You are on page 1of 6

መግቢያ ………………………………………………………………………………….

 የነባራዊ ሁኔታ ትንተና …………………………………………………………2


 የእንስሳት ጤና አገልግሎት አደረጃጀትና አሰጣጥ ነባራዊ ሁኔታ……………...2-4
 በእንስሳት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮች………………… 4-6

1 በአገልግሎት ሰጪው………………………………………………………….
1.1 በተገልጋዩ…………………………………………………………………..

3.1.2 በግል ተቋማት……………………………………………………….

4.የመልካም አስተዳደር አለመኖርና ያልተገባ ጥቅም መገለጫዎቹ -----------------7-8

5.በእንስሳት ጤና አገልግሎት የታዩ ችግሮችን ለመፍታት የምንከተላቸው አሠራሮች 8-10

6. ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎች-------------------------------------------------------------11

7. ማጠቃለያ-------------------------------------------------------------------------------------11

መግቢያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትመራበት በግብርና መር ፖሊሲ ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገታችን አካል የሆነው
የእንስሳት ሀብት ልማታችን ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፡፡ በተደጋጋሚ እንደሚገለጸው ካለን የእንስሳት ሀብት
ልማት አኳያ እየተገኘ ያለው ጥቅም አነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው፡፡ ከእንስሳት ሀብታችን
ተገቢውን ጥቅም ለማግኘት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን የሚያስችሉ ተቋማትን
በማደራጀትና የሰው ሃይል በመመደብ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህም ተግባር በአርሶ አደሩ፣ ከፊል አርብቶ
አደርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ህብረተሰብእንዲሁም በከተሞች ውስጥ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ ላይ
ይገኛል፡፡

ከእንስሳት ሀብታችን አስፈላጊውን ጥቅም እንዳናገኝ ማነቆ ከሆኑ ምክንያቶች አንዱና ወሳኝ
የሆነው የእንስሳት ጤና ችግር ነው፡፡ በተለይም ምርትና ምርታማነትን ከመቀነስ፣የተዋልዶ ብቃትን
ከማውረድ ባለፈ ባልታሰበ ሁኔታ የእንስሳትን ዕልቂት የሚያስከትሉ ከእንስሳት ወደ ሰውና ከሰው ወደ
እንስሳት የሚተላለፉ ተዛማችና ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች በስፋት መኖር የዘርፉን ችግር እያባባሰው
ይገኛል፡፡

በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና በሽታዎችን በመለየት ተገቢውን


የመከላከልና የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት፣የእንስሳት ጤና አገልግሎቱ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን
በማድረግ ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ማሳደግና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ቀዳሚው ዓላማችን
መሆኑ የታወቀ ቢሆንም አሁን ያለንበት ደረጃ ሲታይ ከሚጠበቀው ግብ ለመድረስ ገና ብዙ መስራት
እንዳለብን አመላካች ሁኔታዎች እንዳሉ ነው፡፡

አዲስ አበባ የሀገራችን መዲና የሆነች ከ 3.8 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት ናት፡፡ ነዋሪው የወተት
የስጋ በአጠቃላይ የእንስሳት ውጤቶች፣ፍላጎት በየጊዜው እያደገ የሚገኝባት ከተማ ስለሆነች፤
የነዋሪውን ፍላጎት ለማሟላት በከተማ የዘመናዊና ባህላዊ የእርባታ እንቅስቃሴዎች በግለሰቦች፣
በማህበራት ተደራጅተው በመስራት ለአቅርቦቱ አስተዋፅኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

እነዚህን እንቅስቃሴዎች የሚያግዙ በመንግስት ደረጃ ከከተማ ግብርና እስከ ወረዳ መዋቅር በመዘርጋት
አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በግል በእንስሳት መድሐኒት ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ አስመጪና
አከፋፋዮች፣የጅምላና የችርቻሮ ነጋዴዎች፣ የእንስሳት መድሃኒት ቤትና የግል ክሊኒክ ከፍተው የሚሰሩ
ይገኙበታል፡፡ ከዚህም ሌላ በህገ ወጥ የእንስሳት መድኃኒት ንግድና ህክምና ስራ ላይ የተሰማሩም
ይገኙበታል፡፡ ከዚህ አንፃርየሚሰጠውን አገልግሎት በመንግስታዊም ሆነ በግል ዘርፍ ተደራሽ ለማድረግ
ሰፊ ክፍተት በመኖሩ የቅሬታ ምንጭ ከመሆን ባሻገር የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግር
ጎልቶ ስለሚታይ በመንግስትም ሆነ በግሉ ዘርፍ ያለውን ሁኔታ ስርዓት ለማስያዝ አሰራር ማዘጋጀት
ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

1. የነባራዊ ሁኔታ ትንተና

የመንግስት እንስሳት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ- በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ነው፡፡

 የእንስሳት ጤና የመስክ አገልግሎት፣


 የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ምርመራና አገልግሎት፣
 በተደራጁ ክሊኒኮች የሚሰጥ ልዩ ልዩ ህክምናና ክትባት አገልግሎት ወ.ዘ.ተ

የእንስሳት ጤና የመስክ አገልግሎት(እንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን) ፡- የምንለው በአብዛኛው በመስክ


በአርቢው ግቢና ማሳ ላይ በመገኘት የበሽታ ቅኝት እና ዳሰሳ ጥናት፤ የሙያ ምክር አገልግሎት
መስጠትና አርቢው የተሻሻሉ ዘመናዊ አሰራሮችን እንዲከተል በሱፐርቪዥንና አካላዊ ግምገማ የሚሠጥ
ድጋፍና ክትትል ሥራ ላይ ያተኩራል፡፡

የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት፡- በመስክ ለሚሰሩ ስራዎች ጠንካራ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም
ሲሆን የበሽታዎችን መንስኤና ስርጭት በአይነት በመለየት የመሳሰሉትን በሚገባ በማጥናት በሽታን
በምርመራ በማረጋገጥ መቆጣጠሪያ ስልቱን የማመላከት ሥራን አጣምሮ የያዘ ክፍል ነው፡፡

የክሊኒክ ምርመራና ህክምና አገልግሎትበሽታን መከላከልና መቆጣጠር መንግስት በገነባቸው


ክሊኒኮች የበሽታ ክሊኒካል ምርመራና የህክምና አገልግሎት መስጠት፣የሙያምክርና ቴክኒክ ድጋፍ
እንዲሁም ሥልጠና መስጠትንና ተጓዳኝ አገልግሎቶችን መስጠትን ያካትታል፡፡

1.3. በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 35 ያህል የግል እንስሳት ጤና ክሊኒኮች ያሉ ሲሆን በአብዛኛው የግል
ተቋማቱ በኩል የሚታዩ ችግሮች፣

 ከተፈቀደላቸው ስራ ውጭ መሥራት
 ባለሙያ ያልሆኑትን ቤት ለቤት ሄደው በስማቸው እንዲሰሩ ቢዝነስ ካርድ ሰጥቶ
ማሰማራት
 ተገቢ ያልሆን ከፍተኛ ዋጋ መጠየቅ /መንግስት ዋጋ ሊተምን አይችልም ነጻ ገበያ
መሆኑን መዘንጋት የለብንም ይህን ጉዳይ ከሰው ህክምናም የሚሰራውን ገና ህክምና
ሳያገኙ ለካርድ ብቻ ከ 150 ብር እንደሚከፍል መዘነጋት የለብንም
 በህገወጥ መንገድ የሚሰሩት ለማጋለጥ አለመፈለግና አለመተባበር ግልጽ ቢሆን
 የሰሩትን ሥራ ሪፖርት አለማድረግና አለመተባበር
 የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ማዋል መገለጫው
 የመንግስት ተቋማት ደጋፊ አገልግሎት ሰጪ መሆናቸውን አለመረዳትና የጥቅማቸው
ተቀናቃኝ አደርጎ በማሰብ በመንግስት ተቋማት ጥራት ያለው አገልግሎት እንደማይገኝ
አስመስሎ ማስወራትመገለጫው
4.1.3. በግል ተቋማትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶት በግል የሚሰጡ የእንስሳት ጤና
አገልግሎቶች በተመለከተ

 በግል አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን መለየት እንዲያርሙ ማድረግ፣


የቁጥጥር ሥራ ማጠናከር፣ በአቅራቢያ ለሚገኝ የመንግስት ተቋም ማሳወቅ
 በህገ ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ሥራውን የሚያውኩትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ
ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፣ ህጋዊውን ከህገወጡ ለመለየት የሚያስች መረጃ
አያያዝ ስርአት ሊኖር ይገባል
 በግል ፈቃድ አውጥተው ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በፕሮግራም በአገልግሎት አሰጣጥ
ዙሪያ ውይይት ማድረግ፣
 የተጠናከረ የሪፖርት ሥርዓት መዘርጋት፣ በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚሰሩ ህጋው
እንስሳት ጤና ክሊኒክ ያላቸው ሪፖርት ለክፍለ ከተማው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
በማያደርጉት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ
 በግልም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጡትን መረጃ
መያዝና ቢሮው እንዲያውቀው ማድረግ የቁጥጥር ሥራ ማጠናከር ያለ ቢሮው ወይም ክፍለ
ከተማው ጽ/ቤት እውቅና የሚንቀሳቀሱትን ማስቆም

በግል በእንስሳት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮች

• ባለሙያ ያልሆኑትን ሰዎች ቤት ለቤት ሄደው በስማቸው እንዲሰሩ ቢዝነስ ካርድ ሰጥቶ
ማሰማራት

• ይህን ስራ የሚሰሩት ብቃት ወስደው የሚሰሩት ብቻ ናቸው ወይስ በመንግስት መ/ቤት


ያሉትንም ጭምር ይመለከታል

• ተገቢ ያልሆነ ከፍተኛ ዋጋ መጠየቅ (ነጻ ገበያ መሆኑ መዘንጋት የለበትም መንግስት ዋጋ
መተመን አይችልምተጠቃሚው ፈቅዶ ላሰራበት እኛ ተከራካሪ መሆን አንችልም

• በህገ ወጥ መንገድ የሚሰሩትን ለማጋለጥ አለመፈለግ መገለጫዎች ይጠቀስ

• የሰሩትን ሥራ ሪፖርት አለማድረግ

• የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ማዋል በድጋሚ የተጻፈ

• የመንግስት ተቋማት ደጋፊ አገልግሎት ሰጪ መሆናቸውን አለመረዳት


በግል የእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትአሰራር ላይ የታዩ ችግሮችን ለመፍታት
የምንከተላቸው አሰራሮች በጥናት የተደገፈ ነው የማን የስራ ድርሻ ነው

• በአገልግሎት አሰጣጣቸው ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን(ከተስተዋሉት ውስጥ በዝርዝር


ማቅረብ) በመለየት እንዲያርሙ ማድረግ፣

• በህገ ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ሥራውን የሚያውኩትን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ


ማስቻል(ብቃት ማረጋገጫ ሳይኖራቸው)

• ህጋዊውን ከህገ ወጡ መለየት በግል ፈቃድ አውጥተው ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በፕሮግራም


በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት ማድረግ፣

• የተጠናከረ የሪፖርት ሥርዓት መዘርጋት፣ በክፍለ ከተማው ውስጥ የሚሰሩ ህጋዊ የእንስሳት
ጤና ክሊኒክ ያላቸው ሪፖርት ለክፍለ ከተማው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣ በማያደርጉት ላይ
እርምጃ መውሰድ ወሳጅ ማነው

• በግል በእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚሰጡትን መረጃ መያዝና ቢሮው እንዲያውቀው ማድረግ  

ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች

 ያልተገባ ጥቅም( ማለት ምንማለት እንደሆነ ይገለጽ) ለማግኘት የሚከሰቱ ተጨባጭ


ሁኔታዎች በህግ አግባብ እንዲታዩ ማድረግ የስራ ባለቤቱ ማነው
 ደንብና መመሪያ ተከትሎ እርምጃዎች እንዲወስድ ማድረግ፣የስራ ባለቤቱ ማነው

ማጠቃለያ

 ከመንግስት መዋቅር ውጪ የግል ተቋማት በስራው ዘርፍ የተሰማሩ መሆኑ የህብረተሰቡን


ተጠቃሚነት ከፍ ያደርገዋል፡፡
 የእንስሳት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ በከተማችን የቅሬታ ምንጭ(በዝርዝር ቢቀርብ) በመሆን ላይ
ስለሚገኝ ደረጃ በደረጃ ችግሮቹን ለማቃለል ግልፅነትን መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡
 በግል በእንስሳት ጤና አገልግሎት የተሰማሩ የሠሩትን ስራዎች ለክፍለ ከተማው እንስሳት
ጤናና ህገ ወጥ ዕርድ ሥጋ ዝውውር ቡድን ሪፖርት ማድረግ
 በከተማዋ ውስጥ የተሰሩ ሥራዎችን ለማወቅ የሚረዳ ሲሆን እነዚህን ተግባራት በተቀናጀ
ሁኔታ በመፈፀም የተደራጀ መረጃ በመያዝ ተጠያቂነት ለማጎልበት ሁላችንም የበኩላችንን
ልንወጣ ይገባል፡፡

You might also like