You are on page 1of 4

መግቢያ

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት የመ/ቤቱ የፋይናንስ አሰራር

ጤናማና ከብክነት የፀዳ እንዲሆንና ተግባራትን በብቃት መወጣት እንድንችል በተዘረጋው የውስጥ ቁጥጥር

ስርዓትና በወጡት አዋጆች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎችና የአሰራር ስርዓቶች መሰረት ስራዎች መከናወናቸውን

ኦዲት አድርጎ ማረጋገጥ ነው፡፡ የስራ ክፍሉ የተዋቀረው ዘመናዊ የኦዲት አተገባበር ሂደትን በመከተል የመ/ቤቱን

አሰራርና የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት በመገምገምና የስጋት ተጋላጭነት በመፈተሸ ለመ/ቤቱ ተጨማሪ እሴት

የሚጨምር ውጤታማ የሆነ ስራ ሊከናወን የሚችልበትን ዘዴ ለስራ አመራሩ የምክር አገልግሎት በመስጠት

ለመ/ቤቱ አላማ አስተዋፆ ማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም በዓመቱ ዕቅድ ውስጥ አብዛኛውን ምርመራ የሚያተኩረው የፋይናሻል እንቅስቃሴዎች አፈፃፀም

ኦዲት ላይ ቢሆንም የመኪና አያያዝና የነዳጅ ፍጆታ አጠቃቀም በየሩብ ዓመቱ ለመከታተል በተያዘው ዕቅድ

መሰረት እስከ ታህሳስ ያለውን የነዳድ አጠቃቀም የተመረመረበት መሆኑን እና የዳኝነት ገቢ ሂሳብ በአግባቡ

ተሰብስቦ ወደ ባንክ እየገባ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በበጀት ዓመቱ የበጀት አስተዳደርና በጀት ዘግይቶ በመደልደሉ እና በጀትም አይቤክስ ላይ ባለመፃኑ ምክንያት

የክፍያ መረጃዎች ከምዝገባ/TR/ና ከየተቀፅላቸው/ledger መናበብና ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳብ ኦዲት

በማድረግ ስለትክክለኛነታቸው ማረጋገጥ አለመቻሉ እንደ ችግር የተወሰደ ከመሆኑ ውጪ ጥሩ የመረጃ

አደረጃጀትና አሰራርን የተከተለ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በ 2012 በጀት አመት የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት

ዳይሬክቶሬት ሊያከናውናቸው ካቀዳቸው ዕቅዶች ውስጥ በ 6 ወር ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት

አቅርቧል፡፡

የሪፖርቱ ዓላማ ፡-

የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ለመ/ቤቱ የተመደበ በጀት ወጪ ቆጣቢና የፋይናንስ መመሪያ

በሚያዘው መሰረት መሰራቱን እንዲሁም ግዢዎች ከማጭበርበር የፀዳ ጥራቱን የጠብቀ መሆኑን ለማጣራት፤
መንግስት ለሀብትና ለንብረት ጥበቃ ያወጣቸውን አዋጆች፤ ደንቦችና ህጎች ጠብቆ ግዥ እየተፈፀመ መሆኑን

ለማጣራትና አዋጆችንና ደንቦችን የጠበቀ መሆኑን ለማረጋገጥ፤ እቅድን መሠረት ያደረጉ ስራዎች እየተሠራ

መሆኑን ለማጣራትና የስራ ስህተቶችን እንዲታረሙ ለማድረግና ያልተሠሩ ሥራዎችም ካሉ ለማረምና

በተገኙ ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምት እንዲወሰድ ማድረግ ነው፡፡

የሪፖርት ወሰን ፡- ከሐምሌ 1/2011 እስከ ታህሳስ 30/2012 ዓ.ም ድረስ ይሆናል፡፡

የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት የ 2012 በጀት ዓመት የ 6 ወር ሪፖርት

የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በበጀት አመቱ ያከናወናቸው ተግባራት እንደሚከተለው አቅቧል፤

1. የ 2011 በጀት ዓመት ውጤት ተኮር ዕቅድ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል

ተላልፏል፤

2. ከሐምሌ 1/2011 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ድረስ የየወሩ የፋይናንሻል ኦዲት

ምርመራ ተደርጎ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ተልኳል፤

3. የ 2011 በጀት ዓመት የገቢና የወጪ ሂሳቦች ምርመራ ተደርገዋል፤

4.የነዳጅ አጠቃቀም በሚመለከት ነዳጅ የሚሞላላቸው በጌጅ መሰረት መሆኑን በመመርመር

ግኝቶች ላይ እርምት እንዲወሰድ ተደርጓል፤

6. የዳኝነት የዋስትና እና የዕለት ገቢ ሂሳብ አሰራር ወጥ እንዲሆን የድጋፍና ክትትል

ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ድጋፍና ክትትል ከተደረገባቸው ከፍተኛ ፍ/ቤቶች

ውስጥ ሀላባ፤ ዱራሜ፤ ወላይታ ዞን ከ/ፍ/ቤት፤ ወላይታ ምድብ ችሎትና ሆሳዕና ሲሆኑ

በታዩ የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ አጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና የምክርና ድጋፍ

አገልግሎት ተሰጥቷቸዋል፤

8. የምክርና ሙያ አገልግሎት ተሰጥቷል፤

 ለግ/ፋ/ን/አስ ዳይሬክቶሬት፤ ለጨረታ ኮሚቴዎች፡፡

ያልተከናወኑ ስራዎችን በሚመለከት


1. የንብረት ምርመራ አልተደረገም፤

2. የበጀት አስተዳደር ኦዲት አልተሰራም፤

3. የዳኝነትና፤የዋስትና እና የዕለት ገቢ ሂሳብ አሰራር ወጥ እንዲሆን የድጋፍና ክትትል

ሰራዎች በተለያዩ ዞኖች ድጋፍና ክትትል የተደረገ ቢሆንም ቀሪ እንደ ዕቅድ ከተያዙት

ውስጥ ያልተካተቱ ከፍተኛ ፍ/ቤቶችና ምድብ ችሎቶች መኖራቸው፤

ያልተከናወኑበት ምክንያት

1. ንብረትን ምርመራ በመ/ቤቱ ደረጃ ያላለቀ በመሆኑ፤

2. የበጀት አስተዳደር ኦዲትን በሚመለከት አይቤክስ ላይ በጀት ያልተጫነ በመሆኑ፤

3. የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን በሚመለከት በተለያዩ ምክንያት ያልተከናወነ በመሆኑ

በቀጣይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በበጀት አመቱ ተግዳሮት የነበሩ ጉዳዬችን በሚመለከት፤

1. በኦዲት ውጤት አሰተያየት ላይ ወቅታዊ እና ተገቢ ምላሽ ያለመስጠት፤

2. በጀት በወቅቱ ተደልድሎ ባለመጫኑ ምክንያት፤

3. በየወሩ በሚቀርበው የፋይናንሻል ኦዲት ግኝቶች ላይ አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ

ያለመውሰድ በስፋት የሚታይ ድክመት መሆኑ፤

4. በተደጋጋሚ ወጪዎችን ተገቢ ባልሆነ ኮድ ተመዝግቦ መገኘት፤

5. ወርሃዊ የሂሳብ ምርመራ ለማድረግ ቲአር በጊዜው ፕሪንት አድርጎ አለመስጠት፤

በበጀት አመቱ የታዩ ጠንካራ ጎኖች

1. የ 2012 በጀት ዓመት አጠቃላይ ወርሃዊ የፋይናሻል የኦዲት ሪፖርት በተቀመጠው

እስታንዳርድ መሰረት ባይላክም ነገር ግን TR ሳይጠበቅ ዋናውን ሰነድ መሰራቱ፡፡

You might also like