You are on page 1of 10

የደረሰኝ Aያያዝ፣

Aጠቃቀምና ቁጥጥር
መመሪያ

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን


ነሐሴ 2001 ዓ.ም.
Aዲስ Aበባ
ስለ ደረሰኝ Aያያዝ፣ Aጠቃቀምና ቁጥጥር
መመሪያ ቁጥር 28 /2001

በሕግ የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የተጣለባቸው ግብር ከፋዮች የሚጠቀሙበትን


ደረሰኝ ከማሳተማቸው በፊት ለባለሥልጣኑ ማስመዝገብ Eንዳለባቸውና የህትመት
Aገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችም የግብር ከፋዮችን ደረሰኞች ከማተማቸው በፊት
የደረሰኞች ዓይነትና ብዛት በባለሥልጣኑ ስለመመዝገቡ ማረጋገጥ Eንደሚገባቸው በገቢ
ግብር ደንብ ቁጥር 78/1994 Aንቀጽ 20 ላይ የተደነገገ በመሆኑ፣

የተጨማሪ Eሴት ታክስ ደረሰኝ ባለሥልጣኑ በሚወስነው ዓይነት የሚዘጋጅና


በተጨማሪ Eሴት ታክስ Aዋጅ ቁጥር 285/1994 Aንቀጽ 22 (6) Eና (7) ላይ
በተመለከተው መሠረት ስለደረሰኝ Aጠቃቀም በመመሪያ Eንዲፈቀድ የተደነገገ በመሆኑ፣

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የገቢ ግብር ደንብ


ቁጥር 78/1994 Aንቀጽ 27 Eና በተጨማሪ Eሴት ታክስ ደንብ ቁጥር 79/1994
Aንቀጽ 39 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህን የAፈጻጸም መመሪያ Aውጥቷል፡፡

1. Aጭር ርEስ
ይህ መመሪያ #የደረሰኝ Aያያዝ፣ Aጠቃቀምና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 28/2001$
ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ
በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
1. #የሽያጭ ደረሰኝ$ ማለት Eጅ በEጅ ወይም በዱቤ Eቃ ወይም Aገልግሎት
ስለመሸጡ የሚሰጥ ማረጋገጫ ነው፡፡

2. #የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ$ ማለት ከሽያጭ የተገኘ ገቢ ቢሆንም ባይሆንም


ማንኛውም በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ስለመከፈሉ ወይም ገቢ ስለመደረጉ
የሚሰጥ ማረጋገጫ ነው፡፡
3. #ግብር ከፋይ$ ማለት በገቢ ግብር Eና በሌሎች Aዋጆች ግብር/ታክስ የመክፈል
ግዴታ ያለበት ሰው ነው፡፡
4. “ሰው” ማለት የሕግ ወይም የተፈጥሮ ሰው ነው፡፡
5. #ባለሥልጣን$ ማለት የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ነው፡፡
1
3. የተፈጻሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ ግብር ከፋይ የሆነ ሰው በሚሰጠው በማንኛውም የሽያጭና የገንዘብ
መሰብሰቢያ ደረሰኝ ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

4. የሽያጭ ደረሰኝ መያዝ የሚገባቸው መረጃዎች


1) የሽያጭ ደረሰኝ ቢያንስ የሚከተሉትን መሠረታዊ መረጃዎች ሊይዝ ይገባል፡፡
ሀ. የግብር ከፋዩን ሙሉ ሥም፣ Aድራሻ Eና የተመዘገበ የንግድ ሥም፣

ለ. የግብር ከፋዩን የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ Aሴት ታክስ


ምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥርና የተሰጠበትን ቀን፣

ሐ. የገዢውን ሙሉ ስም፣ Aድራሻና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

መ. ተከታታይ የሆነ የደረሰኝ ቁጥር፣

ሠ. የደረሰኙን Aታሚ ድርጅት ሥምና የታተመበትን ቀን፣

ረ. የተጓጓዘው ወይም የተሸጠው Eቃ ወይም የተሰጠው Aገልግሎት ዓይነትና


መጠን፣
• ግብይቱ የተፈፀመበት Eቃ የኤክሳAይዝ ታክስ የተከፈለበት ሲሆን
የኤክሳAይዝ ታክሱን መጠን፣
• ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ የሚፈለገውን የተጨማሪ Eሴት
ታክስ መጠን፣
ሰ. በፊደል Eና በAሃዝ የተፃፈ የሽያጭ ወይም ታክስ የሚከፈልበት ግብይት
ዋጋ፣

ሸ. ግብር ከፋዩ ለተጨማሪ Eሴት ታክስ የተመዘገበ ካልሆነ ግብይቱ ላይ


ሊከፈል የሚገባውን የተርንOቨር ታክስ መጠን፣
ቀ. ደረሰኙ የተሰጠበትን ቀን፣

በ. ደረሰኙን ያዘጋጀውና ገንዘቡን የተቀበለው ሠራተኛ ሥምና ፊርማ፣


ተ. ደረሰኙ Eንዲታተም በባለሥልጣኑ የተፈቀደበትን ደብዳቤ ቁጥርና ቀን፤
2) የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም የተጨማሪ Eሴት ታክስ
ደረሰኝ የሚይዛቸውን መረጃዎች በተመለከተ ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘው
ናሙና መሠረት ይሆናል፡፡

2
3) ለተጨማሪ Eሴት ታክስ ከፋይነት ያልተመዘገበ ግብር/ታክስ ከፋይ
የሚጠቀምበት ደረሰኝ የሚከተሉትን መሠረታዊ መረጃዎች መያዝ
ይኖርበታል፡፡
ሀ. ተከታታይነት ያለው የደረሰኝ ቁጥር፣ ቀንና ዓመተ ምህርት፣
ለ. የድርጅቱን ስምና Aድራሻ፣
ሐ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
መ. የAቅርቦቱን ዓይነት፣ መጠን፣ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፣
ሠ. የታክስ መጣኔ Eና የገንዘቡን መጠን፣

5. ደረሰኝ የመስጠት ግዴታና Aሰጣጡ ስለሚፈጸምበት ሁኔታ


1. ለተጨማሪ Eሴት ታክስ የተመዘገበ ወይም/Eና በህግ የሂሣብ መዝገብ የመያዝ
ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ Eንዲሁም የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚፈልግ የደረጃ
#ሐ$ ግብር ከፋይ የሚጠቀምበትን ደረሰኝ ከማሳተሙ በፊት በባለሥልጣኑ
Eንዲመዘገብለት ያደርጋል፣ ባለሥልጣኑም ይህንኑ በማሳወቅ ለማተሚያ ቤቶች
ይጽፋል፣

2. በህግ የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ ለሚያከናውነው


ሽያጭ ተከታታይ ቁጥር የታተመበት Eና በባለሥልጣኑ ቁጥሩ የተመዘገበ
ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ Aለበት፣

3. በኮምፒውተር የተዘጋጀ ደረሰኝ የሚጠቀም በተለይም ለተጨማሪ Eሴት ታክስ


ተመዝጋቢ የሆነ ግብር ከፋይ፣ የሚጠቀምበት ደረሰኝ ከዚህ መመሪያ ጋር
በተያያዘው ናሙና ላይ የተመለከቱትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ የደሰረኝ
ኮምፒውተር ሥርዓቱ ስለሚሰራበት ፕሮግራም የጻፈውን ሰው ወይም ድርጅት
በባለሥልጣኑ ዘንድ ማስመዝገብ ይኖርበታል፣

4. በጥሬ ገንዘብ /በካሽ/ መመዝገቢያ መሣሪያ ወይም በኮምፒዩተር የሚጠቀሙ


ግብር ከፋዮች ለሚያካሂዱት ግብይት በማሽኑ ወይም በኮምፒዩተሩ
የተዘጋጀ/የታተመ ደረሰኝ መስጠት Aለባቸው፣ ማሽኑ ስለሽያጭ መመዝገቢያ
መሣሪያዎች የተመለከቱትን ሁኔታዎች የሚያሟላ መሆን ይጠበቅበታል፡፡

5. በAዋጁ Aንቀጽ 22 (7) ላይ Eንደተመለከተው የተጨማሪ Eሴት ታክስን ጨምሮ


ለAቅርቦቱ/ለግብይቱ የሚከፈለው ጠቅላላ ዋጋ ከብር 10.00 /Aስር ብር/
የማይበልጥ Eና ወይም የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የማይጠቀሙ ከሆነ

3
ያለደረሰኝ ሊከናወን ይችላል፡፡ ሆኖም የየEለቱ ሽያጭ ተጠቃሎ የተጨማሪ
Eሴት ታክስ ደረሰኝ ሊቆረጥለት ይገባል፡፡

6. በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (4) Eና (5) የተመለከተው Eንደተጠበቀ ሆኖ


ግብይቱ ሲካሄድ የተጨማሪ Eሴት ታክስ Eየታከለበት መከናወን ያለበትና
በየወሩም የሂሣብ ማጠቃለያ ተዘጋጅቶለት የየEለቱ ሽያጭ ማጠቃለያ በተጨማሪ
Eሴት ታክስ ደረሰኝ ላይ Eየተሞላ የተሰበሰበው የተጨማሪ Eሴት ታክስ
በተጨማሪ Eሴት ታክስ Aዋጅ ቁጥር 285/1994 በተፈቀደው የጊዜ ገደብ
ለባለሥልጣኑ ገቢ መደረግ ይኖርበታል፣

7. ከውጭ Aገርም ይሁን ከAገር ውስጥ በግብር ከፋዩ ሰነድ ሳይመዘገብ ወይም
ሣይታወቅ ገንዘብ ወደ ባንክ ሂሣብ ገቢ ሲደረግ፣ ከባንከ በሚደርሰው የሂሣብ
መግለጫ መሠረት የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ይዘጋጃል፣

8. በህግ የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ደረሰኝ ሲጠይቁ
ከሥራ ፀባያቸው የተነሳ ደረሰኝ መስጠት የማይችሉ በተለይ በAነስተኛ ደረጃና
በባህላዊ የማምረት ዘዴ የተሰማሩ Aምራቾች Eንዲሁም መዝገብ ለመያዝ
የማይገደዱ የደረጃ #ሐ$ ግብር ከፋዮች ለሚሸጧቸው ምርቶች በገዥው የክፍያ
ቫውቸር ወይም ግዢው ስለመፈጸሙ በሚያረጋግጡ የውል ሰነዶች ላይ
ስማቸውንና Aድራሻቸውን በመግለጽ ግብይቱን መፈጸማቸውን በፊርማቸው
ያረጋግጣሉ፣

9. የEቃ ማስተላለፊያ ሰነድ Eና የዋጋ ማቅረቢያ Iንቮይስ ለEቃና Aገልግሎት


ግብይት Eንደደረሰኝ ሊያገለግሉ Aይችሉም፣

6. የተከለከለ ተግባር
1) በማንኛውም ሁኔታ ተመሣሣይ ቁጥር ያለው የሽያጭ ወይም የገንዘብ መቀበያ
ደረሰኝ ደግሞ በማሣተም ጥቅም ላይ ማዋል Aይቻልም፣
2) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) የተደነገገው Eንደተጠበቀ ሆኖ ተመሳሳይ
ቁጥር ያለው ደረሰኝ በስህተት ታትሞ ከተገኘ ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት
ባለሥልጣኑ Eንዲያውቀው ተደርጎ ሙሉ ለሙሉ መሰረዝ Aለበት፡፡

4
3) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) Eና (2) የተደነገገውን ተላልፎ መገኘት በገቢ
ግብር Aዋጅ ቁጥር 286/1994 Aንቀጽ 98 (1)(ለ) መሠረት በወንጀል
ያስቀጣል፡፡

7. የባለሥልጣኑ ኃላፊነት
ባለሥልጣኑ በደረሰኝ ህትመትና Aጠቃቀም ረገድ የሚከተሉትን የመከታተልና
የመቆጣጠር ኃላፊነቶች Aሉት፡-
1. ግብር ከፋዩ ደረሰኝ Eንዲታተምለት ሲጠይቅ ህጋዊና የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ
ያለው መሆኑን የማረጋገጥ፣
2. የደረሰኝ Aጠቃቀም በሕግና ተቀባይነት ባላቸው Aሠራሮች ላይ የተመሠረተ
መሆኑን የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የማረጋገጥ፣
3. Aስፈላጊ የሆኑ የግብር ከፋዮች መረጃ Eና የደረሰኞችን ተከታታይ ቁጥር
የመያዝ፣
4. የህትመት ድርጅቶችን ሙሉ ሥምና Aድራሻ በዝርዝር የመያዝ፣
5. ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄ ላቀረበ ግብር ከፋይ ቅደመ-ሁኔታዎች የተሟሉ
መሆናቸውን በማረጋገጥ Eንዲያሳትም የመፍቀድ፣
6. Eንዳስፈላጊነቱ የደረሰኝ ህትመት ተግባር በሚከናወንባቸው ማተሚያ ቤቶች
በመገኘት የማጣራት፣ የማረጋገጥ፣
7. ከማተሚያ ቤቶች Eና ከተጠቃሚዎች ስለደረሰኝ ህትመትና Aጠቃቀም
ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ወቅታዊ መልስ የመስጠት፣
8. የማተሚያ ቤቶች ስለደረሰኝ ህትመት መረጃ የሚያቀርቡበትን ቅጽ የማዘጋጀት፣
9. በኮምፒውተር (IT) በመደገፍ የደረሰኞች የህትመት ቁጥር ቅደም ተከተሉን
ጠብቆ ሥራ ላይ መዋሉን መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት በመዘርጋት
የመቆጣጠር፣
10. Aንዱ ማተሚያ ቤት የሰጠውን ቁጥር ሌላ ማተሚያ ቤት Eንዳይጠቀምበት በ IT
በመታገዝ ልዩ መለያ በመስጠት የመቆጣጠር፣
11. ለዚህ መመሪያ Aፈጻጸም የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተግባራት የማከናወን፣

8. የማተሚያ ድርጅቶች ኃላፊነት


ማንኛውም ማተሚያ ቤት/ድርጅት፡-
1. የሚታተመው ደረሰኝ በማን ስም Eንደሆነና ተከታታይ ቁጥሩ ተፈቅዶ
ከባለሥልጣኑ ሲገለጽለት ይህንኑ በማረጋገጥ የማተም፣
5
2. በሚያትመው በEያንዳንዱ ደረሰኝ ቅጂ/ቅጠል ላይ ደረሰኝ Eንዲታተም
የተፈቀደበት ቀንና ቁጥር፣ የማተሚያ ድርጅቱን ስም፣ የታተመበትን ቀንና
ዓመተ ምህረት የማመልከት፣
3. በማንኛውም ሁኔታ ተመሣሣይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ በድጋሚ Eንዳይታተም
ተገቢውን ጥንቃቄ የማድረግ፣
4. ለዚህ መመሪያ Aፈጻጸምና ክትትል Eንዲያግዝ ባለሥልጣኑ በሚያዘጋጀው ቅጽ
መሠረት Aስፈላጊውን መረጃ በመሙላት በየሶስት ወሩ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት
የማድረግ፣
ኃላፊነት Aለበት፡፡

9. የመተባበር ግዴታ
ማንኛውም ሰው በዚህ መመሪያ መሠረት ያልተዘጋጀ ደረሰኝ ሲያጋጥመው
ለባለሥልጣኑ ወዲያውኑ ማሳወቅ Aለበት፡፡

10. የመሸጋገሪያ ድንጋጌ


ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት ተጀምረው የነበሩ ጉዳዮች በዚህ መመሪያ
መሠረት ፍጻሜ ያገኛሉ፡፡

11. የተሻሩ መመሪያዎች


የሽያጭ ደረሰኝ Aያያዝ፣ Aጠቃቀምና ቁጥጥርን Aስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩ
መመሪያዎች በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡

12. የመመሪያው ተፈጻሚነት


ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተፈርሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

Aዲስ Aበባ_________ ቀን 2001 ዓ.ም.

መላኩ ፈንታ
የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
ዋና ዳይሬክተር

6
የደረሰኝ ቁጥር ___________
Invoice No
ቀን ___________
Invoice Date

የተጨማሪ Eሴት ታክስ ደረሰኝ


Value Added Tax Invoice

ከ __________________________________ ለ ___________________________________
From _______________________________ To __________________________________
Aድራሻ ክ/ከ___________ ቀ____ የቤ.ቁ _____ Aድራሻ ክ/ከ___________ ቀ____ የቤ.ቁ ______
Address W_____ K ______ H.No ________ Address W_____ K ______ H.No ________
የሻጭ የተ.E.ታ.ቁጥር የተ.E.ታ ቁጥር/ካለው/
Supplier’s VAT Reg. No. ________________ Customer’s VAT Reg.No.
የታክስ ከፋይ መ.ቁ የታክስ ከፋይ መ.ቁ ________________
Supplier’s TIN No. ___________________ Customer’s TIN No
የተመዘገበበት ቀን ________________________ የተመዘገበበት ቀን _______________________
Date of Registration ___________________ Date of Registration ____________________
Eቃው የቀረበበት ቀን ____________________
Date of supply _______________________

* በስተግራ ያለው ባዶ ቦታ በሙሉ በተመዘገበው ሰው ስምና Aድራሻ በቋሚነት መታተም Aለበት፡፡

ተ.ቁ የEቃው ዓይነት መለኪያ ብዛት የAንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ


S.No Description Unit Quantity Unit Price Total Price

ጠቅላላ ድምር
Total
VAT (15%)
ተ.E.ታ
ጠቅላላ ዋጋ
Selling Price

የክፍያ ሁኔታ በፊደል ብር


Mode of Payment In word Birr

በጥሬ ገንዘብ
በካሽ
Cash

የቼክ ቁጥር ፊርማ


Check No. ______________________ Signature ___________________
ቫውቸር ቁጥር
Voucher No.

ክፍፍል፡ 1ኛ ኮፒ ለከፋዩ፣ 2ኛ ኮፒ ለሻጭ፣ 3ኛ ኮፒ ለሂሣብ ክፍል፣ 4ኛ ኮፒ ለጥራዝ


Distribution: 1st copy-Customer 2nd Copy- Seller 3rd Copy-Account 4th Copy-Pad

በ ማተሚያ ድርጅት ቀን ቁጥር Eንዲታተም ተመዝግቦ የተፈቀደ፡፡

7
የደረሰኝ ቁጥር ___________
Invoice No
ቀን
Invoice Date
ማስታወሻ፡-
ለተጨማሪ Eሴት ታክስ ያልተመዘገበ ሰው የሚጠቀምበት የሽያጭ ደረሰኝ ከሆነ የድርጅቱ ስም፣ Aድራሻና የግብር ከፋይ መለያ
ቁጥር ከላይ በቋሚነት የሚታተም ሆኖ የሚከተለውን መረጃ ይይዛል፡፡

ለ ___________________________________
To __________________________________
Aድራሻ ክ/ከ___________ ቀ____ የቤ.ቁ _____ _
Address W_____ K ______ H.No ______ _ _
የግብር ከፋይ መ.ቁ
Customer’s TIN No
የተ.E.ታ ቁጥር/ካለው/
Customer’s VAT Reg.No.

ተ.ቁ የEቃው ዓይነት መለኪያ ብዛት የAንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ


S.No Description Unit Quantity Unit Price Total Price

ጠቅላላ ድምር
Total
ተርንOቨር ታክስ
T.O.T
ጠቅላላ ዋጋ
Selling price

የክፍያ ሁኔታ በፊደል ብር


Mode of Payment In words Birr

በጥሬ ገንዘብ
በካሽ
Cash

የቼክ ቁጥር ፊርማ


Check No. ______________________ Signature ___________________
ቫውቸር ቁጥር
Voucher No.

ክፍፍል፡ 1ኛ ኮፒ ለከፋዩ፣ 2ኛ ኮፒ ለሻጭ፣ 3ኛ ኮፒ ለሂሣብ ክፍል፣ 4ኛ ኮፒ ለጥራዝ


Distribution: 1st copy-Customer 2nd Copy- Seller 3rd Copy-Account 4th Copy-Pad

በ ማተሚያ ድርጅት ቀን ቁጥር Eንዲታተም ተመዝግቦ የተፈቀደ፡፡

8
9

You might also like