Professional Documents
Culture Documents
ም የሳ/ወ/ዓ/ማዛጋጃ /ጽ/ቤት
መግቢያ
የክልሉ መንግስት የከተማ መሬትን በህግ ለማስተዳደር ይረደው ዘንድ በደንብ ቁጥር 123/2007 እና መማሪያ
ቁጥር 07/08 አውጥቶ በስራ ላይ ያዋለ ቢሆንም ነገር ግን የመሬት ልማት ማኔጅመንት ተግባራችን በርካታ
የመልካም አስተዳደር ችግር መፍለቂያ ሆኖ በከተማችን ላይ ለበርካታ የማ/ሰብ ጥያቄዎች ዋናኛ ምንጭ ሆኖ
ይገኛል
በዚህም መሰረት በመሰረተ ልማት ፡በማዘጋጃ ቤተዊ አ/ት አሰጣጥና የመሬት ጋር የተያያዙ ያሉ የመልካም
አስተዳደር ችግሮችን ለማፍታት ግልጽ እንድሁም ሊተገበር የሚችል የመልካም አስተዳደር እቅድን አቅዶ ወደ ስራ
መግበት የግድ ስለሆነ ይህ የመልካም አስተዳደር እቅድ ተቅዶዋል፡፡
የእቅዱ ዋና ዋና አላማ
የእቅዱ ዋናዋና ግብ
1. ከዚህ በፊት መሬታቸው ለልማት የተወሰዳባቸው የከተማ ነዋሪዎች የካሳ ጥያቄ መመለስ ፣
2. በመሬት ጉዳይ በማዘጋጃ ቤት ፣በከተማ ልማት እንዲሁም በወረዳውና ከዚያ በላይ ባሉ መዋቅሮች
የሚንገላቱትን አቤቱታ አቅራቢዎች መቀነስ፣
3. ሁሉም የወረዳውን ነዋሪ በአስተዳደሩ እምነት እንዲኖረው ሁሉም ፈጻሚ ከሌብነት ውጭ
በፍጹም ጫዋነት እቅዱን ማስፋጸም በመመሪያ ና ደንብ መተግበር
- የከፋሉት የአፋር ግብር ገንዘብ ተለቅም ፣ካርኒው ታጥፎ ገንዘብ ለግለሰቦቹ መመለስ ይገበዋል
- የእነዝህን ልጆች ወለጆች ማወያየት ይጣይቃል
- ተግባሩ በወረዳው አስተዳደር ፣ከተማ ልማት ጽ/ቤት እና ገቢ ጽ/ቤት በጋራ ይፈፀማል
ተግባሩ በዚህ ወር እስከ ጳጉሜ 1 ተፋጽሞ ይጠናቀቃል፡፡
1.2 የመሬት ምትክ አሰጣጡ ሲተገበር መሬት ያልተሰጣቸው የአ/አደሩ ልጆች (መስፈርቱን
የሚያሟሉት )200 ካሬ እንዲያገኙ ይደረጋል ተግባሩ ከተራ ቁጥር 1 ጋር በተመሳሳይ ይፋጸማል
1.3 አ/አደሮቹ በመመሪያው መሰረት በአባወራ 500 ካሬ ሜትር እንዲሁም 18 ዓመት የሞላቸው ና
ከዚያ በላይ ለሆኑት አብሮ ተጣቃሚ ለሆኑት ምንም ኣይነት የከተማ ቦታ /ቤት በከተማው ውስጥ
በስማቸው ወይም በትደር አጋራቸው ስም የሌላቸው እንዲሁም 18 ዓመት ባልሞላቸው ልጆቻቸው
ስም እንዲሁም ቤት/ቦታ በከተማው ውስጥ የሌላቸው የባለ ይዞታው ልጆች 200 ካ ሜ እንዲረከቡ
ማድረግ ይህም ስራ እንቀለጠፍ ዘንድ ከከተማ ልማት ጽ/ቤት ጋር በጋራ መሆን እስከ መስከረም
10/2011 ዓ/ም ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
1.4 በተራ ቁጥር 1.3 ላይ የተመዘገበው በተገቢው ከተከናወነ በትርፍ መሬታቸው ላይ የብር
ካሳ በኮሚቴ መሰረት ለሁሉም አ/አደሮች ፤ከዛም የተሰራውን የገንዘብ ካሳ ለአ/አደሩ
በማስፋረም ባባንክ አካውንት እንዲገባለት ማድረግ
- የሁሉም አ/አደር የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወይም የሌላ ያማንኛውም ባንክ ቡክ ማመቻቸት
ማስከፈት በወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት በጣም ባጭር ጊዜ
- የተቋቋመው ካሳ ገመች ኮሚቴ በ1 ሳምንት የሁሉንም መሬት የሄደባቸዉን የካሳ ግመታ ሰርቶ
ለመዘጋጃ መኔጅማንት ማቅረብ
- የተሰራውን የካሳ ግመታ በአስተባባሪው አስገምግሞ ለልምት ተነሺዎች ማስረከብ እስከ መስከረም
10 /2011 ዓ/ም ድረስ
1.5 ሁሉንም መሬት ከ3ኛው ወገን ንጹህ በማድረግ እስከ መስከረም 30 /2011 ዓ/ም
በሲ/ሰርቨንቱ፣በመምህራን ፣በነዋሪዎች ለተደረጁ ማህባራቶች የቤት መስሪያ ቦታ ማስረከብ ፣
- ይህ በሚፋጸምበት ጊዜ ከ400 በለይ አበወራ የከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቦታ ችግር በመቅረፍ የአስተዳደሩን ሞጋች ጥያቄ ምላሽ ማስጠት
- ከከተማ ልማት እና ከወረዳው አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ይፈፀማል የሪፖርት ግንኙነት በየቀኑ
ይሆናል፡፡
የአቤቱታዎቹ አይነቶች
ሀ. ከውልባረግ ሀላባ ዋናው አስፓልት ሲሰራ ቤት ፋረሰብኝ ካሳ አልተሰጠኝም ፤የመሬት ምትክም
አልተሰጠኝም
ለ. ለተለያዩ ልማት የእርሻ መሬቴ ስነሳብኝ ፤የተሰጠኝ የመሬት መጠን አነስተኛ ነው፤በቀሪውም መሬቴ
የገንዘብ ካሳ አልተሰለልኝም
ሐ. ለልማት ተብሎ መሬቴ ከተነሳብኝ ብኋላ የትክ መሬት ሲሰጠኝ ፤በሙሉ ሳይሰጠኝ ቀርቶ
ይጨመርልሀል ተብያለሁ በማለት የሚነሱ ናቸው፡፡
የአቤቱታዎቹ አፋታት ዘዴ
- በቅድሚያ ሁሉንም አቤቱታ አቅራቢዎች መመዝገብ እና መያዝ እንዲሁም በተውጣጣ ባለሙያ (
ከከተማ ልማት ) ጋር በጋራ በመሆን የአቤቱታዎቹን ይዘት መለየት
- ቤት ፋርሶባቸው የቤት ማንሺያ ካሳ ያልተሰጠቸውን
- የትክ ስርዓቱ ሲፋጸም ከመመሪያ ውጭ የተፋጸማባቸውን መለየት (ልጆቻቸው መሬት
ማግኛት ሲገባቸው ያልተሰጠቸው (ከ2007ዓ/ም ወዲህ ያለውን ) መለየት
- ምትክ በምዳባ ከተሰጠቸው ብኋላ የተወሰዳበቸው የመሬት መጣን
- በገንዘብ ምትክ ስም መሬት የተሰጣቸውን ባለይዞታዎች መለየት
ተግባሩን እስከ መስከረም 10/2011 ዓ/ም መፈጸም (ታክስ ፎርሱ የደረሰበትን ግኝት
መጠቀም)
- እነዚህን ተግባራቶች ከተከናወኑ በኋላ በወረዳው አስተዳደር ከአቤቱታ አቅራቢዎች ጋር ስለሁኔታው
መወያየት እና ድምዳሜ ላይ መድረስ መሞከር (አላግባብ አቤቱታ የአቀረቡ ግለሰቦች ጥያቄያቸዉን
እነዲያነሱ ማድረግ)
- ከውይይቱ በኋላ ለይተን ንጹህ ካደረግነው መሬት ላይ ከፍታኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ምላሽ
ሰጥቶ የቅሬታ አቅራቢዎችን እምባ ማበስ እስከ መስከረም 30/2011 ዓ/ም ድረስ
- ለዚህ ተግባር ይረዳ ዘንድ አቤቱታ አቅራቢዎች በሙሉ እንዲመዘገቡ ተደርጓል፡፡
የመንገድ ልማት
ከዚህ በፊት በከተማው ውስጥ ቦሮ እና ሬዳሽ ደፍቶ መንገዶች ለማህበረሰቡ ምቹ ከማድረግ አንጻር
የነበረው አፋጻጸም ዝቅታኛ እንደነበረ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡
በ2011 በጀት ዓመት የወረዳው አስተዳደር በሰጠው ልዩ ትኩረት የተጀመረው የመንገድ ልማት ቀላል አይደለም
- ከቅድመ ማቴሪያል አቅርቦት በፊት ያሉ የህግ አሰራሮች ግልጸኝነት ችግር (የጨረታ ሂደቱን ግልጽነቱን
አለማረጋገጥ)
- ወደ ተግባር ሲገባ የሬድ አሽ/ቦሮ መጠን ማነስ
- የባለሙያ ቁርጣኝነት ችግር
- የተዳፋው ቦሮ /ሬዳሽ በጊዜው ያለመበተን
- የበጀት ውስንነት
የሚወሰዱ መፍትሄዎች
ከቅድመ ማቴሪያል በፊት የሚከናወኑ የጫረታ ፣የውል ተግባራቶችን ሁሉም አስፋጻሚ አካለት ባለበት
ማስኬድ
የሬድ አሽ/ቦሮ መጠኑን በየጊዜው በጥብቅ በባለሙያ ማከታተል፤ስራውን በህዝብ ወገንተኝነት
መፈጸም
የበጀት ውስንነቱን ለመፍታት የከተማውን ማህበረ ሰብ አነቃንቆ ተጨማሪ አቅም መፍጠር
የመንገድ መብራት ልማት
በ2011 ዓ/ም ከሚከናወኑ ቁልፍ ተግባሮቻችን ውስጥ ከተማችንን ከጫለማ የጻዳች ከተማ ማድረግ
ነው በዚህም 5 ኪ.ሜ ሽፋን ያለው የመንገድ መብራት ልማት እንዲከናወን ማድረግ ነው፡፡