላቸው አካላትና
የሚገኘው መረጃ ለምዘናው ውጤት የሚኖረው ድርሻ

8.1.የሥራ ሂደት ምዘና መረጃ ምንጮች የመረጃ ምንጮቹ በውጤት


አሰጣጡ ላይ የሚኖራቸው ድርሻ ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
 የሥራ ሂደቱ አፈፃፀም…………….50 %

 የተገልጋይ እርካታ……………..…..30%

 የሥራ ሂደቱ ሰራተኞች………….…20%


8.2 የስራ ሂደትና የግለሰብ ፈጻሚ ምዘና የመረጃ ምንጮች የስራ
ሂደትና የግለሰብ ምዘና ሲደረግ ከላይ የተመለከቱ ዋና ዋና
መመዘኛዎችን ያካተተ ሲሆን ይህን መሰረት በማድረግ በተቀመጡ
የመመዘኛ ቅፆች መረጃው የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡
8.3 የተገልጋይ እና ፈፃሚዎች መረጃ የሚሰጡባቸው መመዘኛ መስፈርቶችና
የክብደት ነጥቦች፤
ከተገልጋይ መረጃ አሰጣጥ አንጻር

ሀ.በዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ላይ ማሳተፍ………6

ለ.ስለሚሰጡ አገልግሎቶች ግልፅና ተገቢውን መረጃ ለመሰጠቱ…4

ሐ.የአገልጋይነት መንፈስ በተላበሰ መልኩ ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ


ስለመሆኑ…......5

መ.አገልግሎት አሰጣጡ ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ ስለመሆኑ…..…6

ሰ.የሚሰጡ አገልግሎቶች በፍትሃዊነት እየተሰጡ ስለመሆኑ…...…3

ረ.የሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚስተናገዱበት እና ምላሽ የሚሰጥበት አሰራር


ስለመኖሩ….….6
ከፈፃሚዎች መረጃ አሰጣጥ አንጻር

ሀ. በሥራ ሂደቱ በዕቅድ አፈፃፀምና በለውጥ ስራዎች ውጤት


ስለመምጣቱ…………………3
ለ. የተቋሙ ኃላፊዎች ሰራተኛውን በማሳተፍ ሥራዎችን እያከናወኑ
ስለመሆኑ….........…...3
ሐ. የሠራተኛው የአቅምና የአመለካከት ክፍተት የተለየ የማብቃት ስራ
እየተሰራ ስለመሆኑ.2
መ. የተቋሙ ፈጻሚዎች የዕቅድ አፈፃፀም ምዘና በመረጃ የተደገፈና
ፍትሀዊ ስለመሆኑ…….2
ከፈፃሚዎች መረጃ አሰጣጥ አንጻር
ሠ. አመራሩም ሆነ ሰራተኛው የለውጥ ስራዎችን የተቋሙ
ዕቅድ ማሳኪያ አድርጎ በእምነት እየፈጸመ ስለመሆኑ………2
ረ.አገልግሎት በስታንዳርዱ መሰረት እየተሰጠ ስለመሆኑ……...3

ሰ. አመራሩ በተግባር አፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ቅሬታዎችን


ፈጥኖ የመፍታት ልምድ ያደረገ ስለመሆኑ.………2
ሸ. የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን
ለመፍታት የሚሰራው ስራ ለውጥ ስለማምጣቱ…...3
የመረጃ ሰጪ አካላት ዝርዝር መመዘኛ መስፈርቶች

የሥራ ክፍሉን አፈጻጸም ለመመዘን በተቀመጡ ዋና ዋና

የሥራ ሂደቱ ተገልጋይና ፈፃሚዎች መረጃ የሚሰጡባቸው


መመዘኛ መስፈርቶች ስር ዝርዝር መመዘኛ መስፈርቶች
ይኖራሉ፡፡
9. የምዘና መረጃ አሰባሰብና መረጃ ሰብሳቢ አካል
ለምዘናው አስፈላጊ የሆነው መረጃ አሰባሰብ በተቋሙ በተደራጀው
የሱፐርቪዥን ቡድን የሚከናወን ሆኖ አፈፃፀሙ እንደሚከተለው
ይሆናል፡፡
 የተቋሙ የአፈጻጸም ግምገማ የሚደረገው የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶችና የክብደት
ነጥብ መሰረት በሚዘጋጀው ዝርዝር ቼክ-ሊስት ይሆናል፣
 ሱፕርቪዥን ቡድኑ ለተመዛኝ አካላት ምዘና ከሚደረግበት ጊዜ አንድ ሳምንት አስቀድሞ
ቼክ-ሊስት እንዲደርሳቸው ያደርጋል፣ ሱፕርቪዥን ቡድኑ ከታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ 30
እንዲሁም ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 30 ድረስ በሥራ ሂደቶቹ በመገኘት በቼ-ክሊስቱ መሰረት
ይገመግማል፣ ዝርዝር የእቅድ አፈፃፀምና የለውጥ ሥራዎች አፈፃፀም መረጃዎችን
ከተቋሙ ማኔጅመንት፣ ከተገልጋዮችና ፈፃሚዎች ይሰበስባል፣
የምዘና መረጃ አሰባሰብና መረጃ ሰብሳቢ አካል………
 ከየሥራ ሂደቱ የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማደረጃትና በመተንተን
የአፈጻጸም ሪፖርት ከጥር 1 እስከ ጥረ 10 እንዲሁም ከሃምሌ 1 እስከ
ሃምሌ 10 ባለው ጊዜ ይዘጋጃል፣
 በግምገማ ወቅት የታዩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን ይለያል፣ ለኮሌጁ
ማኔጅምንት አቅርቦ ካስጸደቀ በኃላ የጽሁፍ ግብረ-መልስ ለየሥራ
ሂደቶቹ ይሰጣል፣
10. መዛኝ አካል ስለማቋቋም

10.1 የሥራ ሂደትና የግለሰብ ፈፃሚ አካላት የስትራቴጅክ እቅድና ለውጥ


ሥራዎች አፈጻጸም ምዘና የሚያካሂድ ኮሚቴ ይደራጃል፡፡
10.2 የተቋም ምዘና ለማድረግ የሚቋቋም ኮሚቴ አምስት አባላት
የሚኖሩት ሲሆን እነዚህም፡-

ሀ. የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት……ሰብሳቢ

ለ. የለውጥ ሥራዎች ባለሙያ…………..…………… አባል

ሐ. አንድ የትምህርት ክፍል ኃላፊ…….……………….አባል

መ. አንድ ከቴክኖሎጂ ብዜትና ሽግግር ም/ዲን ዘርፍ…..አባል

ሐ. የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት…..ፀሐፊ


10.3 የተቋም ምዘና የሚያደርገው ኮሚቴ በእቅድ ዝግጅት ክትትልና
ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና በለውጥ ሥራዎች የተሰበሰቡ
መረጃዎችን በግብዓትነት የሚጠቀም ይሆናል፡፡
በኮሚቴዎቹ የተሰራው የስራ ሂደትና የግለሰብ ፈፃሚ የምዘና

ውጤት በማኔጅመንቱ ታይቶ የሚጸድቅ ይሆናል፡፡


11. የምዘና ውጤት ማፅደቅና ይፋ ስለማድረግ

አጽዳቂ አካል የቀረበለትን የተጠቃለለ የምዘና ውጤት በቀረበለት

በ5 የስራ ቀናት ውስጥ መርምሮ ያጸድቃል፣


የጸደቀው ውጤት የተለያዩ የማሳወቂያ አማራጮችን በመጠቀም

ወዲያውኑ ይፋ ይደረጋል፣
12. የምዘና ነጥብና ደረጃ
ደረጃ አራት - በጣም ከፍተኛ የአፈጻጸም ደረጃ ከ95-100% የሚደርስ

የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን ያመለክታል፡፡


ደረጃ ሦስት - ከፍተኛ የአፈጻጸም ደረጃ ከ95% በታች እስከ 80%

ያለውን የተጠቃለለ ምዘና ውጤት ያመለክታል፡፡


ደረጃ ሁለት - አጥጋቢ የአፈጻጸም ደረጃ ከ80% በታች እስከ 60%

ያለውን የተጠቃለለ ምዘና ውጤት ያመለክታል፡፡


ደረጃ አንድ - ዝቅተኛ የአፈጻጸም ደረጃ ከ60% በታች ያለውን

የተጠቃለለ ምዘና ውጤት ያመለክታል፡፡


ክፍል ሦስት
በምዘናው የሚሳተፉ እና መረጃ ሰጪ አካላት
14. በምዘናው የሚሳተፉና መረጃ ሰጪ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

14.1 የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተግባርና ኃላፊነት

ሀ. የሥራ ክፍሉን የምዘና ሂደት ያስተባብራል መረጃዎችን ያቀርባል፣

ለ. ለክፍሉ ፈፃሚዎች ስለምዘናው ግንዛቤ ይሰጣል እንዲመዘኑ ያዘጋጃል፣


14.2 የመዛኝ አካል ተግባርና ኃላፊነት
የመዛኝ አካሉ ተጠሪነት ለኮሌጁ ዲን ሆኖ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት
ይኖሩታል፡-
ሀ. ለምዘናው ስራ በሱፕርቪዥን ግምገማ የተገኙ መረጃዎችን በግብዓትነት
ይጠቀማል፣
ለ. በግምገማ የተገኙ የእቅድና ለውጥ አፈጻጸም መረጃዎችን
ይተነትናል፣ይተረጉማል፣
ሐ. በተገኙ መረጃዎች መሰረት ምዘና ያካሂዳል፣ የአፈጻጸም ደረጃ ያወጣል፣
መ. የተጠቃለለውን የምዘና ውጤት ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያጸድቃል፣
ሠ. የጸደቀውን ውጤት ይፋ በማድረግ ለሽልማትና ዕውቅና ኮሚቴ ይልካል፡፡
14.3 በየደረጃው ያሉ ተመዛኝ የሥራ ሂደቶች ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. ከሱፐርቪዥን ቡድን በሚደርሰው ቼክ-ሊስት መሰረት ለእቅድና ለውጥ
ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ የሰነድ ማስረጃዎችን ማደራጀትና ዝግጁ
ማድረግ፣
ለ. በእቅድ ግምገማና ምዘና የሚሳተፉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች
በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት ተሟልተው እንዲጠብቁ ማድረግ፣
ሐ. በለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም የመስሪያ ቤቱ ባለድርሻ አካላት፣ ተገልጋይ እና
ሰራተኛ እንዲገኙ ማድረግ፣
መ. በለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ አስፈላጊውን መረጃ መስጠትና
በግምገማው ሂደት በንቃት መሳተፍ፣
ሠ. በግምገማው ማጠቃለያ በሚሠጠው ግብረ-መልስ ላይ መወያየትና የጋራ
መግባባት ላይ መድረስ፣
ክፍል አራት
ዕዉቅና አሰጣጥ
15. ዕውቅና ሠጪ አካል ስለመሰየም

የእቅድ እና ለውጥ ሥራዎች አፈጻጸም ዕውቅና ሠጪ አካል


ይቋቋማል፣
ዕውቅና ሰጪ አካል ምዘናውን ከሚያከናውነው አካል የተለየ ይሆናል፣

የሥራ ክፍሎችን የአፈጻጸም ምዘና ውጤት መሰረት በማድረግ


የአይነት ወይም የገንዘብ ዕውቅና ይሠጣል፣
በዕውቅና ሰጭነት የሚደራጀው አካል የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-
የትምህርትና ሥልጠና ም/ዲን……ሰብሳቢ
የእቅድ ዝግ/ክት/ግ/ዳይሬክቶሬት …አባል
የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት.……አባል
የኮምኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት…..ጸሀፊ
የሴቶችና ህጻናትና ወጣቶች ጉዳዮች
ዳይሬክቶሬት.....አባል
16. የዕውቅና ሰጪ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 18 ከተዘረዘሩት የሽልማት ዓይነቶች ውስጥ


በመለየት ለየደረጃዎቹ
 የሚሰጡ የሽልማት ዓይነቶችን ይወስናል፣

 የሀብት ምንጭ ይወስናል፣የዕውቅና አሰጣጥ መርሀ-ግብር ያዘጋጃል፣

 አሸናፊዎች ለዕውቅናው ብቁ ያደረጓቸውን የላቁ ክንውኖች እና የተገኙ ምርጥ

ተሞክሮዎች አጭር ሪፖርት በዕውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ ያቀርባል፡፡


 ዕውቅና ይሰጣል፣

 የማጠቃለያ ሪፖርት ያዘጋጃል፣


17. የዕውቅና ደረጃና ዓይነት

17.1 የሥራ ክፍል ዕውቅና


ለውድድር የሚቀርቡ እጩ የሥራ ክፍሎች ለዕውቅና አሰጣጡ ለመወዳደር
ያስመዘገቡት የምዘና ነጥብ ከፍተኛና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 17.1. ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ
በታች በተቀመጠው ደረጃ መሠረት ዕውቅና ይሰጣቸዋል፡፡
 የመጀመሪያ ደረጃ ተሸላሚ

 ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ

 ሦስተኛ ደረጃ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡


በአንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 15.3 መሰረት ዕውቅና የሚሰጣቸው

የመንግስት መስሪያ ቤቶች የምዘና ውጤታቸው 95 እና በላይ ሆኖ


የምዘና ውጤታቸው እኩል ከሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተጨማሪ
መስፈርቶች በመጠቀም ደረጃቸው ይለያል፣

በመዛኙ አካል በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ተቀምሮ ሊስፋፋ የሚችል


የተሻለ ተሞክሮ መኖሩ፣

የዕቅድ አፈጻጸም ውጤታቸውና የለውጥ ስራዎች አፈጻጸም ደረጃ የተሻለና


ጠንካራ ትስስር ያለው መሆኑ፣

መዛኝ ቡድኑ ምዘናውን ባካሄደበት ወቅት ካነጋገራቸው ተገልጋዩች በአንጻራዊነት


ከፍተኛ የተገልጋይ እርካታ የተመዘገበበት መሆኑ፣
17.2 የግለሰብ ፈፃሚዎች ዕውቅና

ለውድድር የሚቀርቡ እጩ ግለሰብ ፈፃሚዎች ለእውቅና አሰጣጡ


ለመወዳደር ያስመዘገቡት የምዘና ነጥብ ከፍተኛና ከዚያ በላይ መሆን
አለበት፣
ከፍተኛ ነጥብ አምጥተው ለውድድር ከቀረቡት ፈጻሚዎች መካከል
በመስፈርቱ መሰረት በጣም ከፍተኛ ያገኙ ፈጻሚዎች ይሸለማሉ፣
ከፍተኛ ነጥብ አምጥተው ለውድድር የቀረቡ ፈጻሚዎች በሁለት ምድብ
(በአካዳሚክና በድጋፍ ሰጪ) ተለይተው እንዲወዳደሩ ይደረጋል፣
 ግለሰብ ፈፃሚዎች ለተቋሙ ስትራቴጂያዊ ግቦች ስኬት
የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፣
 ሆኖም ግን ሴትና ሴት ተወዳድረው እኩል ካመጡና አካል ጉዳተኛ
ካለች ቅድሚያ ይሰጣል፣ በሴቶች የተገለጸውም ለወንዶች የሚሰራ
ይሆናል፡፡
 በዚህ መሰረት ከ1-3 ደረጃ ያገኙ ሠራተኞች ከዚህ በታች
በተቀመጠው ደረጃ መሰረት ዕውቅና ይሰጣቸዋል፣
በዚህ መሠረት፡-
ሀ. የመጀመሪያ ደረጃ ተሸላሚ
ለ. ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ
ሐ. ሦስተኛ ደረጃ ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
ሁለትና ከዚያ በላይ ግለሰብ ፈፃሚዎች የምዘና ውጤታቸው 95 እና

በላይ ሆኖ እኩል ነጥብ ያስመዘገቡ ከሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን


ተጨማሪ መስፈርቶች በመጠቀም ደረጃቸው ይለያል፣
 በመዛኙ አካል በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ተቀምሮ ሊስፋፋ

የሚችል የተሻለ ተሞክሮ ያለው ከሆነ፣

 በተቋሙ ተጨማሪ ተልዕኮዎችን የፈጸመና በከፍተኛ አመራሩ ዘንድ

የተመሰከረለት መሆኑ፣

 ለተቋሙ ስትራቴጂያዊ ግቦች ስኬት ያበረከተው አስተዋጽኦ ደረጃ

ከፍተኛ መሆኑ፣
18. የሽልማት ዓይነቶች

የሚሰጠው ሽልማት “የመልካም ስራ አፈፃፀም ሽልማት” ተብሎ የሚጠራ

ሲሆን ሽልማቱ በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ የሚዘጋጅ ሆኖ


የሚከተሉትን አማራጮች ያካትታል፡፡
 ዋንጫ
 ሜዳሊያ
 በጥሬ ገንዘብ
 የትምህርትና የስልጠና ዕድል
 ታሪካዊ ቦታዎችን ማስጎብኘት
 ሰርተፍኬት
 ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ሌሎች የዓይነት ሽልማቶች
ናቸው፡፡
19. ዕውቅና የሚሰጥበት ጊዜ
ዕውቅና በአመት አንድ ጊዜ ይደረጋል፣ ዝርዝር አፈጻጸሙ ዕውቅና

ሰጪው አካል በሚያዘጋጀው መርሀ-ግብር ይወሰናል፣


20. የዕውቅና አሠጣጥ ሥርዓት

ዕውቅና በአመት አንድ ጊዜ ይደረጋል፣ ዝርዝር አፈጻጸሙ ዕውቅና ሰጪው


አካል በሚያዘጋጀው መርሀ-ግብር ይወሰናል፣
የዕውቅና አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወንበት በዓል ይዘጋጃል፤
በበዓሉ ላይ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች እንዲገኙ ይደረጋል፤የዕለቱን የክብር
እንግዳ የእውቅና አሰጣጥ አካሉ እንዲጋብዝ ይደረጋል፣
ሥነ ሥርዓቱ የሚዲያ ሽፋን ይሰጠዋል፣
አጠቃላይ ሥነ ሥርዓቱ በኮሌጁ ዲን አስፈጻሚነት ይከናወናል፣
ክፍል አምስት
የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት
21. የማመልከቻው ይዘትና አቀራረብ
ቅሬታ የተሰማውና እንዲታይለት የሚፈልግ ማንኛውም የስራ ሂደት
ወይም ግለሰብ ፈጻሚ የቅሬታ ማመልከቻ ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ
አካል ማቅረብ ይችላል፣
የሚቀርበው ማመልከቻ ቀጥሎ የተመለከቱትን ነጥቦች ማካተት
ይኖርበታል፡፡
 የሥራ ክፍል ወይም ግለሰብ ስም፣
 የቅሬታው ዓይነት ወይም ምክንያት፣
 ደጋፊ የሠነድ ማስረጃዎች፣
 ቅሬታው የቀረበበት ቀን፣ ወር እና ዓ.ም
 የቅሬታ አቅራቢው ስምና ፊርማ
22. መመሪያውን ስለማሻሻል

የኮሌጁ ማኔጅመንት መመሪያውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

23. መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ከየካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

You might also like