You are on page 1of 23

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ፋይናንስ ቢሮ

በ2015 በጀት ዓመት የበጀት

ዝግጅት ሂደት ላይ መከተል የሚገባን


የትኩረት ነጥቦች
ግንዛቤ ማስጨበጫ
ሰኔ 2014 ዓ/ም
ሳውላ
1 መግቢያ

በክልላችን የህዝብ ቁጥር መጨመር ፣የከተሞች እድገት፣ እና ከመዋቅር መስፋት ጋር ተያይዞ
የህብረተሰባችን የመልማት ጥያቄ እና ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ
በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለው አለመጣጣም ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ ይገኛል፡፡
የክልሉ መንግስትም ይህን ፍላጎትና አቅርቦት ለማጣጣም በየበጀት ዓመቱ ከተለያዩ የበጀት
ምንጮች የሚገኙ ሀብቶችን በማስተባበርና በዕቅድ በመምራት ውጤት ለማምጣት የላቀ
ሚናውን በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡

”3

በመሆኑም የፋይናንስ ሴክተር የ2015 በጀት ዓመት የሴክተሩን መሪ ዕቅድ መነሻ ያደረገ ዓመታዊ
እቅድ እና መሠረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ እንዲሁም ሚዛናዊ የውጤት ተኮር ሥርዓትን
መሠረት በማድረግ ተደራሽ አገልግሎት እና ቀልጣፋ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት
ከተቋሙ መሠረታዊ ባሕርይ አንፃር ተገቢ ግምት ማግኘት ያለበትን የቁጥጥር ሚና በአግባቡ በመለ የት የክልላችን
ማህብረሰብ የልማት ፍላጎት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ አግባብ ውስን ሀብታችንን ለታለመለት ዓላማ በማዋል
ሁለንተናዊ ልማትን ማረጋገጥ ዋነኛ ዓላማው ነው፡፡


4

በመሆኑም የሴክተሩን አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንዲቻል የሰው ኃይሉን የአመለካከትና የክህሎት ችግር

መፍታት ላይ በማተኮር ከፍተኛ እንቅስቃሴ መደረግ እንዳለበት የታመነ ጉዳይ ሲሆን ባለፉት ጊዜያት የተመዘገቡትን

ስኬቶች በማስቀጠል እና ካጋጠሙን ተግዳሮቶች በመማር በ2015 በጀት ዓመት ቀጣይ የፊሲካል እና የበጀት አስተዳደር

ስራዎች ወቅታዊ እና የጊዜ ሰሌዳዎችን ተከትለው እንዲተገበሩ ወሳኝ የሆኑ የትኩረት ነጥቦችን በመለየት ይህን የገለጻ

ጽሁፍ አዘጋጅቷል፡፡

”5
በቅድሚያ…
በጀት ምንድነው?

6


በጀት ማለት መንግሥት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ስትራቴጂዎቹንና ፖሊሲዎቹን
ለማስፈጸም ከሚጠቀምባቸው
የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ መሣሪያዎች አንዱ ነው፡፡
● በሌላ አገላለጽ የመንግሥት ገቢና ወጪ የሚገመትበትና በወጪው
የሚከናወኑ ግቦችና ተግባሮች የሚመላከቱበት
● ዓመታዊ የገንዘብ ግኝትና አጠቃቀም ዕቅድ ማለት ነው፡፡

”7
የበጀት
አስፈላጊነት
የበጀት አስፈላጊነት በቀጥታ ከእቅድ ዝግጅት ጋር ይገናኛል፡፡ ከጊዜ ሽፋን አንጻር የእቅድ አይነቶች ሶስት
ሲሆኑ የረዥም ፣የመካከለኛ እና የአጭር ዘመን ተብለው ይመደባሉ፡፡
አመታዊ እቅድ (የአጭር ዘመን የልማት እቅድ) ከመካከለኛ ዘመን እቅድ የሚመነዘሩ ዓላማዎች“ ግቦችና
የማስፈፀሚያ ስልቶች ላይ ተመስርቶ የሚዘጋጅ ሲሆን ተጨባጭ የሆነ በጀት የፋይናንስ ምንጭ
ይኖሩታል፡፡፡
የፍላጎትና የአቅም አለመጣጣም በመኖሩ ያለውን ውስን ሀብት ይበልጥ ተፈላጊ ለሆኑ ሥራዎች መመደብ ወይም በጀት
ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
ስለሆነም ያለውን ሀብት በተጣጣመ መልኩ ሥራ ላይ በማዋል የታለመለትን ግብ ለመምታት በጀት አስፈላጊ ይሆናል
ማለት ነው፡፡
8
የ2015 ዓ.ም የፊሲካል ማዕቀፍና
2 የበጀት ዝግጅት ስራዎች የትኩረት
አቅጣጫዎች፣
ሶስት የበጀት ዝግጅት ስራ ዋና ዋና ነጥቦች
(3 Core Issues on Budjet Allocation process)

● ሀ/ የፋይናንስ የጊዜ ሰሌዳ ● ሐ/ የሂሳብ አወቃቀር፣

● ለ / የበጀት ኡደትና የበጀት ስራ መርሆዎች


ፍትሀዊ፣ግልጽ፣ ውጤታማ እና ተጠያቂነት ያለበት የመንግስት በጀት ኡደት፡፡

10
ሀ/ የፋይናንስ የጊዜ ሰሌዳ
yÍYÂNS yg!z@ sl@Ä y:QD ybjT ;#dTN õT¬LÝÝ :QD bjT XNÄ!ÃÃz# |R›T ÆlW
mNgD እንዲዘጋጁ፣XNÄ![Dq$Â ተፈቅደው ስራ ላይ እንዲውሉ ወይም XNÄ!tgb„ bGLA
Ytrg#¥LÝÝ
የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት፣ የሚከናወኑበትን ጊዜ እና ማን እንደሚያከናውናቸው የሚያከናውኑትን
የመንግስት አካላት ለይቶ የሚያመለክት ነው፡፡
xSgÄJ yçn bSÍT y¸¬wQ yÍYÂNS yg!z@ sl@Ä lqLÈÍ ybjT xs‰R bh#l#M ymNGST
XRkñC mñR xSflg! nWÝÝ
bbjT xStÄdR mm¶Ã bGL{ XNdtqm-W yqÈY ›mT ybjT ZGJT S‰
yÍYÂNS yg!z@ sl@Ä የፊሲካል (የመንግስት ገቢ እና ወጪ) ማዕቀፍ ዝግጅት ስራ የሚጀምረው
ታህሳስ ወር ላይ ነው፡፡
11
የበጀት


አዘገጃጀት
ሥርዓት
አስፈጻሚው
አካል የበጀት
ዝግጅት የበጀት ማፅደቅ
እና ወጪ
ለ / የበጀት ኡደት የበጀት እንዲደረግ
መፍቀድ
ቁጥጥር በህግ አውጪው
ሥርዓት ማፀደቅ
ኦዲትና
ግምገማ

የበጀት
አፈፃፀም
ስርዓት፣
በአስፈጻሚው


አካል ስራ ላይ
ማዋል

12
የበጀት ዝግጅት መርሆዎች
● በበጀት ዝግጅት መርሆዎች 4 ዋና ዋና ነጥቦችን ማጤን ተገቢ
ነው፡፡
 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ያቀረቡትን የበጀት ጥያቄ
መመርመር፣
 ለመደበኛ በጀት ዝግጅት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣
 የሰው ሀይል በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር
 የካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት ዝግጅት መርሆዎች

13

1 . የመንግስት መ/ቤቶች ያቀረቡትን የበጀት ጥያቄ መመርመር
ይህ ተግባር የሚፈጸመው ፍትሀዊ እና ግልጽየሀብት ክፍፍል ለማድረግ በምናደርገው የበጀት ሰሚ
ወቅት ነው፡፡ የቀረበው እቅድ የመ/መ/ቤቱን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት በትክክል በተሰጠው ስልጣንና
ሀላፊነት መሰረት ስለመሆኑ የምናጣራበት ሂደት ነው፡፡ በመሆኑም፣
● የመ/መ/ቤቱ የማስፈጸምና የመፈጸም ብቃት ካቀረበው ፊዚካልና ፋይናንሻል እቅድ አንጻር
ያለውን ደረጃ፣
● የቀረበው የበጀት ጥያቄ እና ፊዚካል ዕቅድ የተጣጣመና ያልተጋነነ ስለመሆኑ፣
● መ/ቤቱ በ2014 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶችን ፊዚካልና
ፋይናንሻል አፈጻጸም በዝርዝር መገምገም፣
● የበጀት ድልድሉ ያለፈውን ዓመት የበጀት አፈፃፀምና የቀጣዩን በጀት ዓመት የመ/ቤቱን ዕቅድ ታሳቢ


በማድረግ የተከናወነ መሆኑን መመርመርና ማጣራት ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡

14

2 . ለመደበኛ በጀት ዝግጅት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፡፡
መደበኛ በጀት የምንለው በጠባያቸው በቀጣይነት የሚተገበሩ የደመወዝና ስራ ማስኬጃ ወጪዎችን
ነው፡፡
በመሆኑም ከስራ ማስኬጃ በጀት አንጻር ታሳቢ ማድረግ የሚገባን፣
በዋና ዋና ሂሳብ መደቦች ስር ለሚደራጁ የወጪ መደቦች የተመደበውን በጀት በሚገባ መፈተሽ ላይ
ነው፡፡
በመሆኑም በ6200 ለዕቃና አገልግሎቶች፣በ6300 ለቋሚ ንብረቶች ግዢ እና በ6400 ለሌሎች ክፍያዎች
መ/ቤቱ የመደበውን በጀት መገምገም፡፡
 ለዚህም የመጀመሪያ ተግባራችን በቅድሚያ የግዴታ ወጪዎችን መለየት፡፡ ለመብራት፣ ለስልክ፣ ለውሀ እና
ፖስታ አገልግሎት እንደመ/ቤቱ ባህርይ የአገልግሎት ክፍያዎችም ካሉ በበጀት ድጋፍ ወቅት ታሳቢ ማድረግ፣

”15



የቋሚ ዕቃ ግዢ ለቅንጦት ሳይሆን በዓመታዊ እቅድ መሰረት የወቅቱን የገበያ ዋጋ ታሳቢ የሚያደርግና
በበጀት ጥያቄ ላልተሟሉ ወይም ለተጓደሉ ዕቃዎች ስለመሆኑ፣ ያልተጋነነ፣ አንገብጋቢ ወይም እጅግ
አስፈላጊነቱን ከወጪ ቆጣቢነት አንጻር የቀረበ መሆኑን ማጣራት፣
ለእቃና አገልግሎት በጀት ድጋፍ የባለፈውን አፈጻጸም፣የወቅቱን የገበያ ዋጋ እና የአስፈላጊነት ደረጃ
ካለው ውስን ሀብት አንጻር ወጪ ቆጣቢ በሆነ ሁኔታ ስለመቅረቡ መገምገም፣
 በ6400 ቤት የሂሳብ መደብ ለሌሎች ክፍያዎች የሚመደብ በጀት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡
አስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች (ለምሳሌ፡በማዘጋጃ ቤት ለልማት ተነሺዎች ለተጠና ካሳ ክፍያ) በፋይናንስ
መ/ቤትና በሚመለከተው የበላይ ሀላፊ ታምኖበት ምክር ቤት ካላጸደቀው በስተቀር በዚህ ርዕስ በጀት
መያዝ አይቻልም፡፡

”16

3. የሰው ሀይል በጀት አዘገጃጀትና አስተዳደር
የሰው ሀይል በጀት አዘገጃጀት መርህ የሚከተሉ ጉዳዮችን ታሳቢ ማድረግ ይገባዋል፡፡
 በ6100 ሰብአዊ ለሆኑ አገልግሎቶች ለደመወዝ፣ጡረታና ጥቅማ ጥቅም የሚመደብ በጀት የግዴታ
ወጪ ሲሆን በጀቱ ሲደገፍ፣
 ፓብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መ/ቤት ያጸደቀው የመ/ቤቱ የሰው ሀይል መዋቅር፣ከመዋቅሩ
የተሟላ የሰው ሀይል በስም ዝርዝርና በመቶኛ፣ያልተሟላ በመደብ ዝርዝርና በመቶኛ ቀርቦ መገምገም ይገባዋል፡፡
 ለተሟላ የሰው ሀይል የተደራጀ የሚያዚያና የሰኔ ወር ፔይሮል የባንክ ማረጋገጫ ያለው ፣ በዚህም መሰረት በዝርዝር
የተዘጋጀ ቅጽ መበማ/7 መኖሩን ማረጋገጥ፣
 የሚቀርበውን መረጃ የመንግስት መ/ቤቱ የሰው ሀብት አስተዳደር፣የሂሳብና ክፍያ፣እቅድና በጀት የስራ ክፍሎች
አረጋግጠው በዋናው ሀላፊ ተፈርሞ መቅረብ አለበት፡፡
 ለአንድ የስራ መደብ አንድ ሰራተኛ ብቻ የተመደበ መሆኑን መፈተሸ፣


 ለነባር ሰራተኞች የ12 ወር ደመወዝ በትክክል መያዙን ማጣራት፣
 ከበጀት ድልድል በኋላ አስገዳጅና ላልተሟላ የሥራ መደብ በፋይናንስ ቋት በጋራ በጀት በመያዝ ለበላይ አካል ቀርቦ
17
ሲታመንበትና ሲፈቀድ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
4. የካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት ዝግጅት መርሆዎች

● የበጀት ድልድሉ ያለፈውን ዓመት የፕሮጀክት በጀት አፈፃፀምና የቀጣዩን በጀት ዓመት የመ/ቤቱ ዕቅድ ታሳቢ በማድረግ የሚከናወን ሲሆን
የካፒታል ወጪ ፍላጎትን በተመለከተ ለነባር ፕሮጀክቶች ቅድሚያ በመስጠት በመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ ትኩረት ለተሰጣቸው
ፕሮጀከቶች የበጀት ድልድሉ በፍትሃዊነት ለመፈጸም ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡
● የግንባታ ካፒታል ፕሮጀክቶች የበጀት ድጋፍ ሂደት የካፒታል ፕሮጀክቶችን ፕሮፋይል መሰረት ያደርጋል፡፡ይህ ማለት የፕሮጀክቶች ውል
ዋጋ/ጠቅላላ ዋጋ፣እስካሁን የተከፈለ፣የቀረ፣ተጨማሪ ካለ…/ሊደራጅ ይገባል፡፡
● ነባር ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ አቅም በፈቀደ ለአዲስ ፕሮጀክቶች የሚቀርብ የበጀት ጥያቄ በእቅድና ልማት መ/ቤት ተገምግሞ
መስፈርቱን ያሟላ መሆኑ ተረጋግጦ ሲቀርብ በበጀት የሚደገፍ ይሆናል፡፡


● የሥልጠናና ግዢ ፕሮጀክት የወቅቱን ዋጋ ታሳቢ ያደረገና ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ ስለመዘጋጀቱ መጣራት አለበት፡፡

18

አጠቃላይ ፣
 በበጀት ዝግጅት ወቅት በተለያየ ምክንያት አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ተንከባለው የመጡ እዳዎች ያሉ እንደሆነ
የግዴታ ወጪ ሆነው በአዲሱ በጀት ዓመት ሊደገፉ ይገባል፡፡ (ለምሳሌ፣በአስተዳደር እርከኖች ለሚወሰድ የደመወዝ
ብድር)
 የመ/መ/ቤቶች በ2014 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ ዋና ዋና የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በመገምገም
በዋናነት እድገትን በሚያፋጥኑና ድህነትን ለመቀነስ ቁልፍ ሚና ባላቸው ሴክተሮች ከ65 በመቶ በላይ እና አሁንም የግብርና
ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ በዘርፉ ከ11 በመቶ በላይ የበጀት ድልድል ማድረግን በመርህ ልንከተል ይገባል፡፡
 በክልላችን የመደበኛ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች ከጠቅላላ በጀት የሚኖረውን ድርሻ 58፡በ42 ለማድረስ ባለፉት የእቅድ
አፈጻጸም ዘመናት ግብ የተጣለ ቢሆንም ከክልል ማዕከል በስተቀር በሌሎች አካባቢዎች ማሳካት አልቻልንም፡፡ በመሆኑም


የመደበኛና ካፒታል በጀት ድርሻ ቢያንስ 70፡በ30 እንዲሆን ጥረት ማድረግ ይገባናል፡፡

19

የበጀት ዘገባ ሪፖርት፣
በዓመታዊ በጀት አፈጻጸም የፋይናንስና እቅድ አፈጻጸም ጥምርታ /Ratio/ 1፡1 መሆን ይገባዋል፡፡ ይህ የበጀት
አጠቃቀም በየወቅቱና በዋናነት ደግሞ በየሩብ ዓመቱ አፈጻጸሙ ይገመገማል፡፡ በ3ኛ እና 4ኛ ሩብ ዓመታት የበጀት
አጠቃቀም ግምገማ ወቅት ሥራ ላይ ያልዋለ ወይም ከተያዘ በጀት በላይ ተጨማሪ በጀት የሚያስፈልግ ከሆነ
በበጀት ዝውውር ወይም በተቻለ መጠን የገቢ አቅማችንን በማሳደግ ተጨማሪ በጀት በማወጅ ሊስተካከል
ይገባል፡፡
የበጀት ዘገባ ሪፖርት በዓመቱ መጨረሻ ሂሳብ ከመጠቃለሉ እና ከመዘጋቱ በፊት አጠቃላይ የበጀት አፈጻጸም
ሂደትን የምንገመግምበትና ከበጀት በላይ ያሉ ወጪዎች ካሉ በመፈተሽ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ
ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት የሚቀርብበት አሰራር ነው፡፡

”20
ሐ / የሂሣብ አወቃቀር
የመንግሥት በጀት ተጠቃሚዎች፣ የገቢ ዓይነቶች ፣ የውጭ
ዕርዳታ፣ የውጭ ብድር፣ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር፣ የአገር ውስጥ
ብድር እንዲሁም የወጪ ዝርዝሮች የሚታይበት የሂሣብ
አመዘጋገብ ሥርዓት ነው፡፡
የሂሣብ አወቃቀር ያስፈለገበት ምክንያት፣

 የተጣሩና የወጭና ግልጽ የሆነ የወጪ መደቦች ሥራ ላይ


እንዲውል ለማድረግ፣
 በካፒታልና በመደበኛ በጀቶች ያለውን መለያየት ማስወገድ፣
 በአጠቃላይ ውጤቶች እና በጠቅላላ ውጤቶች መሀል ያለውን
ግንኙነት በግልጽ ለማየት እንዲቻል፣
 የካፒታልና የመደበኛ ወጪዎችን በወጪ ማዕከል ለማገናኘት
ይረዳል፡፡
 በፌዴራልና በክልል መንግሥት ተመሣሣይ የገቢ መለያ ቁጥርን
በመጠቀም አንድ ዓይነት የኮምፒዩተር አሠራር ለመጠቀም
ማስቻል ነው፡፡
21
የሂሣብ አወቃቀር

22
አ መ ሰ ግ ና
ለሁ

23

You might also like