You are on page 1of 71

በጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ትራንዚት አሰራር ስርአት የስልጠና ሰነድ

2013 ዓ.ም
1
የጉምሩክ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም
የጉምሩክ ሰነ -ስርዓት አፈፃፀም ሦስት ንዑሳን ክፍሎች አሉት፡-

የጉምሩክ ትራንዚት ስነ-ስርዓት አፈፃፀም ፣

የጉምሩክ መጋዘን ስነ-ስርዓት አፈፃፀም እና

የጉምሩክ ዕቃ አወጣጥ ስነ-ስርዓት አፈፃፀም ናቸው፡፡

2
የጉምሩክ ትራንዚት ሥነ-ሥርዓት አፈጻጸም

3
የሥልጠናው ይዘት
1) መግቢያ
2) የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት (Inward Transit)
3) የተላላፊ ዕቃዎች (Through Transit)
4) የአገር ውስጥ ትራንዚት (Interior Transit)
5) የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት (Outward Transit)
6) የጉምሩክ ትራንዚት ኦፕሬሽን(customs transit operation)
7) የጉምሩክ ትራንዚት ስነ-ስርዓት አለማክበር(Failure to observe
customs transit procedures

4
የሚጠበቁ ውጤቶች
ሁሉም የጉምሩክ ትራንዚት ዓይነቶች መለየት መቻል

ለትራንዚት ፈቃድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን መለየት መቻል

በጉምሩክ መነሻ ጣቢያዎች፣ በመተላለፊያ መንገዶች የሚገኙ ጣቢያዎች


እና የጉምሩክ መዳረሻ ጣቢያዎች ላይ የሚሰሩ የሥራ ድርሻዎች መለየት
መቻል

5
1) መግቢያ
ሀ. ትርጉም
•“የጉምሩክ ትራንዚት” ማለት ዕቃዎች በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆነው ከአንድ
የጉምሩክ ጣቢያ ወደ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ የሚተላለፍበት የጉምሩክ ሥነ-
ሥርዓት ነው፡፡ 859/2014 (2/37)
•“የትራንዚት ዕቃ” ማለት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ያላጠናቀቀ በጉምሩክ
ቁጥጥር ሥር ሆኖ ከአንድ የጉምሩክ ጣቢያ ወደ ሌላ የጉምሩክ ጣቢያ በተፈቀደ
መስመር የሚጓጓዝ ዕቃ ሲሆን በኮሚሽኑ በተፈቀደ ቦታ የሚጫንና የሚራገፍ
ዕቃን ይጨምራል፡፡ (መ.168(1))
• “የጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀም” ማለት የትራንዚት ዕቃ በጉምሩክ ቁጥጥር
ሥር ሆኖ ከጉምሩክ መነሻ ጣቢያ እስከ መድረሻ ጣቢያ ወይም ወደተፈቀደ ቦታ
የሚተላለፍበት ሂደት ነው፡፡ (መ.168(2))
6
ትርጉም… የቀጠለ
• “የትራንዚት መነሻ ቦታ” ማለት የጉምሩክ ትራንዚት ሥነ-ሥርዓት
የሚጀመርበት የጉምሩክ ቅጽ/ቤት ወይም ጣቢያ ወይም የተፈቀደ ቦታ
ሲሆን በአጎራባች አገራት ያሉ የኮሚሽኑን ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችን
ይጨምራል፤ (መ.168(3))
• “የትራንዚት ማጠናቀቂያ ቦታ” ማለት የጉምሩክ ትራንዚት ሥነ-ሥርዓት
የሚያበቃበት የጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም ጣቢያ ወይም የተፈቀደ
ቦታ ነው ፤ (መ.168(4))

7
ትርጉም… የቀጠለ
 መግቢያ በር ማለት የትራንዚት ዕቃ ወደ ጉምሩክ ክልል ተጓጉዞ የሚገባበት
በር ነው። (መ.168(5))
“የጉምሩክ ማሸጊያ” ማለት በኮሚሽኑ እውቅና የተሰጠው የትራንዚት ዕቃ
ደህንነት ለማስጠበቅ የሚረዳ የዕቃ መያዣወይም የጭነት ማጓጓዣ ማሸጊያ
ነው፡፡ (መ.168(6))

8
ትርጉም… የቀጠለ
“ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት” ማለት በማጓጓዣው ላይ የደረሰ ብልሽት
ወይም አደጋ ወይም በአጓጓዡ ላይ የደረሰ ከባድ ህመም ወይም የመንገድ
መዘጋት ወይም ክልከላ ወይም በፀጥታ ምክንያት የተፈጠረ የጉዞ ወይም
ተዛማጅ ሌላ ማንኛውም አስገዳጅ ሁኔታ ማለት ነው፡፡ (መ.168(7))
“ከአቅም በላይ ለሆነ ምክንያት የሚቀርብ ማስረጃ” ማለት በጉምሩክ
ትራንዚት አፈፃፀም ወቅት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ የገጠመው አጓጓዥ
ሁኔታውን በአቅራቢያው ለሚገኝ የኮሚሽኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ወይም
ጣቢያ ወይም ህግ አስከባሪ ወይም መስተዳደርወይም አግባብ ያለው አካል
አሳውቆ ከዚሁ አካል የተሰጠ የጽሑፍ ማረጋገጫ ነው፡፡ (መ.168(8))

9
ትርጉም… የቀጠለ
“ፖትሮሊንግ” ማለት የትራንዚት ዕቃ ከትራንዚት መተላለፊያ መሥመር
ውጭ ሲንቀሳቀስ ወይም ማጓጓዣው ጉዞውን ገትቶ ዕቃ ሲያራግፍ ወይም
ሲጭን ወይም ሌላ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲኖር የጉምሩክ ቁጥጥር ግብረ-ሃይል
ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ቁጥጥር የሚያደርግበት ሂደት ነው፡፡
(መ.168(9)።

10
ትርጉም… የቀጠለ
“የመተላለፊያ መስመር” ማለት በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ያሉ ገቢና ወጪ
ዕቃዎች እንዲጓጓዙበት በባለስልጣኑ የተወሰነ ማናቸውም መንገድ
ነው፤859/2006 (2/17)
“ማጓጓዣ” ማለት በየብስ፣ በአየር ወይም በውሃ ላይ ሰውን ወይም ዕቃን
የሚያጓጉዝ ማንኛውንም የመጓጓዣ ዘዴ ሲሆን እንስሳትን፣ የኤሌክትሪክ
መስመሮችንና ፈሳሽ ማስተላለፊያዎችን ይጨምራል፣ 859/2006 (2/15)
“የጉምሩክ ማቋረጫ” ማለት ሰውንና መጓጓዣን እንዲሁም የገቢ፣ የወጪና
ተላላፊ ዕቃዎችን ለማስገባት፣ ለማስወጣትና ለማሸጋገር የተፈቀደ የድንበር
መስመር ሲሆን ዓለም አቀፋዊ የድንበር ትራፊክ እንቅስቃሴ የሚፈጸምባቸውን
ሥፍራዎች ይጨምራል፣ 859/2006 (2/43)
11
ትርጉም… የቀጠለ
በጉምሩክ ትራንዚት ቁጥጥር ሥር ሲባል፤
ለትራንዚት ዕቃ ዋስትና ይያዛል

የትራንዚት ዕቃ በተፈቀደ መግቢያ/ መውጫና በተፈቀደ መሥመር ብቻ ይጓጓዛል

ዕቃው የተጫነበት ኮንቴነር /ተሸከርካሪ በሲል ይታሸጋል

በትራንዚት መሥመር ላይ በሚገኙ የጉምሩክ መቆጣጠሪያዎች ቁጥጥር ማድረግ

በፓትሮል ክትትል ማድረግ፣ ወዘተ ማለት ነው፡፡

12
ለ. የጉምሩክ ትራንዚት አስፈጻሚዎች
 የተፈቀደላቸው የዕቃ አስተላላፊዎች

 የመልቲ-ሞዳል ትራንስፖርት ኦፕሬተሮች

 የጉምሩክ አስተላላፊዎች /ትራንዚተሮች

 የፖርት/ ተርሚናል ኦፕሬተሮች

 የመርከብ ድርጅቶች እና የመርከብ ወኪሎች

 የትራንስፖርት ድርጅቶች

 የጭነት አቀናጆች (Consolidators)

 ኢንሹራንስ ድርጅቶች
13
ሐ. የጉምሩክ ትራንዚት ዓይነቶች
የገቢ ትራንዚት (Inward Transit)
National Customs
የወጪ ትራንዚት (Outward Transit)
Transit

የውስጥ ትራንዚት (Interior Transit)

In. Cu. Transit


የተላላፊ ትራንዚት (Through Transit)

14
2. የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት (Inward Transit)
ሀ. ትርጉም
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት ማለት የገቢ ዕቃዎች ከወደብ ወይም ከመግቢያ በር

ወደ ተፈቀደ ቦታ በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆኖ የሚተላለፍበት ሥርዓት ነው፡፡


 Mode of Declaration-------->IM8
 CPC------------------------>8100 800

15
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ
ዕቃዎች በሁለት ዓይነት መንገድ ይጓጓዛሉ፤- እነሱም
1)ዩኒ ሞዳል

•በዩኒሞዳል የሚጓጓዙ ዕቃዎች በዕቃ ዲክላራሲዮን አቅራቢ ወይም በወኪሉ ሙሉ


እውቅና ቀረጥና ታክስ በመክፈል ወይም በዋስትና መሰረት የሚደረጉ ጉዞዎች ማለት
ነው፡፡

NB:-ይህ የትራንዚት ስርዓት ዕቃዎች ጅቡቲ ወደብ እንዲከማቹ ምክንያት


መሆኑን ይታመናል፡፡
16
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ
2) መልቲ ሞዳል፡-
 በመልቲ ሞዳል የሚጓጓዙ ዕቃዎች ከዕቃ ዲክላራሲዮን አቅራቢ ወይም ከወኪሉ
እውቅና ውጭ በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ሎጂስቲክስ አገልግሎት
ድርጅት (ኢባትሎአድ) ዋስትና መሰረት የሚደረጉ ጉዞዎች ማለት ነው፡፡

 ‘’ዓለም ዓቀፍ መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት’’ ማለት ቢያንስ በሁለት የተለያዩ


የማጓጓዣ ዓይነቶች፣ ወጥ በሆነ የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ውል መሰረት
መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አከናዋኙ ከአንድ የተወሰነ ቦታ ተረክቦ በማጓጓዝ
ሌላ አገር ውስጥ የሚገኝ የማስረከቢያ ቦታ ለማስረከብ የሚደረግ የማጓጓዝ ሥራ
ነው፡፡ በአንድ ዓይነት ማጓጓዣ ተጓጉዞ የመጣን ዕቃ ተቀብሎ ማድረስ እንደ
መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አይቆጠርም (የመ.ት.አ 548/1999 (2-1)
17
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ
የመልቲ-ሞዳል ዋና ዋና ባህርያት
 አንድ የኮንትራት ስምምነት (under one contract)
 አንድ ሰነድ (one document)
 አንድ ትራንስፖርት ኦፕሬተር (one responsible party) (MTO) for
the entire carriage
 ሁለትና ከሁለት በላይ የማጓጓዣ ዓይነቶች

18
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ

19
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ
ለ) ቅድመ ሁኔታዎች (Doc. Directive)… (168/2012 (5/1)
1.በዩኒ ሞዳል ከአገር ውስጥ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት
 የትራንዚት ዲክላራሲዮን (IM8) ፣
 ለቀረጥና ታክስ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ፣
 የማጓጓዣ ሰነድ፣
 ዕቃው በኮንቴነር የሚጓጓዝ ከሆነ የኮንቴነር ዋስትና
2.በዩኒ ሞዳል ሆኖ ከጎረቤት አገር የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት
 ኮሜርሻል ኢንቮይስ
 ትራንዚት ዲክላራሲዮን (IM-8)

 የማጓጓዣ ሰነድ፣

 ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ወይም የቀረጥ ነፃ መብት ደብዳቤ፣

3.በመልቲ-ሞዳል ለሚገቡ የትራንዚት ዕቃዎች


 ትራንዚት ዲክላራሲዮን (IM-8) እና T1
 ዋስትና፣ 20
የገቢ ዕቃዎች ትራንዚት…የቀጠለ
Mode of Transport
Code Description
1 MARINE TRANSPORT
2 RAIL TRANSPORT
3 ROAD TRANSPORT
4 AIR TRANSPORT

5 MAIL TRANSPORT

61 UNIMODAL TRANSPORT
(SEA ROAD)
62 MULTIMODAL TRANSPORT
(SEA ROAD)
64 MULTIMODE AIR ROAD

7 FIX TRANSPORT (PIPELINE)

9 UNKNOWN 21
Galafi customs

Multimodal transit
• Receive IM8 & T1 from deriver
•Retrieve IM8 from Ecms
•Chick container and seal number
•Write the remark
Multumodal opertaer
•Prepared each track T1
• the Cargo Clearing Instruction.
•Send the Cargo Clearing
•Instruction to MOP djub.
•MOP in Dji Dispatch the clearing instruction
•Guarantee

Djibouti transistor
•Receive clearing instruction .
•Receive delivery order from shipping agency.
•Finalize port formalities.
•Register and validate IM8 declaration in
Djibouti
•Submit the supporting document(IM 8 and T1
to Djibouti customs
•The system the data by FTP to Ethiopian
system

Check point Destination office


Djibouti customs •Receive T1 from driver •Receive T1 from driver
•Check the supporting documents.
•Check the seal number and
•Validate and print T1s •Check the seal number and container
container number physically
•Give T1 to the clearing agent
•approved in the system and permit number physically
to continue
• validate and confirm
22
3. የተላላፊ ዕቃዎች ትራንዚት (Through Transit)
ሀ. ትርጉም
የተላላፊ ዕቃዎች ትራንዚት ማለት ዕቃ ከአንድ የጉምሩክ መግቢያ በር ወደ ሌላ የጉምሩክ

መውጫ በር በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፍበት የዓለም አቀፍ የአሰራር ሥርዓት


ነው፡፡
ይህንን ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ተላላፊው ዕቃ በሚተላለፍባቸው ሀገሮች መካከል

ስምምነት መኖር አስፈላጊ ነው፡፡


ተላላፊ መንገደኞች የትራንዚት አካባቢውን እስካጠናቀቀ ድረስ የጉምሩክ ቁጥጥር

አይደረግባቸውም፤ ሆኖም ባለሥልጣኑ በትራንዚት አካባቢው ላይ አጠቃላይ ቁጥጥር


ማድረግና የጉምሩክ ወንጀል ተፈጽሟል የሚል ጥርጣሬ ሲኖር አስፈላጊውን እርምጃ
መውሰድ ይችላል፡፡
23
3. የተላላፊ ዕቃዎች ትራንዚት…

24
3. የተላላፊ ዕቃዎች ትራንዚት…

ለ. መመሪያ 168/2012 አንቀፅ 6


 የተላላፊ ዕቃዎች ትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡
1) ዋስትና፣
2) ትራንዚት ዲክለራሲዮን (IM8)፣
3) ኮሜርሻል ኢንቮይስ፣
4) የማጓጓዣ ሰነድ፣
5) ዕቃው ከሚደርስበት አገር የተሰጠ የታደሠ ንግድ ፈቃድ፡፡
• ዓለም አቀፍ ተቋማት እና የእርዳታ ድርጅቶች ለተላላፊ ዕቃ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት የሚከተሉትን
ማቅረብ አለባቸው፤
 ዋስትና፣

 የማጓጓዣ ሰነድ፣

 ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8)

25
Through Proclam
Transit ation
No.
859/200
6
IM8
00 8000800

80 800 None
Removal of Proclam
goods via ation No.
through 859/200
Transit 6,
art.175
26
4. የአገር ውስጥ ትራንዚት (Interior Transit)

ሀ. ትርጉም
የውስጥ ትራንዚት (Interior Transit) ማለት ከአንድ የሀገር ውስጥ የጉምሩክ

ጣቢያ (የተፈቀደ ቦታ) ወደ ሌላ የሀገር ውስጥ የጉምሩክ ጣቢያ (የተፈቀደ ቦታ) ዕቃ


በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ሆኖ የሚተላለፍበት ሥርዓት ማለት ነው፡፡
Mode of Declaration IM8

CPC 8300 800

27
4 የአገር ውስጥ ትራንዚት…

መመሪያ 117/2006 አንቀፅ 7


የሀገር ውስጥ የትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች

መሟላት አለባቸው፣
1) የትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8)

2) የማጓጓዣ ሰነድ

3) ዋስትና

28
ሐ. የውስጥ ትራንዚት ሥርዓት ስዕላዊ መግለጫ/flow
4 የአገር ውስጥ ትራንዚት…

chart/

29
5. የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት (Outward Transit)

ሀ. ትርጉም
የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት ማለት የወጪ ዕቃዎች ከሀገር ውስጥ መነሻ ቦታ ወደ
ውጪ ሀገር በጉምሩክ ቁጥጥር ስር ሆኖ የሚተላለፉበት ሥርዓት ነዉ፡፡

Mode of Declaration EX8

CPC 8200 800

30
5. የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት…

የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት ፈቃድ ለማግኘት 168/2012 (8)

የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት ለማስፈጸም የሚቀርቡ ሰነዶች (ቅድመ ሁኔታ)

ትራንዚት ዲክለሬሽን (EX8)


የተቆጣጣሪ መ/ቤቶች ፈቃድ (እንደአስፈላጊነቱ)

31
5. የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት…
ሐ. የወጪ ዕቃዎች ትራንዚት ሥርዓት ስዕላዊ መግለጫ /flow chart/

?
?

?
?

32
የጉምሩክ ትራንዚት መግቢያ ቦታዎች
መመሪያ ቁጥር 168/13 ወደ ሀገር ለሚገቡ ወይም የተላላፊ የትራንዚት ዕቃዎች
የጉምሩክ ትራንዚት መግቢያ ቦታ የሚሆኑት የጉምሩክ መግቢያ ጣቢያዎች
ሆነው፡-
 ሀ) በጅቡቲ በኩል ለሚገባዕቃ - ጋላፊ፣ ደወሌ እና ታጁራ፣
ለ) በሶማሊያ በኩል ለሚገባ ዕቃ - ቶጐጫሌ፣ ተፈሪ በር፣ ፌረፌር፣ ዱዱብ፣ ቦህ እና
ዶሎአዶ፣
ሐ) በሱዳን በኩል ለሚገባ ዕቃ - ሁመራ፣ መተማ ዮሐንስ፣ አልመሃል፣ በሃምዛ፣ ኩርሙክ
እና ጊዘን፣
መ) በደቡብ ሱዳን በኩል ለሚገባ ዕቃ - መተሐር (ቡርቤ) ፣ ላሬ (ፓጋግ) እና ራድ
ሠ) በኬንያ በኩል ለሚገባ ዕቃ - ሞያሌ እና ኦሞራቴ፣
ረ/ በኤርትራ በኩል ለሚገባ ዕቃ - ቡሬ፣ ዛላ አምበሳ፣ ራማ እና ሁመራ”
ሰ) ኮሚሽኑ የሚወሰኑ ሌሎች መግቢያ በሮች ናቸው፡፡

33
የጉምሩክ ትራንዚት መነሻ ቦታዎች

1) ከሀገር ለሚወጡ ወይም የአገር ውስጥ የትራንዚት ዕቃዎች የጉምሩክ ትራንዚት መነሻ
ቦታ የሚሆኑት፡-
• ሀ/ የጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች
ለ/ በመግቢያና መዉጫ የሚገኙ የጉምሩክ ጣቢያዎች፣
 ሐ/ የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን፣
 መ/ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ዞን፣
 ሠ/ በኮሚሽኑ የተፈቀዱ ሌሎች ቦታዎች ናቸው፡፡

34
...የጉምሩክ ትራንዚት መነሻ ቦታዎች

2) ወደ ሀገር ለሚገቡ ወይም የተላላፊ የትራንዚት ዕቃዎች የጉምሩክ


ትራንዚት መነሻ ቦታ የሚሆኑት፤
ሀ/ የጅቡቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፤
ለ/ የበርበራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት፤
ሐ/ ባለስልጣኑ ወደፊት የሚወስናቸው ሌሎች የጎረቤት አገራት
ወደቦች ናቸው፡፡

35
የጉምሩክ ትራንዚት ማጠናቀቂያ ቦታዎች

1) ወደ ሀገር ለሚገቡ /የሀገር ውስጥ ትራንዚት ዕቃዎች የጉምሩክ ትራንዚት


ማጠናቀቂያ ቦታ የሚሆኑት
• ሀ/ የጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤቶች
ለ/ በመግቢያና መዉጫ የሚገኙ የጉምሩክ ጣቢያዎች፣
 ሐ/ የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን፣
 መ/ ኢንዱስትሪ ዞን፣
 ሠ/ በኮሚሽኑ የተፈቀዱ ሌሎች ቦታዎች ናቸው፡፡
2) ከሀገር ለሚወጡ /ተላላፊ ትራንዚት ዕቃዎች የጉምሩክ ትራንዚት ማጠናቀቂያ
ቦታ የሚሆኑት በአንቀፅ 12 ን/አንቀጽ 1 የተዘረዘሩት መግቢያ ጣቢያወች ይሆናሉ፤

36
MAP
MAP OF
OF ETHIOPIAN
ETHIOPIAN CUSTOMS
CUSTOMS TRANSIT
TRANSIT ROUTES
ROUTES CEP- Customs
Entry/ Exit Post
CCP-Customs
Checking Post
CCO-Customs
Clearing Office

37
6. የጉምሩክ ትራንዚት ኦፕሬሽን
ሀ.የመነሻ የትራንዚት ኦፕሬሽን
(Formalities at the Office of Departure)

ለ) በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት ሥነ ሥርዓት

(en route Transit)

ሐ) ስለጉምሩክ ትራንዚት መጠናቀቅ

(Termination of Customs transit Operation)

38
6. የጉምሩክ ትራንዚት ኦፕሬሽን
ሀ.የመነሻ የትራንዚት ኦፕሬሽን (Formalities at the Office of Departure)

1. የጉምሩክ መዳረሻ ጣቢያው ጭነቱን ለይቶ ለማወቅና ያልተፈቀደ ጣልቃ


ገብነት ተፈጽሞበት ከሆነም ይህንኑ ለይቶ ማወቅ እንዲችል የመነሻ ጉምሩክ
ጣቢያው አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ ሁሉ መውሰድ አለበት፡፡
 የኮንቴነር ቁጥር
 የማሸጊያ ቁጥር ሁኔታ በማረጋገጥ መመዝገብ
 የመዳረሻ ጣቢያ ወይም ቦታ ማስቀመጥ
 የመድረሻ ቀነ ገደብ መመዝገብ
 የትራንዚት ዋስትና መጠንና አግባብነት ማየት

39
ሀ. የመነሻ የትራንዚት ኦፐሬሽን…
2) የጉምሩክ ማሸጊያ የሚያስፈልገው ጭነት በማጓጓዣ የተወሰነ ክፍል ውስጥ ተደርጎ የሚጓጓዝ ሲሆንና የማጓጓዣ ክፍሉ አሠራርና ይዘት፡-

ሀ)የጉምሩክ ማሸጊያ በቀላሉና በአግባቡ ሊደረግበት


የሚያስችል ከሆነ፣
ለ) የመነካካት ምልክት ሳይታይበት ወይም ማሸጊያው
ሳይወገድ ዕቃ ወደ ማጓጓዣው የተወሰነ ክፍል
ለማስገባት ወይም ከማጓጓዣው የተወሰነ ክፍል
ለማውጣት የማያስችል ከሆነ፣
ሐ)ዕቃን ለመሰወር የሚያስችል ድብቅ ክፍል የሌለው
ከሆነ፣ እና
መ)ዕቃን መያዝ የሚችሉ ክፍሎቹ ሁሉ ለጉምሩክ
ቁጥጥር ተደራሽነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ከሆነ፣

የጉምሩክ ማሸጊያው በማጓጓዣው ክፍሉ በራሱ ላይ መደረግ አለበት፡፡

40
ሀ. የመነሻ የትራንዚት ኦፐሬሽን…
3) የጉምሩክ ማሸጊያዎችና ልዩ ምልክቶች
ኮሚሽኑ ጭነቶችን ለማሸግ የሚጠቀምባቸው የጉምሩክ ማሸጊያዎች ወይም ልዩ ምልክቶች
እንደአግባብነቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡‑
1/ በቀላሉ ለማንበብና ለመለየት የሚቻል፣
2/ ካልተሰበረ ወይም ካልተነሳ በስተቀር እቃ ለማውጣትም ሆነ ለማስገባት የማያስችል፣
3/ ከአንድ ጊዜ በላይ አግልግሎት የማይሰጥ (ኤሌክትሮኒክ ሲል ካልሆነ በስተቀር)፣
4/ የጉምሩክ ማሸጊያ ወይም ልዩ ምልክት መሆኑን ለማመላከት በእንግሊዘኛ ‘’ETH-
CUSTOMS’’ የሚል ጽሑፍ የተጻፈበትና ተከታታይ ቁጥር ያለው፣
6/ ለማሸግ ወይም ለመቆለፍ አመቺ የሆነ፣እና
7/ ኮሚሽኑ ለዕቃው ደህንነት አስፈላጊ ናቸው የሚላቸው ሌሎች መስፈርቶች ያሟላ መሆን
አለበት፡፡

41
ሀ. የመነሻ የትራንዚት ኦፐሬሽን…
4. የጉምሩክ ማሸጊያ ዓይነቶች
2
1

5
4
42
ሀ. የመነሻ የትራንዚት ኦፐሬሽን…
5. መታሸግ ያለባቸው ጭነቶች(አንቀፅ 10
1. ማንኛውም የትራንዚት ዕቃ፡-
ሀ)በኮንቴነር ወይም በባቡር ፍርጎ የተጫነ ከሆነ፣
ለ)በሸራ ለማሸግ የሚመች ከሆነ፣
ሐ)የነዳጅ ውጤቶች ከሆነ በጉምሩክ ማሸጊያ መታሸግ ይኖርበታል፡፡
2.ማንኛውም የትራንዚት ዕቃ በኮንቴነር ባይጫንም ወይም በሸራ ለመጫን ባይመችም በቀላሉ
ሊሰበር፣ ሊቀሸብ፣ ሊለወጥ የሚችል ከሆነ እና ዓለም ዓቀፍ ስምምነት የማያስገድድ ከሆነ በጉምሩክ
ማሸጊያ ታሽጎ መጓጓዝ ይኖርበታል
3.በውጭ ሀገር ጉምሩክ አማካይነት የተደረጉ የጉምሩክ ማሸጊያዎችና መለያ ምልክቶች፣
ሀ) በቂ አይደሉም ካልተባሉ፣
ለ) አስተማማኝ ካልሆኑ፣ ወይም
ሐ) ኮሚሽኑ ዕቃውን ለመመርመር ካልወሰነ፣
በስተቀር ለጉምሩክ ትራንዚት አፈጻጸም ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡859/2006 አንቀጽ 19/2

43
ሀ. የመነሻ የትራንዚት ኦፐሬሽን…
6. የማይታሸጉ ጭነቶች(አንቀፅ 11)
1)ትልልቅ የፋብሪካና የፕሮጀክት ማሽነሪዎች

2)የብረት ጭነቶች

3)ከኮንቴነር ውጭ ተጭነው የሚመጡ ተሽከርካሪዎች

4)በውጭ አገር ጉምሩክ ማሸጊያ በትክክል የታሸገ ዕቃ፣

5)በተሽከርካሪ የሚጫን የዕርዳታ እህል፣ ማዳበሪያ እና የድንጋይ ከሰል

6)ለትራንዚት ቁጥጥር አመቺ የሆኑና በግልጽ የሚታዩ ሌሎች ጭነቶች፤

44
ለ) በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት ሥነ -ስርዓት (en route Transit
Procedures)
በጉምሩክ አዋጅ 859/2008 አንቀፅ 20
 1/
በቅድሚያ ፈቃድ መገኘት አለበት ተብሎ በኮሚሽኑ ካልተወሰነ በስተቀር በመዳረሻ
የጉምሩክ ጣቢያ ላይ የሚደረግ ለውጥ አስቀድሞ ማስታወቅ ሳያስፈልግ ተቀባይነት
ይኖረዋል፡፡
2/የጉምሩክ ማሸጊያ ወይም ማሰሪያ እንዲወገድ እስካልተደረገ ወይም እስካልተነካካ ድረስ
ባለሥልጣኑን ማስፈቀድ ሳያስፈልግ ዕቃን ከአንድ ማጓጓዣ ወደ ሌላ ማጓጓዣ
ማዛወር ይቻላል፡፡
3/በጉምሩክ ትራንዚት አፈጻጸሙ ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ የሚያመጣ አደጋ ወይም ያልተጠበቀ
ሁኔታ ሲከሰት ዲክላራሲዮን አቅራቢው ወይም አጓጓዡ ወዲያውኑ በአቅራቢያው ለሚገኘው
የጉምሩክ ጣቢያ ወይም አግባብ ላለው ሌላ የመንግስት አካል ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡

45
ለ. በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…
መተላለፊያ መስመሮች

1. በጅቡቲ በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ የትራንዚት ዕቃ የመተላለፊያ
መስመር የሚሆነው፡-

አፍዴራ--->መቀሌ
ጭፍራ--->ወልዲያ--->ወረታ/መቀሌ

ሀ) ጋላፊ/ሌዪ--->ሰርዶሜዳ--->ሠመራ--->ሚሌ--->አዋሽ--->አዳማ--->ሞጆ--->አዲስ አበባ

አንኮበር--->ደብረብርሃን

ባቲ--->ኮምቦልቻ--->ደብረብርሃን

ለ) ደወሌ--->ቢዮቆቦቤ--->ድሬደዋ>ሐረር--->ጅግጅጋ

46
ለ. በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…

2. በኬንያ በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ


የትራንዚት ዕቃ የመተላለፊያ መስመር የሚሆነው፡-

ሀ) ሞያሌ-->ያቤሎ-->ቡሌ ሆራ-->ዲላ -->ሐዋሳ-- >ሻሸመኔ ---> ሞጆ ->አ.አ

ለ) ሞያሌአርባምንጭወላይታሶዶ-->ሃዋሳ/ቡታጅራ-->ዝዋይ/ሞጆ/አ/አ

47
ለ. በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…
በባለስልጣኑ የተፈቀዱ የትራንዚት መስመሮች …

3.በሱማሌያ በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ የትራንዚት ዕቃ


የመተላለፊያ መስመር የሚሆነው፡-

ሀ) ቶጎጫሌ /ተፈሪ በር /ፌርፌር /ዱዱብ /ቦህ--->ጅግጅጋ--->ሐረር


--->ድሬዳዋ (ሚኤሶ--->አዋሽ--->አዳማ--->ሞጆ--->አዲስ አበባ)

ለ) ዶሎ አዶ--->ነገሌ ቦረና--->ሀዋሳ--->ሻሸመኔ--->ዝዋይ--->ሞጆ--->አ/አ

ሆኖም ዋናውን መንገድ በመከተል ብቻ ይሆናል!!!

48
ለ. በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…
በባለስልጣኑ የተፈቀዱ የትራንዚት መስመሮች …

4. በሱዳን በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ የትራንዚት


ዕቃ የመተላለፊያ መስመር የሚሆነው፡-
ሀ) ሑመራ--->ሽሬ--->መቀሌ/ጐንደር--->ወረታ--->ባህር ዳር--->ደ/ማርቆስ--->አ/አ

ለ) መተማ--->ጐንደር--->ወረታ--->ባ/ዳር--->ደ/ማርቆስ--->አ/አ(ጐንደር-->ሽሬ-->መቀሌ)

ሐ) ጊዘን / ኩምሩክ--->አሶሳ--->ነቀምት--->አምቦ--->አ/አ (ነቀምት--->ጅማ)

መ) አልመሃል--->በሃምዛ--->ቻግኒ--->እንጂባራ--->ባህርዳር/ወረታ (ደ/ማርቆስ--->አ/አ)

49
በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…

5. በደቡብ ሱዳን በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ የትራንዚት ዕቃ
የመተላለፊያ መስመር የሚሆነው፡-

ሀ) መተሃር /ቡርቤ/--->ጋምቤላ--->በደሌ--->ጅማ--->ወልቂጤ--->አ/አ

ለ) ላሬ /ፓጋግ/--->ጋምቤላ--->በደሌ--->ጅማ--->ወልቂጤ--->አ/አ

ሐ) ራድ--->ዲማ--->በበቃ--->ሚዛን--->ቦንጋ(ቴፒ--->ማሻ--->ጎሬ--->መቱ
--->በደሌ)--->ጅማ--->ወልቂጤ--->አ/አ

50
በጉዞ ወቅት ስለሚፈጸም ትራንዚት…

6. በኤርትራ በኩል ወደ ሀገር ለሚገቡና ለሚወጡ እና አገር አቋርጦ ለሚያልፍ የትራንዚት ዕቃ የመተላለፊያ
መስመር የሚሆነው፡-
ሀ) ቡሬ-->ሰርዶ ሜዳ-->ሠመራ-->ሚሌ-->አዋሽ-->አዳማ-->ሞጆ-->አ/አ
ለ) ቡሬ-->ሰመራ-->ሚሌ-->ባቲ---ኮምቦልቻ--->ደብረ ብርሃን
ሐ) ዛላአንበሳ--->ዓዲ ግራት--->መቀሌ--->ወልዲያ--->ኮምቦልቻ--->ደብረ
ብርሃን--->አ/አ
መ) ራማ--->ዓድዋ--->ተምቤን--->መቀሌ--->ወልዲያ--->ኮምቦልቻ--->ደ/ብርሃን---
>አ/አ
ሠ) ሑመራ--->ጎንደር--->ወረታ--->ባህር ዳር--->ደብረ ማርቆስ--->አ/አ
ረ) ሑመራ--->ሽሬ--->መቀሌ
7. በባቡር ተጭነው ለሚጓጓዙ ዕቃዎች በባቡር የሚያልፍባቸው መስመሮች የትራንዚት መተላለፊያ መስመር
ተደረገው ይወሰዳሉ።
51
የትራንዚት የግዜ ገደብ አንቀፅ 19
1) በጅቡቲ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-
ሀ) ከጋላፊ/ሌይ - አዳማ /ሞጆ/ አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣
ለ) ከጋላፊ - ሠመራ በአንድ ቀን ውስጥ፣
ሐ) ከጋላፊ - መቀሌ በሁለት ቀን ውስጥ፣
መ) ከጋላፊ - ወረታ በሦስት ቀን ውስጥ፣
ሠ) ከጋላፊ - ኮምቦልቻ በሁለት ቀን ውስጥ፣
ረ) ከጋላፊ - ደብረ-ብርሃን በሦስት ቀን ውስጥ፣
ሰ) ከደወሌ - ድሬዳዋ በአንድ ቀን ውስጥ፣
ሸ) ከደወሌ - ጅግጅጋ በሁለት ቀን ውስጥ፣
ቀ) ከደወሌ ‑ አዳማ /ሞጆ/ አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣
52
የትራንዚት የግዜ ገደብ…
2. በሶማሊያ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-
 ሀ) ከቶጎጫሌ እና ከተፈሪ በር - ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ በአንድ ቀን ውስጥ፣

 ለ)ከቶጎጫሌ እና ከተፈሪ በር - አዳማ /ሞጆ/ አዲስ አበባ በሦስት ቀን


ውስጥ፣
 ሐ) ከፌርፌር፣ ከዱዱብ እና ከቦህ - ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ በአራት ቀን ውስጥ፣

 መ) ከፌርፌር፣ ከዱዱብ እና ከቦህ - አዳማ / ሞጆ / አዲስ አበባ በሰባት ቀን

ውስጥ፣
 ሠ) ከዶሎ አዶ - አዳማ / ሞጆ / አዲስ አበባ በአምስት ቀን ውስጥ፣

53
የትራንዚት የግዜ ገደብ…
3. በኬንያ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-

ሀ) ከሞያሌ - ሞጆ /አዳማ/ አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣

ለ) ከሞያሌ - ዶሎ አዶ በሦስት ቀን ውስጥ፣

ሐ) ከሞያሌ - ሀዋሳ በሁለት ቀን ውስጥ፣

መ) ሀዋሳ - ሞጆ /አዳማ/ አዲስ አበባ በአንድ ቀን ውስጥ፣

ሠ) ከኦሞራቴ - ሞጆ /አዳማ/ አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣

ረ) ከኦሞራቴ - ሀዋሳ በሁለት ቀን ውስጥ፣

54
የትራንዚት የግዜ ገደብ…
4. በሱዳን በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-

ሀ) ከሁመራ - መቀሌ በሁለት ቀን ውስጥ፣

ለ) ከሁመራ ወይም ከመተማ ዮሐንስ - ወረታ በሁለት ቀን ውስጥ፣

ሐ) ከመተማ ዮሐንስ - ኮምቦልቻ ወይም መቀሌ በሦስት ቀን ውስጥ፣

መ) ከሁመራ ወይም ከመተማ ዮሐንስ - አዲስ አበባ /ሞጆ/ አዳማ በአምስት ቀን ውስጥ፣

ሠ) ከአልምሃል / ከሃምዛ / ከኩርሙክ / ከጊዘን - አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣

ረ) ከጎንደር - መተማ ዮሐንስ ወይም ሁመራ በአንድ ቀን ውስጥ፣

ሰ) ከባህር ዳር - መተማ ዮሐንስ ወይም ሁመራ በሁለት ቀን ውስጥ፣

ሸ) ከጎንደር ወይም ከባህር ዳር - አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣

ቀ) ከነቀምት - አዲስ አበባ በሁለት ቀን ውስጥ፣

በ) ከነቀምት ወይም ከጅማ - አልምሃል /በሃምዛ /ኩርሙክ /ጊዘን በሁለት ቀን ውስጥ፣

ተ) ከአልመሃል ወይም በሃምዛ - ባህር ዳር በሁለት ቀን ውስጥ፣ 55


የትራንዚት የግዜ ገደብ…

5. በደቡብ ሱዳን በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-

ሀ) ከመተሃር (ቡርቤ) ወይም ከላሬ (ፓጋግ) - አዲስ አበባ በአራት ቀን ውስጥ፣

ለ) ከጅማ ወይም ከነቀምት - መተሃር (ቡርቤ) ወይም ላሬ (ፓጋግ) በሁለት ቀን ውስጥ፣

ሐ) ከጅማ - አዲስ አበባ በሁለት ቀን ውስጥ፣

56
የትራንዚት የግዜ ገደብ…
6. በኤርትራ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባ ወይም ከሀገር ለሚወጣ ዕቃ ፡-

ሀ) ከቡሬ - ሠመራ በአንድ ቀን ውስጥ፣

ለ) ከቡሬ - ኮምቦልቻ /ወረታ/ መቀሌ በሁለት ቀን ውስጥ፣

ሐ) ከቡሬ - አዲስ አበባ በሦስት ቀን ውስጥ፣

መ) ከዛላምበሳ ወይም ከራማ - መቀሌ በአንድ ቀን ውስጥ፣

ሠ) ከዛላምበሳ ወይም ከራማ - ወረታ /ኮምቦልቻ/ በሁለት ቀን ውስጥ፣

ረ) ከዛላምበሳ ወይም ከራማ - ሠመራ /ደብረ ብርሃን/ በሦሰት ቀን ውስጥ፣

ሰ) ከራማ ወይም ከዛላምበሳ - አዲስ አበባ በአራት ቀን ውስጥ፣

57
የትራንዚት የግዜ ገደብ…
አገር አቋርጠው ለሚሄዱ ተላላፊ ዕቃዎች አንቀፅ 20
ኢትዮጵያን አቋርጠው የሚሄዱ ተላላፊ ዕቃዎች የትራንዚት የጊዜ ገደብ
ከመግቢያ በር እስከ አዲስ አበባ ወይም ሌላ ማዕከል ድረስ እና ከአዲስ አበባ
ወይም ሌላ ማዕከል እስከ መውጫ በር ድረስ ያለውን ጊዜ ገደብ በመደመር
የሚወሰን ይሆናል፡፡

58
ሐ) ስለጉምሩክ ትራንዚት መጠናቀቅ (Termination of
Customs transit Operation) አዋጅ 859/2006አንቀፅ
21
1) የጉምሩክ ትራንዚት አፈጻጸምን ለማጠናቀቅ ዕቃዎቹ ምንም ለውጥ
ሳይደረግባቸውና አገልግሎት ላይ ሳይውሉ፣ የጉምሩክ ማሸጊያው፣ ማሰሪያው
ወይም መለያ ምልክቱ ሳይነካካ ከሚመለከተው የዕቃ ዲክላራሲዮን ጋር ለመዳረሻ
የጉምሩክ ጣቢያው በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ መቅረብ አለባቸው፡፡
2) የመዳረሻ የጉምሩክ ጣቢያው ዕቃዎቹ በቁጥጥሩ ሥር እንደገቡ ወዲያውኑ ሁሉም
ቅደመ ሁኔታዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ የጉምሩክ ትራንዚት አፈጻጸሙን
ለማጠናቀቅ ሁኔታውን ማመቻቸት አለበት፡፡
3) በጉምሩክ ትራንዚት የሚጓጓዙ ዕቃዎች በኮሚሽኑ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ
መዳረሻ የጉምሩክ ጣቢያው ዘንድ ያልደረሱ ከሆነ በዋስትና የተያዘው ገንዘብ
ለኮሚሽኑ ገቢ ይደረጋል፡፡

59
ሐ) ስለጉምሩክ ትራንዚት መጠናቀቅ…

ለወጪ ዕቃዎች

ወደ ውጪ ሀገር ለሚላክ ዕቃ ከሀገር ወጥቷል ተብሎ ማረጋገጫ የሚሰጠው ከኢትዮጵያ


መውጫ በሆነው የመጨረሻ ጣቢያ ከሚገኘው የጉምሩክ ሹም ዕቃው ከሀገር
መውጣቱን የሚገልጽ ማረጋገጫ ወደ ባለሥልጣኑ አውቶሜሽን ሲስተም ሲገባ ወይም
በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በጽሁፍ ሲደርስ ብቻ ነው፡፡ (859/2006 (141/4))

60
የጉምሩክ ትራንዚት መነሻ ቦታዎች /ጣቢያዎች/ ኃላፊነት

1) ለትራንዚት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ስለመቅረባቸው፣ ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸዉ እና


የተያዘዉ ዋስትና በቂ መሆኑን ማረጋገጥ፤

2) የዕቃዉን ትክክለኛነት ሲጫን በአካል ተገኝቶ በማረጋገጥ በሲል ማሸግና ሲል ቁጥሩን


በአውቶሜሽን ሲስተም በመመዝገብ (T1) ቁጥር በመስጠት ትራንዚቱ እንዲጀምር መፍቀድ፣

3) ትራንዚት የጀመሩ ጭነቶች መረጃ ወደ መረጃ ቴክኖሎጂ ቋት የማስተላለፍ፣

4) ጥርጣሪ ሲኖረው በህግ ማስከበር አባል/ኦፊሰር ታጅቦ ወደ ትራንዚት መድረሻ ጣቢያው


እንዲጓጓዝ የማድረግ፣

5) የመድረሻ ጣቢያ የመቀየር (re-route) ኃላፊነት አለበት፡፡

61
ተግባርና ሃላፊነት

በጉምሩክ ትራንዚት መተላለፊያ መስመር የሚገኙ ጣቢያዎች ኃላፊነት


1) ዕቃው ከመነሻ ጣቢያ የትራንዚት ፈቃድ የተሰጠዉ መሆኑን የማረጋገጥ፤

2) በተፈቀደለት መስመር መጓጓዙን የማረጋገጥ፤

3) በተነሳበት ሁኔታ የደረሰ መሆኑን በማረጋገጥ ትራንዚት ሂደቱን እንዲቀጥል

መፍቀድ፣

62
ተግባርና ሃላፊነት
የጉምሩክ ትራንዚት ማጠናቀቂያ ቦታዎች /ጣቢያዎች/ ኃላፊነት
1) ጭነቱ በተነሳበት ሁኔታ ስለመድረሱ የማረጋገጥ፤
2) በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ የደረሰ መሆኑን በማረጋገጥ ትራንዚቱን ማጠናቀቅ፣
3) በጊዜ ገደቡ የደረሱና ያልደረሱትን በሲስተም የማጣራትና የማስታረቅ
(Reconcilation) ሥራ መስራትና በጊዜ ያልደረሱትን ወደ ህግ ማስከበር
በማስተላለፍ ክትትል እንዲደረግባቸዉና ያስያዙት ዋስትና ለኮሚሽኑ ገቢ እንዲሆን
ማድረግ፣
4) የመድረሻ ጣቢያ ቅያሬ (re-route) እንዲደረግለት የማሳወቅ፣
5) ታጅበው የመጡ ዕቃዎች የደረሱበትን ሁኔታ እና ያለውን ልዩነት እጀባ ላደረገው
ቅ/ጽ/ቤት በጹሁፍ የማሳወቅ፣
6) ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ትራንዚት የሚያደርጉ ዕቃዎች
በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካልደረሱ በዋስትና የተያዘው ገንዘብ ገቢ መሆኑን
የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡
63
ተግባርና ሃላፊነት
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተግባርና ኃላፊነት
1) የሚያጠራጥር ነገር ሲያጋጥም ወይም ኮሚሽኑ ትራንዚት የሚያደርጉ
ዕቃዎች እንዲታጀቡ ሲጠይቅ ያጅባል፣
2) በመተላላፊያ መስመሮች ላይ የጉምሩክ ትራንዚት ዕቃዎች ሥነ-ሥርዓት
አፈፃፀምን ተላልፈው በፖትሮሊንግ ቡድን የሚያዙ ማጓጓዣዎችን እና
እቃዎችን ከመቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት
ዕቃውን ከነማጓጓዣው አጅቦ የጉምሩክ ትራንዚት መድረሻ ቦታ ያደርሳል፤
3) ከዋናው መንገድ የሚወጡትንና ባልተፈቀደላቸው ቦታ የሚቆሙትን
ማጓጓዣዎች አጅቦ ለሚቀጥለው ጣቢያ ያስተላልፋል፡፡
4) የፌዴራል ፖሊስ በዚህ አንቀጽ የተዘረዘሩትን ተግባራት እንደ
አግባብነታቸው የክልል የፀጥታ ወይም ህግ አስከባሪ አካላትን በማሳተፍ
ሊያከናውን ይችላል፡፡
64
ተግባርና ሃላፊነት
የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ተግባርና ኃላፊነት
1) በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አማካኝነት ለሚያስመጣቸው ዕቃዎች በቂ የሆነ የአንድ
ዓመት የኢንሹራንስ ወይም የባንክ አጠቃላይ ዋስትና ማስያዝ፣
2) የተጠቀሰው አጠቃላይ ቦንድ ለቅ/ጽ/ቤቶች ከፋፍሎ ማስያዝ፣
3) አጠቃላይ ቦንድ ያስያዘው ከማብቃቱ አንድ ወር ቀደም ብሎ ይሆናል፣
4) ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም፤የመድረሻ ጣቢያ ለማስቀየር ከፈለገ፤እና
በጊዜ ያልደረሱ ጭነቶች ሲያጋጥሙ በአቅራቢያው ለሚገኝ ቅ/ጽ/ቤት ወይም ህግ
አስከባሪ አካል በነዚህ ድንጋጌዎች በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ የማሳወቅ ግዴታ
አለበት፡፡

65
ተግባርና ሃላፊነት

የማጓጓዣ ኃላፊ ኃላፊነት


1) ፈቃድ ሳይሰጠውና የጉምሩክ ሹም በሥፍራው ሳይኖር ወደ ሀገር የሚገባን ወይም
ከሀገር የሚወጣን ተላላፊ ዕቃ እና ማጓጓዣ ከተወሰነው የጉምሩክ ወደብ ወይም
የመተላለፊያ መስመር ውጪ ማንቀሳቀስ፣ ማቆም፣ ዕቃ መጫን ወይም ማራገፍ፣
ከተፈቀደለት ሰው በስተቀር ማንኛውንም ሌላ ሰው ወደ ማጓጓዣው እንዲጠጋ
መፍቀድ፣ ወይም ማሳፈር፣ የጉምሩክ እሽጐችን መፍታት፣ ማላቀቅ፣ መሥበር ወይም
መቀየር ወይም እነዚሁ ህገ-ወጥ ተግባራት በሌሎች ሰዎች እንዲፈፀሙ ማድረግ
የለበትም ነው፡፡
2) ንዑስ አንቀጽ (1) የተገለፀው ቢኖርም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም ጉዞ
ማቋረጡን ለድክለራሲዮን አቅራቢው በ8 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡

66
ተግባርና ሃላፊነት
የዲክላራሲዮን አቅራቢ ኃላፊነት
1) ከመነሻ የጉምሩክ ትራንዚት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተፈቀደው የመዳረሻ ጣቢያ በመንገድ
ብልሽት ወይም ሌላ አሳማኝ ምክንያት ሲኖር እና የመዳረሻ ጣቢያ ለማስቀየር (re-rout)
ከፈለገ ለመነሻ ጣቢያ ጥያቄውን አቅርቦ ማስፈጸም፣
2) ለትራንዚት አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን አሟልቶና ትክክለኛነታቸውን አረጋግጦ ለጉምሩክ
ኦላይን የትራንዚት ፈቃድ መጠየቅ፣
3) የትራንዚት ፈቃድ ተሰጥቷቸዉ በጊዜ ያልደረሱ ጭነቶች ካሉ በ24 ሰዓት ውስጥ ለመድረሻ
የጉምሩክ ጣቢያ በመቅረብ ማመልከት ይኖርበታል፡፡
4) ቀረጥና ታ ክሱ ከተ ከፈ ለ ወይም ዋስት ና ከተ ያ ዘ በኋላ ዕቃ ው በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ
አገር ውስጥ ያልገባ ከሆነ የተሻሻለ ዲክላራሲዮን እና አዲስ የተሰላውን ቀረጥና ታክስ ወይም
ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

67
ተግባርና ሃላፊነት

የቦንድድ መጋዘን ባለቤት ኃላፊነት


 ማንኛውም የቦንድድ መጋዘን ባለቤት የትራንዚት ዕቃ ተጓጉዞ ወደ መጋዘኑ ሲደርስ
ዲክለር ላደረገበት ቅ/ጽ/ቤት ዕቃው የደረሰ መሆኑን በ24 ሰዓት ውስጥ ማሳወቅ
ይኖርበታል፡፡

68
የጉምሩክ ትራንዚት ስነ-ስርዓት አለማክበር(Failure to observe
customs transit procedures)

ማንኛውም ሰው የጉምሩክ የትራንዚት ስነ-ስርዓትን በሚመለከት ተፈፃሚነት


የሚኖረውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያላከበረ እንደሆነ ከብር 5,000 በማያንስና
ከብር 20,000 በማይበልጥ መቀጮ ይቀጣል፡፡859/2006 አንቀፅ 162.
ማንኛውም አጓጓዥ መ.ቁ 112/2008 አንቀፅ 10/1
ሀ) በኮሚሽኑ ከተፈቀደ የጉዞ መስመር ውጭ ዕቃን ካጓጓዘ ወይም
ለ) ዕቃ ጭኖ እንድቀሳቀስ በተወሰነለት ጊዜ አጓጉዞ ያላደረሰ እንደሆነ ወይም
ሐ) በጉምሩክ ማሸጊያ ታሽጎ መጓጓዝ የሚገባው ሆኖ ሳይታሻግ ሲያጓጉዝ የተገኘ
እንደሆነ ወይም
መ) በኮሚሽኑ ከተፈቀደ የጉምሩክ መውጫና መግቢያ ውጭ ዕቃ ያስወጣ/ያስገባ
እንደሆነ

69
ስነ-ስርዓት አለማክበር…

ከሀ-መ ከተጠቀሱት ድርጊቶች ውስጥ አንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈፀመ ከሆነ ብር


5,000/አምስት ሽህ/ ያስቀጣል፡፡
ማንኛውም አጓጓዥ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተሟላ የመንገደኞች ወይም
የጭነት መግለጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለቀረበ እንደሆነ ብር 3,000/ሶስት ሽህ/
ያስቀጣል፡፡መ.ቁ 112/2008 አንቀፅ 8/1
ማንኛውም ድክለራሲዮን አቅራቢ/ አጓጓዥ በጉምሩክ ትራንዚት አፈፃፀሙ ላይ
በቀጥታ ተፅዕኖ የሚያመጣ አደጋ ወይም ያልተጠበቀ ሁኔታ ሲከሰት በአካባቢው ባለ
የጉምሩክ ጣቢያ ወይም አግባብ ላለው የመንግስት አካል በፅሁፍ ማሳወቅ ሲገባው
ያላሳወቀ እንደሆነ
ሀ) ድርጊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈፀመ ከሆነ ብር 5,000/አምስት ሽህ/ ያስቀጣል፡፡
መመሪያ ቁጥር 112/2008 አንቀፅ 10/3
70
71

You might also like