You are on page 1of 14

የጉምሩክ ዲክላራሲዮን

Aቀራረብን ለመወሰን
የወጣ መመሪያ

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን


ነሐሴ 2001 ዓ.ም.
Aዲስ Aበባ
የጉምሩክ ዲክላራሲዮን Aቀራረብን ለመወሰን
የወጣ መመሪያ ቁጥር 33/2001

የገቢ፣ ወጪና ተላላፊ Eቃዎችን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aፈፃፀም የተቀላጠፈ


በማድረግ ፈጣን የጉምሩክ Aገልግሎት ለመስጠት Eንዲቻል የዲክላራሲዮን ምዝገባ፣
የዋጋ ትመና Eና የክፍያ ሥራዎችን በAስመጪው ወይም በላኪው ወይም በጉምሩክ
ሥነ ሥርዓት Aስፈፃሚው በኩል በማንኛውም ጊዜና ቦታ Eንዲከናወን ማስቻል Aስፈላጊ
በመሆኑ፤

ከባለሥልጣኑ መስሪያ ቤት ውጪ ሊሠሩ የሚችሉ ሥራዎችን በAስመጪው፣ በላኪው


ወይም በጉምሩክ ስነ ስርዓት Aስፈፃሚው Eንዲከናወኑ በማድረግ የጊዜ ብክነትንና
AላAስፈላጊ ወጪዎችን በማስቀረት፣ ባለስልጣኑም በዋና በዋና ሥራዎቹ ላይ
Eንዲያተኩር Eና Aገልግሎቱን በውጤታማነት Eንዲያከናውን ማድረግ Aስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፣

የዲክላራሲዮን Aቀራረብ ስርዓትን በግልጽ በማስቀመጥ ወጥና ተጠያቂነት ያለበት


የAሠራር ስርዓት መዘርጋት Eና ዲክላራሲዮን የማይቀርብባቸውን Eቃዎች ዝርዝር Eና
Aፈፃፀሙን በመመሪያ መደንገግ በማስፈለጉ፣

የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በAዋጅ ቁጥር 622/2001 Aንቀጽ 12 ንUስ


Aንቀጽ (3) Eና Aንቀጽ 15 ንUስ Aንቀጽ (2) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን
መመሪያ Aውጥቷል፡፡

1
ክፍል Aንድ
ጠቅላላ ድንጋጌዎች

1. Aጭር ርEስ
ይህ መመሪያ “የጉምሩክ ዲክላራሲዮን Aቀራረብን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር
33/2001” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2. ትርጓሜ
ለዚህ መመሪያ Aፈፃፀም ሲባል፡-
1) “የጉምሩክ ዲክላራሲዮን” ማለት ወደ Aገር የሚገቡ፣ ወደ ውጭ Aገር የሚሄዱ
ወይም የተላላፊ Eቃዎች ዝርዝር የሚገለጽበትና የጉምሩክ ስነ ስርዓት
የሚፈጸምበት በባለሥልጣኑ የሚዘጋጅ ቅጽ ወይም ሰነድ ሲሆን በቃል ወይም
በAካል Eንቅስቃሴ ወይም በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የሚቀርቡ መግለጫዎችን
ይጨምራል፡፡
2) “የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aስፈፃሚ” ማለት ለገቢ ወይም ለወጪ ወይም
ለተላላፊ Eቃዎች መግለጫ የሚያቀርብ ማንኛውም መግለጫ Aቅራቢ ነው፡፡
3) “የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት” ማለት ወደ Aገር የሚገባ፣ ወደ ውጪ Aገር የሚላክ
ወይም ተላላፊ Eቃ የጉምሩክ ወደብ ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ከጉምሩክ ቁጥጥር
ሥር Eስከሚወጣ ድረስ የሚከናወን ማናቸውም የጉምሩክ Aፈፃፀም ሂደት
ነው፡፡
4) “መግለጫ Aቅራቢ” ማለት ለጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aፈፃፀም የጉምሩክ
ዲክላራሲዮን ለባለሥልጣኑ የሚያቀርብ መንገደኛ ወይም Aስመጪ ወይም ላኪ
ወይም የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aስፈፃሚ ወይም Aግባብ ያለው የባለስልጣኑ
ሠራተኛ ነው፡፡
5) “ቀጥተኛ የነጋዴዎች ግብዓት /D.T.I/” ማለት የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ለማተም
Eና የክፍያ መግለጫ ለማውጣት ፈቃድ የተሰጠው መግለጫ Aቅራቢ የራሱን
ኮምፒዩተር በመጠቀም ከራሱ ቢሮ በማንኛውም ሰዓት መረጃዎችን ወደ
ጉምሩክ የAውቶሜሽን ሥርዓት ማስገባት የሚያስችል የAሰራር ዘዴ ነው፡፡

2
6) “የምዝገባ ቁጥር” ማለት ከጉምሩክ Aውቶሜሽን ስርዓት ጋር ግንኙነት
በመፍጠር በቀጥተኛ የነጋዴዎች ግብዓት (D.T.I) Eንደ ቅደም ተከተሉ
ለመመዝገቡ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የሚሰጥ የዲክላራሲዮን መለያ ቁጥር ነው፡፡
7) “ገደብ የተደረገበት Eቃ” ማለት በሕግ በተደነገገ ሥነ ሥርዓት ሥልጣን ባለው
Aካል በተሰጠ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ወደ Aገር Eንዳይገባ ወይም ከAገር
Eንዳይወጣ ወይም Eንዳይተላለፍ ገደብ የተደረገበት Eቃ ማለት ነው፡፡
8) “የተከለከለ Eቃ” ማለት በሕግ ወይም Iትዮጵያ ባፀደቀቻቸው ዓለም Aቀፍ
ስምምነቶች መሠረት ወደ Aገር Eንዳይገባ፣ ከAገር Eንዳይወጣ ወይም
Eንዳይተላለፍ የተከለከለ ማንኛውም Eቃ ነው፡፡
9) “የጉምሩክ ስነስርዓት ኮድ (C.P.C)” ማለት በገቢና ወጪ Eቃዎች ላይ
Aግባብነት ያላቸውን ሕጐች ለማስፈፀም፣ መረጃዎችን በAግባቡ ለመመዝገብና
ለመያዝ Eንዲሁም የደንበኞችን Aገልግሎት Eንደሁኔታው ለያይቶ ለመስጠት
Eንዲቻል በዲክላራሲዮን ላይ ለተመዘገቡት Eቃዎች የሚሰጥ መለያ ቁጥር
ነው፡፡
10)“የግል ወይም የቤት ውስጥ መገልገያ Eቃዎች” ማለት
ሀ/ መንገደኞች በጉዟቸው ወቅት ለግል መጠቀሚያነት የሚያውሏቸውና
የንግድ መጠን የሌላቸው የግለሰብ የጉዞ Eቃዎች፣ ምግቦችና መጠጦች፣
ለ/ መንገደኛው በሀገር ውስጥ ወይም በውጭ Aገር ለሚገኝ ዘመዱ ወይም
ቤተሰቡ ወይም ጓደኛው ለግል መገልገያነት የሚያመጣቸው ወይም
የሚወስዳቸውን Eያንዳንዳቸው የንግድ መጠን Eና ባህሪ የሌላቸው Aዲስ
ወይም ያገለገሉ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች፣
የመዋቢያ፣ የመመገቢያ፣ የቤትና የማEድ Eቃዎችን Eና Eነዚህኑ
የመሳሰሉ Eቃዎች፤
ሐ/ በውጭ Aገር የሚኖር ዘመድ ወይም ቤተሰብ ወይም ጓደኛ በሀገር ውስጥ
ለሚገኝ ዘመድ ወይም ቤተሰብ ወይም ጓደኛ በሻንጣ፣ በጀሪካን ወዘተ
በመሳሰሉት በስጦታ የሚልካቸው የንግድ መጠን Eና ባህሪ የሌላቸው
Eና ለንግድ ሥራ የማይውሉ፣ ለግል ወይም ለቤተሰብ ወይም ለቤት
ውስጥ መገልገያነት የሚውሉ Aዲስ ወይም ያገለገሉ ልብሶች፣

3
ጫማዎች፣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች፣ የመዋቢያ፣ የመመገቢያ፣
የቤትና የማEድ ቤት የመሳሰሉት Eቃዎች ናቸው፡፡
11) “የንግድ ማስተዋወቂያና የናሙና Eቃዎች” ማለት፡-
ሀ/ የንግድ ድርጅቱ በተሰጠው የንግድ ፈቃድ በሚያካሂደው ንግድ ወይም
በሚሰጠው Aገልግሎት የሚሸፈኑ ወይም በማምረቻ ፈቃዱ
ለሚያመርተው ምርት ግብዓት የሆኑና ጠቅላላ ዋጋቸው ከ5000
/Aምስት ሺ/ ብር ያልበለጡ፣
ለ/ የድርጅቶች ስም፣ ዓርማ ወይም ልዩ መለያ/ምልክት ታትሞባቸው ንግድ
Eና Iንቨስትመንት ለማስፋፋት ለድርጅቶች የሚላኩ የንግድ መጠን
የሌላቸው ለሽያጭ የማይውሉ፣ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው በንግድ
ማስተዋወቂያነት በነፃ የሚሰጧቸው፣
ሐ/ የሃይማኖት፣ የEርዳታ Eና መንግስታዊ ተቋማት የተቋቋሙበትን ዓላማ
ለማስተዋወቅ የሚረዳ ለሽያጭ የማይውል የንግድ መጠን የሌለው
ተቋሙን የሚያመለክት ልዩ ምልክት ታትሞበት በመንገደኛም ይሁን
በጭነት የሚመጣ Eቃ ነው፡፡
12) “የግል ጌጣጌጥ” ማለት ወደ Aገር የሚገባ ወይም ከAገር የሚወጣ መንገደኛ
በAካሉ ላይ ያደረጋቸው ወይም የያዛቸው ከወርቅ፣ ከብር Eና ከሌሎች
ከከበሩ ማEድናት የተሰሩ የEጅ ሰዓት፣ የEጅ ቀለበት Eና ሌሎች ተመሳሳይ
መገልገያና የግል ጌጣጌጦች ናቸው፡፡
13) “የውጭ ምንዛሪ” ማለት በIትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት
ከAገር የሚወጣ ወይም ወደ Aገር የሚገባ መንገደኛ Eንዲይዘው የተፈቀደ
የውጭ Aገር ገንዘብ ነው፡፡
14) “ተመላላሽ መንገደኛ” ማለት ነፃ የAየር ጉዞ ቲኬት ያለውን ጨምሮ በAየር
ወይም በየብስ ቢያንስ በሶስት ወር ውስጥ Aንዴ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ
ውጭ Aገር የሚመላለስ መንገደኛ ነው፡፡
15) “መንገደኛ” ማለት በየብስ ወይም በዓለም Aቀፍ የAየር ማረፊያዎች በኩል
ወደ Iትዮጵያ የሚገባ ወይም ከIትዮጵያ የሚወጣ ሰው ነው፡፡
16) “Aረንጓዴ ማለፊያ” ማለት Eቃ ያልያዘ ወይም ቀረጥ Eና ታክስ
የማይከፈልበት Eቃ የያዘ መንገደኛ የሚያልፍበት ነው፡፡

4
17) “ቀይ ማለፊያ” ማለት ቀረጥና ታክስ የሚከፈልባቸውን Eቃዎች የያዘ
መንገደኛ የሚያልፍበት ነው፡፡
18) “የንግድ መጠን Eና የንግድ ባሕሪ ያለው Eቃ” ማለት ከግል ወይም ከቤተሰብ
ፍጆታ በላይ የሆነና በሽያጭ ወይም በሌላ ማናቸውም መንገድ ጥቅም ላይ
በማዋል ትርፍ ሊያስገኝ የሚችል Eቃ ነው፡፡
19) “የመንገደኛ ጓዝ” ማለት መንገደኛው ከራሱ ጋር ይዞት የሚመጣው የግል
Eና የቤት ውስጥ መገልገያ Eቃ ነው፡፡
20) “ሰነድ” ማለት ለጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aፈፃፀም በAካል ወይም
በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚቀርብ ማናቸውም ደረሰኝ፣ ቅጽ ወይም የጽሑፍ
ማስረጃ ሲሆን፣ መዝገብንም ይጨምራል፡፡
21) “Aባሪ ሰነዶች” ማለት በሕግ ወይም በባለሥልጣኑ በተወሰነው መሠረት
ከጉምሩክ ዲክላራሲዮን ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ማናቸውም ሰነዶች ናቸው፡
22) “Aዋጅ” ማለት የጉምሩክ Aዋጅ ቁጥር 622/2001 ነው፡፡
23) “ባለሥልጣን” ማለት የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ነው፡፡

3. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ መመሪያ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ለባለሥልጣኑ በሚያቀርብ በማናቸውም
መግለጫ Aቅራቢ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት
የኤሌክትሮኒክስ የዲክላራሲዮን Aቀራረብ

4. ፈቃድ ስለማግኘት
1. ማንኛውም መግለጫ Aቅራቢ ወደ Aገር ስለሚገቡ ወይም ከAገር ስለሚወጡ
ወይም ለስሚተላለፉ Eቃዎች የጉምሩክ ዲክላራሲዮን በኤሌክትሮኒክስ መንገድ
ማቅረብ ይችላል፡፡

5
2. በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 1 መሠረት በኤሌክትሮኒክ መንገድ ዲክለራሲዩን
ለማቅረብ መግለጫ Aቅራቢው በቅድሚያ ከባለሥልጣኑ የቀጥተኛ ነጋዴዎች
ግብዓት /D.T.I/ ፈቃድ ማግኘት Aለበት፡፡

5. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ስለመሙላት Eና ተቀባይነት ስለማግኘት


1) ማንኛውም መግለጫ Aቅራቢ በጉምሩክ የAውቶሜሽን /Aሲኩዳ ሲስተም/
ሥርዓት ውስጥ በሚገኘው የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ቅጽ ውሰጥ መረጃ
በጥንቃቄ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
2) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) መሠረት መግለጫ Aቅራቢው በኮምፒዩተሩ
ውስጥ በሚገኘው ኤሌክትሮኒክስ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ቅጽ የመዘገበው
መረጃ በባለሥልጣኑ ወዲያውኑ ተመዝግቦ የምዝገባ ቁጥር ይሰጠዋል፡፡
3) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) መሠረት የተመዘገበው የጉምሩክ ዲክላራሲዩን
ተቀባይነት የሚያገኘው ለጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aፈፃፀም Aስፈላጊ የሆኑ
መረጃዎች በጽሑፍ ወይም በኤሌክትሮኒክስ መንገድ መቅረባቸው ሲረጋገጥ
ይሆናል፡፡

6. የጉምሩክ ዲክላራሲዮንን ስለማረጋገጥና ስለማቅረብ


1) በኤሌክትሮኒክስ መንገድ የተመዘገቡ ዲክላራሲዮኖች Eና ደጋፊ ሠነዶች
ለጉምሩክ ሥነ ሥርዓት Aፈፃፀም ሲባል Oርጅናላቸው Eንዲቀርቡ በተጠየቀ
ጊዜ በበቂ ኮፒ ለባለሥልጣኑ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) መሠረት የሚቀርበው ዲክላራሲዮን
በዲክለራሲዮኑ ውስጥ የተገለፁት ፍሬ ነገሮች በሙሉ ትክክል Eና Eውነተኛ
ስለመሆናቸው Aቅራቢው ስሙን Eና ያቀረበበትን ቀን በመግለጽ በፊርማና
ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

7. ስለተጨማሪ ተግባራት
መግለጫ Aቅራቢው በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 6 ከተዘረዘሩት በተጨማሪ
የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
ሀ/ የክፍያ ማስታወቂያ /Assessment notice/ ያትማል፤

6
ለ/ በታተመው የክፍያ ማስታወቂያ መሠረት ክፍያውን በባንክ ወይም
ለባለሥልጣኑ ገንዘብ ያዥ ይፈጽማል፤
ሐ/ የክፍያ ደረሰኙን፣ ዲክላራሲዮኑን Eና Aባሪ ሰነዶችን በማያያዝ
ለባለሥልጣኑ ሰነድ መቀበያ ዴስክ /Face Vet/ ዲክላራሲዮኑ
በተመዘገበበት Eለት ወይም Eጅግ ቢዘገይ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ማቅረብ
Aለበት፤
መ/ በዚህ ንUስ Aንቀጽ ፊደል ተራ (ሐ) ላይ የተደነገገው Eንደተጠበቀ ሆኖ
መግለጫ Aቅራቢው በባለሥልጣኑ ተቀባይነት Aግኝቶ የምዝገባ ቁጥር የያዘ
ዲክላራሲዮን ለባለስልጣኑ ማቅረብ ካልቻለ ያላቀረበበትን በቂና Aሳማኝ
ምክንያት የምዝገባ ቁጥር ባገኘ በAምስት ቀናት ውስጥ በጽሑፍ
ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ Aለበት፡፡

8. የመግለጫ Aቅራቢው ኃላፊነት


ማንኛውም መግለጫ Aቅራቢ ለጉምሩክ ስነ ስርዓት Aፈፃፀም፣
1) በሚያቀርበው ዲክላራሲዮኑ ላይ የሚገኙት የመረጃ ሳጥኖች በሙሉ በትክክል
መሞላታቸውን የማረጋገጥ፣
2) በሚያቀርበው የኤሌክትሮኒክስ ዲክላራሲዮን Eና የወረቀት ቅጂዎች (Soft &
Hard Copy) ላይ የተገለፁት መረጃዎች Eና Aባሪ ሰነዶች ትክክለኛ
መሆናቸውን የማረጋገጥ፣
3) ዲክላራሲዮን የቀረበበት Eቃ ገደብ የተደረገበት ከሆነ ከሚመለከተው
የተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት ፈቃድ ስለማግኘቱ የማረጋገጥ፣
4) ዲክላራሲዮን የቀረበበት Eቃ ያልተከለከለ ስለመሆኑ የማረጋገጥ፣
5) ለባለሥልጣኑ በቀረበው ዲክላራሲዮን ላይ የተገለፀው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ
Eንዲሁም ሌሎች ክፍያዎች በትክክል ስለመስፈራቸው Eና ክፍያውም
በትክክል ስለመፈፀሙ የማረጋገጥ፣
ኃላፊነትና ግዴታ Aለበት፡፡

7
9. የተሳሳተ መረጃ ማስገባት ስለሚያስከትለው ተጠያቂነት
መግለጫ Aቅራቢው በኤሌክትሮኒክ ዲክላራሲዮን ቅጽ ውስጥ በጫነው መረጃ
ስህተት ቢገኝበት በቂና Aሳማኝ ምክንያት ካላቀረበ በስተቀር በጉምሩክ ስነ ስርዓት
Aስፈፃሚዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

10. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ስለማሻሻል


1. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ተመዝግቦ የምዝገባ ቁጥር ቢያገኝም የጉምሩክ ቀረጥና
ታክስ ከመሰላቱ /Assessment/ በፊት መግለጫ Aቅራቢው ዲክላራሲዮኑን
ሊያሻሽል ይችላል፡፡
2. የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ 1 ድንጋጌ Eንደተጠበቀ ሆኖ የጉምሩክ ቀረጥና
ታክስ ከተሰላ በኋላ የሚቀርብ የዲክለራሲዮን ማሻሻያ ጥያቄ ተፈፃሚ
የሚሆነው በEቃው ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ስለሚፈፀምበት ሁኔታ
የስጋት ሥራ Aመራርን መሰረት ተደርጐ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የሆነ
Eንደሆነ Eና በባለሥልጣኑ ብቻ ነው፡፡

11. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን ስለመሰረዝ


1) በባለሥልጣኑ ተቀባይነት Aግኝቶ የምዝገባ ቁጥር የያዘ ዲክላራሲዮን የምዝገባ
ቁጥር ካገኘበት ቀን Aንስቶ Eስከ Aምስት ቀናት ድረስ ቀጣዩ የጉምሩክ ሥነ
ሥርዓት ካልተፈፀመበት ዲክላራሲዮኑ በገቢ ወይም ወጪ Eቃዎች ቡድን
Aስተባባሪ ሊሰረዝ ይችላል፡፡
2) የዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ Aንድ ድንጋጌ ቢኖርም የጉምሩክ ስነ ስርዓት
ሳይፈፀምበት Eንዲሰረዝ የተደረገውን ዲክላራሲዮን መግለጫ Aቅራቢው
ቀጣዩን ስነ ስርዓት መፈፀም ያልቻለበትን ሁኔታ በበቂ ምክንያት ካላስረዳ በቀር
የባለሥልጣኑን ሥራ በማሰናከል Aግባብነት ባለው ሕግ መሠረት ተጠያቂ
ይሆናል፡፡

8
ክፍል ሶስት
የጉምሩክ ዲክላራሲዮን በቃልና በAካል Eንቅስቃሴ
ስለሚቀርብበት ሁኔታ

12. መሠረት
ማንኛውም ወደ Aገር የሚገባ ወይም ከAገር የሚወጣ መንገደኛ ስለያዘው Eቃ
በAካል Eንቅስቃሴ፣ በቃል ወይም በጽሑፍ የጉምሩክ ዲክላራሲዮን የማቅረብ ወይም
የመፈፀም ግዴታ Aለበት፡፡

13. በቃል ወይም በAካል Eንቅስቃሴ ዲክለራሲዮን ስለማቅረብ


ማንኛውም Aለም Aቀፍ መንገደኛ Eቃ ያልያዘ ስለመሆኑ ወይም የያዘው Eቃ
ቀረጥና ታክስ የሚከፈልበት ወይም የማይከፈልበት ስለመሆኑ በቃል ወይም/Eና
በAረንጓዴ ወይም ቀይ ማለፊያ በኩል በማለፍ የሚያደርገው Aካላዊ Eንቅስቃሴ
የጉምሩክ ዲክለራሲዮን Eንዳቀረበ ይቆጠራል፡፡

14. Aረንጓዴ ማለፊያ


ማንኛውም መንገደኛ Eቃ ካልያዘ ወይም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን Eቃዎች
መያዙን በቃል በማረጋገጥ ወይም/Eና በAረንጓዴ ማለፊያ በኩል ማለፍ ይችላል፡፡
ሀ/ Aንድ CD ማጫወቻ ያለው ቴፕ ሪከርደር ወይም Aንድ ሬዲዮ፣
ለ/ Aንድ ፎቶ ካሜራ፣
ሐ/ Aንድ ሞባይል ቀፎ፣
መ/ ከሁለት ሊትር ያልበለጠ ማንኛውም የAልኮል መጠጥ፣
ሠ/ በቁጥር ከAራት መቶ ወይም ከሃያ ፓኬት ያልበለጡ ሲጋራዎች፣
ረ/ የንግድ መጠን የሌላቸውና ዓይነታቸው የተለያዩ መጽሔቶች፣
መጽሐፍቶች፣ ምስልና ድምጽ የተቀረፀባቸው ካሴቶችና ሲዲዎች፣
ሰ/ ተመላላሽ መንገደኛ ላልሆነ ከ25A ግራም ያልበለጡ፣ ተመላላሽ መንደገኛ
ከ50 ግራም ያልበለጡ የግል ጌጣጌጦች፣

9
ሸ/ ጠቅላላ ዋጋው ወይም ዋጋቸው ከብር 1000/Aንድ ሸህ/ ያልበለጡ
ሽቶዎች፣
ቀ/ በሐኪም ትEዛዝ ለግል ጥቅም የሚውሉ መድሃኒቶች፣
በ/ የንግድ መጠን የሌላቸው Aልባሳት Eና ሌሎች የግል መገልገያ Eቃዎች፡፡

15. ቀይ ማለፊያ
ማንኛውም መንገደኛ በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 12 (2) ከተዘረዘሩት ውጪ Eቃ ከያዘ
በቀይ ማለፊያ በኩል በማለፍ በያዛቸው Eቃዎች ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት
መፈፀም ይኖርበታል፡፡

16. መንገደኞችና ጓዞችን ስለመፈተሽ


1) ባለሥልጣኑ በዚህ መመሪያ Aንቀጽ 12 የተመለከተው ቢኖርም የተከለከለ፣
ገደብ የተደረገበትና ለንግድ ዓላማ የመጣ Eቃ ወይም የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ
የሚከፈልባቸው Eቃዎች ይዟል ብሎ የሚጠረጥረውን ማንኛውንም መንገደኛ
በማስቆም መፈተሽ ይችላል፡፡
2) ባለሥልጣኑ በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) መሠረት በፍተሻ በያዘው Eቃና
በመንገደኛው ላይ ሕጋዊ Eርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡

17. ስለውጭ ምንዛሪ


1) ማንኛውም መንገደኛ ወደ Aገር ሲገባ የያዘው የውጭ ምንዛሪ የIትዮጵያ
ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ላይ ከተገለፀው መጠን በላይ ከሆነ
ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው ዲክላራሲዮን ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
2) በዚህ መመሪያ ንUስ Aንቀጽ Aንድ መሠረት የያዘውን የውጭ ምንዛሬ
Aስመዝግቦ ያስገባ መንገደኛ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላይ በተገለፀው ጊዜ
ውስጥ መልሶ ሲወጣ ገንዘቡን ያስመዘገቡበትን ዲክላራሲዮን ካላቀረበ በስተቀር
ሊያወጣ Aይችልም፡፡
3) ማንኛውም መንገደኛ ወደ Aገር ሲገባ የውጭ ምንዛሬ ባስመዘገበበት የጉምሩክ
ዲክለራሲዮን በተደጋጋሚ የጉዞ ምልልስ ለመጠቀም Aይችልም፡፡

10
ክፍል Aራት
የጉምሩክ ዲክላራሲዮን በጽሑፍ ስለማይቀርብባቸው Eቃዎች

18. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን የማይቀርብባቸው ገቢ Eቃዎች


1) በዚህ መመሪያ መሠረት የጉምሩክ ዲክላራሲዮን በጽሑፍ የማይቀርብባቸው
Eቃዎች፣
ሀ/ የግል ወይም የቤት ውስጥ መገልገያ Eቃዎች፣
ለ/ የንግድ ማስተዋወቂያና የናሙና Eቃዎች፣
ሐ/ የግል ጌጣጌጦች፣
መ/ በህግ ለተመዘገቡ መንግስታዊ Eና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
ለሃይማኖትና ሌሎች ማኀበራዊ ድርጅቶች በስጦታ የሚላኩ፣ የንግድ
መጠን የሌላቸው፣ ያልተከለከሉ Eና ጠቅላላ ዋጋቸው (FOB) ከብር
10,000 /Aስር ሺህ ብር/ ያልበለጡ የስጦታ ሰርተፊኬት Eና ለጉምሩክ
Aገልግሎት ብቻ (for customs purpose only) የሚል ጠቅላላ ዋጋቸውን
የሚያመለክት Iንቮይስ ያላቸው Eቃዎች፣
ናቸው፡፡
2) በዚህ Aንቀጽ ንUስ Aንቀጽ (1) መሠረት ወደ Aገር የሚገቡ Eቃዎች
ባለሥልጣኑ በሚያዘጋጀው ሰነድ /ማኒፌስት/ Eየተመዘገቡ Eንደ Aግባቡ
ቀረጥና ታክስ Eየተከፈለባቸው ወይም ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው ሊገቡ
ይችላሉ፡፡

19. የጉምሩክ ዲክላራሲዮን የማይቀርብባቸው ወጪ Eቃዎች


የሚከተሉት Eቃዎች Eንደ Aግባብነቱ በማኒፌስት Eየተመዘገቡ ከAገር ሊወጡ
ይችላሉ፡፡
1. ለናሙና Eና ለስጦታ የሚላኩ Eና መጠናቸው ወይም ብዛታቸው የውጭ
ምንዛሬ ሳያስገቡ Eንዲወጡ በብሔራዊ ባንክ ወይም ባንኩ ስልጣን የሰጠው
ባንክ የሚፈቅድላቸው፣

11
2. የብሔራዊ ባንክ በፈቀደው መጠን ተጓዦች ለራሳቸው ጥቅም Eንዲውሉ
ይዘዋቸው የሚወጡ፣
3. የማጓጓዣ ኃላፊዎች፣ ረዳቶቻቸው Eና መንገደኞች በጉዞ ወቅት
የሚጠቀሙባቸው፣

ክፍል Aምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

20. ስለ የግልና የቤት ውስጥ መገልገያ Eቃ


በዚህ መመሪያ መሠረት ወደ Aገር የሚገቡ የግልና የቤት ውስጥ መገልገያ
Eቃዎች ዓይነት፣ ብዛት Eና ዋጋ የባለሥልጣኑ የዋጋ መረጃ ማደራጃ Eና ታሪፍ
ምደባ የሥራ ሂደት በሚያወጣው የAነስተኛ Eቃዎች ዋጋ መረጃ (Low Value
Goods) መሠረት ይሆናል፡፡

21. Aስተዳደራዊ Eርምጃ


ማንኛውም ከባለሥልጣኑ ቀጥተኛ የነጋዴ ግብAት (D.T.I) ፈቃድ የተሰጠው ሰው
በዚህ መመሪያ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ተላልፎ ከተገኘ Aግባብ ባለው ሕግ
በወንጀል ተጠያቂነቱ Eንደተጠበቀ ሆኖ ባለሥልጣኑ ፈቃዱን ሊሰርዝበት ይችላል፡፡

22. በልዩነት ስለተገኘ Eቃ


በዚህ መመሪያ ላይ ከተገለፀው መጠን በላይ ወይም ዓይነት ውጪ ይዞ የተገኘ
ማንኛውም መንገደኛ በባለሥልጣኑ Aስተዳደራዊ መመሪያ መሠረት ውሣኔ
Eንዲሰጠው ይደረጋል፡፡

23. የተሻሩና ተፈፃሚነት የሌላቸው መመሪያዎች


ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረኑ ሌሎች መመሪያዎች Eና ልማዳዊ Aሰራሮች በዚህ
መመሪያ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት Aይኖራቸውም፡፡

12
24. መመሪያውን ስለማሻሻል
ይህ መመሪያ Eንደ Aስፈላጊነቱ በባለሥልጣኑ ሊሻሻል ይችላል፡፡

25. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ


ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተፈርሞ ከወጣበት Eለት ጀምሮ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

Aዲስ Aበባ _______________ ቀን 2001 ዓ.ም.

መላኩ ፈንታ
የIትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን
ዋና ዳይሬክተር

13

You might also like