You are on page 1of 26

1

የተሽከርካሪ የክብደት ወሰን እና የትርፍ ጭነት ቅጣት ለማስፈፀም


የወጣ የውስጥ አሰራር ማንዋል
መግቢያ

 የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ግንባታቸዉ የተጠናቀቁ የክፍያ መንገዶችን


ለማስተዳደር እና ለማስጠገን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 310/2006 መሠረት
የመንግስት ልማት ድርጅት ሆኖ በመቋቋም ስለክፍያ መንገድ የወጣ አዋጅ ቁጥር 843/2006
መሠረት የአዲስ አበባ - አዳማ የፍጥነት መንገድ በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡
 በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 9(5) እንደተገለፀዉ ኢንተርፕራይዙ በሚያስተዳድራቸዉ የክፍያ
መንገዶች በአዲስ-አዳማ፣በሞጆ-ባቱ እና ድሬዳዋ-ደወሌ ላይ ያሽከረከረ አሽከርካሪ አግባብ ባለዉ
ህግ ለትርፍ ጭነት ቅጣት እራሱ እንደሚያስፈፅም ይደነግጋል፡፡
የቀጠለ…
 ኢንተርፕራይዙ የፍጥነት መንገድ ለዚህም ቁጥጥር ይረዳ ዘንድ በሁሉም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች
በመግቢያ በሮች እና በቋሚ የክብደት ቁጥጥር ጣቢያዎች ትርፍ ጭነት የጫኑ ተሸከርካሪዎችን ወደ
መንገዱ እንዳይገቡ ለማድረግ እና ለመቅጣት በሀገር ደረጃ ከዚህ ቀድም ተግባራዊ በሆነዉ
ስለተሽከርካሪ መኪኖች ክብደትና ልክ መወሰኛ ደንብ ቁጥር 261/1955፤
 በደንብ ቁጥር 491/2014 የተሸከርካሪ መኪኖች ክብደትና መጠንን ለመወሰንና ለመቆጣጠር የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሰረት በማድረግ በኢንተርፕራይዙ የተሽከርካሪ የክብደት ወሰን እና
የትርፍ ጭነት ቅጣት ተግባራትን ለማስፈፀም የወጣ የውስጥ አሰራር ማንዋል ተዘጋጅቶ
እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
 ስለሆነም ኢንተርፕራይዙ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እና ተጠያቂነትን
ለማስፈን የተሻሻለውን የተሽከርካሪ ክብደት ወሰን እና ትርፍ ጭነት ቅጣት ደንብ ቁጥር 491/2014
መሰረት በማድረግ የተሽከርካሪ የክብደት ወሰን እና የትርፍ ጭነት ቅጣት ለማስፈፀም የወጣ የውስጥ
አሰራር ማንዋል አዘጋጅቷል፡፡
1.1. የውስጥ አሰራሩ ተፈፃሚነት ወሰን

 ይህ የውስጥ አሰራር ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ የክፍያ መንገዶች እና ግንባታቸው ወደፊት የሚጠናቀቁ
የክፍያ መንገዶችን የሚጠቀሙ ጠቅላላ ክብደታቸው ከ3,500 ኪሎ ግራም በላይ በሆነ ተሽከርካሪዎች
ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
 በዚህ አንቀጽ(491 ንዑስ አንቀጽ 1) የተደነገገው ቢኖርም ይህ የውስጥ አሰራር በእሳት አደጋ መከላከያ
ተሽከርካሪዎች፣ የተፈጥሮ አደጋ መከላከል ስራ ላይ በተሰማሩ ተሽከርካሪዎች፣ በድንገተኛ አደጋ
የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ስራ ላይ በተሰማሩ ተሽከርካሪዎች፣ የነዳጅ ጭነት
ተሽከርካሪዎች፤ ሀገሪቱ ከሌሎች መንግስታት ጋር ባደረገችው ስምምነት የሚጓዙ ተሽከርካዎች እና ልዩ
ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው ቢኖርም የግንባታ ሥራ በሚከናወንበት አካባቢ
የሚንቀሳቀሱ የግንባታ ተሽከርካሪዎች የበላይ አመራር ልዩ ፍቃድ የተሰጣቸዉ ተሽከርካሪዎች ላይ
ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
የቀጠለ…

 ሚኒስቴሩ የሚያወጣው መመሪያ አባሪ ተደርጎ የዚህ የውስጥ አሰራር ማንዋል አካል ይሆናሉ፡-
 ስለ መመዘኛ መሳሪያዎች
 የተሽከርካሪን ክብደት እና መጠን ስለመወሰን
 የተፈቀደ የተሽከርካሪ መጠን
 ስለተቀጣይ ተሸከርካሪዎች
 ከተሽከርካሪ አካል ውጭ የሚውል ጭነት
 በመንገድ ላይ እንዲያርፍ የተፈቀደ ከፍተኛ ክብደት
 ከብሪጅ አቅም ጋር በተያያዘ የሚፈቀድ ከፍተኛ ክብደት
 ስለመመዘኛ መሳሪያዎች
 ደንብ ቁ. 491አንቀፅ 4(1) መሰረት በዚህ ደንብ የሚሸፈን ማንኛውም መመዘኛ መሳሪያ
ብቃት ባለው ሰው በሶስትዮሽ ትራንስፖርት እና ትራንዚት ፋሲሊቴሽን ፕሮግራም ደረጃ
መሰረት ፈቃድ ማግኘት እና በሁሉም ሚዛን ጣቢዎች ላይ ይህንን የሚያረጋግጥ የምስክር
ወረቀት መለጠፍ ይኖርበታል፡፡
1.2. ዓላማ

 የተሽከርካሪ መኪናዎች ክብደት መጠንን ለመወሰንና ለመቆጣጠር የወጣ


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በኢንተርፕራይዙ በሁሉም ቅርንጫፍ መስሪያ
ቤቶች ተግባራዊ በማድረግ መንገዶቻችንን ከከፍተኛ ጉዳት ለመጠበቅ የሚያስችል
የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ነው፡፡
 በተጨማሪም በዚህ ደንብ ላይ የተቀመጠው የቅጣት መጠን አሽከርካሪዎችን የሚያስተምር
እና ደግመው ተመሳሳይ ጥፍት እንዳይፈፅሙ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ እና በመንገዳችን ላይ
ለሚደርሰው የጉዳት ካሳ ታሳቢ ያደረገ ነው ፡፡
1.3. ቁጥጥር ስለማድረግ

 ኢንተርፕራይዙ በሁሉም የክፍያ መንገዶች የማናቸውም ተሽከርካሪ ክብደት


ወይም መጠን በዚህ ደንብ በተደነገገው መሰረት መሆኑን ለመቆጣጠር
ተሽከርካሪውን የመመርመር ተግባራትን ይፈጽማል፡፡

 ኢንተርፕራይዙ ሚዛኖችንና ሌሎች ክብደትን ለመመዘን የሚያስችሉ


መሳሪያዎችን በመንገድ ላይ በመትከልና በትራፊክ ምልክቶች አማካኝነት
በማመላከት የማናቸውም ተሽከርካሪ አክስል ክብደት እና ጠቅላላ ክብደት በዚህ
ደንብ በተፈቀደው መሰረት መሆኑን ለመቆጣጠር የመመዘን እና አስፈላጊ የሆኑ
በዚህ ደንብ የተደነገጉ ሌሎች ተግባራትን ይፈጽማል፡፡
1.4. የክብደት መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሁኔታ

o ተሽከርካሪው የክብደት ሚዛን ጣቢያ ከመግባቱ በፊት ያለው የፍጥነት ወሰን በሠዓት
10 ኪሎ ሜትር ማለፍ የለበትም ይህንንም የሚገልፅ ምልክት ወይም የፍጥነት
መቀነሻ ተግባራት መፈፀም ይኖርበታል፡፡

o ወደ ክብደት ሚዛን ጣቢያው ማንኛውም ተሽከርካሪ ተከታትሎ እንዳይገቡ ቁጥጥር


መደረግ ይኖርበታል፡፡

o የክብደት ሚዛን ጣቢያ የትርፍ ጭነት እቃ ማራገፊያ ቦታ ማዘጋጀት እና


አስተማማኝ የጥበቃ ሁኔታ እንዲኖር መደረግ ይኖርበታል፡፡
1.5.ከባድ ተሽከርካሪ የሚያልፍበት ሂደት

ዝግጅት

መለካት
እንዲራገፍ ይደረጋል የተፈቀደ እንዲያልፍ ይደረጋል
ያልተፈቀደ

ክፍያ ይፈፀማል

እንዲመለስ ይደረጋል
1.6. የቅጣት አሰጣጥ ሂደት

ክብደት
ተቆጣጣሪ

ቶል ኦቨር አሽከርካሪ
ፋይናንስ
ሎድ

ኦቨር ሎድ
ሱፐርቫይዘር
1.7. የቅጣት አሰጣጥ ሁኔታ

1. ሳይመዘን ያለፈ ተሽከርካሪ 2000 ብር ተቀጥቶ እንዲመለስ ይደረጋል፡፡

2. የኃላ አክስል ሳያወርድ ጭነት የጫነ ተሽከርካሪ 2000 ብር ተቀጥቶ

እንዲያወርድ ይደረጋል

3. ትርፍ ጭነት በመጫን ትኬት ሳይዝ ጥሶ የገበ ተሽከርካሪ 5000 ብር

ይቀጣል፡፡

4. ጠቅላላ ትርፍ ጭነት እና አክስል ትርፍ ጭነት፤ በትርፍ ጭነቱ ክብደት


2. የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት እና ተግባራት

2.1.የመንገድ ሀብት አስተዳደር ቡድን መሪ


 አጠቃላይ የአሰራር ማንዋሉን ተፈፃሚነት በመከታተል ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፡፡
 ስለ ክፍሉ 24/7 ኦፕሬሽን ከሁሉም የክብደት ሚዛን መቆጣጠሪያ መረጃ በማሰባሰብ ለዳይሬክቶሬቱ መቅረብ ያለበትን ሪፖርት
በወቅቱ ያቀርባል፡፡
 የትርፍ ጭነት የሚወርዱ ማራገፊያ ክሬን በሁሉም የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ጣቢያዎች ላይ እንደ ኦፕሬሽን ሁኔታዎችን
በመከታተል መፍትሔ ይሰጣል፡፡
 በተወሰነ ጊዜ ሱፐርቪዥን በማካሄድ የክፍሉን የክብደት ሚዛን መቆጣጠሪያ ሲስተሞችን/እቃዎችን ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ
ይቆጣጠራል (Inspecation & Supervision) በማድረግ ይፈትሻል፡፡በስራው ሂደት ብልሹ አሰራሮች ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን
በመከታተል አሰራሮችን ይዘረጋል፣ በስራ ላይ የተከሰቱ ግኝቶችን በማጣራት እና በመመርመር እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
 24/7 የኦፕሬሽን መረጃዎች በአግባቡ እና በሚፈለገው የጥራት ደረጃ መመዝገባቸውን ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 የትርፍ ጭነት ክፍያ በአግባቡ መሰብሰቡን እና ያልተሰበሰቡ ክፍያዎች ካሉ በተደራጀው መረጃ መሰረት ቅጣቱን ጨምሮ በ30 የስራ
ቀናት ውስጥ ወደ ህግ አግባቡ በመውሰድ እንዲከፈሉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የክፍያ ሁኔታ በ15 ቀናት ውስጥ ካልተከፈለ 20%
እንዲሁም በ30 ቀናት ውስጥ ካልተከፈለ 50% የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡

 በትርፍ ጭነት ምክንያት የወረዱ የደንበኞች ንብረቶች በአግባቡ ጥበቃ ማግኘታቸውን ክትትል ማድረግ ይኖርበታል፡፡
2.2. የትራፊክ ደህንነት ባለሙያ

 አጠቃላይ የአሰራር ማንዋሉን ተፈፃሚነት በመከታተል የጭነት ሚዛን ቁጥጥር ሂደቱን ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፡፡
 ተንቀሳቃሽ የክብደት ሚዛን ስራ እና የቋሚ ሚዛን ክብደት ስራን በወቅቱ ያከናዉናል፣ ከክብደት በላይ የጫኑ
ተሸከርካሪዎች የትርፍ ጭነት ማራገፍ ስራውን በበላይነት ይመራር፣ ይቆጣጠራል፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ መፍትሔ
ይሰጣል፡፡
 በመንገዱ መግቢያ በሮች ላይ የሚደረጉ የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ስራዎችን በሀላፊነት እንዲሰራ ክትትልና ድጋፍ
በማድረግ አፈጻጸሙን መከታተል፡፡
 በስራ ላይ ለሚከሰቱ ክፍተቶችና ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ያሳያል፤ ከአቅም በላይ ከሆነ ለክፍሉ ቡድን መሪ
በወቅቱ ማሳወቅ፡፡
 ለአሽከርካሪዎች እና ለተሽከርካሪ ባለንብረቶች ስለ ክብደት ጭነት እና ስለ አሰራር ሁኔታው የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስራዎች እንዲከናወን ያደርጋል፤ ያዘጋጃል፤ ሃሳብ ይቀበላል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
 በስራው ሂደት ብልሹ አሰራሮች ሊፈጥሩ የሚችሉ ሠራተኞችን በመከታተል አሰራሮችን ይዘረጋል፣ በስራ ላይ
የተከሰቱ ግኝቶችን በማጣራት እና በመመርመር እርምጃ ይወስዳል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስተዳደራዊ እርምጃ
እንዲወሰድ ሪፖርት ያደርጋል፡፡ይኖርበታል፡፡(ይህ ተግባራዊ የሚሆነው ቋሚ ሚዛን በሚኖርበት ጣቢያ ሲሆን በሌሎቹ ግን
በቶል ኦፐሬሽን በኩል የሚፈፀም ይሆናል)፡፡
2.3.የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሱፐርቫይዘር

 24/7 የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ስራውን የጭነት ተሸከርካሪ ሚዛን ቁጥጥር ሰራተኛ የፈረቃ
ሁኔታ በማመቻቸት ለሚደረጉ ስራዎችን በኃላፊነት እንዲሰራ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ
አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
 በስራው ሂደት ብልሹ አሰራሮች ሊፈጥሩ የሚችሉ ሠራተኞችን በመከታተል አሰራሮችን
ይዘረጋል፣ በስራ ላይ የተከሰቱ ግኝቶችን በማጣራት እና በመመርመር እርምጃ ይወስዳል፣
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 የተሸከርካሪ ባለንብረቶች የትርፍ ጭነት ክፍያ እንዲከፈል ሰነዶችን በማዘጋጀት ፋይናንስ
እንዲከፍሉ ያደርጋል፣ የከፈሉበትን መረጃዎች በማየት እንዲለቀቁ ፍቃድ ይሰጣል፡፡
የቀጠለ…
 የትርፍ ጭነት የሚያወርዱ አሽከርካሪዎች/ባለንብረቶች ከትርፍ ጭነት ክፍያ ውጪ በክፍያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚከናወኑ

የጥበቃ አገልግሎት እና ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ክፍያዎች እንዲከፍሉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 ንብረት የቆየበት ክፍያ፤
 የተሽከርካሪ ማቆያ ክፍያ፤

 የትርፍ ጭነት መረጃዎች በማደራጀት ለቅርብ ኃላፊ የ24 ሠዓት ሪፖርት መላክ ይኖርበታል፡፡
 ከትርፍ ጭነት ጋር ሌላ የመንገድ ሀብት ጉዳት ከደረሰ የተጎዱ ንብረቶች የካሳ ክፍያ እና የአገልግሎት ክፍያ የውስጥ አሰራር

ደንብ 2 የሚፈፀም ይሆናል፡፡


 እያንዳንዱ ወደ ሚዛን ጣቢያ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች በሲስተም ስክሪን በመቆጣጠር የእያንዳንዱን ትርፍ ጭነት

በመመዝገብ በሲስተሙ ጋር መቀናጀት አለበት፡፡


2.4. የጭነት ተሽከርካሪ ሚዛን ቁጥጥር ሰራተኛ

 ክብደታቸው 3500 ኪሎ ግራም በላይ የሆኑ ማንኛውም ተሽከርካሪዎች ጭነት ጫነም አልጫነም
በየተራ ወደ ሚዛን ጣቢያው እንዲገቡ ያደርጋል፡፡
 ከክብደት በላይ የጫነ ተሽከርካሪ መኖሩን ሲስተሙን በመታገዝ ካወቀ እንዲቆም በማድረግ ለትርፍ
ጭነት ማውረጃ የተዘጋጀ ቦታ እንዲሄድ በማድረግ ለቅርብ ኃላፊው የመጣውን ትርፍ ጭነት
ያሳውቃል፡፡
 ወደ ሚዛን ጣቢያው ሳይገባ የሚሄድ ማንኛውም ተሽከርካሪ ቅርብ ላለው ትራፊክ ፖሊስ ወይም
ለቅርብ ኃላፊው በመንገር ወደ ክፍያ ጣቢያው ላይ እንዲያዝ በማድረግ እንዲመዘን በማድረግ
ከክብደት በላይ ጭነት መጫኑ ከተረጋገጠ ለትርፍ ጭነት ማውረጃ የተዘጋጀ ቦታ እንዲሄድ
በማድረግ ለቅርብ ኃላፊው የመጣውን ትርፍ ጭነት ያሳውቃል፡፡
 የክብደት መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሳይግቡ ጥሰው የሚያመልጡ ተሸከርካሪዎችን የሰሌዳ ቁጥራቸውን
በመያዝ ለቅርብ ኃላፊ ያሳውቃል፡፡
 የሲስተም ብልሽት ካጋጠመ ተሽከርካሪዎችን በማቆም ለቅርብ ኃላፊ ባለው መገናኛ ዘዴ ወቅቱ
ሪፖርት በማድረግ እንዲፈታ ያደርጋል፡፡ ችግሩ የማይፈታ ከሆነ በተንቀሳቃሽ ሚዛን መቆጣጠሪያ
2.5. ትራፊክ ፖሊስ ክፍል ኃላፊነት

 24/7 የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ላይ እገዛ በማድረግ የኦፕሬሽኑ ስራ እንዳይደናቀፍ ድጋፍ መስጠት
ይኖርበታል፡፡
 የትርፍ ጭነት የጫኑ ተሽከርካሪዎች የትርፍ ጭነት ለማውረድ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የትራፊክ
አደጋዎችን እንዳይደርሱ መከላከል እና የትራፊክ ፍሰቱ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 የክብደት ሚዛን ጣቢያውን ጥሰው የሚያመልጡ ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ተገቢውን ቅጣት እንዲሰጠው
ማድረግ ይኖርበታል፡፡ አምልጠው ወደ ሌላ ክፍያ ጣቢያ የሄዱ ተሽከርካሪዎች ካሉ በሁሉም ክፍያ
ጣቢያ ካሉ አባላት ጋር በመነጋገር እንዲያዝ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 ማንኛውም የህግ ጥሰት የሚፈፅም ተሽከርካሪ በትራንስፖርት ህግ መቀጣት ያለባቸውን በሙሉ መቅጣት
ይኖርበታል፡፡
2.6. የቶል ኦፕሬሽን (የጣቢያ ኃላፊ) ክፍል ኃላፊነት

• በመግቢያ በሮች በሚደረጉ የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሁኔታን ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ
የትርፍ ጭነት በሚኖርበት ወቅት የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሱፐርቫይዘር ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
• በትርፍ ጭነት ምክንያት የመግቢያ በር ዘግቶ የቆመ ተሽከርካሪ ካለ ንብረት እንዳይጎዳ በማድረግ
መስመሩን እንዲለቅ በማድረግ የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሱፐርቫይዘር ወይም ለሚመለከተው
ክፍል በማሳወቅ እስኪመጡ ድረስ ዳር ይዞ እንዲቆይ መደረግ ይኖርበታል፡፡
• ጥሶ ያመለጠ ማንኛውም ተሽከርካሪ ካለ ለሌሎች ክፍያ ጣቢያዎች ጋር በመነጋገር በመውጫ
በሮች እንዲያዝ በማድረግ በተያዘበት ክፍያ ጣቢያ ላለ የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሱፐርቫይዘር
ወይም ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
• ከትርፍ ጭነት ውጪ ሌሎች ቅጣቶች ካሉ ተፈፃሚ ያደርጋል፡፡
• በመግቢያ በሮች በትክክል የማይመዘን ማንኛውም ተሽከርካሪ በትክክል እንዲመዘን ያደርጋል፣
ችግሮች ካጋጠሙ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
• ሱፐርቫይዘር በሌለበት ጣቢያ ላይ በራሱ በኩል ተገቢው ቅጣት እንዲፈፀም ያደርጋል፡፡
2.7. ኤሌክትሮ ሜካኒካል እና አይሲቲ ክፍል ኃላፊነት

 24/7 የክብደት ሚዛን ቁጥጥር ሂደቱ እንዳይቋረጥ በየቀኑ የሲስተሙን ሁኔታ በማየት ጥገና
እንዲከናወን ማድረግ ይኖርበታል፡፡
 በጥገና ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ካሉ ጊዚያዊ መፍትሔ በመስጠት የኦፕሬሽን ሁኔታው
እንዳይቋረጥ በማድረግ ዘለቀታዊ መፍትሔ መስጠት ይኖርበታል፡፡
 በማታው ክፍለ ጊዜ የሲስተም መቆራረጥ ችግሮች ካጋጠሙ የሲስተም አድሚኒስትሬት
ወይም በፓወር ኦፕሬተር በኩል ችግሩ እንዲፈታ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
2.8. የቶል ፋይናንስ ክፍል ኃላፊነት

o ከመንገድ ሀብት አስተዳደር አባላት የትርፍ ጭነት የመጣለትን የክፍያ ማዘዣ ደብዳቤ
በማረጋገጥ የቅጣት ክፍያ ይሰበብባል፡፡
o ደንበኛው ለከፈለው ክፍያ ሕጋዊ የክፍያ ደረሰኝ ይሰጣል፡፡
o በክፍያው መጠን ላይ ችግሮች ካሉ በቅርብ ካለው የቅርብ ኃላፊ/ባለሙያ ጋር በመሆን
ደንበኞች እንዳይጉላሉ ቅድሚያ በመስጠት በጋራ በመሆን ይፈታል፡፡
o የክፍያ ስሌት ስህተት ካለ በወቅቱ ክፍያውን ያዘጋጀው/ያረጋገጠው ባለሙያ ኃላፊነት
ይወስዳል፡፡
2.8. የህግ አገልግሎት ክፍል ኃላፊነት

 ደንበኛው ለትርፍ ጭነት የተጣለ ክፍያውን በ30 የስራ ቀናት ያልተከፈለ ከሆነ ተሸከርካሪው
ባለንብረት ቅጣቱንም በኢትዮጵያ የፍትሓ ብሔር ህግ መሰረት እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡
 የትርፍ ጭነት ክፍያ አቅም በላይ መሆኑን ባለጉዳይ በደብዳቤ ካሳወቀ ክፍያ ለመፈፀም
ፍቃደኛ ያልሁኑትን ደንበኞች በሚደርሰው መረጃ መሰረት ሙሉ ሰነዱን በመቀበል
በኃላፊነት ይከታተላል እንደአስፈላጊነቱ በህግ ይጠይቃል፡፡
 በዚህ አንቀፅ ከንዑስ አንቀፅ (1) እና (2) መሰረት የትርፍ ጭነት ቅጣት ክፍያ ጉዳዩን
ሲያስፈፅም ክፍያ እንዲቀበሉ ዳይሬክቶሬት በፁሑፍ ያሳውቃል፡፡ ከሕህግ ጋር የሚያያዙ
ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ያከናውናል፡፡
3. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

3.1.የቅሬታ አቀራረብ
 ባለጉዳዮች የትርፍ ጭነት ክፍያ ላይ ቅሬታ ያላቸው ከሆነ ለኢንተርፕራይዙ ዋና ስራ አስኪጅ
ወይም ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 ዋና ስራ አስኪያጅ (ቅርንጫፍ ) ወይም ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚመለከተው የስራ ክፍል ዳይሬክቶሬት ቅሬታውን በማየት በአምስት የስራ ቀን ውስጥ
አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡

 ቅሬታው የተመራላቸው ባለሙያዎች በተመራላቸው 48 ሰዓት የስራ ቀን ውስጥ ተገቢውን


የውሳኔ ሀሳብ በማዘጋጀት ለዳይሬክቶሬቱ ያሳውቃል፡፡
 ዳይሬክቶሬቱ የውሳኔ ሀሳቡን ቅሬታውን ለመራለት ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም ምክትል ስራ
አስኪያጅ ቀርቦ እንዲፀድቅ ካደረገ በኋላ ለመንገድ ሀብት አስተዳደር ክፍል እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
3.2. የኃላፊነት እና ተጠያቂነት

 በዚህ የውስጥ አሰራር ማንዋል እና የተሽከርካሪ መኪናዎች ክብደትና መጠንን ለመወሰንና


ለመቆጣጠር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ውስጥ የተመለከቱ የኢንተርፕራይዙ
የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በውስጥ አሰራር ማንዋል መሰረት ግዴታቸውን ያልተወጡ
እንደሆነ በኢንተርፕራይዙ የሥራ ደንብ እና መመሪያ መሰረት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
3.3 የውስጥ አሰራር ማንዋል ስለማሻሻል
 ይህ የውስጥ አሰራር ማንዋል አስፈላጊነቱ በኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪ ሲታመን
በማንኛውም ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡
3.4.የተሻሩ አሰራሮች

 የተሽከርካሪ የክብደት ወሰን እና የትርፍ ጭነት ቅጣት ጋር ተያይዞ ቀደም ሲልየነበሩ የውስጥ
አሰራሮች በዚህ ማንዋል ተሽሯል፡፡
 ከዚህ የተሽከርካሪ የክብደት ወሰን እና የትርፍ ጭነት ቅጣት የውስጥ አሰራር ጋር ተቃራኒ ይዘት
ያላቸው ቀደም ሲል ሲሰራባቸው የነበሩ ማንኛውም አሰራሮች በዚህ ማኑዋል ተሽሯል፡፡
3.5.የውስጥ አሰራር ማንዋሉ የሚፀናበት ጊዜ
 ይህ የውስጥ አሰራር ማንዋል በኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ የፀና
ይሆናል፡፡
ትርፍ ጭነት ሲገኝ የሚጣለው ቅጣት
ከተደነገገው አክስል በላይ ትርፍ ጭነት ሲገኝ የሚጣለው ቅጣት
ግብዓት ርቀት(ኪ.ሜ) ESA/ኪ.ሜ (ብር) የጥሰት ውጤት n-value
variables 300 1,21 6 4
አክስል መሪ አክስል የሚነዳ ነጠላ አክስል ጥንድ አክስል ባለሶስት አክስል
የተፈቀደ ክብደት = 8ቶን የተፈቀደ ክብደት= 10ቶን የተፈቀደ ክብደት =18ቶን የተፈቀደ ክብደት =24ቶን
የተፈቀደ ESA= 2.16 የተፈቀደ ESA= 1.45 የተፈቀደ ESA= 3.93 የተፈቀደ ESA= 3.68
ትርፍ ጭነት
የሚጣል ቅጣት መጠን (ብር)
ኪ. ግ ቶን
400 0.4 1010 603 794 7054
800 0.8 2179 1285 1634 8066
1200 1.2 3519 2056 2530 9129
1600 1.6 5045 2924 3484 10244
2000 2 6774 3895 4497 11412
2400 2.4 8724 4978 5573 12636
2800 2.8 10912 6182 6715 13916
3200 3.2 13357 7514 7924 15255
3600 3.6 16079 8984 9204 16654
4000 4 19097 10601 10557 18116
4400 4.4 22433 12374 11985 19641
4800 4.8 26108 14313 13493 21232
5200 5.2 30144 16428 15081 22891
5600 5.6 34563 18730 16755 24620
6000 6 39391 21229 18515 26420
6400 6.4 44651 23937 20365 28294
6800 6.8 50367 26863 22309 30243
25 7200 7.2 56567 30021 24350 32243
!
! !!
ለ ሁ
ግ ና

አ መ

You might also like