You are on page 1of 4

Office of The Federal Auditor General

የኦዲት ማስታወሻ
ኦዲት ተደራጊው መ/ቤት: ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ

ኦዲት የሚደረገው በጀት ዓመት፡ 2010

ስም የኃላፊነት ደረጃ ቀን ፊርማ


ያዘጋጀው እሸቴ ጥበቡ ኦዲተር 03/11/10
የከለሰው ሰይድ አብዱልቃድር ከፍተኛ ኦዲተር 05/11/10
የከለሰው ሲሳይ ተክሉ ኦዲት ሥራ አስኪያጅ
የከለሰው ሠይፉ ከበደ ኦዲት ዳይሬክተር

ለአቶ ሃይሉ ታደሰ ፡የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር


ማስታወሻው የተሰጠበት ቀን ፡ 06/11/10

የኦዲት ማስታወሻ ቁጥር ፡ 14

የሂሳብ መደብ ፡ 6231

የተከፈለ ገንዘብ መጠን ፡ ብር 151,650.05

የኦዲት ማስታወሻው አርዕስት ፡ ከመመሪያ ዉጭ የተከፈለ አበል

የግኝቱ መግለጫ፣

የመንግስት ሰራተኞች የቀን ዉሎ አበል መመሪያ ሰኔ /2004 ዓ.ም ክፍል 2 የዉሎ አበል ክፍያ አፈፃፀም አንቀፅ 5 ንዑስ
አንቀፅ 1 ማንኛዉም የመንግስት ሰራተኛ ከመደበኛ የስራ ቦታዉ ዉጭ ወደ ሌላ ቦታ ለስራ ጉዳይ ሄዶ እለቱን መመለስ ካልቻለ
በስራ ተሰማርቶ ቁርስ፤ ምሳና እራት በተመገበባቸዉ የክልላዊ ከተማ ፤ የዞን ከተማ፤ የወረዳ ከተማና የከተማ አስተዳደሮች
እንዲከፈል የተመደበዉን አበል ለእያንዳንዱ ቀን ይከፈላል፡፡ በተጨማሪም ንዑስ አንቀፅ 2 ላይ ከሙሉ የአንድ ቀን ተመን
ዉስጥ 10% ለቁርስ፤ 25% ለምሳ፤ 25% ለእራት እና 40% ለአልጋ የተመደበ መሆኑ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ይህ በእንዲህ
እያለ በዚሁ መመሪያ ክፍል 3 አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ ማንኛዉም የመንግስት ሰራተኛ ከመደበኛ የስራ ቦታዉ ዉጭ
ወደ ሌላ ቦታ ለስራ ጉዳይ ከመላኩ በፊት የዉሎ አበል መጠየቂያ ፤ መፍቀጃና መክፈያ ቅፆች ለጉዳዩ አግባብ ባላቸዉ
ሰራተኞች ወይም ሃላፊዎች መሞላት እንዳለባቸዉ ይገልፃል፡፡ በተጨሪም በዚሁ አንቀፅ ላይ ንዑስ አንቀፅ 2 እና ንዑስ አንቀፅ
3 የዉሎ አበል ተከፍሎት ወደ ሌላ የስራ ቦታ የተላከ ሰራተኛ ሲመለስ የቀን ዉሎ አበል ክፍያ መቆጣጠሪያና የስራ ክንዉን
መመዝገቢያ ቅፅ በመሙላት የስራ መግለጫ ያቀርባል ፡፡ እንዲሁም የዉሎ አበል እንዲከፈለዉ ያሳሰበዉ ወይም የጠየቀዉ የስራ
ሃላፊ በሰራተኛዉ የተሞላዉ ቅፅ በትክክል መሞላቱን ማረጋገጥ እንዳለበት በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲዉ በተለያዩ
ጊዜዎች አበል ሲከፈል ሰራተኞች በተንቀሳቀሱበትና ባደሩበት ቦታ መሆን ሲገባዉ እና ማወራረጃዉ ላይም በትክክል ለቁርስ፤ ለምሳ፤
ለእራት እና ለአልጋ የተመደበዉ ሳይሞላ ዝም ብሎ በጥቅሉ የተመደበዉን ቀን ብዛት በማሰብ በድምሩ ብር 151,650.05 የተከፈለ
መሆኑን በኦዲት ወቅት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ዝርዝር ሁኔታዉም እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡
ተ የወጭ ቀን የወጭ የቀ ብዛ ስራዉ የተሰራበት ቦታ በላከዉ አካል የተገለፀ ውሎ አበሉ የተከፈለዉ ገንዘብ
. ቁጠር ት የተከፈለበት
Office of The Federal Auditor General

ቁ መነሻ ቦታ
ቦታ
1 20/5/10 57863 20 ጭሮ ሆለታ፣ቢሾፍቱ፣ሞጆ፣መተሃራ፣አዳማና አሰላ በአ/አበባ 33,494.85
8
2 16/8/10 57922 22 ጭሮ አ/አበባ፣ደሴ፣ሃዋሳ፣ደ/ብርሃንና ዲላ በአ/አበባ 26,338.60
2
3 01/7/10 57885 15 ጭሮ ሃዋሳና አዳማ በሃዋሳ 26,834.50
8
4 10/6/10 57848 18 ጭሮ አ/አበባ፣ወንዶገነት፣ባሌ፣አሰላ በአ/አበባ 21,444.60
2
5 10/12/1 57783 20 ጭሮ ሃዋሳ፣ጁማ፣ወልድያ፣መቀሌና ደ/ብርሃን በመቀሌ 43,537.50
0 4
ጠቅላላ ድምር 151,650.05

ስጋት

- መንግስት በተለያየ ጊዜ የሚያወጣቸው አዋጆችና መመሪያዎች ተግባራዊ ላይደረጉ ይችላሉ፡፡

- ወጭ የተደረገዉ የዉሎ አበል ትክክለኛ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ በዚህም የተነሳ የመንግስት ዉስን
ሃብት ለብክነት ሊዳረግ ይችላል፡፡

- ከህግ እና መመሪያ ዉጭ የሆኑ ዉሳኔዎችን በመወሰን የሚከፈል ክፍያ ተጠያቂነት ሊያመጣ ይችላል፡፡

የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መወሰድ ያለበት የማሻሻያ እርምጃ ፣

የተወራረዱ በሚል የተያዙ ወይም የታለፉ ሂሳቦች በድጋሚ ህጉ እና መመሪያዉ በሚያዝዘዉ መሰረት ሊወራረዱ እና ተመላሽ
የሚሆን የመንግስት ገንዘብ ካለ ወደ መንግስት ካዘና ተመላሽ ተደርጎ ሪፖረት ሊቀርብ ይገባል ፡፡ እንዲሁም ለወደፊቱ ተመሳሳይ
ስህተት እንዳይደገም ጥንቃቄ ሊደረግና ማንኛዉም ክፍያ ሲፈፀም የመንግስት የክፍያ መመሪያዎች ተጠብቀው ተግባራዊ ሊደረጉ
ይገባል፡፡

የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ምላሽ፣


Office of The Federal Auditor General

የኃላፊው ስምና ፊርማ ----------------- ቀን -------------------

የኦዲተሩ አስተያየት፣

ስምና ፊርማ ------------------------- ቀን ------------------------


Office of The Federal Auditor General

You might also like