You are on page 1of 27

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት

የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2 ሺ01

የካቲት 2sሺ01 ዓ.ም

አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

የኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ
ቁጥር 8)#7/2ሺ6 አንቀጽ $3(2) እና በቦርዱ ማቋቋሰሚያና አሠራሩን መወሰኛ የሚኒስትሮች
ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 3)32/2ሺ7 አንቀጽ "2 መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

፩. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “በሂሳብ ሙያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት


የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2ሺ01” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ትርጓሜ

በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-

1. “ቦርድ” ማለት የኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ነው፤

2. “አዋጅ” ማለት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 8)#7/2ሺ6 ነው፤

3. “ደንብ” ማለት የኢትዮጵያ የሂሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ማቋቋሚያና አሠራሩን መወሰኛ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 3)32/2ሺ7 ነው፤

4. “የታወቀ ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ” ማለት በሀገር አቀፍ ደረጃ አግባብ ባለው የመንግስት
አካል እወቅና ያለው ዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ነው፡፡

5. “የኃላፊነት የሥራ መደብ” ማለት በሂሳብ አያያዝ ሥራ ሂሳብን አጠናቅሮ መዝጋት፣ የሂሳብ
መዛግብት ማዘጋጀትና ማስመርመር፣ በሥር ላሉ ሠራተኞች አመራር መስጠት ሆኖ በሥራ
መደብ አጠራር የፋይናንስ ኃላፊ ወይም የውስጥ ኦዲት ኃላፊ እንዲሁም በውጭ የኦዲት
ድርጅት ወይም የሌሎች ድርጅቶች ሂሳብ ኦዲት በሚያደርግ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ኦዲተርና
ከዚያ በላይ የሆነ የሥራ መደብ ማለት ነው፡፡

6. “ኃላፊነት ያለበት ግለሰብ” ማለት በቦርዱ የድርጅት ምዝገባ ፈቃድ በተሰጠው የተመሰከረለት
የሂሳብ ባለሙያ ወይም ኦዲተር የተሰየመ እና በሂሳብ መግለጫ ወይም በኦዲት ሪፖርት ላይ

1
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ስለ ሰያሚው ሆኖ እንዲፈርም በቦርዱ የተፈቀደለት የሙያ ስራ የምስክር ወረቀት ያለው


ግለሰብ ነው፡፡

7. “አባል” ማለት በሂሳብ ሙያ ማኅበር የቀረቡለትን ሁሉንም የሙያ ፈተናዎችን ያጠናቀቀና


ሌሎች መስፈርቶችን አሟልቶ የማኅበሩ አባል የሆነ ግለሰብ ነው፤

8. “አገልግሎት ማስቀጠል" ማለት አንድ የተመሰከረለት የሂሳብ ወይም የኦዲት ባለሙያ በፅኑ
ሕመም፣ በሞት፣ ችሎታ በማጣት ወይም ግዴታውን እንዳይፈፅም የሚከለክል ያልታሰበና
ድንገት ደራሽ ሁኔታ ሲያጋጥም የጀመረውን አገልግሎት በሌላ ባለሙያ ለማስቀጠል
የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

9. “የሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ" ማለት የተመሰከረላቸው የሂሣብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች


የሚመሩበት ቦርዱ የሚያወጣው ወይም ዓለም አቀፍ የሂሳብ ባለሙያዎች ፌዴሬሽን ወይም
እርሱን የሚተካው አካል የሚያወጣውና ቦርዱ የተቀበለው የሥነ-ምግባር ደንብ ነው፤

0. “የሠራተኞች ብዛት” ማለት ሪፖርት አቅራቢው አካል በሂሣብ ዓመቱ በእያንዳንዱ ወር


በሥራ ውል ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሆነው ወሩን ሙሉ ባይሰሩም ጠቅላላ
ድምር በሂሣብ ዓመቱ ላሉት ወራት ቁጥር ሲካፈል የሚገኘው አማካይ የሠራተኞች ብዛት
ነው፡፡

01. “ጠቅላላ ሀብት” ማለት በሪፖርት አቅራቢው አካል የሀብትና ዕዳ መግለጫ ላይ የሰሠፈረው
ጠቅላላ የሀብት መጠን ነው፡፡

02 “በቦርዱ የታወቀ/ተቀባይት ያገኘ አሰሪ” ማለት …………….……..

03. በአዋጁ እና በደንቡ አንቀጽ 2 ሥር የተሰጡ ትርጓሜዎች ለዚህ መመሪያም ተፈፃሚ


ይሆናሉ፡፡

2
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ክፍል ሁለት

የሪፖርት አቅራቢ አካላት መለያ መስፈርትና ምዝገባ

፫. ሪፖርት አቅራቢ አካላት

በአዋጁ አንቀጽ 2(07) እና አንቀጽ 4(1)(መ) መሠረት የሕዝብ ጥቅም ያለባቸው አካላት እና
አነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጅቶች ከዚህ በታች ባሉ አንቀጾች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች
የሚያሟሉ ሪፖርት አቅራቢ አካላት ናቸው፡፡

፬. የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ሪፖርት አቅራቢ አካላት መለያ መስፈርት

1. ድርጅቱ ከሚሰጠው የአገልግሎት አይነት ወይም ባህሪ አኳያ፡-

ሀ) የሚያወጣው የግዴታ ወይም የአክሲዮን የምስክር ወረቀት ቁጥጥር በሚደረግበት


የካፒታል ገበያ ለግብይት ማዋል የሚችል ወይም ለማውጣት በዝግጅት ወይም በሂደት
ላይ የሆነ ማንኛውም ድርጅት፤

ለ) ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋሞች፣ የቁጠባ ሂሣብ


የሚያንቀሳቅስ ማንኛውም ተቋም፣ የካፒታል ቁሳቁሶችን ፋይናንስ የሚያደርግ ማንኛውም
ድርጅት እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር የሚደረግበት ማንኛውም
የፋይናንስ ተቋም፤

ሐ) አግባብ ባለው የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል ቁጥጥር የሚደረግበት ማንኛውም የጡረታ


ወይም ፕሮቪደንት ፈንድ፣ የጋራ የኢንቨስትመንት ሥራና ሌላ መሠል ተቋም፤

መ) ከሁለት በላይ ለሆኑ ከድርጅቱ ውጪ ያሉ አካላትን ሀብት በአደራ ማስተዳደርን ወይም


መያዝን እንደ ዋነኛ ወይም ተቀዳሚ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው አድርጎ የሚያካሂድ
ማንኛውም የንግድ ድርጅት፤

That hold assets in fiduciary capacity for a broad group of outsiders as one of
their primary businesses;

3
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሠ) በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘ ማንኛውም የመንግሥት


የልማት ድርጅት፤

ረ) በኢትዮጵያ የምርት ገበያ የተመዘገበ ማንኛውም የግብይት ተዋዋይ አባል ወይም አገናኝ
አባል፤

ሰ) ለሕብረተሰቡ በግዢ የሚሰራጩ አስፈላጊ አገልግሎቶችን በመንግስት የግዢ ሥርዓት


መሠረት የሚያቀርብ ድርጅት፤

Any entity that provides essential/basic public services and is subject to public
procurement;

ሸ) በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ኤጅንሲ ቁጥጥር የሚደረግበትና በሕግ የፋይናንስ


ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ ያለበት ማንኛውም ለትርፍ ያልተቋቋመ የበጎ አድራጎት
ድርጅትና ማኅበር፤

የሕዝብ ጥቅም ያለባቸው አካላት ናቸው፡፡

2. ከድርጅቱ የሀብት መጠንና የሰራተኞች ብዛት አኳያ፡-

በባለፈው የሂሳብ ዓመት ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን ያሟላ
ማንኛውም የንግድ ድርጅት የሕዝብ ጥቅም ያለበት አካል ነው፡፡

ሀ) ዓመታዊ ገቢው 50 ሚሊዮን ብርና ከዚያ በላይ የሆነ፤

ለ) ጠቅላላ ሀብቱ 100 ሚሊዮን ብርና ከዚያ በላይ የሆነ፤

ሐ) የሰራተኞቹ ብዛት 100 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤

መ) የባለአክሰዮኖችን ሀብት ሳይጨምር ጠቅላላ ተከፋይ ሂሳቡ 100 ሚሊዮን ብርና ከዚያ
በላይ የሆነ፡፡

4
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

፭. የአነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጀቶች መለያ መስፈርት

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 4 ሥር የተዘረዘሩትን የማያሟላ ማንኛውም የአክስዮን ማኅበር ወይም


ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፤ ወይም የባለፈው አመት ዓመታዊ ገቢው አንድ ሚሊዮን
ብርና ከዚያ በላይ የሆነ የሽርክና ማኅበር ወይም የግል የንግድ ድርጅት እንደ አነስተኛ ወይም
መካከለኛ ድርጅት ይቆጠራል፡፡

፮. የጥቃቅን ድርጅቶች መለያ መስፈርት

በዚህ መመሪያ አንቀጽ 4 እና 5 ሥር የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የማያሟላ የሽርክና ማኅበር


ወይም የግል የንግድ ድርጅት እንደ ጥቃቅን ድርጅት ይቆጠራል፡፡

፯. የሂሳብ ዓመት አቆጣጠር/ስሌት

ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም ሲባል የሪፖርት አቅራቢው አካል የሂሳብ ዓመት 12 ወራት
በማይሞላበት ጊዜ ከፍተኛው የገቢ መጠን ዐሃዞች ተመጣኖ ይሰላል፡፡

፰. የሪፖርት አቅራቢ አካል ግዴታዎች

1. ማንኛውም ሪፖርት አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣው ማስታወቂያ መሠረት የምዝገባ


ክፍያ በመክፈል መመዝገብ እና ከዚህ በታች በተዘረዘረው አግባብ በየዓመቱ ኦዲት የተደረገ
የሂሳብ ሪፖርት መግለጫ ማቅረብ አለበት፡፡

ሀ) የሕዝብ ጥቅም ያለበት አካል ከሆነ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች፤

ለ) አነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጅት ከሆነ ለአነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጅት በወጣው
ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች፤

ሐ) የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ከሆነ በአለም አቀፍ የፐብሊክ ሴክተር የሂሳብ አያያዝ
ደረጃዎች፡፡

2. ማንኛውም ሪፖርት አቅራቢ አካል ለማንኛውም ዓላማ ሲባል በተለያየ ጊዜ የሚያዘጋጀው


እና ለሌላ አካል የሚያቀርበው የሂሳብ መግለጫና ኦዲት ሪፖርት በዚህ አንቀፅ በተደነገገው

5
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

የፋይናንስ እና የኦዲት ደረጃ መሰረት ተዘጋጅቶ በቅድሚያ ለቦርዱ መቅረብ ያለበት ሲሆን
ለሌላ አካል የሚቀርበው ሪፖርትም ለቦርዱ የቀረበው ኦርጂናል ቅጂ መሆን አለበት፡፡

3. ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሪፖርት አቅራቢ አካላት አመታዊ የሂሳብ መግለጫቸውን ለቦርዱ
ሲያቀርቡ እንደአግባብነቱ በተመሰከረለት ወይም በፐብሊክ ኦዲተር የማስመርመር ግዴታ
አለባቸው፡፡

4. በዚህ አንቀጽ የተጠቀሱ ሪፖርት አቅራቢ አካላት የሂሳብ መግለጫቸውን የድርጅቱ የሂሳብ
ዓመት ባለቀ በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ለቦርዱ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ሪፖርቱን ያላቀረበ ማንኛውም
ሪፖርት አቅራቢ አካል ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን ተገቢውን ቅጣት ይከፍላል፡፡

ክፍል ሦስት

የሙያ ሥራና የምዝገባ ምሥክር ወረቀት አሰጣጥ

፱. የተመሰከረለት የሂሣብ ባለሙያ (ሲፒኤ) ሆኖ ለመመዝገብ የሚያስችሉ መሰፈርቶች

በደንቡ አንቀጽ 07 መሠረት የተመሰከረለት የሂሣብ ባለሙያ ሆኖ በቦርዱ ለመመዝገብ


የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፡-

1. ቦርዱ በሚያስተዳድረው እና/ወይም ዕውቅና በሰጠው አካል የሚዘጋጁ የሂሣብ ሙያ ብቃት


ፕሮግራሞችን ተከታትሎ ያጠናቀቀ፤

2. ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል ከሆነ በኋላ ወይም
ከመሆኑ በፊት በቦርዱ በታወቀ/ተቀባይት ባገኘ አሰሪ ዘንድ ቢያንስ ለሦስት ዓመታት
በሂሣብ ሙያ እና/ወይም በኦዲተርነት የሥራ ልምድ ያለው፤

መሆን አለበት፡፡

፲. የሂሳብ ሙያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ መስፈርቶች

የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ ለመስራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በደንቡ አንቀጽ


07(3) ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፡-

6
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

1. ከሁለት ላላነሱ ዓመታት ሳያቋርጥ ቦርዱ አክሬዴሽን/ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር


ውስጥ አባል የሆነና ግዴታውን የተወጣ፤

2. ቦርዱ አክሬዴሽን ወይም ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል ከሆነ በኋላ የሙያ
ሥራ የምሥክር ወረቀት ለማግኘት ካመለከተበት ቀን በፊት ባሉት አምስት ዓመታት
ውስጥ ለሶስት ዓመታት በቦርዱ በታወቀ/ተቀባይት ባገኘ አሠሪ በሂሣብ ሙያ እና/ወይም
በኦዲተርነት የሥራ ልምድ ያለው፤

3. በቦርዱ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ ፖሊሲ መሠረት ቢያንስ አርባ ነጥብ/ዩኒት ያለው
ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ያደረገ ከዚህ ውስጥ ሃያ ነጥብ/ዩኒት በማስረጃ አስደግፎ
በቦርዱ የተዘጋጀውን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ ያቀረበ፤

4. ከሰራበት ድርጅት የቅርብ ኃላፊ እና በቦርዱ ከተመዘገበ የሂሣብ ባለሙያ ወይም ኦዲተር
የተሰጠ አስተያየት ያቀረበ፤

5. መልካም ሥነ-ምግባር ያለው እና በእምነት ማጉደል ወይም በማጭበርበር ወንጀል ተሳታፊ


ሆኖ በማንኛውም ሀገር ጥፋተኛ ያልተባለ መሆኑን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ ያቀረበ፤

6. የቦርዱን የሙያ ሥነ- ምግባርና የዲሲፕሊን ሥነ ሥርዓት ደንብ ለማክበር ማረጋገጫ


የሚሰጥ፤

7. ባለፉት አምስት ዓመታት በማንኛውም ተቋም በከባድ አስተዳደራዊ እርምጃ/በዲሲፕሊን ክስ


ያልተቀጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሰጠ፤

8. የፀና የንግድ ፈቃድ ያቀረበ፤

9. በአግባቡ የተደራጀ ቢሮ ያለው፤

0. በሞት ወይም በችሎታ ማጣት ምክንያት አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ የማድረጊያ ስምምነት


ያለው መሆኑን ማረጋገጫ የሚያቀርብ፤

01. እንደአግባብነቱ መጨረሻ ከሰሩበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ የሚችል፤

7
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

02. ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ተገቢውን የምዝገባ ክፍያ ሰለመክፈሉ


ማረጋገጫ ደረሰኝ በማያያዝ ቦርዱ እንዲመዘግበውና የምዝገባ የምሥክር ወረቀት
እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡፡

፲፩. የተመሰከረለት ኦዲተር (ሲኤዩ) ሆኖ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

የተመሰከረለት ኦዲተር ሆኖ በቦርዱ ለመመዝገብ የሚፈልግ የተመሰከረለት የሂሣብ ባለሙያ


በደንቡ አንቀጽ 08 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፡-

1. ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር ውስጥ ከአምስት


ላላነሱ ዓመታት ሳያቋርጥ አባል የሆነና ግዴታውን የተወጣ፤

2. ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል ከሆነ በኋላ
ወይም ከመሆኑ በፊት በቦርዱ በታወቀ/ተቀባይት ባገኘ አሰሪ ዘንድ ቢያንስ ለስምንት
ዓመታት በሂሣብ ሙያ እና/ወይም በኦዲተርነት የሥራ ልምድ ያለው፤

3. የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል ከሆነ በኋላ ለሙያ ሥራ የምሥክር ወረቀት ለማግኘት


ካመለከተበት ቀን በፊት ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ለሰላሣ ስድስት ወራት በቦርዱ
በታወቀ/ተቀባይት ባገኘ አሠሪ በተመሰከረለት ኦዲተር ቁጥጥር ሥር በኦዲት
ማናጀርነት ወይም ከዚያ በላይ ባለ የሥራ መደብ የሥራ ልምድ ያለው ሆኖ ከዚህ
ውስጥ ክፍያ ለተጠየቀባቸው ቢያንስ ለስድስት መቶ ወይም ተመጣጣኝ ሰዓታት
በኦዲትና ማረጋገጥ አገልግሎት የሰጠ፤

4. በቦርዱ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ ፖሊሲ መሠረት ቢያንስ አርባ ነጥብ/ዩኒት
ያለው ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ያደረገ ከዚህ ውስጥ ሃያ ነጥብ/ዩኒት የኦዲትና
ማረጋገጥ ትምህርት የወሰደና በትጋት ስለመከታተሉ በማስረጃ አስደግፎ በቦርዱ
የተዘጋጀውን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ ያቀረበ፤

መሆን አለበት፡፡

8
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

፲፪. የተመሰከረለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት የሚያስችሉ መስፈርቶች

የተመሰከረለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በደንቡ አንቀጽ 08


ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፡-

1. ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና ከሠጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል የሆነና


ግዴታውን የተወጣ፤

2. በቦርዱ ከተመዘገቡ ሁለት ኦዲተሮች የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ፤

3. ኢትዮጵያዊ ከሆነ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ኢትዮጵያዊ ካልሆነ ላለፉት አሥራ ሁለት


ወራት በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ስለመሆኑ ማረጋገጫና የሥራ ፈቃድ ወይም የሥራ
ፈቃድ ከማቅረብ ግዴታ በሕግ ነፃ የተደረገ ከሆነ ይህንን የሚያረጋግጥ አግባብነት
ያለው ማስረጃ ቅጂ፤

4. የቦርዱን የሙያ ሥነ ምግባርና የዲሲፕሊን ሥነ ሥርዓት ደንብ ለማክበር ማረጋገጫ


የሰጠ፤

5. ባለፉት አምስት ዓመታት በማንኛውም ተቋም በከባድ አስተዳደራዊ


እርምጃ/በዲሲፕሊን ክስ ያልተቀጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሰጠ፤

6. የፀና የንግድ ፈቃድ ያቀረበ፤

7. በአግባቡ የተደራጀ ቢሮ ያለው፤

8. እንደአግባብነቱ መጨረሻ ከሰራበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ የሚችል፤

9. ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ተገቢውን የምዝገባ ክፍያ ሰለመክፈሉ


ማረጋገጫ ደረሰኝ በማያያዝ ቦርዱ እንዲመዘግበውና የምዝገባ የምሥክር ወረቀት
እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡፡

፲፫. ፐብሊክ ኦዲተር ሆኖ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መሥፈርቶች

ፐብሊክ ኦዲተር ሆኖ በቦርዱ ለመመዝገብ የሚፈልግ የተመሰከረለት ኦዲተር በአዋጁ አንቀጽ


08 መሠረት ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፡-

9
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

1. ከአምስት ላላነሱ ዓመታት ሳያቋርጥ ቦርዱ አክሬዴሽን ወይም ዕውቅና በሠጠው


የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል የሆነና ግዴታውን የተወጣ፤

2. ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና በሰጠው የሂሣብ ሞያ ማኅበር አባል ከሆነ በኋላ
በቦርዱ በታወቀ/ተቀባይት ባገኘ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ቢያንስ ለአስር ዓመታት
በኦዲትና ማረጋገጥ የሥራ ልምድ ያለው ሆኖ ከዚህ ውስጥ ለአምስት ዓመታት
በኦዲት ማናጀርነትና ከዚያ በላይ ባለ የሥራ መደብ የሥራ ልምድ ያለው፤

3. በቦርዱ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ ፖሊሲ መሠረት ቢያንስ አርባ ነጥብ/ዩኒት
ያለው ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ያደረገ ከዚህ ውስጥ ሃያ ነጥብ/ዩኒት የኦዲትና
ማረጋገጥ ትምህርት የወሰደና በትጋት ስለመከታተሉ በማስረጃ አስደግፎ በቦርዱ
የተዘጋጀውን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ ያቀረበ፤

መሆን አለበት፡፡

፲፬. ፐብሊክ ኦዲተር ሆኖ ለመመዝገብና ለመስራት ስለሚቀርብ ማመልከቻ

ፐብሊክ ኦዲተር ሆኖ ለመዝገብና ለመስራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፡-

1. በቦርዱ ከተመዘገቡ ሁለት ፐብሊክ ኦዲተሮች የተሰጠ አስተያየት ማቅረብ፤

2. ቦርዱ አክሪዲቴሽን ወይም ዕውቅና ከሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል የሆነና


ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ፤

3. የቦርዱን የሙያ ሥነ ምግባርና የዲሲፕሊን ሥነ ሥርዓት ደንብ ለማክበር ማረጋገጫ


የሰጠ፤

4. ባለፉት አምስት ዓመታት በማንኛውም ተቋም በከባድ አስተዳደራዊ


እርምጃ/በዲሲፕሊን ክስ ያልተቀጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሰጠ፤

5. የፀና የንግድ ፈቃድ፤

6. በአግባቡ የተደራጀ ቢሮ ያለው፤

7. የብር 10000000.00 (አስር ሚሊዮን) የሙያ መድን የገንዘብ ዋስትና የሚያቀርብ፤

10
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

8. እንደአግባብነቱ መጨረሻ ከሰሩበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ የሚችል፤

9. ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላትና ተገቢውን የምዝገባ ክፍያ


ስለመክፈሉ ማረጋገጫ ደረሰኝ በማቅረብ እንዲመዘግበውና የምዝገባ የምሥክር
ወረቀት እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡፡

፲፭. በሂሣብ ሙያ ወይም በኦዲት አገልግሎት ድርጅትነት ለመመዝገብ ስለሚቀርብ ማመልከቻ

1. የሂሣብ ሙያ ወይም የኦዲት አገልግሎት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት


በደንቡ አንቀጽ !(3) ሥር ከተጠቀሱትን መሥፈርቶች በተጨማሪ፡-

ሀ) የፀና የንግድ ፈቃድ፤

ለ) በቦርዱ ተቀባይነት ያለው የድርጅት ስም፤

ሐ) በአግባቡ የተደራጀ ቢሮ ያለው፤

መ) የሂሣብ ሙያ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት ብር 1000000.00 (አንድ ሚሊዮን)


፤ ለኦዲት ድርጅት ብር 5000000.00 (አምስት ሚሊዮን) የሙያ መድን የገንዘብ
ዋስትና የሚያቀርብ፤

ሠ) ሸሪኮቹ መጨረሻ ከሰሩበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ፤

ረ) ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ተገቢውን የምዝገባ ክፍያ


ሰለመክፈሉ ማረጋገጫ ደረሰኝ በማያያዝ ቦርዱ እንዲመዘግበውና የምዝገባ
የምሥክር ወረቀት እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡፡

2. ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ተገቢውን የንግድ ፈቃድ ባገኘ በአስራ አምስት የሥራ
ቀናት ውስጥ ቦርዱ ዘንድ በመቅረብ መመዝገብ አለበት፡፡

፲፮. ሀላፊነት ያለበት ግለሰብ

1. ማንኛውም የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሙያ፣የተመሰከረለት ኦዲተር ወይም ፐብሊክ


ኦዲተር ሀላፊነት ያለበት ግለሰብ ሆኖ ሊሰየም እና በሂሳብ መግለጫ ወይም ኦዲት
ሪፖርት ላይ ሊፈርም የሚችለው የሚከተሉትን ሲያሟላ ነው፡፡

11
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሀ) የሰያሚው ድርጅት የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ ከሆነ፤

ለ) የጸና የሙያ ስራ የምሰክር ወረቀት ያለው ከሆነ፤

ሐ) በሂሳብ ወይም በኦዲት ድርጅቱ የተሰየመ ከሆነ ፤

መ) በቦርዱ የተፈቀደለት ከሆነ፤

ሠ) አዋጁን፣ ደንቡን፣ የቦርዱን መመሪያዎች እና የሙያ ሥነ-ምግባር ደንቦች


ለማክበር ለቦርዱና ለሰየመው ድርጅት በጽሁፍ ማረጋገጫ የሰጠ ከሆነ እና

ረ) ባለፉት ሁለት አመታት በቦርዱ ወይም አባል በሆነበት የሙያ ማህበር


በዲሲፕሊን ክስ ያልተቀጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሰጠ ከሆነ ፤

2. ሀላፊነት ያለበት ግለሰብ የሂሳብ ወይም የኦዲት ስራውን በሚያከነውንበት ወቅት


የሂሳብ፣ የኦዲትና ተያያዥ የሆኑ የጥራት ቁጥጥር ደረጃዎችን ማክበር እና ቦርዱ
ያወጣቸውን የሙያ ሥነ-ምግባር ደንቦች ማክበር ይኖርበታል፡፡

3. በዚህ አንቀፅ አግባብ ሀላፊነት ያለበት ግለሰብ የሚሰይም ድርጅት ከዚህ በሚከተለው
የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ባለሙያ የሙያ መድን ሽፋን ማቅረብ አለበት፤

ሀ) የሂሳብ ሙያ አገልግሎት ድርጅት ከሆነ ብር 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ ብር)

ለ) ለኦዲት ድርጅት ከሆነ ብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን ብር)

ክፍል አራት

የምዝገባና የሙያ ሥራ የምስክር ወረቀት እድሳት

፲፯. የምዝገባና የሙያ ሥራ ምሥክር ወረቀት ዕድሳት

1. በዚህ መመሪያ መሰረት የተሰጠ የምዝገባና የሙያ የምስክር ወረቀት በየዓመቱ


መታደስ አለበት፡፡

2. የተሰጠበት ቀን ግምት ውስጥ ሳይገባ የምዝገባና የሙያ የምሥክር ወረቀት የሚፀናው


በየዓመቱ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ነው፡፡

12
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

3. የሂሳብ/የኦዲት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የአገልግሎት ጊዜው


ከማብቃት ከአንድ ወር በፊት የእድሳት ማመልከቻ ከተገቢው ክፍያ ጋር መቅረብ
አለበት፡፡

4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) የተጠቀሰው ቢኖርም የድርጅት ምዝገባ የምስክር
ወረቀት በየዓመቱ እስከ ታህሳስ 30 ድረስ ብቻ አስፈላጊውን ግዴታዎች በማሟላት
ያለቅጣት ይታደሳል፡፡

፲፰. የሙያና የምዝገባ የምሥክር ወረቀት እድሳት

1. ማንኛውም የሙያ ስራ የምስክር ወረቀት ለማሳደስ የሚፈልግ የሂሳብ ባለሙያ፣


ኦዲተር ወይም ፐብሊክ ኦዲተር፡-

ሀ) የእድሳት ማመልከቻና የክፍያ ደረሠኝ፤

ለ) ቦርዱ አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና ከሰጠው የሂሣብ ሙያ ማኅበር አባል


ሆኖ ግዴታውን የተወጣ ስለመሆኑ ማረጋገጫ፤ እና

ሐ) በቦርዱ ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ ፖሊሲ መሠረት ቢያንስ አርባ


ነጥብ/ዩኒት ያለው ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ያደረገና ከዚህ ውስጥ ሃያ
ነጥብ/ዩኒት ስለመከታተሉ ማስረጃ፤

በማቅረብ ማሳደስ ይችላል፡፡

2. ማንኛውም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማሳደስ የሚፈልግ የሂሣብ ወይም


የኦዲት ሙያ አገልግሎት ድርጅት፡-

ሀ) የእድሳት ማመልከቻና የክፍያ ደረሠኝ፤

ለ) ለሂሳብ አገልግሎት ድርጅት ከሆነ ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) ፤


ለኦዲት ድርጅት ከሆነ ከብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ያላነሰ
የታደሰ የሙያ መድን ሽፋን፤

13
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሐ) ድርጅቱ የሽርክና ማኅበር ካልሆነ በቀር በሞት ወይም በችሎታ ማጣት


ምክንያት አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ የማድረጊያ ውል/ስምምነት ያለው
መሆኑን፤

መ) በዚህ መመሪያ አንቀጽ 06 መሠረት ፈራሚ ያሰመዘገበ ድርጅት ለእያንዳንዱ


ፈራሚ የተገባ ከብር 5,000,000.00 (አምስት ሚሊዮን) ያላነሰ የሙያ መድን
ሽፋን፤

ሠ) በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የነበሩትን የደንበኞቹን ዝርዝር፣ አድራሻና


የተሰማሩበትን የንግድ ወይም የሥራ ዓይነት፣ ስራው የተጠናቀቀበትን ጊዜ
እና ሥራውን ያከናወነው ሸሪክ/ፈራሚ ስም ያካተተ ዓመታዊ የሥራ
ሪፖርት፤

ረ) የድርጅቱ ኦዲት የተደረገ ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ፤

ሰ) ድርጅቱ የሕዝብ ጥቅም ያለባቸውን አካላት ኦዲት የሚያደርግ ከሆነ በአለም


አቀፍ የኦዲት ጥራት ቁጥጥር ደረጃ መሠረት ውጤታማ የኦዲት ጥራት
ቁጥጥር ሥርዓት መተግበሩን ማረጋገጫ፤

በማቅረብ ማሳደስ ይችላል፡፡

3. በዚህ መመሪያ አንቀፅ 07 ንዑስ አንቀፅ (2) እና (4) በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያልቀረበ
የእድሳት ማመልከቻ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን ተገቢውን መቀጮ በመክፈል ሊታደስ
ይችላል፡፡

4. የእድሣት ጊዜው ካለፈ እስከ ሁለት ወር ያልታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት በቦርዱ
ይታገዳል፡፡

5. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (4) የታገደ ምዝገባ እድሳቱ የዘገየው ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት መሆኑን በኮሚቴ ታይቶ ተቀባይነት ካገኘና በኮሚቴው የሚቀርበው የውሳኔ
ሀሳብ በዋና ዳይሬክተሩ ከፀደቀ እድሳቱ ለዘገየበት እያንዳንዱ ቀን ተገቢውን መቀጮ
በመክፈል ሊታደስ ይችላል፡፡

14
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) ስር የተገለፀው ቢኖርም በማንኛውም ሁኔታ ሳይታደስ
አንድ ዓመት ያለፈው የምዝገባ የምሥክር ወረቀት ይሰረዛል፡፡

፲፱. እድሳትን ስለሚገመግም ኮሚቴ

በዚህ መመሪያ አንቀፅ 08 (5) መሰረት የሚቀርቡ የእድሳት ማመልከቻዎችን ገምግሞ የውሳኔ
ሀሳብ የሚያቀርብ ከ---------፣---------- እና ------------ የሚወከሉ አባላት ያሉት ኮሚቴ በቦርዱ
ዋና ዳይሬክተር ይዋቀራል፡፡

ክፍል አምስት

አስተዳደራዊ እርምጃዎች

፳. ቀላል አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች

የቦርዱ ክስ ሰሚዎች በባለሙያዎች እና በድርጅቶች ላይ በሚከተሉት ምክንያቶች ተግሳፅ፣


ማስጠንቀቂያ ወይም የገንዘብ ቅጣት ሊወስኑ ይችላሉ፡-

ሀ) የቦርዱ ሠራተኛ ሥራውን በሚመለከት ለሚያቀርበው ጥያቄ አለመተባበር፤

ለ) ለሙያው በቂ እውቀት የሌላቸውን ሰራተኞች ቀጥሮ ማሰራት፤

ሐ) የደንበኞችን መረጃ በአግባቡ አደራጅቶ አለመያዝ፤

መ) በስሩ ቀጥሮ የሚያሰራቸውን ሰራተኞች መረጃ በአግባቡ አለመያዝና ለቦርዱ


አለማሳወቅ፤

ሠ) በክስ ሰሚዎች እይታ የተፈፀመው የህግ ወይም የሙያ ስነ ምግባር ጥሰት


ቀላል ሆኖ ሲገኝ

፳፩. የምስክር ወረቀት የሚታገድበት ሁኔታ

1. ቦርዱ ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት የተመሠከረለት የሂሣብ ባለሙያን


የተመሠከረለት ኦዲተርን እና የፐብሊክ ኦዲተርን የሙያ ሥራ እና የድርጅት ምዝገባ
የምስክር ወረቀት ሊያግድ ይችላል፡-

15
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሀ) ባለሙያው አባል በሆነበት የሙያ ማኅበር የተሰጠው የአባልነት እና/ወይም


የብቃት ማረጋገጫ ከታገደ፤

ለ) የአድራሻ፣ የድርጅት ስም እና ማናቸውም መረጃዎች ላይ ለውጦች ሲኖሩ


በአስራ አራት ቀናት ውስጥ ካላሳወቀ፤

ሐ) ባለሙያው መውሰድ ከሚገባው ተከታታይ የሙያ ማጎልበቻ ትምህርት


ውስጥ ዝቅተኛውን ነጥብ/ዩኒት ያልተከታተለ ሲሆን፤

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተዘረዘሩትን ጥፋቶች መፈጸሙ የቦርዱ ክስ


ሰሚዎች ሲያረጋግጡ የሙያ ሥራ እና የድርጅት ምዝገባ የምስክር ወረቀቱን ከመቶ
ሰማንያ ቀናት ላልበለጠ ጊዜ እንዲታገድ ውሳኔ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡

3. የምሥክር ወረቀቱ የታገደ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ቦርዱ የዕገዳውን ውሳኔ
ባሳወቀበት ደብዳቤ ላይ ከተጠቀሰው የእገዳ የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አስር
የሥራ ቀናት ውስጥ ከቦርዱ የተሰጠውን ዋናውን የምሥክር ወረቀት ለቦርዱ
መመለስ አለበት፡፡

፳፪. የምስክር ወረቀት የሚሰረዝበት ሁኔታ

1 ቦርዱ ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት የተመሰከረለት የሂሣብ ባለሙያን፣


የተመሰከረለት ኦዲተርን እና የፐብሊክ ኦዲተርን የሙያ ሥራ እና የድርጅት
ምዝገባ የምስክር ወረቀት ሊሰርዝ ይችላል፡-

ሀ) ከባድ የሙያ ሥነ-ምግባርና የአሰራር ደንብ እና የሙያ አፈፃፀም ደረጃዎች


ጥሰት መፈፀሙ ከተረጋገጠ፤

ለ) የተመዘገበው በማስመሰል ወይም በማጭበርበር ሲሆን፤

ሐ) አዋጁን፣ ደንቡን፣ ይህንን መመሪያ እና የቴክኒክ ማጣቀሻዎች በከባድ


ሁኔታ የሚጥስ ድርጊት ፈፅሞ ሲገኝ፣

መ) በዚህ መመሪያ አንቀጽ ! እና !1 የተዘረዘሩትን ጥፋቶች በተደጋጋሚ


ወይም በተደራራቢ ፈፅሞ ሲገኝ፣
16
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሠ) ከእምነት ማጎደል ጋር በተያያዘ ወንጀል በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ


ውጭ ጥፋተኛ ሆኖ የገንዘብ ቅጣት አማራጭ በሌለው እሥር ባለሙያው
ከተቀጣ ወይም ድርጅቱ የገንዘብ ቅጣት ከተጣለበት፣

ረ) የሙያ ስራ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ባለሙያ ከዚህ አለም በሞት ሲለይ፤

ሰ) በህግ ወይም በፍርድ ችሎታ ያጣ መሆኑ ሲረጋገጥ፤

ሸ) በፈቃዱ የድርጅት ምዝገባ የምስክር ወረቀቱን ሲመልስ፤

ቀ) ለግብር አስገቢው ባለሥልጣንና ለሌላ አግባብ ላለው የመንግስት አካል


ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ መስጠቱ ሲረጋገጥ፤

በ) የቦርዱ ሠራተኛ ሥራውን በሚመለከት ለሚያቀርበው ጥያቄ መሰናክል


መፍጠር ወይም ሀሰተኛ መረጃ መስጠት፤

ተ) በታገደ የሙያ ወይም የድርጅት ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሂሳብ ወይም


የኦዲት አገልግሎት መስጠት፤

ቸ) የሙያ የምስክር ወረቀት ይዞ የድርጅት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ሳይኖረው


የሂሳብ ወይም የኦዲት አገልግሎት መስጠት፤

ኀ) በግልም ሆነ በሽርክና የሂሳብ ወይም የኦዲት ስራ ለመስራት የድርጅት


ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከወሰደ/ዱ በኋላ የድርጅት ምዝገባ የምስክር
ወረቀቱን ተመላሽ ሳያደርግ ተቀጥሮ ከሰራ፤

ነ) የምስክር ወረቀቱ ከሚፈቅደው የሙያ አገልግሎት ውጭ ሲሰራ ከተገኘ፤

ኘ) የሂሳብ ወይም የኦዲት ሥራ አገልግሎት ለመስጠት ከደንበኛው ጋር የተደረገ


የፅሁፍ ውል ሳይኖረው አገልግሎት መስጠት፤

አ) የሙያ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀቱን ሌላ ሰው እንዲገለገልበት አሳልፎ


ሰጥቶ ከተገኘ ወይም የሙያ ሥራውን በውክልና አሰርቶ ከተገኘ፤

17
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ከ) የሙያ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀቱ የእገዳ ጊዜው ሲያበቃ ለእገዳው


ምክንያት የሆነው ነገር ካልተስተካከለ ወይም እገዳው እንዲነሳለት
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላመለከተ፤

2. የምሥክር ወረቀቱ የተሰረዘ ማንኛውም ድርጅት ወይም ባለሙያ ከተሰረዘበት ቀን


ጀምሮ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ከቦርዱ የተሰጠውን ዋናውን የምሥክር ወረቀት
ለቦርዱ መመለስ አለበት፡፡

3. በዚህ መመሪያ መሠረት ቦርዱ የሙያ ወይም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሲሰርዝ
የንግድ ፈቃድ ለመስጠትና ለመቆጣጠር ኃላፊነት ለተሰጠው እና ለሌሎች
ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፡፡

4. በዚህ መመሪያ መሠረት የተወሰነ ማንኛውም የቅጣት ውሳኔ በባለሙያው ወይም


ድርጅቱ የግል ማኅደር ውስጥ እንዲመዘገብ/እንዲያያዝ ይደረጋል፡፡

፳፫. እገዳ የሚነሳበት ሁኔታ

1. በዚህ መመሪያ መሠረት የምስክር ወረቀቱ የታገደ ባለሙያ ወይም ድርጅት እገዳው
እንዲነሳለት የእገዳው ጊዜ ባለቀ በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ለቦርዱ ማመልከቻ
ማቅረብ አለበት፡፡

2. እገዳውን ያስተላለፈው አካል ማመልከቻውን ተቀብሎ በጥልቀት ከመረመረ በኋላ


ለእገዳው ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በአግባቡ መስተካከላቸውን ካመነ እገዳውን
ያነሳል፡፡

፳፬. ወደመዝገብ ስለመመለስ

1. በማንኛውም ምክንያት ከመዝገብ የተሰረዘ ባለሙያ ወይም ድርጅት በድጋሚ


ለመመዝገብ በአዋጁ፣ በደንቡ እና በዚህ መመሪያ ስለፈቃድና ምዝገባ በተደነገጉት
መሰረት እንደ አዲስ ማመልከት አለበት፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፈቃዱ ወይም ምዝገባው
የተሰረዘው በዚህ መመሪያ አንቀጽ 18(6) በተደነገገው ጊዜ ውስጥ ፈቃዱን/የምስክር

18
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ወረቀቱን ባለማሳደሱ ከሆነ ፈቃዱ/የምስክር ወረቀቱ እስከተሰረዘበት ቀን ድረስ


ያለውን ቅጣት ከፍሎ እንደ አዲስ ለመመዝገብ ማመልከት ይችላል፡፡

ክፍል ስድስት

አክሬዲቴሽን እና ዕውቅና

፳፭. በውጭ ሀገር ለተቋቋመ የሙያ ማኅበር ዕውቅና ስለመስጠት

1. ቦርዱ ያስቀመጣቸውን መሥፈርቶች ላሟላ በውጪ ሀገር ለተቋቋመ የሙያ ማኅበር


እና ቅርንጫፉ እንደ ሂሣብ ሙያ ማኅበር ዕውቅና ይሰጣል፡፡

2. የሙያ ማኅበሩ እና ቅርንጫፉ ዕውቅና ለማግኘት በአዋጁ አንቀጽ !6 ከተደነገገው


በተጨማሪ ቦርዱን በሚያሳምን ሁኔታ፡-

ሀ) የዓለም ዓቀፍ የሂሣብ ባለሙያዎች ፌደሬሽን አባል ስለመሆኑና የአባልነት


ግዴታውን ስለማክበሩ፤

ለ) ለቅርንጫፉ እውቅና እንዲሰጥ ለቦርዱ ማመልከቻ ከማቅረቡ በፊት የማኅበሩ


ምክር ቤት ቅርንጫፉን ለመክፈት የወሰነ ስለመሆኑ፤

ሐ) በፋይናንስም ሆነ በአሠራሩ ረገድ ፀንቶ በሥራ ላይ የቆየና ለወደፊትም


እንደሚቀጥል ሊገመት የሚችል ስለመሆኑ፤

መ) በሀገሪቱ ውስጥ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍሎች በሚያካትት ሁኔታ ዓላማ


ለማሣካት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችና መዋቅሮች በተጨባጭ ያለው
ስለመሆኑ፤

ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

፳፮. በሀገር ውስጥ ለተቋቋመ የሙያ ማኅበር አክሬዲቴሽን ስለመስጠት

1. ቦርዱ ያስቀመጣቸውን መሥፈርቶች ላሟላ ሀገር በቀል ማኅበር እና ቅርንጫፉ


እንደ ሂሣብ ሙያ ማኅበር አክሬዲቴሽን ይሠጣል፡፡

19
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

2. የሙያ ማኅበሩ እና ቅርንጫፉ አክሬዲቴሽን ለማግኘት በአዋጁ አንቀጽ !6


ከተደነገገው በተጨማሪ ቦርዱን በሚያሳምን ሁኔታ፡-

ሀ) የዓለም ዓቀፍ የሂሣብ ባለሙያዎች ፌደሬሽን አባል የሆነ ወይም


ለመሆን የሚያስችለውን ፕሮግራም ቀርፆ የሚንቀሳቀስ ስለመሆኑ፤

ለ) ለቅርንጫፉ አክሬዲቴሽን እንዲሰጥ ለቦርዱ ማመልከቻ ከመቅረቡ በፊት


የማኅበሩ ምክር ቤት ቅርንጫፉን ለመክፈት የወሰነ ስለመሆኑ፤

ሐ) በፋይናንስም ሆነ በአሠራሩ ረገድ ፀንቶ በሥራ ላይ የቆየ ወይም


ለመቆየት የሚያስችለው ፕሮግራም ያለው እና ለወደፊትም
እንደሚቀጥል ሊገመት የሚችል፤

መ) በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚወክል መርሀ


ግብር እና ይህንንም ለመተግበር የሚያስችል መዋቅር በተጨባጭ
ያለውና ቢያንስ ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች እና በአራት ክልሎች
ውስጥ አባላት ያሉት ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

፳፯. አክሬዲቴሽን ወይም ዕውቅና ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ

1. ቦርዱ እንደሂሣብ ሙያ ማኅበር ዕውቅና እንዲሰጠው የሚፈልግ በሀገር ውስጥ


ወይም በውጪ ሀገር የተቋቋመ የሙያ ማኅበር እና ቅርንጫፉ ቦርዱ ያዘጋጀውን
የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ማመልከቻ ማቅረብ አለበት፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚቀርብ ማመልከቻ ከተገቢው የምዝገባ
ክፍያ ጋር መቅረብ አለበት፡፡

፳፰. የአክሬዲቴሽን ወይም የዕውቅና እድሳት

1. በቦርዱ የተሠጠው ዕውቅና ወይም አክሬዴቴሽን ለማሳደስ የሚቀርብ ማመልከቻ


ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ከእድሳት ክፍያ ጋር መቅረብ
አለበት፡

20
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

2. በቦርዱ የተሠጠ ዕውቅና ወይም አክሬዲቴሽን ለማሳደስ የሚቀርብ ማመልከቻ


በየዓመቱ የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ከማብቃቱ ከአንድ ወር በፊት መቅረብ አለበት፡፡

3. በቦርዱ የተሰጠውን ዕውቅና ወይም አክሬዲቴሽን ከጊዜው ቀድሞ ወይም በጊዜው


ሣያሣድስ ከቀረ ከመደበኛው የእድሳት ክፍያ በተጨማሪ ቅጣት በመክፈል
የሚታደስ ይሆናል፡፡

፳፱. የድርጅቶች ትሥሥርና ስም አሠጣጥ

1. የዓለም ዓቀፍ ኦዲት ትሥሥር ድርጅት አባል የሆነ አንድ የኦዲት ድርጅት
የትሥሥር ድርጅቱን ስም ከመጠቀሙ/ከመቀበሉ በፊት ለቦርዱ የግንኙነቱን
ዝርዝር ጨምሮ፡

ሀ) የድርጅቱን የባለቤትነት መዋቅር፤

ለ) የትርፍና/ወጪ ክፍፍሉን ሥርዓት፤

ሐ) የትሥሥር ሥርዓቱ የሚያስከትለውን የጋራ ፖሊሲዎች፣ ሥነ


ሥርዓቶች፣ ስምና እስትራቴጂ፤

መ) የባለሙያ አቅርቦቶች የመጋራት ሥርዓቶችን (ካለ)ማሣወቅ ይኖርበታል፡፡

2. አንድ የኦዲት ድርጅት አባል የሆነበትን የኦዲት ትሥሥር ስም መጠቀም ወይም


መቀበል የሚችለው ቦርዱ ዝርዝር የትሥሥር ሥርዓቱን መርምሮ፣ ስያሜውንና
ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን ካፀደቀ ብቻ ይሆናል፡፡

21
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ክፍል ሰባት

የምስክር ወረቀት ስለመስጠት

፴. የምሥክር ወረቀት ስለመስጠት

ቦርዱ ሲመዘግብና አክሬዴቴሽን ሲሰጥ፡-

1. በቦርዱ ቅጽ 1(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት የተመሠከረለት


የሂሣብ ባለሙያ የምዝገባ የምሥክር ወረቀት፤

2. በቦርዱ ቅጽ 2(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት የተመሠከረለት


ኦዲተር የሙያ ሥራ የምሥክር ወረቀት፤

3. በቦርዱ ቅጽ 3(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት የፐብሊክ


ኦዲተር የሙያ ሥራ የምሥክር ወረቀት፤

4. በቦርዱ ቅጽ 4(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት እንደየአግባቡ


የሂሳብ ድርጅት፣ የኦዲት ድርጅትና የፐብሊክ ኦዲት ድርጅት የምዝገባ የምሥክር
ወረቀት፤

5. በቦርዱ ቅጽ 5(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት የህዝብ


ጥቅም ያለበት አካል የምዝገባ የምሥክር ወረቀት፤

6. በቦርዱ ቅጽ 6(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት የአነስተኛና


መካከለኛ ድርጀቶች የምዝገባ የምሥክር ወረቀት፤

7. በቦርዱ ቅጽ 7(ለ) እና የመጀመሪያው ሠንጠረዥ በሠፈረው መሠረት እንደሂሣብ


ሙያ ተቋም፣ማኅበር እና ቅርንጫፍ የዕውቅና ወይም የአክሬዴቴሽን የምሥክር
ወረቀት ይሠጠዋል፡፡

፴፩. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ

1. በአዋጁ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሠረት በቦርዱ እንደፐብሊክ ኦዲተር የተመዘገበ


ድርጅት ይህ መመሪያ ፀንቶ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ሦስት ዓመታት

22
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ውስጥ በዚህ መመሪያ ለግለሰብም ሆነ ድርጅት፣ ፐብሊክ ኦዲተር የተዘረዘሩትን


መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡ ይህን ያላሟላ ድርጅት የህዝብ ጥቅም
ያለበት አካል ኦዲት ማከናወን አይችልም፡፡

2. ቦርዱ ዝግጁ ሆኖ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 9 •ስር በተዘረዘሩት መስፈርቶች


መሠረት መስጠት እስኪጀምር ድረስ እንደተመሰከረለት የሂሳብ ባለሙያ (ሲፒኤ)
ሆኖ ለመመዝገብና የብቃት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ለመውሰድ የሚፈልግ
አመልካች ሊመዘገብ የሚችለው፡-

ሀ) ቢያንስ ከታወቀ የኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ በሂሳብ አያያዝ የመጀመሪያ


ዲግሪ ወይም የታወቀ የሂሳብ ሙያ ማህበር አባል የሆነ፤

ለ) በሂሳብ አያያዝ/በኦዲት በሀላፊነት የሥራ መደብ የሶስት ዓመት


የሥራ ልምድ ያለው፤

ሐ) በቦርዱ የሚሠጠውን ከዓለም አቀፍ የፋይናንስና ሪፖርት አቀራረብ


ደረጃዎች እና ከታክስ ጋር ተዛማጅነት ያለውን ፈተና ያለፈ፤

መ) በተመሰከረለት የሂሳብ ባለሙያነት ከተመዘገበ በኋላ በሦስት ዓመት


ውስጥ በቦርዱ የሚሠጠውን ተዛማጅ የሙያ ፈተናዎች መርሀ
ግብር ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በጽሁፍ የሚያረጋግጥ፤

ሠ) የቦርዱን የሙያ ሥነ ምግባርና የዲሲፕሊን ሥነ ሥርዓት መመሪያ


ሙሉ በሙሉ ለማክበር በጽሁፍ የሚያረጋግጥ፤

ረ) የቦርዱን ተከታታይ የሞያ ማጎልበቻ (ተሞማ) ትምህርት ሙሉ


በሙሉ ለመከታተል በጽሁፍ የሚያረጋግጥ፤

3. በዚህ መመሪያ አንቀጽ 01 የሠፈሩትን መስፈርቶች ባያሟላም እንኳ በቦርዱ እንደ


ተመሰከረለት ኦዲተር (ሲ.ኤዩ.) ለመመዝገብና የብቃት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት
ለመውሰድ የሚፈልግ አመልካች ሊመዘገብ የሚችለው፡-

23
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ሀ. የታወቀ የሂሳብ ሙያ ማህበር አባል የሆነና አባል ከሆነበት የሙያ ማህበር የስራ ምስክር
ወረቀት (Practicing Certificate) በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ያገኘ እና አባል ከሆነ በኋላ በኦዲት
ድርጅት ውስጥ በኦዲተርነት የሰራ፤

ለ. የታወቀ የሂሳብ ሙያ ማህበር አባል ሆኖ በሙያው ለመሰማራት የሚያስችለውን የስራ


ምስክር ወረቀት (Practicing Certificate) ከኢትዮጵያ ውጭ ሆነ ያገኘ ከሆነ፡-

1. የስራ ምስክር ወረቀት (Practicing Certificate) ካገኘ በኋላ በውጭ አገር ከ2 ዓመት
ያላነሰ የስራ ልምድ በአዲተርነት ካለው በኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ የ3 ወራት የስራ
ልምድ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ያለው ወይም
2. የስራ ምስክር ወረቀት (Practicing Certificate)በውጭ አገር አግኝቶ ከ1 አመት ተኩል
እስከ 2 ዓመት ጊዜ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ሲሰራ ቆይቶ የተመለሰ ከሆነ
በኢትዮጵያ ውስጥ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ቢያንስ ስድስት ወር የስራ ልምድ
ያለው ወይም
3. ከውጭ አገር የስራ ምስክር ወረቀት (Practicing Certificate) በውጭ ካገኘ በኋላ
በውጭ አገር ምንም የስራ ልምድ ሳይኖረው ወይም በታወቀ የኦዲት ድርጅት ከ1 ዓመት
ላነሰ ጊዜ ሲሰራ ቆይቶ የተመለሰ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በታወቀ የኦዲት ድርጅት
ውስጥ 2 ዓመት የስራ ልምድ ያለው ወይም፤
4. ውጭ አገር እያለ የታወቀ የሂሳብ ሙያ ማህበር አባል ሆኖ ምንም ሳይሰራ ወደ
ኢትዮጵያ ተመልሶ ኢትዮጵያ ውስጥ 2 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ በታወቀ የኦዲት ድርጅት
ውስጥ ሲሰራ ቆይቶ የስራ ምስክር ወረቀት(Practicing Certificate) ያገኘ

4. እንደ አግባብነቱ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 0 ወይም 02 የተደነገገው ባያሟላም


የተመሰከረለት የሂሳብ ባለሙያ ወይም የተመሰከረለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት የሚፈልግ
ማንኛውም ሰው በደንቡ አንቀጽ 07(3) እና 08 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ፡-
ሀ. ከሰራበት ድርጅት የቅርብ ኃላፊ እና በቦርዱ ከተመዘገበ የሂሣብ ባለሙያ ወይም
ኦዲተር የተሰጠ አስተያየት ያቀረበ፤

24
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

ለ/ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው እና በእምነት ማጉደል ወይም በማጭበርበር ወንጀል


ተሳታፊ ሆኖ በማንኛውም ሀገር ጥፋተኛ ያልተባለ መሆኑን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልቶ
ያቀረበ፤
ሐ/ የቦርዱን የሙያ ሥነ- ምግባርና የዲሲፕሊን ሥነ ሥርዓት ደንብ ለማክበር
ማረጋገጫ የሚሰጥ፤

መ/ ባለፉት አምስት ዓመታት በማንኛውም ተቋም በከባድ አስተዳደራዊ


እርምጃ/በዲሲፕሊን ክስ ያልተቀጣ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሰጠ፤
ሠ/ የፀና የንግድ ፈቃድ ያቀረበ፤

[ረ / በአግባቡ የተደራጀ ቢሮ ያለው፤


ሰ/ በሞት ወይም በችሎታ ማጣት ምክንያት አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ የማድረጊያ
ስምምነት ያለው መሆኑን ማረጋገጫ የሚያቀርብ፤

ሸ/ መጨረሻ ከሰሩበት ተቋም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ የሚችል፤

ቀ/ ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ቅፅ በመሙላት ተገቢውን የምዝገባ ክፍያ ሰለመክፈሉ


ማረጋገጫ ደረሰኝ በማያያዝ ቦርዱ እንዲመዘግበውና የምዝገባ የምሥክር ወረቀት
እንዲሰጠው ማመልከት ይችላል፡፡
5 በዚህ አንቀጽ ንዑሥ አንቀጽ (2) እና (3) መሠረት የተመዘገበ የተመሠከረለት የሂሳብ
ባለሙያ ወይም የተመሰከረለት ኦዲተር ቦርዱ ዝግጁ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በ3 ዓመት
ጊዜ ውስጥ በአንቀጽ 9 እና 02 ሥር የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ካላሟላ ምዝገባው
ይሠረዛል፡፡

ክፍል ስምንት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

፴፪. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች

25
የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

በሂሳብ ሙ ያ ስለመሰማራት፣ ስለሙያ ማኅበራትና ሪፖርት አቅራቢ አካላት የወጣ መ መሪያ ቁ ጥር 01/2011

የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ፣ የውስጥ ደንብ ወይም


አሰራር በዚህ መመሪያ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

፴፫. መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የዳይክተሮች ቦርድ ከፀደቀበት ቀን


ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ የካቲት ……….. ቀን 2ሺ01 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ

26

You might also like