You are on page 1of 6

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የሰበር መዝገብ ቁጥር 220213

ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ/ም

ዳኞች ፡- ተፈሪ ገብሩ (ዶ/ር)

ቀነዓ ቂጣታ

ፈይሳ ወርቁ

ደጀኔ አያንሳ

ብርቅነሽ እሱባለው

አመልካች፡- ሃጁታ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- አልቀረቡም

ተጠሪ፡- ገቢዎች ሚኒስቴር፡- ነ/ፈጅ ቆንጂት ተስፋዬ

ፍርድ

የ2010 ዓ/ም ትርፍ ለባለአክስዮኖች ሳይከፋፈል ለድርጅቱ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ሰኔ 30 ቀን


2011 ዓ/ም ከማለፉ በፊት ቃለጉባኤ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተመዝግቦ ፀድቆ በወረፋ
ምክንያት 5 ቀናት ዘግይቶም ቢሆን የካፒታል ዕድገት ለውጡ በንግድ ኢንዱስሪ ልማት ቢሮ የተሰጠው
ማስረጃ በመመሪያው በተቀመጠው ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠሪ እንዲያውቀው መደረጉ አከራካሪ
ባልሆነበት እና የሰነድ ማስረጃም ቀርቦ ባለበት ፤ እንዲሁም የ2010 ዓ/ም ትርፍ በሙሉ ለካፒታል
ማሳደጊያነት መዋሉ በተጠሪ ባልተካደበት እና በማስረጃ ተረጋግጦ ባለበት በመመሪያው የተቀመጠው ቅድመ
ሁኔታ ተሟልቶ እያለ የካፒታል ለውጡ በንግድ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተመዘገበው ከአሥራ ሁለት
ወራት ጊዜ ገደቡ በቀናት ዘግይቶ መቅረቡ የፕሮሲጀር (ሂደት) እንጅ ትርፍ ሳይከፋፈል ለካፒታል
ማሳደጊያነት መዋሉን የሚያረጋግጥ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ተወስዶ ትርፉ ሳይከፋፈል ለካፒታል ማሳደጊያነት
የዋለ ለመሆኑ ብቸኛ ማሳያ በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የፀደቀው ቃለጉባኤ ሆኖእያለ ፤ ዘግይቶ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
መመዝገቡ ጥፋት ነው ከተባለም በንግድ ሥራ አዋጅ እና መመሪያዎች መሠረት ራሱን ችሎ ከሚያስቀጣ
በቀር ሳይከፋፈል ለካፒታል ማሳደጊያነት የዋለን ትርፍ ለካፒታል ማሳደግያነት እንዳልዋለ ተቆጥሮ
ላልተከፋፈለ ገቢ የትርፋ ድርሻ ገቢ ግብር እንዲከፈልበት መወሰኑ አዋጅ ቁጥር 938/2008 ፣ 686/2002
እና መመሪያ ቄጥር 7/2011 የሚጣረስ በመሆኑ አመልካች የገቢ ግብር ፣ ወለድ እና ቅጣት ሊከፍል
አይገባም ተብሎ እንዲወሰን አመልካች ጥር 24 ቀን 2014 ዓ/ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መነሻነት መዝገቡ
ለችሎት ሊቀር ችሏል፡፡

ጉዳዩ የአክስዮን ትርፍ ድርሻ የገቢ ግብርን የሚመለከት ሆኖ ተጠሪ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ/ም ቁጥሩ
ገ/ሚ/መ/2/3354/ሀ በሆነው ለአመልካች በፃፈው ደብዳቤ 251,821.92 (ሁለት መቶ ሀምሳ አንድ ሽህ
ስምንት መቶ ሀያ አንድ ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) የአክስዮን ትርፍ ድርሻ ግብር እንዲከፍል የደረሰውን
የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ ቅር በመሰኘት ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ባቀረበው ይግባኝ፡- የ2010 ዓ/ም ትርፉን
ለድርጅቱ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ባለአክስዮኖች ያደረጉት ስምምነት ቃለጉባኤ በሰነዶች ምዝገባ እና
ማረጋገጫ ጽ/ቤት ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም ቀርቦ ጸድቆ በመመሪያው በተቀመጠው የሁለት ወር ጊዜ ውስጥ
ተጠሪን ስላሳወቀ ንግድ ሚኒስቴር በነበረው ወረፋ ምክንያት ያደገው ካፒታል በድርጅቱ የንግድ ፈቃድ ላይ
የታየው የ12 ወራት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ቢሆንም በገቢ ግብር አዋጅም ሆነ በመመሪያ ቁጥር 7/2011
ከንግድ ሚኒስቴር የሚቀርበው ማስረጃ ዘግይቶ መቅረቡ የትርፍ ድርሻ ክፍፍል ግብር ይክፈል የሚል
ድንጋጌ ባለመኖሩ የአክስዮን ትርፍ ድርሻ ክፍፍል ገቢ ግብር እንዲከፈል መጠየቁ ተገቢ ባለመሆኑ አመልካች
ድርጅት እንዲከፍል የተጠየቀው ግብር ቅጣት እና ወለድ ከህግ አግባብ ውጭ ሲሆን ፤ ድርጅቱ ይክፈል
ከተባለም ለውጡን ባለማሳወቅ የሚጣል አስተዳደራዊ ቅጣት ብቻ ሊሆን ይገባል በማለት ቅሬታ አቅርቧል፡፡

ተጠሪም በመልሱ፡- የአመልካች አቤቱታ በታክስ ግባኝ ኮሚሽን የሚታየው በቅድሚያ በአቤቱታ አጣሪ ጽ/ቤት
ታይቶ ውሳኔ ሲሰጥበት ሆኖእያለ በቀጥታ ለኮሚሽኑ መቅረብ የለበትም በማለት የመጀመሪያ ደረጃ
መቃወሚያ በማስቀደም በፍሬ ነገር ክርክሩም፡- አመልካች በ2010ዓ/ም ያገኘውን ትርፍ የሂሳብ ጊዜው
በተጠናቀቀ በ12 ወራት ውስጥ የትርፍ ድርሻን ለድርጅቱ ካፒታል ማሳደጊያነት ማዋሉን በሰነዶች ማረጋገጫ
እና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ የባለአክስዮኖች ቃለጉባኤ እና ካፒታሉ ስለማደጉ የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
ሁለቱንም ማስረጃዎች በህግ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ሲያቀርብ በመመሪያ ቁጥር 7/2011 መሠረት
ካልተከፋፈለው ትርፍ ድርሻ ግብር ነፃ እንደሚሆን በተመለካተው አግባብ ማቅረብ ሲገባቸው የካፒታል
ዕድገቱ የተመዘገበው የ12 ወራት ጊዜ ካፈ በኋላ በመሆኑ አመልካች ከግብር ነፃ የሚሆኑበት የተቀመጡ
ቅደመ ሁኔታዎች ተሟልተው ስላልቀረቡ አመልካች የተጠለበትን ግብር ፣ ቅጣት እና ወለድ እንዲከፍሉ
መወሰኑ በሕጉ አግባብ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡

ጉዳዩ በዚህ መልክ የቀረበለት የኢፌዲሪ ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008
አንቀጽ 56 እና 88 በግልጽ እንደተቀመጠው በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ታክስ ከፋይ ውሳኔውን በተቀበለ
በ30 ቀናት ውስጥ የይግባኝ ማስታወቂያውን ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ሊያቀርብ እንደሚችል በሚደነግገው

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
መሠረት አመልካች የይግባኝ አቤቱታን ያቀረበ በመሆኑ በተጠሪ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ
አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል፡፡ በፍሬ ነገር ክርክር ረገድም የገንዘብ ሚኒስቴር በገቢ ግብር
አዋጅ በተሰጠው ስልጣን ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ስለሚጣል ግብር አፈጻጸምን በሚመለከት ባወጣው
መመሪያ ቁጥር 7/2011 መሠረት ትርፍ የተገኘበት የግብር ዘመን ባለቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ
የባለአክስዮኖች የአክስዮን ድርሻ ስለማደጉ የሚገልጸውን ቃለጉባኤ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት
እንዲጸድቅ እና የድርጅቱ ካፒታል ስለማደጉ ንግድ ሚኒስቴር በሚሰጠው የንግድ ፈቃድ ላይ ታይቶ
ማስረጃዎቹ በሁለት ወራት ውስጥ ለተጠሪ መቅረብ እንዳለባቸው በግልጽ ተመላክቷል፡፡ የአመልካች
ባለአክስዮኖች በ2010 ዓ/ም የተገኘው ትርፍ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል ሰኔ 05 ቀን 2011 ዓ/ም
የያዙት ቃለጉባኤ ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት እንዲጸድቅ መደረጉ
በተጠሪ መስሪያ ቤት ስላልተካደ በንግድ ፈቃድ ላይ የታየው የ12 ወራት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ቢሆንም
የመመሪያ ዓላማ ባለአክስዮኖች ያገኙትን ትርፍ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ለማስፋት አውለውት ከሆነ
ትርፉን እንዳልተከፋፈሉት ተቆጥሮ ከትርፍ ድርሻ ገቢ ግብር ነጻ ማድረግ በመሆኑ ፤ አመልካች ያገኘውን
ትርፍ ለካፒታል ማሳደጊያነት ለማዋል ያቀደ መሆኑ ቃለ ጉባኤ በመያዝ ፣ ቃለጉባኤውንም በ12 ወራት ጊዜ
ውስጥ በሚመለከተው የመንግስት አካል አጸድቆ የ12 ወራት ጊዜው በተጠናቀቀ በሁለት ወራት ውስጥ
ማስረጃውን ለተጠሪ ማሳወቁ ያገኘውን ትርፍ እንዳልተከፋፈለ የሚያሳይ ሆኖእያለ ትርፉ እንደተከፋፈለ
ተቆጥሮ ግብር ቅጣት እና ወለድ እንዲከፈል ማድረግ ከህግ አግባብ ውጭ ነው በማለት ወስኗል፡፡

በውሳኔው ባለመስማማት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረዙ ተጠሪ
ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ይዘትም፡- አዋጁ ሆነ
በመመሪያው መሰረት የአመልካች ድርጅት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ካፒታሉን ሳያሳድግ ቃለ ጉባኤ
በመጽደቁ ብቻ አመልካች ግብር መክፈል የለበትም በማለት በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን የተሰጠው ውሳኔ
ሊታረም ይገባል በማለት አቅርቦ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም አመልካች የንግድ
ቢሮ የሚሰጠው ማስረጃ ባለማቅረቡ ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት መሆን አለመሆኑን በጭብትነት ይዞ
መዝገቡ እንደመረመረው፡- አመልካች የ2010 ዓ/ም በጀት ዓመት በተጠናቀቀ በ12 ወራት ውስጥ ትርፉን
ባለአክስዮኖችን የአክስዮን መጠን እንዳሳደጉበት የሚገልጽ ቃለ ጉበኤ ቢኖረውም በተገኘው ትርፍ ልክ
ካፒታልቸው ማደጉን የሚገልጽ ከንግድ ቢሮ የተሰጠ ማስረጃ አለመቅረቡ አከራካሪ አለመሆኑን ገልፆ ፤ በገቢ
ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት ያልተከፋፈለ የአክስዮን ትርፍ ድርሻ ግብር የሚከፈልበት መሆኑን
በመደንገጉ የገንዘብ ሚኒስቴር በአዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ካልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር
የማይከፈልበትን ሁኔታ የሚገዛ መመሪያ ቁጥር 7/2011 አውጥቷል፡፡ በመመሪያው አንቀጽ 5(2) መሰረት
አንድ ድርጅት ባለተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር እንዲከፈል የማይጠየቀው በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ
የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ውስጥ የአባላቱን የአክስዮን ድርሻ
መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው የተጣራ የትርፍ መጠን ካሳደገ ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
በተጨማሪም ያልተከፋፈለ ትርፍ አለመኖሩን ለማስረዳት የሚቀርቡ ማስረጃዎች በመመሪያው አንቀጽ 6(1)

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
(ለ) ላይ ትርፉ ለካፒታል ማሳደጊያነት ስለመዋሉ የሚያሳይ በሰነዶች ምዝገባ እና መረጋገጫ ጽ/ቤት የጸደቀ
ቃለ ጉባኤ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ካፒታሉ በእርግጥ ስለማደጉ የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ
እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ ማስረጃዎቹም አንዱ አንዱን በሚተካ መልክ ሳይሆን ሁለቱም ተሟልተው መቅረብ
እንዳለባቸው በመመሪያው በግልጽ ተመልክቷል፡፡ በተያዘው ጉዳይም አመልካች የ2010 ዓ/ም በጀት ኣመት
በተጠናቀቀ በ12 ወራት ውስጥ ትርፉን የባለአክስዮኖችን የአክስዮን መጠን እንዳሳደጉበት የሚገልጽ ቃለጉባኤ
ቢኖራቸውም በተገኘው ትርፍ ልክ ካፒታላቸው ስለማደጉ የሚገልጽ ከንግድ ቢሮ የተሰጠ ማስረጃ አለመቅረቡ
በሕጉ የተመለከተው ቅድመ ሁኔታ አለመሟላቱን ስለሚያመለክት ፤ ማስረጃዎቹ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ
ውስጥ ተሟልተው አለመቅረብ በመመሪያው አንቀጽ 7(3) መሰረት ፍሬ ግብር ፣ ወለድ እንዲሁም ቅጣት
እንደሚከፈል በግልጽ ስለሚደነግግ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ውሳኔ
አግባብነት የለውም በማለት በተጠሪ የሰጠውን የግብር ውሳኔ በማጽናት ወስኗል፡፡

አመልካች በውሳኔው ቅር በመሰኘት በሥር ፍርድ ቤት ተፈጽሟል የሚሉትን መሰረታዊ የሕግ ስህተት
በመዘርዘር ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ የመረመረው ሰበር አጣሪ ችሎቱ አመልካች በንግድ ስራ ያገኘውን
ትርፍ ለካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል የባለአክስዮኖች ቃለጉባኤ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ጽ/ቤት
ቀርቦ ጸድቆ በወረፋ ምክንት ቢዘገይም ተመዝገብቦ እያለ በንግድ ሚኒስቴር የተመዘገበው 12 ወር ካለፉ በኋላ
ነው ተብሎ አመልካች ግብር ፣ ቅጣት እና ወለድ እንዲከፈል የተወሰነበት አግባብ ከመመሪያ ቁጥር 7/2011
አንፃር መጣራት ያለበት መሆኑ ታምኖበት ለሰበር ይቅረብ በማለቱ ተጠሪ በሰጠው ምላሽ፡- በገቢ ግብር
አዋጅ ቁጥር 979/2008 እና በመመሪያ ቁጥር 7/2011 መሰረት አንድ ድርጅት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ
ግብር እንዲከፍል የማይጠየቀው በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው
በተጠናቀቀ በ12 ወራት ውስጥ የአባላቱን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው የተጣራ
ትርፍ መጠን ካሳደገ ሆኖ በመመሪው መሰረት ግብር ልከፍል አይገባም በማለት መከራከር የሚቻለው የበጀት
ዓመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት 12 ወራት ጊዜ ውስጥ ትርፉ የአባላት የአክስዮን ድርሻን (የድርጅቱን
ካፒታል) ለማሳደግ የዋለ መሆኑን የጸደቀ ቃለጉባኤ እና ከንግድ ቢሮ ካፒታሉ ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ
በጣምራ በማቅረብ ሲሆን የነዚህ ማስረጃዎች በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ተሟልተው አለመቅረብ ካፒታል
እንዳደገ ስለማይቆጠር ፤ ትርፉ ለካፒታል ማሰደጊያነት የዋለው ከ12 ወራት በኋላ ከሆነም በመመሪያው
ቁጥር 7(3) ድንጋጌ መሠረት ግብር የሚከፈልበት በመሆኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሚነቀፍ የሕግ
ምክንያት አለመኖሩን ፤ አመልካች ዋናውን በመንግስት አካል ተረጋግጦ የሚሰጠውን የካፒታል ዕድገት
ማስረጃ ወደጎን በመተው ትርፍ ለባለአክስዮኖች ሳይከፋፈል የድርጅቱን ካፒታል ለማሳደግ የዋለ መሆኑን
ለማረጋገጥ በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርቦ የፀደቀውን የባለአክስዮኖች ቃለጉባኤ በቂ ነው
ሲል ያቀረበው መከራከሪያ የሕግ ድጋፍ የሌለው መሆኑን ፤ የአንድን ድርጅት የካፒታል ዕድገትም ሆነ
የካፒታል መቀነስ በሚያረጋግጠው ይህንኑ ከሚመዘግበው የመንግስት አካል በሚቀርብ ሰነድ እንጅ
በቃለጉባኤ ባለመሆኑ ዋናውን ካፒታል ስለማደጉ የሚያስረዳውን ማስረጃ አመልካች ጥቅም የለውም በማለት
ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፤ አመልካች ካፒታል አሳድጌያለሁኝ በማለት ያቀረቡት

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
ማስረጃ የ12 ወራት ጊዜ ካበቃ በኋላ ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ/ም ሆኖ ማስረጃውም በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ
ተረጋግጦ የተሰጠ ባለመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው በመመሪያው ቁጥር 7(3) መሠረት አመልካች መብቱን
እንደተወው ተቆጥር ባልተከፋፈለው ትርፍ ላይ ግብር ፣ መቀጫ እና ወለድ የሚከፈል መሆኑ ጊዜው ካለፈ
በኋላ ሊስተናገዱ የሚችሉበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን ፤ የሁለት ወር ጊዜውም ለተጠሪ ማሳወቂያ ጊዜ
እንጅ የካፒታል ማሳደጊያ ጊዜ አለመሆኑና ያልተከፋፈለ ትርፍ ለካፒታል ማሳደጊያነት ሳይውል ጊዜ ካበቃ
በኋላ የተደረገ የካፒታል ማሳደግ ለተጠሪ ማሳወቅ የአመልካችን ግብር የመክፈል ኃላፊነት የማያስቀር
መሆኑ አመልካች የትርፍ ድርሻውን ለካፒታል ማሳደጊያነት በመዋሉ ለግብር ነፃ ሊሆን በሚችልበት የጊዜ
ገደብ ውስጥ ተገቢ የሆኑት ማስረጃዎች ባለማቅረባቸው ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት
ተከራክረዋል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተውን ሲመስል ለሰበር ቅሬታው ምክንያት የሆነው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ
ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ አግባብነት ካለው ሕግ አንፃር መዝገቡ እንደሚከተለው
ተመርምሯል፡፡

ያልተከፋፈለ ትርፍን የድርጅቱ የሂሳብ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ባለው 12 ወራት ጊዜ ውስጥ ለባለአክስዮኖች
ያልተከፈለ ወይንም የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ ያልዋለ የተጣራ ትርፍ ነው የሚል ትርጉም
ተሰጥቶታል፡፡ ያልተከፋፈለ ትርፍ በአዋጁ አንቀጽ 61 መሠረት አሥር በመቶ (10%) ግብር ስለሚከፈልበት
በሕጉ የተመለከተው 12 ወራት ጊዜ ካበቃ በኋላ ባለው ሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ግብር ከፋዩ አስታውቆ
መከፈል ያለበት መሆኑ ፤ በዚህ አግባብ ግብሩን አሳውቆ አለመክፈል ከፍሬ ግብር በተጨማሪ መቀጫ እና
ወለድ የሚያስቀጣ መሆኑን ፤ በልተከፋፈለ ትርፍ ግብር የማይከፈለው ድርጅቱ በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ
የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላትን የአክስዮን ድርሻ
መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው ትርፍ ካደገ ሆኖ ይኸንኑን የሂሳብ ጊዜው ካበቃ በኋላ ያለው የ12
ወራት ጊዜ ከተጠናቀቀ ባለው ሁለት ወር ወይንም ቀደም ብሎ ባለው ጊዜ ውስጥ የፀደቀ ቃለጉባዔ እና
ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ወይንም አግባብነት ባለው አካል የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ
በማቅረብ ድርጅቱ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ ያለበት መሆኑንና በዚህ አግባብ አግባብነት ያለው ማስረጃ
በማቅረብ በመመሪያው በተመከለተ ጊዜ ውስጥ አለማሳወቁ ግብር ከመወሰኑ በፊት ከታወቅ አስተዳደራዊ
ቅጣት የሚያስቀጣ ሲሆን ነገር ግን በሕጉ በተመለከተው ጊዜ ውስጥ አላማሳወቁ ግብር ፣ መቀጫ እና
ወለድ ከተወሰነ በኋላ ከታወቀ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚጣል መሆኑን ፤ የድርጅቱ ትርፍ የአባላቱ
አክስዮኖች ድርሻ እና የድርጅቱ ካፒታል ለማሳደግ ያዋለው የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት በኋ ላ
ከሆነ መብቱን እንደተወውና ያልተከፋፈለ ትርፍ እንዳለው ተቆጥሮ ግብር ፣ መቀጫ እና ወለድ የሚጣልበት
መሆኑን ፤ አንድ ድርጅት የአባላቱ አክስዮን ድርሻ እና የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን ለማስረዳት ለባለሥልጣኑ
ማቅረብ ያለበት ማስረጃ አግባብነት ባለው አካል የፀደቀ ቃለጉባዔ እና ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
ወይንም አግባብነት ባለው አካል የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ በማቅረብ ነው፡፡ ( ባልተከፋፈለ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም
ትርፍ ላይ ስለተጣለው ግብር አፈፃፀም የወጣው መመሪያ ቁጥር 7/2011 ቁጥር 3(1) ,5 ,6 እና 7
ይመለከቷል፡፡)

በተያዘው ጉዳይ አመልካች ባልተከፋፈለው ትርፍ የሂሳብ ጊዜ በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላቱን
አክስዮን ድርሻ መጠን እና ድርጅቱ ካፒታል በተገኘው የተጣራ ትርፍ መጠን ማደጉን በሕጉ በተመለከተው
አግባቢነት ያለው ማስረጃ በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ አቅርቦ ባለማስረዳቱ ግብር ፣ አስተዳደራዊ
ቅጣት እና ወለድ እንዲከፍል መወሰኑ የሚነቀፍ ባለመሆኑ ተከታዩ ተወስኗል፡፡

ውሳኔ

1. የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 203347 ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው
ችሎት የሰጠውን ፍርድ እና ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348(1) መሠረት ፀንቷል ።
2. በሰበር ክርክሩ የደረሰውን ወጪ እና ኪሳራ ግራ ቀኙ የግላቸውን ይቻሉ።
መዝገቡ ውሳኔ ስላገኘ ተዘግቷል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ሠ/ኃ

ማ ስታወሻ፡- ይህ የሰበር ችሎት ውሳኔ ሰነድ ለጥናትና ምርምር ሥራ ወይም ለግንዛቤ እንጂ
ለፍርድ አፈጻጸም ዓላማ አያገለግልም

You might also like