You are on page 1of 8

Abrham Yohanes Law Corner

ሇግሌ መገሌገያ እንዱውለ ወዯ አገር


የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ
ዕቃዎችን ሇመወሰን የወጣ መመሪያ
ቁጥር 923/2014

የገንዘብ ሚኒስቴር
ነሐሴ 2014
Abrham Yohanes Law Corner
ሇግሌ መገሌገያ የሚውለ ዕቃዎች ወዯ አገር የሚገቡበትን ሁኔታ ሇመወሰን የወጣ
መመሪያ ቁጥር 923/2014

የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች ወዯአገር የሚገቡበትን ሁኔታ የሚወስነው በሥራ ሊይ ያሇው


መመሪያ ሇሕገ ወጥ ንግዴ በር የከፈተ እና አገሌግልት አሰጣጡ ሊይ አለታዊ ተፅዕኖ
ያሳዯረ በመሆኑ ዓሇምአቀፍ አሠራሮችን በተከተሇ አኳኋን መመሪያውን አሻሽል
ማውጣት በማስፈሇጉ፤

በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (በአዋጅ ቁጥር 1160/2011 እንዯተሻሻሇው) አንቀፅ


33(2) የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው ወዯ አገር የሚገቡበት እና
ከአገር የሚወጡበትን ሁኔታ እንዱወስን ሇገንዘብ ሚኒስቴር ሥሌጣን የተሰጠው
በመሆኑ፤

የገንዘብ ሚኒስቴር የሚከተሇውን መመሪያ አውጥቷሌ፡፡

ጠቅሊሊ ዴንጋጌ
ክፍሌ አንዴ
1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “ሇግሌ መገሌገያ እንዱውለ ወዯ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር


የሚወጡ ዕቃዎችን ሇመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 923/2014” ተብል ሉጠቀስ
ይችሊሌ፡፡

2. ትርጉም

የቃለ አገባብ ላሊ ትርጉም የሚያሰጠው ካሌሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1) “ሇንግዴ የማይውሌ ዕቃ” ማሇት ጠቅሊሊ ብዛቱ በዚህ መመሪያ ከተወሰነው


መጠን ያሌበሇጠ፤ ሇባሇመብቱ ወይም ሇቤተሰቡ የግሌ መገሌገያ ወይም ፍጆታ
የሚውሌ ባሇመብቱ ይዞት ወይም ከባሇመብቱ ተሇይቶ የሚመጣ ዕቃ ነው፡፡

2) “የግሌ መገሌገያ ዕቃ” ማሇት ጠቅሊሊ ብዛቱ በዚህ መመሪያ ከተወሰነው መጠን
የማይበሌጥ፤ ሇባሇቤቱ ወይም ሇቤተሰቡ የግሌ መገሌገያ ወይም ፍጆታ
እንዱውሌ በዚህ መመሪያ የተፈቀዯሇት ባሇመብት ይዞት ወይም ከባሇመብቱ
ተሇይቶ ወዯአገር የሚገባ ወይም ከአገር የሚወጣ ዕቃ ነው፡፡

1
Abrham Yohanes Law Corner
3) “የስጦታ ዕቃ” ማሇት ማንኛውም በውጭ አገር ያሇ ሰው ወይም ዴርጅት
ኢትዮጵያ ውስጥ ሇሚገኝ ቤተሰብ፣ ዘመዴ፤ ጓዯኛ ወይም ዴርጅት የሚሌከው
የግሌ መገሌገያ ዕቃ ነው፡፡

4) “መንገዯኛ” ማሇት ማንኛውም በየብስ ወይም በዓሇምአቀፍ የአየር ማረፊያዎች


በኩሌ ወዯ ኢትዮጵያ የሚገባ ወይም ከኢትዮጵያ የሚወጣ ሰው ሲሆን
በማጓጓዣው ሊይ መዯበኛ ሥራቸውን እየሰሩ ያለ የትራንስፖርት አገሌግልት
ሰጪ ዴርጅት ሠራተኞችን እና ተመሊሊሽ ነጋዳዎችን አይጨምርም፡፡

5) “ተመሊሽ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ” ማሇት ከኢትዮጵያ ወጥቶ


ከአንዴ አመት ሊሊነሰ ጊዜ በውጭ አገር የሥራና የመኖሪያ ፍቃዴ አግኝቶ
ሲኖር የነበረ ወይም በስዯት ውጭ አገር የቆየ ሆኖ ጓዙን ጠቅሌል ኢትዮጵያ
ውስጥ ሇመኖር የሚመሇስ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

6) “የውጭ አገር ባሇሙያ” ማሇት በተሇያዩ መንግሥታዊ መ/ቤቶች፣ መንግሥታዊ


የሌማት ዴርጅቶች፣ መንግሥታዊ ያሌሆኑ ዓሇምአቀፍ፣ አህጉርአቀፍ ወይም
አገር አቀፍ ዴርጅቶች፣ ሕጋዊ ማህበራት፣ የግሌ ዴርጅቶች፣ የመንግሥትና
የግሌ የጋራ ዴርጅቶች ውስጥ በሙያው ሇማገሌገሌ በሕጋዊ መንገዴ ተቀጥሮ
ወይም በላሊ ሕጋዊ ስምምነት ወዯ ኢትዮጵያ የሚመጣ ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ
ወይም የውጭ አገር ዜጋ ነው፡፡

7) “ወጥ የሆነ የታሪፍ መጣኔ” ማሇት በጉምሩክ ታሪፍ ዯንብ ምዕራፍ 98


አወቃቀር ውስጥ ሇተቀመጠው የዕቃ አይነት መግሇጫ የተሰጠው ሌዩ የታሪፍ
መጣኔ ነው፡፡

8) “ከስዯት ተመሊሽ” ማሇት በተሇያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ወጥቶ በስዯት


የኖረና በመንግሥት ስምምነት ወይም ከነበረበት አገር ተገድ ወዯ ኢትዮጵያ
የሚመሇስ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

9) “ኮሚሽን” ማሇት የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ነው፡፡

10) “ሚኒስቴር” ማሇት የገንዘብ ሚኒስቴር ነው፡፡

11) “አዋጅ” ማሇት የጉምሩክ አዋጅ ነው፡፡

12) በዚህ መመሪያ ጥቅም ሊይ የዋለ ላልች ቃሊትና ሀረጎች በአዋጁ የተሰጣቸውን
ትርጓሜ ይይዛለ፡፡

2
Abrham Yohanes Law Corner
ክፍሌ ሁሇት
ተፈሊጊ ማስረጃዎች እና ሇግሌ መገሌገያ የሚፈቀደ ዕቃዎች

3. ማስረጃዎች
ማንኛውም መንገዯኛ፣ ተመሊሽ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ ፣ የውጭ
አገር ባሇሙያ እና የስጦታ ዕቃ ከውጭ አገር የተሊከሇት ሰው በዚህ መመሪያ
የተመሇከተው መብት ተጠቃሚ መሆን የሚችሇው የሚከተለትን ማስረጃዎች
ሲያቀርብ ይሆናሌ፤

1/ መንገዯኛ፣

ሀ) ፓስፖርት ወይም መንገዯኛ መሆኑን የሚያሳይ ላሊ የጉዞ ሰነዴ፣


ሇ) በዚህ መመሪያ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆኖ ወዯ አገር እንዱገባ ከተፈቀዯው
ውጭ ሇሆኑ ዕቃዎች ዝርዝር መግሇጫና የዋጋ ሰነዴ፣

2/ ተመሊሽ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ

ሀ) ፓስፖርት ወይም ላሊ የጉዞ ሰነዴ፣


ሇ) አንዴ ዓመትና ከዚያ በሊይ ውጭ አገር የኖረ መሆኑን የሚያሳይ ከአገር
ሲወጣ እና ወዯአገር ሲመሇስ አግባብ ባሇው የመንግሥት አካሌ በፓሰፓርቱ
ሊይ የሰፈረ ማረጋገጫ ወይም በሚኖርበት አገር ከሚገኘው የኢትዮጵያ
ኢምባሲ ወይም ቆንስሊ ጽ/ቤት የተሰጠና በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር
የተረጋገጠ ማስረጃ፣
ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2(ሇ) የተገሇፀው እንዯተጠበቀ ሆኖ በተገሇፀው
ቆይታ ወቅት መካከሌ ወዯ ኢትዮጵያ መጥቶ ከዘጠና ቀናትና በሊይ አገር
ውስጥ ያሌቆየ/ች ስሇመሆኑ የሚቀርብ ማስረጃ፣
መ) የዕቃዎች ዝርዝርና ዋጋ መግሇጫ፣
ሠ) ዕቃው አንዴ ዓመትና ከዚያ በሊይ ያገሇገሇ ስሇመሆኑ በባሇመብቱ የቀረበ
ማረጋገጫ፣
ረ) ከስዯት ተመሊሾች ከስዯት ተመሊሽ ስሇመሆናቸው የሚያረጋግጥ
ከሚመሇከተው የመንግሥት አካሌ የቀረበ ማስረጃ፤

3/ የውጭ አገር ባሇሙያ

አግባብ ካሇው የመንግሥት፣ የግሌ ወይም መንግሥታዊ ያሌሆነ ዴርጅት


ወይም አሇምአቀፍ ተቋም ጋር ያዯረገውን በመስሪያ ቤቱ የበሊይ ኃሊፊ
የተረጋገጠ ውሌ፤

3
Abrham Yohanes Law Corner
4/ የስጦታ ዕቃ ከወጭ አገር የተሊከሇት ሰው

ማንኛውም የኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ከውጭ አገር በስጦታ የመጣሇትን


የዕቃ ዝርዝር መግሇጫ፣ የተሊከውን ዕቃ ዋጋ ሰነዴ፣ የመኖሪያ መታወቂያ እና
የሊከሇትን ሰው ማንነት የሚገሌጽ ማስረጃ፤

4. ሇግሌ መገሌገያ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆነው የሚገቡ ዕቃዎች

1/ ማንኛውም መንገዯኛ የሚከተለትን ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሌ ሇግሌ


መገሌገያነት ወዯ አገር ውስጥ ማስገባት ይችሊሌ፤
ተ.ቁ. የዕቃ ዝርዝር መሇኪያ የሚፈቀዯው መጠን
1 ሲጋራ ግራም 200
2 ሲጋር በቁጥር 20
3 ብትን ትንባሆ ግራም 250
4 የአሌኮሌ መጠጥ ሉትር 2
5 ሇስሊሳ ሽቶ ሚሉ ሉትር 500
6 ሽቶ ሚሉ ሉትር 500
7 ሞባይሌ በቁጥር 2
8 ሊፕቶፕ በቁጥር 1
9 የፎቶ ግራፍ ካሜራ በቁጥር 1
10 ዊሌቸር በቁጥር 1
11 የእጅ ሳዓት በቁጥር 1
12 የጺም ወይም የጸጉር መሊጫ በቁጥር 1
13 የጸጉር ማዴረቂያ በቁጥር 1
14 የጸጉር መተኮሻ በቁጥር 1

15. መንገዯኛው የሚጠቀምባቸው በቁጥር


ሇአንዴ ሰው
መዴሃኒቶች እና የህክምና
በሚያስፈሌግ
መገሌገያዎች
መጠን

16. በጉዞ ወቅት ጥቅም ሊይ በቁጥር


ሇአንዴ ቤተሰብ
የሚውለ እና ሇቤተሰብ
ከሚያስፈሌገው
የሚያገሇግለ፤ሌብሶች፤ጫማዎች
ያሌበሇጠ
እና የጽዲት እቃዎች
16
4
Abrham Yohanes Law Corner

2/ ማንኛውም ተመሊሽ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ

ሀ) ተሽከርካሪን ሳይጨምር ቢያንስ ሇአስራ ሁሇት ወራት ሲገሇገሌባቸው


የነበሩትን የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆኖ ወዯ
አገር ውስጥ ማስገባት ይችሊሌ፡፡

ሇ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2(ሀ) የተገሇፀው እንዯተጠበቀ ሆኖ


ባሇመብቱ የሚያስመጣው የግሌ መገሌገያ ኤላክትሮኒክስ የሆነ እንዯሆነ
ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ሆኖ ወዯ አገር ማስገባት የሚችሇው ከእያንዲንደ
የኤላክትሮንስ ዓይነት አንዴ ብቻ ነው፡፡

3/ ማንኛውም የግሌ መገሌገያ ዕቃ በስጦታ የተሇከሇት ስው፣

ሀ) የግብር ከፋይ መሇያ ቁጥር የላሇው ከሆነ ዕቃው ወዯ አገር በሚገባበት


ወቅት ሉከፈሌ ከሚገባው የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ በተጨማሪ የጉምሩክ
ቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ ሊይ የሚሰሊ 30 በመቶ የገቢ ግብር ይከፍሊሌ፡፡

ሇ) በስጦታ የሚሊክሇት ዕቃ ዋጋ የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ መሰረት ከሆነው


እስከ ማስጫኛ ወዯብ ዴረስ ካሇው ዋጋ ( ኤፍ.ኦ.ቢ) ከ1000 የአሜሪካን
ድሊር ሉበሌጥ አይችሌም፡፡

ሐ) በአንዴ አመት ውስጥ ከሁሇት ጊዜ በሊይ ስጦታ ሉቀበሌ አይችሌም፡፡

4/ ሇንግዴ ዓሊማ የማይውለ ወዯ ውጭ የሚሊኩ ሇግሌ ፍጆታ የሚውለ የአገር


ውስጥ ምርቶች የንግዴና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ
መሠረት ይስተናገዲለ፡፡

ክፍሌ ሶስት
የግሌ መገሌገያ ዕቃ የታሪፍ መጣኔ እና የዋጋ አተመመን

5. ወጥ የሆነ የታሪፍ መጣኔ እና የዋጋ አተማመን

1/ በዚህ መመሪያ ከተፈቀዯው በሊይ ከመንገዯኛ ጋር የሚመጡ ሇንግዴ የማይውለ


የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ የሚከፈሌባቸው ሲሆን፣ ወጥ በሆነ
የታሪፍ መጣኔ ቀረጥና ታክስ ተከፍልባቸው ይስተናገዲለ፡፡

5
Abrham Yohanes Law Corner
2/ ሇንግዴ የማይውለ ወዯ አገር የሚገቡ የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች የቀረጥ መጣኔ
በጉምሩክ ታሪፍ ምዕራፍ 98 መሠረት ይወሰናሌ፡፡

3/ ኮሚሽኑ ከአጠቃሊይ የዋጋ አተማመን መርህ ጋር በማጣጣም ሇንግዴ የማይውለ


የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች የቀረጥ ማስከፈያ መነሻ ዋጋ ያዘጋጃሌ፡፡

6. ወጥ በሆነ የታሪፍ መጣኔ የማይስተናገደ ዕቃዎች

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ወጥ በሆነ የታሪፍ መጣኔ ሉስተናገደ አይችለም፤

1/ ባሇመብቱ ሇራሱ እና ሇቤተሰቡ ጥቅም ሊይ ሉያውሇው ከሚችሇው መጠን በሊይ


በተዯጋጋሚ የሚያስመጣቸው በስጋት ሥራ አመራር ክትትሌ የተያዙ ዕቃዎች፣

2/ ሇንግዴ ሉውለ የሚችለ ዕቃዎች፣

7. የስጋት ሥራ አመራር

1/ ኮሚሽኑ ወዯ አገር ሇሚገቡ ሰዎችና ዕቃዎች የሚሰጠውን ቀሌጣፋ አገሌግልት


እና በሂዯቱ ሊይ የሚዯረገውን ቁጥጥር ሇማመጣጠን የሚያስችሌ ዓሇምአቀፍ
አሠራርን የተከተሇ ዘመናዊ የስጋት ሥራ አመራርን ተግባራዊ ያዯርጋሌ፡፡

2/ ሇዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 አፈፃፀም ሲባሌ ሁለም የአየር ትራንስፖርት


አገሌገልት ሰጪ ዴርጅቶች የመንገዯኞችን ዝርዝር የሚገሌፅ መረጃ አውሮፕሊን
ከማረፉ በፊት ሇኮሚሽኑ መስጠት ይኖርባቸዋሌ፡፡

3/ የኢትዮጵያ ሲቪሌ አቪዬሽን ባሇሥሌጣን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2


መሠረት ሇጉምሩክ ቁጥጥርና የስጋት ሥራ አመራር የሚያስፈሇጉ መንገዯኛን
የሚመሇከቱ መረጃዎችን በማይሰጡ አጓጓዦች ሊይ ከጉምሩክ ኮሚሽን
በሚዯርሰው መረጃ መሠረት እርምጃ ይወስዲሌ፡፡

+251-911-190-299
6
Abrham Yohanes Law Corner
ክፍሌ አራት
ሌዩ ሌዩ ዴንጋጌዎች
8. ገዯብ

1/ ማንኛውም ሇንግዴ ዓሊማ የማይውሌ የግሌ መገሌገያ ዕቃ ወዯአገር የሚያስገባ


ተመሊሽ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውሌዯ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጭ አገር ሰራተኛ
የሚያስገባቸውን ዕቃዎች በሙለ በአንዴ ሰነዴ አጠቃል ወዯ ኢትዮጵያ በገባ
በስዴስት ወር ጊዜ ውስጥ ወዯአገር ማስገባት አሇበት፡፡

2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተመሇከተው ባሇመብት የግሌ መገሌገያ


ዕቃዎቹን በአየር መንገዴ እና በየብስ አንዴ ጊዜ የሚያስገባ ሆኖ ከሁሇቱ
የማስጫኛ ዘዳዎች በአንደ ብቻ መጠቀም ከፈሇገ በየብስ ወይም በአየር መንገዴ
ሁሇት ጊዜ ብቻ ማስገባት አሇበት፡፡ ሆኖም በዚህ መመሪያ በተፈቀዯው መብት
ተጠቃሚ ሉሆን የሚችሇው ሇአንዴ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

9. ክሌከሊ
ማንኛውም መንገዯኛ በዚህ መመሪያ ከተፈቀዯው ውጪ የንግዴ ዕቃዎችን ወዯ
አገር ማስገባት አይችሌም፡፡

10. የተሻረ መመሪያ ወይም አሠራር

1/ የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች መመሪያ ቁጥር 51/2010 ከነማሻሻያው በዚህ መመሪያ


ተሽሯሌ፡፡
2/ ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ፣ አሠራርና ሌማዴ በዚህ
መመሪያ በተሸፈኑ ጉዲዮች ሊይ ተፈፃሚነት አይኖረውም፡፡

3/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ቢኖርም ይህ መመሪያ በላሊ ሕግ መሠረት


የተፈቀዯን የግሌ መገሌገያ ዕቃዎች የቀረጥና ታክስ ነፃ መብት አያስቀርም፡፡

11. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ


ይህ መመሪያ ከነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናሌ፡፡

አዱስ አበባ ነሐሴ 23 ቀን 2014ዓ.ም

አህመዴ ሺዳ
የገንዘብ ሚኒስትር

You might also like