Professional Documents
Culture Documents
ም የመነሻ እቅድ
መግቢያ፡-
የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ መንግስት የ 5 ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመንድፍ በርካታ ተግባራት
በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡ ስለሆነም የልማት ፣ የመልካም አስተዳደርና የመ /ስ/ግንባታ ተግባራትን በቀጣይነትና
በዘላቂነት ለመተግበር የተደራጀ የልማት ሰራዊት ፈጥሮ መገንባት አማራጭ የሌለዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም የጥራት
ያለው ትምህርት አለመስጥ፣ በት/ቤቶች ስታንዳርዱን የጠበቀ ክፍል፣ወንበርና ሌሎች የትምህርት መሳሪያዎች
አለመኖር ከስር መሰረቱ ለመፍታት ትምህርት ሙያተኛውና የመረሱ የልማት ሰራዊት አደረጃጀት በማዋቀር
ተግባራትን መፈጸም ከተጀመረ ዉሎ አድሯል ፡፡
በመሆኑም ከማኔጅመንት ኮሚቴ እስከ 1 ለ 5 አደረጃጀት በማደራጀትና ወደ ስራ በማስገባት ባለፈዉ ዓመት የተሻለ
ጅምር ስራ ተሰርቷል ፡፡ በዚህ በጀት ዓመትም ሁሉን የጽ/ቤት ተግባራት በኃላፊነት ለመፈፀም ያመች ዘንድ ይህን
የማኔጅመንት ኮሚቴ እቅድ ተዘጋጅቷል ፡፡
የዕቅዱ ዋና ዓላማ
የእቅዱ አስፈላጊነት
ግንባታ ማዕከል ያደረገ ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ጠንካራ ጎኖቻችንን ማጎልበትና ከደክመቶቻችን
ፈጥነን እንድንወጣ የሚያስችል የማስተካከያ ስራ በመስራት ደረጃ በመለየት እዉቅና በመፍጠር ማኔጅመንቱን የስራዊት
ቁመና በማላበስ ትምህርት ሙያተኛውና የመረሱ የልማት ሰራዊት ለመፍጠርና ለመገንባት ነው፡፡
ግብ 1 የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚን አምሮው የሚፀየፍ የልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ በመስሪያ ቤታችን
እንዲገነባ አልሞ የሚሰራ የለዉጥ ሀዋሪያ የሆነ ሰራተኛ መፍጠር
የሚከናወኑት ተግባራት
ሁሉን የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች ከእቅድ ዝግጅት እስከ ማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ተግባራትን በበላይነት
እንዲፈፅሙና የሀላፊነት መንፈስ እንዲላበሱ ማድረግ
ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በተከታታይ ለማድረግ ሰራተኛዉን ደረጃ መለየት
የእለት ግምገማ በማድረግ በየቀኑ ሞዴል ሰራተኛ መፍጠር
በየሳምንቱ በየወሩ ኮከብ ሰራተኞችን መለየትና ማበረታታት
አጫጭር ስልጠናዎች በማዘጋጀት በጽ/ቤቱ ያሉ የአመለካከት፣ የክህሎት፣የአስ /አደረጃጀት ችግሮችን በየጊዜዉ መፍታት
፡፡
የጽ/ቤታችን የሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለቅሞ በመለየት ራሱን የቻለ ዕቅድ በማዘጋጀት ችግሮች
መፍታትና መላዉ ሰራተኛ አገልግሎት አሰጣጡን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል ፡፡
ምርጥ ተሞከክሮችዎችን መቀመርና ማስፋፋት
ግብ 4 በስድስቱም የስራ ሂደቶች ያሉትን አደረጃጀቶች በጥብቅ በመፈተሸና አቅም በመገንባት የልማት ሰራዊት
ማፍሪያ ማዕከል ማድረግ ፡፡
የ 1 ለ 5 ዕለታዊ ዉይይት በዕቅዱ መሰረት እየገመገሙ አፈፃፀሙን ለዉጤት በሚበቃ ሁኔታ መምራት
የስራ ቡድን አደረጃጀት በሳምንቱ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ
በስራ ሂደቱ ባሉ ባለሙያዎች ተቀራራቢ እውቀትና ክህሎት ለመማማርና እድገት ፕሮግራም ወደ ተቀራረበ
አፈጻጸም እንዲኖራቸው ማድረግ
በሁሉም የስራ ሂደቶች ተግባራትን በልማት ሰራዊት ግንባታ ስራዎች እንዲፈጸሙ ማድረግ
ማኔጅመንት ኮሚቴ ዋና ዋና የአሰራር ስልቶች
የማኔጅመንት ኮሚቴው የየሳምንቱ ተግባራትን መሰረት ያደረገ የስራ ግምገማ ሰኞ ሰኞ ዉይይት በጽ /ቤት ኃላፊው
በዋነኝነት ሚካሄድ ሲሆን ጽ/ቤት ኃላፊ በሌለበት በጽ/ቤት ተወካይ እንዲመራ ይደረጋል ፡፡
አካሄድን በሚመለከት
ሁሉም ስራ ሂደት ከቁልፍና አበይት ተግባራት አንጻር አጭር ሪፖርት በማቅረብ የስራ ግምገማ እንዲካሄድ ማድረግና
የቀጣይ ሳምንት የትኩረት አቅጣጫ ወይም ቸክሊስት ለሂደቶች እንዲደርሱ ማድረግ ፡፡
በሁሉም የስራ ሂደቶች ያሉ ሁሉም ባለሙያዎች በተገኙበት ጥቅል የሴክተር አፈጻጸምን በወር አንድ ቀን ይገመግማል ፡፡
የማኔጀመንት ኮሚቴው በወር መጨረሻ ለእቅድ ዝግጅት በሲ/ሰርቪስ የለውጥ ኮሚቴ የሚወጣ ደረጃ መሰረት በማድረስ
ያፀድቃል፡፡
የሁሉም የስራ ሂደት በየሩብ ዓመቱ ተግባርን መሰረት ያደረገ የስራ አፈጻጸም ሂስና ግለሂስ በማካሄድ ፈጻሚውን ክፍተት
መሙላት ፡፡
የክትትል ድጋፍ ሪፖርት ስርዓት
የሁሉም የስራ ሂደቶች አባላት የተገመገመ የስራ ሂደት ሪፖርት ለማኔጅመንት በማቅረብ ይገመግማል
ሁሉም የስራ ሂደት አስተባባሪ የሁለት ሳምንት ሪፖርት ለግምገማ ያቀርባል ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
የሳምንቱ ኮከብ ሰራተኛ ይመርጣል በማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲለጠፍ ያደርጋል ፡፡
በየወሩ ኮከብ የስራ ሂደት በማናጅመንት ኮሚቴ ይገመገማል ያሳውቃል፡፡