You are on page 1of 20

መመሪያ ቁጥር 9/ 2ዐዐ5 ዓ/ም

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የነባር እና አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ
አቅርቦት ፣አሠጣጥና ግንባታን ለመወሰን የወጣ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት መመሪያ

በክልሉ ባለፉት አምስት ዓመታት በከተሞች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ አሠጠጥ ከኪራይ ሰብሳቢነት በነፃ መልኩ
ለማስተናገድ ያመች ዘንድ ታግዶ የቆየ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከልም ሆነ ለማስወገድ የማያስችል
የህግና የአሠራር ዝግጅት የተከናወነ በመሆኑ፣

በክልሉ ውስጥ በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ የቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ተደራጅተው የሚገኙ ዜጐች የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቦታ ጥያቄ ስያቀርቡ በመቆየታቸው ለእነዚህ ዜጐች ምላሽ በመስጠት ዜጐች የመኖሪያ ቤት የማግኘት
መብታቸው እንዲረጋገጥ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡፡

ዜጐች ቁጠባን ባህል በማድረግና በማህበር በመደራጀት የመኖሪያ ቤትን በቀላሉ መስራት እንዲችሉ በማስቻል የቁጠባና
የመደራጀትን ፋይዳ እንዲገነዘቡ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ

በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች የሚገኙ ዜጐችን የቦታ አቅርቦት ጥያቄን ለመመለስ መሬትን በቁጠባና ፍትሃዊ በሆነ
መልኩ መጠቀም በማስፈለጉ፣

የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ መሠረት የከተማ ቦታ በምደባ ከሚያስተናገድባቸው መንገዶች አንዱ
በመንግስት ለሚካሄዱ የመኖሪያ ቤቶች ልማት ማህበራት ኘሮግራሞችና በመንግስት እየተወሰኑ ለሚካሄዱ በራስ አገዝ
የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበራት ለሚደራጁ ማህበራት በመሆኑ፣

በአማራ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 7 እና
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋምና ስልጣንና ተግባራቸውን
ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 176/2ዐዐ3 አንቀጽ 36 መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፣
ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1.አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የነባር እና አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ አቅርቦትን


፣አሠጣጥና ግንባታን ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 9/2ዐዐ5 ዓ/ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2.ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ፣


1. “ አዋጅ “ ማለት የህብረት ሠራ ማህበራትን ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 134/1998 ፡፡
2. “የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር” ማለት የመኖሪያ ቤት ችግር ያላቸው ሰዎች የመኖሪያ ቤት
ችግራቸውን ለመቅረፍ በመኖሪያ አካባቢያቸው፣ በመስሪያ ቤታቸው በፈቃደኝነት በጋራ ተሰባስበው
ገንዘባቸውን ፣ እውቀታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን በማቀናጀት በጋራ የሚያቋቁሙትና
ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንግድ የሚያሰተዳድሩት ማህበር ማለት ነው፡፡
3. “ ማህበር “ ማለት በህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 134/98 መሠረት የተደራጀ እና የተመዘገበ
የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር ነው፡፡
4. “ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር” ማለት በከተሞች እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር ከሰኔ 3ዐ/2ዐዐ1
ዓ.ም በፊት ተቋቁሞ እስካሁን ድረስ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ ያልተረከበ ህብረት ሥራ ማህበር ነው፡፡
5. “አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር” ማለት እንደ ኢትዩጵያ አቆጣጠር ከሃምሌ ዐ1/2ዐዐ1 ዓ.ም
ጀምሮ የተቋቋመ እና ወደፊት የሚቋቋም የቤት ሥራ ማህበር ማለት ነው፡፡
6. “ራስ አገዝ የመኖ/ቤ/ህ/ስ / ማህበር “ ማለት በከተሞች የሚኖሩና መኖሪያ ቤት ለመስራት የሚደራጁ
ሲሆኑ በጉልበታቸው ጭምር በቤት ግንባታ ላይ የሚሳተፉ አባላትን ያካተተ ነው፡፡
7. “አሠሪ መ/ቤት “ ማለት በስሩ የመኖሪያ ቤት ለመስራት በህብርት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ለሚገኙ
ወይም ለሚደራጁ ሠራተኞች የቤት ግንባታ ወጪውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመሸፈን ለመስራት
ወይም ለማሰራት ፈቃደኛ ወይም ዝግጁ የሆነ መ/ቤት ወይም ኢንተርኘራይዝ ነው፡፡
8. “ዝግ ሂሳብ” ማለት የመኖሪያ ቤት ለመስራት በህብረት ሥራ ማህበር የተደራጀ ማንኛውም ግለሰብ
የኘሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲችል በቅድሚያ በህብረት ሥራ ማህበሩ አማካኝነት የቤቱን ግንባታ
ወጪ መቶ በመቶ ማስቀመጥ እንዲችል በባንክ ቤት በማህበሩ ስም የሚከፈትለት የማይንቀሳቀስ የቁጠባ
ሂሳብ ማለት ነው፡፡
9. “የቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ “ ማለት በማህበር የተደራጁም ሆነ በግልና በመንግስት ቤት
እንዲገነባላቸው ለሚፈለጉ አካላት በጠየቁትና በሚኖራቸው ውል መሠረት የቤት ግንባታ ለማካሄድና
ለማስረከብ ፈቃድ የተሰጠውና በመንግስት የተቋቋመ የቤት ልማት ድርጅት ነው፡፡
10. “ አደራጅ አካል” ማለት የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን ለማደራጀትና ለመመዝገብ በአዋጅ
ስልጣንና ኃላፊነት የተሰጠው የክልሉ ህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጄንሲንና በየደረጃው የሚገኙ
የህብረት ሥራ ማስፋፊያ አካላትን ያጠቃልላል፡፡
11. “ሰው “ ማለት የተፈጥሮ ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡
12. “ባንክ “ ማለት በኢትዬጵያ ብሔራዊ ባንክ እውቅና የሰጠው ባንክ ማለት ነው፡፡
13. ቢሮ ማለት የኢንዱስትራና ከተማ ልማት ቢሮ ነው፡፡

3.የፆታ አገላለጽ

በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው አገላለጽ የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

4.የተፈፃሚነት ወሠን

ይህ መመሪያ በክልሉ ከተሞች በሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ተመዝጋቢ ለመሆንና


ለመደራጀት በሚፈልጉ ግለሰቦች/ ማህበራት እና ማህበሩን ለማደራጀትና ለመመዝገብ ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ
ቦታ ለማመቻቸትና ለመስጠት እንዲሁም የግንባታ ሁኔታዎችን ተፈፃሚ ለማድረግ ግንኙነት ባለው ማንኛውም
ሰው ወይም አካል ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ክፍል ሁለት
የመመሪያው ዓላማዎችና መርሆዎች
5.የመመሪያው ዓላማዎች

1. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ በማህበራት የመኖሪያ ቤት ለማግኘት ለመደራጀት የሚፈልጉ አባላት


ሊያሟሉ የሚገባቸውን ቅድመ ሀኔታዎች ፣ ኃላፊነትና ግዴታዎች እንዲያውቁ በማድረግ ግልጽና ፍትሃዊ
የሆነ የምዝገባና አደረጃጀት ስርዓት ለመዘርጋት፣
2. ፈቃደኛ የሆኑና ፍላጐት ያላቸው ዜጐች በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ተደራጅተው ገንዘባቸውን
፣ ዕውቀቃቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን በማቀናጀት የመጠለያ ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት ሊፈቱ
የሚችሉበትን አማራጭ ለመፍጠር፣
3. ከዚህ በፊት በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተውና ገንዘብ ቆጥበው በመጠባበቅ ላይ
የሚገኙና እንዲሁም በአዲስ መልክ ለሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን የቤት ችግር
ለመፍታት፣
4. የመንግስትን የፖሊሲ አቅጣጫ ተከትለው ወጪ ቆጣቢ የመኖሪያ ቤቶችን ለመስራት በማህበራት
ለሚደራጁ ነዋሪዎች አስፈላጊውን የተቀናጀ ድጋፍና እገዛ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመቻቸት፣
5. በልማቱ የሚሳተፉ ባለሚናዎች ግልጽ የሆነ የአደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት ለማመልከትና የተቀናጀ ድጋፍ
ለማድረግ ነው፡፡

6.መርሆዎች

በአዋጅ ቁጥር 134/ 98 የተቀመጡት የህብረት ሥራ ማህበርት መርሆዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤


1. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር የሚታቀፉ አባላት ግዴታቸውን እስካሟሉ ድረስ ያለምንም
ልዩነት እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሠራር መከተል፣
2. የመኖሪያ ቤት ችግርን በራስ አቅም ለመፍታት የሚደረግ የገንዘብና የእውቀት አስተዋጽኦን የሚደግፍና
የሚያበረታታ አቅጣጫ መከተል፣
3. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር የሚደራጁ አባላት በህብረት ሥራ ማህበሩ ውሳኔ የመገዛት
ግዴታ እና የመሳተፍ መብታቸው እንዲጠበቅ በማድረግ ዲሞክራልያዊ አስተሳሰብን የተላበሱ እንዲሆን
ማድረግ፣
4. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር የመኖሪያ ቤት ቦታ ተጠቃሚነት የሚወሰነው በዕጣ አውጣጥ ስነ
ስርዓት ሆኖ በመጀመሪያ ደረጃ በዕጣ አወጣጡ የሚስተናገዱት እንደ ተመሰረቱበት አመተ ምህረት
ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን በማስቀደምና አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ
ማህበራትን በማስቀጠል ይሆናል፡፡
5. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት የቤት ልማት ኘሮግራም ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን
ተሳትፎ ያረጋገጠ ይሆናል፣
ክፍል ሦስት
የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባልነት ምዝገባ መስፈርቶች

7.በአጠቃላይ የአባልነት ምዝግባ መስፈርቶች

የአባልነት ምዝገባ መስፈርቶች በህብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 134/98 የተመለከተ ቢሆንም ለዚህ መመሪያ
አፈፃፀም ሲባል፣

1. ዕድሜው ከ18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ በህግና በፍርድ ያልተከለከለ ኢትዩጵያዊ
2. በሚደራጅበት ወይም በሚኖሪበት ከተማ ለተከታታይ ሁለት ዓመታት ነዋሪ የሆነ እንዲሁም ሠራተኛ ከሆነ
ደግሞ በሚኖርበት ከተማ በሚገኙ ተቋማት ውስጥ ቢያንስ ሁለት አመት በቋሚነት ተቀጥሮ የሠራ እና እየሠራ
ያለ፣
3. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በከተማው ውስጥ ባይኖርም በስራ ፣ በትምህርት ወይም በህክምና ምክንያት
ከከተማው ውጭ የኖረበትን ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፣
4. የህብረት ሥራ ማህበር አባልነት መመዝገቢያ ክፍያ መክፈል የሚችል፣
5. የቤቱን የግንባታ ወጪ 2ዐ በመቶ ከተደራጁ በኋላ በዝግ ሂሳብ የሚያስቀምጥ፤ 3ዐ በመቶውን የግንባታ
ፈቃድና መሬት ተዘጋጅቶ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ ህጋዊ እውቅና በሚጋኝበት ወቅት መክፈል
የሚችል መሆን ይኖርበታል ፣
6. ቀሪውን 5ዐ በመቶ በሂደት በመቆጠብ በግንባታው ሂደትና በማጠናቀቂያ ወቅት የሚከፈል ይሆናል፣
7. ለመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ ለተሰጠው ቦታ የመሬት ካሳ የራሱን ድርሻ መክፈል የሚችል፣
8. የህብረት ሥራ ማህበሩን ዓላማና መርሆዎች ለማክበርና የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ

9. በሚደራጅበት ከተማ ከዚህ በፊት በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም የመኖሪያ ቤትም ሆነ የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቤትም ሆነ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የሌለው ወይም ቦታ ኖሮት ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ ቦታ
ለማግኘት አይመዘገብም፣
10. በመንግስት በተዘረጉት ሌሎት የቤት ልማት ኘሮግራሞች ላይ በራሱም ሆነ በትዳር ጓደኛው ስም ተጠቃሚ
ያልሆነ ወይም ለመጠቀም ያልተመዘገበ ወይ ተመዝግቦም ከሆነ ምዝገባውን መሠረዙን ወይም መተውን
ግዴታ መግባት የሚችል፣

8.ተጨማሪ የምዝገባ መስፈርቶች

በዚህ መመሪያ በአንቀፅ 7 ሥር የተዘረዘሩት እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባል
የሆነ ተመዝጋቢ፣
1.ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ኘሮግራም ውስጥ ተጠቃሚ ለመሆን

ሀ. አሁን በሚኖርበት ከተማ ከዚህ በፊት በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባልነት ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝና
የህብረት ሥራ ማህበሩም ነባር አባል መሆኑን በዳግም ምዝገባ ማረጋገጥ አለበት፣

ለ. ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባለ ለመሆኑ በክልል አስተዳደር ባሉ የህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ
ኤጀንሲ ወይም በኤጄንሲው አካላት በአካል ቀርቦ ወይም በተወካዩ አማካኝነት በዳግም ምዝገባ ማረጋገጥ ይኖርበታል፣

ሐ. ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ከዚህ በፊት በህብረት ሥራ ማህበሩ ሥም ያስያዙት ዝግ ሂሳብ ካለ
በአዲሱ የግንባታ ወጪ ስሌት መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

መ. ነባርም ሆነ አዲስ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች በግንባር ቀርበው ለሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት
ሥራ ማህበር አባላት የቤት ፍላጐት ማሳወቂያ ቅጽ ዐዐ4 መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡

2.በአዲስ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ለመደራጀት የሚያበቁ መስፈርቶች

በህብረት ሥራ ማቋቋሚያ አዋጅ 134/ 98 የአደረጃጀት መስፈርት መሠረት

ሀ.በመኖሪያ አካባቢ የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባላትን በተመለከተ

1.በመኖሪያ አካባቢ የሚተዋወቁ፣ ተመሳሳይ የቤት ዓይነት፤ ፍላጐትንና አቅም ያላቸው እና በፈቃደኝነት በጋራ ለመስራት
የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባት አስፈላጊ ቅጻቅጾች መሙላትና አደራጁ አካል ዘንድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.በመኖሪያ አካባቢ የተሰባሰቡ የመኖያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባላት የስም ዝርዝራቸውን ይዘው ወደ ህብረት ሥራ
ማህበራት ማስፋፊያ አካል ከመቅረባቸው በፊት በሚኖሩበት ከተማ ውስጥ ነዋሪ መሆናቸውን ማረጋገጫ በቀበሌው
አስተዳደር አማካኝነት ከከተማው አስተዳደር ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፣

ለ.በስራ አካባቢ የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባለትን በተመለከተ

1. በሥራ ቦታቸው የሚተዋዋቁ፣ ተመሳሳይ የቤት ዓይነት ፍላጉትና አቅም ያላቸው እና በፈቃደኝነት በጋራ
ለመስራት የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፤
2. በመስሪያ ቤቶች የሚደረግ ምዝገባን በተመለከተ መስሪያ ቤቱ የማህበር መባላት ዝርዝር በማረጋገጥና ማህተም
በማድረግ ለአደራጁ አካል በሸኚ ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል፡፡

ሐ. በአሠሪው መስሪያ ቤት የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባላትን በተመለከተ

1 . በአንድ መስሪያ ቤት ወይም ተቋም ውስጥ የሚሠሩ፣ ተመሳሳይ የቤት ዓይነት ፍላጐትና አቅም ያላቸው እና
በፈቃደኝነት በጋራ ለመስራት የተስማሙ መሆኑን ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፣
2.በአሰሪ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የአባላትን ዝርዝር፣ በእያንዳንዱ አባል ስም የተቆጠበና ከመስሪ የቤት የሚሸፈንለት የቤት
የግንባታ ወጪ ግምት፣ የሚገነባውን የቤት ብዛት፣ የዲዛይን ዓይነትና ጠቅላላ ዋጋ የያዘ ሠነድ ለአደራጁ አካል ማቅረብ
ይሮባቸዋል፣

ክፍል አራት

የቦታ ስፋት፣ የቤቶች ዓይነት ፣ የግንባታ ዋጋ እና የአባላት ብዛት

9. የቦታ ስፋት

በማህበራት ልማት የትግበራ ማዕቀፍ በተቀመጠው አግባብ፣

1. ከ1ዐዐ,ዐዐዐ የህዝብ ብዛት በላይ በሚኖርባቸው ከተሞች እስከ 15ዐ ካ.ሜ


2. ከ5ዐ,ዐዐዐ-99,999 የህዝብ ብዛት ባላቸው ከተሞች እስከ 2ዐዐ ካ.ሜ
3. ከ10,000-49,999 የህዝብ ብዛት ባላቸው ከተሞች እስከ 25ዐ ካ.ሜ
4. ከ2,000-9,999የህዝብ ብዛት ባላቸው ከተሞች እስከ 3ዐዐ ካ.ሜ ይሆናል፡፡
5. ከላይ በአንቀጽ 9 ተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ ለተከፈቱና ከዋና መንግድ ርቀው
በሚገኙ የወረዳ መቀመጫ በሆኑ የመሪ ማዘጋጃና ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ከተሞች እስከ 35ዐ ካ.ሜ የቦታ መጠን
በቤት ሥራ ማህበር ተደራጂተው ለሚመጡ ማስተናገድ ይቻላል፡፡

1ዐ.የቤቶች ዓይነት

1. የሚገነባው የቤት አይነት እንደ የከተማው ደረጃ ሊለያይ የሚችል ሆኖ በሜተሮፖሊተን ከተሞች ጂ+1 እና
በላይ ፣ በመካከለኛ እና በዞን ዋና ከተሞች ጂ +0 እና በላይ በሌሎች አነስተኛ ከተሞች ቪላ(Duplex) ወይም
ታውን ሃውስ መሆን ይኖርበታል፡፡
2. የቤቶች አማካይ ስፋት ባለ አንድ መኝታ ክፍል ቤት 45 ካ.ሜ ፣ ባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤት 65 ካ.ሜ ፣ ባለ
ሦስት መኝታ ክፍል ቤት 8ዐ ካ.ሜ በአማካይ ይሆናል፡፡
3. የዲዛይኑን አይነት በራሳቸው መርጠው ለሚያሠሩና አቅምና ፍላጐት ላላቸው በአንድ ቤት እስከ 1ዐዐ ካ.ሜ
ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡ ማህበራት ከዚህ ካሬ ሜትር በላይ የመገንባትአቅም ካላቸው የሚያስይዙት የገንዘብ
መጠን ተሰልቶ የሚጨመር ይሆናል፡፡
4. በአነስተኛ ከተሞች በራስ አገዝ የሚገነቡ ቤቶች አንድ ክፍል(core) ከተሠራ በኋላ እያደገ የሚሄድ ይሆናል፡፡

11.የቤቶች ግንባታ ዋጋ

የሚገነባው ቤት ቪላ(Duplex) ሆኖ ስፋቱ በአንቀጽ 1ዐ(2) የተገለፀው ከሆነ፣

1. ለባለ አንድ መኝታ ክፍል ቤት ብር 9ዐ,ዐዐዐ ፣ ለባለሁለት መኝታ ክፍል ቤት ብር 13ዐ,ዐዐዐ አና ለባለሦስት
መኝታ ክፍል ቤት ብር 16ዐ, ዐዐዐ ይሆናል፡፡
2. በራስ አገዝ የመኖያ/ቤ/ህ/ሥ/ማህበር የሚገነቡ ቤቶች የግንባታ ዋጋ በጋራ የሚሠራው(c0re) 2ዐ ካሬ ሜትር ክፍል
ታሳቢ በድረግ ብር 32,ዐዐዐ ይሆናል፡፡
3. ከላይ በአንቀጽ 11.1 እና 2 የተጠቀሰው የመነሻ ዋጋ ሲሆን እንደ አካባቢው ሁኔታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ
መደረግ አለበት፡፡
4. የዲዛይኑን አይነት በራሳቸው መርጠው ለሚያሠሩ የቤቱ ግንባታ ዋጋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 11.1
የተጠቀሰው ሊሆን አይችልም ፣ ሆኖም ማህበሩ የሚያቀርበውን ዲዛይን መሠረት በማድረግ የሚመለከተው
አካል በሚገምተው የግንባታ ዋጋ ይሆናል፣
5. ግንባታው የሚከናወነው ለልማት ተነሽዎች ቦታ ላይ ከዋለ ከቤቱ ግንባታ ዋጋ በተጨማሪ ለማስነሻ የካሳ ክፍያ
በህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት የሚሸፈን ይሆናል፣
6. የቤቶች ግንባታ ዋጋ የማጠናቀቂያ ሥራንና ወለድን አያካትትም፣ ዋጋውም በወቅቱ እንደሚኖረው የገበያ ዋጋ
ሊጨምር ወይም ሊቀንስ እንደሚችል ታሳቢ መደረግ ይኖርበታል፣

12.የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባላት ቁጥር

በ2ዐዐ4 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይፋ በተደረገው የከተሞች የህዝብ ብዛት መረጃ መሠረት፣

1. የህዝብ ብዛታቸው ከ100,000 በላይ በሆኑ ከተሞች አንድ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ዝቅተኛው ከ14
ያላነሱ ከፍተኛው 24 ያልበለጡ አባላት ይኖሩታል፣
2. የህዝብ ብዛታቸው ከ1ዐዐ ሺህ በታች በሆኑ ከተሞች አንድ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ከ1ዐ ያላነሱ
ከ24 ያልበለጡ አባላት ይኖሩታል፣
3. በዚህ አንቀጽ ከ1-2 የተጠቀሱት ቤኖሩም አደራጂ መስሪያ ቤቱ በጥናት በተረጋገጠ አዋጭ የሆነውን የመነሻ ቁጥር
በአደረጃጀት መመሪያው ሊወስን ይችላል፣
4. ከ2፣
5. 2,ዐዐዐ ህዝብ በታች ባላቸው ከተሞች በማህበር መደራጀት አይጠበቅም፣
6. ሁሉም የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት የአባላት ብዛት ሙሉ ቁጥር መሆን አ ለበት፣
ክፍል አምስት
13.የአደረጃጀት ሂደት

1. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችና የቤት አይነት ምርጫ ያከናወነ አዲስም ሆነ ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር
ሥራ ማህበር አባል አግባብ ባለው አደራጅ አካል ቀርቦ በአለው የህብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀት መመሪያ
መሰረትበመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ይደራጃል ፣ ነባር አባልና ህብረት ሥራ ማህበርም በዳግም ምዝገባና አደረጃጀት
መረጋገጥ አለበት፣

2. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራቱ ለመዝገባ ሲቀርቡ ከቤት ፍላጐት ምዝገባ ቅጻቅጾች በተጨማሪ በአዋዱ አንቀጽ 11
የተዘረዘሩትን በሙሉና ( የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመስራች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ወዘተ… ) የሥራ አመራር አመራረጥና
በተለያዩ ቦታዎች ማህበሩን ወክለው ጉዳዩ የሚያስፈጽሙ አካላትን ውክልና ጭምር የያዘ ሠነድ ለአደረጁ አካል ማቅረብ
ይኖርባቸው፣

3.አደራጁ አካል የመኖሪየ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ ለቅድመ ምዝገባ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን አሟልቶ ሲገኝ
ለሚመለከተው የመንግስት ባንክ በህብረት ሥራ ማህበሩ ስም ዝግ ሂሳብ እንደከፈት የትብብር ደብዳቤ ይፅፋል፡፡

4.በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ሲደራጁ የቤቱን የግንባታ ወጪ 2ዐ በመቶ እያንዳንዱ የህብረት ሥራ ማህበሩ
አባል መንግስት በሚያውቀውና በህብረት ሥራ ማህበሩ ሥም በተከፈተ ዝግ ሂሳብ ገቢ ያደርጋል፣ ገቢ የተደረገበትን
ማስረጃም በማህበሩ አማካኝነት ለአደረጁ አካል ያቀርባል፡፡

5. አደራጁ አካል የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩን አስፈላጊ የምዝገባና የባንክ ሂሳብ ሠነዶችን በማያያዝ
ለሚመለከተው አካል የመሬት አስተዳደር ተቋም የመሬት ዝግጅት/ ቲፖሎጂ መረጣ እንዲያደርጉ የትብብር ደብዳቤ
ይጽፋል፡፡

6.የተደራጀው የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር የቤቱን መስሪያ መሬት ከነማረጋገጫ ኘላኑና ሠነዱ ሲያቀርብና ለቤቱ
ግንባታ ወጪ 3ዐ በመቶውን ገቢ ሲያደርግ የህብረት ሥራ ማህበር ምዝገባ እውቅና ይሰጠዋል፡

14.የነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን ስለማጠናከር

1. ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር በዚህ መመሪያ አንቀጽ 7 እና 8 የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የቤት አይነት
ምርጫ እስካሟላ ድረስ ነባርነቱን በማረጋገጥ ማስረጃ ይሰጠዋል፡፡

2. አንድ ነባር የመኖሪያ ህብረት ሠራ ማህበር የነበረበትን የአደረጃጀት ችግር ማስተካከልና በስሩ ያሉ አባላት የቤት ግንባታ
ወጪያቸውን መቶ በመቶ መሸፈን እንዲችሉ በማድረግ የፋይናንስ ችግሩን መፍታት ይጠበቅበታል፡፡

3.የሚደራጁት የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባላት እንደየ ከተሞቹ ደረጃ ቁጥራቸው በአንቀጽ 12 የተቀጠሰው
እንደተጠበቀ ሆኖ ከዚህ በፊት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት ቁጥራቸው ከተገለፀው
ካነሰ ከሌሎች የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት ቁጥር ጋር ለመዋሃድ ይችላሉ፤ የተዋሃዱት የህብረት ስራ
ማሃበሩ አባላት ቁጥር በአንቀጽ 12 ከተጠቀሰው ማነስ የለበትም፣ ከዚህ ካነሰ እና ከነባር ማህበራት መተካት የማይቻል
ሆኖ ሲገኝ በአደራጅ መስሪያ ቤቱ አማካኝነት አዲስ አባል መተካት ይቻላል፡፡

4. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራቱ ቤቶች ግንባታ የሚከናወነው ከከተማው አስተዳደር ጋር በገቡት ውለታ መሰረት
በቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ ወይም ራሳቸው በመረጡት የኮንስትራክሽን ተቋራጭ ይሆናል፣

15 አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት የምዝገባ አፈፃፀም ስርዓት

1. አዲስ የሚቋቋሙ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ለምዝገባ ሲቀርቡ በሥራ አካባቢ ወይም በመኖሪያ አካባቢ
የሚተዋወቁና በፈቃደኝነት በጋራ ለመስራት የተሰባሰቡ መሆኑን የሚያሳይ ግዴታ ይፈርማሉ፣
2. አዲስ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አባላት የቤት ግንባታ ወጪያቸውን በራሳቸው አቅም መቶ በመቶ
ለመሸፈን ሲስማሙ 2ዐ በመቶ ከከፈሉ ይመዘገባሉ፣ሆኖም የህብረት ሥራ ማህበር አባላቱ በሚደራጁበት ወቅት
የሚመርጡትን ቤት ዋጋ 2ዐ በመቶውን ከከፈሉ በኋለ 3ዐ በመቶ የመሬት ዝግጅቱ ተጠናቆ ከግንባታ ፈቃድ በፊት
አጠናቀው በማህበሩ ሂሳቡ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸው፡፡

3. የህዝብ ብዛታቸው ከ2ዐዐዐ-1ዐዐዐዐ በሆኑ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች በራስ አገዝ የ መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር
የሚደራጁ በመሆኑ በጐልበት የሚያደርጐት ተሳትፎ በገንዘብ ታስቦ ከቤቱ ዋጋ ተቀናሽ ይሆናል፡፡

4. ከላይ አንቀጽ 15 ንዑስ 3 የተመለከተው ቢኖርም 1ዐዐዐዐ ህዝብ በላይ በሚኖርባቸው ከተሞች በራስ አገዝ የመኖሪያ ቤት
ህብረት ሥራ ማህበር እንደራጃለን የሚሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ካሉ የከተማው ደረጃ ታሳቢ ባደረገ የግንባታ ስታንዳርድ
መሠረት ሊስተናገዱ ይችላሉ፡፡የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ቤቶች ግንባታ የሚከናወነው ከከተማው አስተዳደር
ጋር በገቡት ውለታ መሠረት በቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ ወይም ራሳቸው በመረጡት

የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጭ ይሆናል፡፡ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ቤታቸውን የሚስገነቡት በመረጡት


ኮንትራክተር ከሆነ ክፍያቸውን በባንክ በዝግ ሂሣብ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ክፍል ስድስት

ተግባርና ኃላፊነቶች

16. የአባላት ተግባርና ኃላፊነት

1. ማንኛውም የተመዝጋቢ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባል በህብረት ሥራ ማህበሩ አማካኝነት ለመደራጀትና
ምዝገባ ለማካሄድ በቅደሚያ በዚህ መመሪያ የቀመጠውን መስፍርት በማሟላት በግንባር በመቅረብ ወይም በህጋዊ ተወካዩ
አማካኝነት ትክክለኛ መረጃ በመስጠት መመዝገብ ይኖርበታል፣

2. ከዚህ መመሪያ ውጭ ከምዝገባም ሆነ ከአደረጃጀትና ከቤት ማስተላለፍ ጋር በተያያዘ በአባላት ለማፈጽሙ ህገወጥ
ድርጊቶች በጋራም ሆነ በተናጠል ኃላፊነት ይወስዳሉ፣

3.ማንኛውም የተመዝጋቢ ህብረት ሥራ ማህበር አባል በአደረጃጀትና በአመዘጋገብ ሂደት የተከሰቱና ከዚህ መመሪያ ውጭ
እየተፈጽሙ ያሉ ማናቸውም ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለአደራጁ አካል የመጠቆም ኃላፊነት አለበት፣

4. ማንኛውም የህብረት ሥራ ማህበሩ አባል በመረጠው ቤት ዲዛይን አማካኝነት የቤቱን ወጪ በአንቀጽ 14(2) መሠረት
በህብረት ሥራ ማህበሩ ሂሳብ ገቢ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

5. የህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት የቤቶችን ግንባታ በቅርብ በበመከታተል በዕወቀት፣ በጉልበት ወዘተ… ይደግፋሉ ፣

6. የቤቶች ግንባታ ሲጠናቀቅ በቦታው በመገኘት በህብረት ሥራ ማህበሩ አማካኝነት ይረከባሉ፣


17. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ ተግባርና ኃላፊነት

1. ተመሳሳይ ፍላጐትና አቅም ያላቸውን ወይም በመኖሪያና በሥራ አካባቢ የሚተዋወቁ መሆናቸው በማረጋገጥ አባላትን
ይመዘግባል፣

2. የህብረት ሥራ ማህበሩን የመመስረቻ ቃለጉባኤ፣ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች አስፈላጊ ሠነዶችን አዘጋጅቶ ለምዝገባ
ያቀርባል፣

3. አባላትን በመወከል ከምዝገባ ጀምሮ ያሉትን የመሬት ፣ የዝግ ቁጠባ ሂሳብ፣ የግብዓትና የተለያዩ ውሎችን ይዋዋላል፤
በኃላፊነትም ያስፈጽማል፣

4. አባላቱ የሚፈለግባቸውን የቤት መስሪያ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከፍለው ሲያጠናቅቁ በህብረት ሥራ ማህበሩ ስም ገንዘቡን
ለሚገነባው አካል ያስተላልፋል ወይም ገቢ ያደርጋል ፣

5. የቤቶቹ ግንባታ በተቀመጠው ስታንዳርድና በውሉ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፣

6.የቤቶች ግንባታ መጠናቀቁን በማረጋገጥ መተዳደሪያ ደንቡን ተከትሎ አባላት እንዲረከቡ ያመቻቻል፣

18. የህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲና አካላቱ ተግባርና ላፊነት / የአደራጁና መዝጋቢው
አካል/ ተግባርና ኃላፊነት

1 . አደራጁ ተቋም ስለመኖሪያ ቤቶች ህብረት ሠራ ማህበራት አደረጃጀት ፣ ይዘትና አስፈላጊት እንዲሁም ስለአመዘጋገብ
ስርዓቱ በቂ መረጃ መስጠት አለበት፣

2.አደራጁ አካል የአባልነት ምዝገባ፣ የመስራች ቃለጉባኤ ፎርሞችና ሌሎች አስፈላጊ ቅፃቅጾችና ደጋፊ ሠነዳች ማዘጋጀትና
ስለአሞላሉ ለባለጉዳዩች ተፈላጊውን ማብራሪያና ድጋፍ መስጠት አለበት ፣

3.ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ለምዝገባ ብቁ እስከሆነና የምዝገባ መስፈርቱን አሟልቶ በአካል
እስከቀረበ ድረስ በመመዝገብና በማረጋገጥ ማስረጃ መስጠት አለበት፣

4.በማህበሩ የተሞሉት ቅፆችና ሠነዶች በአግባቡ መደራጀትና መያዝ ይኖርበታል፣

5.የመኖሪያ ቤት ህብረት ሠራ ማህበራት ቅድመ ሁኔታውን አሟልተው ሲቀርቡ የተለያዩ የትብብርና ድጋፍ ደብዳቤዎች
ለሚመለከታቸው አካላት መጻፍ አለባቸው፣

6.በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አማካኝነት ተደራጅተው በልዩ ልዩ ምክንያት የህብረት ሥራ ማህበሩ ፈረሶ በዝግ
ሂሳብ የተያዘው ሂሳብ እንዲመለስ ሲጠየቅ አግባብ ባለው መመሪያ መሰረት መፍትሄ ይሰጣል፣

19.የአሠሪ መስሪያ ቤት ተግባርና ኃላፊነት

1.አሠሪ መስሪያ ቤቱ ቤት የሌላቸው የተቋሙ ሠራተኞች በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው ተጠቃሚ
ለመሆን ከፈለጉ እገዛ ያደርጋል፣

2.ለተቋሙ ሠራተኞች የቤቱን ዋጋ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን ከሆነ የተደራጀውን ማህበርና አባላት ዝርዝር
በማዘጋጀት በቅርቡ ባለው አደራጅ ወይም መዝጋቢ አካል ቀርቦ ያስመዘግባል፣ ገንዘቡንም ግንባታውን ለሚከታተል
ኢንተርኘራይዝ በውለታ መሠረት ያስረክባል/ገቢ ያደርጋል፣

3. የቤቶች ግንባታ ሲጠናቀቅ ግንባታውን ካከናወነው አካል በመረከብ እንደአስፈላጊነቱ በተሸፈነው ወጪ ልክ በገንዘብ
አመላለስ ውል መሠረት ያስረክባል፣ በአሰሪ መ/ቤቱ የተሸፈነውን የቤቱን የግንባታ ወጪ/ ብድር አመላለሳቸውንም
ይከታተላል፣

4. በተለያዩ ምክንያት ከመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበሩ ለሚለቁ ሠራተኞች አስፈላጊውን የክፍያና ተያያዥ ሁኔታዎች
ግልጽ በማድረግ የአባልነት መስፈርቱን የሚያሟሉ አባላትን በመለየት እንዲተኩ ለህብረት ሥራ ማህበሩ እና ለአደራጁ
መ/ቤት ይጠይቃል፣

5. በወጭ አገር የሚኖሩ ኢትዩጵያውያንና ትውልድ ኢትዩጵያውያንን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በህብረት ሥራ
ማህበር ሊመዘገቡ የሚችሉትን ዝርዝር ኃላፊነት ወስዶ ሊያቀርብ ይችላል፣

2ዐ የከተማው አስተዳደር ኃላፊነት

1. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው የምዝገባ ሰርቲፊኬት ያገኙ ህብረት ሥራ ማህበራት በአደራጁ
አካል በሚቀርብ ጥያቄ አማካኝነት የመሬት ዝግጅት ያደርጋል፣ የግንባታ ፈቃድ ይሰጣል፣ የቤቱን መስሪያ መሬት
ከነማረጋገጫ ኘላኑና ሠነዱ ጋር በማዘጋጀት ለህብረት ሠራ ማህበሩ ይሰጣል፣ ስለመስጠቱም ለአደራጅ መ/ቤቱ
ያሳውቃል፣
2. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አባል ለመሆን ለሚጠይቁ ግለሰቦች የቤት ምዝገባ መረጃ ህጋዊነት
ከሚመለከተው የቤቶች ልማት ተቋም ጋር በመሆን ያጣራል፣
3. ከመሰረተ ልማት ተቋማት ጋር በመተባበር ለግንባታው የሚያስፈልግ መሠረተ ልማት ፣ የግንባታ ግብዓት
እንዲሟላ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣

21.የባንክ ኃላፊነት

1. በሚደረሰው የሶትዬሽ ስምምነት መሠረት በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅቶ በአደራጅ አካሉ አማካኝነት

ዝግ ሂሳብ እንዲከፈት ወይም እንዲለቀቅ ሲጠየቅ ይከፍታል ወይም ይለቃል፣

2. የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ግንባታውን ከሚያካሂደው አካል ጋር ባላቸው ውል መሠረት ገንዘቡ

እንዲንቀሳቀስ ማህበሩ ሲያዝዝ በህብረት ሥራ ማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት እንዲንቀሳቀስ ይፈቅዳል፡፡

ወይም ገንዘብ ያስተላልፋል፡፡


3.በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አማካኝነት ተደራጅተው በልዩ ልዩ ምክንያት የህብረት ሥራ ማህበሩ ፈርሶ በዝግ
ሂሳብ የተያዘው ሂሳብ እንዲመለስ ሲጠየቅ ወይም የአባላት መተካካት ሲኖር በአደራጁ አካልና በህብረት ሥራ ማህበሩ
አማካኝነት በሚቀርብ ጥያቄ ባለው የባንኩ አሠራር መመሪያ መሠረት በዝግ የተያዘውን ሂሳብ እንዲመለስ ያደርጋል፡፡

22.የቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ ወይም የግል የመኖሪያ ቤት የግንባታ ተቋማት ኃላፊነት

1. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተውና ዕውቅና ተሰጥቷቸው ከሚመለከተው አደራጅ አካል ከሚቀርቡ
ህብረት ሥራ ማህበራት ጋር ስለ ቤቱ ግንባታ ፣ ፋይናንስና ርክክብ ጉዳይ ውል ይዋዋላል ፣

2. ለግንባታ የሚያስፈልገውን በዝግ የተቀመጠ የህብረት ሥራ ማህበሩን ገንዘብ ግንባታውን ለመጀመር የሚያስችለውን
ፋይናንስ እና ቀሪ ገንዘብም በሚቀርብ የግንባታ አፈፃፀም ደረጃ እየታየ እንዲለቀቅለት ይጠይቃል፣

3. ህብረት ሥራ ማህበራቱ በተረከቡት መሬት ላይ በአግባቡና በዲዛይኑ መሠረት የስራ ተቋራጮችን ፣ አማካሪዎችንና
አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርኘራይዞችን በማሳተፍ የቤቶችን ግንባታ በተቀመጠው ስታንዳርድና ውል መሠረት ያከናውናል፣

4. ግንባታው ሲጠናቀቅ በውሉ መሠረት ቤቶችን ያስረክባል፣

1. መኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራትን የቤት ግንባታ ለመደገፍ የሚያስችሉ ሞዴል መመሪያዎች፣ ማንዋሎችና
ስታንዳርዳይዝድ ዲዛይኖች ያዘጋጃል፣የአሠራር ስርዓት ይዘረጋል፣ አፈፃፀማቸውንም ይገመግማል፣

2. በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት ቤቶች ግንባታ የሚሳተፉ አካላት እንዲደራጁ ያደርጎል፣ የአቅም ግንባታና
የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፣

3. ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተቀናጅተውና ትስስር ፈጥረው ለመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አስፈላጊውን የመሠረተ
ልማት፣ የግብዓት አቅርቦት ወዘተ… ድጋፍ እንዲያደርጉ ያመቻቻል፣

23.የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ሃላፊነት

1. መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራትን የቤት ግንባታ ለመደገፍ የሚያስችሉ ሞዴል መመሪያዎች፤ ማንዋሎችና
ሰታንዳርዳይዝ ዲዛይኖች ያዘጋጃል፤ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈፃፀማቸውንም ይገመግማል፤

2. በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ቤቶች ግንባታ የሚሳተፉ አካላት እንዲደራጁ ያደርጋል፤ የአቅም ግንባታና
የክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤

3. ሌሎች የባለድረሻ አካላት ተቀናጅተውና ትስስር ፈጥረው ለመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት አስፈላጊውን የመሰረተ
ልማት፤ የግብኣት አቅርቦት ወዘተ…ድጋፍ እንዲያደርጉ ያመቻቻል፤
ክፍል ሰባት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

24. የቅድሚያ ተጠቃሚነት አወሳሰን

1. ነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት በዚህ መመሪያ መሠረት መስፈርቱን አሟልተው ከተደራጁ በቦታ ምደባና
በግንባታ ሂደት ድጋፍ ቅደሚያ የሚሠጣቸው ይሆናል፡፡

2. ነባር የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበር የቦታ አቅርቦት ቅድሚያ ሊያገኙ የሚችሉት ከላይ በአንቀጽ 24 ተራ ቁጥር 1
የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት የተቋቋሙበት አመተ ምህረት ቅደም ተከተልን
መሠረት ያደረገ ይሆናል፣

3. የነባር የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር የተቋቋሙበት አመተ ምህረት ተመሳሳይ አመት ከሆነና የተዘጋጀው የቦታ
መጠን ሁሉንም ማህበር በአንዴ ማስተናገድ የማይቻል ከሆነ ቅድሚያ ለማግኘት በተመሳሳይ አመተምህረት የተመሰረቱ
ማህበራት በእጣ እንዲለዩ ይደረጋል፣

25. ክልከላ

1. አንድ የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር አባል ካሉት የቤት ልማት ኘሮግራሞች ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ
መመዝገብ አይችልም ፣በየትኛውም ኘሮግራም ከአንድ ጊዜ በላይ ከተመዘገበ ከሁሉም ኘሮግራም አንዲሠረዝ ይደረጋል፡፡

2. ባለትዳሮች የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበርን ጨምሮ በትኛውም የቤት ልማት ኘሮግራም ላይ በባል ወይም
በሚስት ስም ከአንድ ጊዜ በላይ መመዝገብ ክልክል ነው፣

3. ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች የሆነ በራሱም ሆነ በሞግዚቱ አማካኝነት በመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር
ሊደራጅና ሊመዘገብ አይችልም፣

4.በራሱ ወይም በትዳር አጋሩ ስም የመኖሪያ ቤት ወይም የመኖሪያ ቤት መሣሪያ ቦታ ያለው ወይም ከዚህ ቀደም በቤት
ልማት ኘሮግራም ግንባታ ተጠቃሚ የሆነ ሠው በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር መደራጀትና በቤት ፈላጊዎች ምዝገባ
ላይ መመዝገብ አይችልም፣

26.ቅሬታ አቀራረብ

1. መዝጋቢው ወይም አደራጁ አካል በሚሰጣቸው የምዝገባና የማደራጀት ውሳኔዎች ቅሬታ ያደረበት ማንኛውም ተመዝጋቢ
እንዳልመዘገብ ተከልክያለሁ ወይም ከምዝገባ ያለአግባብ ተሠርዣለሁ ካለ ቅሬታውን በጽሁፍ በ5 ቀናት ውስጥ ለአደራጅ
መስሪያ ቤት ያቀርባል፣
2. ያቀረበው ቅሬታ ካልተፈታለት በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው መደበኛው የአስተዳደሩ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በ5 ቀናት ውስጥ
ማቅረብ ይችላል፡፡

27. ቅጣት

ማንኛውም ተመዝጋቢ በዚህ መመሪያ የተዘረዘሩትን አንቀፆች በመተላለፍ የተመዘገበ፣ ለመመዝገብ የሞከረ፣ ያሳሳተ፣
የምዝገባውን ሂደት ያወከ እንደሆነ አግባብ ባለው የፍትሐብሔር ወይም የወንጀል ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

28. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው ይህን መመሪያ ከማስፈጸም አኳያ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

29. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው መመሪያዎች


ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሠራር በዚህ መመሪያ በተሸፈኑ ገዳዩች ላይ ተፈፃሚነት
አይኖረውም፡፡

3ዐ. መመሪያውን የማሻሻል ስልጣን

ይህን መመሪያ ማሻሻል ሲያስፈልግ የአስተዳደር ምክር ቤቱ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

31. መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተፈርሞ ከወጣበት ከነሃሴ 2ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ባህር ዳር

ነሀሴ 20/2005 ዓ/ም

ፊርማ አለው

አያሌው ጎበዜ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር


አባሪዎች

ቅፅ004

አባሪ አንድ፣ በመኖሪያ ወይም በሥራ አካባቢ የሚደራጁ የመኖሪያ ቤት የህብረት ሥራ ማህበራት

ለማደራጀት የአባልነት ማመልከቻ ቅፅ


ፎቶ

1. የህብረት ሥራ ማህበሩ መጠሪያ ---------------------------------------------------------------------- የመኖሪያ ቤት


ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ
2. የአመልካች ሁኔታ፣
2.1 ስም---------------------------የአባት ሥም -------------------------የአያት ስም -------------------------
ፆታ --------------ዕድሜ---------------------ብሔር----------------------

2.2 የአመልካች እናት ስም ---------------------------------------የእናት አባት ሥም ------------------------------

የእናት አያት ስም --------------------------------------

2.3 የትዳር ሁኔታ፣

ያገባ/ች ያላገባ/ች በፍቺ የተለየ/ች በሞት የተለየ/ች

2.4 ያገባ/ች ከሆነ የትዳር ጓደኛ ስም ከነአያት ---------------------------------------------------------------------


2.5 የአመልካች መኖሪያ አድራሻ ፣-
 ክልል ------------------------------------ከተማ -------------------------------------
 ዞን/ክ/ከተማ ------------------------------ወረዳ -----------------------------------
 ቀበሌ --------------------------------------የቤት ቁጥር ----------------------------
 የቤት ስልክ ቁጥር -----------------------------የሞባይል ስልክ ቁጥር -----------------------
 የቀበሌ( የመ/ቤት )መታወቂየ ( የፓስፖርት )ቁጥር ---------------------------------
3. የሥራና የገቢ ሁኔታ
3.1 የሥራ ሁኔታ፣
የመንግሥት ተቀጣሪ መንግስታዊ ያልሆነ (የግል ተቀጣሪ ) በግል ሥራ
3.2 የሥራ አድራሻ
የመ/ቤቱ ስም -----------------------------------------የሚገኝበት ክልል ---------------------ዞን ---------------
ከተማ -----------------------------ወረዳ -------------------------------ስልክ ቁጥር ----------------------------
ፖ.ሣ.ቁ-------------------------------
3.3 የአመልካች የወር ገቢ መጠን በብር -----------------------------------------------------
4. የሚፈልጉት የቤት አይነትና የክፍል ብዛት
4.1 ቪላ ከሆነ፣
ባለ 1 መኝታ ባለ 2 መኝታ ባለ 3 መኝታ ሌላ ---------------
4.2 የጋራ ህንፃ (ፎቅ ) ከሆነ ፣
ባለ 1 መኝታ ባለ 2 መኝታ ባለ 3 መኝታ ሌላ --------------
4.3 በራሳቸው ዲዛይን ለሚገነቡ የሚፈልጉት የቦታ ስፋት ------------------ካ.ሜ
5. በህብረት ሥራ ማህበር የተደራጁበት ሁኔታ፣
በመኖሪያ አካባቢ በመስሪያ ቤት በሌላ ተመሳሳይ ፍላጐት
6. በመስሪያ ቤት የተቋቋመ ከሆነ የቤቱ ወጪ አሸፋፈን ሁኔታ፣
ሙሉ በሙሉ በተቋሙ የሚሸፈን በከፊል ሌላ ካለ -------------------
7. የሚኖርበት / ቤት ሁኔታ፣
የቀበሌ የኪራይ ቤቶች ደባል ጥገኛ ከግለሰብ ኪራይ ሌላ
8. እኔ ስሜ ከላይ የገለጸው አመልካች
8.1 ቀደም ሲል በመንግስት በተዘረጉት በማናቸውም የቤት ልማት ኘሮግራሞች ያለተመዘገብኩ መሆኑን፣
8.2 በ------------------------ ከተማ ውስጥ በስሜ ወይም በትዳር ጓደኛዬ ስም የተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ወይም
የቤት መስሪያ ቦታ የሌለኝ እና ከዚህ በፊትም የነበረኝን በሽያጭ ወይም በስጦታ ለሶስተኛ ወገን
ያላስተላለፍኩ እና በቤት ልማት ፕሮግራም ከዚህ በፊት ተጠቃሚ ያልሆንኩኝ መሆኑን፣
8.3 ለምዝገባ ብቁ የሚያደርገኝ የቤቱን ግንባታ ዋጋ 20 በመቶ በምዘግባ ወቅትና ቀሪውን 3ዐ በመቶ ለማህበሩ
ፈቃድ በሚሰጥበት ጊዜ በዝግ ሂሳብ የማስቀመጥ መሆኑን፣
8.4 በከተማው ውስጥ ለሁለት ዓመታት የኖርኩና/ የሠራሁና እየኖርኩ /እየሠራሁ ያለሁ መሆኔን፣
8.5 በምረከበው ቤት በጋራ ህንፃ ህግ መሠረት ለመተዳደር ፈቃደኛ መሆኔን፣
8.6 እኔም ሆነ የትዳር ጓደኛዬ የምንኖረው በመንግስት ቤት ከሆነ ቤቱን ለሚያስተዳድረው አካል ቤቱን
በተረከብኩ በ3ዐ ቀን ውስጥ ለማስረከብ ፈቃደኛ መሆኔን፣
8.7 በዚህ ማመልከቻ ቅጽ የሞላሁትና የሰጠሁት ማረጋገጫ ሀሰተኛ ሆኖ ቢገኝ የምዝገባው ውል የሚፈርስ
መሆኑንና ቤቱን ለሚመለከተው ለማስረከብ ወይም በከፍተኛ የሊዝ ዋጋ ታስቦ በቅጣቱ ለመክፈል
የምስማማ መሆኑን፣
8.8 ወደፊት የሚጠየቁ መረጃዎችን ለምሳሌ የጣት አሻራና ሌሎች መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኔን
እንደሁም
8.9 በተ.ቁ 1 ላይ በተገለፀው የመኖሪያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበር ስም ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር
በፈቃደኝነት ለመደራጀትና የመኖሪያ ቤት ለመስራት የሚያስፈልገውን ቅድመ ሁኔታና መሰፈርቶች በአዋጁና
በመመሪያው መሠረት ያሟላሁ በመሆኑ ህብረት ሥራ ማህበሩ በአባልነት እነዲቀበለኝና ከላይ የመላሁት
መረጃ ሀሰት ሆኖ ቢገኝ በህጉ መሠረት ተጠያቂ እንደምሆን በመስማማት ይህን ቅጽ የሞላሁ መሆኑን
በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

የህ/ስ/ማ አባሉ ሙሉ ሥም----------------------------------

ፊርማ --------------------------

ቀን ---------------------------

ማሳሰቢያ ፣ - ይህ ቅጽ በእያንዳንዱ የህ/ስ/ማህበሩ አባል ተሞልቶ የሚቀርብ ነው፡፡

You might also like