You are on page 1of 67

መግቢያ

1
ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝ በመሆኑ በየጊዜው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ዕውቀትና ክህሎትን
ለተማሪዎች በተለያዩ መንገዶች ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው፡፡ የተማሪዎችን የማመዛዘን የመፍጠርና የመመራመር አቅም ከፍ በማድረግ
ሁለንተናዊ ስብዕና ያላቸው ዜጎች ሆነው ወደ ህብረተሰቡ በመቀላቀል ሀገርን የመገንባትና የማሳደግ ኃላፊነት የሚሰማቸው ምርታማና
በመልካም አስተዳደር መስፈን ትልቁን ሚና መጫወት የሚችሉ በማድረግ የመደበኛውን ትምህርት ለማገዝ በት/ቤቶች የተጓዳኝ
ትምህርት አደረጃጀቶች ተፈጥረው እየተሰራባቸው መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ዕውነታዎች ወደ ተግባር ለመለወጥ ይቻል ዘንድ በተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ክፍል ውስጥ በሚሰጥ ትምህርት
ብቻ ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማውጣት እንደማይቻል ይታመናል፡፡ በክፍል ውስጥ የተማሪ፣ የመምህራንና የሥርዓተ ትምህርቱ መስተጋብር
ቆይታው በተወሰኑ እጅግ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው ፤ የግንኙነት ጊዜ እጥረቱ በሚፈለገው ደረጃ የሚፈለገውን እውቀት ማስጨበጥ
የማያስችል ነው፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ በኪነጥበብ በስፖርት በተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች በንቃት
በመሳተፍ ጊዜያቸውን በቁምነገር ላይ ሊያሳልፉ ይገባል፡፡ይህ ሲሆን የዕውቀት አድማሳቸው ክህሎታቸውና አመለካከታቸው በሚፈለገው
ደረጃ ይዳብራል፡፡ ከዚህ አንፃር የተጓዳኝ ትምህርት ፕሮግራሞችን ከመደበኛው የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ሂደት ጎን ለጎን
በማደራጀት የተማሪዎችን ሁለንተናዊ እድገት ለማሟላት እንዲቻል እንደሌሎች አገሮች ሁሉ በኢትዮጵያም ዘመናዊ የትምህርት ስርዓት
ከተጀመረ አንስቶ እንቅስቃሴዎች ሲካሄድ ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሁሉም ት/ቤቶች የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀትን በመጠቀም
በሚፈለገው መጠን ውጤታማ ስራዎችን ሰርተዋል ለማለት አያስደፍርም፡፡

ስለተጓዳኝ ትምህርት ጠቀሜታ አሰራርና አፈፃፀም በቂ ግንዛቤ ያላቸው ት/ቤቶች የተሻለ በመስራት ውጤት ለማስመዝገብ የቻሉ ሲሆን
ሌሎች የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት አሰራርና አፈፃፀም በተገቢው ግንዛቤው የሌላቸው ግን በሚፈለገው ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ
ያልቻሉበት ሁኔታ ታይቷል፣

የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት አመጣጥ ፣ አሠራርና ጠቀሜታ በተለያዩ አጋጣሚዎችና ሰነዶች ሲገለጽና ሲቃኝ የኖረ ነው ፡፡ ሆኖም
በሀገራችን ብሎም በከተማችን የሚጠበቀውን ያህል ስኬታማ ነው ማለት ያዳግታል ፡፡በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የክበባት ህይወትና
ድምቀት ቅኝት እንደሚያስፈልገው በርካታ አመላካቾች ይስተዋላሉ ፡፡ ለአብነት ያህልም የሚከተሉትን እጥረቶች እንጠቅሳለን ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ፣ በተለይም ክበባት የባለቤትና የአደረጃጀት ክፍተት አለባቸው ፣ ወጥ የሆነ መመሪያ የላቸውም ፣

 አደረጃጀታቸውም ሆነ አፈፃፀማቸው በእውቀት ፣ በተጠያቂነትና በአሳታፊ መዋቅር ላይ የተመሠረተ ነው ለማለት ያዳግታል ፣

 በእቅድ የተያዘና በመርሀ ግብር የተገዘ የአፈፃፀም ፣ የክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ እጥረት ይታይበታል ፣

 የተደራጀ ወቅታዊ ተገቢ የመረጃ አያያዝ ችግር ይንፀባረቃል፣በአደረጃጀት ፣ በአተገባበርና በተጨበጠ ስኬት ላይ የተመሠረተ
የማትጊያና የእውቅና መስጫ ጠንካራ ሥርዓት የለውም፣

 የግበአት እጥረት ፣ የበጀት አለመመደበና በፍትሃዊነት ያለመጠቀም ችግሮች ይታያሉ ፣

 ከባለድርሻ አካላት ጋር ተገቢ የሆነና ዘላቂነት ያለው የትስስርና የመዋቀር ግንኙነት ክፍተት አለበት ፣

2
 የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀትና አተገባበርን በየጊዜው ከሚስተዋለው የሣይንስና የቴከኖሎጂ እድገትና ለውጥ ጋር እየፈተሹ ፣
እያሻሻሉና እያደራጁ አለመጓዝ ወዘተ ቁልፍ አመላካች እጥረቶች በየጊዜው ይስተዋላሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የግንዛቤና ትኩረት ሰጥቶ ወደ ተግባር ያለመግባት ችግሮችን ለመፍታት በቢሮ ደረጃ አንድ ወጥና ግልፅ የሆነ ማንዋል
ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ የት/ቤቶችን ግንዛቤና አረዳድ በተቀራራቢ ደረጃ ላይ እንዲገኝ ማድረግና
ለተፈጻሚነቱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በድጋፍና ክትትል ማገዝ በሚያስችል መልኩ ለማዘጋጀት ተፈልጓል፡፡

በመሆኑም ቀደም ሲል በ 1989 ዓ.ም. በትምህርት ሚ/ር የተዘጋጀውን የተጓዳኝ ትምህርት የአፈፃፀም መምሪያ (ማኑዋል) መነሻ
በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የሚመራቸው የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ት/ቤቶች እንዲጠቀሙበትና
ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር እንዲችሉ ይህ የአፈፃፀም መምሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

ዓላማ

የመምሪያው ዋና ዋና ዓላማዎች

 ከት/ቢሮ እስከ ት/ቤቶች የሚገኙ አመራሮች አደረጃጀቱን አሰራሩንና አፈጻጸሙን በዕውቀት ለመምራት እንዲችሉ አቅም
በመፍጠር፤

 በተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ተሳትፊ የሚያደርጉትና ቀጥታ የሚመለከታቸው መምህራንና ተማሪዎች መምሪያውን
እየተጠቀሙ ዕቅድን፤ መረጃን፣ ሂደትንና ውጤትን መሠረት ያደረገ ስራ እንዲሰሩ በማስቻል፤

 ተማሪዎች የሥራ የአመራር ባህልንና የተለያዩ ክህሎቶችን አዳብረው ዝግጁ በመሆን ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ ሊሰጡ በሚችሉ
ስራዎች ላይ በቂ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማድረግ

በት/ቤቶች ተቀራራቢ የተጓዳኝ አደረጃጀት አፈፃፀምና አሰራር እንዲኖራቸው ማስቻልና የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎች የበለጠ
እንዲረዱትና ወደ ተግባር እንዲለውጡት ማስቻል ነው፡፡

ክፍል አንድ

1. የተጓዳኝ ትምህርት ፅንሰ ሀሳብ፣ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ

1.1. የተጓዳኝ ትምህርት ፅንሰ ሀሳብ

የተጓዳኝ ትምህርት ከክፍል ውጭ በተማሪዎችና በመምህራን ፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ከመደበኛው የትምህርት ፕሮግራም
ወይንም የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ሂደት ውጭ ባለው ሰዓት የሚፈፀም ነው፡፡ የተጓዳኝ ትምህርት ትርጉም

3
በእንግሊዝኛው ቋንቋ የተለያዩ ስያሜዎች የተሰጠው ሲሆን የተወሰኑ አገሮች ‹‹co-curricular ›› ሲሉት ሌሎች ደግሞ
‹‹Extra-class ›› ፣ ‹‹extra-curricular›› እንዲሁም‹‹Student Activities ይሉታል፡፡

በመሠረታዊ በቀደምት ዓመታት ፕሮግራሞቹ በቀጥታ ከተዘጋጀው በክፍል ውስጥ ከሚተገበረው የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ጋር
ያልተካተቱ ሀሳቦችን የያዘ በመሆኑ ይዘቱ ስለሚለይ እንደተጨማሪም አድርገው በማየት ‹‹Extra-curricular ›› የሚል ስያሜ
የሰጡት መሆኑ ይታወቃል፣ ነገር ግን ቴክኖሎጂ እያደገ የአስተሳሰብ አድማስም እየሰፋ በመጣበት በአሁኑ ወቅት የሀገራችን
የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ የተጓዳኝ ትምህርትን ያካተተና ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት በተጨማሪ እነዚህ ተግባራት
የሚከናወኑበት የራሱ ጊዜ የተመደበ በመሆኑ የተጓዳኝ ትምህርትን ሊገልፅ የሚችለው የእንግሊዝኛ ቃል ‹‹ co-curricular ››
የሚለው ገለጭ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

‹‹ co-curricular ›› የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል በሀገራችን ‹‹የተጓዳኝ ትምህርት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ይህም
ከክፍል ውስጥ ትምህርት ውጭ በመደበኛው የትምህርት አሰጣጥና ስልት መሠረት ከሚፈፀሙ ተግባራት በተጨማሪ የተማሪዎችን
ፍላጎት መሠረት በማድረግ የሚከናወን ተግባር ነው፡፡በመሆኑም መምህራን የተጓዳኝ ትምህርትን ተማሪዎችን እንደ
ዝንባሌያቸው በማስተባበርና በመምራት የሚፈለገውን የባህሪ ለውጥ በተማሪዎች እንዲፈጠር ለማድረግና ተማሪዎች ተጠቃሚ
የሚሆኑበትን ሁኔታ በትምህርት ቤቶች የማመቻቸት ስራ ያከናውናሉ፡፡

1.2. የተጓዳኝ ትምህርት ጠቀሜታዎች

የተጓዳኝ ትምህርት የሚደራጁበት ዓላማ ከአጠቃላይ ትምህርት ማዕቀፋችን ፋይዳ ተነጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ በተገቢው የተደራጁና
ተግባር ውስጥ የገቡ አደረጃጀቶች የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል ፣

1. በክፍል ውስጥ የሚሰጠውን የንድፍ ሃሳብ ትምህርት በተግባር መረዳት እንዲችሉ በማድረግ የግልና የማህበራዊ ዕድገትን
ያፋጥናል ፣

2. የሰብዓዊ ግንኙነት ክህሎትን በማዳበር ሌሎችንም የማክበርና የመከበር ስርዓትን ይማሩበታል ፣

3. ራስን የመግለፅ ከሰዎች ጋር የመወያየት ፣ የማመንና የማሳመን፣ የማወቅና የማሳወቅ፣ የውይይት ስነስርዓቶችን የማወቅ፣ ውሣኔ
የመስጠትንና በውይይት የመተማመንን ሂደትእነዲሁም አመራርን ሀላፊነትን ተጠያቂነትን ሁሉ እንዲማሩበትና እንዲለማመዱበት
ያግዛል ፣

4. የመቻቻል ባህልን በማዳበር ቅራኔዎችን በውይይት የመፍታትን ህግና ደንብ ስርዓት እንዲማሩበት ያግዛል፡፡

5. ለሥራ አክብሮት መስጠትን ፣ የጊዜን ጠቀሜታ መረዳትን ፣ ሥራ ማህበራዊ መሆኑን የመገንዘብና የቡድን ሥራን እንዲለማመዱ
ይረዳል ፣

6. የፈጠራ ችሎታ በማሳደግ ለቴክኖሎጂ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተማሪዎች ልዩ ልዩ ፈጠራዎችና ተሰጥዖ እንዲጎለብት
ያድርጋል፣

7. በትምህርት አቀባበላቸው ደከም ያሉ ተማሪዎች እንዲታገዙበት ያደርጋል፤

4
8. የት/ቤቱንና የህብረተሰቡን ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ፣

9. የወደፊት ሥራንና ሙያን የማስተዋወቅ ጠቀሜታ አለው ፣

10. አካባቢያዊ ፣ክልላዊ ፣ አገራዊና አለም አቀፋዊ የሆኑ ጉዳዮችንና አዳዲስ ክስተቶችን እንዲሁም ችግሮችንና ግኝቶችን የማስተዋወቅ
ጠቀሜታ አለው ፣

11. ጤናማ ዜጋ በት/ቤቶች ለማፍራት ያስችላል ፣

12. በስነምግባራቸው የበቁ የተሻለ ውጤት ባለቤት ሊሆኑ የሚችሉ ተማሪዎችን ኮትኩቶ ለሀገር ዕድገት፣ ለዲሞክራሲ ግንባታና
ለመልካም አስተዳደር መስፈን አስተዋፅዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ዜጐችን ማፍራት ያስችላል ፣

1.3. የተጓዳኝ ትምህርት ይዘትና ቅርፅ

የተጓዳኝ ትምህርት ምንጭ ከማህበራዊ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ባህልና ስነጥበብ ፣ስፖርትና ቱሪዝም፣ ወዘተ… የተገኘ
ነው፡፡ መሠረታዊ ሀሳቡ በክፍል ውስጥ ሊሰጥ ከተዘጋጀውና ከዚያም ውጭ ባሉ ማህበረሰባዊ ጉዳዮች የሚወሰድ በመሆኑ ወደ ተግባር
የሚለወጥና ጠቀሜታ ያለው አሰራር ሲሆን በማንኛውም የትምህርት ቤት ደረጃና የመማር ማስተማር ስራአጋዥ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ት/ቤቶች እንደ ራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ስርዓተ ትምህርቱን ወደ ተግባር ይለውጡታል ተብሎ የሚታመንባቸውን ጉዳዮች
በመለየት በተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች እንዲታቀፉ ያደርጋሉ፡፡ አደረጃጀቱ ለአመራር እንዲመችና የነበረውን የክበባት ያለ
ልክ መለጠጥ ለማስቀረት በት/ቤት ደረጃ የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት ቅርፅ በዚህ መምሪያ /ማንዋል/ ላይ ለማስቀመጥ
ተሞክሯል፡፡ በየአደረጃጀቱ ስር ተያያዥነት ያላቸው ተጨማሪ ተግባራትንና ክበባትን ማዋቀር የሚቻል ሲሆን በመምሪያው የቀረበው
መነሻ ሃሳብ መሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡ በተጨማሪም በ 1.3.12. የተዋቀረው ተማሪዎች አደረጃጀት ከክበባት በተለየ ሁኔታ
የሚደራጅ ይሆናል፡፡

1.3.1. የስፖርት ክበብ

ት/ቤቶች ወጣቱን በአዕምሮና በአካል ብቃት አዘጋጅቶና ኮትኩቶ ለማውጣት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ
በመሆኑ በስፖርት እንቅስቃሴዎችና ውድድሮች ተማሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሮአቸው እንዲያድጉ ለማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት
ነው፡፡ በዚህ አደረጃጀት ስር የሚተገበሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፡-

- አትሌቲክስ /ሩጫ ፣ውርወራ፣ ዝላይ… ወዘተ/ ፣

- ኳስ ጨዋታዎች ( የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ ፣ የቅርጫት ኳስ ፣የእጅ ኳስ ፤ የጠረጴዛ ኳስ….. ወዘተ)

- የጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች

- የሀገር ባህል ስፖርታዊ እንቅስቃሴና

- ዘመናዊ የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን ያጠቃልላል፣

የክበቡ ዋና ዋና ተግባራት

5
የተማሪዎችን አካልና አዕምሮአዊ ዕድገት በሚፈለገው መልኩ እንዲጎለብት ማድረግ መሰረታዊ ዓላማው ሲሆን ክበቡ
የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

 ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በየዘርፉ መመዝገብ፤

 በየዘርፉ ብቁ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ስልጠና መስጠት፤

 በየስፖርት ዓይነቱ የፕሮግራም ድልድል በመስራት የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን መምረጥ፤

 የት/ቤቱን የውስጥ ውድድር መርሃ ግብር ማዘጋጀትና ወደ ተግባር መግባት፤

 በወረዳ፤ በክ/ከተማ ፤በከተማ እንዲሁም በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጁ ውድድሮች ራስን ማብቃትና መሳተፍ፤

 አስፈላጊውን የማበረታቻ ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ፤

 የላብ መተኪያ እና ለተለያዩ ቁሳ ቁሶች የሚሆን በጀት ማፈላለግና ተግባራዊ ማድረግ፤

 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ሊወዳደሩ የሚችሉበትን ዘርፍ መለየት፣ ማብቃትና በውድድር ተሳታፊ
የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

1.3.2. የኪነ-ጥበብ ክበብ፤

በክበቡ ሊካተቱ የሚገባቸው የድራማ፤ ሙዚቃ ፤ ስዕል፤ ቅርጻ ቅርጽ ፤የባህል አልባሳት ትርዒት፤ፋሽን ሾው ፤የትምህርት ቤት ሽብርቅ
ስራዎች፤ ወዘተ. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ተማሪዎች በገሀዱ ዓለም ያለውን ዕውነታ የሚገልጹበት፣ የሚያስተዋውቁበትና ፍላጎታቸውን የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም
ከትምህርት ቤት ማህበረተሰብ ጋር የሚግባቡበትና ትምህርታዊ መረጃ የሚያስተላልፉበት መንገድ አድርጎ የማደራጀትና ጥቅም ላይ
የማዋል ስራ መስራት ይገባል፡፡ ተማሪዎች የአለምን ተጨባጭ ሁኔታ የማወቅና የመረዳት፣ በመዝናናት መረጃ የማግኘትና
ፍላጎታቸውን የሚያዳብሩበት መድረክና አደረጃጀት ይፈልጋሉ፣ በዚህ መሰረት የክበቡ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለው
ተዘርዝሯል፡፡

የኪነ-ጥበብ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸው በዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 ለክበቡ የተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ ግብዓትን ማሟላት(የሙዚቃ መሳሪያዎች፤አልባሳት፤ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች፤ቅርጻ-

ቅርጾች፤የስዕል መሳሪያዎች ወዘተ.)

 በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የድራማ፣ የሙዚቃና የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ የአልባሳት ትርዒት የስዕልና ቅርጻ
ቅረጽ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 የኪነ ጥበብ ስራዎችን የሚመለከቱበትና ልምድ የሚቀስሙበትን ሁኔታዎች መፍጠር፤

6
1.3.3. የቋንቋ ክበብ

ይህ ክበብ ስነ-ጽሁፍ፤ ክርክር፤ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት፤ የንባብ ልምድ፤የቤተ መጻህፍት፤ ውይይት፤ ጉባዔ፤ ህትመት
ነክ ስራዎች(መጽሄት ፤በራሪ ጽሁፎች፤ጋዜጣ ወዘተ)ያጠቃልላል፡፡

ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ በቋንቋ ትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በክበቡ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮአቸው ራሳቸውንና
ሀሳባቸውን መግለፅ የሚችሉ ከመጻፍ፣ ማንበብና ሀሳባቸውን በተገቢው ከመግለፅ ባለፈ ቋንቋን ተጨማሪ ዕውቀት የማግኛ መሣሪያ
አድርጎ ለመጠቀም ይረዳል፡፡ በቋንቋ እጥረት ምክንያት ሊመጣ ከሚችለው ችግር ለመውጣትና በተለይም የመማር፣ የክርክር፣
ስነፅሑፍና ውይይት ኮንፈረንስ የማዘጋጀት ስራ ለማከናወን ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በት/ቤት ደረጃ ተግባራዊ ሲሆን የተሻለ ውጤት
የሚመዘገብበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የቋንቋ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸውና በየዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 በተለያዩ የክበቡ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 የትምህርት ቤቱን ዓመታዊ መጽሄት ማዘጋጀት፤

 ከተለያዩ ዓለማት የተገኙ መረጃዎችን ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ዘገባ ማቅረብ፤

 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የክርክርና የውይይት መድረክ ማዘጋጀት ፤

 የትምህርት ቤቱ ልሳን ሆኖ ማገልገል፤

 የተለያዩ ስነ ጽሁፎችና መነባንቦችንና ጥያቄና መልስ ውድድሮችን ማካሄድና ለተማሪዎች በሚኒ ሚዲያ
ማቅረብ፤

 የቤተ መጻህፍት ግብዓቶችን እንዲሟሉ ማድረግ(ጋዜጦች፤መጽሄት፤ማጣቀሻ መጻህፍት፤ጆርናሎችን ወዘተ.)፤

 ት/ቤቱን ለንባብ ምቹ ማድረግና የንባብ ውድድሮችን ማካሄድ፤

 ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ስነ-ቃሎችንና የተለያዩ የቋንቋ ትውፊቶችን ማዳበር፤

 የቋንቋ ማሻሻያ ስልቶችን በመቀየስ ወደ ተግባር መግባት፤

1.3.4. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ

የፈጠራ ስራዎች፤ አይ ሲቲ፤ የቤተ ሙከራ አጠቃቀም ፤የጥናትና ምርምር ስራዎች ወዘተ.ተማሪዎች የተለያዩ የፈጠራ
ችሎታቸውን አውጥተው ወደ ተግባር ሊለወጡበት የሚችሉበት ዕድል ለመፍጠር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ መቋቋም ት/ቤቶች
ተማሪዎችንና የመምህራንን አቅም በመጠቀም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረትና ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በክበቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ
ያደርጋል ፡፡ በክበቡ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሌሎች ሀገሮች የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የሚያስችለን ሁኔታ መፍጠር

7
እንችላለን፡፡ ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂን ውጤት ከሚጠቀሙ ተቋማትና እንዱስትሪዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት
በማድረግ መስራት ይችላሉ ተብሎም ይታመናል፣

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብን በማጠናከር በተሻለ ለመስራት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ ያቻላል፡፡በተጨማሪም በየደረጃው
ከተቀመጠው ስርዓተ ትምህርት የተቀዳ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ግብዓት ሆኖ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ሊያሳድግ የሚችል ንድፈ
ሀሳብ ከሂሳብ፣ ከፊዚክስ፣ ከኬሚስትሪ ከባዮሎጂና… ወዘተ የትምህርት ዓይነቶች በመውሰድ ቴክኖሎጂ የሚፈጠርበትና የሚሰራበት
ሁኔታን የማመቻቸት ስራ ት/ቤቶች መስራት ይገባቸዋል፡፡ከዚህ አንጻር የሳይንስን ቴክኖሎጂ ክበብ ሃላፊነትና ተግባር እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 በሳይንስና በፈጠራ ስራ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች መመዝገብ፤

 ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር ስልጠናዎችን ማመቻቸት፤

 ለሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ለፈጠራ ስራ የሚያግዙ ግብዓቶችን ማሟላት (ኮምፒተሮች፤ ኢነተርኔት፤ ፐላዝማ ቴሌቭዥን፤
ሬዲዮኖች፤ የሳይንስ ቤተ ሙከራ ዕቃዎችንና፤ ከአግልግሎት ውጪ የሆኑ ሌሎች ቁሳቁሶች)፤

 የምርምር መርሃግብር፤ጊዜና ቦታ ማመቻቸት፤

 ጥናታዊ የምርምር ጽሁፎችን ማዘጋጀት፤

 ተማሪዎች በቤተ ሙከራና በትምህርት ማበልጸጊያ እንዲጠቀሙ ማበረታታት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማካሄድ፤

 የሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የማጠናከሪያ ትምህርትና ድጋፍ መስጠት፤

1.3.5. የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ

በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሀገርህን እወቅ፤ ቅርስ ጥበቃና ክብካቤ፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፤መጤ ባህሎች፤የህ/ሰብ ሳይንስ
ትምህርቶች ፤ወዘተ. ሊደራጁ ያችላሉ፡፡

የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ አደረጃጀት በት/ቤቶች መኖር በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ንድፈ ሀሳቦችን የሚያጠናክር በመሆኑ
ተማሪዎች የጂኦግራፊ፤ የታሪክ፣ ፣የኢኮኖሚክስ፤ ቢዝነስ ትምህርቶች ከማህበራዊ ህይወታቸው ጋር በማገናኘት ሊገነዘቡ
የሚችሉት በርካታ አስተሳሰቦችና ተግባራት እንዲኖሩ ያደርጋል፣ ተማሪዎች አካባያቸውን በውል የሚረዱበትና የማህበረሰባቸውን
ወግና ባህል በማወቅ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ተግባራዊ የሚያደርጉበት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን እንደ ፍላጎታቸውና ዝንባሌያቸው ምዝገባ ማካሄድ፤

8
 በክበቡ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤

 ከባህል ያፈነገጡ፣ መጤና አላስፈላጊ ድረጊቶች የሚወገዱበት ሁኔታ ላይ መስራት(ፖርነግራፊ፤ግብረ ሰዶማዊነት፤የእብደት ቀን

ወዘተ.)

 ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች የሚቀረፉበት ሁኔታ ላይ መስራት፤

 ትምህርታዊ ጉብኝት ማዘጋጀት፤ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ፤

 ተማሪዎች ለብሄራዊ ማንነታቸውና ለታሪካቸው ክብር እንዲሰጡ ማብቃት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፤

1.3.6. የስነዜጋና ሥነምግባር ክበብ

ክበቡ ተማሪዎች የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር እሴቶችን የሚያጎለብቱበት፤ ስነ ምግባራቸውን የሚያሻሻሉበት፤ የአመራር ጥበብን
የሚለማመዱበት፤ ኪራይ ሰብሳቢነትን በአመለካከትና በተግባር የሚያወግዙበት ባህል የሚፈጥሩበት እና የት/ቤት የአካባቢ ሰላምና
ደህንነት የሚጠብቁበት ከመሆኑም በላይ የእርስ በርስ ግጭትና ከስርዓት ውጭ ሆኖ የመገኘት ሁኔታን ለመከላከል ያስችላል፡፡

የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ክበብ በእውቀትና በክህሎት ብቻ የዳበሩ ተማሪዎችን ከማፍራት ባሻገር በስነ ምግባርም የታነጹ እንዲሆኑ እገዛ
ያደርጋል፡፡ የተማሪዎች ፓርላማና ተመሳሳይነት ያላቸው አደረጃጀቶች በዚህ ክበብ ስር ይደራጃሉ፡

የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 ክበቡ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፤

 የተማሪዎች የስነ-ምግባር መመሪያቸውን በጥብቅ እንዲከተሉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 የት/ቤትና አካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚቆጣጠሩ አባላትን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባት፤

 የትምህርት ብክነትን ከመከላከል አኳያ ተማሪዎች ድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል፤

 ከት/ቤቱ የምክር አገልግሎት ባለሙያ ጋር በቅርርብ መስራት፤

 በህገ መንግስቱ ዙሪያ የጠለቀ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ጉብኝቶችን ማካሄድ፣

 ለንባብ የሚሆኑ መጻህፍት፤ጋዜጦች እና ልዩ ልዩ የህትመት ውጤቶች እንዲኖሩ ማድረግ፤የጥያቄና መልስ ወደድሮችን ማካሄድ፤

 በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ መካከል ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ማድረግ፤

 የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር እሴቶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ መስራት፤

9
1.3.7. የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ

ክበቡ የበጉ አድራጐት ፣ የትራፊክ ፣ የፖስታ ፣ የስካውት ወዘተ አገልግሎቶችን የሚያካትት ሲሆኑ የክበቡ ዓላማ በተማሪዎች የሚከሰቱ
የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ ነው ፡፡

የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸት፣

 የትራፊክ ደንቦችን በማስተዋወቅ አደጋዎችን መከላከል ፣

 ተማሪዎች የፖስታ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የስካውት አገልግሎት የሚስፋፋበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

1.3.8. የጤና አጠባበቅ ክበብ

ክበቡ ትኩረት የሚያደርግባቸው ዘርፎች የግልና የአካባቢ ንፅሕና አጠባበቅ ፣ የቀይ መስቀል ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና
መቆጣጠር ፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፣ የአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ሕገወጥ ዝውውርና አጠቃቀም መከላከል
እንዲሁም የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሲሆኑ ዓላማውም በተማሪዎች የሚከሰቱ የተለያዩ ከጤናና ከሥነ ተዋልዶ ጋር የተሳሰሩ
ችግሮች በመፍታት የመማር ማስተማር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆንበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የጤና አጠባበቅ ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥነ ተዋልዶ ጉዳይ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን
ማዘጋጀት ፣

 ለክበቡ አባላት ል ልዩ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት ፣

 በኤች አይ ቪ ኤድስና በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ ተማሪዎችን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት
የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የት/ቤት ግቢንና መማሪያ ክፍሎችን ማፅዳት ፣

 ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በፅዳት ዘመቻዎች ላይ መሳተፍ ፣

 በአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ተጠቂ የሆኑትን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ፣

10
 ለጤና ጠንቅ የሆኑ በትምህርት ቤት ዙሪያ የሚገኙ አዋኪ ሁኔታዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የመከላከል
ስራ መስራት ፣

 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በማድረግ እርዳታ የሚፈልጉ ተማሪዎችን መርዳት ፣

 ከሕክምና ተቋማት ተቀናጅቶ በመሥራት የተለያዩ በሽታዎችና አደጋዎችን መከላከል፣

 በት/ቤቶች በተማሪዎችና መምህራን የደም ልገሳ እንዲከናወን ማድረግ ፣

 የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠት

 በግልና በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ የክበቡ አባላት አርአያ ሆነው እንዲገኙ ማብቃት

1.3.9. የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ

የክበቡ ዓላማ ተማሪዎች ስለአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው የነቃ ተሣትፎ እንዲያደርጉና ምቹ የመማር ማስተማር
አካባቢ መፍጠር ነው ፡፡

የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የትምህርት ቤት ግቢ ማስዋብና በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፍ ፣

• ግንዛቤ በማሳደግ አካባቢ ከብክለትን መከላከል ፣

• በችግኝ ተከላ ላይ መሳተፍ ሌሎች እንዲሳተፉም ቅስቀሳ ማድረግ፣

• ምቹ የማጥኛ፣ የመመገቢያ ፣ የመጫወቻና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሟሉ ጥረት ማድረግ፣

• ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች የሚወገዱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• ለአደጋ የሚያጋልጡ ስጋቶች (ጉድጓዶች፤የፍሳሽ ቱቦዎች፤የተላጡ የኤሌትሪክ ሽቦዎች፤ገንዳዎች ወዘተ) በመለየት የሚወገዱበት
ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ገቢ ማሰባሰብ

• በቂ የመፀዳጃና የውሀ አገልግሎት እንዲኖር ጥረት ማድረግ

1.3.10. የሥርዓተ-ፆታ ክበብ

11
የክበቡ ዓላማ በሥርዓተ-ፆታ ዙሪያ የተስተካከለ አመለካከት እንዲፈጠር በማድረግ በሴትና ወንድ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ
ፆታዊ ትንኮሳዎችን በመከላከል ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ በንቃት የሚሳተፉበትና የአመራር አቅማቸውን
የሚያሳድጉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥርዓተ ፆታ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• ግንዛቤን በማሳደግ ፆታዊ ትንኮሳን መከላከል ፣

• ለሴት ተማሪዎች የሚያለግሉ የተለያዩ ግብዓቶችን ማቅረብ ፣

• ለሴት ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ማመቻቸት ፣

• ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ክበባትና ኮሚቴዎች በአመራር የሚሳተፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

1.3.11. የነገው መምህር ክበብ

የክበቡ ዓላማ ተማሪዎች መምህርነት የተከበረ ሙያ መሆኑን በመገንዘብ ራሳቸውን በማስተማር ተግባር እንዲለማመዱ በማድረግ
አቅማቸውን የሚያጐለብቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የነገው መምህር ክበብ አበይት ተግባራት

•ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 ስለመምህርነት ሙያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• የመምህርነት ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመለየትና የግል ማህደር በማዘጋጀት በየወቅቱ ተገቢ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ
በትምህርት ውጤታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ማድረግ፣

• በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ሞዴል መምህራን በክበቡ የሚታቀፉበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር

• ከትምህርት ቤቱም ሆነ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ስኬታማ የሆኑ መምህራንን በመጋበዝ ልምዳቸውን ለተማሪዎች
የሚያካፍሉበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ፣

• ተማሪዎች በማጠናከሪያ ትምህርት ወቅት በማስተማር ተግባር እንዲሳተፉ በማድረግ ተግባራዊ ልምምድ እንዲያደርጉ ማስቻል

1.3.12. የተማሪዎች ልዩ አደረጃጀት

12
በዚህ አደረጃት የተማሪዎች የልማት ቡድን ፤አንድ ለአምስት የጥናት ቡድን፤ ቶፕ-10 ንና ቶፕ-20፤የአለቆች ህብረት ወዘተ…
የሚካተቱ ናቸው፡፡ዓላማውም ተማሪዎች በአደረጃጀቱ ጠቀሜታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በመረዳዳት መርህ
የራሳቸውን አቅም ከማጐልበት ባሻገር በት/ቤታቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገራችን በተያያዘችው የልማት፤
የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስርዐት ግንባታ ሂደት ላይ የአመራር ሚና ማጎልበት ነው ፡፡

የተማሪዎች አደረጃጀት አበይት ተግባራት

• በተማሪዎች አደረጃጀት ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• የርስ በርስ የመረዳዳት ባህል በማጐልበት የትምህርት ውጤታቸውንና ስነ ምግባራቸውን ማሻሻል፣

• በተለያዩ ኮሚቴዎች በመሳተፍ የተማሪዎችን መብትና ጥቅም ማስከበር ፣

• ተማሪዎች የአመራር ሚናቸውን የሚያጐለብትበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የትምህርት ቤታቸውንና የአካባቢያቸውን ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣

• የት/ቤታቸውን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ከአደጋ መከላከል ፣

1.4. በሁሉም ተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ሊከናወኑ የሚገባቸው ዓበይት ተግባራት

• በክበባትና የተማሪ አደረጃጀቶች ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር

• የአባላት ምዝገባ ማከናወን

• የአመራር ምርጫ ማከናወን

• የዓመቱን የሥራ ዕቅድና የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት

• የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ ማዘጋጀትና ማፀደቅ

• ቋሚ የግኑኙነትና የግምገማ ጊዜ መወሰን

• በአደረጃጀት ስር እንደተገለፀው የክበባት አመራሮች በክበቡ ስር የተዘረዘሩትን የስራ ዘርፎች ተከፋፍሎ መምራት

• የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት

• ቃለ ጉባኤዎች፤ ሰነዶችና ስታስቲካዊ መረጃዎች ማደራጀት

• የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ማዘጋጀት

• ለሥራ ማስኬጃና ለሌሎች ተግባራት የሚውል ሀብት ማፈላለግ

• የማትጊያና የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት

13
• የውስጥ ኦዲት አሠራር መዘርጋት

• የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት

1.5. የተጓዳኝ ትምህርት መለያ ባህሪያት

 የተጓዳኝ ትምህርት በአመራሩና በአፈፃፀሙ ተማሪ ተኮር የሆነ ቀጥተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ በስርዓተ
ትምህርቱ የተካተቱት ንድፈ ሀሳቦች ወደ ተግባር የሚለወጡበት አደረጃጀት ነው፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት ትኩረቱ በተማሪዎች ቀጥተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ ሲታቀድና ሲታሰብ
ተማሪውን ለማዝናናት ፣ አካላዊ ማህበራዊና ሥነ ውበታዊ ተሰጥኦውን ለማበለፀግ ፣ የአመራር ችሎታን
ለማዳበር ወዘተ ሊሆን ይገባል ፡፡ በአጠቃላይ ተጓዳኝ ትምህርት ተማሪ - ተኮር እንቅስቃሴ ነው ፡፡

 በተራ ቁጥር 1.3.12. ከተጠቀሰው በስተቀር ተሣትፎ በፈቃደኝነት ነው ፡፡ ምንም እንኳን ተማሪዎች
ተሣታፊ እንዲሆኑ ቢመከሩ ፣ አመራር ቢያገኙና ግፊት ቢደረግባቸውም አምነውና ሙሉ ፈቃደኛ ሆነው
ካልተሳተፉ በስተቀር ግዴታ የለባቸውም ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች እንደ ክፍል ውስጥ ትምህርትና ተሳትፎ ከነጥብ /ማርክ/ ጋር የተያያዘ
ግምገማና ምዘና አይካሄድበትም ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት አመራርና አስተዳደር በተማሪዎችም ተሳትፎ ይከናወናል ፡፡ እንዲያውም ከዕቅድ

አወጣጥ እስከ አፈፃፀም ድረስ ተማሪዎች ራሳቸው እንዲያቅዱ ፣ እንዲመሩ ፣ እንዲቆጣጠሩ ፣
እንዲያከናውኑ ፣ እንዲገመግሙና እንዲስተባብሩ ይጠበቃል ፡፡ መምህራን በረዳትነት ፣ በአማካሪነት ፣
አቅጣጫ በማስያዝና አዳዲስ ዕውቀቶችንና ክህሎቶችን በማስጨበጥ የትምህርት ዓላማዎች ከግብ
እንዲደረሱ በመምራት ይሳተፋሉ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት የተወሰነ የአሠራርና የጥናት መንገድ አይታይበትም ፡፡ አንዳንዱ እንቅስቃሴና ዝግጅት
ለህብረተሰቡ የሚቀርብ /ለምሳሌ ፡- ድራማ ፣ ኤግዚቢሽን ፣ የወላጆች በዓል ወዘተ …./ ሊሆን ይችላል፡፡
አንዳንዱ ደግሞ የግል ፍላጎትንና ስሜትን ለማርካት ብቻ የማከናወን ፣ /ለምሳሌ ፡- የሥዕል ፣ የፎቶግራፍ /
ሲሆን እንደየ አደረጃጀቱ ባህሪ በግልም ሆነ በቡድን ሊሰራ ይችላል፡፡ የልምምድ ጊዜው እንደ ክፍል
ትምህርት የተወሰነና የተመጠነ ካለመሆኑም በላይ የመምህራን ኃላፊነትና የሥራ ድርሻም የሚያይልበት
ጊዜ ይኖራል፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ወይም ተግባሮች ሙሉ በሙሉ በተማሪዎችና በመምህራን በት/ቤት

ደረጃ የሚታቀዱ ናቸው ፡፡ እንደ ክፍል ውስጥ ትምህርት ተዘጋጅቶ የሚላክ የመምህሩ መምሪያ ፣
የተማሪው መጽሐፍ ወይም ሲለበስ የለውም፡፡

14
 በአንዳንድ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ላይ የክፍል ደረጃና ዕድሜ ሳይለይ ማንኛውም ተማሪ
የሚሳተፍበት ሁኔታ ይኖራል ፡፡ ለምሳሌ ፡- በድራማ ክበብ የ 9 ኛ ፣ 1 ዐኛ ፣ 11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል
ተማሪዎች በጋራ ሊሳተፉ ይችላሉ ፡፡

ክፍል ሁለት ፡

2. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት ፣ አመራርና አሠራር

2.1. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት

 የት/ቤቱን ማህበረሰብ በፍላጐታቸውና በዝንበሌያቸው መሠረት በአባልነት ይመዘግባል ፣

 በአባላቱ ምልዐተ ጉባኤ ከ 5-7 የሚሆኑ የሥራ አመራርን ያስመርጣል ፣

 የመተዳደሪያ ደንብና ሥርዓት ያወጣል ፣

 የትምህርት ዘመኑን የተጓዳኝ ትምህርት ዕቅድና የድርጊት መርሀ ግብር ያዘጋጃል፣

 የሥራ ክፍፍል ያደርጋል ፣

 የግምገማ ሥርዓት ይዘረጋል ፣

2.2. በተጓዳኝ ትምህርት የልዩ ልዩ ክፍሎች ሀላፊነትና ተግባር

ሀ/ በተጓዳኝ ትምህርት የመምህራን ሀላፊነትና ተግባር

መምህራን በሀላፊነት የተረከቧቸውን ተማሪዎች በየደረጃቸው በሚሰጡት ትምህርት በእውቀት ፣ በክህሎት በአመለካከትና በአካል
በመገንባት አምራች ፣ በስነ ምግባር የተሻሉ እንዲሆኑ ኮትኩቶ ብቁ ዜጋ የማድረግ ከባድ ሀላፊነት ተሸክመዋል ፡፡ ዕውቀታቸው ፣
የመምራትና የማስተማር ዘዴያቸው እንደዚሁም ሞያተኝነታቸው እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም በተለይ ለተጓዳኝ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና
አቋም በአደረጃጀቶቹ ውጤታማነት ላይ የወሳኝነት ሚና ይኖረዋል ፣

ስለዚህ በተጓዳኝ ትምህርት አስተባባሪነትና መሪነት የሚመረጡ መምህራን የሚከተሉት ሃላፊነቶች ይኖራቸዋል፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት ጽንሰ ሀሳብንና ዓላማን ተገንዝበው ለተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ፣

 በተጓዳኝ ትምህርት ኘሮግራሞችና የክበቦችን ዕቅድ አወጣጥና አፈፃፀም ላይ በንቃት መሳተፍ ፣

15
 ተማሪዎችን በመርዳትና በማማከር እንዲሁም በማነቃቃትና በማስተባበር ለትምህርት ፣ለተሳትፎና ለሥራ ማዘጋጀት ፣

 ተማሪዎች በአመራር፣ በአደረጃጀት፣ በክትትልና ድጋፍ እንዲሁም በግምገማ ስርዓት እየተሳተፉ እንዲለማመዱ
ማዘጋጀት ፣

 በክፍል ውስጥ ከሚሰጡት ትምህርቶች ጋር ተዛማጅና ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራዊ ኘሮጀክቶችን፣ የምርምር
ሥራዎችንና ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ ፣

 ፣የተለያዩ ባለሙያዎችን፣ወላጆችንና መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር የፋይናንስ ፣

የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ የሚገኝበትን አግባብ ማመቻቸት ፣

 ሀላፊነትን በሙሉ ፈቃደኝነት በመቀበልና በሌሎችም ተግባራት ከፍተኛ ሚና በመጫዎት አርአያ ሆኖ መገኘት፣

ለ/ በተጓዳኝ ትምህርት የተማሪዎች ሀላፊነትና ተግባር ፣

 ተማሪዎች የመማር፤ የመመራመር፤ የፈጠራ ችሎታቸውን ለማዳበርና በመብታቸው ለመጠቀም በተማሪነታቸው

ያለባቸውን ግዴታና ኃላፊነት በብቃት መወጣት ፣

 ንቁና ታታሪ ተማሪዎች ሆኖ መገኘት ፣

 ከዕቅድ እስከ ዕቅድ አፈፃፀምና ውጤት ባለው ሂደት በንቃት መሳተፍ፣

o የሀላፊነትና የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር፣

o የዲሞክራሲ ባህል እንዲሰፍን ሚናቸውን መወጣት፣

o የህብረተሰቡን ጠቃሚ ልምድ፣ ወግና ባህል ማክበርና በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ተግባራዊ ማድረግ፣

o የራስ ተነሳሽነትና የአመራር ብቃትን መለማመድ፣

o በት/ቤቱ በሚደራጁና በሚካሄዱ የክፍል ውስጥና ውጭ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችና ኘሮግራሞች ሁሉ ንቁ ተሣትፎ

ማድረግ ፣

o የመፍጠርና የመመራመር ችሎታቸውን ማጎልበት፣

o ስነ ውበትንም የማድነቅ፣ የተፈጥሮ ሁብትንና የሀገር ታሪካዊ ቅርሶችን የመንከባከብ ብቃትን ማዳበር፣

ሐ/ የትምህርት ቤት አመራር ኃላፊነትና ተግባር

 የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት እንዲኖር ስርዓት ይዘረጋል ፣

16
 የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ያዘጋጃል ፣

 ስለተጓዳኝ ትምህርት ጠቀሜታ በማስገንዘብ ተማሪዎችና መምህራንን እንደየፍላጐታቸውና ዝንባሌያቸው እንዲመዘገቡ ያደርጋል ፣

 የአመራር አካላትን እንዲመረጡ ያስተባብራል፤እውቅና ይሰጣል፣

 በትምህርት ቤቱ ዕቅድ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ያካትታል፤ ይከታተላል ፣ ይደግፋል ፣

 የማትጊያ ስርዓት ይዘረጋል ፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤

 የግማገማ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጋል ፣

 ለስራ ማስኬጃና ለስልጠና በጀት ይመድባል፤ ለስራ የሚሆኑ ምቹ ቦታዎችን ያዘጋጃል፤

 የንብረትና የበጀት አጠቃቀም የመንግስትን ፋይናንስ ስርዐት መከተሉን ያረጋግጣል፤

 የተጓዳኝ ትምህርትን በሚመለከት የተሟላ መረጃ ይይዛል፤ሪፖርትም ያደርጋል፡፡

መ/ የክፍለ ከተማና የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ሀላፊነትና ተግባር

- በዕቅዳቸው መሰረት በቼክሊስት የተደገፈ ወቅታዊ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ

- ለተጓዳኝ ትምህርት አመራሮች ስልጠና ያዘጋጃሉ፣

- በምክክር መድረክ ላይ በመገኘት ሀሳብና አቅጣጫ ይሰጣሉ ፣

- የተጓዳኝ ትምህርት አውደ ርዕይ ያዘጋጃሉ

- በትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋሉ፤

- ግምገማን መሰረት በማድረግ በተጓዳኝ ትምህርት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ትምህርት ቤቶችና መምህራንና ተማሪዎች
እንዲሁም አደረጃጀቶች የማትጊያ ስርአት ተጠቃሚ ያደርጋሉ፤

- ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፤

ሰ/ በትምህርት ቤት ደረጃ የወተመህ ሚና

- በተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ የወላጆችንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ያጎለብታል፤

- ለተማሪዎች ተሳትፎ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፤

ረ/ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊነትና ተግባር

17
- የተጓዳኝ ትምህርት በተመለከተ መመሪያዎችን፤ ማኑዋሎችን፤ ደንቦችን ወዘተ ያዘጋጃል፤ ያሻሽላል፤
አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፤

- ለተመረጡ ናሙና ት/ቤቶች በቼክሊስት በተደገፈ የድጋፍ ክትትልና ግብረ መልስ ሥራ ይሠራል ፣

- በከተማ ደረጃ የትምህርት ፌስቲቫልና የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ያዘጋጃል፤የላቀ ውጤት ላስመዘገቡም እውቅና ይሰጣል ፣
ይሸልማል፤

- ለተጓዳኝ ትምህርት አመራሮች ስልጠና ያዘጋጃል፣

- በምክክር መድረክ ላይ በመገኘት ሀሳብና አቅጣጫ ይሰጣል ፣

- ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤

- በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ንድፈ ሃሳቦች በተማሪ አደረጃጀቶችና ክበባት ወደ ተግባር ስለመለወጣቸው የዳሰሳ ጥናት ያደርጋል

- በትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋል፤

2.2. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች የአሰራር መርሆዎች

 በትምህርት ቤቶች የተጓዳኝ ትምህርት በት/ቤቱ አመራር በጋራ የሚመራ ሆኖ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ር/መምህር በበላይነት
ያስተባብራል፤

 በአዲስ መልክ የሚዋቀር ክበብ ወይም የተማሪዎች አደረጃጀት ከት/ቢሮ እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ ማዋቀር አይቻልም፤

 ክበባት ከጾታ፣ ከዘር፣ ከእምነት፣ ከኢኮኖሚ ደረጃ፣ ወዘተ… ልዩነት የጸዱ መሆን አለባቸው፤

 የማነቃቂያና የማበረታቻ ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል፤

 ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል፤

 አመራሮቻቸውን በዲሞክራሲያዊ መርህ መምረጥ ይኖርባቸዋል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ትምህርታዊ እሴት ያላቸው መሆን አለባቸው፤

 ተማሪዎች በተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ላይ በንቃት መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሃላፊነትንም ጭምር መጋራት ይኖርባቸዋል፤

 የትምህርት ቤቱ መምህራን ቢያንስ በሁለት ክበባት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፤

 ለሁሉም የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤

 ለመደበኛው ትምህርት የሚሰጠውን ትኩረት ያህል ለተጓዳኝ ትምህርትም ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፤

18
 አንድ ክበብ ለማቋቋም እንደት/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ ቢያንስ ሃያ አምስት ፈቃደኛ ተማሪዎች፤ መምህራንና
የአስተዳደር ሰራተኞችን ያቀፈ ሆኖ ቢደራጅ ለአሰራር አመቺ ይሆናል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች የተማሪዎችን ፍላጎት፣ ዝንባሌ እና ስሜት መሰረት ያደረጉ ይሆናሉ፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ከመደበኛው ትምህርት ሰዓት ውጪ የሚከናወኑ ይሆናሉ፤

 የክበባት አስተባባሪዎች የአገልግሎት የስራ ዘመን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ብቻ ይሆናል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት ለልዩ ፍላጎትና ለሴቶች ተሳትፎ ልዩ ትኩረት መስጠት ይኖርበታል፤

2.3. መደራጀት የሚገባው የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ አወሳሰን

 ለትምህርት ዓላማዎች መሳካት ያላቸው አስተዋጽዎ፤

 ከተማሪዎች ፍላጎት የመነጩ ስለመሆናቸው፤

 ከእንቅስቃሴው አንጻር ፍላጎትና ችሎታ ያላቸው ወይም ሊመደቡ የሚችሉ መሪ መምህራን መኖራቸው፤

 ጊዜ ፤ግብዓትና ቦታ መኖሩ ሲረጋገጥ፤

 የበርካታ ተማሪዎችን ተሳትፎ የሚጠይቁ እንቅስቃሴ ኣይነቶች ከሆኑ፤

 በህብረተሰቡ ተቀባነት ያላቸው መሆኑ፤

 የመንግስት ፖሊሲና ህጎችን የማይቃረኑ መሆናቸው፤

 ለአደጋዎች የማያጋልጡ መሆናቸው፤

 በተማሪዎች ላይ የወጪ ጫና የማያስከትሉ ከሆኑ፤

 ዲሞክራሲዊነታቸውና ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

2.4. የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ግምገማ ስርዓት

የአንድ ት/ቤት የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መሰረታዊ የግምገማ ሂደት የተማሪዎችን አጠቃላይ ደህንነት ለማስጠበቅና ሁለንተናዊ እድገት
ለማሻሻል በሚያስችል ሁኔታ መከናወን ይኖርበታል፡፡ ግምገማው ከአካባቢያዊ አደረጃጀትና ሁኔታዎች መመቻቸት፤ ከባህሪይ ለውጥ
ማምጣት፤ ከስራ ውጤት፤ ከአሰራር ለውጥና መሻሻል አኳያ የሚታይ ሲሆን ዝርዝር የመገምገሚያ ነጥቦቹ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 የክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን ከማዳበር አንጻር፤

 የተማሪዎችን ፍላጎት እና ስሜት ስለማርካታቸው፤

 ብቃትና ፍላጎት ያላቸው መሪ መምህራን ስለመመደባቸው፤

19
 አስተባባሪ መምህራኑ የተመረጡበት ሁኔታ፤

 በእንቅስቃሴው የተማሪዎች ተሳትፎ ደረጃ፤

 ለእንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ እና ዕድል የተፈጠረ ስለመሆኑ፤

 የማበረታቻ ስርዓት ስለመዘርጋቱ፤

 በእያንዳንዱ አደረጃጀት ምን ያህል ተማሪዎች (ወነድና ሴት) እንደተሳተፉ፤

 ተማሪዎች ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚያበረክቱት አገልግሎት፤

 ህብረተሰቡ ስለሰአደረጃጀቱ ያላቸው እይታ፤

 እያንዳንዱ አደረጃት የመተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀቱ፤ማስፀደቁና ተግባራዊ ስለማድረጉ፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች የፋናንስ ሀ፤ኔታ

 በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአደረጃጀቱ ወቅታዊ ግምገማ ስለመደረጉ፤

 የእያንዳንዱ አደረጃጀት እንቅስቃሴ መረጃ በሚገባ ስለመያዙ፤ወዘተ.ይሆናል፡፡

ክፍል ሶስት
የክትትል፣ድጋፍ፣ግምገማና ግብረመልስ እንዲሁም የሪፖርት ስርዓት
3.1. በክትትል፤ ድጋፍ፤ ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓት በየእርከኑ ያሉ አካላት ሚና

3.1.1. የትምህርት ቤቶች ሚና

 አጠቃላይ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መረጃዎችንና ተማሪዎች አደረጃጀቱን ጠጠቅመው የሚያሳዩትን
ወቅታዊ ለውጥ መከታተል፣ መቀመርና ማደራጀት መያዝ፣ ለወረዳዎችና ለሚመለከታቸው አጋር አካላት
ማስተላለፍ
 የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በወቅቱ ማስተላለፍ
3.1.2. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
 ለትምህርት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
 ግብረመልስ መስጠት
 መረጃና ሪፖርት በማደራጀት ለክፍለ ከተማና ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ
3.1.3. የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች
 ለትምህርት ቤቶችና ለወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፣ግብረመልስ መስጠት
 አጠቃላይ የክፍለ ከተማውን ወቅታዊ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መረጃና የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
በማጠናቀር ለትምህርት ቢሮና ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ
3.1.4. የትምህርት ቢሮ
 ለክፍለ ከተሞች፣ ለወረዳዎችና ለትምህርት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ ግብረመልስ መስጠት
 ከክፍለ ከተማ የተገኘውን መረጃ ማደራጀት፣መተንተን፣የተገኘውን የትንተና ውጤት ለቀጣይ ስራዎችና
ዕቅዶች በግብዓትነት መጠቀም ለአጋርና ለተባባሪ አካላት ማሰራጨት፤
3.2. የክትትልና ድጋፍ አግባብ
ክትትልና ድጋፉ ሁሉንም መስተጋብሮች ማለትም
20

በመስክ ጉብኝት

በሪፖርት

የአካል ግምገማ (በስብሰባ፣በኮንፍረንስ፣በምክክር መድረክና በቋሚ የግንኙነት ጊዜ)
የዳሰሳ ጥናት ማድረግን ባካተተ መንገድ ይከናወናል፡፡
ስለሆነም ተግባራቱ በሚዘጋጀው እቅድ መሰረት የሚተገበሩ ሲሆን ሪፖርቶች ደግሞ እንደየስራው ባህሪ በጽሁፍ
ይቀርባሉ፡፡በቀረበው ሪፖርት መሰረት የግብረ-መልስ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ይከናወናል፡፡
የአካል ግምገማ በማድረግም ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቶች የሚስተካከሉበት አሰራር ይፈጸማል፡፡
በተጨማሪም የሱፐርቪዥን ስራ በምልከታ እና የተለያዩ ችግር ፈቺ ቼክሊስቶችን በማዘጋጀት ወርዶ በመደገፍ ተጨባጭ
በሆነ ሁኔታ የክትትልና ግምገማ ስርአቱ ቀጣይነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ይከናወናል፡፡

አባሪ ሰነዶች

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምሀርት ቢሮ

ታህሳስ 2007

አዲስ አበባ
21
1.የስፖርት ክበብ

ት/ቤቶች ወጣቱን በአዕምሮና በአካል ብቃት አዘጋጅቶና ኮትኩቶ ለማውጣት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ
በመሆኑ በስፖርት እንቅስቃሴዎችና ውድድሮች ተማሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሮአቸው እንዲያድጉ ለማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት
ነው፡፡ በዚህ አደረጃጀት ስር የሚተገበሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፡-

- አትሌቲክስ /ሩጫ ፣ውርወራ፣ ዝላይ… ወዘተ/ ፣

- ኳስ ጨዋታዎች ( የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ ፣ የቅርጫት ኳስ ፣የእጅ ኳስ ፤ የጠረጴዛ ኳስ….. ወዘተ)

- የጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች

- የሀገር ባህል ስፖርታዊ እንቅስቃሴና

- ዘመናዊ የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን ያጠቃልላል፣

የክበቡ ዋና ዋና ተግባራት

የተማሪዎችን አካልና አዕምሮአዊ ዕድገት በሚፈለገው መልኩ እንዲጎለብት ማድረግ መሰረታዊ ዓላማው ሲሆን ክበቡ
የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

 ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በየዘርፉ መመዝገብ፤

 በየዘርፉ ብቁ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ስልጠና መስጠት፤

 በየስፖርት ዓይነቱ የፕሮግራም ድልድል በመስራት የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን መምረጥ፤

 የት/ቤቱን የውስጥ ውድድር መርሃ ግብር ማዘጋጀትና ወደ ተግባር መግባት፤

 በወረዳ፤ በክ/ከተማ ፤በከተማ እንዲሁም በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጁ ውድድሮች ራስን ማብቃትና መሳተፍ፤

 አስፈላጊውን የማበረታቻ ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ፤

 የላብ መተኪያ እና ለተለያዩ ቁሳ ቁሶች የሚሆን በጀት ማፈላለግና ተግባራዊ ማድረግ፤

22
 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ሊወዳደሩ የሚችሉበትን ዘርፍ መለየት፣ ማብቃትና በውድድር ተሳታፊ
የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

2.የኪነ-ጥበብ ክበብ፤

በክበቡ ሊካተቱ የሚገባቸው የድራማ፤ ሙዚቃ ፤ ስዕል፤ ቅርጻ ቅርጽ ፤የባህል አልባሳት ትርዒት፤ፋሽን ሾው ፤የትምህርት ቤት ሽብርቅ
ስራዎች፤ ወዘተ. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ተማሪዎች በገሀዱ ዓለም ያለውን ዕውነታ የሚገልጹበት፣ የሚያስተዋውቁበትና ፍላጎታቸውን የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም
ከትምህርት ቤት ማህበረተሰብ ጋር የሚግባቡበትና ትምህርታዊ መረጃ የሚያስተላልፉበት መንገድ አድርጎ የማደራጀትና ጥቅም ላይ
የማዋል ስራ መስራት ይገባል፡፡ ተማሪዎች የአለምን ተጨባጭ ሁኔታ የማወቅና የመረዳት፣ በመዝናናት መረጃ የማግኘትና
ፍላጎታቸውን የሚያዳብሩበት መድረክና አደረጃጀት ይፈልጋሉ፣ በዚህ መሰረት የክበቡ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለው
ተዘርዝሯል፡፡

የኪነ-ጥበብ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸው በዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 ለክበቡ የተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ ግብዓትን ማሟላት(የሙዚቃ መሳሪያዎች፤አልባሳት፤ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች፤ቅርጻ-

ቅርጾች፤የስዕል መሳሪያዎች ወዘተ.)

 በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የድራማ፣ የሙዚቃና የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ የአልባሳት ትርዒት የስዕልና ቅርጻ
ቅረጽ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 የኪነ ጥበብ ስራዎችን የሚመለከቱበትና ልምድ የሚቀስሙበትን ሁኔታዎች መፍጠር፤

1.5.1. የቋንቋ ክበብ

ይህ ክበብ ስነ-ጽሁፍ፤ ክርክር፤ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት፤ የንባብ ልምድ፤የቤተ መጻህፍት፤ ውይይት፤ ጉባዔ፤ ህትመት
ነክ ስራዎች(መጽሄት ፤በራሪ ጽሁፎች፤ጋዜጣ ወዘተ)ያጠቃልላል፡፡

ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ በቋንቋ ትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በክበቡ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮአቸው ራሳቸውንና
ሀሳባቸውን መግለፅ የሚችሉ ከመጻፍ፣ ማንበብና ሀሳባቸውን በተገቢው ከመግለፅ ባለፈ ቋንቋን ተጨማሪ ዕውቀት የማግኛ መሣሪያ
አድርጎ ለመጠቀም ይረዳል፡፡ በቋንቋ እጥረት ምክንያት ሊመጣ ከሚችለው ችግር ለመውጣትና በተለይም የመማር፣ የክርክር፣
ስነፅሑፍና ውይይት ኮንፈረንስ የማዘጋጀት ስራ ለማከናወን ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በት/ቤት ደረጃ ተግባራዊ ሲሆን የተሻለ ውጤት
የሚመዘገብበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡
23
የቋንቋ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸውና በየዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 በተለያዩ የክበቡ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 የትምህርት ቤቱን ዓመታዊ መጽሄት ማዘጋጀት፤

 ከተለያዩ ዓለማት የተገኙ መረጃዎችን ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ዘገባ ማቅረብ፤

 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የክርክርና የውይይት መድረክ ማዘጋጀት ፤

 የትምህርት ቤቱ ልሳን ሆኖ ማገልገል፤

 የተለያዩ ስነ ጽሁፎችና መነባንቦችንና ጥያቄና መልስ ውድድሮችን ማካሄድና ለተማሪዎች በሚኒ ሚዲያ
ማቅረብ፤

 የቤተ መጻህፍት ግብዓቶችን እንዲሟሉ ማድረግ(ጋዜጦች፤መጽሄት፤ማጣቀሻ መጻህፍት፤ጆርናሎችን ወዘተ.)፤

 ት/ቤቱን ለንባብ ምቹ ማድረግና የንባብ ውድድሮችን ማካሄድ፤

 ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ስነ-ቃሎችንና የተለያዩ የቋንቋ ትውፊቶችን ማዳበር፤

 የቋንቋ ማሻሻያ ስልቶችን በመቀየስ ወደ ተግባር መግባት፤

1.5.2. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ

የፈጠራ ስራዎች፤ አይ ሲቲ፤ የቤተ ሙከራ አጠቃቀም ፤የጥናትና ምርምር ስራዎች ወዘተ.ተማሪዎች የተለያዩ የፈጠራ
ችሎታቸውን አውጥተው ወደ ተግባር ሊለወጡበት የሚችሉበት ዕድል ለመፍጠር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ መቋቋም ት/ቤቶች
ተማሪዎችንና የመምህራንን አቅም በመጠቀም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረትና ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በክበቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ
ያደርጋል ፡፡ በክበቡ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሌሎች ሀገሮች የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የሚያስችለን ሁኔታ መፍጠር
እንችላለን፡፡ ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂን ውጤት ከሚጠቀሙ ተቋማትና እንዱስትሪዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት
በማድረግ መስራት ይችላሉ ተብሎም ይታመናል፣

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብን በማጠናከር በተሻለ ለመስራት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ ያቻላል፡፡በተጨማሪም በየደረጃው
ከተቀመጠው ስርዓተ ትምህርት የተቀዳ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ግብዓት ሆኖ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ሊያሳድግ የሚችል ንድፈ
ሀሳብ ከሂሳብ፣ ከፊዚክስ፣ ከኬሚስትሪ ከባዮሎጂና… ወዘተ የትምህርት ዓይነቶች በመውሰድ ቴክኖሎጂ የሚፈጠርበትና የሚሰራበት
ሁኔታን የማመቻቸት ስራ ት/ቤቶች መስራት ይገባቸዋል፡፡ከዚህ አንጻር የሳይንስን ቴክኖሎጂ ክበብ ሃላፊነትና ተግባር እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

24
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 በሳይንስና በፈጠራ ስራ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች መመዝገብ፤

 ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር ስልጠናዎችን ማመቻቸት፤

 ለሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ለፈጠራ ስራ የሚያግዙ ግብዓቶችን ማሟላት (ኮምፒተሮች፤ ኢነተርኔት፤ ፐላዝማ ቴሌቭዥን፤
ሬዲዮኖች፤ የሳይንስ ቤተ ሙከራ ዕቃዎችንና፤ ከአግልግሎት ውጪ የሆኑ ሌሎች ቁሳቁሶች)፤

 የምርምር መርሃግብር፤ጊዜና ቦታ ማመቻቸት፤

 ጥናታዊ የምርምር ጽሁፎችን ማዘጋጀት፤

 ተማሪዎች በቤተ ሙከራና በትምህርት ማበልጸጊያ እንዲጠቀሙ ማበረታታት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማካሄድ፤

 የሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የማጠናከሪያ ትምህርትና ድጋፍ መስጠት፤

1.5.3. የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ

በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሀገርህን እወቅ፤ ቅርስ ጥበቃና ክብካቤ፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፤መጤ ባህሎች፤የህ/ሰብ ሳይንስ
ትምህርቶች ፤ወዘተ. ሊደራጁ ያችላሉ፡፡

የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ አደረጃጀት በት/ቤቶች መኖር በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ንድፈ ሀሳቦችን የሚያጠናክር በመሆኑ
ተማሪዎች የጂኦግራፊ፤ የታሪክ፣ ፣የኢኮኖሚክስ፤ ቢዝነስ ትምህርቶች ከማህበራዊ ህይወታቸው ጋር በማገናኘት ሊገነዘቡ
የሚችሉት በርካታ አስተሳሰቦችና ተግባራት እንዲኖሩ ያደርጋል፣ ተማሪዎች አካባያቸውን በውል የሚረዱበትና የማህበረሰባቸውን
ወግና ባህል በማወቅ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ተግባራዊ የሚያደርጉበት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን እንደ ፍላጎታቸውና ዝንባሌያቸው ምዝገባ ማካሄድ፤

 በክበቡ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤

 ከባህል ያፈነገጡ፣ መጤና አላስፈላጊ ድረጊቶች የሚወገዱበት ሁኔታ ላይ መስራት(ፖርነግራፊ፤ግብረ ሰዶማዊነት፤የእብደት ቀን

ወዘተ.)

 ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች የሚቀረፉበት ሁኔታ ላይ መስራት፤

 ትምህርታዊ ጉብኝት ማዘጋጀት፤ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ፤

25
 ተማሪዎች ለብሄራዊ ማንነታቸውና ለታሪካቸው ክብር እንዲሰጡ ማብቃት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፤

1.5.4. የስነዜጋና ሥነምግባር ክበብ

ክበቡ ተማሪዎች የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር እሴቶችን የሚያጎለብቱበት፤ ስነ ምግባራቸውን የሚያሻሻሉበት፤ የአመራር ጥበብን
የሚለማመዱበት፤ ኪራይ ሰብሳቢነትን በአመለካከትና በተግባር የሚያወግዙበት ባህል የሚፈጥሩበት እና የት/ቤት የአካባቢ ሰላምና
ደህንነት የሚጠብቁበት ከመሆኑም በላይ የእርስ በርስ ግጭትና ከስርዓት ውጭ ሆኖ የመገኘት ሁኔታን ለመከላከል ያስችላል፡፡

የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ክበብ በእውቀትና በክህሎት ብቻ የዳበሩ ተማሪዎችን ከማፍራት ባሻገር በስነ ምግባርም የታነጹ እንዲሆኑ እገዛ
ያደርጋል፡፡ የተማሪዎች ፓርላማና ተመሳሳይነት ያላቸው አደረጃጀቶች በዚህ ክበብ ስር ይደራጃሉ፡

የስነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 ክበቡ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፤

 የተማሪዎች የስነ-ምግባር መመሪያቸውን በጥብቅ እንዲከተሉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

 የት/ቤትና አካባቢውን ሰላምና ደህንነት የሚቆጣጠሩ አባላትን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማስገባት፤

 የትምህርት ብክነትን ከመከላከል አኳያ ተማሪዎች ድርሻቸውን እንዲወጡ ማስቻል፤

 ከት/ቤቱ የምክር አገልግሎት ባለሙያ ጋር በቅርርብ መስራት፤

 በህገ መንግስቱ ዙሪያ የጠለቀ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ጉብኝቶችን ማካሄድ፣

 ለንባብ የሚሆኑ መጻህፍት፤ጋዜጦች እና ልዩ ልዩ የህትመት ውጤቶች እንዲኖሩ ማድረግ፤የጥያቄና መልስ ወደድሮችን ማካሄድ፤

 በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ መካከል ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት እንዲሰፍን ማድረግ፤

 የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር እሴቶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ መስራት፤

1.5.5. የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ

ክበቡ የበጉ አድራጐት ፣ የትራፊክ ፣ የፖስታ ፣ የስካውት ወዘተ አገልግሎቶችን የሚያካትት ሲሆኑ የክበቡ ዓላማ በተማሪዎች የሚከሰቱ
የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ ነው ፡፡

የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸት፣
26
 የትራፊክ ደንቦችን በማስተዋወቅ አደጋዎችን መከላከል ፣

 ተማሪዎች የፖስታ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የስካውት አገልግሎት የሚስፋፋበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

1.5.6. የጤና አጠባበቅ ክበብ

ክበቡ ትኩረት የሚያደርግባቸው ዘርፎች የግልና የአካባቢ ንፅሕና አጠባበቅ ፣ የቀይ መስቀል ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና
መቆጣጠር ፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፣ የአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ሕገወጥ ዝውውርና አጠቃቀም መከላከል
እንዲሁም የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሲሆኑ ዓላማውም በተማሪዎች የሚከሰቱ የተለያዩ ከጤናና ከሥነ ተዋልዶ ጋር የተሳሰሩ
ችግሮች በመፍታት የመማር ማስተማር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆንበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የጤና አጠባበቅ ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥነ ተዋልዶ ጉዳይ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን
ማዘጋጀት ፣

 ለክበቡ አባላት ል ልዩ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት ፣

 በኤች አይ ቪ ኤድስና በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ ተማሪዎችን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት
የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የት/ቤት ግቢንና መማሪያ ክፍሎችን ማፅዳት ፣

 ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በፅዳት ዘመቻዎች ላይ መሳተፍ ፣

 በአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ተጠቂ የሆኑትን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ፣

 ለጤና ጠንቅ የሆኑ በትምህርት ቤት ዙሪያ የሚገኙ አዋኪ ሁኔታዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የመከላከል
ስራ መስራት ፣

 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በማድረግ እርዳታ የሚፈልጉ ተማሪዎችን መርዳት ፣

 ከሕክምና ተቋማት ተቀናጅቶ በመሥራት የተለያዩ በሽታዎችና አደጋዎችን መከላከል፣

 በት/ቤቶች በተማሪዎችና መምህራን የደም ልገሳ እንዲከናወን ማድረግ ፣

27
 የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠት

 በግልና በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ የክበቡ አባላት አርአያ ሆነው እንዲገኙ ማብቃት

1.5.7. የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ

የክበቡ ዓላማ ተማሪዎች ስለአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው የነቃ ተሣትፎ እንዲያደርጉና ምቹ የመማር ማስተማር
አካባቢ መፍጠር ነው ፡፡

የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የትምህርት ቤት ግቢ ማስዋብና በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፍ ፣

• ግንዛቤ በማሳደግ አካባቢ ከብክለትን መከላከል ፣

• በችግኝ ተከላ ላይ መሳተፍ ሌሎች እንዲሳተፉም ቅስቀሳ ማድረግ፣

• ምቹ የማጥኛ፣ የመመገቢያ ፣ የመጫወቻና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሟሉ ጥረት ማድረግ፣

• ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች የሚወገዱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• ለአደጋ የሚያጋልጡ ስጋቶች (ጉድጓዶች፤የፍሳሽ ቱቦዎች፤የተላጡ የኤሌትሪክ ሽቦዎች፤ገንዳዎች ወዘተ) በመለየት የሚወገዱበት
ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ገቢ ማሰባሰብ

• በቂ የመፀዳጃና የውሀ አገልግሎት እንዲኖር ጥረት ማድረግ

1.5.8. የሥርዓተ-ፆታ ክበብ

የክበቡ ዓላማ በሥርዓተ-ፆታ ዙሪያ የተስተካከለ አመለካከት እንዲፈጠር በማድረግ በሴትና ወንድ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ
ፆታዊ ትንኮሳዎችን በመከላከል ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ በንቃት የሚሳተፉበትና የአመራር አቅማቸውን
የሚያሳድጉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥርዓተ ፆታ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

28
• ግንዛቤን በማሳደግ ፆታዊ ትንኮሳን መከላከል ፣

• ለሴት ተማሪዎች የሚያለግሉ የተለያዩ ግብዓቶችን ማቅረብ ፣

• ለሴት ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ማመቻቸት ፣

• ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ክበባትና ኮሚቴዎች በአመራር የሚሳተፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

1.5.9. የነገው መምህር ክበብ

የክበቡ ዓላማ ተማሪዎች መምህርነት የተከበረ ሙያ መሆኑን በመገንዘብ ራሳቸውን በማስተማር ተግባር እንዲለማመዱ በማድረግ
አቅማቸውን የሚያጐለብቱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የነገው መምህር ክበብ አበይት ተግባራት

•ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 ስለመምህርነት ሙያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• የመምህርነት ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በመለየትና የግል ማህደር በማዘጋጀት በየወቅቱ ተገቢ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ
በትምህርት ውጤታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ማድረግ፣

• በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ሞዴል መምህራን በክበቡ የሚታቀፉበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር

• ከትምህርት ቤቱም ሆነ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ስኬታማ የሆኑ መምህራንን በመጋበዝ ልምዳቸውን ለተማሪዎች
የሚያካፍሉበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ፣

• ተማሪዎች በማጠናከሪያ ትምህርት ወቅት በማስተማር ተግባር እንዲሳተፉ በማድረግ ተግባራዊ ልምምድ እንዲያደርጉ ማስቻል

1.5.10. የተማሪዎች ልዩ አደረጃጀት

በዚህ አደረጃት የተማሪዎች የልማት ቡድን ፤አንድ ለአምስት የጥናት ቡድን፤ ቶፕ-10 ንና ቶፕ-20፤የአለቆች ህብረት ወዘተ…
የሚካተቱ ናቸው፡፡ዓላማውም ተማሪዎች በአደረጃጀቱ ጠቀሜታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በመረዳዳት መርህ
የራሳቸውን አቅም ከማጐልበት ባሻገር በት/ቤታቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገራችን በተያያዘችው የልማት፤
የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስርዐት ግንባታ ሂደት ላይ የአመራር ሚና ማጎልበት ነው ፡፡

የተማሪዎች አደረጃጀት አበይት ተግባራት

• በተማሪዎች አደረጃጀት ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• የርስ በርስ የመረዳዳት ባህል በማጐልበት የትምህርት ውጤታቸውንና ስነ ምግባራቸውን ማሻሻል፣

29
• በተለያዩ ኮሚቴዎች በመሳተፍ የተማሪዎችን መብትና ጥቅም ማስከበር ፣

• ተማሪዎች የአመራር ሚናቸውን የሚያጐለብትበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የትምህርት ቤታቸውንና የአካባቢያቸውን ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣

• የት/ቤታቸውን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ከአደጋ መከላከል ፣

1.6. በሁሉም ተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ሊከናወኑ የሚገባቸው ዓበይት ተግባራት

• በክበባትና የተማሪ አደረጃጀቶች ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር

• የአባላት ምዝገባ ማከናወን

• የአመራር ምርጫ ማከናወን

• የዓመቱን የሥራ ዕቅድና የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት

• የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ ማዘጋጀትና ማፀደቅ

• ቋሚ የግኑኙነትና የግምገማ ጊዜ መወሰን

• በአደረጃጀት ስር እንደተገለፀው የክበባት አመራሮች በክበቡ ስር የተዘረዘሩትን የስራ ዘርፎች ተከፋፍሎ መምራት

• የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት

• ቃለ ጉባኤዎች፤ ሰነዶችና ስታስቲካዊ መረጃዎች ማደራጀት

• የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ማዘጋጀት

• ለሥራ ማስኬጃና ለሌሎች ተግባራት የሚውል ሀብት ማፈላለግ

• የማትጊያና የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት

• የውስጥ ኦዲት አሠራር መዘርጋት

• የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት

1.7. የተጓዳኝ ትምህርት መለያ ባህሪያት

 የተጓዳኝ ትምህርት በአመራሩና በአፈፃፀሙ ተማሪ ተኮር የሆነ ቀጥተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ በስርዓተ
ትምህርቱ የተካተቱት ንድፈ ሀሳቦች ወደ ተግባር የሚለወጡበት አደረጃጀት ነው፡፡

30
 የተጓዳኝ ትምህርት ትኩረቱ በተማሪዎች ቀጥተኛ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ነው፡፡ ሲታቀድና ሲታሰብ
ተማሪውን ለማዝናናት ፣ አካላዊ ማህበራዊና ሥነ ውበታዊ ተሰጥኦውን ለማበለፀግ ፣ የአመራር ችሎታን
ለማዳበር ወዘተ ሊሆን ይገባል ፡፡ በአጠቃላይ ተጓዳኝ ትምህርት ተማሪ - ተኮር እንቅስቃሴ ነው ፡፡

 በተራ ቁጥር 1.3.12. ከተጠቀሰው በስተቀር ተሣትፎ በፈቃደኝነት ነው ፡፡ ምንም እንኳን ተማሪዎች
ተሣታፊ እንዲሆኑ ቢመከሩ ፣ አመራር ቢያገኙና ግፊት ቢደረግባቸውም አምነውና ሙሉ ፈቃደኛ ሆነው
ካልተሳተፉ በስተቀር ግዴታ የለባቸውም ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች እንደ ክፍል ውስጥ ትምህርትና ተሳትፎ ከነጥብ /ማርክ/ ጋር የተያያዘ
ግምገማና ምዘና አይካሄድበትም ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት አመራርና አስተዳደር በተማሪዎችም ተሳትፎ ይከናወናል ፡፡ እንዲያውም ከዕቅድ

አወጣጥ እስከ አፈፃፀም ድረስ ተማሪዎች ራሳቸው እንዲያቅዱ ፣ እንዲመሩ ፣ እንዲቆጣጠሩ ፣
እንዲያከናውኑ ፣ እንዲገመግሙና እንዲስተባብሩ ይጠበቃል ፡፡ መምህራን በረዳትነት ፣ በአማካሪነት ፣
አቅጣጫ በማስያዝና አዳዲስ ዕውቀቶችንና ክህሎቶችን በማስጨበጥ የትምህርት ዓላማዎች ከግብ
እንዲደረሱ በመምራት ይሳተፋሉ፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት የተወሰነ የአሠራርና የጥናት መንገድ አይታይበትም ፡፡ አንዳንዱ እንቅስቃሴና ዝግጅት
ለህብረተሰቡ የሚቀርብ /ለምሳሌ ፡- ድራማ ፣ ኤግዚቢሽን ፣ የወላጆች በዓል ወዘተ …./ ሊሆን ይችላል፡፡
አንዳንዱ ደግሞ የግል ፍላጎትንና ስሜትን ለማርካት ብቻ የማከናወን ፣ /ለምሳሌ ፡- የሥዕል ፣ የፎቶግራፍ /
ሲሆን እንደየ አደረጃጀቱ ባህሪ በግልም ሆነ በቡድን ሊሰራ ይችላል፡፡ የልምምድ ጊዜው እንደ ክፍል
ትምህርት የተወሰነና የተመጠነ ካለመሆኑም በላይ የመምህራን ኃላፊነትና የሥራ ድርሻም የሚያይልበት
ጊዜ ይኖራል፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ወይም ተግባሮች ሙሉ በሙሉ በተማሪዎችና በመምህራን በት/ቤት

ደረጃ የሚታቀዱ ናቸው ፡፡ እንደ ክፍል ውስጥ ትምህርት ተዘጋጅቶ የሚላክ የመምህሩ መምሪያ ፣
የተማሪው መጽሐፍ ወይም ሲለበስ የለውም፡፡

 በአንዳንድ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ላይ የክፍል ደረጃና ዕድሜ ሳይለይ ማንኛውም ተማሪ
የሚሳተፍበት ሁኔታ ይኖራል ፡፡ ለምሳሌ ፡- በድራማ ክበብ የ 9 ኛ ፣ 1 ዐኛ ፣ 11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል
ተማሪዎች በጋራ ሊሳተፉ ይችላሉ ፡፡

ክፍል ሁለት ፡

2. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት ፣ አመራርና አሠራር

2.1. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት

 የት/ቤቱን ማህበረሰብ በፍላጐታቸውና በዝንበሌያቸው መሠረት በአባልነት ይመዘግባል ፣

31
 በአባላቱ ምልዐተ ጉባኤ ከ 5-7 የሚሆኑ የሥራ አመራርን ያስመርጣል ፣

 የመተዳደሪያ ደንብና ሥርዓት ያወጣል ፣

 የትምህርት ዘመኑን የተጓዳኝ ትምህርት ዕቅድና የድርጊት መርሀ ግብር ያዘጋጃል፣

 የሥራ ክፍፍል ያደርጋል ፣

 የግምገማ ሥርዓት ይዘረጋል ፣

2.2. በተጓዳኝ ትምህርት የልዩ ልዩ ክፍሎች ሀላፊነትና ተግባር

ሀ/ በተጓዳኝ ትምህርት የመምህራን ሀላፊነትና ተግባር

መምህራን በሀላፊነት የተረከቧቸውን ተማሪዎች በየደረጃቸው በሚሰጡት ትምህርት በእውቀት ፣ በክህሎት በአመለካከትና በአካል
በመገንባት አምራች ፣ በስነ ምግባር የተሻሉ እንዲሆኑ ኮትኩቶ ብቁ ዜጋ የማድረግ ከባድ ሀላፊነት ተሸክመዋል ፡፡ ዕውቀታቸው ፣
የመምራትና የማስተማር ዘዴያቸው እንደዚሁም ሞያተኝነታቸው እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም በተለይ ለተጓዳኝ ትምህርት ያላቸው አመለካከትና
አቋም በአደረጃጀቶቹ ውጤታማነት ላይ የወሳኝነት ሚና ይኖረዋል ፣

ስለዚህ በተጓዳኝ ትምህርት አስተባባሪነትና መሪነት የሚመረጡ መምህራን የሚከተሉት ሃላፊነቶች ይኖራቸዋል፡፡

 የተጓዳኝ ትምህርት ጽንሰ ሀሳብንና ዓላማን ተገንዝበው ለተማሪዎች ግንዛቤ ማስጨበጥ ፣

 በተጓዳኝ ትምህርት ኘሮግራሞችና የክበቦችን ዕቅድ አወጣጥና አፈፃፀም ላይ በንቃት መሳተፍ ፣

 ተማሪዎችን በመርዳትና በማማከር እንዲሁም በማነቃቃትና በማስተባበር ለትምህርት ፣ለተሳትፎና ለሥራ ማዘጋጀት ፣

 ተማሪዎች በአመራር፣ በአደረጃጀት፣ በክትትልና ድጋፍ እንዲሁም በግምገማ ስርዓት እየተሳተፉ እንዲለማመዱ
ማዘጋጀት ፣

 በክፍል ውስጥ ከሚሰጡት ትምህርቶች ጋር ተዛማጅና ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ተግባራዊ ኘሮጀክቶችን፣ የምርምር
ሥራዎችንና ልዩ ልዩ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ ፣

 ፣የተለያዩ ባለሙያዎችን፣ወላጆችንና መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር የፋይናንስ ፣

የሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ የሚገኝበትን አግባብ ማመቻቸት ፣

 ሀላፊነትን በሙሉ ፈቃደኝነት በመቀበልና በሌሎችም ተግባራት ከፍተኛ ሚና በመጫዎት አርአያ ሆኖ መገኘት፣

ለ/ በተጓዳኝ ትምህርት የተማሪዎች ሀላፊነትና ተግባር ፣

32
 ተማሪዎች የመማር፤ የመመራመር፤ የፈጠራ ችሎታቸውን ለማዳበርና በመብታቸው ለመጠቀም በተማሪነታቸው
ያለባቸውን ግዴታና ኃላፊነት በብቃት መወጣት ፣

 ንቁና ታታሪ ተማሪዎች ሆኖ መገኘት ፣

 ከዕቅድ እስከ ዕቅድ አፈፃፀምና ውጤት ባለው ሂደት በንቃት መሳተፍ፣

o የሀላፊነትና የባለቤትነት ስሜትን ማዳበር፣

o የዲሞክራሲ ባህል እንዲሰፍን ሚናቸውን መወጣት፣

o የህብረተሰቡን ጠቃሚ ልምድ፣ ወግና ባህል ማክበርና በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ተግባራዊ ማድረግ፣

o የራስ ተነሳሽነትና የአመራር ብቃትን መለማመድ፣

o በት/ቤቱ በሚደራጁና በሚካሄዱ የክፍል ውስጥና ውጭ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችና ኘሮግራሞች ሁሉ ንቁ ተሣትፎ

ማድረግ ፣

o የመፍጠርና የመመራመር ችሎታቸውን ማጎልበት፣

o ስነ ውበትንም የማድነቅ፣ የተፈጥሮ ሁብትንና የሀገር ታሪካዊ ቅርሶችን የመንከባከብ ብቃትን ማዳበር፣

ሐ/ የትምህርት ቤት አመራር ኃላፊነትና ተግባር

 የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀት እንዲኖር ስርዓት ይዘረጋል ፣

 የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ያዘጋጃል ፣

 ስለተጓዳኝ ትምህርት ጠቀሜታ በማስገንዘብ ተማሪዎችና መምህራንን እንደየፍላጐታቸውና ዝንባሌያቸው እንዲመዘገቡ ያደርጋል ፣

 የአመራር አካላትን እንዲመረጡ ያስተባብራል፤እውቅና ይሰጣል፣

 በትምህርት ቤቱ ዕቅድ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ያካትታል፤ ይከታተላል ፣ ይደግፋል ፣

 የማትጊያ ስርዓት ይዘረጋል ፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤

 የግማገማ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጋል ፣

 ለስራ ማስኬጃና ለስልጠና በጀት ይመድባል፤ ለስራ የሚሆኑ ምቹ ቦታዎችን ያዘጋጃል፤

 የንብረትና የበጀት አጠቃቀም የመንግስትን ፋይናንስ ስርዐት መከተሉን ያረጋግጣል፤

 የተጓዳኝ ትምህርትን በሚመለከት የተሟላ መረጃ ይይዛል፤ሪፖርትም ያደርጋል፡፡

33
መ/ የክፍለ ከተማና የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ሀላፊነትና ተግባር

- በዕቅዳቸው መሰረት በቼክሊስት የተደገፈ ወቅታዊ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ

- ለተጓዳኝ ትምህርት አመራሮች ስልጠና ያዘጋጃሉ፣

- በምክክር መድረክ ላይ በመገኘት ሀሳብና አቅጣጫ ይሰጣሉ ፣

- የተጓዳኝ ትምህርት አውደ ርዕይ ያዘጋጃሉ

- በትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋሉ፤

- ግምገማን መሰረት በማድረግ በተጓዳኝ ትምህርት የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ትምህርት ቤቶችና መምህራንና ተማሪዎች
እንዲሁም አደረጃጀቶች የማትጊያ ስርአት ተጠቃሚ ያደርጋሉ፤

- ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፤

ሰ/ በትምህርት ቤት ደረጃ የወተመህ ሚና

- በተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ የወላጆችንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ያጎለብታል፤

- ለተማሪዎች ተሳትፎ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፤

ረ/ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ ኃላፊነትና ተግባር

- የተጓዳኝ ትምህርት በተመለከተ መመሪያዎችን፤ ማኑዋሎችን፤ ደንቦችን ወዘተ ያዘጋጃል፤ ያሻሽላል፤

አፈፃጸማቸውን ይከታተላል፤

- ለተመረጡ ናሙና ት/ቤቶች በቼክሊስት በተደገፈ የድጋፍ ክትትልና ግብረ መልስ ሥራ ይሠራል ፣

- በከተማ ደረጃ የትምህርት ፌስቲቫልና የፈጠራ ሥራዎች አውደ ርዕይ ያዘጋጃል፤የላቀ ውጤት ላስመዘገቡም እውቅና ይሰጣል ፣
ይሸልማል፤

- ለተጓዳኝ ትምህርት አመራሮች ስልጠና ያዘጋጃል፣

- በምክክር መድረክ ላይ በመገኘት ሀሳብና አቅጣጫ ይሰጣል ፣

- ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለፈጠራ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤

- በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ንድፈ ሃሳቦች በተማሪ አደረጃጀቶችና ክበባት ወደ ተግባር ስለመለወጣቸው የዳሰሳ ጥናት ያደርጋል

- በትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋል፤

34
2.2. የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች የአሰራር መርሆዎች

 በትምህርት ቤቶች የተጓዳኝ ትምህርት በት/ቤቱ አመራር በጋራ የሚመራ ሆኖ የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ር/መምህር በበላይነት
ያስተባብራል፤

 በአዲስ መልክ የሚዋቀር ክበብ ወይም የተማሪዎች አደረጃጀት ከት/ቢሮ እውቅና እስካልተሰጠው ድረስ ማዋቀር አይቻልም፤

 ክበባት ከጾታ፣ ከዘር፣ ከእምነት፣ ከኢኮኖሚ ደረጃ፣ ወዘተ… ልዩነት የጸዱ መሆን አለባቸው፤

 የማነቃቂያና የማበረታቻ ስርዓት ሊኖራቸው ይገባል፤

 ከባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል፤

 አመራሮቻቸውን በዲሞክራሲያዊ መርህ መምረጥ ይኖርባቸዋል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ትምህርታዊ እሴት ያላቸው መሆን አለባቸው፤

 ተማሪዎች በተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ላይ በንቃት መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ሃላፊነትንም ጭምር መጋራት ይኖርባቸዋል፤

 የትምህርት ቤቱ መምህራን ቢያንስ በሁለት ክበባት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፤

 ለሁሉም የተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ተገቢው ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፤

 ለመደበኛው ትምህርት የሚሰጠውን ትኩረት ያህል ለተጓዳኝ ትምህርትም ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፤

 አንድ ክበብ ለማቋቋም እንደት/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ ቢያንስ ሃያ አምስት ፈቃደኛ ተማሪዎች፤ መምህራንና
የአስተዳደር ሰራተኞችን ያቀፈ ሆኖ ቢደራጅ ለአሰራር አመቺ ይሆናል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች የተማሪዎችን ፍላጎት፣ ዝንባሌ እና ስሜት መሰረት ያደረጉ ይሆናሉ፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች ከመደበኛው ትምህርት ሰዓት ውጪ የሚከናወኑ ይሆናሉ፤

 የክበባት አስተባባሪዎች የአገልግሎት የስራ ዘመን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት ብቻ ይሆናል፤

 የተጓዳኝ ትምህርት ለልዩ ፍላጎትና ለሴቶች ተሳትፎ ልዩ ትኩረት መስጠት ይኖርበታል፤

2.3. መደራጀት የሚገባው የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ አወሳሰን

 ለትምህርት ዓላማዎች መሳካት ያላቸው አስተዋጽዎ፤

 ከተማሪዎች ፍላጎት የመነጩ ስለመሆናቸው፤

 ከእንቅስቃሴው አንጻር ፍላጎትና ችሎታ ያላቸው ወይም ሊመደቡ የሚችሉ መሪ መምህራን መኖራቸው፤

35
 ጊዜ ፤ግብዓትና ቦታ መኖሩ ሲረጋገጥ፤

 የበርካታ ተማሪዎችን ተሳትፎ የሚጠይቁ እንቅስቃሴ ኣይነቶች ከሆኑ፤

 በህብረተሰቡ ተቀባነት ያላቸው መሆኑ፤

 የመንግስት ፖሊሲና ህጎችን የማይቃረኑ መሆናቸው፤

 ለአደጋዎች የማያጋልጡ መሆናቸው፤

 በተማሪዎች ላይ የወጪ ጫና የማያስከትሉ ከሆኑ፤

 ዲሞክራሲዊነታቸውና ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

2.4. የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ ግምገማ ስርዓት

የአንድ ት/ቤት የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መሰረታዊ የግምገማ ሂደት የተማሪዎችን አጠቃላይ ደህንነት ለማስጠበቅና ሁለንተናዊ እድገት
ለማሻሻል በሚያስችል ሁኔታ መከናወን ይኖርበታል፡፡ ግምገማው ከአካባቢያዊ አደረጃጀትና ሁኔታዎች መመቻቸት፤ ከባህሪይ ለውጥ
ማምጣት፤ ከስራ ውጤት፤ ከአሰራር ለውጥና መሻሻል አኳያ የሚታይ ሲሆን ዝርዝር የመገምገሚያ ነጥቦቹ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

 የክፍል ውስጥ ትምህርታቸውን ከማዳበር አንጻር፤

 የተማሪዎችን ፍላጎት እና ስሜት ስለማርካታቸው፤

 ብቃትና ፍላጎት ያላቸው መሪ መምህራን ስለመመደባቸው፤

 አስተባባሪ መምህራኑ የተመረጡበት ሁኔታ፤

 በእንቅስቃሴው የተማሪዎች ተሳትፎ ደረጃ፤

 ለእንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ እና ዕድል የተፈጠረ ስለመሆኑ፤

 የማበረታቻ ስርዓት ስለመዘርጋቱ፤

 በእያንዳንዱ አደረጃጀት ምን ያህል ተማሪዎች (ወነድና ሴት) እንደተሳተፉ፤

 ተማሪዎች ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚያበረክቱት አገልግሎት፤

 ህብረተሰቡ ስለሰአደረጃጀቱ ያላቸው እይታ፤

 እያንዳንዱ አደረጃት የመተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀቱ፤ማስፀደቁና ተግባራዊ ስለማድረጉ፤

 የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴዎች የፋናንስ ሀ፤ኔታ

 በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአደረጃጀቱ ወቅታዊ ግምገማ ስለመደረጉ፤

36
 የእያንዳንዱ አደረጃጀት እንቅስቃሴ መረጃ በሚገባ ስለመያዙ፤ወዘተ.ይሆናል፡፡

ክፍል ሶስት

የክትትል፣ድጋፍ፣ግምገማና ግብረመልስ እንዲሁም የሪፖርት ስርዓት

3.1. በክትትል፤ ድጋፍ፤ ግምገማና ግብረ መልስ ስርዓት በየእርከኑ ያሉ አካላት ሚና

3.1.1. የትምህርት ቤቶች ሚና

 አጠቃላይ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መረጃዎችንና ተማሪዎች አደረጃጀቱን ጠጠቅመው የሚያሳዩትን
ወቅታዊ ለውጥ መከታተል፣ መቀመርና ማደራጀት መያዝ፣ ለወረዳዎችና ለሚመለከታቸው አጋር አካላት
ማስተላለፍ
 የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን በወቅቱ ማስተላለፍ
3.1.2. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት
 ለትምህርት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
 ግብረመልስ መስጠት
 መረጃና ሪፖርት በማደራጀት ለክፍለ ከተማና ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ

3.1.3. የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች

 ለትምህርት ቤቶችና ለወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ፣ግብረመልስ መስጠት
 አጠቃላይ የክፍለ ከተማውን ወቅታዊ የተጓዳኝ ትምህርት እንቅስቃሴ መረጃና የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
በማጠናቀር ለትምህርት ቢሮና ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ

3.1.4. የትምህርት ቢሮ
 ለክፍለ ከተሞች፣ ለወረዳዎችና ለትምህርት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ ግብረመልስ መስጠት
 ከክፍለ ከተማ የተገኘውን መረጃ ማደራጀት፣መተንተን፣የተገኘውን የትንተና ውጤት ለቀጣይ ስራዎችና
ዕቅዶች በግብዓትነት መጠቀም ለአጋርና ለተባባሪ አካላት ማሰራጨት፤

3.2. የክትትልና ድጋፍ አግባብ

ክትትልና ድጋፉ ሁሉንም መስተጋብሮች ማለትም
 በመስክ ጉብኝት
 በሪፖርት
 የአካል ግምገማ (በስብሰባ፣በኮንፍረንስ፣በምክክር መድረክና በቋሚ የግንኙነት ጊዜ)
የዳሰሳ ጥናት ማድረግን ባካተተ መንገድ ይከናወናል፡፡
ስለሆነም ተግባራቱ በሚዘጋጀው እቅድ መሰረት የሚተገበሩ ሲሆን ሪፖርቶች ደግሞ እንደየስራው ባህሪ በጽሁፍ
ይቀርባሉ፡፡በቀረበው ሪፖርት መሰረት የግብረ-መልስ ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ይከናወናል፡፡
37
የአካል ግምገማ በማድረግም ጠንካራ ጎኖችንና ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቶች የሚስተካከሉበት አሰራር ይፈጸማል፡፡
በተጨማሪም የሱፐርቪዥን ስራ በምልከታ እና የተለያዩ ችግር ፈቺ ቼክሊስቶችን በማዘጋጀት ወርዶ በመደገፍ ተጨባጭ
በሆነ ሁኔታ የክትትልና ግምገማ ስርአቱ ቀጣይነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ይከናወናል፡፡

አባሪ ሰነዶች

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምሀርት ቢሮ

ታህሳስ 2007

አዲስ አበባ

38
39
1.የስፖርት ክበብ

ት/ቤቶች ወጣቱን በአዕምሮና በአካል ብቃት አዘጋጅቶና ኮትኩቶ ለማውጣት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ
በመሆኑ በስፖርት እንቅስቃሴዎችና ውድድሮች ተማሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሮአቸው እንዲያድጉ ለማድረግ የሚያስችል አደረጃጀት
ነው፡፡ በዚህ አደረጃጀት ስር የሚተገበሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፡-

- አትሌቲክስ /ሩጫ ፣ውርወራ፣ ዝላይ… ወዘተ/ ፣

- ኳስ ጨዋታዎች ( የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ ፣ የቅርጫት ኳስ ፣የእጅ ኳስ ፤ የጠረጴዛ ኳስ….. ወዘተ)

- የጂምናስቲክ እንቅስቃሴዎች

- የሀገር ባህል ስፖርታዊ እንቅስቃሴና

- ዘመናዊ የቤት ውስጥ ጨዋታዎችን ያጠቃልላል፣

የክበቡ ዋና ዋና ተግባራት

የተማሪዎችን አካልና አዕምሮአዊ ዕድገት በሚፈለገው መልኩ እንዲጎለብት ማድረግ መሰረታዊ ዓላማው ሲሆን ክበቡ
የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡

 ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች በየዘርፉ መመዝገብ፤

 በየዘርፉ ብቁ ሊያደርጋቸው የሚችለውን ስልጠና መስጠት፤

 በየስፖርት ዓይነቱ የፕሮግራም ድልድል በመስራት የተሻሉ ተወዳዳሪዎችን መምረጥ፤

 የት/ቤቱን የውስጥ ውድድር መርሃ ግብር ማዘጋጀትና ወደ ተግባር መግባት፤

 በወረዳ፤ በክ/ከተማ ፤በከተማ እንዲሁም በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚዘጋጁ ውድድሮች ራስን ማብቃትና መሳተፍ፤

 አስፈላጊውን የማበረታቻ ስልት መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ፤

 የላብ መተኪያ እና ለተለያዩ ቁሳ ቁሶች የሚሆን በጀት ማፈላለግና ተግባራዊ ማድረግ፤

 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ሊወዳደሩ የሚችሉበትን ዘርፍ መለየት፣ ማብቃትና በውድድር ተሳታፊ
የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

አባሪ ሰነዶች

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

40
ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

41
2.የኪነ-ጥበብ ክበብ

42
በክበቡ ሊካተቱ የሚገባቸው የድራማ፤ ሙዚቃ ፤ ስዕል፤ ቅርጻ ቅርጽ ፤የባህል አልባሳት ትርዒት፤ፋሽን ሾው ፤የትምህርት ቤት ሽብርቅ
ስራዎች፤ ወዘተ. ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ተማሪዎች በገሀዱ ዓለም ያለውን ዕውነታ የሚገልጹበት፣ የሚያስተዋውቁበትና ፍላጎታቸውን የሚያንጸባርቁበት እንዲሁም
ከትምህርት ቤት ማህበረተሰብ ጋር የሚግባቡበትና ትምህርታዊ መረጃ የሚያስተላልፉበት መንገድ አድርጎ የማደራጀትና ጥቅም ላይ
የማዋል ስራ መስራት ይገባል፡፡ ተማሪዎች የአለምን ተጨባጭ ሁኔታ የማወቅና የመረዳት፣ በመዝናናት መረጃ የማግኘትና
ፍላጎታቸውን የሚያዳብሩበት መድረክና አደረጃጀት ይፈልጋሉ፣ በዚህ መሰረት የክበቡ ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለው
ተዘርዝሯል፡፡

የኪነ-ጥበብ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸው በዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 ለክበቡ የተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ ግብዓትን ማሟላት(የሙዚቃ መሳሪያዎች፤አልባሳት፤ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶች፤ቅርጻ-

ቅርጾች፤የስዕል መሳሪያዎች ወዘተ.)

 በተለያዩ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የድራማ፣ የሙዚቃና የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ የአልባሳት ትርዒት የስዕልና ቅርጻ
ቅረጽ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 የኪነ ጥበብ ስራዎችን የሚመለከቱበትና ልምድ የሚቀስሙበትን ሁኔታዎች መፍጠር፤

 አባሪ ሰነዶች

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

 ዋቢ ጽሁፎች

 ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ

አበባ፡፡

43
44
3.የቋንቋ ክበብ

ይህ ክበብ ስነ-ጽሁፍ፤ ክርክር፤ የሚኒ ሚዲያ አገልግሎት፤ የንባብ ልምድ፤የቤተ መጻህፍት፤ ውይይት፤ ጉባዔ፤ ህትመት
ነክ ስራዎች(መጽሄት ፤በራሪ ጽሁፎች፤ጋዜጣ ወዘተ)ያጠቃልላል፡፡
45
ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደት ላይ በቋንቋ ትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በክበቡ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮአቸው ራሳቸውንና
ሀሳባቸውን መግለፅ የሚችሉ ከመጻፍ፣ ማንበብና ሀሳባቸውን በተገቢው ከመግለፅ ባለፈ ቋንቋን ተጨማሪ ዕውቀት የማግኛ መሣሪያ
አድርጎ ለመጠቀም ይረዳል፡፡ በቋንቋ እጥረት ምክንያት ሊመጣ ከሚችለው ችግር ለመውጣትና በተለይም የመማር፣ የክርክር፣
ስነፅሑፍና ውይይት ኮንፈረንስ የማዘጋጀት ስራ ለማከናወን ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ በት/ቤት ደረጃ ተግባራዊ ሲሆን የተሻለ ውጤት
የሚመዘገብበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

የቋንቋ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 ተማሪዎችን በየፍላጎታቸውና በየዝንባሌያቸው እና በየዘርፉ ለይቶ መመዝገብ፤

 በተለያዩ የክበቡ ዘርፎች ስልጠና መስጠት፤

 የትምህርት ቤቱን ዓመታዊ መጽሄት ማዘጋጀት፤

 ከተለያዩ ዓለማት የተገኙ መረጃዎችን ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ዘገባ ማቅረብ፤

 በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የክርክርና የውይይት መድረክ ማዘጋጀት ፤

 የትምህርት ቤቱ ልሳን ሆኖ ማገልገል፤

 የተለያዩ ስነ ጽሁፎችና መነባንቦችንና ጥያቄና መልስ ውድድሮችን ማካሄድና ለተማሪዎች በሚኒ ሚዲያ
ማቅረብ፤

 የቤተ መጻህፍት ግብዓቶችን እንዲሟሉ ማድረግ(ጋዜጦች፤መጽሄት፤ማጣቀሻ መጻህፍት፤ጆርናሎችን ወዘተ.)፤

 ት/ቤቱን ለንባብ ምቹ ማድረግና የንባብ ውድድሮችን ማካሄድ፤

 ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ስነ-ቃሎችንና የተለያዩ የቋንቋ ትውፊቶችን ማዳበር፤

 የቋንቋ ማሻሻያ ስልቶችን በመቀየስ ወደ ተግባር መግባት፤

 አባሪ ሰነዶች

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

46
 ዋቢ ጽሁፎች

 ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ

አበባ፡፡

47
4.የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ

የፈጠራ ስራዎች፤ አይ ሲቲ፤ የቤተ ሙከራ አጠቃቀም ፤የጥናትና ምርምር ስራዎች ወዘተ.ተማሪዎች የተለያዩ የፈጠራ
ችሎታቸውን አውጥተው ወደ ተግባር ሊለወጡበት የሚችሉበት ዕድል ለመፍጠር የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ መቋቋም ት/ቤቶች
48
ተማሪዎችንና የመምህራንን አቅም በመጠቀም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረትና ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች በክበቡ ግንዛቤ እንዲያገኙ
ያደርጋል ፡፡ በክበቡ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሌሎች ሀገሮች የደረሱበት ደረጃ ላይ መድረስ የሚያስችለን ሁኔታ መፍጠር
እንችላለን፡፡ ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂን ውጤት ከሚጠቀሙ ተቋማትና እንዱስትሪዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት
በማድረግ መስራት ይችላሉ ተብሎም ይታመናል፣

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብን በማጠናከር በተሻለ ለመስራት የሚያስችሉ ጥናቶችን ማካሄድ ያቻላል፡፡በተጨማሪም በየደረጃው
ከተቀመጠው ስርዓተ ትምህርት የተቀዳ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ግብዓት ሆኖ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ሊያሳድግ የሚችል ንድፈ
ሀሳብ ከሂሳብ፣ ከፊዚክስ፣ ከኬሚስትሪ ከባዮሎጂና… ወዘተ የትምህርት ዓይነቶች በመውሰድ ቴክኖሎጂ የሚፈጠርበትና የሚሰራበት
ሁኔታን የማመቻቸት ስራ ት/ቤቶች መስራት ይገባቸዋል፡፡ከዚህ አንጻር የሳይንስን ቴክኖሎጂ ክበብ ሃላፊነትና ተግባር እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ዋና ዋና ተግባራት

 በሳይንስና በፈጠራ ስራ ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች መመዝገብ፤

 ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር ስልጠናዎችን ማመቻቸት፤

 ለሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ለፈጠራ ስራ የሚያግዙ ግብዓቶችን ማሟላት (ኮምፒተሮች፤ ኢነተርኔት፤ ፐላዝማ ቴሌቭዥን፤
ሬዲዮኖች፤ የሳይንስ ቤተ ሙከራ ዕቃዎችንና፤ ከአግልግሎት ውጪ የሆኑ ሌሎች ቁሳቁሶች)፤

 የምርምር መርሃግብር፤ጊዜና ቦታ ማመቻቸት፤

 ጥናታዊ የምርምር ጽሁፎችን ማዘጋጀት፤

 ተማሪዎች በቤተ ሙከራና በትምህርት ማበልጸጊያ እንዲጠቀሙ ማበረታታት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማካሄድ፤

 የሳንይስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ማዘጋጀት፤

 ለሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የማጠናከሪያ ትምህርትና ድጋፍ መስጠት፤

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

49
 ዋቢ ጽሁፎች

 ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ

አበባ፡፡

50
5.የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ

51
በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሀገርህን እወቅ፤ ቅርስ ጥበቃና ክብካቤ፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፤መጤ ባህሎች፤የህ/ሰብ ሳይንስ
ትምህርቶች ፤ወዘተ. ሊደራጁ ያችላሉ፡፡

የህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ አደረጃጀት በት/ቤቶች መኖር በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ንድፈ ሀሳቦችን የሚያጠናክር በመሆኑ
ተማሪዎች የጂኦግራፊ፤ የታሪክ፣ ፣የኢኮኖሚክስ፤ ቢዝነስ ትምህርቶች ከማህበራዊ ህይወታቸው ጋር በማገናኘት ሊገነዘቡ
የሚችሉት በርካታ አስተሳሰቦችና ተግባራት እንዲኖሩ ያደርጋል፣ ተማሪዎች አካባያቸውን በውል የሚረዱበትና የማህበረሰባቸውን
ወግና ባህል በማወቅ በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ተግባራዊ የሚያደርጉበት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በህብረተሰብ ሳይንስ ክበብ የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን እንደ ፍላጎታቸውና ዝንባሌያቸው ምዝገባ ማካሄድ፤

 በክበቡ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት፤

 ከባህል ያፈነገጡ፣ መጤና አላስፈላጊ ድረጊቶች የሚወገዱበት ሁኔታ ላይ መስራት(ፖርነግራፊ፤ግብረ ሰዶማዊነት፤የእብደት ቀን

ወዘተ.)

 ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች የሚቀረፉበት ሁኔታ ላይ መስራት፤

 ትምህርታዊ ጉብኝት ማዘጋጀት፤ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶችን መጠበቅና መንከባከብ፤

 ተማሪዎች ለብሄራዊ ማንነታቸውና ለታሪካቸው ክብር እንዲሰጡ ማብቃት፤

 የዎርክ-ሽትና ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፤

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

 ዋቢ ጽሁፎች

 ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

52
53
6.የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ

54
ክበቡ የበጉ አድራጐት ፣ የትራፊክ ፣ የፖስታ ፣ የስካውት ወዘተ አገልግሎቶችን የሚያካትት ሲሆኑ የክበቡ ዓላማ በተማሪዎች የሚከሰቱ
የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮችን በመቅረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ ነው ፡፡

የማህበራዊ አገልግሎት ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ያለባቸውን ተማሪዎች በመለየት ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ማመቻቸት፣

 የትራፊክ ደንቦችን በማስተዋወቅ አደጋዎችን መከላከል ፣

 ተማሪዎች የፖስታ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የስካውት አገልግሎት የሚስፋፋበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

 ዋቢ ጽሁፎች

 ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ

አበባ፡፡

55
7.የጤና አጠባበቅ ክበብ

56
ክበቡ ትኩረት የሚያደርግባቸው ዘርፎች የግልና የአካባቢ ንፅሕና አጠባበቅ ፣ የቀይ መስቀል ፣ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና
መቆጣጠር ፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ፣ የአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ሕገወጥ ዝውውርና አጠቃቀም መከላከል
እንዲሁም የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሲሆኑ ዓላማውም በተማሪዎች የሚከሰቱ የተለያዩ ከጤናና ከሥነ ተዋልዶ ጋር የተሳሰሩ
ችግሮች በመፍታት የመማር ማስተማር ሂደቱ ውጤታማ የሚሆንበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የጤና አጠባበቅ ክበብ አበይት ተግባራት

 ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥነ ተዋልዶ ጉዳይ፣ በኤች አይ ቪ ኤድስና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን
ማዘጋጀት ፣

 ለክበቡ አባላት ል ልዩ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀት ፣

 በኤች አይ ቪ ኤድስና በተላላፊ በሽታዎች የተጠቁ ተማሪዎችን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት
የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

 የት/ቤት ግቢንና መማሪያ ክፍሎችን ማፅዳት ፣

 ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በፅዳት ዘመቻዎች ላይ መሳተፍ ፣

 በአደገኛ መድሃኒቶች እና ዕፆች ተጠቂ የሆኑትን በመለየት ተገቢውን የድጋፍና የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ
ማመቻቸት ፣

 ለጤና ጠንቅ የሆኑ በትምህርት ቤት ዙሪያ የሚገኙ አዋኪ ሁኔታዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የመከላከል
ስራ መስራት ፣

 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና በማድረግ እርዳታ የሚፈልጉ ተማሪዎችን መርዳት ፣

 ከሕክምና ተቋማት ተቀናጅቶ በመሥራት የተለያዩ በሽታዎችና አደጋዎችን መከላከል፣

 በት/ቤቶች በተማሪዎችና መምህራን የደም ልገሳ እንዲከናወን ማድረግ ፣

 የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መስጠት

 በግልና በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ የክበቡ አባላት አርአያ ሆነው እንዲገኙ ማብቃት

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ

57
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

58
8.የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ

የክበቡ ዓላማ ተማሪዎች ስለአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው የነቃ ተሣትፎ እንዲያደርጉና ምቹ የመማር ማስተማር
አካባቢ መፍጠር ነው ፡፡
59
የአካባቢ ጥበቃና እንከብካቤ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 የትምህርት ቤት ግቢ ማስዋብና በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ መሳተፍ ፣

• ግንዛቤ በማሳደግ አካባቢ ከብክለትን መከላከል ፣

• በችግኝ ተከላ ላይ መሳተፍ ሌሎች እንዲሳተፉም ቅስቀሳ ማድረግ፣

• ምቹ የማጥኛ፣ የመመገቢያ ፣ የመጫወቻና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሟሉ ጥረት ማድረግ፣

• ጊዜ ያለፈባቸው ኬሚካሎች የሚወገዱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• ለአደጋ የሚያጋልጡ ስጋቶች (ጉድጓዶች፤የፍሳሽ ቱቦዎች፤የተላጡ የኤሌትሪክ ሽቦዎች፤ገንዳዎች ወዘተ) በመለየት የሚወገዱበት
ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የጓሮ አትክልቶችን በማልማት ገቢ ማሰባሰብ

• በቂ የመፀዳጃና የውሀ አገልግሎት እንዲኖር ጥረት ማድረግ

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

60
61
9.ሥርዓተ-ፆታ ክበብ

62
የክበቡ ዓላማ በሥርዓተ-ፆታ ዙሪያ የተስተካከለ አመለካከት እንዲፈጠር በማድረግ በሴትና ወንድ ተማሪዎች ላይ የሚደርሱ
ፆታዊ ትንኮሳዎችን በመከላከል ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ በንቃት የሚሳተፉበትና የአመራር አቅማቸውን
የሚያሳድጉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው ፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ክበብ አበይት ተግባራት

• ተማሪዎችን በክበቡ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምዝገባ ማካሄድ፤

 በሥርዓተ ፆታ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• ግንዛቤን በማሳደግ ፆታዊ ትንኮሳን መከላከል ፣

• ለሴት ተማሪዎች የሚያለግሉ የተለያዩ ግብዓቶችን ማቅረብ ፣

• ለሴት ተማሪዎች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ማመቻቸት ፣

• ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ክበባትና ኮሚቴዎች በአመራር የሚሳተፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

63
64
የተማሪዎች ልዩ አደረጃጀት

65
በዚህ አደረጃት የተማሪዎች የልማት ቡድን ፤አንድ ለአምስት የጥናት ቡድን፤ ቶፕ-10 ንና ቶፕ-20፤የአለቆች ህብረት ወዘተ…
የሚካተቱ ናቸው፡፡ዓላማውም ተማሪዎች በአደረጃጀቱ ጠቀሜታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ በመረዳዳት መርህ
የራሳቸውን አቅም ከማጐልበት ባሻገር በት/ቤታቸው ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገራችን በተያያዘችው የልማት፤
የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስርዐት ግንባታ ሂደት ላይ የአመራር ሚና ማጎልበት ነው ፡፡

የተማሪዎች አደረጃጀት አበይት ተግባራት

• በተማሪዎች አደረጃጀት ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣

• የርስ በርስ የመረዳዳት ባህል በማጐልበት የትምህርት ውጤታቸውንና ስነ ምግባራቸውን ማሻሻል፣

• በተለያዩ ኮሚቴዎች በመሳተፍ የተማሪዎችን መብትና ጥቅም ማስከበር ፣

• ተማሪዎች የአመራር ሚናቸውን የሚያጐለብትበት ሁኔታ ማመቻቸት ፣

• የትምህርት ቤታቸውንና የአካባቢያቸውን ሠላምና ደህንነት ማስጠበቅ፣

• የት/ቤታቸውን ሀብትና ንብረት ከብክነትና ከአደጋ መከላከል ፣

1.8. በሁሉም ተጓዳኝ ትምህርት አደረጃጀቶች ሊከናወኑ የሚገባቸው ዓበይት ተግባራት

• በክበባትና የተማሪ አደረጃጀቶች ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር

• የአባላት ምዝገባ ማከናወን

• የአመራር ምርጫ ማከናወን

• የዓመቱን የሥራ ዕቅድና የድርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት

• የመተዳደሪያ ውስጠ ደንብ ማዘጋጀትና ማፀደቅ

• ቋሚ የግኑኙነትና የግምገማ ጊዜ መወሰን

• በአደረጃጀት ስር እንደተገለፀው የክበባት አመራሮች በክበቡ ስር የተዘረዘሩትን የስራ ዘርፎች ተከፋፍሎ መምራት

• የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት

• ቃለ ጉባኤዎች፤ ሰነዶችና ስታስቲካዊ መረጃዎች ማደራጀት

• የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ማዘጋጀት

• ለሥራ ማስኬጃና ለሌሎች ተግባራት የሚውል ሀብት ማፈላለግ

• የማትጊያና የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት

66
• የውስጥ ኦዲት አሠራር መዘርጋት

• የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት

ቅጽ

ተ.ቁ ግብ የታቀዱ ዋና የተከናወኑ የታዩ ሊስተካሉ በባለሙያዎች ምርመራ

ዋና ተግባራት ጠንካራ የሚገባቸው የተሰጠ
ተግባራት ጎኖች አስተያየት

ዋቢ ጽሁፎች

ስጦታው ይማም (1989)፤የተጓዳኝ ትምህርት አፈጻጸም ማኑዋል/መምሪያ፤ ትምህርት ሚኒስቴር፤አዲስ አበባ፡፡

67

You might also like