You are on page 1of 16

በትምህርት ሚኒስቴር

የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጎት ትምህርት ዴስክ

በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የመስክ ሱፐርቪዥን ሪፖርት

አዘጋጅ ፣-

ሽፈራው ማሞ

ኤፍሬም አሊ

ሰኔ 21/2015 ዓም

አዲስ አበባ

1
1. መግቢያ

ትምህርት ሚኒስቴር አርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ክልሎችን ልማት ለማፋጠንና ከሌሎች
ክልሎች ጋር ለማመጣጠን በትምህርት ልማት ዘርፍ ከክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ
የትምህርት ስትራቴጂ ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም በውጤታማነት ለመፈጸምና
ለማስፈጸም በአራቱ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች (አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ)
አማካሪ ባለሙያዎችን በመመደብ ከክልል እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ የዘለቀ ሙያዊ ድጋፍና
ክትትል እየሰጡ ይገኛሉ። በዚህ መሰረት በበጀት ዓመቱ ከዝግጅት ምእራፍ እስከ ማጠቃለያ
ምእራፍ ለልዩ ድጋፉ በታቀዱትና በቼክ-ሊስት ተዘጋጀው በሁሉም ባለሙያዎች ስምምነት
ተደረሶባቸው ከክልሎች ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አስማምተው እንዲፈጽሙ በተደረገው ስምሪት
መሰረት በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የተከናወኑትን ግቦችንና ተግባራትን ክትትልን ድጋፍ በማካሄድ
የተገኘው ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2. የክትትልና ድጋፍ ዓላማ ፣- ጥንካሬና ክፍተቶችን በመለየት ጥንካሬዎችን በማጠናከር


ክፍተቶችን በማሻሻል የትምህርትን ስራ ውጤታማ ማድረግ።
3. የክትትልና ድጋፍ አስፈላጊነት ፣-
 የተማሪዎች የመማር ውጤትና ስነምግባራቸውን ለማሻሻል
 በተመረጡ ወረዳዎችና ት/ቤቶች እርስ በርስ ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ
 ት/ቤቶች ደረጃቸውን ለማሻሻል
 የሚሰጠውን ድጋፉ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ
 የድጋፍ ባለሙያዎችን የስራ ክንውን በማየት ድጋፍ ለማድረግ
4. በክትትልና ድጋፍ የሚጠበቀው ውጤት፡-
 የተሻሻለ የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር
 ደረጃቸውን ያሻሻሉ ትቤቶች
 ቀልጣፋ የስራ ክንዋኔ
5. የክትትልና ድጋፍ ወሰን ፣- በሶማሌ ክልል በሽንሌ ዞን በተመረጡ 2 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና
2 የ2ኛ ደረጃት/ቤቶች ናቸው(የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ
ት/ቤት፣ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ
ት/ቤት)

1
6. በክትትልና ድጋፍ የሚታዩ የትኩረት ግቦች፣-

ግብ 1 የትምህርት ፍትሃዊነትና አካታችነትን በማስጠበቅ የተማሪ ተሳትፎን ማሳደግ

ተግባር 1 ፤- ሁሉም ተማሪዎች በት/ት ገበታቸው ላይ አዘውትረው እንዲገኙ በማድረግ አቋራጭ


ተማሪዎች እንዳይኖር የተከናወኑ ተግባራት ፣-
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አቋራጭ ተማሪዎችን በተመለከተ በ1ኛ ሴሚስተር
ያቋረጡ ተማሪዎች 13 ሲሆኑ እነዚህን ተማሪዎች ወደ ት/ት ገበታ ለመመለስ አቋራጭ
አስመላሽ ተማሪዎች ኮሚቴ ቢኖርም ተማሪዎቹን በተለያዩ ምክንያት ወደ ት/ት ገበታ
ለመመለስ አልተቻለም።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አቋራጭ ተማሪዎችን በተመለከተ በ1ኛ ሴሚስተር
ያቋረጡ ተማሪዎች 12 ሲሆኑ እነዚህን ተማሪዎች ወደ ት/ት ገበታ ለመመለስ በአቋራጭ
አስመላሽ ተማሪዎች ኮሚቴ አማካኝነት 3 ተማሪዎች የተመለሱ ሲሆን 9ኙ ተማሪዎች
በተለያዩ ምክንያት ወደ ት/ት ገበታ ለመመለስ አልተቻለም።
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አቋራጭ ተማሪ በተመለከተ በዚህ
ሴሚስተር ምንም አቋራጭ ተማሪዎች የሉትም። ይህ የሆነበት ምክንያት ት/ቤቱ መምህርን
የቀሩትን ተማሪዎች ለት/ቤቱ ሪፖርት በማድረግ የት/ቤቱ ወመህና የት/ቤቱ አስተዳደር
በጋራ በመሆን በወቅቱ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ተማሪዎች ከት/ት ገበታቸው
እንዳያቋርጡ በማድረጋቸው ነው።
 ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አቋራጭ ተማሪ በተመለከተ በዚህ ሴሚሰተር
60 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች /Remidial/ ት/ት ባለመውሰዳቸው ምክንያት ከት/ት
ገበታቸው አቋርጠዋል ነገር ግን ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍል አቋራች ተማሪ የለም።
ተግባር 2 ፤- ት/ቤቶች ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደ ጉዳት
ዓይነታቸውና ፍላጎታቸው ድጋፍና ክትትል በተመለከተ፤-
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በተመለከተ 3 ተማሪዎች
ሲኖሩ 1 ተማሪ የማየት ችግር ፣ 2 ተማሪዎች አእምሮ ውስነነት ፣ አላቸው ለእነዚህ
ተማሪዎች መምህራን ለተማሪዎቹ ተለያ ቁሳቁስ በመስጠት ድጋፍ ያደርግላቸዋል።

2
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በተመለከተ ወንድ 30 ሴት 28
ድምር 58 ተማሪዎች በጉዳት አይነታቸው የተለዩ ሲሆን በዚህ መሰረት ከፍተኛ ማየት
የተሳናቸው ተማሪዎች 6 ፣መካከለኛ ማየት የተሳናቸው 5 ተማሪዎች የመስማት ችግር
ያለባቸው 3፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው 4፣ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው 1 ፣አንደበት ችግር
ያለባቸው 32 ፣የባህሪ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች ተለይተው ለእነዚህ ተማሪዎች የት/ቤቱ
አስተዳደርና መምህራኖች ለተማሪዎች ቅድሚያ የትምህርት መሳሪያዎች በመስጠት የማየት
ችግር ያለባቸውን ደግሞ በመማር ማስተማር ግዜ ወደፊት በማቅረብ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል
በተጨማሪም የአካል ችግር ላለባቸው ደግሞ ልዩ ወንበር በማዘጋጀት እንዲቀመጡ
ያደርገውላቸዋል።
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በተመለከተ 5
ማየት የተሳናቸው ወንድ 4 ሴት 1 በድምሩ 5 ተማሪዎች ያሉት ሲሆን የት/ቤቱ
አስተዳደርና መምህራን የት/ት ቁሳቅስ ፣ዪኒፎርም፣ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል። መምህራንም
በመማር ማስተማር ጊዜ ወደፊት በማምጣት ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።
 ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በተመለከተ 7
ተማሪዎች ያሉ ሲሆን 2 ማየት የተሳናቸው፣ 1 የአካል ጉዳት፣3 መስማት የተሳናቸው፣1
የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎች የተለዩ ሲሆን እነዚህን ተማሪዎች የት/ቤቱ
አስተዳደር፣ መምህራንና ተማሪዎች በማንበብ፣ወንበር ቅድሚያ በመስጠት፣በመጻፍ
ድጋፍ ያደርጉላቸዋለ። ነገር ግን የሰለጠነ የልዩ ፍላጎት መምህር በት/ቤቱ የለም።
ተግባር 3 ፤- ለሴት ተማሪዎች ምቹ ሁኔታ ስለመፈጠሩ የተሌ ድጋፍ እየተደረገላቸው ስለመሆኑ
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቱ ላሉ ሴት ተማሪዎች ቅዳሜና እሁድ
የቲቶሪያል ት/ት በሁሉም መምህራን እየተሰጠ ይገኛል። በደረጃው ያለው ምጥጥን
አፈጻጸም/GPI/ በተመለከተ በት/ቤቱ የተመዘገቡት ተማሪዎች ወንድ 228 ሴት 182 ድምር
410 ሲሆኑ ምጥጥኑ 0.79 ነው ምጥጥኑ እንደዚህ ሊሰፋ የቻለው ሴት ተማሪዎች 7ኛ ክፍል
ሲደርሱ ወደጋብቻ ሰለሚሄዱ የሴቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቱ ላሉ ሴት ተማሪዎች ማጠናከሪያ
ት/ት ቅዳሜና እሁድ ይሰጣል በተጨማሪም በመያድ ለ5ኛና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች
ማጠናከሪያ ት/ት ድጋፍ ይደረጋል። ለሴት ተማሪዎች በት/ቤቱ አስተዳደር ትምህርት
ቅሳቁስ ድጋፍ ደረጋል በዚህ መሰረት የሴት ተማሪዎች የት/ት ተሳትፎ ጨምሯል።ምጥጥኑ
በተመለከተ 0.93 ነው።

3
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቱ ላሉ ሴት ተማሪዎች ማጠናከሪያ
ት/ት ቅዳሜና እሁድ ይሰጣል። በየዕለቱ አርብ ከሴት ተማሪዎች ጋር በሚያጋጥማቸው
ችግር ውይይት ያደርጋሉ።ምጥጥኑ 0.70 ሲሆን ምጥጥኑ ሊሰፋ የቻለው ሴት ወደ ጋብቻ
ሰለሚገቡ ነው የሚል ምክንያት በት/ቤቱ ተገልጻል።
 ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ሴት
ተማሪዎች ማጠናከሪያ ት/ት ቅዳሜና እሁድ ይሰጣል። ምጥጥኑ 0.51 ነው የምጥጥኑ
መስፋት በሌሎች ት/ቤት ላይ ያለው ችግር ስለሚከሰት ነው።

ግብ 2 ፣- የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በማጎልበት ተጠያቂነት የሰፈነበት የትምህርት


ስርዓት መፍጠር

ተግባር 1 ፤- የትምህርት አመራሮችን፣ ባለሙያዎችንና መምህራንን አቅም


ለመገንባት የሚስችል የተሰጡ ስልጠናዎች
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ወንድ 10 ሴት 8 በድምሩ 18 ለሆኑ መምህራን በሌሰን
ፕላን ዝግጅት፣በፈተና አወጣጥ፣የተማሪዎች ደብተር አያያዝ፣ ላይ በተመለከተ የ2
ቀን ከግማሽ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተሰጥቷቸዋል።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ወንድ 7 ሴት 1 ድምር 8 መምህራን በተከታታይ
ምዘና ፣ በክፍል አያያዝ ላይ በተመለከተ የ3 ቀን አቅም ግንባታ ስልጠና
ተሰጥቷቸዋል።
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመምህራን አቅም ግንባታ ስልጠና
አልሰጠም ምክንቱም በስልጠና በጀት ችግር።
 ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወንድ 2 ሴት 1 ድምር 3 መምህራን በዚህ
ሰሚስቴር በትምርት ማሻሻያ/SIP/ ፣ in-services training ፣ ዓመታዊ እቅድ
አዘገጃጀት በተመለከተ ለሁለት ቀን አቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል
ተግባር 2 ፣- ከአሁን በፊት የተሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ የልምድ
ልውውጦች፣ የተቀሰሙ ተሞክሮዎችና የተሰጡ ግብረ-መልሶች በተግባር ተፈጻሚ
ስለመሆናቸውና በአቅም ግንባታ ስልጠናው የተገኘ ውጤት
 ተከታታይ ምዘና ማዘጋጀት ችለዋል
 የትምህረት ማሻሻ ፕሮግራም እውቀት አግኝተዋል

4
 ዓመታዊ እቅድ ማዘጋጀት ችለዋል

 ከልምድ ልውውጦችና ከተቀሰሙ ተሞክሮዎች የተገኘው የልምድ ልውውጥ


በትምህርት ቤቶች መካከል
 በትምህርት ቤቶች መካከል የልምድ ልውውጥ አልተካሄደም።

ተግባር 3 ፣- ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ቋሚ የሆነ የግንኙነት መድረክ በመፍጠር


የትምህርት ስራን እንዲደግፉ የተፈጠሩ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችና የተፈቱ ችግሮችና
የተከናወኑ ተጨባጭ ስራዎች በተመለከተ

 ት/ቤቶች ከወመህ ጋር በወር 2 ጌዜ በየ15 ቀኑ አንድ ግዜ ግንኙነት ግዜ


ሲኖራቸው በግንኙነት መድረክ የተፈቱ ችግሮች አርፍዶ በሚመጡ ተማሪዎች
ላይ በሰአቱ እንዲመጡና በማይመቱት ላይ ጋራ እርምጃ መውሰድ፣በተማሪና
በመምህራን መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችን በጋራ መፍታት፣ለመመር ማስተማሪ
ስራ የሚገጥሙትን ችግሮች በጋራ መፍትሄ መፈለግ ፣በተማረና ተማሪ መካከል
የሚፈተረው ግጭት መፍትሄ መፈለግ በግንኙነት ግዜ የጋር ግንዛቤ ወስደው
በጋር እየሰሩ ይገኛሉ።

ግብ 3 ፣-የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻልና የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ በማድረግ


የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ማሻሻል

ተግባር 1 ፤-የአንደኛ ሴሚስተር የተማሪዎች ውጤት ተተንትኖ ለተማሪዎች፣


ለወላጆች፣ ለመምህራንና ሌሎች የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ የማሳወቅ እና የማሻሻያ
ምክክሮች ስለመደረጋቸው
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ውጤት ትንተና አልተደረገም ለተማሪ
ወላጆችም ሆነ ከመምህራን ጋር የምክክር መድረክ አልተካሄደም።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ውጤት ትንተና አልተደረገም
ለተማሪ ወላጆችም ሆነ ከመምህራን ጋር የምክክር መድረክ አልተካሄደም።
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ውጤት ትንተና
አካሂዷል ለተማሪ ወላጆች ፣ለወመህ የተማሪዎችን ውጤት ገለጻና ምክክር

5
በመደረጉ ተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር ተሻሽሏል ተማሪዎች ቤተመጽሀፍ
ገብተው የማንበብ ልምድ አሻሽለዋል።
 ሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተማሪዎች ውጤት ትንተና አካሂዷል
ለተማሪ ወላጆች ፣ለወመህ የተማሪዎችን ውጤት ገለጻ ተደርጓል።

ተግባር 2 ፣- ዝቅተኛ ውጤት ያመጡትን ተማሪዎች በመለየትና ለሴት ተማሪዎች የተለየ


የማብቃት ስልት በመቀየስ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ስለመሆኑና የታዬ ለውጥ
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤትና የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝቅተና ውጤት
ያመጡ ተማሪዎችን የመለየት ስራ አልተካሄደም።
 የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ት/ቤት ተማሪዎችን ውጤት
በመተንተን በ9ኛ ክፍል ዝቅተኛ ውጤት ያመቱትን ወንድ 7 ሴት 2 ድምር 9
ተማሪዎች በመለየት ማተናከሪያ ትምህርት እንዲሰጣቸው ተደርጓል
በተጨማሪም ለሴት ተማሪዎች ዝቅተና ውጤት ላመጡ ልዩ ትኩረት በማድረግ
ኬሚስትሪ ውጤት 100‰ እንዲሻሻል ተደርጓል።
 ኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝቅተኛ ውጤት ላመቱ ተማሪዎች
ድጋፍ አድርገናል ብለዋል ነገር ግን በመረጃ የተደገፈ ማስረጃ ማቅረብ
አልቻሉም።
ተግባር 3 ፣- ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች በተጨባጭ መረጃ በመለየት የማብቃት
ስራዎች ስለመከናወናቸው

 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች መለየት ስራ


ተስርቷል በዚህ መሰረት 2ኛ ክፍል 10 ተማሪዎች3ኛ ክፍል 7 ተማሪዎች
ተለይተዋል ። በተደረገላቸው ድጋፍ መሰረት 2ኛ ክፍል ከተለዩት 10
ተማሪዎች ውስጥ 9ኙ አሻሽለዋል ከ3ኛ ክፍል ደግሞ 7ቱም አሻሽለዋል።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ተማሪዎች
መለየት ስራ ተስርቷል በዚህ መሰረት 2ኛ ክፍል 3 ተማሪዎች3ኛ ክፍል 4
ተማሪዎች ተለይተዋል ። በተደረገላቸው ድጋፍ መሰረት 2ኛ ክፍል
ከተለዩት3ቱም ተማሪዎች አሻሽለዋል ከ3ኛ ክፍል ደግሞ 4ቱም አሻሽለዋል።

6
ተግባር 4 ፣-ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በእቅድ የተደገፈና በተመረጡ የትምህርት አይነቶች
የማጠናከሪያ ትምህርት ስለመሰጠቱ
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ61 8ኛክፍል ተማሪዎች በእቅድ የተደገፈና
በተመረጡ የትምህርት አይነቶ ቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርት
ተሰጥቷል(ጄነራል ሳይንስ፣አካባቢ ሳይንስ፣ሂሳብ፣እንግሊዘኛ፣ሶማሌኛ)
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ71 8ኛክፍል ተማሪዎች በእቅድ የተደገፈና
በተመረጡ የትምህርት አይነቶ ቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርት
ተሰጥቷል( ሳይንስ፣ሂሳብ፣እንግሊዘኛ፣ሶማሌኛ)
 የኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወንድ 39 ሴት 47 ድምር 86
ለሆኑ የ12ኛክፍል ተማሪዎች በእቅድ የተደገፈና በተመረጡ የትምህርት
አይነቶ ቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርት ተሰጥቷል(ኬሚስትሪ፣
ፊዚክስ፣ሂሳብ፣እንግሊዘኛ፣)
 የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛክፍል ተማሪዎች በእቅድ
የተደገፈና በተመረጡ የትምህርት አይነቶ ቅዳሜና እሁድ የማጠናከሪያ
ትምህርት ተሰጥቷል (ኬሚስትሪ፣ፊዚክስ፣ሂሳብ፣እንግሊዘኛ፣) ሌሎች
ትምህርት ዓይነቶችንም መምህራን በፍላጎታቸው እየሰጡ ይገኛሉ።
ተግባር 5 ፣- የመማሪያ ክፍሎች፣ የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች (ቤተ-መጽሃፍት፣ ቤተ-
ሙከራ፣ የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል፣ ICT ማዕከል ወዘተ)፣ ሁለገብ የስፖርት
ማዘውተሪያ ቦታ፣ ሌሎች ልዩ ፍላጎት ላለቸው ተማሪዎች የሚሆን ቁሳቁስ በስታንዳርዱ
መሰረት ስለመሟላታቸው
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከላይ ከተጠቀሱት የመማሪ ክፍሎች
ያሉት ሲሆን የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ሁሉም የሌሉት መሆኑን ለማየት
ተችላል ።እንዲያውም የትምህርት ቤቱ ግቢ በግለሰቦች ተወስዶ የመኖሪ
ቤት እየሰሩበት ይገኛል።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከላይ ከተጠቀሱት የመማሪ
ክፍሎች ያሉት ሲሆን የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ሁሉም የሌሉት
መሆኑን ለማየት ተችላል።

7
 የኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከተጠቀሱት የመማሪ
ክፍሎች እና ከአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ቤተመጽሃፍ ያለው ሲሆን
ሌሎቹ ክፍሎች የሉትም።
 የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከተጠቀሱት የመማሪ
ክፍሎች ያሉት ሲሆን የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ሁሉም የሌሉት
መሆኑን ለማየት ተችላል።

ተግባር 6 ፣-የአዲሱ ስርዓተ-ትምህርት ትግበራ አፈጻጸም በተመለከተ ያለበት ሁኔታ


 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የአዲሱ ስርዓተ ት/ት ትግበራ በተመለከተ
ከክልሉ ት/ቢሮ የተላከለትን/Soft copy/ እና hard copy የመፅሀፍት ችግር
በህብረተሰብ ተሳትፎ ከተገኘ የውስጥ ገቢ ለመምህራን የማስተማሪያ መፅሀፍትን
አትሞ በመስጠት ትግበራ ላይ ይገኛል። በአዲሱ የት/ት ስርዓት ትግበራ አፈጻተም
ላይ ወንድ 10 ሴት 8 ድምር 18 መምህራኖች ስልጠና ተሰጥቷል።
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የአዲሱ ስርዓተ ት/ት ትግበራ በተመለከተ
ከክልሉ ት/ቢሮ የተላከለትን/Soft copy/ እና hard copy የመፅሀፍት ችግር
በህብረተሰብ ተሳትፎ ከተገኘ የውስጥ ገቢ ለመምህራን የማስተማሪያ መፅሀፍትን
አትሞ በመስጠት ትግበራ ላይ ይገኛል። በአዲሱ የት/ት ስርዓት ትግበራ አፈጻተም
ላይ ወንድ 32 ሴት 17 ድምር 40 መምህራኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

8
ተግባር 7 ፤- ለድጋፍ የተመረጡት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው እንዲሻሻል ለማድረግ
ፕሮፋይላቸው በግብዓት፣ በሂደትና በውጤት ስለመለየቱና ቀደም ሲል የኢንስፔክሽን ግምገማ
ውጤት
 በትምህርት ቤቶቹ የውስጥ ኤንስፔክሽን ግምገማ የተካሄደ ሲሆን

ትምህርት ቤት የት/ቤት ደረጃ በግብዓት በሂደት በውጤት የት/ቤቱ


አማካይ
ደረጃ
ሙሉ 1ኛ
የአዳዳሌ ደረጃ 10፣8 17.82 22.26 50.88 ደረጃ 2
ሙሉ 1ኛ ደረጃ
የጎዴ ካውንስል ደረጃ 14 17 22 53.6 2
የኡጋስ
ኢብራሁም ደረጃ
አብዶ ሁለተኛ ደረጃ 12.16 21.5 25.3 59.06 2
የሰይድ
መሀመድ ሀሰን ሁለተኛ ደረጃ 13 19 21 53 ደረጃ 2

 የተለዩ ዋና ዋና የቅድሚያ ስታንዳርዶችና አመላካቾች


 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
 ስታንዳድር 1፣3፣7፣8፣10፣14፣15፣17፣19ና 21ናቸው
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
 ቅድሚያ ትኩረት ስታንዳረትዶችን ለይተናል ቢሉም
በመረጃ የተደገፈ ማስረጃ አላቀረቡም።
 የኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
 ስታንዳርድ1፣7፣14፣19፣17 ናቸው
 የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
 ስታንዳርድ 1፣2፣3፣9፣14፣18፣16 ናቸው

9
ተግባር 8 ፣- በክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ስራዎች ምልከታ፣ የርስ በርስ መደጋገፍና
ሙያዊ መሻሻል እንዲመጣ የተሰሩ ስራዎች
 የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣- በክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር
ስራዎች ምልከታ፣ የርስ በርስ መደጋገፍና ሙያዊ መሻሻል እንዲመጣ
የተሰሩ ስራዎች በት/ቤቱ የለም
 የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር
ስራዎች ምልከታ፣ የርስ በርስ መደጋገፍና ሙያዊ መሻሻል እንዲመጣ
የተሰሩ ስራዎች አሉ ቢሉም በመረጃ የተደገፈ ማስረጃ የለም
 የኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በክፍል ውስጥ የመማር
ማስተማር ስራዎች ምልከታ፣ የርስ በርስ መደጋገፍና ሙያዊ መሻሻል
እንዲመጣ የተሰሩ ስራዎች አሉ እነሱም ጠንካራ ተማሪ ደከም ላሉ
ተማሪዎች ድጋፍ ያደርጋሉ ። በክፍል ውስጥ የሱፐርቪዥን ምልወከታ
ያደርጋሉ።
 የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በክፍል ውስጥ የመማር
ማስተማር ስራዎች ምልከታ፣ የርስ በርስ መደጋገፍና ሙያዊ መሻሻል
እንዲመጣ የተሰሩ ስራዎች አሉ እነሱም በወር 1 ጊዜ የሱፐርቪዥን
ምልከታ ያደርጋሉ፣ተማሪዎችን የጥያቄ መልስ ውድድር ያደርጋሉ፣
ጎበዝ ተማሪዎች በትምህርታቸው ደከም ላሉት ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።

10
ግብ 3 ፣- ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም ስርዓትን ማሻሻል

ተግባር 1፣ -በትምህርት ቤት የወላጆችን/አሳዳጊዎችን እና የአካባቢውን ህብረተሰብ


ግንኙነትና ተሳትፎ በማጠናከር በእውቀት፣ በጉልበት፣ በአይነት እና በገንዘብ
እንዲደግፉ የተሰሩ ተግባራት

የተሰበሰበ ኃብት
ትምህርት
ወረዳ የት/ቤት ደረጃ በጥሬ ምርመራ
ቤት በጉልበት በዓይነት ድምር
ገንዘብ
አዳዳሌ ቅድመ መደበኛ የለም 7,500 300, 000 1, 050 ,000
1ኛደረጃ 000
መካከለኛ ደረጃ
ኡጋስ 2ኛደረጃ ት/ቤት 16 ,500 8,500 25,000 የትቤቱን ጽዳት
አዳዳ ኢብራሁ 9-12ኛ ማድረግ
ሌ ም አብዶ

ጎዴ ቅድመ መደበኛ የለም የለም የለም ------- ህብረተሰቡ ምንም


ካውንስል 1ኛደረጃ እና ድጋፍ አላደረገም
መካከለኛ ደረጃ
ጎዴ ሰይድ 2ኛደረጃ ት/ቤት የለም የለም 109 ,500 109 ,500 3 መማሪያ ክፍል
ካውስ መሀመድ 9-12ኛ ሰርተዋል
ል ሀሰን መብራትና
አምፖል
በየክፍሎቹ
አስገብተዋል
ድምር 1,184 500 00

11
ተግባር 2 ፤- ለትምህርት ቤቱ የተገኘ ሀብትና በጀት (School grant, Block grant,
Performance Award, Additional grant ወዘተ ለታለመላቸው ዓላማና ተግባራት ስለመዋላቸው
ትምህርት ብሎክ በአፈፃጸም
የት/ቤት ደረጃ ድጎማ በጀት ድምር
ቤት ግራንት የተገኘ
አዳዳሌ ቅድመ መደበኛ 1ኛ ደረጃ --------
መካከለኛ ደረጃ - 26,030.00 --- 26,030.00
ኡጋስ
ኢብራሁም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት/9-12ኛ/ 171,
አብዶ 27,270.00 144,000.00 ----- 270..00
ጎዴ ቅድመ መደበኛ 1ኛደረጃ --------
ካውንስል እና መካከለኛ ደረጃ - 46,360.00 ---- 46,360.00
ሰይድ
መሀመድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት/9-12ኛ/ --------
ሀሰን 120,000.00 75,680.00 ----- 195,680.00

ያጋጠሙ ችግሮች ፣-
 የተማሪና የመምህራን ሽንት ቤት ያለመኖር
 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ያለመኖር
 የመምህራን ስታፍ ያለመኖር
 ቤተመጽሃፍ ፣ቤተሙከራ፣የትምህርት ማዕከላት ወዘተ ያለመኖር
 ሶማሌኛ፣ አማረኛ ሂሳብ፣አይሲቲ መምህር ያለመኖር
 የመብራት ችግር
 በት/ቤት ግቢ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት መስራት(አዳዳሌ ት/ቤት)
 የመጠጥ ውሃ ያለመኖር
 አዳዳሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ብሎክ ግራንት የ1 ወር/12,000 ብቻ መሰጠታቸው

12
የተወሰደው የመፍትሄ ሀሳብ ፣-
 ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ (ወረዳና ክልል ቢሮዎች)
 እጥረት ባለባቸው ት/ቤቶች ሌሎች መምህራን እየገቡ ማስተማር
 ለተማሪዎች በቦቲ መኪና የመጠጥ ውሃ ማቅረብ

የሱፐርቪዥን ቡዱኑ በተመረጡ ት/ቤቶች ያደረገው የሱፐርቪዥን ስራ በፎቶግራፍ

የአዳዳሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት

13
የኡጋስ ኢብራሁም አብዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

የጎዴ ካውንስል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት

14
የሰይድ መሀመድ ሀሰን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

15

You might also like