You are on page 1of 8

ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል

ቅጣት
1. ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ታክስ ቀንሶ ለባለሥልጣኑ ማስተላለፍ ያለበት ማንኛውም ሰው ሳይቀንስ የቀረው ወይም
ቀንሶ ለባለሥልጣኑ ያላስተላለፈውን ታክስ 10% (አሥር በመቶ) ቅጣት ይከፍላል፡፡

2. የዚህ ተራ ቁጥር (|) ለድርጅት ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ፣ በዚሁ መሠረት ከሚጣለው ቅጣት በተጨማሪ
የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ፣ ዋና የሂሳብ ሹም ወይም ታክስ ተቀንሶ መያዝ እንዳለበትና የተያዘውም ታክስ መከፈል
እንዳለበት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ማንኛውም ሌላ የድርጅቱ ሠራተኛ እያንዳንዳቸው ብር 2 ሺ (ሁለት ሺ
ብር) ቅጣት ይከፍላሉ፡፡

3. በሀገር ውስጥ ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ አቅራቢውና
ገዥው እያንዳንዳቸው ብር 20 ሺ (ሃያ ሺ ብር) ቅጣት ይከፍላሉ፡፡

4. በሀገር ውስጥ ከሚፈፀሙ ክፍያዎች ላይ ግብር ቀንሶ ማስቀረት መሠረት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ የሚከፈልን
ታክስ ለማስቀረት በማሰብ በዚህ መሠረት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ታክስ ቀንሶ የመክፈል ግዴታ ላለበት ሰው ዕቃዎችን
ወይም አገልግሎቶችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ብር 10 ሺ (አሥር ሺ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡

5. ከተከፋይ ሒሳብ ላይ ግብር ቀንሶ ባለመክፈል የሚጣለው ቅጣት ተፈጻሚ የሚሆነው ከተከፋይ ሒሳብ ላይ
ተቀንሶ የቀረው ገንዘብ በታክስ መክፈያ ጊዜ ባለመክፈሉ ይሆናል፡፡

6. ግብር ቀንሶ ገቢ ያላደረገ:-

ሀ) የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ፣ እና

ለ) ዋና የሒሳብ ሹም ወይም ዋና ሒሳብ ሹም የሌለ እንደሆነ ታክስ ቀንሶ መያዝ እንዳለበትና የተያዘውም ታክስ
መክፈል እንዳለበት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ማንኛውም ሌላ የድርጅቱ ሠራተኛ በእያንዳንዱ የታክስ መክፈያ
ጊዜ ተቀንሶ ገቢ ላልተደረገ ግብር እያንዳንዳቸው ብር 2000 ቅጣት ይከፍላሉ፣

7. በዚህ ተራ ቁጥር 4| የተደነገገ ቢኖርም አንድ ሰው ከአንድ በላይ ኃላፊነቶች ደርቦ የሚሠራ ከሆነ የሚጣለው
ቅጣት ተፈፃሚ የሚሆነው እንደ አንድ ኃላፊ ብቻ ይሆናል፡፡

አቅራቢውና ገዥው እያንዳንዳቸው ብር 20 ሺ (ሃያ ሺ ብር) ቅጣት ተፈጻሚ የሚሆነው ባለሥልጣኑ


ያልተከፈለውን የግብር መጠን በመወሰን እና የጽሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት ያልተከፈለውን ተቀንሶ መያዝ
የነበረበትን ግብር ከአቅራቢው ወይም ከገዥው ላይ ማስከፈል ተፈጻሚ በሚደረግባቸው ገዢ እና አቅራቢ ላይ ነው፡፡

ከፌስቡክ በተጨማሪ የታክስ ትምህርቶችንና መረጃዎችን ከሥር በተቀመጡት ዓማራጮች ማግኘትይችላሉ፡-

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚዎች ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች፡-

• እውቅና ያልተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አለመጠቀም፡፡

• በባለሥልጣኑ ዘንድ ያልተመዘገበ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አለመጠቀም፡፡


• የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያውን ከተርሚናል ጋር አለማለያየት፡፡

• የመሣሪያው አቅራቢ፤ መሣሪያውን ከውጪ ማስገባትና አቅርቦት ከመጀመሩ በፊት


እውቅና ከባለሥልጣኑ ሊያገኝ ይገባል፡፡

• መሣሪያው ብልሽት ቢያጋጥመውና ተጠቃሚው የመሣሪያውን እሽግ ሳይሰብር


ሊያስተካክለው የማይችል ከሆነ በመሣሪያው መጠቀሙን ወዲያውኑ አቋርጦ ብልሽቱ
ያጋጠመበትን ጊዜ በምርመራ መዝገቡ ላይ መመዝገብና በ 2 ሰዓት ውስጥ ለባለሥልጣኑና
ለአገልግሎት ማዕከሉ በስልክ ማስታወቅ አለበት፡፡

• የተበላሸው መሣሪያ እስከሚስተካከል ወይም በሌላ መሣሪያ እስከሚተካ ተጠቃሚው


በባለሥልጣኑ ፈቃድ በታተመ ደረሰኝ ግብይቱን ማከናወን አለበት፡፡ ሆኖም በታተመ ደረሰኝ
ግብይት ማከናወን የሚችለው በአንድ ዓመት ውስጥ ከ 5 ቀናት ለማይበልጥ ጊዜ ብቻ
ይሆናል፡፡

• የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው የባለቤትነት መብት ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት


የተላለፈ እንደሆነ ቀደም ሲል የመሣሪያው ባለቤት የነበረው ሰው ወይም ድርጅት
ይጠቀምበት የነበረው የፊሲካል ማስታወሻ ከመሣሪያው እንዲወጣ ተደርጎ በአዲስ
ይተካል፡፡

• የባለቤትነት ለውጥ ሲደረግ መሣሪያውን የገዛው ሰው ከተመዘገበ የአገልግሎት ማዕከል


ጋር ውለታ መግባት ያለበት ሲሆን መሣሪያውን መጀመሪያ ይጠቀምበት ለነበረው ተጠቃሚ
የሸጠው የመሣሪያ አቅራቢ ይህንኑ ለውጥ ለባለሥልጣኑ በ 5 ቀን ውስጥ ማስታወቅ
ይገባዋል፡፡ አዲሱ ተጠቃሚም መሣሪያውን በባለሥልጣኑ ዘንድ ማስመዝገብ አለበት፡፡

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ የባለቤት ለውጥ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ፤

አንድ ግብር ከፋይ ይጠቀምበት የነበረውን የሽያጭ መዝገቢያ መሣሪያ የባለቤት ለውጥ
በማድረግ ወደ ሌላ ተጠቃሚ ማዘዋወር ሲፈለግ፡-

• የንግድ ድርጅቱ የተዘጋ ከሆነ ሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያው ተመላሽ የተደረገበትን


ደብዳቤ ማቅረብ፤

• ከአንድ በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ መኖሩ ከታወቀ ይህንን የሚያሳይ ማስረጃ፤
የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ፤
• አስተላላፊውና የሚተላለፍለት ግብር ከፋይ /አዲሱ ተጠቃሚ/ መስማማታቸውን
የሚያሳይ ለየብቻ በእያንዳንዳቸው የተጻፈ ደብዳቤ ከሙሉ መረጃቸው ጋር በማመልከቻ
ለግብር ማዕከሉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

General crimes related to my receipt.


1. Any tax payer who has the obligation to give a receipt has committed a
purchase without receiving a receipt will be fined from 25,000.00 (twenty
five thousand birr) to 50,000.00 (fifty thousand birr) and imprisonment of 3-5
years.
2. Anyone who registers different prices on copies of the same receipt given
in one market and lower the selling price will be punished by 100,000.00 birr
and 5 to 7 years imprisonment.

3. If the actual price of the sale exceeds 100,000.00 birr (one hundred
thousand birr) the punishment based on this ordinary number (2) will be the
maximum amount of money seen on the recipients and imprisonment of
seven to ten years.
4. A person who gives or receives a receipt without shopping will be
punished by a fine of 100,000.00 birr to 200,000.00 birr and imprisonment of
seven to ten years.
5. The penalty imposed in this ordinary number (4) is equal to the amount of
money above 200,000.00 birr (two hundred thousand birr) will be imposed
on this ordinary number (1) by a fine equal to the amount received and
imprisonment of ten years to fifteen years.
6. A person who prints a tax receipt without the permission of the authorities
will be punished by a fine of 300,000.00 to 500,000.00 (five hundred
thousand birr) and imprisonment of two to five years.
7. If a person who is found guilty according to the above row number (6) is
found guilty for the second time, the printing machine and the printing
company will be confiscated and his business license will be canceled.
M.O.R East Addis Ababa Branch
የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የሚፈቀድባቸው እና የማይፈቀድባቸው ሁኔታዎች

የታክስ መክፈያ ጊዜን ስለማራዘም

ታክስ ከፋዩ በታክስ ሕግ መሠረት የመክፈያ ጊዜው የደረሰ ታክስ የመክፈያ ጊዜው እንዲራዘምለት
ለባለሥልጣኑ የጽሑፍ ማመልከቻ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት ማመልከቻ በሚቀርብበት ጊዜ
ባለሥልጣኑ በቂ ምክንያት መኖሩን ካረጋገጠ ታክስ ከፋዩ የታክስ ከፋዩ የታክስ መክፈያ ጊዜውን
ሊያራዝምለት፤ ወይም ባለሥልጣኑ በሚወስነው መሠረት ታክሱን በመከፋፈል በተወሰነ ጊዜ ውስጥ
እንዲከፍል ሊያደርገው ይችላል፡፡

ባለሥልጣኑ በዚህ መሠረት ለቀረበው ማመልከቻ የሰጠውን ውሳኔ የሚገልጽ የጽሑፍ ማስታወቂያ ለታክስ
ከፋዩ ይሰጠዋል፡፡ ታክሱን በመከፋፈል በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲከፍል የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ የአንድን
ጊዜ ክፍያ ካልከፈለ ታክስ ከፋዩ ክፍያውን ባቆመበት ጊዜ ያለውን ቀሪ ክፍያ በሙሉ እንዲከፍል
ባለሥልጣኑ ወዲያውኑ እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡ የታክስ መክፈያ ጊዜው እንዲራዘም ወይም ታክሱን
በመከፋፈል በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንዲከፍል የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ በዘገየው ክፍያ ላይ ከመጀመሪያ
የታክስ መክፈያ ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ወለድ የመክፈል ግዴታውን አያስቀርም፡፡

የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች

• የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት የሚፈቀደው:-

ታክስ ከፋዩ የታክስ ዕዳውን በአንድ ጊዜ መክፈል የማይችል ሲሆን፣

ታክስ ከፋዩ በታክስ ማስታወቂያ ወይም የታክስ ስሌት ማስታወቂያ በደረሰው ጊዜ በከፍተኛ የስጋት
ደረጃ ውስጥ የማይገኝ መሆኑ ሲረጋገጥ፡፡

• በከፍተኛ የሥጋት ደረጃ የተለየ፣ ሀብት በዕዳ የተያዘበት ወይም ንብረት እንዲሸጥ ጨረታ የወጣበት ታክስ
ከፋዩ ዕዳውን ለመክፈል ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ ለዕዳው ተመጣጣኝ የሆነ የባንክ ዋስትና ሲያቀርብ ብቻ
ይሆናል፡፡

የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የማይፈቀድባቸው ሁኔታዎች

የጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት የማይፈቀድባቸው ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው:-


• በታክስ ማስታወቂያ ጊዜ መከፈል ያለበት የታክስ ዕዳ ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስ ወይም ከተከፋይ ሂሳብ ላይ
ተቀንሶ ገቢ መደረግ ያለበት ሲሆን፣

• ታክስ ከፋዩ አስቀድሞ የክፍያ ጊዜ ስምምነት የተሰጠው ሆኖ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ከአቅም
በላይ የሆነ ምክንያት ሳይኖር ዕዳውን ያልከፈለ ሆኖ ሲገኝ፣

• የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ የተጠየቀበት የታክስ ዕዳ መጠን እንደ ታክስ ከፋዩ አመዳደብ ከተቀመጠው
አነስተኛ የገንዘብ መጠን በታች ከሆነ፣

• ታክስ ከፋዩ:-

በታክስ ዘመኑ በከፍተኛ የሥጋት ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነ፣

ለዕዳው ማስከፈያ ሃብት እና ንብረት የተያዘበት ከሆነ፣

በዕዳው የተያዘበትን ንብረት ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ የወጣበት ከሆነ፣ የክፍያ


Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር / 
 

መልካም ዜና ለደንበኞቻችን በሙሉ!


ነሐሴ 11፣ 2014 (ገቢዎች ሚኒስቴር)
በተለያዩ ጊዜያት የገቢ እና የታክስ አስተዳደርን በተመለከተ በርካታ አዋጆች፣ ደንቦች፣
መመሪያዎች እና ሰርኩላሮች ወጥተው በስራ ላይ መዋላቸው ይታወቃል፡፡
እነዚህ ሰነዶች በጣም ብዙ በመሆናቸው ብሎም በአንድ ላይ ለማግኘት የማይቻሉ
በመሆናቸው ሁሉም አመራር፣ ባለሞያዎች እና ደንበኞቻችን አውቀዋቸው እና ሰነዶቹንም
በእጆቻቸው ይዘው ስራቸውን ለመስራትም ሆነ መብቶቻቸውን በአሰራሩ መሰረት
ለማስከበር ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች ይህን ችግር በመገንዘብ ዛሬ ላይ በስራ ላይ ያሉት አዋጆች፣
ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ሰርኩላሮችን በአንድ ላይ የያዘ ስብስብ የገጽ ብዛታቸው 2,242
የሆኑ እንደየርእሰ ጉዳያቸው በ 6 ጥራዝ በማሳተም ለተጠቃሚ አካላት በሀርድ እና በሶፍት
ኮፒ ማሰራጨት የጀመረ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ላቀ አያሌው ገልጸው
ደንበኞች ሰነዶቹን በማንበብ እና ጥቅም ላይ በማዋል የአሰራሮች ተጠቃሚ እና ተገዥ
እንዲሆኑ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በአንድ ላይ ተዘጋጅተው የታተሙ ሰነዶች ዝርዘርም የሚከተለው ነው፡-
1. የገቢ ግብር ሕጎች እና ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 744
2. የታክስ አስታዳደር ሕጎች እና ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 357
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕጎች እና ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 605
4. የኤክሳይዝ ታክስ ሕጎች እና ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 170
5. የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ፣ የቴምብር ቀረጥ እና የወጪ መጋራት ሕጎች እና
ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 152
6. የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ታርክ ሕጎች እና ሰርኩላሮች ገጽ ብዛት … 214
ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አክለውም ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች በሙሉ አሰባበስቦ እንዲዘጋጁ
ለማድረግ በውስጡ ጠንካራ አባላት ያሉት አንድ ቡድን በማዋቀር ቡድኑ እረዥም ጊዜ
ወስዶ አሁን በስራ ላይ ያሉትን አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ሰርኩላሮች በማሰባሰብ
በጥራት እንዲታተሙ በማድረጉ በገቢዎች ሚኒስቴር ስም ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል፡፡
የሰነዶቹ ስርጭት በትላንትናው እለት ሚኒስቴሩ የ 2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና
የ 2015 በጀት ዓመት እቅድ ውይይቱን አድርጎ ባጠናቀቀበት ወቅት ለሁሉም የገቢዎች
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስራ አስኪያጆች እና ምክትል ስራ አስኪያጆች በማስረከብ
ተጀምሯል፡፡
M.O.R East Addis Ababa Branch
 

የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ለማግኘት ማሟላት ያለበት ቅድመ ሁኔታ


1. ማንኛውም ታክስ ከፋይ የማንዋል ደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ሲጠየቅ ሊቀርብ
የሚገባ ማስረጃ፡-
ሀ. በኢንቨስትመንት ሂደት ላይ ያለና የንግድ ሥራ ያልጀመረ ሲሆን ከተከፋይ
ሂሳብ
ላይ ለተቀነሰ ግብር የሚሰጥ ደረሰኝ ለማሳተም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና
የኢንቨስትመንት ሰርተፊኬት፤
ለ. ከተከፋይ ሂሳብ ላይ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ውክልና
የተሰጣቸው ድርጅቶች፣ መሥሪያ ቤቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴዎች ከተከፋይ
ሒሳብ ላይ ለተቀነሰ ግብር የሚሰጥ ደረሰኝ ለማሳተም የግብር ከፋይ መለያ
ቁጥር፤
ሐ. የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላወጣና የመደበኛ ሽያጭ ያልጀመረ ሰው የሙከራ
ምርት ለመሸጥ ወይም ከግንባታ ሥራ የተረፈ ዕቃ ለመሸጥ የሚያገለግል ደረሰኝ
ለማሳተም ከላይ በተራ ቁጥር () (ሀ) ከተገለጸው በተጨማሪ ምክንያቱን
የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
መ. በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ ታክስ ከፋይ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ሕጋዊ
የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ ምስክር ወረቀት (ሰርተፊኬት)፤
ሠ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀንሶ ገቢ የማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት ወኪል
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ አለበት፤
2. በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራም ሆነ ያልተሠማራ ሰው በሚታተመው ደረሰኝ
ላይ የድርጅቱ የንግድ ምልክት (logo) እንዲካተት ጥያቄ ያቀረበ እንደሆነ
ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የንግድ ምልክቱ የተመዘገበበትን ማስረጃ
ማቅረብ አለበት፤
3. በተራ ቁጥር (1) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄ
የሚያቀርበው ሰው በሚታተመው ደረሰኝ ላይ የንግድ ስም እንዲጠቀስ
በሚፈለግበት ጊዜ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ፤
4. ከላይ በተራ ቁጥር (1) የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ
የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የማንዋል ደረሰኝ ሊይዝ የሚገባውን መረጃ
ያካተተ እና ማሳተም የሚፈለገውን የደረሰኝ ብዛትና የዓይነት ናሙና ማቅረብ
አለበት፤
5. ማንኛውም ደረሰኝ ለማሳተም ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ለማሳተም
የሚፈልገውን የማንዋል ደረሰኝ ዓይነትና ብዛት ከደረሰኝ ናሙናው ጋር በደረሰኝ
ህትመት መጠየቂያና መፍቀጃ ቅፅ ላይ በመሙላት ታክስ ለሚከፈልበት
ቅ/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
ከላይ በተራ ቁጥር (4) እና (5) መሠረት ታክስ ከፋዩ እንዲታተም የሚፈልገውን
የደረሰኝ ናሙና ሲያቀርብ የደረሰኝ ናሙና ቅፅ ጋር በማመሳከር ደረሰኙ
ሊይዛቸው የሚገቡ መረጃዎችን ስለማሟላቱ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት
መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

You might also like