You are on page 1of 17

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ት/ቢሮ

የመምህራንና፣ የትምህርት ቤት
አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና
እድሳት ዳይሬክቶሬት

የ 2013 የበጀት ዓመት ዕቅድ

ግንቦት 2012 ዓ.ም


የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

ሀዋሳ
መግቢያ
በክልላችን የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በየደረጃው ያሉ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች
በመማር ማስተማሩ ሂደት የማይተካ ሚና አላቸው፤ እነዚህ ባለሙያዎች ትውልድን በዕውቀት፣ በክህሎትና
በሥነ ምግባር ቀርጾ ለማውጣት የተጣለባቸው ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ተፈላጊው ሙያዊ ብቃት
ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህንንም የሙያ ብቃት ለማረጋገጥ የብቃት ስታንዳርድ በማዘጋጀት የጽሁፍና የማህደረ
ተግባር ምዘና በማካሄድ በድምር ውጤቱ መስፈርቱን ለሚያሟሉ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት የሙያ ፈቃድ አስጣጥና ዕደሳት ዳይሬክቶሬት አዲስ ወደ ሙያው ለሚገቡም ሆነ በስራ ላይ
ላሉ ነባር መምህራንና ት/ቤት አመራሮች ስታንዳርዱን መሰረት ባደረገ ምዘና ሙያዊ ብቃታቸውን የማረጋገጥ
ሥራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በ 2012 የበጀት ዓመት መግቢያ የ 2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የታዩ
ጠናካራ አፈጻጸሞችንና የተስተዋሉ ጉድለቶችን በመገምገም የ 2012 በጀት ዓመት በክልሉ በሚገኙ 5 ቱም
የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች አዲስ ተመርቀው ለሚወጡ መምህራን እና በስራ ላይ ለሚገኙ ነባር የ 1 ኛ
እና 2 ኛ ደረጃ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና
የማህደረ ተግባር ምዘና በብቃትና በጥራት ለመመዘን የሚያስችል የቅድመ ስራ በመስራትና በሙያ ፍቃድ
አሰጣጥና ዕድሳት ዝርጋታ ዙሪያ የተለያዩ አካላትን ግንዛቤ ለማጎልበት የሚያስችል ዕቅድ በማቀድ የዓመቱን
ተግባራትን ወቅቱ በሚፈቅደው መሰረት ሊተገበሩ የታቀዱ ተግባራት ፤ የተከናወኑ ተግባራት፣ የተመዘገቡ
ውጤቶች ፣ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የተደረጉ ጥረቶች በሚገልጽ መልኩ
የዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ዓላማ
በተያዘው የበጀት አመት በበመምህራን የትምህርት ቤት አመራር ሙያፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳሬይክቶሬት
ውስጥ ለመስራት ከታቀዱ ተግባራት መካክል የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸሞችን በተገቢው ሁኔታ በመገምገም
በጥንካሬ የታዩትንና በጉድለት የተከሰቱትን ተግባራት በመፈተሸ ለቀጣይ የበጀት ዓመት/2012 ዓ.ም /የተግባር
አፈጻጸም እንደ ግብዓት በመጠቀም የዳይሬክቶሬቱን ብሎም የትምህርት ቢሮ ዓላማ ማሳካት ፡፡
1. በበጀት ዓመቱ አንኳር አንኳር የእቅድ ተግባራት አፈጻጸም
በ 2012 የበጀት አመት በዓመቱ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማከናወን ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም በተሟላ
ግልፀኝነት ለመፈፀም በየደረጃው ያለውን ፈጻሚ አካላትን ማብቃት የማይዘለል ተግባር በመሆኑ የትምህርት ጥራትን
ማረጋገጥ የሚችልና ለውጡን የሚመራ ግንባር ቀደም ፈጻሚ ለመፍጠር የበጀት አመቱ ቁልፍ ተግባር

Page 1
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

በማድረግ ወደ ስራ ተገብቷል ፡፡ በዚህም መሰረት የ 2012 የበጀት ዓመት የእቅድ ዝግጅትና አፈጻጸምን
በዝግጅት ምዕራፍና በተግባር ምዕራፍ በማጠቃለያ ምዕራፍ መከናወን ያለባቸዉ ተግባራት በደንብ በመለየት
በጋራ ተወያይቶ እቅዱን የማጽደቅ እና የመከለስ እንዲሁም በየአደረጃጀቱ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት

ዳይሬክቶሬት ፈጻሚ አካላትን በተጠናከረ ሁኔታ የማደራጀት እና አጠቃላይ በ 2012 ዓ.ም በዳይሬክቶረቱ
በዓመቱ ለማከናወን የተጣሉ ግቦችን ለማሳካት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በዚህም መሰረት የ 2012
በጀት ዓመት አንኳር አንኳር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
1.1 የበጀት ዓመቱ የእቅድ ዝግጅትና አተገባበርና ክትትል በተመለከተ

 የ 2012 በጀት ዓመት የእቅድ ዝግጅትን በዝግጅት ምዕራፍና በተግባር ምዕራፍ በማጠቃለያ ምዕራፍ
መከናወን ያለባቸዉ ተግባራት በደንብ በመለየት በጋራ ተወያይቶ እቅዱን የማጽደቅ እና በየ 6 ወራት
ላይ የመከለስ ስራ መስራት ተችሏል ፡፡
 ዳይሬክቶሬቱ የእቅድ አፈጻጸም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የፈጻሚዎች አቅም የማጎልበት ስራ
በአመቱ ዕቅድ ውስጥ ለይቶ በማስቀመጥ ሁሉንም ፈጻሚዎች ወደ ተግባር ማስገባት ተችሏል
 በዳይሬክቶሬቱ የሚገኙ ፈጻሚዎችና ሰራተኞች የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ መነሻ በማድረግ ውጤት
በሚያመጣ መልኩ በየስድስት ወራት የግለስብ ዕቅድ በማቀድና የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት
ተግባራቸውን አከናውነዋል ፡፡
 በየአደረጃጀት እርከኑ ያሉ የዳይሬክቶሬቱ ፈጻሚዎች እቅዳቸዉን በሚዛናዊ የዉጤት ተኮር ስርአት
መሰረት የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ለባለሙያዎች በየስድስት ወራት ውጤት ተሰርቶ ተሰቷል ፡፡
 የዳይሬክቶሬቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ለመገምገም ተገልጋዮች የሰጡትን አስተያየት በመተንተን
ጠንካራ ጎኖችን በመውሰድ መሻሻል የሚገባቸውን እንደ ግብዓት መጠቀም ተችሏል፡፡
 በ 2011 ዓ.ም የተሰጡ ምዘናዎች እርማት በማካሄድ ውጤት በማጠናቀር ለሁሉም ዞኖች/ልዩ ወረዳዎች
እና ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖርት ፎሊዮ እንዲሞላላቸው ተልከዋል ፡፡
 የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ለመስጠት በሁለተኛው የዓመቱ አጋማሽ ፕሮግራም ቢያዝም ግንዛቤ
ማስጨበጥ ሥራ በኮሮና ምክንያት መስራት አልተቻለም ፡፡
1.2 የምክክር መድረክ ማካሄድ በተመለከተ
 የ 2011 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም እና የ 2012 ዓ.ም እቅድ አተገባበር ዙሪያ ከዞን/ልዩ ወረዳ/ከተማ
አስተዳደር የዳይሬክቶሬቱ ፈጻሚዎች እና ከሌሎች የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና ባለሙያዎች ወንድ 35
ሴት 6 በድምሩ 41 ተሳታፊዎች ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር በአፈጻጸምና በቀጣይ ተግባራት ላይ
ውይይት ተደርጓል፡፡
በዚህ ውይይት 41 ተሳታፊዎች ሲገኙ በውይይቱ የተነሱ ዓብይ ጉዳዮች፡-
- የ 2011 የዕቅድ አፈጻጸም ፤

Page 2
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

- የ 2012 ዓ.ም ዕቅድ ፤


- የ 2012 ዓ.ም የየነባር የአንደኛ ደረጃ መምህራንና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የት/ቤቶች አመራር
ወቅቱን ጠብቆ ምዝገባና ምዘና ለማከናወን የታቀደ ዕቅድ ላይ
- በበጀት አመቱ በርካታ ተመዛኞች እስከ ት/ቤት በመውረድ ግንዛቤ ማጎልበት በሚቻልበት ሁኔታ በሚሉ
ርዕሶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡
- ከመምህራንና ት/ት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት እና የመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያፈቃድ
አሰጣጥና ዕደሳት ዳሬይክቶሬት በሻሸመኔ ከተማ የሁለቱንም ዳሬይክቶረቶች የ 6 ወራት የሥራ
አፈጻጸም ሁሉም ባለሙያዎች ባሉበት በዘርፍ ደረጃ ተገምግመዋል ፡፡
1.3 የምዘና ውጤት ትንተና በተመለከተ
 አጠቃላይ እስከ አሁን ለአዲስ ዕጩ ተመራቂ መምህራን ከ 70% እና በላይ እንዲሁም ለነባር
የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የተሰጡ የጽሁፍ ምዘናዎችን
አፈጻጸም 62.5% እና በላይ የውጤት ትንተና ከ 2005 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም አፈጻጸም በንፅፅር
በመስራት የሚመለከታቸው አካላት ውጤትን መሰረት አድርገው የመምህራን የሙያ ብቃታቸውን
ሊያሳድጉ በሚችሉበት ደረጃ መስራት እንዲችሉ አጠቃላይ የውጤት ትንተና ስራ በመስራት በ 2012
የክልሉ የትምህርት አስተዳደር ጉባኤ ቀርበዋል ፡፡

 በ 2010 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ 5 ቱም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ተመረቀው ለወጡ ዕጩ


ተመራቂ መምህራንና የ 1 ኛ ደረጃ ነባር መምህራንና የትምህረት ቤት አመራሮች የተሰጠውን የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ውጤት ትንተና በተመለከተ ከመምህራንና ት/ት አመራር ልማት
ዳይሬክቶሬት እና የመምህራንና የትምህርት አመራር ሙያፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳሬይክቶሬት እና
5 ቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጆች አመራር አካላት በተገኙበት እንደዘርፍ በተዘጋጀው የምክክር
መድረክ በ 2010 ዓ.ም የተሰጠውን የጽሁፍ ምዘና የውጤት ትንተና በማቅረብ በውጤት ትንተና ላይ
ውይይት ተካሂዷል፡፡
 በተመሳሳይ በበጀት ዓመቱ በ 2011 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ 5 ቱም የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ
ተመርቀው ለሚወጡ ለ 6,262 ዕጩ ተመራቂ መምህራንን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የተሰጠ
ሲሆን ከተመዘኑ 6,262 ተመዛኞች መካከል 808 (12.9 %) ተመዛኞች ውጤት የማደራጀት ስራ
ከመስራት በተጨማሪ ከትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅተው የተላኩ የምዘና ጥያቄዎች ተገቢነት
በየትምህርት ዓይነቱ በመተንተን (Item And Gap Analysis) ያለውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት
በመለየትና የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት እና ምዘና ለሚያዘጋጁ አካላት
የማሳወቅ/ግብረ-መልስ/ የመስጠት ስራ ለመስራት በሚያስችል መንገድ ተደረጅቶ የጠቀመጠ
ቢሆንም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ግበረ መልስ መስጠት አልተቻለም ፡፡

Page 3
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

1.4 የክንዋኔ ማህደረ ተግባር (Portfolio) ምዘና በተመለከተ


 በ 2011 ዓ.ም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ከተመዘኑ 2,811 ነባር 2 ኛ ደረጃ ተመዛኝ
መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች መካከል 953 (33.9%) ተመዛኞች የማህደረ ተግባር ምዘና
ለማካሄድ (62.5% እና በላይ ያመጡ) በየትምህርት ዓይነቱ የምዘና ውጤትና መረጃ የማደራጀት ስራ
በመስራት የማህደረ ተግባር ምዘና መዝነው ውጤቱን እንዲልኩ ለሁሉም ዞኖች/ልዩ ወረዳዎች/ከተማ
አስተዳደር እና ወረዳዎች የመላክ ስራ ተሰርቷል፡፡
 በ 2011 ዓ.ም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በ 35 ማዕከላት ለ 9181 ተመዛኞች በ 21
የትምህርት ዓይነቶች የት/ቤት አመራሮችን ጨምሮ ምዘና ተስጥተዋል
 ከተመዘኑት የአንደኛ ደረጃ መምህራን 62.5 በላይ ለፖርት ፎሊዮ ምዘና ያለፉ ወንድ-- 981፣ ሴት 201
በድምሩ 1182 ሲሆን አፈጻጸሙ 12.87 % ነው
 ምዘናው ከተሰጣቸው 259 የአንደኛ ደረጃ ር/መምህራን 62.5 በላይ ያመጡ የሌሉ ሲሆን ከ 59
ሱፐርቫይዘሮች 62.5 በላይ ያመጡ 17 ብቻ ናቸው ፡፡
 ምዘናው ከተሰጠባቸው ዞኖች ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ምዘና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ጉራጌ ፤ወላይታ፤
ከፋ ፤ ጋሞ ፤ሲዳማ ፣ስልጤ እና ሀዲያ ዞን በቀደም ተከተል ሲሆኑ ባስኬቶ ፤ ቡርጂ ፤አሌ ፤ሀላባ ኮንታ
ዝቅተኛ አፈጻጸም ያሳዩ ናቸው ፡፡
 በውጤቱ ዙሪያ በተደረገው ግምገማ በየዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን የተነጻጸሩ ሲሆን የ 2010 ና የ 2011
ዓመት ውጤት ሲነጻጸር
 በ 2010 ዓ .ም የአንደኛ ደረጃ ነባር መምህራንና የት/ቤት አመራሮች መካከል 62.5 በላይ ያመጡት 12.3%
፤ ዕጩ መምህራን 9.4% እና የ 2 ኛ ደረጃ መምህራን 9.6% ሲሆኑ
 በ 2011 ዓ .ም የአንደኛ ደረጃ ነባር መምህራን 62.5 በላይ ያመጡት 12.87% ና ዕጩ መምህራን
12.9% እንዲሁም የ 2 ኛ ደረጃ መምህራን 37.9% እንደሆነ መረጃው ሲያመለክት በየዓመቱ መጠነኛ
መሻሻል ቢያሳይም ከተቀመጠው ግብ አንጻር ግን በሁሉም ደረጃዎች የማለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ ነው ፡፡
1.5 የሙያ ፈቃድ ማስረጃ /ሰርተፊኬት/ መስጠትን በተመለከተ
የሙያ ፈቃድ ማስረጃ /ሰርተፊኬት/ ከመስጠት በአንጻር፡- አጠቃላይ ከ 2008 - እሰከ 2010 ዓ.ም ድረስ የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የክንዋኔ ማህደረ ተግባር ምዘና ተመዝነው ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ (70 % እና
በላይ) ያመጡ (627)አዲስ ተመራቂ መምህራን ፣ (178) ነባር 2 ኛ ደረጃ መምህራን እና (1,686) ነባር የመጀመሪያ ደረጃ
መምህራን፣ (78) ር/መምህራን፣ (95) ሱፐርቫይዘሮች በድምሩ (2,557) የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ መምህራንና
የትምህርት ቤት አመራሮች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል፡፡
1.6 የ 2011 ዓ.ም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና አፈጻጸም

Page 4
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 በበጀት ዓመቱ በአምስተኛው የትምህርት ልማት ዘርፍ /ESDP V/ እቅድ ላይ የተቀመጠውን ግብ


ለማሳካት በ 2012 ዓ.ም በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ አጠቃላይ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች
መካከል 31,000 /ሰላሳ አንድ ሺህ/ ነባር መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት
ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ለመስጠት በታቀደው መሰረት እስከ አሁን 20,149 (ሴት 5,259) የመጀመሪያ
ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራር 5,636 (ሴት 1,136) የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና
የትምህርት ቤት አመራር በድምሩ 25,785 (ሴት 6,395) ነባር የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
መምህራንና የትምህርት ቤት አመራር በመመዝገብና በየመዋቅሩ የተመዛኞችን መረጃ በማደራጀት
ምዘናውን በ 45 ማዕከላት ለምዘና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ብንገኝም ት/ሚ በጻፈው ደብዳቤ በኮሮና
ምክንያት በ 2012 ዓም ምዘና ማከናወን አልተቻለም ፡፡
1.7 ድጋፍና ክትትል በተመለከተ

 በበጀት ዓመቱ በዳሬይክቶሬቱ በስድስት ወራት ሁለት ጊዜ ለዞኖች/ልዩወረዳና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና
አምስቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጆችን የድጋፍና ክትትል ለማደረግ ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም በ 6 ዞኖች
የድጋፍና ክትትል ለማደረግ ሲቻል በቀሪ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የድጋፍና ክትትል ለማከናወን በኮሮና - 19
ምክንያት ለማከናወን አልተቻለም ፡፡
 በ 5 መምህራን ትምህርት ኮሌጆች ለተመራቂ ዕጩ መምህራን ገንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ በተከሰተው
ኮሮና በሺታ ምክንያት ዕጩ ተመራቂ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው በመላካቸው ግንዛቤ ማስጨበጥ
ሥራ አልተሰራም ፡፡
 ለ 5 ቱ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በዓመቱ ውስጥ ሁለት ጊዜ ድጋፍ ለማደረግ ዕቅድ ተይዞ በ 3
መምህራን ትምህርት ኮሌጅ /ሀዋሳ ዲላ እና በአርባምንጭ /መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አንድ ጊዜ
ድጋፍና ክትትል የጠደረገ ሲሆን ቀሪውን ድጋፍና ክትትል ለማደረግ በኮረና ምክንያት መደገፍ
አልተቻለም ፡፡
1.8 የአህዝቦት ስራዎችን በተመለከተ
በዳይሬክቶሬቱ የሚከናወኑ ተግባራትን በተለያዩ ሚዲዎች በማስደገፍ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የማጎልበት
ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ የ 2012 ዓመት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ምዘና የሚካሄድበትን
ቀንና ተመዛኞች ተገቢውን ዝግጅት አድርገው እንዲመዘኑ በሻሻመኔ ፋና ሬዲዮ ፣በደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን
እና በወላይታና በሚዛን ሬዲዮ ጣቢያዎች መጠነ ሰፊ ቅስቀሳዎች በሁለተኛው መንፈቀ ዓመት በዕቅድ የጠያዘ
ቢሆንም በወቅቱ በተከሰተው የኮረና ወረርሽን ምክንያት ት/ቤቶች በመዘጋታቸው ቅሰቀሳ ሥራውን
ማከናወን አልተቻለም ፡፡
1.9 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳራቶችና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች
1.9.1 ያጋጠሙ ተግዳራቶች

Page 5
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 የ 2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ተመዛኞች በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ለማሳካት ያልተቻለው የብቃት
ምዘናውን በወሰዱና ባልወሰዱ መምህራን በብቃት ምዘናው አጥጋቢ ውጤት አስመዝግበው የምስክር
ወረቀት በተሰጣቸውና በሌላቸው መምህራን መካከል ልዩነት የሚፈጥር ምንም ዓይነት የማበረታቻ
ሥርዓት ባለመኖሩ የብቃት ምዘናውን ለመመዘን ተመዝጋቢ መምህራን ፍላጎት ማጣታቸው፣
 አብዛኞቹ ት/ቤቶች እየተመሩ ያሉት የአመራርነት ስልጠና ባልወሰዱ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቨይዘሮች
በመሆናቸው  የአመራርነት ሥልጠና ያልወሰዱ የት/ቤት አመራሮች ምዘናውን ለመውሰድ የሙያ ፈቃድ
መመሪያ ስለማይጋብዝ የትምህርት አመራሩ ምዝገባ ዕቅድ ማሳካት አለመቻሉ ፡፡
 አብዛኛው የዞን/ልዩ ወረዳ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች አዲስ በመሆናቸው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ላይ የተሟላ ግንዛቤ ባለመጨበጣቸው በተደራጀ ቼክሊስት በስራቸው ለሚገኙ
መዋቅሮች በተለይም ለት/ቤቶች ድጋፍ አለማድረግ፣ ታማኒና ወቅታዊ መረጃዎችን ያለማደራጀትና
አለማሰራጨት፣ ወዘተ ክፍተቶች መኖር፣
 የተላኩ የዳይሬክቶሬቱን ቁልፍ ሰነዶች በት/ቤትደረጃ አለማደራጀትና እንዲነበቡ አለማድረግ፣
 በየደረጃው ባሉት አንዳንድ የዳይሬክቶሬቱ መደቦች ባለሙያዎች በቋሚነት ባለመመደባቸው ተግባራትን
በባለቤትነት መንፈስ ትኩረት ያለመስራትና ተገቢ የሆኑ መረጃዎች አደራጅቶ አለማሰራጨት ፣
 ከት/ቤት ፤ ወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል ድረስ ያለው መረጃ ልውውጥ ሥርዓት የተሳለጠ አለመሆን፣
 በየወቅቱ የሰለጠነና ልምድ ያለው ባለሙያ ፍልሰት፣
 ሥራው በባህሪው በጀት የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን በጀት በወቅቱና በሚፈለገው መጠን ማቅረብ
አለመቻል፣
 የተመዛኝን መረጃ ለማደራጀት በየመዋቅሩ የሰው ኃይል አለመሟላት
 በየእርከኑ ያለው አመራር ተገቢ ድጋፍና ትኩረት አለመስጠት
 የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በዕቅድ በስፋት አለመሰራቱ
 የ 2011 ዓ፣.ም የክርምትና የሳምንት ተመዛኞች እርማት ለማከናወን የበጀት እጥረት መኖር የ 2012 በጀት
ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሲገመገም የታዩ ክፈተቶች ናቸው ፡፡
1.10 በአፈጻጸም ሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ እርምጃዎች
 በዳሬክቶሬቱ በሁሉውም አካባቢ ወጥነት ያለው ሥራ መስራት እንዲያስችል የማትግያ ማነዋል ረቂቅ
በማዘጋጀት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ፡
 የበጀት እጥረት በመኖሩ በመደበኛ ካፒታል በጀት እንዲያዝ ከቢሮ ጋር ውይይት በማደረግ ፕሮጀክት
የተቀረጸ መሆኑን ፡፡
 በዞንና /በልዩ ወረዳ የባለሙያዎች ፍልስት እንዳይኖር በመደበው ላይ ከሌሎች ባለሙያዎች
እኩል ክፍያ እንዲኖረው በሰው ሀብት በኩል ጥናቶች እንዲደረጉ የማደረግ

Page 6
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 አብዛኛው ባለሙያዎች አዲስ በመሆናቸው የግንዛቤ እጥረት በመኖሩ በ 2013 ዓ.ም በቂ የሆነ
በጀት በማስመደብ ለዞንና /ልዩ ወረዳዎች ሥልጠናዎችን እንዲስጥ ማደረግ ናቸው

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ዳይሬክቶሬት 2013 ዓ.ም ዕቅድ

1. የዕቅዱ ዓላማ
የዓመቱን የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ ከነበሩበት ችግሮች በማላቀቅ በበቂ ቅድመ ዝግጅትና ንቅናቄ በመምራት ብቃት
ባላችው መምሀራንና የትምህርት ተቋማት አመራሮች ሙያው እንዲሸፈን በማድረግ የትምህርት ጥራትን ማሻሻል
ነው፡፡

2. የእቅዱ ዝግጅቱ መነሻ

የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳትን በተመለከተ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣


በአምስተኛውን የትምህርት ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የታቀዱትን በዋናነት መነሻ በማድረግ ዳይሬክቶሬቱ
በ 2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ (2012 ሪፖርት) ላይ በታቀደው መሠረት ያልተከናወኑ
በዝቅተኛ አፈፃፀም የተገመገሙ ተግባራትን፣ ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን በመቅረፍ
ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል ዕቅዱን በካፒታልና በመደበኛ በጀት በማስደገፍ እንደሚከተለው
አቅዷል፡፡

ተጠያቂነትን የተላበሰ ጠንካራ


የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት መኖሩን
ለማረጋገጥ
በዳይሬክቶሬቱ የተጣሉ ዋና
ዋና ግቦች
 መምህራንንና በሙያ ፈቃድ ምዘና ብቃታቸውን ማረጋገጥ።

 የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን በሙያ ፈቃድ ምዘና ብቃታቸን ማረጋገጥ።

 የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮችን በሙያ ፈቃድ ምዘና ብቃታቸውን ማረጋገጥ።

Page 7
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ


በ ዓ ም በዳይሬክቶሬቱ ለመተግበር
2013 .

የተጣሉ ዓመታዊ ግቦችና


የሚከናወኑ ተግባራት
ግብ 1 ፡- በሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሂደት ውስጥ ያለፉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በ 2012 ዓ.ም
ከነበረው 90.1% በ 2013 ዓ.ም 95% ማድረስ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በ 2012 ዓ.ም ከነበረው
16.1% በ 2013 ዓ.ም 55.1% ማድረስ፣
የሚከናወኑ ተግባራት፡-
 በበጀት አመቱ የሚመዘኑ መምህራን መረጃ በተመረቁበት የትምህርት ዓይነት፣ ደረጃ እና በሰለጠኑበት
እርከን መሰረት በማድረግ በጥራት በመሰብሰብ ማደራጀት፡፡
 በክልሉ የሚሰጡና የሚዘጋጁ የብሔረሰቦች አፍ መፍቻ ቋንቋ የትምህርት አይነቶች የሙያ ብቃት
ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ቁጥር መጨመር፣
 ለተመዛኝ አማካይና አመች የሆኑ የምዘና ማዕከላትን በመምረጥና በማስፋት ለሚመለከታቸው
አካላት ማሳወቅ
 በየትምህርት ዓይነቱ የተዘጋጁ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘናዎችን ለነባር የአንደኛና ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በተመረጡ የምዘና ማዕከላት ምዘናዉን መስጠት፣
 በክልሉ በሚገኙ 5 ቱም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ለሚመረቁ ዕጩ ተመራቂ መምህራን ከኮሌጅ
ሳይወጡ በየትምህርት ዓይነቱ የተዘጋጁ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና መስጠት
 በበጀት ዓመት የተመዘኑ ነባር የአንደኛ ደረጃ እና ዕጩ ተመራቂ መምህራን የመልስ ወረቀት በጥራት
በማረም ውጤታቸውን ማጠናቀር፡፡

Page 8
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 ለመምህራን በተሰጠው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የይዘትና የማስተማር ስነ ዘዴ ውጤት
ትንተና በማካሄድ በትንተናው መሰረት ተመዛኞች የታየባቸውን ክፍተቶች በመለየት
ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መስጠትና ሪፖርት ማድረግ፤
 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ተመዝነው የማህደረ ተግባር ምዘና ለመመዘን የማለፊያ
ነጥብ ያመጡ መምህራን የስም ዝርዝር ለታችኛው መዋቅር በመላክ የማህደረ ተግባር (Portfolio)
ምዘና ሂደትን መደገፍና መከታተል፡፡
 ለመምህራን የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ
ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ
መስጠት፡፡
 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የማህደረ ተግባር (Portfolio) ምዘና ተመዝነው ተፈላጊውን የማለፊያ
ነጥብ (70 % እና በላይ) ላመጡ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት መስጠት፣፣
ግብ 2 ፡- በሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሂደት ውስጥ ያለፉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን
በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 51.5% በ 2013 ዓ.ም 67.7% ማድረስ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ
መምህራን በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 25.5% በ 2013 ዓ.ም 34.8% ማድረስ፣
የሚከናወኑ ተግባራት፡-
 በበጀት አመቱ የሚመዘኑ ርዕሰ መምህራን በተመረቁበት የትምህርት ደረጃ እና በሰለጠኑበት እርከን
መሰረት በማድረግ ጥራቱን በጠበቀ ደረጃ የተመዛኞችን መረጃ በመሰብሰብ ማደራጀት፡፡
 በየደረጃው ተዘጋጅተው የመጡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ለአንደኛና ለሁለተኛ ደረጃ
የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን በተመረጡ የምዘና ማዕከላት ምዘናዉን መስጠት፤
 በበጀት ዓመቱ የተመዘኑ የአንደኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራን የመልስ ወረቀት በጥራት በማረም
ውጤታቸውን ማጠናቀር፣
 ለርዕሰ መምህራን የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ውጤት ትንተና በማካሄድ
ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መስጠትና ሪፖርት ማድረግ፤
 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ተመዝነው የማህደረ ተግባር ምዘና ለመመዘን የማለፊያ
ነጥብ ያመጡ ርዕሰ መምህራን የስም ዝርዝር ለታችኛው መዋቅር በመላክ የማህደረ ተግባር
(Portfolio) ምዘና ሂደትን መደገፍና መከታተል፣
 ለርዕሰ መምህራን የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት
ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ
መልስ መስጠት፡፡

Page 9
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የማህደረ ተግባር (Portfolio) ምዘና ተመዝነው
ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ (70 % እና በላይ) ላመጡ ርዕሰ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ሰርተፊኬት በማዘጋጀት መስጠት፣፣

ግብ 3፡- በሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሂደት ውስጥ ያለፉ ከቅድመ አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 68.2% በ 2013 ዓ.ም
78.8% ማድረስ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙያዊ ድጋፍ የሚሰጡ የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች
በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 0.6% በ 2013 ዓ.ም 25.5% ማድረስ፣
የሚከናወኑ ተግባራት፡-
 በበጀት አመቱ የሚመዘኑ ሱፐርቫይዘሮች በተመረቁበት የትምህርት ደረጃ እና በሰለጠኑበት እርከን
መሰረት የተመዛኞችን መረጃ በጥራት በመሰብሰብ ማደራጀት፡፡
 በየደረጃው ተዘጋጅተው የመጡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ለአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ
የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች በተመረጡ የምዘና ማዕከላት ምዘናዉን መስጠት፤
 በበጀት ዓመቱ የተመዘኑ የአንደኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮች የመልስ ወረቀት በጥራት በማረም
ውጤታቸውን ማጠናቀር፣
 ለሱፐርቫይዘሮች የተሰጠውን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ውጤት ትንተና በማካሄድ
ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መስጠት፣
 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ተመዝነው የማህደረ ተግባር ምዘና ለመመዘን የማለፊያ
ነጥብ ያመጡ የትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮችን የስም ዝርዝር ለታችኛው መዋቅር በመላክ የክንዋኔ
ማህደረ ተግባር ምዘና ሂደትን መከታተል፣
 ለሱፐርቫይዘሮች የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት
ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ
መልስ መስጠት፡፡
 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የማህደረ ተግባር ምዘና ተመዝነው ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ (70
% እና በላይ) ላመጡ ትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት
መስጠት፣

ግብ 4፡- የሙያ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወስደው ከአጥጋቢ ውጤት በታች በማምጣት በዳግም የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሂደት ውስጥ ያለፉ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በ 2012
ዓ.ም ከነበረው 0.0% በ 2013 ዓ.ም 25.7% ማድረስ፣
የሚከናወኑ ተግባራት፡-

Page 10
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 በበጀት ዓመቱ የሚመዘኑ የዳግም ተመዛኝ መምህራን በየዞኑና ልዩ ወረዳ ባሉ የዳግም ተመዛኝ
መምህራን ብዛት መሰረት ኮታ በመደልደል ለታቸኛዉ መዋቅር መላክ፣
 በበጀት አመቱ የሚመዘኑ የዳግም ተመዛኝ መምህራንና በተመረቁበት የትምህርት ዓይነት ደረጃ እና
በሰለጠኑበት እርከን መሰረት የተመዛኞችን መረጃ በጥራት በመሰብሰብ ማደራጀት፡፡
 ለዳግም ተመዛኝ መምህራን አማካይና አመች የሆኑ የምዘና ማዕከላትን በመምረጥና በማስፋት
ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ፣
 በየትምህርት ዓይነቱ የተዘጋጁ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ለዳግም ተመዛኝ መምህራን
በተመረጡ የምዘና ማዕከላት ምዘናዉን መስጠት፣
 በበጀት ዓመቱ የዳግም ምዘና የተመዘኑ የአንደኛ ደረጃ ተመዛኝ መምህራን የመልስ ወረቀት
ምስጥራዊነቱን በጠበቀና በጥራት በማረም ውጤታቸውን ማጠናቀር፣
 ለዳግም ተመዛኝ መምህራን በተሰጠው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የይዘትና የማስተማር
ስነ ዘዴ ውጤት ትንተና በማካሄድ የተመዛኞችን ክፍተት በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ
መልስ መስጠትና ሪፖርት ማድረግ፤
 ዳግም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ተመዝነው ለማህደረ ተግባር ምዘና ተፈላጊውን
የማለፊያ ነጥብ ያመጡ መምህራን የስም ዝርዝር ለታችኛው መዋቅር በመላክ የማህደረ ተግባር
(Portfolio) ምዘና አተገባበርን መደገፍና መከታተል፣
 ለዳግም ተመዛኝ መምህራን የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የምዘና ጥያቄ ትንተና እና
የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለሚመለከታቸው አካላት
ግብረ መልስ መስጠት፣
 ዳግም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የማህደረ ተግባር ምዘና ተመዝነው ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ
(70 % እና በላይ) ላመጡ መምህራን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት በማዘጋጀት መስጠት፣
ግብ 5፡- የሙያ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወስደው ከአጥጋቢ ውጤት በታች በማምጣት በዳግም የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ሂደት ውስጥ ያለፉ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 0.0% በ 2013 ዓ.ም 50% ማድረስ፣
የሚከናወኑ ተግባራት፡-
 በበጀት ዓመቱ የሚመዘኑ የዳግም ተመዛኝ የትምህርት ቤት አመራር በየዞኑና ልዩ ወረዳ ባሉ የዳግም
ተመዛኝ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ብዛት መሰረት ኮታ በመደልደል ለታቸኛዉ መዋቅር
መላክ፣
 በበጀት አመቱ የሚመዘኑ የዳግም ተመዛኝ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በተመረቁበት
የትምህርት ደረጃ እና በሰለጠኑበት እርከን መሰረት የተመዛኞችን መረጃ በጥራት በመሰብሰብ
ማደራጀት፡፡

Page 11
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 በየሙያው ተዘጋጅተው የመጡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ለዳግም ተመዛኝ የአንደኛና
ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ቤት አመራር በተመረጡ የምዘና ማዕከላት ምዘናዉን መስጠት፤
 በበጀት ዓመቱ የዳግም ምዘና የተመዘኑ የአንደኛ ደረጃ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የመልስ
ወረቀት በጥራት በማረም ውጤታቸውን ማጠናቀር፣
 ለዳግም ተመዛኝ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በተሰጠው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ
ምዘና ውጤት ትንተና በማካሄድ ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መስጠትና ሪፖርት ማድረግ፣
 ዳግም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና ተመዝነው ለማህደረ ተግባር ምዘና ተፈላጊውን
የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የስም ዝርዝር ለታችኛው መዋቅር በመላክ
የክንዋኔ ማህደረ ተግባር (Portfolio) ምዘና አተገባበርን መደገፍና መከታተል፡፡
 ለዳግም ተመዛኝ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና
የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት
ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ መስጠት፡፡
 የዳግም የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እና የማህደረ ተግባር ምዘና ተመዝነው ተፈላጊውን የማለፊያ
ነጥብ (70 % እና በላይ) ላመጡ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት
በማዘጋጀት መስጠት፣

ግብ 6፡- በተሻሻሉ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት አፈጻጸም መመሪያዎች፣ በሙያ ብቃት ስታንዳርዶች እና በምዘና
መለኪያዎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት የፈጻሚ አካላትን እውቀትና ክህሎት ማሳደግ፣

 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤- የሁሉም ዞኖች/ ልዩ ወረዳዎች፤ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር


የመምህራንና የት/ቤቶች አመራር ሙያፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት አስተባባሪዎችና ፈጻሚዎች 200 በአራት
ማእከላት ለአምስት ቀናት በዳግም ምዘና በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት አተገባበር ላይ የግንዛቤ
ማስጨበጫ የአሰልጣኞች ስልጠና ይሰጣል፡፡ ለዚህም ለዞኖች/ ልዩ ወረዳዎች፤ወረዳዎች እና ለከተማ
አስተዳደሮች ቅጻቅጽ በማዘጋጀት ይላካል፡፡ ዳይሬክቶሬቱም የታችናው መዋቅር በተላከው ቅጻቅጽ
መሰረት መረጃውን አደራጅተው እንዲሊኩ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጠበጫ
ስልጠና ሰነድ ያዘጋጃል፣
በተሳታፊዎች ብዛት ሰነዶችን አባዝቶ ያሰራጫል፡፡
ግብ 7፡- በ 2012 ዓመት የሚመዘኑ ተመዛኞችን መረጃ በሚያስተምሩበት የትም/ት
እርከን፤የትም/ት ደረጃና በተመረቁበት የትም/ት በዞን፣ በልዩ ወረዳ እና በከተማ
አስተዳደሩ 100% ጥራቱን ጠብቆ መረጃዉ ተሰብስቧል፡
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

Page 12
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

 ደረጃዉን የጠበቀ መረጃ ማሰባሰቢያ ቅጽ በማዘጋጀት ለዞኖች ፤ልዩ ወረዳዎችና ለከተማ አሰተዳደሩ በመላክ
ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፡፡
 ከዞኖችና ከልዩ ወረዳዎች የተሰበሰበው መረጃ በክልል ደረጃ ይደራጃል ፡፡

ግብ 8፡- በክልሉ በሚሰጡ 13 የብሔረሰቦች አፍ መፍቻ ቋንቋ የትም/ አይነቶች የምዘና


መሳሪያዎች ዝግጅት ቁጥር ማሳደግ፡፡
 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- በክልሉ በ 13 የብሔረሰቦች አፍ መፍቻ ቋንቋ የት/አይነቶች የሚዘጋጁትን የአፍ
መፍቻ ቋንቋ ተቋማዊ በሆነ መልኩ እንዲዘጋጅ የመግባቢያ ሰነድመፈራረም፣
 የምዘና መሳሪያዎች አዘጋጆችና ኤዲተሮችን በተቀመጠው መስፈርት እንዲመለመሉ በማድረግ ስለአዘገጃጀቱ
በቂ ገለጻ በመስጠት ወደ ተግባር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
 የዝግጅትና የኤዲቲንግ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ምስጥራዊነቱን በጠበቀ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል
ይደረጋል፡፡
ግብ 9፡- በበጀት ዓመቱ የተመዘኑ 64046 ተመዛኞችን የመልስ ወረቀት ደረጃዉን በጠበቀና በጥራት በማረም
ውጤታቸው 100% በማጠናቀር በተገኘው ውጤት ላይ ከሚመለከተው አካል ጋር ውይይት በማድረግ ተላልፏል፡፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- ለእርማት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የመለየትና የማዘጋጀት፣ የቅድመ እርማት ሥራ

ለማከናወን ምስጢር ቁጥር የመስጠት እና እርማቱን የሚያከናዉኑ አካላትን የማስመልመል እንዲሁም የቅድመ-እርማትና

የእርማት ሥራ የሚያከናውኑ መምህራንን አሰፈላጊዉን ኦሬንቴሽን በመስጠት እርማቱ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡ የታረመው
ውጤት በተዘጋጀው ሮስተር የማጠናቀር ስራ ይሰራል፡፡ ውጤቱ ከተጠናቀረ በኋላ በተገኘው ውጤት ላይ ከሁሉም ዞኖች፣
ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳሩ ከሚመጡ ሀላፊዎችና የዳይሬክቶሬቱ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ ከቢሮው ሀላፊዎችና
ባለሙዎች፣ ከኮሌጅ ሀላፊዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ለ 3 ቀናት ውይይት ይደረጋል፡፡ በውይይቱ የተገኘውን
ግብኣት መሰረት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ይተላለፋል፡፡

ግብ 10፡- በበጀት ዓመቱ ለ 64,046 ተመዛኝ መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የተሰጠውን የብቃት
ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የተገኘውን የእውቀትና የክህሎት
ክፍተት በመለየት ለሚመለከታቸው ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት ግብረ-መልስ አሰጣን ማጎልበት፡፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ስራ የሚሰሩ ባለሙያዎችን

በመመልመል አሰፈላጊዉን ኦሬንቴሽን በመስጠት የምዘና ጥያቄ ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ ጥናቱ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡
 በተካሄደው የዳሰሳ ጥናት የተገኘውን የተመዛኝ የእውቀትና የክህሎት ክፍተት በመለየት ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት
የማሳወቅ ስራ ይሰራል፡፡
 በጥያቄ ትንተናው መሰረት የተለዩ ተገቢነት ያላቸውን ጥያቄዎችም በ Item Bank የማደራጀት ስራ ስራ
ይሰራል፡፡

Page 13
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

ግብ 11፡- በ 2012 ዓ.ም የተመዛኞች ውጤት ትንተና ላይ እና በዳሰሳ ጥናት በተገኘው የተመዛኝ የእውቀትና የክህሎት
ክፍተት መሰረት በማድረግ ከሚመለከታቸውና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- ለመምህራን፣ ለርእሳነ መምህራን እና ለሱፐርቫይዘሮች የሚሰጠውን የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ ለማሳካት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትና የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች የበኩላቸውን
አስተዋእጾ ማድረግ እንዲችሉ በተመዛኞች ውጤት ላይ የምክክር ውይት በክልል ደረጃ ይካሄዳል፡፡ በዚህ
የምክክር ስብሰባ በድምሩ 650 ተሳታፊዎች ይገኛሉ፡፡
ግብ 12፡- በ 2013 ዓ.ም የብቃት ማረጋገጫ ምዘና በመውሰድ ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ ላገኙ የ 1 ኛ ደረጃ እና የ 2 ኛ
ደረጃ መምህራን፣ ርእሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ/ሰርተፊኬት ለመስጠት
የማለፊያ ነጥብ ያመጡ ተመዛኞች በሰርተፊኬት ላይ በጥራት ተሰርቷል፡፡
 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- ዳይሬክቶሬቱ ከት/ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተጓደሉ ነገሮች እንዲሟሉ
በማድረግ ሰርተፊኬት የሚዘጋጅበት ሁኔታ የማመቻቸት ስራ በመስራት የብቃት ማረጋገጫ ምዘና በመውሰድ
ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ ላገኙ የ 1 ኛ ደረጃ እና የ 2 ኛ ደረጃ መምህራን፣ ርእሳነ መምህራንና
ሱፐርቫይዘሮች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ/ሰርተፊኬት ለመስጠት ለሰርተፊኬት ህትመትና በጥራት
በሰርተፊኬት ላይ የመምህራን፣ ርእሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ስም የመጻፍ ስራ (Caligraphically
writing names of candidates on licensing certificate) ይሰራል፡፡

ግብ 13፡- በአጠቃላይ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት አተገባበር ዙሪያ ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ አፈፃፀም ከ 60% ወደ
100% ማድረስ፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡- ደረጃዉን የጠበቀ መረጃ ማሰባሰቢያ ቅጻቅጾችና


ቼክሊስት በማዘጋጀት በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በት/ቤቶች እና በኮሌጆች
በአካልበመገኘት ለሁለት ዙር ድጋፍና ክትትል ይደረጋል፡፡
 በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣ በት/ቤቶች እና በኮሌጆች በአካል በመገኘት
ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በአንድ ዙር 12 ባለሙዎች በ 4 ቡድን በመሆን ጋፍ ያደርጋሉ፡፡

የ 2013 የካፒታል በጀት ዕቅድ ማጠቃለያ በጊዜና በበጀት የሚያሳይ ሠንጠረዥ

የዳይሬክቶሬቱ የክንዉን ጊዜያት የሚያስፈልግ የበጀት


ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ምንጭ
1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ ጠቅላላ ወጪ

ለእጩ ተመራቂ መምህራን እና ነባር መምህራን የሚሰጠው የሙያ


ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና በ 13 የብሔረሰብ የአፍ መፍቻ ቋንቋ
1   X X   5,200,000 በመንግስት
የትምህርት አይነቶች (የሲዳሚኛ፣ ወላይታቶ፣ ጋሞኛ፣ ጎፍኛ፣ ሲልጢኛ፣
ሀዲይሳ፣ ካምባቲሳ እና የጌዴኦፋ፣ የካፍኖኖ፣ ዳውሮኛ፣ ዳሸቴ፣ ሸክኖኖ

Page 14
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

የዳይሬክቶሬቱ የክንዉን ጊዜያት የሚያስፈልግ የበጀት


ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ምንጭ
1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ ጠቅላላ ወጪ
እና የኮረቴ) የምዘና ጥያቄዎችን በክልል ደረጃ በማዘጋጀት አጠቃላይ
በ 32 የትምህርት ዓይነቶች በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁ የምዘና
ጥያቄዎች/መሳሪያዎች ሕትመት /ፈተና ብዜት/፣ ጥረዛ እና የድልደላ
ሥራ በመስራት በተመረጡ 48 የምዘና ጣቢያዎች የሙያ ብቃት
ማረጋገጫ የፅሁፍ ምዘና መስጠት
ለእጩ መምህራን እና ነባር መምህራንና የትምህርት ቤት አመራር
የተሰጠውን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የጽሁፍ ምዘና እርማት በማከናወን
ተፈላጊውን የማለፊያ ነጥብ ላገኙ ተመዛኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ማስረጃ ለመስጠት ሰርተፊኬት ህትመት ክፍያና ተመዛኙ የመለሳቸው
2 መልሶችና የምዘና ውጤት ወደ መረጃ ቋት በማስገባት የምዘና ጥያቄ   X x  2,500,000 በመንግስት
ትንተና እና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በመስራት የተገኘውን የእውቀትና
የክህሎት ክፍተት በመለየት ለመ/ራን ትምህርት ኮሌጆችና
ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ-መልስ በመስጠት የምክክር ውይይት
ማድረግ፡፡
 
በየደረጃው ለሚገኙ መምህራን፣ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እና
የትምህርት ባለሙያዎች በሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕደሳት አፈጸጸም መመሪያ፣

3
በሙያዊ ብቃት ጄነሪክ ስታንደርድ እና በክንዋኔ ማህደረ-ተግባር ምዘና
 
x   1,500,000 በመንግስት
አፈጻጸም መመሪያ/ ሩብሪክ /Portfolios Assessment tools/ ላይ የግንዛቤ
ማስጨበጫ የአሰልጣኞች ስልጠና እና ለማህደረ-ተግባር ምዘና መዛኞች
ስልጠና መስጠት፡፡

       
በበጀት ዓመቱ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ በላቀ ደረጃ ለመፈጸም በየሩብ አመቱ 150,000
4 በ 2013 እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳዎችና ከከተማ X
አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር የውይይቶች ማድረግ

የ 2013 የካፒታል በጀት ዕቅድ ማጠቃለያ በጊዜና በበጀት የሚያሳይ ሠንጠረዥ

Page 15
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕደሳት ዳይሬከቶሬት የ 2013
ዓ.ም ዕቅድ

የዳይሬክቶሬቱ የክንዉን ጊዜያት የሚያስፈልግ የበጀት


ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ምንጭ
1ኛ 2ኛ 3ኛ 4ኛ ጠቅላላ ወጪ

በበጀት ዓመቱ ከአምስቱ የመ/ራን ትም/ኮሌጆች ተመራቂ ዕጩ


መምህራንን ጨምሮ ለ 64,046 ለነባር የ 1 ኛ እና የ 2 ኛ ደረጃ
5 መምህራንና የትም/ቤት አመራሮች ለምዘና ጣቢያነት በተመረጡ   X X  8,200,000 በመንግስት
45 የምዘና ማዕከላት ምዘናዉ 100% ያለ ምንም እንከን
ማከናወን

በ 2013 በጀት አመት የተመዘኑ 64,046 የአንደኛ ደረጃ ነባር


መምህራንና የት/ቤት አመራሮች እና ተመራቂ ዕጩ መምህራን የምዘና
6   X  2,561,840 በመንግስት
ወረቀት በማረምና ውጤት በማጠናቀር በተገኘው ውጤት ላይ
ከሚመለከተው አካል ጋር ውይይት በማድረግ ውጤቱ ማስተላለፍ፡፡

በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች፣ በከተማ አስተዳደሮች፣


በት/ቤቶች እና በኮሌጆች በአካል በመገኘት በዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ X 
7     X 275,760 በመንግስት
አፈጻጸም እና በማህደረ ተግባር ምዘና አፈጻጸም ላይ ድጋፍና ክትትል
ማድረግ፡፡

       
20,387,600
ጠቅላላ ድምር

Page 16

You might also like