Professional Documents
Culture Documents
4 5897899500898355282
4 5897899500898355282
የትራንስፖርት ባለስልጣን
ታህሳስ/2013
አዲስ አበባ
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
1. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ---/2013 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም እንዲሰጠው ካላስፈለገ በስተቀር በትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 2
እና የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 1074/2010 አንቀጽ 2 የተዘረዘሩት ቃላት ትርጉም በዚህ
መመሪያ ውስጥ ተፈጻሚ ይሆናሉ::
የሚከተሉት ተጨማሪ ቃላትም ከዚህ በታች የተዘረዘረው ትርጓሜይኖራቸዋል፡፡
1. ”ባለስልጣን” ማለት የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ነው
2. ”አዋጅ” ማለት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫፈቃድ አዋጅ ቁጥር 1074/2010 ነዉ
3. ”ደንብ” ማለት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 1074/2010 ን ለማስፈፀም
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀ ደንብ ነዉ
4. “ተሀድሶ ስልጠና”ማለት የአሽከርካሪዎች ወይም በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ የተሰማሩ
ባለሙያዎች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ የተሻለ የአፈፃፀም ክህሎት እንዲኖራቸውና ከአዳዲስ
ቴክኖሎጂ ጋር ለማስተዋወቅ ታስቦ የሚሰጥ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ነው
5. “የሰልጣኝ መታወቂ”ማለት ፈቃድ ሰጪ አካል በሚያወጣዉ መስፈርት መሰረት የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ
ተቋማት አዘጋጅቶ ለሰልጣኞች የሚሰጡት መታወቂ ነው
1
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
6. “ተቆጣጣሪ” ማለት ከምዝገባ እስከ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ፤ እድሳትና ግልባጭ አሰጣጥ
ያለውን ሂደት የሚቆጣጠር የባለስልጣን ወይም የፈቃድ ሰጪ አካል ሰራተኛ ነው፡፡
7. “ፈቃድ ሰጪ”ማለት ብቃቱ የተረጋገጠ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንዲሰጥ በባለስልጣኑ
ውክልና የተሰጠው የመንግስት አካል ነው፡፡
8. “አራተኛ ክፍል ያጠናቀቀ” ማለት በመደበኛ ትምህርት አራተኛ ክፍልን ያጠናቀቀበት የትምህርት
ማስረጃ ነው፡፡
9. “ስምንተኛ ክፍል ያጠናቀቀ” ማለት የስምንተኛ ክፍል ፈተና ማለፉን የሚያሳይ አግባብነት ካለው
ትምህርት ቢሮየተሰጠ የት/ት ማስረጃ ነዉ፡፡
10. “አሥራኛ ክፍል ያጠናቀቀ” ማለት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የአስረኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና
መዉሰዱን ወይም በመደበኛ ትምህርት ሂደት የአስረኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቁ እና ወደ አስራ አንደኛ
ክፍል መዛወሩን የሚያሳይ የት/ት ማስረጃ ነዉ
11. “ማስተማሪያ ፈቃድ” ማለት ባለስልጣን መ/ቤቱ በሚያወጣው መስፈርት መሰረት ፈቃድ ሰጪ አካላት
አዘጋጅቶ ለአሰልጣኞች የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡
12. “ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ“ ማለት የአውቶሞቢል ምድብ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድን
ለማግኘት በእራሱ ወይም በቤተሰብ ተሸከርካሪ የሚሰለጥን ሰልጣኝ ለአንድ የስልጠና ዙር
እንዲያሰለጥን የሚሰጥ የማስተማሪያ ፈቃድ ነው፡፡
13. ”ቤተሰብ” ማለት እስከ ሁለተኛ ደረጃ የሚቆጠር የሥጋ ወይም የጋብቻ ዝምድና ያለው ዘመድ ነው፡፡
14. ”ኤጀንሲ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀፅ 33 (4) (ረ) መሰረት የተቋቋዉ የስደተኞችና ከስደት
ተመለሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ማለት ነዉ
3. ዓላማ
ግልጽ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የእጩ አሽከርካሪዎች የምዝገባ፣ የስልጠና፣የምዘና እንዲሁም የአሽከርካሪ
ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እና የእድሳት አገልግሎት አሰጣጥን ማስፈን የሚስችል የአሰራር ስርዓት እንዲኖር
ማድረግ ነው፡፡
2
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ክፍል ሁለት
ስለ አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
4.የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ስልጠና ለመውሰድ ሰልጣኞች ስለሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎች
1. የጤንነት ማረጋገጫ የመስክር ወረቀት እንዲሰጥ ፈቃድ ከተሰጠውና በአካባቢው ከሚገኝ የመንግስት
ወይም የግል የህክምና ተቋም የተሰጠ የጤንነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣
2. የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የልደት ሰርተፍኬት ወረቀት፣
3. የሰልጣኝ ዕድሜ ሁኔታ አጠራጣሪ ሆኖ ከተገኘ የልደት ሰርተፊኬት ማስረጃ እንዲያቀርብ ይገደዳል፣
4. ለምድቡ የተቀመጠውን የዕድሜ ገደብ ያሟላ እና አግባብነት ያለውን የትምህርት ማስረጃ፣
5. የሞተር ሣይክል እና የአውቶሞቢል አመልካቾች ቢያንስ 4 ኛ ክፍል የሌሎች ምድብ አመልካች ቢያንስ
10 ክፍል ማጠናቀቁን የሚያሳይ የትምህርት ማስረጃ
6. ከሞተር ሣይክል እና ከአውቶሞቢል አመልካቾች በስተቀር የሌላ ምድብ አመልካቾች አግባብነት ካለው
ትምህርት ቢሮ የተሰጠ የ 8 ኛ ክፍል ሰርተፍኬትየትምህርት ማስረጃ፣
7. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 የተጠቀሰዉን ማቅረብ የማይችሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
ከሚሰሩበት መ/ቤት ወይም ትምህርት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ በመ/ቤቱ ወይም በዩኒቨርሲቲ መታወቂያ
መመዝገብ ይችላሉ፣
8. የዉጭ ሀገር ዜጎች የታደ ሰፓስፖርት፣ ለምድቡ የተቀመጠውን የዕድሜ ገደብ እና የትምህርት ደረጃ እንዲሁም በዚህ
አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ አንድ(1) የተጠቀሰውን ማስረጃ ማቅረብ፣
9. ማንኛዉም በኢትዮጵያ ዕዉቅና ያገኘ ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ለምድቡ የተቀመጠዉን የዕድሜ ገደብ፣
የትምህርት ደረጃ፣ በኤጀንሲዉ የተሰጠ መታወቂያ እና በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ አንድ(1) የተጠቀሰዉን ማስረጃ
ማቅረብ፣
5.ስለሰልጣኞችምዝገባ
3
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
1. ሰልጣኞች በፖስታ ወይም በቀጥታ መስመር ወይም በግንባር ወይም በወኪል መመዝገብ ይችላሉ፡፡
2. የተጭበረበረ ወይም አስመስሎ የተዘጋጀ ማስረጃ የሚያቀርብ ሰልጣኝ ጉዳይ በታወቀበት ጊዜ
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫፈቃድ አሰጣጥ ስርዓት እንዲያቋርጥ ለሰራው ወንጀል በህግ እንዲጠየቅ
ይደረጋል፡፡
3. ሰልጣኙ የተቋሙን የምዝገባ ቁጥር የያዘ የስልጠና መታወቂያ (Learener permit) መያዝ አለበት፡፡
4. ማሰልጠኛ ተቋሙ የተመዘገቡትን ሰልጣኞች ስም ዝርዝር በመረጃ መረብ ወይም በአካል ስልጠና
ከመጀመሩ ከ 3 ቀን በፊት ከተሟላ መረጃ ጋር ለፈቃድ ሰጪ አካል ማስተላለፍ አለበት፡፡
5. የሰልጣኞች መረጃ ፎቶ ኮፒዉ ከዋናው ጋር ተገናዝቦና ተረጋግጦ ፎቶኮፒውበፈቃድ ሰጪው አካል ሊያዝ
ይገባል፡፡
6. የንድፈ ሀሳብስልጠና
1. ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ በተሰጠዉ አሰልጣኝ ከሚሰለጥኑ የአውቶሞቢል ምድብ ሰልጣኞች በስተቀር
የሌሎች አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምድቦች የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በተዘጋጀው የስልጠና ስርዓተ-
ትምህርት መሰረት ፈቃድ ባላቸው ማሰልጠኛ ተቋማት ይሰጣል፡፡
2. ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ በተሰጠው አሰልጣኝ የሚሰለጥኑ የአውቶሞቢል ምድብ ሰልጣኞች በስርዓተ
ትምህርት በተዘጋጀው ማስተማሪያ መፅሃፍ መሰረት እራሳቸውን አዘጋጅቶ ለፈተና መቅረብ
ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ከተጠናቀቀ በኋላ በኮምፒዩተር የሙከራ ፈተና ልምምድ በማሰልጠኛ ተቋም
መሰጠት አለበት::
4. ማሰልጠኛ ተቋሙስልጠና ያጠናቀቁት እናለፈተና ብቁ የሆኑትን ሰልጣኞች ስም ዝርዝር በኮምፒዩተር
መረብ ወይም በደረቅ ፋይልለፈቃድ ሰጪ አካል ማስተላለፍ አለበት::
5. የምድቡ የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሰዓት እስኪጠናቀቅ ድረስ አንድ ሰልጣኝ በቀን ሁለት(2) ሰዓት መሰልጠን
አለበት፡፡
6. በማንኛውም የአሽከርካሪ የስልጠና ምድብ የተጀመረው የምድቡ ስልጠና መርሀ ግብር እስኪጠናቀቅ
ድረስ ሌላ የተመሳሳይ ምድብ የስልጠና መርሀ ግብር መጀመር የተከለከለ ነው፡፡
7. የተግባር ስልጠና
1. በአንድ የስልጠና ዙር በአንድ ተሽከርካሪ የተግባር ስልጠና መሰልጠን የሚችል የሰልጣኝ ብዛት ከአስር
(10) መብለጥ የለበትም
2. ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ በተሰጠዉ አሰልጣኝ ከሚሰለጥኑ የአውቶሞቢል ምድብ ሰልጣኞች
በስተቀር የሌሎች አሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ምድቦች በሥርዓተ ትምህርቱ መሰረት
ፈቃድ በተሰጣቸዉ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም ገብቶ መሰልጠን ይኖርባቸዋል፡፡
4
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
3. የትራፊክ ኮምፕሌክስ በገነቡት ክልሎች ከሚሰጠው አጠቃላይ የየምድቡ የተግባር ስልጠና ሰዓት
መካከል 30%ቱን በትራፊክ ኮምፕሌክስ ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ቀሪው 70% የስልጠና ሰዓት ከትራፊክ
ኮምፕሌክስ ውጭ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ይሆናል፡፡
4. ትራፊክ ኮምፕሌክስ በሌላቸው ክልሎች ከሚሰጥ አጠቃላይ የየምድቡ የተግባር ስልጠና ሰዓት መካከል
30% የትራፊክ ፍሰትበሌለበት ቦታ ላይ የሚሰጥ ሲሆን የተቀረው 70% የስልጠና ሰዓት በመስፈርቱ
መሰረት በተመረጠ ቦታ ላይ ይሆናል
5. የተግባር ስልጠና መስጫ መስመሮች ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ጠመዝማዛማ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የትራፊክ
መብራት፣ የመንገድ ላይ ቅቦች፣ አደባባይ አካቶ የያዘ መሆን አለበት፡፡
6. አንድ ሰልጣኝ የተቀመጠውን የተግባር ስልጠና ሙሉ በሙሉ ሰልጥነው ከማጠናቀቁ በፊቱ በስልጠና
ወቅት ብቻውን ማሽከርከር የሚችል መሆኑን አሰልጣኙ ባመነበት ጊዜ ብቻውን እያሽከረከረ
መለማመድ አለበት፡፡
7. የምድቡ ተግባር ስልጠና እስኪጠናቀቅ ድረስ አንድ አሰልጣኝ በቀን አንድ ሰዓት የተግባር ስልጠና
መሰልጠን አለበት፡፡
8. በማንኛውም የአሽከርካሪ የስልጠና ምድብ የተጀመረው የምድቡ የስልጠና ፕሮግራም እስኪጠናቀቅ
ድረስ በተመሳሳይ ተሽከርካሪ ሌላ የስልጠና ፕሮግራም መጀመር የተከለከለ ነው፡፡
8 . በቤተሰብ ወይም በሰልጣኝ ተሽከርካሪ የሚሰጥ የአውቶሞቢል ምድብ ስልጠና እና ፈተና
1. የአውቶሞቢል ምድብ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ስልጠና በማሰልጠኛ ተቋም ወይም ጊዜያዊ
የማሰልጠን ፈቃድ በተሰጠዉ አሰልጣኝ በሰልጣኙ ቤተሰብ ወይም በሰልጣኙ ተሽከርካሪ ሰልጥኖ
ለፈተና መቅረብ ይችላሉ፡፡
2. የአውቶሞቢል ምድብ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ስልጠናንበግል የሚሰለጥኑሰልጣኞች ስልጠና
ለመዉሰድ የሚጠየቁየትምህርት ደረጃ፣ ዕድሜ፣ የቀበሌ መታወቂያ እና የጤንነት ማረጋገጫ ምስክር
ወረቀትመሟላታቸዉን የማጣራት ሃለፊነት የፈቃድ ሰጪው አካል ይሆናል፡፡
3. የአውቶሞቢል ምደብ ዕጩ አሽከርካሪ ሰልጣኞች የንድፈ ሀሰብ ስልጠናን ማስልጠኛ ተቋም ገብቶ
መሰልጠን የግድ ሳይሆን በግሉ ተዘጋግጅቶ እና በራሱ ወይም በአሰልጣኙ ቀጠሮ በማስያዝ መፈተን
ይችላሉ፡፡
4. የአውቶሞቢል ምድብ ዕጩ አሽከርካሪ የተግባር ስልጠና ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ የተሰጠዉ
አሰልጣኝ በስልጠና ወቅት ሊደርስ ለሚችል ችግር ሁሉ ኃላፊነት አለበት፡፡
5. በቤተሰብ ወይም በሰልጣኙ ተሽከርካሪ የአውቶሞቢል ምድብ ሥልጠና የሚሰጥ አሰልጣኝ ቢያንስ 10 ኛ
ክፍልን ያጠናቀቀ እና ዕድሜው ከ 24 ዓመት ያላነሰ መሆን አለበት
5
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
6. በጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ የአውቶሞቢል ተግባር ስልጠና የሚያሰለጥን አሰልጣኝ የስልጠና መስጫ
ቦታንለፈቃድ ሰጪ አካል አስቀድሞ ማሳወቅ እና ቦታው ለስልጠና ምቹ መሆኑ ተረጋግጦ ሲፈቀድለት
ብቻ ስልጠና የሚጀመር ይሆናል፡፡
7. ከሞተር ሳይክል፣ ከባለሶስት እግር እና ከልዩ ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ማንቀሳቀሻ ፈቃድ በስተቀር
የማንኛውም ምድብ ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይዞ ቢያንስ የአምስት(5) ዓመት
የማሽከርከር ወይም የሶስት(3) ዓመት የአሰልጣኝነት ልምድ ያለዉ ሰው በጊዜያዊ ፍቃድ
የአውቶሞቢል የተግባር ስልጠና መስጠት ይችላል፡፡
8. የአነዳድ ስልጠና ሰዓት ጊዜ ርዝመት በስርዓተ ትምህርት ከተጠቀሰው የአውቶሞቢል ምድብ የስልጠና
ሰዓት (20 ሰዓት) ያነሰ መሆን የለበትም፡፡
9. በጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ በተሰጠዉ ሰዉ የአውቶሞቢል ምድብ ስልጠና ያጠነቀቁ ዕጩ
አሽከርካሪዎች በራሳቸው ወይም በአሰልጣኙ ቀጠሮ በማስያዝ በፈቃድ ሰጪ አካል የሚሰጠዉን ፈተና
መፈተን ይችላሉ፡፡
10. የተግባር ስልጠና መስጫ ተሽከርካሪ በሰልጣኙ ቤተሰብ ወይም በሰልጣኙ ስም የተመዘገበ መሆን አለበት
11. የተግባር ስልጠና መስጫ ተሽከርካሪ ባለስልጣን መ/ቤት የወጣዉንየ ተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት
ማረጋገጫ መስፈርት ያሟላ እና የዘመኑን የቴክኒክ ብቃት ምርመራ ሰርተፍኬት የተሰጠው ስለመሆኑ
በፈቃድ ሰጪ አካልመረጋገጥ አለበት
12. በስልጠና ወቅት የሰልጣኙን ሁኔታ በቅርብ ሆኖ አሰልጣኝ እንዲቆጣጠር የስልጠና መስጫ ተሽከርካሪ
የመቆጣጠሪያ ፔዳል የተገጠመለት መሆን አለበት
13. ጊዜያዊ ፈቃድ በተሰጠው አሰልጣኝ ሰልጥኖ ሁለት ጊዜ የተግባር ወይም የንድፈ ሀሳብ ወይም
ሁለቱንም የወደቀ ሰልጣኝ ፈቃድ በተሰጣቸው ማሰልጠኛ ተቋም ገብቶ እንደ አዲስ ሙሉ ስልጠና እና
ፈተና መውሰድ አለበት፡፡
14. የክልል እና ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ፈቃድ ሰጪ አካላት በግል የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
የተግባር ስልጠና ለሚያሰለጥ ሰዉ ጊዜያዊ የማሰልጠን ፈቃድ ይሰጣሉ፡፡
9. ስለንድፈ ሀሳብ ፈተና
1. ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ የስልጠና መከታተያ መታወቂያ ካርድና የቀጠሮ
ወረቀት ይዞ ካልቀረበ ወደ ፈተና አዳራሽ መግባት አይችልም
2. ፈተና ከመጀመሩ በፊት የሚመለከተው አካል ስለፈተናው አሰራር በግልጽ ተገቢውን ማብራሪያ
መስጠት አለበት
3. ፈተናው በሴኩሪቴ ካሜራ ቁጥጥር እየተደረገበት ለእያንዳንዱ ተፈታኝ በተዘጋጀ ኮምፒዩተር ላይ
ይሰጣል፡፡
6
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
4. ፈተናውን የሚፈተነው ተፈታኝ የሚፈተንበትን ቦታና ሰዓት በሰለጠነበት ማሰልጠኛ ተቋም በኩል
ከሰባት (7) ቀን በፊት አስቀድሞ ማወቅ አለበት፡፡
5. የጽሁፍ ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚወስደው ጊዜ 60 ደቂቃ ብቻ ነው
6. የጽሁፍ ፈተና ጥያቄዎችብዛት 50 እና ሁሉም ጥያቄዎች ምርጫ ሆኖ እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት ነጥብ
ይኖራቸዋል
7. የንድፈ ሀሳብ ፈተና ዝቅተኛ የማለፊያ ነጥብ 74% ሆኖ ከሃምሳ ጥያቄዎች መካከል ቢያንስ 37
ጥያቄዎችን መመለስ ይኖርበታል
8. ተፈታኞች ፈተና ከመጀመሩ 15 ደቂቃ ቀደም ብሎ በፈተና ቦታ መገኘት የሚጠበቅባቸው ሲሆን
የፈተና ሰዓት 15 ደቂቃ አሳልፎ የሚመጡ ተፈታኞች በእለቱ የጽሁፍ ፈተና እንዳይፈተኑ ይደረጋል፡፡
9. ሰዓት አሳልፈው የሚመጡ ተፈታኞች በተለዋጭ ፕሮግራም ከሌሎች ተፈታኞች ጋር መፈተን
እንዲችሉ ሁኔታዎች መመቻቸት አለባቸው
10. በፈተና ወቅት የሚኮራረጁ ተፈታኞች ከተገኙ ሁለቱም ማለትም ኮራጁ እና አስኮራጁ ከፈተና
አዳራሽ ከፈተና አዳራሽ እንዲወጡ ተደርጎ የእለቱ ኮራጁ እና አስኮራጁ ፈተና ይሰረዛል፡፡ ከተያዙበት
ቀን ጀምሮ ለሶስት ወራት ፈተና እንዳይፈተኑ ይታገዳሉ
11. ሌላ ሰዉ ፈተና እንዲፈተንለት ያደረገ ሰልጣኝ የዕለቱ የተፈታኙ ፈተና ተሰርዞ ከተያዘበት
ዕለትጀምሮ ለአንድ ዓመት ከፈተና የሚታገድ ሲሆን በወቅቱ ሲፈተን የተገኘዉም ጥፋተኛ ተፈታኝ
እና እንዲፈተንለት ያደረገው በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል
12. እያንዳንዱ ተፈታኝ ፈተናውን እንደጨረሰ ወዲያውኑ በተፈተነበት ኮምፒዩተር የፈተና ውጤት
እንዲያውቅ ይደረጋል
13. በፌዴራል ደረጃ ተዘጋጅቶ ከተሰራጨው የፈተና ባንክ ውስጥ የጽሁፍ ፈተና ጥያቄዎች ሁሉንም
የትምህርት ዓይነት ያካተተ ሆኖ የጥያቄዎቹ ብዛት እንደስልጠናው ሰዓት ስፋት የተለያዩ ሆኖ
በተቀመጠው ቀመር መሰረት መሆን አለበት
14. የጽሁፍ ፈተና የወደቀ ተፈታኝተጨማሪ ስልጠና መውሰድ ሳይጠበቅበት ሁለት ጊዜ በተከታታይ
መፈተን ይችላል፡፡ ሁለት ጊዜ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ ሰልጣኝ ክፍተቱ ሊሞላ የሚችል ዝግጅት
በማድረግ በ 1 ዓመት 2 ጊዜ ሙሉ የንድፈ ሀሳብ ፈተና መውሰድ ይችላል፡፡
15. የጽሁፍ ፈተና አልፎ የተግባር ፈተና ወይም የተግባር ፈተና አልፎ የፅሑፍ ፈተና የወደቀ ተፈታኝ
የአንድ ጊዜ የጽሁፍ ወይም የተግባር ፈተና ውጤት ለአንድ ዓመት ብቻ ያገለግላል:: ከአንድ ዓመት
በኋላ በራሱ ወጪ እንደ አዲስ ሰልጣኝ ማሰልጠኛ ተቋም ገብቶ ሙሉዉን የንድፈ ሀሳብና የተግባር
ስልጠና መሰልጠን ይጠበቅበታል፡፡
7
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
8
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
14. የሞተር ሳይክል የመሰናክል የተግባር ፈተና ተፈታኝ አንድ ጉቶ ከጣለ ወደሚሄድበት አቅጣጫ
የተሰጠውን የመሰናክል ነጥብ ሙሉ በሙሉ ያጣል፡፡
15. የጽሁፍ ፈተና የወደቀ ሰልጣኝ የተግባር ፈተና መፈተን ይችላል፤ እንደዚሁም የተግባር ፈተና የወደቀ
የጽሁፍ ፈተና መፈተን ይችላል፡፡
16. የትራፊክ ኮምፕሌክስ የመፈተኛ ሜዳ በሌለበት የሚፈተኑ ተፈታኞች ብቻቸውን እያሽከረከሩ
በቪዲዮ ካሜራ እየተቀረፀ መፈተን አለባቸው
17. አንድ አሽከርካሪ የተግባር ፈተና በሚፈተንበት ጊዜ ከፈተና ካርታ ውጪ ካልወጣ እና ጥፋቱ አደጋን
የማያስከትል ከሆነበሰራው ስህተት ነጥብ እንዲቀነስበት ይደረጋል እንጂ ፈተናውን እንዲያቋርጥ
አይደረግም
18. በሞተር ሳይክል የመሰናክል ፈተና ወቅት የተፈታኙ እግር መሬት ከነካ የሚፈተንበት
አቅጣጫየተሰጠውን ነጥብ ሙሉ በሙሉ ያጣል፡፡
19. የመሰናክል ፈተናን ጨምሮ ከአጠቃላይ የተግባር ፈተና ውጤት 40%ቱን በትራፊክ ኮምፕሌክስ
ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ቀሪውን 60% በተመረጡት መንገድ ላይ የመንገዱን የትራፊክ ሁኔታ እና የአየር
ንብረት ሁኔታን ግምት ውስጥ በማስገባት በዝቅተኛ፣ በመካከለኛ እና በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር
ይሰጣል
20. የትራፊክ ኮምፕሌክስ የሌላቸው ከመሰናክል ፈተና በስተቀር ሌላውን የአነዳድ ፈተና በመስፈርቱ
መሰረት በተመረጠ ቦታ ላይ የሚሰጥ ይሆናል
21. ለሁሉም ምድቦች የተግባር ፈተና ቀጥሎ በተገለፀው ሠንጠረዥ መሰረት የሚሰጥ ይሆናል
የፈተና መስመር ጎዳና ላይ የሚሰጥ ፈተና የመሰናክል ጠቅላላ
ተ.ቁ ምድብ ርዝመት ደርሶ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ፈተና ሰዓት የተግባር
መልስ በኪ.ሜ ድረስ የሚወስደው ጊዜ በደቂቃ ፈተና ሰዓት
በደቂቃ በደቂቃ
1 አውቶሞቢል፣ 10 30 20 50
ባለሦስት እግር
ህዝብ 1፣ ደረቅ 1 10 35 25 60
2 ደረቅ 2፣ ፈሳሽ 1 10 40 25 65
እና ህዝብ 2
3 ፈሳሽ 2፣ እና 10 50 15 65
ደረቅ 3
4 ህዝብ 3 10 45 25 70
5 ሞተር ሣይክል 10 25 10 35
9
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
10
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
11
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ተ. የተሰጠ
ቁ የፈተና ይዘት ነጥብ
12
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
1 ቅድመ ጉዞ በሚመለከት 4
1.1 ተሸከርካሪ ከማንቀሳቀሱ በፊት መፈተሽ የሚገባውን በተግባር ማሳየት 2
1.2 በር አከፋፈትና አዘጋግ/ጋቢና አገባብ/ 1
1.3 መቀመጫ ወንበር ፤ መስታወት፤ የደህንነት ቀበቶ ማስተካከልና ማሰር ' 1
2 ሞተር ማስነሳት በሚመለከት 4
2.1 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ አገባብ፣ 1
2.2 የሞተር ማስነሻ ቁልፍ አዟዟር፣ 1
2.3 ሞተር ማስነሳት 1
2.4 ዳሽ ቦርድ ምልከታ 1
3 ጉዞ አጀማመር እና ጉዞን በሚመለከት 8
3.1 መነሻ ማርሽ አገባብ፣ 2
3.2 የእጅ ፍሬን አለቃቀቅና የእግር ፍሬን አያያዝ 1
3.3 መሪ አያያዝ 1
3.4 መስታወት ምልከታ 1
3.5 የምልክት አሰጣጥ/ፍሬቻና የእጅ ምልክት/፣ 2
3.6 ነዳጅን ከመነሻ ማርሽ ጋር አጣጥሞ ስለመነሳት፣ 1
4 በተለያዩ የመንገድና ትራፊክ ሁኔታዎች ላይ የአነዳድ ባህሪ በተመለከተ 54
4.1 ረድፍ አጠባበቁ፣ 3
4.2 ረድፍ አለዋወጡ 3
4.3 መቅደምና ማስቀደም 3
4.4 መስታወትና ፍሬን አጠቃቀም 1
4.5 ፍጥነቱ 2
4.6 ርቀት ጠብቆ ማሽከርከር 3
4.7 ምልክት፤ መብራት፤ መስመር አጠቃቀም
2
4.8 ፍሪስዮን አጠቃቀም 2
4.9 የነዳጅ መስጫ ፔዳል አጠቃቀም 2
4.1® ማርሽአጨማመርና አቀናነስ በተለያየ የመንገድ ሁኔታ' 4
4.11 ፍሬን አጠቃቀም 3
4.12 የመሪ አጠቃቀም 3
4.13 እይታ ምልከታ (Observation) ጥንቃቄ 3
4.14 ለእግረኛና ለሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ቅድሚያ መስጠት በሚመለከት 2
4.15 ¨ወደግራና ወደቀኝ አዟዟሩ 3
4.16 የኋላ ሚዛን አጠባበቅ 3
4.17 የኋላ አነዳድ በቀጥታና በኩርባ መንገድ 3
4.18 በመስቀለኛ በመገናኛ፤በባቡር ሀዲድ ስለማቋረጥና ስለመተላለፍ 3
4.19 ዞሮ ስለመመለስ U, turn, 3
13
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
14
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
15
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
16
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ አንድ(1) የሚሰጥ ፈተና ወይም በተገመገመው ቪዲዮ ካሜራ ውጤት
የወደቀ እጩ አሽከርካሪ ብቁ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ተጨማሪ ክፍያ መክፈል ሳይጠበቅበት ቀደም ሲል
በሰለጠነበት ማሰልጠኛ ተቋም ሰልጥኖ ብቁ ሲሆን እንደገና ይፈተናል፡፡
3. ለሙያ ቅርበት ያላቸው እና የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ይወጣሉ ተብሎ የታመነባቸው
ባለሙያዎችን ያቀፈ የገለልተኛ አካል ኮሚቴ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም በክልል
ወይም በከተማ መስተዳድር ትራንስፖርት ቢሮ ሊቋቋም ይችላል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 2 የተሰጠዉን ውሳኔ በማይቀበሉ አካላት ላይ ቀጥሎ ከአንቀጽ 5 እስከ 8
የተጠቀሱት እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡
5. የተሰጠዉን ውሳኔ ተቀብሎ ተግባራዊ በማያደርግ ማሰልጠኛ ተቋም ለ 3 ወር ምንም ዓይነት ስልጠና
እንዳይሰጥ ተደርጎ ሀሳቡን ሲቀይር፣ ለፈፀመዉ ጥፋት በጽሁፍ ይቅርታ ሲጠይቅና ውሳኔውን ተቀብሎ
ተግባራዊ ሲያደርግ ወደ ዘርፉ ይመለሳል፡፡ ነገር ግን ውሳኔውን እስከ መጨረሻ የማይቀበል ከሆነ ፈቃዱ
ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል፡፡
6. የተሰጠዉን ውሳኔ ተቀብሎ ተግባራዊ የማያደርግ ዕጩ አሽከርካሪ ከአንድ አመት በኋላ እራሱን
አብቅቶ ለፈተና እንድቀርብ ይደረጋል፡፡
7. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 6 የተሰጠዉን ዉሰኔ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ዕጩ አሽከርካሪ እስከ
መጨረሻ በየትኛውም ቦታ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንዳያገኝ የግለሰቡ መረጃ
ለሚመለከተው አካል ተላልፎ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
8. በወቅቱ ፈታኝ የነበረዉ ቴክኒሽያን ከቦታ ተነስቶ በየተኛውም አከባቢ የአሽከርካሪብቃት ማረጋገጫ
ስልጠናም ሆነ ፈተና መስጠት እንዳማይችል የሚገልፅ የግለሰቡ መረጃ ለሚመለከተው አካላት ሁሉ
ይተላለፋል፡፡
17
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ሠንጠረዥ አንድ(1) ፡- የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ከአንድ ምድብ ወደ ሌላ ምድብ ሲቀየር
ተ.ቁ (ሀ) ስልጠና
ከ የተግባር
የሚሰጡ ወደ (ለ)ሰዓት
ምድብ የተግባር ስልጠና
ምድብ ሲቀየር ሰዓት ምርመራ
1 የምድብ (ሀ)ን ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት
ደረቅ 1 10
ማረጋገጫ ፈቃድ ከተሰጠዉ በኃላ
ህዝብ 1 ደረቅ 2 25 የምድብ (ሀ)ን ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት
ማረጋገጫ ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
ፈሳሽ 1 25
የማሽከርከር ልምድ
ደረቅ 1 5 ------
ህዝብ 2 -----
ደረቅ 2፣ ፈሳሽ 1 10
2
3 ደረቅ 1 5 -----
ደረቅ 2፣ ፈሳሽ 1 10 -----
ህዝብ 3 የምድብ (ሀ) የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈሳሽ 2፣
15 ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
ደረቅ 3
የማሽከርከር ልምድ
4 የምድብ (ሀ)ን ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት
ህዝብ 1 10
ማረጋገጫ ፈቃድ ከተሰጠዉ በኃላ
ደረቅ 1 የምድብ (ሀ)ን ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት
ፈሳሽ 1 ማረጋገጫ ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
25 የማሽከርከር ልምድ
5 ህዝብ 1 5 -----
የምድብ (ሀ) የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ህዝብ 2 10 ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
የማሽከርከር ልምድ
ደረቅ 2
ፈሳሽ 1 5 ------
ፈሳሽ 2 የምድብ (ሀ) የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
25 ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
የማሽከርከር ልምድ
ህዝብ 1 5
ደረቅ 3 ህዝብ 2 10
18
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ደረቅ 2 5
ደረቅ 3 10
9 አዉቶሞቢ
ህዝብ 1፣ ደረቅ 1 20
ል የምድብ (ሀ)ን ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት
10 ሞተር ማረጋገጫ ፈቃድ ይዘዉ ቢያንስ የአንድ ዓመት
ባለሶስት እግር 8
ሳይክል የማሽከርከር ልምድ
11 ባለሶስት
ሞተር ሳይክል 10
እግር
12 ባለሶስት ወደ ሌሎች የምድቡን ሙሉ
እግር ምድቦች የስልጠና ሰዓት
ወይም
19
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ሞተር
ሳይክል
13 ሌሎች ባለሶስት እግር የባለሶስት እግር
ምድቦች ወይም ሞተር ወይም የሞተር
ሳይክል ሳይክል ሙሉ
የስልጠና ሰዓት
14. በታክሲ አገልግሎት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎችን ለማሽከርከር ስለሚጠየቁ መስፈርቶች እና የምስክር ሰርተፍኬት
ስለማደስ
ሀ. ስለሚጠየቁ መስፈርቶች
1. የአገልግሎት ጊዜ ያላላፈበት ቋሚየህዝብ ወይም የአውቶሞቢል ምድብ የአሽከርካሪ ብቃት
ያለው
2. የትምህርት ደረጃው ቢያንስ አስረኛ (10) ክፍል ያጠናቀቀ
3. እድሜው ከ 22 ዓመት ያላነሰ
4. የሚሰጠውን ልዩ የታክሲ ስልጠና ወስዶ የታክሲ አሽከርካሪ የምስክር ሰርተፍኬት ያለዉ
20
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
16. ጊዜያዊ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ወደ ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ስለመቀየር
1. ጊዜያዊ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ወደ ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ
የሚቀየረው በሁለት ዓመት ውስጥ ያደረሰው የትራፊክ ጥፋት ሪከርድ ነጥብ ከ 11 ያልበለጠ መሆን
አለበት፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ አንድ(1) መሰረት ወደ ቋሚ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሊቀየርለት
ያልቻለ እንደሆነ እና ያደረሰው የትራፊክ ጥፋት የሪከርድ ነጥብ ከ 12 እስከ 15 ከሆነበድጋሚ የተግባር እና
የንድፈ ሃሳብ ፈተና ወስዶ ብቃቱ ሲረጋገጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጊዜያዊ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ በድጋሚ ለ 2 ዓመት ይሰጠዋል፡፡
3. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ አንድ(1) በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ጊዜያዊ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ ያለው አሽከርካሪ ያደረሰው የትራፊክ አደጋ ወይም ጥፋት ሪከርድ ነጥብ 16 እና ከ 16 በላይ የሆነ
እንደሆነ የተሰጠው ጊዜያዊ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰረዛል፡፡
17. ስለጠፋ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ምትክ ወይም ግልባጭ ስለመስጠት
1. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የጠፋበት በአካል መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዞ መቅረብ
2. አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በትክክል መጥፋቱን በተዘጋጀው የቃለ መሃላ ቅጽ በፊርማ
ማረጋገጥ
21
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
3. የጠፋበት አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የእድሳት ጊዜ ገደቡ ያላለፈበት ከሆነ የአገልግሎት እና
የደብተር ክፍያ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡
4. የጠፋበት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የዕድሳት ጊዜ ያለፈበት ከሆነ አሽከርካሪው በዚህ
መመሪያ አንቀፅ 15 ንዑስ አንቀፅ አንድ (1) መሰረት የተግባር ፈተና ማለፍ አለበት
5. ፈቃድ ሰጪው አካል የጠፉ ፈቃዶችን በመረጃ መረብ ወይም በሌሎች መገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት ዋጋ
እንደሌላቸው ማሳወቅ እና መረጃዉን በየስድስት ወሩ ለባለስልጣን መ/ቤት ማስተላለፍ አለበት፡፡
6. በአንድ ዓመት ውስጥ ከሁለት ጊዜ በላይ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የጠፋበት መሆኑን
በመግለፅ ምትክ እንዲሰጠው ጥያቄ የሚያቀርብ አሽከርካሪ ግልባጭ ማግኘት የሚችለው የምትክ
መደበኛ ክፍያ ሶስት እጥፍ እንዲከፍል ይደረጋል
7. ግልባጭ ወይም ምትክ የወሰደ አሽከርካሪ በእጁ ሁለት(2) የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይዞ
ከተገኘ የተሰጠው ፈቃድ ለሁለት ዓመት ይታገዳል
18. ኢንተርናሽናል ወይም መደበኛ የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ
1. የኢትዮጵያን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ከሚቀበሉት ሀገራት ኢንተርናሽናል ወይም የሀገሩን
መደበኛ መንጃ ፈቃድ ይዘው የሚመጡ ዜጎች ለ 45 ቀናት የያዙትን መንጃ ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ መንጃ
ፈቃድ መቀየር ሳይጠበቅባቸው የአውቶሞቢል ወይም በአውቶሞቢል የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ ማሽከርከር የተፈቀደ ማንኛውም ተሽከርካሪ ማሽከርከር ይችላሉ፡፡
2. በያዘው የውጪ ሀገር መንጃ ፈቃድ ለ 45 ቀናት ማሽከርከር እንዲፈቀድለት ጥያቄ የሚያቀርብ ዜጋ
የፓስፖርት እና የያዘውን መንጃ ፈቃድ ኮፒ ለፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ለክልል
ትራንስፖርት ቢሮ ወይም ለከተማ መስተዳድር ትራንስፖርት ቢሮ ሲያቀርብ ከኢትዮጵያ ጋር
ስምምነት ካላቸው ሀገር የመጣ መንጃ ፈቃድ ስለመሆኑ ተረጋግጦ ጊዜያዊ ፈቃድ ይሰጣል፣
3. የሚሰጠው የ 45 ቀን ጊዜያዊ የማሽከርከር ፈቃድ ቀን የሚቆጠረው ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት
ቀን ጀምሮ ይሆናል
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ-2 መሰረት ፈቃድ የተሰጠውሰው ጊዜያዊው ፈቃድ እስኪያበቃ ድረስ
በሚያሽከረክርበት ጊዜ ሁሉ ከውጭ ሀገር ይዞ የመጣውን መንጃ ፈቃድ ዋናውን (ኦርጅናል)፣
የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ እና ፓስፖርቱን ይዞ መገኘት አለበት፣
5. ከ 45 ቀን በላይ በኢትዮጵያ የሚቆይ ማንኛውም ግለሰብ ከውጭ ሀገር ይዞ የመጣውን መንጃ ፈቃድ
ወደ ኢትዮጵያ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋጫ ፈቃድ መቀየር ይኖርበታል፣
6. የውጭ ሀገር መደበኛ መንጃ ፈቃድ ወይም ኢንተርናሽናል መንጃ ፈቃድ ወደ ኢትዮጵያ መንጃ ፈቃድ
ሲቀየር የኢትዮጵያን መንጃ ፈቃድ የሚቀበሉት ሀገር መንጃ ፈቃድ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
7. በመንጃ ፈቃድ ሰጪ ዉጭ ሀገር ወይም በሚመለከተው አካል ግለሰቡ የያዘውን መንጃ ፈቃድ ትክክለኛ
እና የአገልግሎቱ ጊዜ ያላለፈበት ስለመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ማረጋገጫ
22
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
23
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
1. አዲሱ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በአንድ በማዕከል እስኪታተም ድረስ በየክልሉ
የሚሰጠውየአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በስታንዳርድ መሰረት መሆን አለበት፡፡
2. የትራፊክ ኮምኘሌክስ የሌለው የፈቃድ ሰጪ አካል ይህ መመሪያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት አመት ጊዜ
ውስጥ የተሟላ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ማዘጋጀት አለበት፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን የፈተና ስርዓቱ
በተመረጠው የተግባር ፈተና መስጫ ቦታ ማለትም ክልሉ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የትራፊክ
ኮምኘሌክስ ለመገንባት ዕቅድ በያዘላቸው ከተሞች የተግባር ፈተና መፈተን አለበት
3. የተግባር ፈተና ለመፈተን የሴኩሪቲ ካሜራ የሌላቸው የፈቃድ ሰጪ አካላት በቪዲዮ ካሜራ የታገዘ
የተግባር ፈተና መፈተን አለባቸው
ክፍል ሶስት
የተለያዩ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
23. የባለስልጣኑ ተግባርና ኃላፊነት
24
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ይኖሩታል፤
1. በፈቃድ ሰጪው አካል መሟላት የሚገባቸውን ዝርዝር መስፈርቶች ማውጣት፣
2. ለፈቃድ ሰጪው አካል ዉክልና መስጠት፣ ተግባሩን በአግባቡ እያከናወነ መሆኑን መከታተል፣ ብቃት
የሌለው ሆኖ ሲገኝ የተሰጠውን ዉክልና ማገድ ወይም መሠረዝ፣
3. የአሽከርካሪ ብቃት ሥልጠና ለሚሰጡ ተቋማት የሚያስፈልገውን የስልጠና መስጫ ስርዓተ ትምህርት
ዝግጅት ከቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ጋር ማዘጋጀት፣
4. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ደብተር ጥራትን፣ ይዘትንና ቅርጽን መወሰን፣ የብቃት ማረጋገጫ
ካርዶችን በማሳተም በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
5. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ የወሰዱ እና ጥፋት የፈጸሙ አሽከርካሪዎችን ዝርዝር በአገር አቀፍ
ደረጃ መያዝ
6. የማሰልጠኛ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን ሀገር አቀፍ
መስፈርቶች የመወሰን፣ ተግባራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ ስለመሆናቸው ቁጥጥርና ክትትል የማድረግ፣
ብቃታቸው የተጓደለ ሆኖ ሲያገኘው የምስክር ወረቀታቸው እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ የማድረግ፤
7. የማሽከርከር ብቃት ስልጠና የሚሰጡ የማሰልጠኛ ተቋማት፣ አሰልጣኞች እና የማሽከርከር ብቃት
ማረጋገጫ ፈተና የሚሰጡ የፍቃድ ሰጪ አካል ባለሞያዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶችንና
ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ-ምግባር መርሆዎችን እንዲሁም መስፈርቶቹን ሲያጓድሉ ወይም የስነ-ምግባር
መርሆዎቹን የሚጻረር ተግባር ሲፈፅሙ የእርምት እርምጃ መዉስድ
25
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
26
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
10. በንድፈ ሀሳብ ፈተና ወቅት ለተፈታኞች የፈተና ጥያቄ መልስ ከመናገር መቆጠብና የሚኮርጁትን
ተፈታኞች በጥብቅ መከታተል
27
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
17. ሥልጠና ከተጀመረ በኋላ የተግባር ስልጠና መስጫ ተሽከርካሪ የቴክኒክ ብልሽት ቢያጋጥም ወዲያውኑ
ለፈቃድ ሰጪ አካል በማሳወቅ ደረጃውን የሚመጥን ሌላ ተሽከርካሪ የመተካት ግዴታ አለባቸው፡፡
18. በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 17 የሚተካ ተሸከርካሪ በምድብ የተቀመጠ መስፈርት የሟላ የአመቱን
የቴክኒክ ብቃት መረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው እና በፍቃድ ሰጪ አካላት የቴክኒክ ብቃት የተረጋገጠ
እንዲሁም ጥምር ፍሬን እና ፍሪሲዮን የተገጠመለት መሆን አለበት፡፡
19. በስልጠና እና በፈተና ወቅት በተሽከርካሪ ለሚደርሰው አደጋ ማሰልጠኛ ተቋሙ ተጠያቂ ይሆናል፡
20.በየዙሩ እና በየምድቡ የንድፍ ሃሳብና የተግባር ፈተናካስፈተናቸው ሰልጣኞች መካከል 70 በመቶ እና
ከዚያ በላይ ማሳለፍ
21. የአሰልጣኞችን ወይም የሰልጣኞችን ማስረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣ የቀረበው ማስረጃ አጠራጣሪ ሆኖ
ሲገኝ ማስረጃውን ከሰጠው አካል ማረጋገጫ መጠየቅ
28.የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት መስፈርት(Standards)
የትራንስፖርት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 7(2)(በ) ባለሞተር ተሽከርካሪ መንዳት
ለሚያስተምሩ ሰዎችና ማሰልጠኛ ተቋማት የሥራ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ማውጣትና ተግበራዊነቱን
መከታተል እንዲሁም በአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 1074/2010 አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀፅ 8
የማሰልጠኛ ተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸዉ ሀገር አቀፍ
መስፈርቶችን በመመሪያ የመወሰንበተሰጠው ሥልጣን መሠረትማሰልጠኛ ተቋማት የሚያቋቁሙ
የመንግስት አካላት እና የግል ባለሀብቶች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ ከዚህ በታች
የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አውጥቷል፡፡
28
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
29
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
የሞላ
የህዝብ 2፣ የደረቅ 2፣ ለፈሳሽ 1
ቢያንስ 30 ዓመት የሞላ
ህዝብ 3፣ ደረቅ 3 እና ፈሳሽ 2
ቢያንስ 35 ዓመት የሞላ
4 ቢሮዎች /መፀዳጃ ክፍል ቢያንስ 20 ካሬ ሜትር ስፋት፣ ስፋቱ ከ 8 ካሬ ሜትር ያለነሰ በቂና
ከሶስት ያለነሰ ወንበር እና ጠረጴዛ ምቹ ወንበር እና ጠረጴዛ ያለዉ
እንዲሁም ቴሌቪዥን ያለው የአሰልጣኞች ቢሮ
የሚል የእንግዳ መቀበያ ለወንድና ሴት ለብቻ ሆኖ ስፋቱ ቢያንስ
ስፋቱ ቢያንስ 10 ካሬ ሜትር የሆነ 6 ካሬ ሜትር የሆነ መፀዳጃ ክፍል
ወንበር እና ጠረጴዛ ያለዉ
ዳይሬከተር ቢሮ
ስፋቱ 5 ሜትር በ 6 ሜትር (30) የማስተማሪያ ቻርቶች፣ ሞዴል
ካሬ ሜትር የሆነ የትራፊክ መብራት ምልክት
25 ደረጃቸውን የጠበቁ ምቹና በአንድ ጊዜ እስከ 25 ሰልጣኞችን መያዝ
ማስደገፊያ ያላቸው ወንበሮች እና የሚችል
ጠረጴዛዎች፣ ጣሪያቸው ቢያንስ 2.5 ሜትር ከፍ ብሎ
በቂ ብርሃንና ተስማሚ አየር የተሰሩ ክፍል
ማስተማሪያ ክፍል
5 የሚያስገቡ መስኮቶች ያለዉ በኢንተርኔት መረብ ከኢንፎርሜሽ
የመማር ማስተማር ሂደትን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ጋር የተገናኘ
የሚያፈጥኑ በንክኪ የሚሰራ ማስተማሪያ ክፍል
እስክሪን ያለዉ ሰሌዳ (touch
screen board) ወይም ነጭ ሠሌዳ፣
ኮምፒዉተር፣ ፕሮጄክተር፣ ፍላት
እስክሪን ቲቪ
6 የቤተ መፃህፍት እና የኮፒውተር ምቹ እና በቂ ወንባር እና ጠረጴዛ ያለዉ
አገልግሎት በአንድ ላይ መስጠት በኢንተርኔ መረብ የተገናኙ የመላማመጃ
ቤተ መፃህፍት እና የሚያስችል ስፋቱ ቢያንስ 25 ካሬ እና የፈተና ጥያቄዎች የተጫነበት
ኮፒውተር ክፍል ሜትር የሆነ ክፍል ቢያንስ አስር (10) ኮፒዉተር ከዩፒየስ
በስርዓተ ትምህርቱ መሰረት ሃይል ማግኘት እንዲችሉ ተደርጎ
የተዘጋጀ ቢያንስ 20 የማስተማሪያ
30
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
31
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
32
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ጋር ተመሳሳይነት ያለው)
10 የተግባር ስልጠና መስጫ በግል ወይም በጋራ የእጅ መፍታቻ በኪራይ ወይም በኮንትራት ወይም በራስ
ቦታ እና የመሰናክል ማለማመጃ በቂና ይዞታ የተያዘ ቦታ መሆን የሚችል ሆኖ
ምቹ ቦታ ያለዉ የኪራይ ወይም የኮንትራት ዉሉ ከአንድ
ዓመት ያለነሰ
11 የስልጠና አሰጣጥ እቅድ በስርዓተ ትምህርጥ መሰረት የተዘጋጀ የአንድ ዙር የስልጠና እቅድ /አጠቃላይ እና
(Lesson plan) ሳምንታዊ/ የማስተማሪያ መረሃ ግብር
12 ጥምርታ በአንድ ተሸከርካሪ ሊኖር የሚችል የሰልጣኝ ብዛት ከአስር (10) መብለጥ የለበትም
13 ህጋዊ ሰነዶች የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ህጋዊ መተዳደሪያ ደንብ
14 የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ ፣ በተሻለ ቴክኖሎጂ መልእክቶችን መስተላለፍ
የማስታወቂ ቦርድ
የሚችል/ቴሌግራም ፔጅ ያለው
15 የሃሳብ መስጫ የሃሳብ መስጫ ሳጥን እና የሃሳብ መስጫ መዝገብ ያለው
16 ምዝገባና ቀጠሮ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ኢንተርኔት አገልግሎት፣ እስካነር፣ ዲጂታል ካሜራ እና
ማከናወኛ እና የሰልጣኞች ንደፈ ሀሳብ ፈተና ሂደት መቆጣጠር የሚያስችል ሲስተም ያለው ማሰልጠኛ
ለሰልጣኞች መታወቂያ ተቋም
መስሪያ
ይህ ስታንዳርድ ከፀደቀ ቀን ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የአሽከርካሪ
17 ማሰልጠኛ ተቋም ወይም ቅርንጫፍ ማሰልጠኛ ተቋም ለመክፈት የፈቃድ ጥያቄ
ከተራ ቁጥር 1 እስከ 16 በሚያቀርቡ የአሽከርካሪ ማሰልጣኛ ተቋማት ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ነጥቦች አተገባበር ሁኔታ ቀደም ሲል ወደ ዘርፉ የገቡ የአሽከርካሪ ማሰልጣኛ ተቋማት ይህ መመሪያ ከፀደቀ
ቀን ጀምሮ ባለዉ አንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ የወጣዉን ስታንዳርድ ሙሉ በሙሉ
ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
28.2. የአሽከርካሪዎች የተግባር ስልጠና መስጫ ተሽከርካሪዎች ስታንዳርድ
እያንዳንዱ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም በሚሰጠዉ የስልጠና ዓይነት እና የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ ምድብ የተግባር ስልጠና መስጠት በሚያስችል መልኩ በቁ የሆኑ እና ደረጃቸዉን የጠበቁ
ተሽከርካሪዎች ከዚህ በታች በሰንጠራዥ በተገለፀዉ መሰረት ሊኖራቸዉ ያስፈልጋል
ተ. የተሽከርካሪ የአሽ/ብ/ማ/ የማስተማሪያ ተሽከርካሪ ደረጃ ብዛት
ቁ ዓይነት ፈቃድ
ምድቦች
ከ 125 ሲሲ በላይ ጉልበት ያለዉ ባለሁለት የሰልጣኝና የተሽከርካሪ ጥምርታን
1 ሞተር ሳይክል ሞ
እግር ሞተር ሳይክል ባገናዘበ መልኩ
ባለሶስት እግር ከ 200 ሲሲ በላይ ጉልበት ያለዉ ባለሶስት የሰልጣኝና የተሽከርካሪ ጥምርታን
2 ባለ-3 እግር
ሞተር ሳይክል እግር ሞተር ሳይክል ባገናዘበ መልኩ
33
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
34
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ግዴታ አለባቸው
ጊዜ ድረስ ብቻ ነዉ
ማስተማሪ አይቻልም
ይሆናል
35
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
1. አደረጃጃት
ሀ. የተቋሙ ዳይሬክተር
ለ. የምዝገባና ገንዘብ ተቀባይ ሠራተኛ
ሐ. የንድፈሀሳብና የተግባር አሰልጣኞች (የትራንስፖርት ቴክኒሽያን)
መ.ለሰልጣኝና ለባለጉዳይ እንዲሁም ለሠራተኞቹማረፊያ የሚሆን በቂ ወንበር እና ጠረጴዛዎች ማዘጋጀት
ያስፈልጋል
ሠ. በማሰልጠኛ ተቋሙ ለሰልጣኞች እና አሰልጣኞች መታወቂያ መስጠት የሚያስችል ዲጅታል ካሜራ
ከነኮምፒዩተሩ ማዘጋጀት
2. ማስተማሪያ ክፍል፤ ቤተ መፃህፍት እና ኮምፒውተር ክፍልአደረጃጀት
ሀ.በአንድ ጊዜ እስከ 25 ሰልጣኞችን መያዝ የሚችል ስፋቱ 5 ሜትር በ 6 ሜትር (30 ካ.ሜ)የሆነ የተሟላ
ነጠላ ዴስክ፣ ጠረጴዛዎች፣ ነጭ ወይም ጥቁር ሠሌዳ ያለው ማስተማሪያ ክፍሎች ፤
K. በቂ ብርሃንና ተስማሚ አየር የሚያስገቡ መስኮቶች ያሉትና ጣሪያቸው ቢያንስ 2.5 ሜትር ከፍ ብሎ
የተሰሩ ክፍሎች
ሐ.በስርዓተ ትምህርቱ መሰረት የተዘጋጀ በቂ የማስተማሪያ መጽሃፍ፣ የተለያየ የተሸከርካሪ ማንዋል፣
የማጣቀሻ መጽሃፎች፣ መጽሄት፣ ጋዜጣዎች… ወዘተ ያለውና ቢያንስ በአንድ ጊዜ 20 ሰው
የሚያስተናግድ ቤተ መጽሃፍት፤
መ.እያንዳንዱ ሰልጣኝ በኮምፒዉተርላይ ማሰልጠን በሚያስችል ደረጃ የተደራጀ የፅሁፍ ፈተና ጥያቄ
የተጫነበት ቢያንስ አስር (10) ኮሚፒዩተር ያለው የኮምፒዩተር ማለማመጃ ክፍል
ሠ.የማስተማርና የመማር ሂደቱን የማያደናቅፍ ጫጫታ የሌለው አካባቢ መሆን
ረ. የመጸዳጃ ከፍል ለወንድና ለሴት ለየብቻ
3. የወርክሾፕ አደረጃጃት
ስፋቱ ከ 35 ካ.ሜ ያላነሰ እና በበቂ ቁሳቁስ የተደራጀ ወርክ ሾፕ ሆኖ በዉስጡ
ሀ.ተገጣጥሞ የሚታይየተሽከርካሪሞተር
ለ. የተሟላ ሀይል አስተላላፊክፍል
ሐ. የተሟላ የመሪ ክፍል
መ. የተሟላ የፍሬን ክፍል
ሠ. በአየር የሚሰሩ የተሽከርካሪ ክፍሎች (ለከባድ ተሽከርካሪዎች)
ረ. ተገጣጥሞ የሚታይ እና የሚሰራየኤሌክትሪክ ክፍል
ሰ.የተሟላ የማቀዝቀዣ ክፍል
ሸ. የተሟላ የነዳጅ ማስተላፊያ ክፍል
ቀ. መጠናቸውና ዓይነታቸው የተለያየ የጥገና መሣሪያዎች
36
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
37
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
38
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
39
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
29. የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርት
በአዋጅ ቁትር 1074/2010 አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2 መሰረት ባለስልጣኑ ለአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች የሚከተለውን መስፈርት አውጥቷል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም የመንግስት
መ/ቤትየአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለመስጠት የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፡፡
40
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
41
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
42
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
2. ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት ዘርፍ ዝቅተኛው የትምህርት ደረጃ ዲፕሎማ፣ 12+2፣ 10+3፣ ደረጃ 3 እና
COC
43
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
2. ፈቃድ ሰጪ አካል በተቀመጠዉ ጊዜ ገደብ መፍትሄ ካልሰጠ ወደ ክልል ትራንስፖርት መ/ቤት በመቅረብ
እንዲታይለት ይደረጋል፡፡
3. በክልል ወይም ከተማ መስተዳዳር ትራንስፖርት መ/ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ ያልተስማማ ወይምዉሳኔዉ
ከህግና መመሪያ አንፃር አግባብ አይደለም የሚል ቅሬታ አቅራቢ ለፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን
ማቅረብ ይችላል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡
ክፍል አራት
33. የዲሲፕሊን ቅጣቶች
ሰንጠረዥ 3፡- በፈቃድ ሰጪ አካላት ላይ የሚወሰድ የዲሲፕሊን ዕርምጃ
ተ.ቁ የጥፋት ዓይነት የሚወስደው የዲሲኘሊን እርምጃ እርምጃ እርምጃ
የሚወስደው መወሰዱን
የሚከታተል
1 ማሰልጠኛ ተቋማትን ለመጀመሪያ ጊዜ የመጀመሪያ የክልል ፌደራል
በመመሪያው መሰረት ያልደገፈ፣ የፅሁፍ ማጠንቀቂያ ይሰጣል ወይም ትራንስፖር
ያልተከታተለ፣ ያልተቆጣጠረ ለሁለተኛ ጊዜ የመጨረሻ የፅሁፍ የከተማ ት
ፈቃድ ሰጪ አካል ማስጠንቀቂያ ይሰጣል መስተዳር ባለስልጣን
ለሦስተኛ ጊዜ ፈቃዱ ይሰረዛል ትራንስፖር
ት ቢሮ
2 የት/ደረጃ፣ጤና፣ ዕድሜ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጀመሪያ የክልል ፌደራል
ባልተሟሉበት ሁኔታ ሰልጣኞችን የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ለፈቃድ ወይም ትራንስፖር
ፈትኖ የተገኘ ወይም ሰጪ አካል ይሰጣል የከተማ ት
ሠልጣኞች የቀረቡትን ማስረጃ ለሁለተኛ ጊዜ የመጨረሻ የፅሁፍ መስተዳደር
ትክክለኛት ማሰልጠኛ ተቋማት ማጠንቀቂያ ይሰጣል ትራንስፖር ባለስልጣን
44
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
45
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ፈቃዱ ይሰረዛል ት ቢሮ
46
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
47
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ሰንጠረዥ 5፡-ጥፋት ፈፅመዉ በተገኙት የአሽከርካሪ ማሠልጠኛ ተቋማት ላይ የሚወሰድ የዲሲኘሊን እርምጃ
48
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
49
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ተገቢውን ስልጠና ያጠናቀቀን ሰልጣኝ ለሶስተኛ ጊዜ ተመሳ ሳይ ጥፋት ፈፅሞ ከተገኘ ፈቃድ
ለፈተና ሳያቀርብ ያጉላላ ወይም ይሰረዛል
የሰልጣኞችን የፈተና ቀጠሮ ቅደም
ተከተል በማዛባት አድሎ ያደረገ ወይም
ለፈተና ማስቀጠሪያ፣ ለፈታኞች ዉሎ
አበል ክፍያ ወዘተ… በማለት ተጨማሪ
ክፍያ ሰልጣኝ እንዲከፍሉ ያደረገ
9 ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጀመረው ስልጠና እንዲያቋርጥ
ሳያገኝ ፈቃድ ከተሰጠው ቦታ ውጭ ተደርጎ የተቋሙ ፈቃድ ይሰረዛል፡፡ ለፈጸመው ድርጊትና
ስልጠና የሰጠ ወይም በዜጎች ላይ ለሚደርሰው ላለስፈላጊ የጊዜ፣ የገንዘብ
ሳያሳውቅ እና ሰይፈቃድለት ቅርንጫፍ ወጪዎች ተጠያቂ ይሆናል
ከፍቶ ሲሰራ የተገኘ
10 የፈቃድ አገልግሎት ጊዜ ሲያበቃ እንዲያሳድስ የተሰጠዉን የጊዜ ገደብ ካበቃበት ቀን ጀምሮ
በተሰጠዉ ጊዜ ገደብ ውስጥ ፍቃዱን ባሉት 30 ቀናት ዉስጥ ካቀረበ ከማስጠንቀቅያ ጋር ብር
ያላሳደሰ 3000 ተቀጥቶ ይታደሳል
በቅጣት የሚያሳድስበት ጊዜ ገደብ ካበቃ ለተቋሙ ማሳወቅ
ሳያስፈልግ ፈቃዱ እንደተሰረዘ ይቆጠራል
11 ተገምግሞበት ፈቃድ የወሰደበትን ማሳወቅ ካለበት ጊዜ 1 ወር አሳልፎ ከቀረበ የፅሁፍ
አድራሻ ሲለዉጥ ለፈቃድ ሰጪ አካል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት አዲሱን አድራሻ በባለሙያ
ያላሳወቀ እንዲገመገም ይደረጋል
በሁለት ወር ውስጥ አዲሱን አደራሻ ያላሳወቀ ሥራን
እንዳቆመ ተቆጥሮ ፈቃዱ ይሰረዛል፡፡
12 አሰልጣኝ ወይም ተሽከርካሪ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ የፅሁፍ ማጠንቀቂያ ተሰጥቶት በአንድ
ሳይኖር ያለው በማስመሰል ወር ውስጥ እንዲያሟላ ይደረጋል
ዶክመንቶችን በማቅረብ ፈቃድ ወስዶ በማንኛውም ዓይነት ጥፋት የመጀመሪያ የፅሁፍ
የተገኘ ተቋም ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ከሆነ ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት ለ 3 ወር
ከስልጠና እንዲታገድ ይደረጋል
በማንኛውም ዓይነት ጥፋት ለ 3 ወር የታገደ ተቋም ከሆነ
ለ 3 ኛ ጊዜ ጥፋት ፈፅሞ ከተገኘ ፈቃዱ እንዲሰረዝ
ይደረጋል
13 ብቻውን ማሽከርከር የማይችል ለመጀመሪያ ጊዜ የፅሁፍ ማጠንቀቂያ ይሰጣል
ተፈታኝ ለፈተና ያቀረበ ወይም
50
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
51
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ወይም
ሰልጣኞች ስልጠና ሳይሰለጥኑ ወይም
ፈተና ሳይፈተኑ ከሌላ አካል ጋር
በመተባበር የአሽከርካሪ ብቃት
ማረጋገጫ ፈቃድ ያሰጠ ወይም
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ
እናሰጣለን በማለት ገንዘብ የተቀበለ
52
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
35. ክልከላ
• ቀደም ሲል ወደ ዘርፉ የገቡ የአሽከርካሪ ማሰልጣኛ ተቋማት ይህ መመሪያ ከፀደቀ ቀን ጀምሮ
ባለዉ አንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ የወጣዉን ስታንዳርድ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
• ነገር ግን በሰንጠረዥ 8 ሥር የተጠቀሱ የአሽከርካሪዎች ተግባር ስልጠና መስጫ ተሽከርካሪዎች
ስታንዳርድ ይህ መመሪያ ከፀደቀ ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
• ይህን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አሰራር በምንም ሁኔታ
ተፈፃሚነት አይኖረውም
36. መመሪያውን ስለማስፈፀምና የመተባበር ግዴታ
1. የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ የክልል ትራንስፖርት ቢሮዎች እንዲሁም የፈቃድ ሰጪ
አካላት ይህንን መመሪያ ተቀናጅተው ያስፈፅማሉ፡፡
2. ማንኛውም የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ይህን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የመተባበር
ግዴታ አለበት
37. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ህጐች
1. ይህን መመሪያ የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሰራር በዚህ መመሪያ
በተመለከቱት ጉዳዩች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም
2. ይህ መመሪያ ከፀደቀ ቀን ጀምሮ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አሰራር መመሪያ ቁጥር 1/2007
የተቀመጠዉ ማንኛዉም አሰራር ተፈፃሚነት አይኖረዉም፡፡
53
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
አብዲሳ ያደታ
አባሪ ሰነድ
54
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
የዕምነት ቃል ስለመስጠት
ቅፅ 2 የውጭ ሀገር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ላላቸው ግለሰቦች የሚሰጥ የ 45 ቀን ጊዜያዊ
የማሽከርከር ፈቃድ
57
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
58
የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሰራር መመሪያ ቁጥር ----/2013
59