You are on page 1of 71

አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰው ሀይል አስተዳደር ዲይሬክቶሬት

በ2008 ዓ.ም ለአሰልጣኞች እና ኢንስትራክተሮች


የተዘጋጀ የተፈላጊ ችሎታ መመሪያ እና በ2005
ዓ.ም የወጣ የአሰልጣኞች እና
የኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት የአፈጻጸም
መመሪያ ላይ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠና
በ2008 ዓ.ም ለዓሰልጣኞች እና
ኢንስትራክተሮች የተዘጋጀ
የተፈላጊ ችሎታ መመሪያ
•የሲ ደረጃ አሰልጣኞች
በነባሩ የብቃት ማዕቀፍ እንደተገለፀው የሲ ደረጃ አሰልጣኞች በቴ/ሙ/ት/ስ/ሙያዎች በደረጃ 3
ወይም 4 ወይም 5 ሥልጠና ያጠናቀቁ ብቃታቸውን በሙያው ብቃት ምዘና ያረጋገጡና
የማሰልጠና ስነ-ዘዴ የወሰዱ እንዲሆኑ ያሳያል፡፡ ይህ ሲደረግ በወቅቱ አብዛኛው ሙያዎች
የሙያ ደረጃቸው እስከ ደረጃ ሶስትና አራት ብቻ የወጣላቸው በመሆኑ፣ የደረጃ አምስት
አጠናቃቂዎች ቁጥር እጅግ አንስተኛ መሆናቸውና በቂ አሰልጣኝ ከገበያ ላይ ማግኘት
ስለማይቻል፣ በወቅቱ የሥራ ገበያውና የቴክኖሎጂ ፍላጎት በዝቅተኛ ደረጃ የበቁ የሲ ደረጃ
አስልጣኞች መመለስ እንደሚችሉ በመታመኑ እና በቀጣይ ከሚኖረው ሃገራዊ የሠው ሀይል
ፍላጎት አንጻር ማሻሻያ እንደሚደረግበት ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡
በሂደትም የሥልጠና ካሪኩለም መሠረት በሆነው የሙያ ደረጃዎች ላይ በኢንዱስትሪው
ተከታታ ማሻሻያይ በመደረጉ የደረጃ 3 ሠልጠና አጠናቀው በሲ ደረጃ አሰልጣኝነት የተመደቡ
አሰልጣኞች ለስራ ገበያው የበቃ የሰው ሀይል ከማቅረብ እና ምርጥ ቴክኖሎጂ ከማቅረብ
አንጻር አፈጻጸማቸው በቂ አለመሆኑ በተግባር ታይቷል፡፡
………..የቀጠለ

ስለሆነም ለሙያዎቹ የሚጠበቀው እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ከስራ


ገበያው ፍላጎት እድገት አንጻር ከቴክኖሎጂ ፍላጎት በፍጥነት ከማደግ እና
በዘርፍ ለአሰልጣኙ ከሚሰጠው ተደራራቢና ውስብስብ ተልዕኮ አንጻር
ማለትም የተቋም ውስጥ ስልጠናና ከኢንዱስትሪው ጋር በትብብር ስልጠና
መስጠት፣ የጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው የድጋፍ
ፓኬጅ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት ብቁ የሚሆኑ
ለሲ ደረጃ አሰልጣኝነት የትምህርት ዝግጅት ደረጃ አራት እና አምስት
ያጠናቀቁትን በማድረግ ተሻሽሏል፡፡
የሲ ደረጃ አሰልጣኞች ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት፣ ተፈላጊ የስራ
ልምድና የሚጠበቅበት ውጤት በሚከተለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡
ሠንጠረዥ 1
የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ የሲ ደረጃ አሰልጣኞች ተፈላጊ ችሎታ
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች

1 ጀማሪ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ የሙያ - 0 ዓመት የስራ ልምድ


አሰልጣኝ
ብቃት ማዕቀፍ በሚሰጡ - በሚያሰለጠኑበት ደረጃ በሙያ ብቃታቸው
ሙያዎች በደረጃ አራት በሙያው ብቃት የተረጋገጠ፣
ስልጠና ያጠናቀቁ
- የማስልጠን ስነ-ዘዴ ስልጠና ወስዶ አግባብ
ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር
ወረቀት ያለው፤

- ለሲ ደረጃ አሰልጣኞች የሚሰጠውን የቅድመ


ስራ ስልጠና ወስዶ ያጠናቀቁ፡፡
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ መስፈርቶች
መጠሪያ
2 ረዳት የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ ስልጠና - ለደረጃ አራት በሰለጠኑበት ደረጃ ብቃታቸው በሙያ
አሠልጣኝ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/
የሙያ ብቃት ማዕቀፍ
አሰልጣኝነት የ2 ዓመት የስራ ልምድ እና ተዘጋጅቶ
በሚሰጡ ሙያዎች በደረጃ በቀረበ ዲዛይን አንድ ምርጥ ቴክኖሎጂ 100%
አራት ወይም በደረጃ በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልል ደረጃ እውቅና
አምስት ያጠናቀቀ
የተሰጠው ወይም በሰለጠኑበት ደረጃ ብቃታቸው
በሙያ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ በኢንዱስትሪ
ውስጥ በማምረት ሂደት በሙያው አግባብነት ያለው
የ4 ዓመት የስራ ልምድ ያለው፣
- ለደረጃ አምስት 0 አመት የስራ ልምድ እና
በሰለጠኑበት ደረጃ ብቃታቸው በሙያው ብቃት
ምዘና የተረጋገጠ፣
- ለሁሉም አልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሰልጠና
ወስዶ አግባብ ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ መዋቅ የምስክር
ወረቀት ያለው፣

- ለሲ ደረጃ አሰልጣኞች የሚሰጠውን የቅድመ ስራ


ስልጠና ወስዶ ያጠናቀቀ፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
3 አሰልጣኝ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ - ለደረጃ አራት በሰለጠኑበት ደረጃ
የሙያ ብቃት ማዕቀፍ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና
በሚሰጡ ሙያዎች የተረጋገጠ ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/
በደረጃ አራት ወይም አሰልጣኝነት የ4 ዓመት የስራ ልምድ እና
አምስት ያጠናቀቀ ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን ሁለት ምርጥ
ቴክኖሎጂ 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልል ደረጃ
እውቅና የተሰጠው ወይም በሰለጠኑበት
ደረጃ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና
የተረጋገጠ ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ
በማምረት ሂደት በሙያው አግባብነት
ያለው የ6 ዓመት የስራ ልምድ ያለው፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ መስፈርቶች
መጠሪያ ዝግጅት
- ለደረጃ አምስት በሰለጠኑበት ደረጃ ብቃታቸው
በሙያው ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ
አሰልጣኝነት የ2 ዓመት የስራ ልምድና ተዘጋጅቶ በቀረበ
ዲዛይን ሁለት ምርጥ ቴክኖሎጂ 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና
ለዚህም በክልል ደረጃ እውቅና ያለው ወይም በሰለጠኑበት
ደረጃ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ
በኢንዲስትሪ ውስጥ በማምረት ሂደት በሙያው አግባብነት
ያለው የ4 ዓመት የስራ ልምድ ያለው፣
 
- ለሁሉም አልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሰልጠና ወስዶ
አግባብ
ካለው የቴ /ሙ/ት/ስ መዋቅ የምስክር ወረቀት ያለው፣

-ለሲ ደረጃ አሰልጣኞች የሚሰጠውን የቅድመ ስራ ስልጠና


ወስዶ
ያጠናቀቀ፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች

4 ከፍተኛ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ የሙያ - ለደረጃ አራት በሰለጠኑበት ደረጃ


አሰልጣኝ ብቃት ማዕቀፍ በሚሰጡ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ
ሙያዎች በደረጃ አራት ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/ አሰልጣኝነት የ7 ዓመት
ወይም አምስት የስራ ልምድ እና ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን
ያጠናቀቀ ሶስት ምርጥ ቴክኖሎጂ 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልል ደረጃ
እውቅና የተሰጠው ወይም በሰለጠኑበት
ደረጃ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና
የተረጋገጠ ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ
በማምረት ሂደት በሙያው አግባብነት
ያለው የ9 ዓመት የስራ ልምድ ያለው፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ መስፈርቶች
መጠሪያ ዝግጅት

- ለደረጃ አምስት በሰለጠኑበት ደረጃ ብቃታቸው በሙያው


ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ
አሰልጣኝነት የ5 ዓመት የስራ ልምድና ተዘጋጅቶ በቀረበ
ዲዛይን ሁለት ምርጥ ቴክኖሎጂ 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ በማድረግ የቻለና
ለዚህም በክልል ደረጃ እውቅና ያለው ወይም በሰለጠኑበት
ደረጃ ብቃታቸው በሙያ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ሆኖ
በኢንዲስትሪ ውስጥ በማምረት ሂደት በሙያው አግባብነት
ያለው የ7 ዓመት የስራ ልምድ ያለው፣
- ለሁሉም አልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሰልጠና ወስዶ
አግባብ ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ መዋቅ የምስክር ወረቀት
ያለው
- ለሲ ደረጃ አሰልጣኞች የሚሰጠውን የቅድመ ስራ ስልጠና
ወስዶ ያጠናቀቀ
•የቢ ደረጃ ኢንስትራክተር

በነባሩ የብቃት ማዕቀፍ እንደተገለፀው የቢ ደረጃ ኢንትራክተሮች በቴ/ሙ/ት/ስልጠና


በሚሰጥባቸው ሙያዎ የመጀመሪያ ዲግሪ ስልጠና ያጠናቀቁ፤ ብቃታቸውን በሙያው
ብቃት ዘና ያረጋገጡና የማሰልጠን ስነ-ዘዴ የወደሱ እንዲሆኑ ያሳያል፡፡ እንደሚታወቀው
በግንባታ እና ማኑፋክቸሪንግ ሙያዎች በአብዛኛው ወደ ዘርፉ የሚቀላቀሉት የምህንድስና
ባለሙያዎች ቢሆኑም በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ አሰልጣኝነት እንዲሰሩ የተቀጠሩት ያላቸውን
የትምህርት ዝግጅት ታሳቢ ያደረገ ባለመሆኑ አሰልጣኞችን ለመሳብና ያሉትንም ለማቆየት
ፈታኝ ሆኗል፡፡
በዚህም መሰረት በማንኛውም መዋቅር እንደተደረገው ምህንድስና ሙያዎች የመጀመሪያ
ዲግሪ ያላቸውና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አሠልጣኝነት ማገልገል
ለሚፈልጉ የቢ ደረጃ ኢንስትራክተርነት እንዲቀጠሩ/እንዲያርፉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ይህም በዋናነት በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ የተያዘውን በአጭር ጊዜ ቴክኖሎጂ የመቅዳት በረጅም
ጊዜ የማሻሻልና የመፍጠር የአቅም ግንባታ መርሃ-ግብር ተጨባጭ ለማድረግ እንሚቻል
ይታመናል፡፡
የቢ ደረጃ ኢንስትራክተሮች ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት፣ የስራ ልምድና የሚጠበቅበት
ውጤት በሚከተለው ሠንጠረዥ ቀርቧል፡፡
ሠንጠረዥ 2
የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ የቢ ደረጃ ኢንስትራክተሮች ተፈላጊ ችሎታ

ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
1 ጀማሪ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ - 0 ዓመት የስራ ልምድ
ኢንስትራክር
በሚሰጥባቸው ሙያዎች - በሚያሰለጠኑበት ደረጃ በሙያው ብቃት
ከምህንድስና ሙያዎች ምዘና ብቁ የሆኑ
ውጭ የመጀመሪያ ዲግሪ
ያላቸው - የማስልጠን ስነ-ዘዴ ስልጠና ወስዶ አግባብ
ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር
ወረቀት ያለው፤
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
2 ረዳት የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ - በምህንድስና ሙያዎች 0 ዓመት የስራ
ኢንስትራክተ ልምድ፣
ር በሚሰጥባቸው - በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያው ብቃት
ሙያዎች ምዘና ብቁ የሆኑ፤
ከምህንድስና - በምህንድስና ባልሆኑ ሙያዎች የመጀመሪያ
ዲግሪ ላላቸው በሚያሰለጥኑበት ደረጃ
ሙያዎች ማለትም
በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆነው
በምህንድና እና በቴ/ሙ/ት/ስ ዘርፍ በአሰልጣኝነት የ2
በምህንድስና ባልሆኑ ዓመት የሥራ ልምድ እና ቢያንስ ሁለት
ምርጥ ቴክሎጂዎችን ሙሉ ዲዛይን
ሙያዎች
በማዘጋጀትና 100% በመቅዳት
የመጀመሪያ ዲግሪ የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ያላቸው ማድረግ የቻሉና ለዚህም በክልል ደረጃ
እውቅና የተሰጣቸው ወይም
በሚያሰለጥኑበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና
ብቁ ሆነው በኢንዱስትሪ ውስጥ በማምረት
ሂደት የተገኘ በሙያው አግባብነት ያለው 4
ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
- ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ
ስልጠና ወስዶ አግባብ ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት
ያለው፣
3 ኢንስትራክተ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ - በምህንድስና ሙያዎች በሚያሰለጥንበት
ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
ር ስልጠና በሚሰጥባቸው
በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በአሠልጣኘት የተገኘ 2
ሙያዎች ማለትም ዓመት የስራ ልምድና አዋጭነቱ የተረጋገጠ
በምህንድስና እና ሁለት ምርጥ ቴክሎጂ ዲዛን በማዘጋጀት
በምህንድስና ባልሆኑ 100% በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን
ሙያዎች የመጀመሪያ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልል
ዲግሪ ያላቸው ደረጃ እውቅና ያለው፣ ወይም
በሚያሰለጥኑበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና
ብቁ ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ በማምረት
ሂደት የተገኘ በሙያው አግባብነት ያለው 4
ዓመት የስራ ልምድ፣
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች
መጠሪያ ዝግጅት ተፈላጊ መስፈርቶች
ምህንድስና ባልሆኑ ሙያዎች የመጀመሪያ ድግሪ
ላላቸው በሚያሰለጥኑበት ደረጃ በሙያ ብቃት
ምዘና ብቁ ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ
በአሰልጣኝነት የተገኘ 4 ዓመት የስራ ልምድ
ሶስት ምርጥ ቴክኖሎጂዎችን ዲዛይን
በማዘጋጀት እና 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ
የቻለናለዚህም በክልል ደረጃ እውቅና
የተሰጠው፣ ወይም ቢያሰለጥንበት ደረጃ
በሙያው ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ በኢንዱስትሪ
ውስጥ በማምረት ሂደት የተገኘ በሙያው
አግባብነት ያለው 6 ዓመት የስራ ልምድ
-ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ
ስልጠና ወስዶ አግባብ ካለው
የቴ/ሙ/ት/መዋቅር የምስክር ወረቀት ያለው
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ ዝግጅት መስፈርቶች
4 ከፍተኛ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ - በምህንድስና ሙያዎች በሚያሰለጥንበት
ኢንስትራክተ ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
ስልጠና
ር በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በአሠልጣኘት የተገኘ 5
በሚሰጥባቸው ዓመት የስራ ልምድና አዋጭነቱ የተረጋገተ
ሙያዎች ማለትም ሶስት ምርጥ ቴክሎጂ ዲዛን በማዘጋጀት
100% በመቅዳት እንዲሁም የ1 ቴክኖሎጂ
በምህንድስና እና
ሙሉ ዲዛን በማሻሻል እና በመስራት
በምህንድስና የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ባልሆኑ ሙያዎች ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልልና በሃገር
አቀፍ ደረጃ እውቅና የጠሰጠው ወይም
የመጀመሪያ ዲግሪ
በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና
ያላቸው ብቁ ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ በምርምር
የጥራት ማስጠበቅና ቁጥጥር ስራዎች
የተገኘ በሙያው አግባብነት ያለው 8 ዓመት
የስራ ልምድ
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ ዝግጅት መስፈርቶች
ምህንድስና ባልሆኑ ሙያዎች የመጀመሪያ
ዲግሪ ላላቸው በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በአሰልጣኝነት የ7 ዓመት
የስራ ልምድ 3 ምርጥ ቴክኖሎጂ ዲዛይን
በማዘጋጀትና 100% በመቅዳት እንዲሁም የ1
ቴክኖሎጂ ሙሉ ዲዛይን በማሻሻል እና
በመስራት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልልና በሃገር አቀፍ
ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
በኢንዱስትሪ ውስጥ በምርምር፣የጥራት
ማስጠበቅና ቁጥጥር ስራዎች የተገኘ በሙያው
አግባብነት ያለው የ9 ዓመት የስራ ልምድ
ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ
ስልጠና ወስደው አግባብ ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት
ያላቸው
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
ምህንድስና ባልሆኑ ሙያዎች የመጀመሪያ
ዲግሪ ላላቸው በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በአሰልጣኝነት የ7 ዓመት
የስራ ልምድ 3 ምርጥ ቴክኖሎጂ ዲዛይን
በማዘጋጀትና 100% በመቅዳት እንዲሁም የ1
ቴክኖሎጂ ሙሉ ዲዛይን በማሻሻል እና
በመስራት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ለዚህም በክልልና በሃገር አቀፍ
ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
በኢንዱስትሪ ውስጥ በምርምር፣የጥራት
ማስጠበቅና ቁጥጥር ስራዎች የተገኘ በሙያው
አግባብነት ያለው የ9 ዓመት የስራ ልምድ
ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ
ስልጠና ወስደው አግባብ ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት
ያላቸው
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች ተፈላጊ
መጠሪያ መስፈርቶች
5 መሪ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ ስልጠና - በምህንድስና ሙያዎች
ኢንስትራክተ በሚሰጥባቸው ሙያዎች በሚያሰለጥንበት ስልጠና በሚሰጣቸው
ር ማለትም በምህንድስና ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
እና በምህንድስና ባልሆኑ ሙያዎች ማለትም በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ
ሙያዎች የመጀመሪያ በአሰልጣኝነት የተገኘ በምህንድስና እና
ዲግሪ ያላቸው የ9 ዓት የሥራ ልምድ እና ሶስት
በምህንድስና ባልሆኑ ምርጥ ቴክኖሎጂ
ዲዛይን በማሻሻል 100% ሙያዎች
የመጀመሪያ በመቅዳት እንዲሁም የ2
ቴክኖሎጂ ዲግሪ ያላቸው ዲዛይን
በማሻሻል ቴክኖሎጂውን የሰራ
•የኤ ደረጃ ኢንስትራክተሮች

በነባሩ የብቃት ማዕቀፍ እንደተገለፀው የኤ ደረጃ ኢንስትራተሮች


በቴ/ሙ/ት/ሥልጠና በሚሰጥባቸው ሙያዎች የሁለተኛ ዲግሪ ሥልጠና ያጠናቀቁ
ብቃታቸውን በሙያ ብቃት ምዘና የረጋገጡና የማሰለጠን ስነ-ዘዴ የወሰዱ እንደሆኑ
ያሳያል፡፡ የዚህ ደረጃ የትምህርት ዝግጅት የተለወጠ ነገር ባይኖረውም ሌሎች
ተፈላጊ ችሎታዎችን ወቅቱ በሚጠይቀው እውቀት፣ክህሎት፣አመለካከት እና
ሃገራዊ ተልዕኮ አንፃር ተቃኝቶ ቀርቧል፡፡ ይህ ሲባል በዋናነት የኤ ደረጃ አሰልጣኞች
ከሚሰጡት ሥልጠና በበለጠ በትኩረት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሃገራዊ ጠቀሜታ
ባላቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ በማሰብ የተዘጋጀ ነው፡፡

የኤ ደረጃ ኢንስትራክተሮች ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና


የሚጠበቅ ውጤት በሚከለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡
ደረጃ የስራ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች
መደብ ተፈላጊ መስፈርቶች
መጠሪያ
1 የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ -0 ዓመት የሥራ ልምድ
ኢንስትራክተ
ር ሥልጠና በሚሰጥባቸው -በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያው ብቃት ምዘና ብቁ
ዘርፎች የሁለተኛ ዲግሪ የሆነ
ያላቸው -የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሥልጠና ወስደው አግባብ ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/ መዋቅር የምስክር ወረቀት ያላቸው
2 ከፍተኛ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ -በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያ ብቃትምዘና ብቁ ሆኖ
ኢንስትራክተ
ር ሥልጠና በሚሰጥባቸው በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በኢንስትራክተርነት የተገኘ የ3
ዘርፎች የሁለተኛ ዲግሪ ዓመት የሥራ ልምድ እና የሁለት ምርጥ ቴክኖሎጂውን
ያላቸው በመሥራት ለተጠቃሚዎች ያቀረበ እና ለዚህም
በሃቀር አቀፍ እውቅና ያላቸው ወይም
በሚያሰልጥንበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ ሆኖ
በኢንዱስት ውስጥ በምርምር ፣የጥራት ማስጠበቅና
ቁጥጥር ሥራዎች የተገኘ በሙያው አግባብነት ያለው
6 ዓመት የሥራ ልምድ
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች
መጠሪያ ተፈላጊ መስፈርቶች
-ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሥልጠና
ወስደው አግባብ ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር
3 መሪ የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ -በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና ብቁ
ኢንስትራክተር
ሥልጠና የሚሰጥባቸው ሆኖ በቴ/ሙ/ት/ዘርፍ በኢንስትራክተርነት የ7 ዓት
ዘርፎች የሁለተኛ ዲግሪ የሥራ ልምድ እና የአራት ምርጥ ቴክሎጂዎችን
ያላቸው በመሥራት ለተጠቃሚዎች ያቀረበ እና ለዚህም
በሃቀር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው ወይም
በሚያሰለጥንበት ደረጃ በሙያው ብቃት ምዘና ብቁ
ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ በምርምር፣የጥራት
ማስጠበቅና ቁጥጥር ሥራዎች የተገኘ በሙያው
አግባብነት ያለው 10 ዓመት የሥራ ልምድ
-ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዴ ሥልጠና
ወስደው አግባብ ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር
የምስክር ወረቀት ያላቸው
ደረጃ የስራ መደብ የትምህርት ዝግጅት የስራ ልምድ (በዓመት እና ሌሎች
መጠሪያ ተፈላጊ መስፈርቶች
4 ዋና የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ በኢንስትራክተርነት ወይም
ኢንስትራክትር
ስልጠና በሚሰጥባቸው በኢንዱስትሪ ውስጥ ተመራማሪነት የ11 ዓመት የሥራ
ዘርፎች የሁለተኛ ልምድ እና ቢያንስ የአራት ቴክኖሎጂዎችን ዲዛይን
ዲግሪ ያላቸው በማሻሻልና በማምረት እንዲሁም ሁለት አዳዲስ
ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ለተጠቃሚዎች ያቀረቡ
እና ለዚህም በሃቀር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸው
ወይም በሚያስለጥነበት ደረጃ በሙያ ብቃት ምዘና
ብቁ ሆኖ በኢንዱስትሪ ውስጥ በምርምር፣የጥራት
ማስጠበቅና ቁጥጥር ሥራዎች የተገኘ በሙያው
አግባብነት ያለው የ15 ዓመት የሥራ ልምድ
-ለሁሉም አሰልጣኞች የማሰልጠን ስነ-ዘዱ ሥልጠና
ወስደው አግባብ ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር
ወረቀት ያላቸው
በ2005 ዓ.ም የወጣ
የአሰልጣኞች እና
የኢንስትራክተሮች የደረጃ
እድገት የአፈጻጸም መመሪያ
1. መግቢያ
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ አጠቃላይ ዓላማ በሀገሪቷ ብቁ፤
ተነሳሽነትና የፈጠራ ክህሎት ያለው የሰው ሃይል በመፍጠር ድህነትን
ማስወገድና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ ነው፡፡ይህም
የሚተገበረው በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተና ከፍተኛ
ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት እንዲሁም
የቴ/ሙ/ት/ሥ ተቋማት አዳዲስ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት፣
በማሻሻልና በመፍጠር ወደ ኢንዳስትሪው በማስተላለፍ ኢንዳስትሪውን
በተለይም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ምርትና አገልግሎት በዓለም
አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቱን ማሳደግ እንዲችሉ በማድረግ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ቁልፍ ተግባራት ለመፈፀም ወሳኙን ድርሻ የሚጫወቱት
አሰልጣኞች መሆናቸው እሙን ነው፡፡ በመሆኑም አሰልጣኞችና
ኢንስትራክተሮች ጥራትና ብቃት ያለውን ስልጠና በመስጠት ሙያዊና ሀገራዊ
ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተገቢውን የማትጊያና የጥቅማ ጥቅም እንዲሁም
ተከታታይነት ያለው የደረጃ እድገት ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ በ2005 ዓ.ም
በሀገር አቀፍ የቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት አሰልጣኞችና ኢንስትሪክተሮች የደረጃ
ዕድገት እንዲሁም የተቋም አመራሮች ምልመላና ምደባ አፈጻጸም
ማስተግበሪያ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር የተገባ መሆኑ ይታወቃል
 ክፍል አንድ
 1.1 የደረጃ ዕድገት አስፈላጊነት

 ይህ “ አገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና


ተቋማት አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት
እንዲሁም ምክትል ዲኖች ምልመላና ምደባ አፈጻጸም
መመሪያ “ዉጤት ተኮር ስልጠና ስርአቱን በሚገባ ወደተግባር
በመለወጥ የስትራቴጂዉ ቁልፍ ግቦች መሳካት እንዲችሉ
በአሰልጣኞች እና ኢንስትራክተሮች ልማት ረገድ ያለዉ ስራ
ወሳኝ በመሆኑ ይህ መመሪያ የተቋማት የአሰልጣኞች
ማትጊያ ስርአትን ለመተግበር እንዲያስችል ተደርጎ በአገር
አቀፍ ደረጃ /ወጥ በሆነ መልኩ/ተግባራዊ እንዲሆን
ተዘጋጅተዋል
ትርጉም
 ዲን

ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠ የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለመተግበር


ቁርጠኝነት ያለው በቴ/ሙ/ት/ስተቋማት ካሉት የኤ-ደረጃ ወይም የቢ-ደረጃ አሠልጣኞች
መካከል በክልሉ/ከተማአስተዳደሩ የቴ/ሙ/ት/ስ/ ኤጀንሲ/ቢሮ ተወዳድሮ የሚመደብ
የቴ/ሙ/ት/ሥ ተቋምን በበላይነት የሚመራ ኃላፊ ማለት ነው፡፡
ምክትል ዲን
ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠና የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ለመተግበር
ቁርጠኝነት ያለው ከ ቢ-ደረጃ ወይም ከ ኤ-ደረጃ አሠልጣኞች መካከል አብዛኛው
ሥልጠና ከሚሰጥባቸው የሙያ ዘርፎች ተወዳድሮ የሚመደብ የቴ/ሙ/ት/ሥ ተቋም
የውጤት ተኮር ሥልጠና የሥራ ሂደትና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን
የሥራ ሂደትን በባለቤትነት የሚመሩና በምክትል ዲንነት ደረጃ የሚመደቡ ማለት ነው፡፡
ግንባር ቀደም አሰልጣኝ/ኢንስትራክተር
ማለት የቴ/ሙ/ት/ስ ስትራቴጂ እና ውጤት ተኮር ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ሥርዓትን
በሚገባ ተገንዝቦ እራሱ አርዓያ ሆኖ ሌሎች እንዲከተሉት በማድረግ
ለተግባራዊነቱ በቁርጠኝነት የሚሰራ እና ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የቻለ
አሠልጣኝ/ ኢንስትራክተር ማለት ነው፡፡
 የደረጃ እድገት
ማለት ለአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደመወዝ ለውጥ ሊያስገኝ የሚችል ከአንድ የስራ ደረጃ
ወደ ሌላ ደረጃ የሚደረግ ለውጥ/ሽግግር ማለት ነው፡፡
 “ክልል”
ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት አንቀጽ 47/1/
መሰረት በክልልነት የታወቁት ሲሆኑ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ አስተዳደርንም ይጨምራል፡፡
 የቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲ/ቢሮ

ማለት በክልሉ ወይም በከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ የቴ/ሙ/ት/ሥ
በበላይነት የሚያስተባብርና የሚመራ አካል ነው፡፡
 ተቋም

ማለት ከፌ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲ፣ ከክልል/ከተማ አስተዳደር ቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ/ኤጀንሲ


እውቅና አግኝቶ በተለየዩ የቴ/ሙ/ት/ሥ የሙያ መስኮችና የስልጠና ደረጃዎች ሰልጣኞችን
ተቀብሎ ስልጠና የሚሰጥና የሚያበቃ የማሰልጠኛ ተቋም ሲሆን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችን፣
ኮሌጆችን እና ተቋማትን ያጠቃልላል፡፡
 የዘርፍ
አስተባባሪዎች
ማለት በቴ/ሙ/ት/ሥ ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ ተመሳሳይነት ያላቸውን የስልጠና
መስኮች በውጤት ተኮር ስልጠና በመምራት በጋራ አቅደው እንዲሰሩ
የሚያስተባብሩ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ማለት ነው፡፡
 አሰልጣኝ

ማለት በቴ/ሙ/ት/ሥ ዘርፍ በሚሰጡ ሙያዎች በደረጃ IV/V


ስልጠናውን ያጠናቀቀና ባጠናቀቀበት ሙያ ከደረጃ I እስከ ደረጃ
IV/V በየደረጃው በምዘና የሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ እና የማሰልጠንና
የማብቃት ስራ ላይ የተሰማራ ባለሙያ ነው፡፡

 ኢንስትራክተር

ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በሚሰጥባቸው


ሙያዎች ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ
ዲግሪ/በሁለተኛ ዲግሪ ስልጠናውን ያጠናቀቀ፤ ስልጠናውን
ባጠናቀቀበት ሙያና በሚያሰለጥኑበት ደረጃ ከደረጃ I እስከ ደረጃ
IV/V በየደረጃው በምዝና ብቃቱ የተረጋገጠ እና የማሰልጠንና
የማብቃት ስራ ላይ የተሰማራ ባለሙያ ሲሆን የተቋማት
ሃላፊዎችንም ይጨምራል፡፡
ባለድርሻ አካላት
ማለት በቴ/ሙ/ት/ሥ ስርአት ውስጥ
ጉልህ ሚና ያላቸው እንደ መንግስታዊ
አካላት፤ የልማት ድርጅቶች፤
ዩኒቨርስቲዎች፣ የዘርፍ
ኢንስቲትዩቶችና የምርምር ተቋማትን
እንዲሁም የአሰሪና የሰራተኛ ማህበራት
ተወካዮችና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡
3. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አሰልጣኞችና
ኢንስትራክተሮች ፕሮፋይል
 C-ደረጃ አሠልጣኝ
በደረጃ IV ወይም በደረጃ V ስልጠናውን
ያጠናቀቀና ባጠናቀቀበት ሙያ ከደረጃ I እስከ ደረጃ
IV/V በየደረጃው ተመዝኖ የሙያ ብቃቱ
የተረጋገጠ እና የሙያ ምዘና ብቃት ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት በየደረጃው ያለው፤
የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ወስዶ አግባብነት ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት
የተሰጠው፤
. B-ደረጃ ኢንስትራክተር
 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በሚሰጥባቸው ሙያዎች ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/
ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዲግሪ ስልጠናውን ያጠናቀቀ፤
 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናውን ባጠናቀቀበት ሙያ እና በሚያሰለጥንበት ደረጃ
ከደረጃ I እስከ ደረጃ IV በየደረጃው ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ እና በየደረጃው የሙያ
ምዘና ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው፤
 የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ወስዶ አግባብነት ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር
ወረቀት ያለው፤

A-ደረጃ ኢንስትራክተር
 በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠናው በሚሰጥባቸው ሙያዎች ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ/
ኢንስቲትዩት በ2ኛ ዲግሪ ስልጠናውን ያጠናቀቀ፤
 በሰለጠነበት ሙያ እና በሚያሰለጥንበት ደረጃ ከደረጃ I እስከ ደረጃ V በየደረጃው
ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ እና በየደረጃው የሙያ ምዘና ብቃት ማረጋገጫ የምስክር
ወረቀት ያለው፤
 የማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ወስዶ አግባብነት ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር
ወረቀት ያለው፤
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አመራሮች ፕሮፋይል
 በአዋጅ ቁጥር 954/2008 ዓ.ም አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ 20 እና 21
በግልፅ እንደተቀመጠው የተቋም አሰልጣኞችና አመራሮች
ፕሮፋይል፡-
የዲኖች/ ዳይሬክተሮች/ የተቋም መሪ/ ፕሮፋይል
 በቴ/ሙ/ት/ሥ/ተቋም ከሚሰጡ የትኩረት ዘርፎች በአንዱ ሙያ በቢ-ደረጃ
ኢንስትራክተር ወይም በኤ-ደረጃ በኢንስትራክተርነት ያለውን የአሰልጣኝነት
ፕሮፋይል የሚያሟሉ፤
 በአሰልጣኝነት ቆይታ ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያላቸው፤
 የውጤት ተኮር ስልጠና ስርዓትን ለመተግበር የሚያስችል በፌደራል ወይም
በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና የአመራርነት ስልጠና
የወሰዱና አግባብነት ካለው የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት የተሰጠው
ወይም ስልጠናውን ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ፤
 የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ በየደረጃው የወሰዱና የብቃት ምዘና ማረጋገጫ
የምስክር ወረቀት ያለው
የምክትል ዲኖች/ዳይሬክተሮች/ተቋም መሪዎች ፕሮፋይል
 በቴ/ሙ/ት/ሥ/ተቋም ከሚሰጡ የትኩረት ዘርፎች በአንዱ

ሙያ በቢ-ደረጃ ኢንስትራክተርና በኤ-ደረጃ ኢንስትራክተርነት


ያለውን የአሰልጣኝነት ፕሮፋይል የሚያሟሉ፤
 በአሰልጣኝነት ቆይታቻው ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ያላቸው፤

 የውጤት ተኮር ስልጠና ስርአትን ለመተግበር የሚያስችል


በፌደራል ወይም በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን የቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና የአመራርነት ስልጠና የወሰዱና አግባብነት ካለው
የቴ/ሙ/ት/ስ/መዋቅር የምስክር ወረቀት የተሰጠው ወይም
ስልጠናውን ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ፤
 የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ በየደረጃው የወሰዱና የብቃት
ምዘና ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያለው
የተቋም ዲኖች እና ም/ዲኖች ምልመላ እና አመዳደብ
የተቋም ዲኖች እና ም/ዲኖች ምልመላ፣ አመዳደብና ፈፃሚ አካል
 የተቋም አመራሮች ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና
አሰልጣኞች መካከል የሚወዳደሩት በዚህ መመሪያ
በተዘጋጀው መመልመያ መስፈርት መሠረት ሲሆን በክልሉ
ወይም በከተማ አስተዳደሩ የቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ/ኤጀንሲ
ደረጃ በሚቋቋም አወዳዳሪ ኮሚቴ ወይም በክልሉ ወይም
በከተማ አስተዳደሩ የቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ/ኤጀንሲ ህጋዊ
ውክልና በተሰጠው አካል አማካኝነት ተከናውኖ ለክልሉ
ወይም ለከተማ አስተዳደሩ ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና/ቢሮ/ኤጀንሲ
ኃላፊ ቀርቦ ይፀድቃል
የተቋም ዲኖች እና ም/ዲኖች መመልመያ መስፈርት
 የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመተግበር ቁርጠኛ የሆኑ
እና ራሳቸውን ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ያጸዱና
ኪራይ ሰብሳቢዎችን በጽናት የሚታገሉ፤
 በስራው ከሌሎች የተሻለ ምርጥ ፈጻሚ በመሆን አርአያ
ሆኖ በሚሰለጥኑበትና በሚያሰለጥኑበት ሙያ ልዩ ድጋፍ
ለሚያስፈልጋቸው ሰልጣኞችና አሰልጣኞች ድጋፍ
በማድረግና በማብቃት የተሻለ ፈጻሚ እንዲሆኑ ያደረገ፤
 የቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ተቋሙ ያለበትን ክልሉን የስራ ቋንቋ
የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
የዲኖችና ምክትል ዲኖች ምልመላ መስፈርት ነጥብ አሰጣጥ
 የ18ወራት ስራ አፈጻጸም 30%
 የትምህርት ደረጃ 10%

 የተለያየ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ማለትም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ


ዲገሪ እና በፒኤችዲ ዲግሪ ደረጃ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ተወዳዳሪዎች
በሚወዳደሩበት ወቅት የነጥብ አሰጣጡም ለመጀመሪ ዲግሪ 8%፣ ለሁለተኛ
ዲግሪ 9% እና ለፒኤችዲ ዲግሪ 10% የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 የስራ ልምድ (አገልግሎት) 10%

 ለዲንና ምክትል ዲን ለመወዳደር ዝቅተኛ አገልግሎት እንደየክልሉ ተጨባጭ


ሁኔታ ከ2-5 ዓመት ሁኖ፤ ለእያንዳንዱ ተወዳዳሪ የሚሰጠው የስራ ልምድ
ውጤት እንደየአገልግሎቱ መጠን ከሁለት ዓመት እስከ 10 ዓመት አገልግሎት
ያለው ከ2-10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ከ10 ዓመት እና በላይ የስራ ልምድ
አገልግሎት ያለው በተመሳሳይ 10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ፈተና (የጽሁፍ፣
የቃል) 35% 10
 በክልሉ/ዞኑ/ከተማ አስተዳደሩ ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ/ኤጀንሲ ሀላፊ የሚሞላ 15%
የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ምልመላና አመዳደብ
የተቋማት የስልጠና ዘርፍ አስተባባሪዎች ምልመላና ምደባ በተመለከተ በተቋሙ ውስጥ
በዘርፉ ካሉ አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች መካካል ተወዳድረው የሚመደቡ ሆነው ቀጥሎ
ያለውን መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡፡
 የ18 ወራት ስራ አፈጻጸም 30%

 የትምህርት ደረጃ 10%

 በተለያየ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ማለትም በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲገሪ እና


በፒኤችዲ ዲግሪ ደረጃ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት ወቅት
የነጥብ አሰጣጡም ለመጀመሪ ዲግሪ 8%፣ ለሁለተኛ ዲግሪ 9% እና ለፒኤችዲ ዲግሪ እና
10% የሚሰጥ ይሆናል፡፡
 የስራ ልምድ (አገልግሎት) 10%

 ለዘርፍ አስተባባሪነት ለመወዳደር ዝቅተኛ አገልግሎት ሁለት ዓመት እና በላይ ሁኖ፤


ለእያንዳንዱ ተወዳዳሪ የሚሰጠው የስራ ልምድ ውጤት እንደየአገልግሎቱ መጠን ከሁለት
ዓመት እስከ 10 ዓመት አገልግሎት ያለው ከ2-10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ከ10 ዓመት እና
በላይ የስራ ልምድ አገልግሎት ያለው በተመሳሳይ 10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡
 ፈተና (የጽሁፍ፣ የቃል) 35%

 በተቋሙ ማኔጅመንት ኮሚቴ የሚሞላ 15%


 ዲኖች እና ምክትል ዲኖች ለደረጃ እድገት ለመወዳደር
ሊያመሉ የሚገባቸዉ መስፈርቶች
 የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ዲኖች እና ምክትል ዲኖች
አሰልጣኞችን/ኢንስትራክተሮችን እና የተቋሙን ማህበረሰብ
በማስተባበር፤የስራ እቅድ የማዘጋጀት ፡የማስፈጸም ፤ እና ክትትል
የማድረግ የመገምገምና ተግባሮችን ለማከናወን እንዲሁም በአካባቢዉ
ካሉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ጋራ
ጤናማ ግንኙነት በመፍጠር ተግባር ተኮር የትብብር ስልጠና ደረጃዉን
በጠበቀ ሁኔታና እንዲሰጥና የበቁ ሰልጣኞችን አፍርተዉ/ችግር ፈቺ
ቴክኖሎጂዎችን ለኢንዳስትሪዉ/ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት
በማቅረብ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማቱን ተወዳዳሪነት የማረጋገጥ
ከፍተኛ ሓላፊነት የሚጣልባቸዉ ናቸዉ፡፡በመሆኑም ይህንን የዲኖች እና
ም/ዲኖች ሰፊ የአመራርና የማስተባበር ብቃታቸዉን በመለካት ሌሎች
አሰልጣኞች ከአንድ ደረጃ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለማደግ በሚመዘኑበት
መስፈርት መሰረት የደረጃ እድገታቸዉ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ለደረጃ እድገት ለመቅረብ
ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች
1.የሲ-ደረጃ አሰልጣኞች ለደረጃ
እድገት ለመቅረብ ማሟላት
የሚገባቸዉ መስፈርቶች
የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች
ከጀማሪ አሰልጣኝነት በጀማሪ አሰልጣኝነት ቢያንስ ሁለት(2) አመት በ
ወደረዳት አሰልጣኝነት ስራ
የሁለት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካ
65% እና በ
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢ
ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማ
በአማካ

በቆይታው በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ለጥ.አ.ኢ


ድጋፍ በመስጠትና በምዘና ብቃታቸውን እንዲ
በማድረግ ሀብት እንዲያፈ
ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን መሰረት አንድ አዋጭ
100% በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን
ተ.ቁ
የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች
2
በረዳት አሰልጣኝነት ቢያንስ ሁለት(2) አመት
ከረዳት በማሰልጠን ስራ ያገለገለ፤
አሰልጣኝነት ወደ የሁለት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ
አሰልጣኝነት ውጤት 70% እና በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ
እንደ ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት
ግብ በአማካኝ ያሟላ
በቆይታው በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ለጥ.አ.ኢ
የተሟላ ድጋፍ በመስጠትና በምዘና ብቃታቸውን
እንዲያረጋግጡ በማድረግ ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፣
ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን መሰረት ሁለት አዋጭ
ቴክኖሎጅ 100% በመቅዳት
የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና
ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤
የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ
ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች
3 በአሰልጣኝነት ቢያንስ ሶስት(3) አመት በማሰልጠን ስራ
ከአሰልጣኝነት ወደ ያገለገለ፤
ከፍተኛ አሰልጣኝነት
የሁለት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት
75% እና በላይ የሆነ፤

በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ


ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ
በአማካኝ ያሟላ
ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን መሰረት ሁለት አዋጭ ቴክኖሎጅ
100% በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤
በዘርፉ ለሚገኙ ለጀማሪና ረዳት አሰልጣኞች ተከታታይ
ሙያዊ ድጋፍ ያደረገ

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


. የB-ደረጃ ኢንስትራክተሮች
ለደረጃ እድገት ለመቅረብ
ማሟላት የሚገባቸዉ
መስፈርቶች
ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

1 ከጀማሪ ኢንሰስትራክተርነት በጀማሪ ኢንሰስትራክተርነት ቢያንስ ሁለት(2) አመት


ወደረዳት ኢንስትራክተርነት በማሰልጠን ስራ ያገለገለ፤
የሁለት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት
75% እና በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ
ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ
በአማካኝ ያሟላ
በቆይታው በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ለጥ.አ.ኢ የተሟላ
ድጋፍ በመስጠትና በምዘና ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ
በማድረግ ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፣

ለሲ-ደረጃ አሰልጣኞች ተከታታይ ሙያዊ ድጋፍ ያደረገ

ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን መሰረት አንድ አዋጭ ቴክኖሎጅ


100% በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


ተ.ቁ
የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች
2 በረዳት ኢንሰስትራክተርነት ቢያንስ ሁለት(2) አመት በማሰልጠን
ከረዳት ኢንሰስትራክተርነት ወደ ስራ ያገለገለ፤
ኢንሰስትራክተርነት የሁለት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት 80%
እና በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ ሃገር
ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ በአማካኝ ያሟላ

በቆይታው በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች ለጥ.አ.ኢ የተሟላ ድጋፍ


በመስጠትና በምዘና ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ በማድረግ ሀብት
እንዲያፈሩ ያደረገ፣

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች እና ጀማሪ ኢንስትራክተሮች


ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ
ተዘጋጅቶ በቀረበ ዲዛይን መሰረት ሁለት አዋጭ ቴክኖሎጅ 100%
በመቅዳት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና
ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

3 በአሰልጣኝነት ቢያንስ ሶስት(3) አመት በማሰልጠን ስራ


ከኢንሰስትራክተርነት ወደ ከፍተኛ ያገለገለ፤
ኢንሰስትራክተርነት የሶስት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት
85% እና በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ
ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ በአማካኝ
ያሟላ

በቆይታው ቢያንስ የ 3 አዋጭ ቴክኖሎጂ ዲዛይን በማዘጋጀትና


100% በመቅዳት እንዲሁም የ1 ቴክኖሎጂ ሙሉ ዲዛይን
በማሻሻል እና በመስራት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች ፤ጀማሪ እና ረዳት


ኢንስትራክተሮች ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

በአሰልጣኝነት ቢያንስ አራት(4) አመት በማሰልጠን ስራ


ያገለገለ፤
የአራት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት
90% እና በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ
ሃገር ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ
በአማካኝ ያሟላ

በቆይታው ቢያንስ የ 3 አዋጭ ቴክኖሎጂ ዲዛይን


በማዘጋጀትና 100% በመቅዳት እንዲሁም የሁለት
ከከፍተኛ ኢንሰስትራክተርነት ወደ መሪ ቴክኖሎጂዎች ዲዛይን በማሻሻልና ቴክኖሎጂዎችን በመስራት
4
ኢንሰስትራክተርነት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና ሀብት
እንዲያፈሩ ያደረገ፤

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች ፤ጀማሪ እና ረዳት


ኢንስትራክተሮች ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


የA-ደረጃ
ኢንስትራክተሮች ለደረጃ
እድገት ለመቅረብ ማሟላት
የሚገባቸዉ መስፈርቶች
ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

1 በኢንስትራክተርነት ቢያንስ ሶስት(3) አመት በማሰልጠን ስራ


ከኢንሰስትራክተርነት ወደ ያገለገለ፤
ከፍተኛ ኢንሰስትራክተርነት የሶስት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት 90% እና
በላይ የሆነ፤
በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ ሃገር
ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ በአማካኝ ያሟላ

በቆይታው ሁለት አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን ዲዛይን በማሻሻልና


ቴክኖሎጂውን በመስራት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ
ማድረግ የቻለና ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች ፤ጀማሪ እና ረዳት ኢንስትራክተሮች


ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


በኢንስትራክተርነት ቢያንስ አራት(4) አመት በማሰልጠን ስራ ያገለገለ፤

የአራት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት 95% እና


በላይ የሆነ፤

በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ ሃገር ለአመቱ


የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ በአማካኝ ያሟላ

ከከፍተኛ በቆይታው ሶስት አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን ዲዛይን በማሻሻል እና


2 ኢንሰስትራክተርነት ወደ ቴክኖሎጂዎችን የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና
መሪ ኢንሰስትራክተርነት ሀብት እንዲያፈሩ ያደረገ፤

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች ፤ጀማሪ እና ረዳት ኢንስትራክተሮች


ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ

የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ


ተ.ቁ የዉድድር ደረጃ መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች
በኢንስትራክተርነት ቢያንስ አራት(4) አመት በማሰልጠን ስራ
ያገለገለ፤

የአራት ዓመት አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም አማካይ ውጤት 95% እና


በላይ የሆነ፤

በቆይታው ካሰለጠናቸው ሠልጣኞች መካከል ቢያንስ እንደ ሃገር


ለአመቱ የተቀመጠውን በምዘና የማብቃት ግብ በአማካኝ ያሟላ
መሪ ኢንሰስትራክተርነት
3 ወደ ዋና በቆይታው አራት አዋጭ ቴክኖሎጂዎችን ዲዛይን በማሻሻልና
በማምረት እንዲሁም ሁለት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር
ኢንሰስትራክተርነት የጥ/አ/ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ማድረግ የቻለና ሀብት
እንዲያፈሩ ያደረገ

በዘርፉ ለሚገኙ አሰልጣኞች ፤ የBእናየA ኢንስትራክተሮች


ተከታታይ ድጋፍ ያደረገ
የትብብር ስልጠናን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያደረገ
የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደመወዝ ደረጃ ዕድገት አሰጣጥ
ሂደት
 የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደመወዝ ደረጃ ዕድገት አሰጣጥ ሂደት
ዓይነቶች ሶስት (3) ሲሆኑ እነዚህም፡-
 ከአንዱ ደረጃ ወደ ሚቀጥለው የደረጃ ተዋረድ አምዳዊ ዕድገት (Vertical
Career) የሚሰጠው ለየደረጃው በተቀመጡት የመቆያ ጊዜያትና በተገኙት
ሥራ የግምገማ ውጤቶች ላይ ተመስርቶ የሚከናወን ይሆናል፡፡
 ሀ. ከጥር 1 እስከ ሰኔ 30 መካከል አዲስ ለሚቀጠሩ ወይም በደረጃ ዕድገት
ሁለት እርከንና በላይ ያገኙ ወይም በዲሲፕሊን ከደረጃ ዝቅ ያሉ አሠልጣኞች
መደበኛ የደመወዝ ጭማሪ የሚያገኙት ከሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ ነው፤
 ለ. ከሐምሌ 1 እና ታህሳስ 30 መካከል አዲስ የተቀጠሩ ወይም በደረጃ
ዕድገት ከሁለት እርከንና ከዚያ በላይ ያገኙ ወይም በዲሲፒሊን ከደረጃ
ዝቅ ያሉ አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች መደበኛ ጭማሪ የሚያገኙት
ከጥር 1 ጀምሮ ይሆናል፤
 የጎናዊ የእርከን ደመወዝ ጭማሪ (Horizontal Career) የሚሰጠው
በሌላ መመሪያ ወደ ፊት እስካልተተካ ድረስ በየዓመቱ የሚታይ ሲሆን
እንደ ሃገር ለሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ሲፈቀድ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
 የትምህርት ማሻሻያ የደመወዝ ዕድገት ጭማሪ አሰጣጥ

 ከሚመለከተው የቴ/ሙ/ት/ስ/ዘርፍ መዋቅር ጋር በህግ ፊት የጸና


ውል ይዘው በሀገር ውስጥ እውቅና ካላቸው ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት
እንዲሁም ከሀገር ውጪ ትምህርታቸውን አሻሽለው ለሚመለሱ
አሠልጣኞች ከዚህ በታች በተቀመጠው ሠንጠረዥ መሠረት
የሚፈጸም ይሆናል፡፡
ከትምህርት ማሻሻል በፊት ከትምህርት ማሻሻል በኋላ ምርመራ
የነበረበት ደረጃ የሚደርሱበት አዲሱ ደረጃ

የC ጀማሪ አሰልጣኝ B ጀማሪኢንስትራክተር በተቋሙ ፍላጎትና እቅድ


መሰረት ወደ ከፍተኛ
ትምህርት ተቋም
የC ረዳት አሰልጣኝ Bጀማሪኢንስትራክተር ተልከው
ትምህርታቸውን
አሻሽለው ሲመለሱ
በሙያው በሚጠበቀው
የC አሰልጣኝ B ረዳት ኢንስ Aትራክተር ደረጃ በምዘና
ብቃታቸውን ማረጋገጥ
ይጠበቅባቸዋል
የC ከፍተኛ አሰልጣኝ B ኢንስትራክተር

የ Bጀማሪኢንስትራክተር የ A ኢንስትራክተር

የB ረዳት ኢንስትራክተር የ A ኢንስትራክተር

የB ኢንስትራክተር የ A ኢንስትራ Aክተር

የB ከፍተኛ ኢንስትራክተር የ A ከፍተኛ ኢንስትራክተር


የB መሪ ኢንስትራክተር የ A መሪ ኢንስትራክተር
በየደረጃው የሚፈጸም የደረጃ ዕድገት ሥርዓት

የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት በተቋም የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ


ተቋቁሞ ለደረጃ ዕድገት የሚቀርቡ አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ
ዕድገት አፈፃፀም በተቋም ደረጃ ተግባራዊ የሚሆነው የውጤት ተኮር ትምህርትና
ስልጠናው እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደቱ ማለትም የተቀዱና የተሻሻሉ እና
አዳዲስ የተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች የተቋሙ ማኔጅመንት በሃላፊነትና በተጠያቂነት
አይቶና ገምግሞ ለተቋሙ ቦርድ በማፀደቅ ወደ
በክልል/ከተማ/አስ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ/ኤጀንሲ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው
ኮሚቴ ተልኮ ሲይፀድቅ ነው፡፡
የተቋም አመራሮች የደረጃ ዕድገት ተግባራዊ የሚሆነው በተቋሙ ማኔጅመንት
በተጠያቂነት ገምግሞ እና በቦርዱ ታይቶ ለክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ
ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ/ኤጀንሲ ቀርቦ ሲጸድቅ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልል/ከተማ
አስተዳደር ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮዎች/ኤጀንሲዎች እንዲሁም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በተቀመጠው አሰራር መሰረት የቴክኖሎጂ ቅጂ፣
ማሻሻል እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በተሰጣቸው ሃላፊነት መሰረት
ሚናቸውን ይወጣሉ፡፡
በየደረጃው የሚፈጸም የደረጃ ዕድገት ሥርዓት

የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት በተቋም የደረጃ


ዕድገት ኮሚቴ ተቋቁሞ ለደረጃ ዕድገት የሚቀርቡ አሠልጣኞችና
ኢንስትራክተሮች ዉድድሩ በተቋም ደረጃ ከተከናወነ በሐዋላ
ተግባራዊ የሚሆነው የተቋሙ ማኔጅመንት አይቶና ገምግሞ
በተቋሙ ቦርድ ሲይፀድቅ ነው፡፡
የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት ኮሚቴ አባላት
 የተቋም የውጤት ተኮር ሥልጠና ም/ዲን-------------------------ሰብሳቢ
 የተቋም ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን----አባል
 የአሠልጣኙ ዘርፍ ተጠሪ -------------------------------------------አባል
 የተቋሙ መምህራን ማኅበር ሰብሳቢ ------------------------------አባል
 የሰው ሀይል አስተዳደር የስራ ሂደት ባለቤት------------------------ጸሃፊ
 ከሰው ሀይል የስራ ሂደት አንድ ባለሙያ---------------------------አባል
 የመምህራን ማህበር ሥርዓተ- ፆታ ተጠሪ--------------------------አባል
የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ደረጃ ዕድገት ኮሚቴ ተግባርና
ኃላፊነት
 በዘመኑ ለደረጃ ዕድገት የሚቀርቡ አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ለደረጃ
ዕድገቱ ከመቅረባቸው በፊት ያከናወኗቸውን ተጨባጭ መስፈርቶች
የሚገልፅ ዝርዝር መረጃ በተቋሙ በሚመለከታቸው ምክትል ዲን እና
ይቀርባል፡፡/የሰዉ ሐይል አስተዳደር የሚመለከተዉን መረጃ የማጠናቀር
ይሰራል ይህም ማለ/
 የቀረቡ መረጃዎች ታአማኒነት ኮሚቴዉ ያረጋግጣል፡፡

 ኮሚቴዉ ተገቢ ቃለጉባኤ በመያዝ ለደረጃ እድገቱ የተቀመጠዉን

መስፈርት ያመሉትን በየደረጃዉ የእድገት መሰላል መሰረት አጣርቶ


ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለተመ 㔫 ጋር ቋሙ ማናጅሜንት
ያስተላልፋል::
 የተቋሙ ማናጅሜንት ከደረጃ ዕድገት የቀረበለትን ዝርዝር መረጃ ካጣራ
በሐዋላ ለተቋሙ ቦርድ አቅርቦ ያጸድቃል
የዲኖች እና ም/ዲኖች የሰረጃ እድገት አፈፃፀም
ዲኖች እና ምክትል ዲኖች በአሰልጣኞች ና ኢንስትራክተሮች
የደረጃ እድገት መሰላል በደረሱበት ደረጃ ላይ ደረጃ
የሚያስገኝላቸዉን ደሞዝ ያገኛሉ፤በሚያሳዩት ተጨባጭ ጥረትና
ዉጤት እንዲሁም በቆይታቸዉ ወቅት በአመቱ የተቀመጠዉን
የሙያ ብቃት ምዘና ግብ አማካይ ያመሉ በአሰልጣኙና
ኢንስትራክተሮች የደረጃ እድገት መሰላል መሰረት
ወደሚቀጥለዉ ደረጃ ያድጋሉ
የአቤቱታ እና ቅሬታ አቀራረብ ሂደት
አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች በየደረጃው ባለ የደረጃ
ዕድገታቸው አፈጻጸም ላይ ቅሬታ ካላቸው አቤቱታቸውን
በሲቪል ሰርቪስ የቅሬታ አቀራራብ አሰራር መሰረት በየደረጃው
ላሉ የሚመለከታቸው አካላት ቀርቦ በተገቢው መረጃ ላይ
ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡
የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜን በተመለከተ፤
 ቅሬታ ያለባቸው አሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ጉዳዩን ለቅርብ አለቃ
ወይምለሚመለከተዉ ሐላፊ በማቅረብ ውሳኔ ከተወሰነበት/ዉይይት/
ቀን ጀምሮ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻቸውን ለተቋሙ
የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 ከፍ ሲል በተወሰነው ጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት
የቅሬታውን ማመልከቻ ሊያቀርብ ያልቻለ ከሆነ ከአቅም በላይ የሆነው
ምክንያት በተወገደ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ ማመልከቻውን ሊያቀርብ
ይችላል፡፡
 ቅሬታ ማጣራትን በተመለከ፤
 የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፡-

 የቅሬታ ማመልከቻውን እና አግባብ ያላቸው ማስረጃዎች በመመርመር፣ ጉዳዩን


የሚመለከታቸውን ሁሉ አግባብነት ያላቸው ህጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና
የአሰራር ልምዶችን በማገናዘብ የቀረበለትን ቅሬታ ያጣራል፡፡ የምርመራውን
ውጤትና የውሳኔ ሀሳብ የያዘ ሪፖርት ለተቋሙ ዲን በአስር የስራ ቀናት ውስጥ
በማቅረብ ያስወስናል፡፡ የተቋሙ ዲን አንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የኮሚቴውን
ውሳኔ የማጽደቅ ወይም በቂ ምክንያት ሲኖረው የተለየ ውሳኔ የመስጠት ወይም
ኮሚቴው ጉዳዩን እንዲያጣራ ማድረግ ይችላል፡፡
 አቤቱታው የአስተዳዳራዊ አፈጻጸም ችግር የሚኖረው ሆኖ ከተገኘ ቅሬታ ያነሱ
የአሰልጣኞችንና ኢንስትራክተሮችን ቅሬታዎች የተቋሙ ዋና/ምክትል ዲን
በማደራጀት ደረጃውን በመጠበቅ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ ለክልል
ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የክልል ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ የቀረበለትን
አቤቱታ አግባብነት ባላቸው ህጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎችና የአሰራር ልምዶችን
በማገናዘብ የቀረበለትን ቅሬታ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያጣራል፤ ውሳኔም
ይሰጣል፡፡

ልዩ ልዩ ሁኔታዎች

 አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ከማሠልጠን ሥራ መደብ በራሳቸው ፍላጎት ወደ


ቴ/ሙ/ት/ስ ጽ/ቤት/ቢሮ/ኤጀንሲ ተመድበው ከሠሩ በዚያ ደረጃ የሚሰጠው ግምገማ
በተቋም ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራት ጋር ተመሳሳይነት ስለሌለው ምዘናው ለደረጃ
ዕድገት ውድድር አይያዝላቸውም፡፡
 እያንዳንዱ የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት የራሱ የቆይታ ጊዜ
ያለው ስለሆነ አሠልጣኞች እና ኢንስትራክተሮች በደረሱበት ደረጃ የቆይታ
ጊዜአቸውን ሳያሟሉ በተለያዩ ምክንያቶች ከስራ ገበታቸው ተለይተው ቆይተው
ሲመለሱ ከመሄዳቸው በፊት በነበሩበት ደረጃ ተመልሰው የቆይታ ጊዜያቸውን
ጠብቀውና ተገምግመው የደረጃ ዕድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
 አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች በጤና ችግር ምክንያት በማሠልጠን ሥራ ሊቀጥሉ
ካልቻሉ ይኸው በሐኪም ቦርድ ሲረጋገጥ ለቴ/ሙ/ት/ስ ጽ/ቤት/ቢሮ/ኤጀንሲ ቀርቦ
በሌላ ሥራ መደብ ቦታ ካለው በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት ተዛውረው እንዲሰሩ
ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህ በኋላ የደረጃ ዕድገቱም የሚታይላቸው ከህመሙ
ተሽሎአቸው ወደ አሠልጣኝነት ወይም ኢንስትራክተርነት የሥራ መደብ ተመልሰው
ሲመደቡና ዕድገቱ የሚፈልገውን የቆይታ ጊዜ ሲያሟሉ የዕድገቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
 2
…………….የቀጠለ
 አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች በራሳቸው ፍላጎት ወደ ሌላ መሥሪያ ቤት
ከተዛወሩና ከተወሰነ ጊዜ ቆይታ በኋላ ወደ አሠልጣኝነት ሙያ ለመመለስ ጥያቄ
ቢያቀርቡ የሰለጠኑበት ሙያ በተቋሙ ውስጥ ሥልጠና የሚሰጥበት ከሆነና
የአሠልጣኝ እጥረት ካለ በሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት ሲሰጡ የነበሩት ሥልጠና
ውጤታማ መሆኑ ተጣርቶና በጀት መኖሩ ተረጋግጦ ወደ ሥራ ተመልሰው
ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ ሲመለሱም ቀደም ሲል በነበረበት ሙያ እና ደረጃ ይሆናል፡፡
ነገር ግን የትምህርት ደረጃ ለውጥ የሚመጣ ከሆነ የቀድሞ አገልግሎትና የሙያ
ደረጃ ተገናዝቦ በሚመጥነው ደረጃ ይመደባሉ
 ………………………የቀጠለ
 አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ከአንድ ደረጃ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ለማደግ
በሚደረገው ሂደት በመጀመሪያው የእድገት ውድድር ቴክኖሎጂ በመቅዳት፣ በማሻሻልና
በአዳዲስ ፈጠራ ስራዎች ከሆነ ያላለፉ ለ2ኛ ጊዜ ለውድድር ለመቅረብ የተከታዩን አንድ
አመት ሁለት የግምገማ ውጤት በማካተት እና መደበኛ ስልጠናን ፣ ገበያ-ተኮር አጫጭር
ስልጠናን፣ የትብብር ስልጠናን እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
የሚሰጠውን ድጋፍ ጥራትና ብቃት ለማረጋገጥ የሙያ ብቃት ምዘና በየደረጃው
በማምጣት እና ብቃቱን በማረጋገጥ ባሉበት ደረጃ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚወዳደሩ
ይሆናል፡፡ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ካለፉ ለሚቀጥለው ደረጃ ዕድገት የሚቀርቡት ዕድገቱን
ካገኙበት ቀን ጀምሮ የመቆያ ጊዜ ጠብቆ ይሆናል፡፡ ይህም በአሠልጣኞች
ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት ሂደት ውስጥ ለአንድ ጊዜ ብቻ ሊሰጥ የሚችል ዕድል
ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ካሉት ደረጃዎች በአንዱ ላይ ብቻ የሚሰጥ ዕድል ሆኖ በሌላው
ደረጃ ላይ በድጋሚ የዚህ አይነቱ እድል ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የዚህ ዓይነት ሁኔታ
ሲያጋጥም የመቆያ ጊዜአቸውን እየጠበቁ የሙያ ብቃት ምዘና በየደረጃው በማምጣት
ለዕድገት የሚቀርቡ ይሆናል፡፡ ተወዳድረው ካላለፉ ባሉበት ደረጃ የተሰጣቸውን የቆይታ
ጊዜ ጠብቀው ሊቀርቡ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ይህንንም የሙያ ብቃት ምዘና
የኢንዱስትሪ ውስጥ መሪ መዛኞችን በማፍራት አሰልጣኞችን፣ ኢንስትራክተሮችንና
አመራሮችን በየደረጃ ብቃታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ለዚህም በየደረጃው ያለ
የሙያ ደረጃና ብቃት ምዘና ማዕከላት ተግባሩን በበላይነት መምራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 ……………………..የቀጠለ
 ለአመራሮች፣ አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የሚሰጥ የደረጃ እድገት ለሥራ
አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ባለሙያዎችን ለመሳብና ለማነቃቃት ከሚደረጉ
የአበል ክፍያዎች እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጋር ግንኙነት አይኖረውም፡፡
 የአሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች የደረጃ ዕድገት አሰጣጥ በአሠልጣኞችና
ኢንስትራክተሮች መካከል የሚደረግ ውድድር ሳይሆን በተቀመጠው የመመዘኛ
መስፈርት ስታንደርድ በሆነ መለኪያ የሚመዘኑበት ወይም የሚለኩበትና
የተቀመጠውን ስታንዳርድ መለኪያ ሲያሟሉ ለዕድገት የሚቀርቡበት ሂደት
ነው፡፡
 የአሰልጣኞችና ኢንስትራክተሮች ለደረጃ እድገት የሚወዳደሩት ከተቀጠሩበት
ቀን ጀምሮ የቆይታ ጊዜያቸውን ሲያሟሉ ሆኖ የደረጃ እድገት ውድድሩ
የሚካሄደው በየአመቱ ሐምሌ እና ጥር ወር ነው፡፡ የግምገማ ማጠናቀቂያና የደረጃ
ዕድገት ማግኛ ወቅት በየተቋሙ የግምገማ ጊዜ ከሐምሌ 1 እስከ ታህሳስ 30 እና
ከጥር 1 አስከ ሰኔ 30 ሲሆን አሠልጣኞችና እንስትራክተሮችም በደረሱባቸው
ደረጃ ካላቸው ቆይታ አኳያ ይሆናል፡፡
 ……………………………የቀጠለ
 በዲሲፕሊን ጉዳዮች የሚሰጡ ውሳኔዎች የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደር ደንብን
መሠረት በማድረግ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
 ለሙያ ብቃት ምዘና የተሰጠ ማስረጃ የሚያገለግለው ለደረጃ ዕድገት ባለቡት
የአሰልጣኝነት ደረጃ ለደረጃ ዕድገት ውድድር ቆይታ በሚጠይቀው ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡
 የማህበረሰብ ክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከላት በገበያ ፍላጎት ላይ በመመርኮዝ የደረጃ 1
እና 2 እንዲሁም አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት በርካታ ስራ አጥ ዜጎችን አብቅቶ
ወደ ስራ ለማሰማራት የሚያግዙ ማዕከላት ሆነው በሲ ደረጃ ከፍተኛ አሠልጣኝ
የሚመሩ ይሆናል፡፡
 ለደረጃ ዕድገት የሚቀርቡ አሠልጣኞችና ኢንስትራክተሮች አገልግሎት የሚያዘው
በመንግስት ተቋም ውስጥ በአሠልጣኝነት ያገለገሉበት ጊዜ ብቻ ታሳቢ ተደርጎ
ይሆናል፡፡
 በግል ተቋማት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ወይም በቢሮ በመሥራት የተገኘ የስራ
ልምድ በተቋም ውስጥ ለሚደረግ የደረጃ እድገት ውድድር አይያዝም፡፡ እንዲሁም
በተለያየ ምክንያት ከሥራ ቦታው የተለየበት ጊዜ ወይም ለትምህርትና ስልጠና ተብሎ
ከ 3 ወር በላይ የተሰጠ ፈቃድ ለደረጃ ዕድገት የቆይታ ጊዜ አይያዝም፡፡ ነገር ግን ከላይ
በቁጥር 2.10.14 የተጠቀሰው ፈቃድ የወሊድ ፍቃድን አይመለከትም፡፡
………………….የቀጠለ
 አንድ አሠልጣኝ/ኢንስትራክተር ለደረጃ ዕድገት ቀርቦ ካለፈና ቀደም ሲል
ሲከፈለው የነበረው ደመወዝ ለሚወዳደርበት ደረጃ ከተያዘው መነሻ ደመወዝ
ጋር ተመሳሳይ ወይም ከዚ በላይ የሚያገኝ ሆኖ ከተገኘ ወደ ጎን አንድ እርከን
(Horizontaly) የሚጨመርለት ይሆናል፡፡
 በሌላ መመሪያ ካልተፈቀደ በስተቀር በደረጃ ዕድገት ጊዜ የጎንዮሽና ዓምዳዊ
ዕድገት በአንድ ጊዜ ሊያገኝ አይችልም፡፡
 በተቋም ዲኖችና ምክትልዲኖች ምልመላ ወቅት ብቁ የሆኑ ሴቶችን ወደ
ሀላፊነት ማምጣት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡
 ከውጪ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃን በተመለከተ አሻሚ ሆኖ ከተገኘ
በሚመለከተው እውቅና ሰጪ አካል ተረጋግጦና አቻ ግምት ወጥቶለት ሲቀርብ
ተግባራዊ ይሆናል

 በየደረጃው ባለው የመምህራን ማህበር ፅ/ቤት ተመራጮች እንደማነኛውም


አሰልጣኝ/ኢንስትራክተር የደረጃ ዕድገቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን በሙሉ ጊዜ
እና በተመላላሽ በማህበሩ ፅ/ቤት የሚያገለግሉ አሰልጣኞች/ኢንስትራክተሮች
የሚገመገሙት ለማህበሩ አመራር ተዘጋጅቶ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈው
የመገምገሚያ ቅፅ ሁኖ በማህበሩ ፅ/ቤት በሚሞላላቸው የግምገማ ውጤት
ለደረጃው የተቀመጠውን ነጥብ ሲያሟሉ የደረጃ ዕድገት ተጠቃሚ ይሆናሉ

You might also like