Professional Documents
Culture Documents
16
16
የኦዲት ማስታወሻ
የሂሳቡ ዝርዝር ሁኔታ፡- ለግንባታ ከመደበኛ በጀት ለካፒታል በጀት ተከፍሎ የተገኘ
የግኝቱ መግለጫ
የፌዴራል መንግስት የፋይናንስ ኃላፊነት መመሪያ ቁጥር 6/2003 ክፍል ሁለት የፋይናንስ ኃላፊነት የመንግስት
መ/ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች ቁጥር 6(ለ) የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ እንዲሁም አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው
የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ላይ በመመርኮዝ የወጡት መመሪያዎች በመ/ቤቱ ውስጥ በተሟላና ተገቢ በሆነ መንገድ ሥራ
ላይ መዋላቸውን በማረጋገጥ ረገድ ላይ ተጠያቂነት እንዳለባቸው ይገልፃል :: የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር
190/2002 ስለፌዴራል መንግስት የፋይናስ አስተዳደር የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ክፍል ሦስት
የመንግስት ገንዘብ ክፍያ አንቀጽ 12 የመንግስት ገንዘብ ክፍያ ሊፈፀም ወይም ወጪ ሊደረግ የሚችለው የተፈቀደ
በጀት ሲኖር ብቻ እንደሆነ ይገልጻል ፡፡ ይሁን እንጂ ዩኒቨርሲቲው ለካፒታል የተፈቀደ በጀት ሳይኖር በተለያየ ቀን
ለተለያዩ ፕሮጀክት በድምሩ ብር 1,053,535.11 ከመደበኛ በጀት ተከፍሎ ተገኝቷል፤ ዝርዝሩ እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡
በቀን 15/03/10 በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር 477468 በሂሳብ መደብ 6244 ብር 188,392.98 ከአዲሱ
አበራ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ውል በመግባት ለአራት ሽንት ቤት እና ሻወር ቤት ግንባታ በሚል ከመደበኛ በጀት ለካፒታል
በጀት የተከፈለ መሆኑ
በቀን 9/4/10 በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር 477653 በሂሳብ መደብ 6244 ብር 408,590.03 ከአዳነች እና
እዮብ ውል በመግባት የፊኒሽንግ ስራ በሚል ከመደበኛ በጀት ለካፒታል በጀት የተከፈለ መሆኑ
AQ Page 1
የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት 2010
በቀን 08/04/10 በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር 477645 በሂሳብ መደብ 6244 ብር 176,433.92 ከአዲሱ
አበራ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ውል በመግባት ለአራት ሽንት ቤት እና ሻወር ቤት ግንባታ በሚል ከመደበኛ በጀት ለካፒታል
በጀት የተከፈለ መሆኑ
በቀን 22/03/10 በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር 477536 በሂሳብ መደብ 6244 ብር 208,804.04 ከአዳነች እና
እዮብ ውል በመግባት የፊኒሽንግ ስራ በሚል ከመደበኛ በጀት ለካፒታል በጀት የተከፈለ መሆኑ
በቀን 06/04/10 በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ቁጥር 477646 በሂሳብ መደብ 6244 ብር 71,314.14 ከአዲሱ አበራ
ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ውል በመግባት ለአራት ሽንት ቤት እና ሻወር ቤት ግንባታ በሚል ከመደበኛ በጀት ለካፒታል በጀት
ተብሎ በአጠቃላይ በድምሩ ብር 1,053,535.11 ተከፍሎ የተገኘ መሆኑ በኦዲት ወቅት ተረጋግጧል።
ወጪው ብር 1,053,535.11 በሂሳብ መደብ 6324 መመዝገብ ሲገባው በሂሳብ መደብ 6244 ተመዝግቦ ሪፖርት
ስጋት
የመንግስትን በጀት ከደንብና መመሪያ ወጪ መጠቀም የመንግስት መመሪያን ከመጣሱም በላይ ለምዝበራና ለብክነት
ሊያጋልጥ ይችላል ፡፡
ደንብና መመሪያ ተፈጻሚ እንዳይሆን ከማድረጉ በተጨማሪ የሂሳቡን ትክክለኛ ገጽታ እንዳያሳይ ሊያረግ ይችላል፡፡
AQ Page 2
የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት 2010
ፊርማ ----------------
ቀን ፡- --------------------
የኦዲተሩ አስተያየት፣
ፊርማ ----------------
ቀን ፡- --------------------
AQ Page 3
የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት 2010
AQ Page 4