You are on page 1of 5

አባሪ 1

የሥጋት ትንተና መግለጫ/Risk Analysis Sheet/


ኦዲት ተደራጊው መ/ቤት:-የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
የኦዲት አካባቢ፡- በኢሚግሬሽ፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የወሳኝ ኩነቶች ምስገባ አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑን በተመለከተ
ኦዲቱ የሚሸፍነው ጊዜ፣ ከ 2010 እስከ 2013 በጀት ዓመት

ተ.ቁ. መመዘኛ መስፈርት አስተያየት የተሰጠው


የስጋት ደረጃ

1 መግቢያ /Backgraound/ የፌዴራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 76 ዐ/2 ዐዐ 4 እና በደንብ ቁጥር 278/2 ዐዐ 5

መሰረት በአገር አቀፍ ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት በመዘርጋት የኩነቶች ምዝገባ ወጥና

ቀጣይነት ባለው የአሰራር ስርዓት ላይ እንዲመሰረት ተግባሩን በበላይነት የማስተባበር፣ በአገር ደረጃ

ከኩነቶች ምዝገባ የተገኘውን መረጃ በማእከል አደራጅቶ በመያዝ ለአገሪቱ ፖሊሲ ቀረጻ፣

ስትራቴጂክ እቅድ አቅጣጫ፣ ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ለተለያዩ ፕሮግራሞች እቅድ ብቁና ጥራቱን

የጠበቀ መረጃ የማቅረብ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ሲሆን ከመጋቢት 9/20011 ዓ.ም ጀምሮ በደምብ

ቁጥር 449/2011 ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር በመዋሃድ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት
ኤጀንሲ በመባል ተሰይሟል፡፡

የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በአገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሆነ፣ ጥራትና ተአማኒነት ያለው እንዲሁም

ደህንነቱ የተረጋገጠ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣ የብሄራዊ መታወቂያና የኢሚግሬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም
ሲሆን ኤጀንሲዉ ተልእኮዉን ለመወጣት በ 2011 በጀት ዓመት የኤጀንሲዉን ማቋቋሚያ ደንብ እና ተቋማዊ

መዋቅር በማዘጋጀት እና ጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ በማድረግ፣ የሰዉ ሃይሉን በተዘጋጀዉ መዋቅር ላይ

ለመደልደል የሚያስችል ማስፈጸሚያ መመሪያ በማዘጋጀት እና በመመደብ፣ ተቋማዊ እቅዱን አዘጋጅቶ ወደ

ስራ ገብቷል፡፡

2 ጉልህነት /Materiality/ በገንዘብ፡- ከፍተኛ

 ኤጀንሲው የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት እና በዕቅድ የያዛቸውን ሥራዎች ለማስፈጸም


የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ምንጭ የሚያገኘው መንግስት በሚይዝለት በጀት ሲሆን
የኤጀንሲዉን የበጀት አቅም ከማጠናከር አንጻር ከተባባሪ አካላት ማለትም ከዩኒሴፍና ከአለም ባንክ
ድጋፍ ያገኛል፤ በዚህም ከተባባሪ አካላት ጋር ግንኙነት በማድረግ ተቋማዊ እቅዱን ለማሳካት
የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርጉ በማድረግ በጀቱን በበጀት አመቱ በእቅድ ለተያዙ ቁልፍ ተግባራት
ማስፈጸሚያ እንዲሆን የማድረግ ስራ ይሰራል
 በባህሪና በይዘት፡-

የወሳኝ ኩነቱ አሰራር የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር የሚፈልግ ነው፡፡ በመሆኑም
ተባባሪ አካላት ለክልሉና ለፌደራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲዎች የፋይናንስ ድጋፍ ማድረጋቸው
እንደመልካም አጋጣሚ የፈጠረ ቢሆንም በተደረገው የጋራ መግባባት ሁሉም ተባባሪ አካላት ድጋፍ
ለመስጠት ፈጥነው ወደ ስራ ያልገቡ በመሆኑ የምዝገባ ስርአቱን የሚያጓትት አጋጣሚ የተፈጠረ ሆኗል

3 የገንዘብ ፋይዳ /Value for ኤጀንሲው ከዓለም ዓቀፍ ትላልቅ ድርጅቶች በሚያገኛቸው እርዳታ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዎችን ከፍተኛ
Money/ የሚሰራ ቢሆንም አጠቃላይ አፈፃፀሙን ሊያሳይ የሚችል ጥናት ባለመሰራቱ ለተለያዩ የስራ
መስተጓጎል እንዲሁም ስራውን በቅንጅት ለመስራት አዳጋች ያደርገዋል፡፡

4 የህዝብ ተጠያቂነት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ተቋማዊ ለውጥ ግንባታ ከፍተኛ
/Public በማድረግ ረገድ በጠንካራ አቋም ለመምራትና የክራይ ሰብሳቢነት በመታገል ረገድ የህዝብ ተጠያቂነት
Accountability/ የሰፋ ነው

5 ሊገኝ የሚችል ዘለቄታዊ በኤጀንሲው የወሳኝ ኩነት ምዝገባና አፈፃፀም ላይ ኦዲቱ ቢከናወን ሊያስገኝ የሚችለው ጥቅም ከፍተኛ
ፋይዳ /Possible Impact/ ያለውን ጠንካራ ጎን በማበረታታትና የተገኙ ድክመቶችን በመለየት የማሻሻያ ሃሳብ መስጠት
እንዲሁም ተጠያቅነትን ማምጣት ነው፡

6 ከሕግ አውጭው/ከሕዝቡ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሄራዊ መታወቂያ አሰራር ሂደት ኦዲት መደረጉ የህግ አውጪው ፍላጎት ከፍተኛ
ፍላጎት /Legislative or ነው፡፡
public interest/

7 የኦዲት ተደራጊ ኃላፊዎች ኦዲቱ በተለይ በአሁኑ ሰዓት ላይ መከናወኑ ኤጀንሲው ከዚህ በፊት የነበረውን ክፍተት ከወዲሁ ከፍተኛ
ለኦዲቱ ያላቸው ፍላጎት እንዲያሻሽል ስለሚረዳው ለኦዲቱ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ እና ኤጀንሲውም ኦዲቱን በከፍተኛ
/Departmental Issues/ ደረጃ ተጠያቅነትን ለማጠናከርና ውሳኔ ለመስጠት የሚፈልገው መሆኑን የማኔጅመንት አባላት
ገልጸዋል፡፡

8 ኦዲቱ አከባቢ አመቺነት ኦዲቱን ሊገቱ የሚችሉ አጋጣሚዎች የሉም፤ ስለዚህ ኦዲቱን ለማከናወን አመቺ ነው፡፡ እንዲሁም ከፍተኛ
(Sutability) በደሰሳ ወቅት የተከለሱ መረጃዎችና ከድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች ጋር የተደረገው ቃለ መጠይቅና
የተሰጠው መልስ የኦዲቱን ቀጣይነት ያመለክታሉ፡፡ ሆኖም ግን ኤጀንሲ መረጃዎችን በማቅረቡ ሂደት
ከፍተኛ ችግር አለ፡፡

9 ተስማሚነት በኤጀንሲው የክዋኔ ኦዲቱ መከናወኑ በዘርፉ/ ግንባታ/ ሲካሄድ የነበረውና ለሚካሄደው ግንባታዎች ከፍተኛ
/Relevance/ ተጠያቅነት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ በመሆኑ ለኤጀንሲው አጋዥ ነው፡፡
10 ኦዲቱን ለማከናወን ኦዲቱን ለማከናወን መረጃዎች ሊገኙ የሚችሉ ቢሆንም ኤጀንሲው ተባባሪ አለመሆኑ እንደ አንድ መካከለኛ
የሚቻል ወይም የማይቻል ችግር የሚታይ ሲሆን የሰው ኃይል እንደሚመደብልን ታሳቢ በማድረግ መከናወን የሚቻል ቢሆንም
ስለመሆኑ /Auditability/ ግንባታዎቹ በውለታ ሰነድ/specifications/ መሰረት ደረጃውንና ጥራቱን ጠብቆ መስራቱን
የሚያረጋግጥ የዘርፉ ባለሙያ ዕገዛ የሚያስፈልግ ይሆናል፡፡

11 ወቅታዊነት /Timeliness/ ኤጀንሲው ኦዲቱ እንዲከናወን ውሳኔዎችን ለማስተላለፍና ተጠያቅነትን ለማምጣት ስለሚፈልገው ከፍተኛ
ወቅታዊነቱ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

12 ከዚህ በፊት የክዋኔ ኦዲት ከዚህ በፊት የክዋኔ ኦዲት አልተከናወነም፡፡ ከፍተኛ
ስለመከናወኑ

/Previous audit work/

13 ከፍተኛ የሥራ ዕቅዶች ኤጀንሲው በዘርፉ ያሉትን ችግሮች፣ ማለትም የወጪ ልዩነት፣ የጊዜ ልዩነትና የጥራት ችግር ከፍተኛ
ወይም በሂደት ላይ ያሉ አስጠንቶ ያውቃል፡፡
የኦዲት አካባቢን የሚነኩ
ጉዳዮች /Other major
work planned or in
progress/

14 መደምደሚያና የተሰጠው በአጠቃላይ በኤጀንሲው የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችና ቢሮዎች
ጠቅላላ ትኩረት ግንባታው የተጀመረው ከ 2003 ዓ.ም ሲሆን፣ የተጀመሩት ፕሮጀክቶችም 17 ነበሩ፡፡ ከነዝህ
/Conclusion and ግንባታዎች 15 ቱ ሲጠናቀቁ ሁለቱ ማለትም ቀብሪደሃር እና ነገሌ ቦረና ያላለቁ ሲሆን በግንባታው
overall priority/ ሂደት ከፍተኛ የወጪ፣ የጊዜ እና የጥራት ልዩነት ከገቡበት ውል ጋር ተነጻጽረው ከተሰራው ከጤና
ጥበቃ ሚ/ር የጤና መሰረተ-ልማቶች ዳይሬክቶሬት ግንባታ ክትትል ቡድን ሪፖርት መሰረት ከፈተኛ
ልዩነት መኖሩበደሰሳው ወቅት ከተከለሱ ማስረጃዎች ለመገንዘብ መቻሉ፤

You might also like