You are on page 1of 35

የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.

ም ዕቅድ

ክፍል 1
የ 2009 ዓ.ም የወረዳው አጠቃላይ ትምህርት ዋና ዋና እቅዶች አፈፃፀም የሁኔታ ግምገማ
የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ፓኬጅ :-
በትምህርት ዘመኑ በወረዳው የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን በማሻሻልና የምዕተ ዓመቱን ግብ በውጤታማነት በመፈፀም የብቁ ዜጋ
ማፍራት ተልዕኮን የማሳካት ወሳኝ ግብ ዕውን ለማድረግ የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታችን ለማፋጠን ዓመታዊ እቅድ ተዘጋጅቶ ነበር
፡፡ ይህም እቅድ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ፣ የትምህርት ሽፋንን ለማሳድግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጁትን መርሃ-ግብሮች
መነሻ በማድረግ ከወረዳችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተገናዝቦ በዋና ዋና ግቦችና ተግባራት ታቅዷል::

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ አፈፃፀም ቁልፍ ተግባራት (70%) የወረዳውን አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማስጠበቅ
ተግባር ከክልል ት/ቢሮ መነሻ በማድረግ በውስጡ የተካተቱትን

1. የትም/ቤት ማሻሻል መርሃ-ግብር፣

2. የመምህራን ልማት መርሃ-ግብር፣

3. የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ት/ት መርሃ-ግብር፣

4. የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ መርሃ-ግብር፣

5. የትምህርት አመራር፣አሠራርና አደረጃጀት ማሻሻያ መርሃ-ግብር

6. የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ አገልግሎት የማስፋፋት

መርሃ-ግብር መነሻ በማድረግ ዕቅድ ታቅዶ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት

ሲደረግ ቆይቷል፡፡

1. የትምህርት አመራር አሰራርና አደረጃጀት ማሻሻያ መርሃ- ግብር


የትምህርት ሽፋኑን ፍትሃዊነትና ብቃቱን ለማሻሻል ከሀገሪቱ የልማትና ዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ግቦች ጋር አስተሳስሮ በብቃት እያቀደና
እቅዱን እየፈፀመ በቀጣይነት የሚሄድ አሠራርና አደረጃጀት አቀናጅቶ ከወረዳ እስከ ትምህርት ቤት የሚመራ የሰው ሃይል ልማት
ይጠይቃል፡፡

በዚህ መሰረትም የተለያዩ የአጭርና ረጅም ጊዜ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን
ማጠናከርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስተላለፍ እንዲሁም ከወረዳው ትም/ጽ/ቤት እስከ ት/ቤት ድረስ የትምህርት አመራሩን
የማብቃትና ውጤታማ የሆነ የአሰራርና አደረጃጀት ስርዓቱን ለማጠናከር የሚያስችል ተግባራት ታቅደው ተተግብረዋል፡፡

የወረዳው ትም/ቤቶች በሙሉ በአግባቡ ተመርጠው በቋሚነት በተመደቡ ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እንዲመሩ በማድረግና
ተከታታይ ስልጠና በመስጠት ለትምህርት ተቋማት ባለቤት እንዲኖራቸው ተደርጓል ፡፡ይኸውም ካሉት 83 የመንግስት አንደኛ ደረጃ
ት/ቤቶች እንዲሁም 2 2 ኛ ደ/ት/ቤቶች በጥቅሉ 79 ት/ቤቶች በቋሚ ር/መምህር የሚመሩ ሲሆን እነዚህ 85 ት/ቤቶች በ 20 ጉድኝት
ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን 19 ቱ ጉድኝቶች ሱፐርቫይዘር እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ ከወረዳ ትምህርት ሴክተር አደረጃጀትና አመራሩ ከጽ/ቤት እስከ ት/ቤት ድረስ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ
ፓኬጅ መርሃ-ግብሮችን ለመምራት በሚያስችል መልኩ የተደራጀ ቢሆንም በቀጣይነት ተልዕኮውን በውጤታማነት መምራት የሚችሉ
ት/ቤቶች የብቁ ዜጋ ማፍራት ተልዕኳቸውን እንዲወጡ በስነ- ምግባራቸው፣በሙያቸው፣በአመራር ብቃታቸው ፣በስራ ተነሳሽነታቸው
የትምህርት ሀብትን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል የሚችሉት የት/ቤት ጠንካራ አሰራር ሲኖር በመሆኑ አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት
ይጠበቃል፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 1


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

2. የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ-ግብር


 የትምህርት ቤት መሻሻል መርሃ-ግብር የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ አራት መሰረታዊ የሆኑ ርዕሰ ጉዳዮችን ማለትም፡-መማር-
ማስተማር፣ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢ፣የትምህርት ቤት አመራርና የህብረተሰብ ተሳትፎ ማዕከል በማድረግ በየትምህርት ቤቶች
በሚደረገው የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ ጥራት መነሻነት ይተገበራል፡፡በወረዳችን ካሉት 83 የመንግሰት የመጀመሪያ
ት/ቤቶች ውስጥ 80 ት/ቤቶች የ 3 ዓመት ስትራቴጅካዊ ዕቅድ አዘጋጅተዉ ከ 3 ዓመት የተቀዳ የ 2009 ዓ.ም
ዓመታዊ ዕቅድ አዘጋጅተው ወደተግባር ተገብቶ ይህን እቅድም እንደ ወረዳ ግምገማ ተደርጎ የግምገም ውጤቱን
ለትምህርት ቤቶች በመላክ ከወረዳው ግምገማ ተነስተውና ማሻሻያዎችን በመውሰድ እቅዱን እንዲከልሱ
ተደርጓል፡፡

በሁሉም ትምህርት ቤቶች በበጀት ዓመቱ ተማሪዎች ያለባቸውን የአቅም ችግር በመለየት እንዲበቁ ለማድረግ
ሰፊ ስራዎች ሲሰሩ የቆየ ሲሆን

1 ኛ ክፍል ከተለዩት ወ-2872 ሴት-2608 ድምር-5480 ዉስጥ

ወ =2702 ሴ =2398 ድ =5100 ተማሪዎች በቅተዋል አፈፃፀሙም 93.06% ደርሷል፡፡

ከ 2-5 ከተለ 0 ዩ ወ 3394 ሴት-3921 ድምር 7315

ወ =3074 ሴ =3637 ድ =6711 ተማሪዎች የበቁ ሲሆን አፈፃፀሙም 91.74% በቅተዋል፡፡

የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሀ-ግብር ዋናው ግብ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ሆኖ ሳለ የተማሪዎች


ውጤት ከጣሉት ግብ አንፃር በአብዛኛው ትምህርት ቤቶች ማድረስ ያልተቻለ ሲሆን የተማሪዎች ውጤትም
በሚፈለገው አግባብ በመጠኑ ቢሆን መሻሻል አሳይቷል ፡፡

ከዚህ መርሀግብር ረገድ ባግባቡ ተግባራዊ ያለመሆን ምክንያቶች

-የትምህርት አመራሩ፣መምህራን፣ወላጆችና ተማሪዎች በትምህርት ቤት መሻሻል ምንነትና ጠቀሜታ የያዙት ግንዛቤ


ወጥነት ያለው አለመሆን

-በተፈጠረው የወረዳ የጸጥታ ችግር በትምህርት ቤት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ችግር መኖርና ይህን
ምክንያት በማድረግ ተማሪዎች በተደጋጋሚ ት/ቤት አለመገኘት

-የትምህርት ቤትና የህብረተሰብ ግንኙነት አናሳ መሆን

-የትምህርት ክፍለ-ጊዜ በምክንያትና ያለበቂ ምክንያት መባከንና የባከኑትንም በአግባቡ ተይዘው አለመካካሳቸው

-የተማሪ ውጤት ማሻሻል ማለት የቁጥር እድገት ብቻ አድርጎ ማየትና ተማሪዎችን ሁለንታናዊ
እውቀት፣አመለካከት፣ክህሎትና የባህሪ ለውጥ ማምጣት መሆኑን አለመረዳት

ስለሆነም በሚቀጥለው ዓመት በዚህ መርሀ-ግብር ዙሪያ ውጤታማ ስራ በመስራት በተማሪዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ
ለማምጣት ሁሉም የትምህርት ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 2


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

- በወረዳችን የትምህርት ቤት ግቢዎችን ማራኪ የማድረግ ተግባራዊነት በጣም አናሳ መሆኑ ይታዎቃል፡፡ ስለሆነም በዚህ ተግባር ከፍተኛ
ስራ መስራት ይጠበቃል፡፡

-ወሳኝ የሆኑ የትምህርት ቤት የውስጥ ድርጅት የማሟላት፣ቤተ-መጽሀፍት /ፈርኒቸር ፣መጻህፍት፣የትምህርት መርጃ መሳሪያ፣ልዩ ልዩ
አገልግሎት ወዘተ/
-ወላጆችን በትምህርት ጥራት ላይ እንዲመክሩ በማድረግ
-ለተማሪዎች ድጋፍ ስርዓት ዘርግቶ ማስተማር በተለይ ማንበብና መፃፍ የማይችሉ ከ 2-5 ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለይቶ በማስተማርማብቃት፣
- የመማሪያ መፅሃፍትን በመገምገም ረገድ ጥሩ ጅምሮች መታየት ቢጀምሩም ቀጣይነት እንዲኖራቸው በቁርጠኝነት መነሳት
ይኖርብናል፡፡
3. የመምህራን ልማት መርሃ-ግብር
ቅድመ ስራ ላይ ስልጠናን በተመለከተ

 በ 2009 ዓ/ም ወደተለያዩ ኮሌጆጅ ተመልምለው የተላኩ እጩ መምህራን ብዛት

o ቅድመ መደበኛ በሰርፍትኬት ወ=0 ሴ=4 ድ=4

o በአዲሱ ሞዳሊት በዲፕሎማወ=22 ሴ=29 ድ=51

o በልዩ ፍላጎት በዲፕሎማ ወ=1 ሴ=0 ድ=1

o በድምሩወ=23 ሴ=33 ድ=56 አስፈላውን ፎርማሊቲ አሟልተው የመገጣጠሚያ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ወደ


ስልጠና ገብተዋል፡፡

የስራ ላይ ስልጠናን በተመለከተ

 የ 2009 ዓ/ም ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ተከታታይ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን በት/ት ዓይነት 300 መምህራን
ተወዳድረው ያለፉ ወ=31 ሴ=21 ድ=52 ለሚመለከተው አካል ልከናል፡፡

 ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ር/መ/ራን ወ=6 ሴ=1 ድ=7 መረጃ ለመምሪያው ልከናል፡፡

 የፒጀዲቲ ስልጠናን በተመለከተ የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ወ=15 ሴ=8 ድ=23 መልምለን ልከናል፡፡

 በሁለተኛ ዲግሪ የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን ወ=8 ሴ=2 ድ=10 መልምለን ልከናል፡፡

 ከፍትህ የትምህርት ውል የወሰዱ መ/ራን ወ=22 ሴ=12 ድ=34 እና የት/ቤት አመራሮች ወ=5 ሴ=4 ድ=9 ናቸው

በተሙማ የሚሳተፉ መ/ራን

በተሙማ የሚሳተፉ መ/ራን


በኢንዳክሽን ኮርስ (አዲስ መ/ራን) ነባር መ/ራን
የት/ት ደረጃ ወ ሴ ድ አማካሪ ወ ሴ ድ
ሰርትፍኬት 1 18 19 14 4 4 8
ዲፕሎማ 125 88 213 72 285 254 539
ዲግሪ 3 3 6 2 29 10 39
ድምር 129 109 238 88 318 268 586
በተሙማ የሚሳተፉ የት/ቤት አመራር
  ወ ሴ ድ
ር/መ/ር 73 6 79
ም/ር/መ/ር 5 0 5

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 3


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ሱ/ር 19 0 19

ሌሎች አጫጭር ስራላይ ስልጠናዎችን በተመለከተ

 1 ኛደ/ት/ቤት 1-4 የሚያስተምሩ መምህራን ወ=37 ሴ=61 ድ=98 ኤይከል ከተማ በተሰጠው አፍ መፍቻ ቋንቋ ስልጠና
ተሳትፈዋል፡፡

 የ 1 ኛደ/ት/ቤት ሱ/ር ወ=1 ሴ=0 ድ=1 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስልጠና ወስደዋል፡፡

 የሴት አመራሮችን አቅም ለማሳደግ ከ 1-4 የሚመሩሴ=2 ር/መ/ራንን ወደ ባህረዳር ዩኒቨርሲቲ ለ 3 ወር ስልጠና እንዲሳተፉ
ተደርጓል፡፡

 በ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ሱ/ር ወ=1 ሴ=0 ድ=1 እና መምህራን ወ=2 ሴ=0 ድ=2 ተሙማን በተመለከተ የአሰልጣኞች ስልጠና
ተሳትፈው ኮኪት 2 ኛ ደ/ት/ቤት ስልጠናውን የሰጠ ሲሆን ሸንፋ 2 ኛ ደ/ት/ቤትም በተመሳሳይ ስልጠናውን አካሂደዋል::

 በሙያ ፈቃድ እደሳት ዙሪያሱ/ር ወ=1 ሴ=0 ድ=1 ስልጠና ወስደዋል፡፡

 በሙያ ፈቃድ እደሳት ዙሪያ ር/መ/ር ወ=6 ሴ=1 ድ=7 ስልጠና ተሳትፈዋል፡፡

 በጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን በሳይንስ እና በሂሳብ ትምህርት ወ=6 ሴ=2 ድ=8
ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

 ለ 2 ኛ ዲግሪ ት/ት የሚወዳደሩ የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መርሱወችን መረጃወችን ለቅመናል፡፡

መ/ራንን ም/ር/መ/ራን ር/መ/ራን


ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ
9 2 11 2 0 2 2 0 2

 የፒጂዲኤሰኤል/PGDSL/ የሚሰለጥኑ የት/ት አመራሮች መረጃ ተደራጂቷል፡፡

ር/መ/ራን ሱ/ሮች
ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ
2 1 3 3 0 3
 የት/ቤት አመራሮች ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎትን በተመለከተ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጂነት አይከል ከተማ የ 3 ቀን ስልጠና በተሰጠን
መስፈርት መሰረት መልምለን ወ= 19 ሴ=1 ድ =20 መገጣጠሚያ ሰጥተን እንዲሰለጥኑ አድርገናል፡፡
 የሳይንስ እና ሂሳብ መምህራንን ስልጠና እንዲሰለጥኑ ወ=6 ሴ=2 ድ=8 መ/ራን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ መገጣጠሚያ ሰጥተን ልከናል::

በጉድኝት ሱ/ሮች የተሰጡ አጫጭር ስልጠናወች

በ 5 ጉድኝት የተሰጡ አጫጭር ስልጠናወች የተሳተፉ መምህራን ወ 155 ሴ 155 ድ 310

4- የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት መርሃ -ግብር


ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 4
የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 የዚህመርሀ ግብር ዓላማ የሀገራችንን ማህበራዊ እሴቶች በትምህርት ቤትና ከት /ቤት ውጭ እንዲሰርፅ በማድረግ
የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን መሰረት ለመጣልና ብቁ ዜጋ የማፍራ ተልዕኮን ለማሳካት ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግ
በሁሉም ት/ቤት የክልል እና የፌደራል ባንዴራ እንዲውለበለብ ተደርጓ መዝሙሩን በማዘመር መርሀ ግብሩ በሳምንት አንድ ቀን
ተስጥቶችት በሁሉም ት/ቤቶች በሰለጠነ መምህር ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ትምህርቱን የበለጠ ለማስፈፅ የአለቆች ህብረት እና
የጎበዝ ተማሪዎች ህብረት በሁሉም ት/ቤቶች እንዲቋቋሟም ተደርጓል፡፡
 በትክክል ቁጠባ የጀመሩ እና ቁጥር አዘል በማድረግ በሪፖረት ያሳወቁ 18 ት/ቤት ሲሆኑ ጥቅል መረጃዉም
920 ተማሪዎች 105919 ብር በባንክና ብድር ቁጠባ እዲቆጥቡ ሆኗል፡፡
በተቋም ደረጃ 70 ተቋማት ቦነድ የገዙ ሲሆን ጠቅላላ የገነዘቡ መጠን 53400.00(በ 2009

5- የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ መርሃ-ግብር


 ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የተሠራጩ የማስተማሪያ መፃህፍት ብዛት 78593
 አቋርጠው ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ ተማሪዎች ብዛት 336
 የማቋረጥ ምጣኔ በቅድመ መደበኛ 0℅
 የማቋረጥ ምጣኔ በመጀመሪያ ደረጃ 7.18 ℅
 የማቋረጥ ምጣኔ በሁለተኛ ደረጃ ከ 9-10 ኛ 11.12 ℅

 የባከነ ክፍለ ጊዜ

 እንደ ወረዳ የባከነ ክፍለ ጊዜ ብዛት 8053


 ከባከነው ውስጥ የተካካሰው ክፍለጊዜ ብዛት 7174

በ 2 ኛ ደረጃ የባከነ ክፍለ ጊዜ

 የባከነ ክፍለ ጊዜ ብዛት 118


 የተካካሰው ክፍለጊዜ ብዛት 116

6-የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጅ አገልግሎት መርሃ-ግብር


በሀገራችን ለትምህርት እድገት ማነቆ ሆነው የቆዩ ችግሮችን ለማስወገድ የትምሀርት ጥራትን ለማጎልበት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ
አገልግሎት ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርግ ነው፡፡ ማለትም ይህ መርሃ-ግብር ትምህርትን በቴክኖሎጅ ታግዞ እንዲሠጥ በማድረግ የጥራት ችግሩን
ለማሻሻልና ፍትሃዊ ትምህርትን ለማዳረስ አይነተኛ መሳሪያ ነው ፡፡

 በፍሌሽ የሬዲዮ ትም/ የሚሰጡ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብዛት 83

 1 ሬድዮ በአንድ ክፍል ሬሽዎ እየተሰራ ይገኛል፡፡


 በ 6 1 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የፕሪንተር ማሽን በመግዛት እየተገለገሉ ይገኛሉ፡፡
የትምህርት ሽፋንን ማሳደግ /25 %/
 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት
በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ወ 14837 ሴ 15708 ድ 30545 ተማሪዎችን ለማስተናገድ ታቅዶ ክንውኑ ወ 12362 ሴ
13259 ድ 25621 አፈፃፀሙም 83.87% የሴት ተማሪዎች ድርሻ 51.75% ደርሷል፡፡በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ወ-917 ሴ-

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 5


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

1134 ድ-2051 ተማሪዎችን ለማስተናገድ ታቅዶ ክንውኑ ወ-456 ሴ-524 ድ-980 ሲሆን አፈፃፀሙም 47.78% ሆኖ የሴቶች
ድርሻ 53.46% ነው፡፡

ቅድመ-መደበኛ ትምህርት መርሀ-ግብርን በሁሉም የወረዳችን ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመክፈትና ከ 4-6 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ
ህፃናትን ለመደበኛ ትምህርት ማዘጋጀት፡፡ በዚህምመሰረት ማህበረሰብ አቀፍ ወ-5488 ሴ-5359 ድ-10847 ለማስተናገድ ታቅዶ
በ 78 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ክንውኑ ወ-1790 ሴ-1812 ድ-3602 ሲሆን አፈፃፀሙ ደግሞ 33.2% ደርሷል ፡፡በ 4 አፀደ
ህፃናት ተቋም ወ-1031 ሴ-1166 ድ-2197 ህፃናትን ለማስተማር ታቅዶ ክንወኑ ወ-314 ሴ-347 ድ-661 ሲሆን ይህም
አፈፃፀም 30% ነዉ፡፡ቅድመ-መደበኛ ዕቅድወ-6519 ሴ-6525 ድ-13044 ክንውን ወ-2104 ሴ-2159 ድ-4263 ሲሆን አፈፃፀሙ
ደግሞ 32.7% ደርሷል
የልዩ ፍላጎት በአካቶ ትምህርት ወ 317 ሴ 271 ድ 588 ህፃናትን ለማስተማር ታቅዶ ክንዉኑ ወ 89 ሴ 73 ድ 162
በመማር ላይ ሲሆኑ አፈፃፀሙም 27.55% ነው፡፡ ለ 588 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በሶስት ትምህርት እንዲሰጥ
ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ ወ= 27 ሴ= 27 ድ=54 ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በ 3 ዩኑት ትምህርት እየተሰጠ ነው፡፡
-የጎልማሶች ትምህርትን በሁሉም ቀበሌዎች በማስፋፋት ሁሉንም ጎልማሶች የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ
በዘመኑ የተከፈቱ የመማሪያ ጣቢያዎች ብዛት

 አዲስ የተከፈቱ ጣቢያዎች ብዛት 22


 የነባር ጣቢያዎች ብዛት 115
 ከተለያዩ የበጀት ምንጮች አማካይነት የተቀጠሩ አመቻቾች ብዛት
 በወረዳ በተመደበ በጀት የተቀጠሩ አመቻቾች ብዛት ወ 23 ሴ 87 ድ 110(እየሰሩ ያሉ)

 እንደወረዳ በደረጃ 1 እና በደረጃ 2 ወ-4188 ሴ-10254 ድ-14442 ጎልማሶችን ለማሰልጠን ታቅዶ ወ-


2465 ሴ-1915 ድ-4380 ያህሉን ማሰልጠን ተችሏል፡፡ አፈፃፀሙም 30.32% ነዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ የሴቶች
ድርሻ 43.72% ሲሆን አፈፃፀሙን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት ቅንጂትን ይጠይቃል፡፡

ለዚህ ውጤት መብቃት ዋና ዋና ምክንያቶች

- በትምህርት ባለሙያዎች በመምህራንና በልዩ ልዩ አደረጃጀቶች የተቀናጀና የተጠናከረ እንቅስቃሴ በመደረጉ


- ህብረተሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት የመላክ ባህሉ እየተሻሻለ መምጣትና ህ/ሰቡ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን በማሟላት ሂደት ተሳትፎ በማድረጉ፣
- ት/ቤቶች የሚያስተምሩትን የክፍል ደረጃ ማሳደጋቸው
- በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች የጎልማሶች የንቅናቄ መድረክ በሰፊው በመደረጉ፣ለዚህም መሳካት የመምህራን፣የአመቻቾች፣የወመህና ቀትስቦ ቁርኝት
የተጠናከረ መሆኑ
-በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ ተግባራት እየተሻሻሉ መምጣት

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 6


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

o ያጋጠሙ ችግሮች

 የትምህርት ቤት አመራሮች የመርሱ መረጃዎችን በቸልተኝነትና በግምት ሞልቶ መላክ፡፡


 ተግባር ተኮር በተመለከተ አብዛኛው ማ/ሰብ ለት/ቱ ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታ አጋጥሟል፡፡
 ጽ/ቤቱ የኮፒ ማሽን ባለመኖሩ ምክንያት የተለያዩ ሰነዶችንና ቸክሊስቶችን ለየተቋማቱ አባዝተን ለመስጠት አስቸጋሪ መሆኑ፡፡
 መምህራን የራሳቸውን መረጃ በትክክል ያለማወቅ ችግር፡፡
 የበጀት እጥረት በመኖሩ መርሱዎችን በጉድኝትና በተቋም ደረጃ በመሄድ መደገፍና ሥራዎችን በበቂ ሁኔታ
መገምገም አልቻልንም፡፡
 አደረጃጀቶች የተፈጠሩት ለፖለቲካ ፍጆታ ነው የሚል የተዛባ አስተሳሰብ መያዙ፤
 ት/ቤቶች ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ሂደቱን በሚመለከቱ መረጃዎች አጠናክሮ ሳምንታዊ፣ወርሃዊ፣ሩብ
አመት እና አፋጣኝ ሪፖርቶችን አለመላክ እንዲሁም የሚላኩት ሪፖርቶች የተሟላ አለመሆን፤
 ት/ቤቶች የተሟላ መረጃ በወቅቱ ያለመድረስ እና በተጠየቀዉ አግባብ መሰረት መረጃ አለመስጠት፣
 የአቋራጭ ተማሪዎች ቁጥር በአፋጣኝ መጨመር፤
 የ 3 ኛ ክፍል አማረኛ መጸሃፍ የ 4 ኛ ተብሎ ከፌደራል መላክ (57 ካርቶን መጸሃፍ)
 ያልታተሙ መጸሃፍት አጥረት፤
 የጎልማሳ ት/ት በሚፈለገው ልክ አለመሄድ፤
 የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የመብራት ችግር፤
 የተማሪዎች የመጸሃፍ አያያዝ ችግር፤
 የዉሃና የመፀዳጃ ቤት ግንባታዉን ለማስኬድ የጨረታ መጓተት፤

የተወሰዱ መፍትሄዎች

 መረጃዎችን በመፈተሸ ችግር ያለበትን መረጃ ለት/ቤት አመራሮች በመመለስ እስተካክለው አንደያመጡ፣ በስልክ
እና ከማህደር ክፍል በመፈተሸ ችግርችን መፍታት ተችሏል፡፡
 መምህራን መረጃቸውን በአካል እንዲያረጋግጡ እና ከማህደር ክፍል በመፈተሸ ችግሮችን መቅረፍ ችለናል፡፡
 በቸክ ሊስትና በግብረ መልስ መደገፍ፣ መገምገም እንዲሁም የቀጣይ በጀት አመትን ታሳቢ በማድረግ በግል ወጭ
መስክ መዉጣት ተችሏል፡፡
 አደረጃጀቶችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸዉ የትም/ት ጥራት ማረጋገጫ ሁነኛ መሳሪያ እንደሆኑ ማስገንዘብ መቻሉ፡፡
 ት/ቤቶች በሙሉ ወቅቱን ጠብቀው ማለትም ወሩ በገባ እስከ 20 ኛው ቀን ወርሃዊ ሪፖርት እንዲልኩ፣ ሳምንታዊ
ሪፖርቶች በወቅቱ እንዲልኩ በስልክ፣በደብዳቤ እና በተለያዩ የስብሰባ አጋጣሚዎች ማሳወቅ፡፡
 የመረጃ ልዉዉጡ ፈጣንና የተሟላ ለማድረግ በስልክ መረጃ መቀበልና መስክ የወጡ ፈጻሚዎችን በማሳተፍ ለመቅረፍ ጥረት
ተደርጓል፡፡
 አቋራጭ ተማሪዎችን ለመመለስ አመራሩን፣ የቀበሌ መዋቅሩን በመጠቀም፣ መምህራንን እና የአቋራጭ ተከላካይ ግብረ ሃይል
በመጠቀም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ጥረት ተደርጓል፡፡
 ባለዉ መጸሃፍ ተቋማት አብቃቅተዉ እንዲጠቀሙ ተደረጓል፡፡
 በክፍል ሃላፊ መምህራን አማካኝነት ተማሪዎች መፅሃፋቸዉን እንዲሸፍኑ ተደርጓል፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 7


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ክፍል 2

የ 2010 ዓ.ም አጠቃላይ ዕቅድ መነሻዎች፣ታሳቢዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች


2.1 የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት

ራዕይ፡-

 ትምህርትና ስልጠናን በስፋት በማዳረስ ስብዕናው የተሟላ የስራ ባህልን ያሳደገ ብቁ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት

ተልዕኮ፡-

 በትምህርትና ስልጠና ውጤታማና ብቁ ዜጋዎች ማፍራት

 የጽ/ቤቱ እሴቶች ( values)


 በስነ-ምግባር መርሆች ተገዥ መሆን
 ጥራት ያለው ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት መስጠት
 በጋራ የመስራት ባህልን ማዳበር
 የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ማበረታታትና ማዳበር፣
 በግልጽነትና በታማኝነት ላይ የተመሰረተ የቡድን መንፈስ ማጎልበት፣
 አቅምን በማሳደግ በራስ መተማመን፣
 የህ/ሰቡን ባህል ማዳበር፣
 በሂስና ግለሂስ ማመን፣

 የመነሻ ዕቅዱ አስፈላጊነት/Importancy/


በዘመኑ ውጤታማ ስራ ለመስራት ከወረዳ እስከ ት/ቤት ያሉ አስተባባሪዎችና ፈፃሚዎች የሚከተሉትን አቅጣጫ በግልፅ በማሳየት
እንዲጠቀሙበት ለማድረግ ነው፡፡

 የዕቅዱ አጠቃላይ ግብ/Goal/


የትምህርትን ጥራት በማስጠበቅ ድህነትን መቅረፍ የሚችል ዜጋ በማፍራት ሀገራዊ ራዕይ እንዲሳካ የበኩሉን ድርሻ መወጣት

 የዕቅዱ ዋና ዋና አላማዎች/Aims/
 የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ የብቁ ዜጋ ማፍራት ተልዕኮን ማሳካት፣
 የትምህርት ሽፋንንና ጥራትን ማሳደግ፣
 የትምህርት ፍትሀዊነትን ማረጋገጥ፣
 የትምህርት ብቃትን ማሻሻል/ማሳደግ/፣

 የዕቅዱ ዝርዝር አላማዎች

 ከወረዳ እስከ ት/ቤቶች የተቀናጀ የልማት ሰራዊት መፍጠር

 የትም/ት ውጤትን ማሻሻል

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 8


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትን በሙሉ ትምህርት ማስገባት

 የመምህራንን ሙያዊ አቅም ማሻሻል

 የስነ-ዜጋና የስነ-ምግባር እሴቶችን ለህዝቡ በሚገባ ማስረፅ

 ዕቅዱን ለመፈፀም የምንከተላቸዉ መርሆች

-የዘመኑን ዕቅድ ለመፈጸም በመሳሪያነት የምንጠቀመዉ የመሰረታዊ ሥራ ሂደት ለዉጥ ጥናት ዉጤቶችን ነዉ፡፡ በጥናቶች ማስተግበሪያ
ማንዋሎቻችን ደግሞ ግልፅ የሆኑ መርሆችን አስቀምጠናል፡፡ በመሆኑም ዕቅድ ዝግጅቱ፣ትግበራዉ፣ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓቱም ሥራ
ሂደት ተኮር መሆን ስላለበት የሚከተሉትን የተወሰኑ መርሆች እንከተላለን ፡፡ ሌሎችንም እንደ ሁኔታዉ መጨመር ይቻላል፡፡
 አመራር ሰጭነት፡- ፓኬጁ የአመራሩን የበላይ ሚና በጉልህ አመልክቷል ፡፡ በመሆኑም አመራሩ ድርሻዉን በተገቢዉ መንገድ
ሊወጣ ይገባል፡፡
 የግብ ስኬት (Outcome based) ፡-አተኩሮ መንቀሳቀስ የፓኬጁም ሆነ የምዕተ ዓመቱ ግቦች ስኬት የሚለካዉ ብቁ ዜጋ
ማፍራት ላይ ነው፡፡ ግብዓትና ሂደት ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ቢሆንም መቋጠሪያው ግን ውጤት ላይ ማጠንጠን ይሆናል፡፡
 ደንበኛ ተኮር( customer focused) :- መሆን በትምህርት ሴክተር ዋና ደንበኞች/ ተማሪ፣ መንግስትና ወላጅናቸው፡፡
በመሆኑም ስናቅድ፣ስንተገብር፣ስንገመግም የደንበኛውን ፍላጎት ያማከልን መሆናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
 ብቃትን ማሳደግ (Empowerment ) :- ፈፃሚ የመወሰን አቅሙን ለማሳደግ ማበረታታትና የኃላፊዎችን ደጋፊነት ሚና
ማጠናከር፣
 የመረጃ አጠቃቀምን ማሻሻል (Improve ICT using system)፡- መረጃን በአግባቡና አማክሎ በማደራጀት ለፓኬጁ
አፈፃፀምም ሆነ ለአብይ ተግባራት ትንተና በአግባቡ መጠቀም፣
 የመረጃና መገናኛ ቴክኖሎጅ (ICT) አጠናቅሮ መጠቀም ፡- ከከተማ አስከ ት/ቤት በአጠቃላይ ስራችንን ማሳለጫነቱን
በመረጃነት የላቀ ተጠቃሚ መሆናችን እያረጋገጥን መሄድ፣
 አሳታፊነት(participatory) ፡- የትምህርት ስራ በባህርይው የብዙ ባለድርሻዎችን ተሳትፎ የሚጠይቅ ከመሆኑ በላይ ፓኬጁም
ይህንኑ የተግባር ግዴታ ስለሚያመለክት ልዩ ትኩረት እንሰጠዋለን፡፡
 ችግር ፈችነት ( problem solving) ፡-እቅዶቻችን አቅደን ወደ ተግባር ስንገባ የሚያጋጥሙ ችግሮች በርካታ ናቸው፡፡
ኃላፊዎች በተለይም በየጊዜው ለችግሮች አስቀድመው የመተንበይ እና መፍትሄ ሰጭነት ባህል መላበስ ይኖርብናል፡፡
 ግልፀኝነትና ተጠያቂነት(Transparncy & Accountability) ፡- ተልዕኳችን ግልጽ ነው፡፡ ውጤታችንም ተመሳሳይ ሊሆን ይገባል፡፡
ከዚህ በየደረጃው የሚጠበቅበትን ውጤት ያላስመዘገበ ደግሞ ቅድሚያ ለህዝብ ጥቅም ሲባል ተጠያቂ ሊሆን ይገባል፡፡
 የማትጋት ስርዓት ( Reward ) :- መልካም አፈፃፀሞች ትኩረት ይሻሉ፡፡ ለእነሱም እንደ ግለሰብም ሆነ ተቋማዊ በሆነ መልኩ
ዘወትር ልንለያቸው፣ልናበረታታቸውና ለሌሎች ልናስተላልፈው የምንችለውን የማትጊያ ስርዓት አቅደን ስንተገብረው
ይሆናል፡፡
 የእቅዱ ተፈፃሚነት ወሰን( Scope of the plan)
ከወረዳ ትም/ጽ/ቤት እስከ ት/ቤትና ቀበሌ ድረስ ያሉትን ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላትን እንዲሁም ባለድርሻዎች የሚተገብሩትን
ተግባራት ያካትታል፡፡

የትምህርት ዘመኑ ዕቅድ ዋና ዋና ይዘቶች


 የተዘጋጀን እቅድ ከወረዳ እስከ ት/ቤት በተደራጀ እንቅስቃሴ በውጤታማነት መፈፀም ፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 9


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 የአመለካከትና የክህሎት ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ተግባራትን መፈፀም፣

 የትምህርት ተሳትፎ ጊዜውን ጠብቆ በፍጥነት ማሳደግና

 ንቅናቄውን በህዝብ ግንኙነት እቅድ አቅዶ መፈፀም

የትምርት ሴክተር የልማት ሰራዊት በሁሉም የት/ተቋማት በመፍጠር በተቀናጀ እንቅስቃሴ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጁን
በውጤታማነት ማስፈፀም፣

 በየደረጃው ያሉትን የአመለካከት ችግሮች ለመፍታት የሚሰጡ ግምገማዊ ስልጠናዎች፣


 በየደረጃው ያሉ የግንዛቤና የክህሎት ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ተግባራት
 ንቅናቄዉን በተለያዩ ስራዎች አጅቦ መፈፀም፣
 እያደገ ያለው የትምህርት ተሳትፎ ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲሄድ ማድረግ፣
 በየደረጃው የተጠናከረ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፣
 ዕቅዱ መነሻ ያደረጋቸው ታሳቢዎች

 የወረዳችን የሶስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ


 የ 2009 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና ሪፖርት
 በትምህርት ሴክተር የሚወርዱ ልዩ ልዩ መመሪያና
 የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፖኬጅ ስድስት መርሃ-ግብሮች
 የምዕተ ዓመቱ ግቦች፣
 የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፖኬጅ የህዝብ ንቅናቄ መፍጠሪያ ሃገራዊና ክልላዊ ዕቅድ፣
 የተሻሻለው የር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ስምሪት መመሪያ፣
 የበጀት ምንጭ

 ከመንግስት የሚደብ መደበኛና ካፒታል በጀት /ብሎክ ግራንት/ና ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች በሚገኝ በጀት
 ከትምህርት ተቋማት የሚገኝ የውስጥ ገቢ

 ከህብረተሰቡ በገንዘብ፣ጉልበትና ማቴሪያል በሚደረግ ተሳትፎ/ድጋፍ/

ክፍል 3
የ 2010 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ዕቅድ
ቁልፍ ተግባር:- የተደራጀ የት/ት ልማት ሠራዊት መፍጠር 70%
ግብ 1፡- በ 2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት የአጠቃላይ የትምህርት
ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅን በውጤታማነት በመፈፀም ሁሉም ተማሪዎች በሁሉም የክፍል ደረጃዎችና
የትምህርት አይነቶች 50 እና በላይ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 10


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 1፡- በተደራጀ የትምህርት የልማት ሰራዊት የተማሪዎች ውጤት በሁሉም የትምህርት ዓይነት ሁሉም
ተማሪዎች 50℅ እና ከዚያ በላይ ማስመዝገብ፣
ተግባር 2፡- በሂደት ደረጃ የ 1 ለ 5 ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሂደቱ አባላት የጋራ በማድረግ ወደ ተግባር ማስገባት፣
ተግባር 3፡-ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የትምህርት ልማት ሰራዊትን ያካተተ ዕቅድ አዘጋጅተው ወደ ስራ
እንዲገቡ ማድረግ፣
ተግባር 4፡-በሁሉም ትምህርት ቤቶች የተማሪና የመምህራን የ 1 ለ 5 ና የልማት ቡድን አደረጃጀት ማደራጀት፤፣

ተግባር 5፡- ወመህ እና ቀትስቦ ት/ቤቶችን በባለቤትነት መንፈስ እንዲመሩ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በተግባርና በየሃላፊነታቸው
የአቅም ማጎልበቻ አጫጭር ስልጠና በመስጠት በየወሩ እየተገናኙ ት/ቤቶችን እንዲመሩ ማድረግ፡፡
1. የትምህርት አመራር አሰራርና አደረጃጀት ማሻሻያ መርሃ-ግብር

ግብ አንድ ፡-
በት/ቤቶች አጠቃላይ የት/ት ጥራት ማስጠበቂያ ኘሮግራምና የምዕተ ዓመቱን ግብ አቀናጅቶ
የሚፈፅም የትምህርት አመራር ሀይል በየደረጃው መፍጠር፡፡

ተግባር 1፡- አዲስ ለተቀጠሩ የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች ውጤት ተኮር ውል መስጠትና እነሱም በተዋረድ ለር/መ/ራን
እንዲሰጡና የአፈፃፀም ውጤትንም መሙላት፣
ተግባር 2 ፡- የሚመጡ አዳዲስ መመሪያዎችን ወደ ት/ቤቶች በማውረድ ለሱፐርቫይዘሮች፣

ለር/መ/ራንና ለመ/ራን በማስተዋወቅ ተግባር ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣

ተግባር 3 ፡- ከጉድኝት እስከ ት/ቤት ድረስ የተጠናከረ ተቋማዊ የውድድር ስርዓት


በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ መ/ራንና የት/ት አመራር አካላት በውጤታማነት እንዲወጡ ማድረግ፣
ተግባር 4 ፡- በት/ቤቶች የሴቶችን የአመራር ተሳትፎ አሁን ካሉበት የአመራር አቅም ወደ ተሻለ ተሳትፎ በማሳደግ
አቅማቸውን ማጠናከር፡፡

ግብ ሁለት ፡-
ት/ቤቶች በብቁና ለደረጃው በሚመጥኑ፣በአግባቡ በተመረጡና በሰለጠኑ ር/መ/ራንና
ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም በሌሎች ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች እንዲመሩ ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- ከ 1-8 ባሉ ት/ቤቶች 20 ክላስተር 20 ሊኒየር ዲፕሎማ መምህራን፣9 ር/መ/ራን ት/ቤቶች 5 ድገፍ ሰጭ
ሰራተኞችን እና ለ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 6 ድገፍ ሰጭ ሰራተኞችን በአዲስ ቅጥር በመፈፀም በወቅቱ እንዲመደብላቸው
ማድረግና ት/ቤቶች የተፈለገውን ግብ እንዲመቱ ማድረግ፣

ተግባር 2፡- የረዥም ጊዜ የስራ ላይ ስልጠና ያልጀመሩትን ር/መ/ራንና ሱፐርቫይዘሮች ከዞን በሚሰጠው ኮታ መሰረት የክረምት
ትምህርት በማስጀመር ለሚመሩት ት/ቤት ደረጃቸውን ብቁ ማድረግ፣

ተግባር 3፡- ሁሉም ሱፐርቫይዘሮችና ር/መ/ራን ከዞን በሚመጣ በወረዳ ደረጃ በሚዘጋጅ የአጭር ጊዜ ልዩ ልዩ ስልጠና እንዲያገኙ
ማድረግ፣

2.የመምህራን ልማት መርሃ-ግብር


ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 11
የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ግብ ሶስት፡-
በክልሉ መ/ራን ትም/ኮሌጆች የሚሰጠውን የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ቅድመ ስራ
ለማሰልጠን በሚሰጠን ኮታ መሰረት መፈፀም፡፡

ተግባር 1፡- የዞኑ የመርሱ ልማት ዋና የስራ ሂደት በሚልከው የእጩ ሰልጣኝ መ/ራን ምልመላና መረጣ ኘሮግራም በሚሰጠው
ኮታ መሰረት ማስታወቂያ በማውጣት ጥሪ ተደርጐ በሚዘጋጀው ስታንዳርድ መሰረት በመመዝገብ ለሚመለከታቸው አካላት
መላክ፣

ተግባር 2፡- በኮሌጆች የቃልና የፅሁፍ ፈተና አልፈው የተሰጠውን ክልል አቀፍ መረጣ ላለፉ ሰልጣኞች እንዲገለፁና እንዲሁም
የተመደቡበትን ኮሌጅና የመመዝገቢያ ቀን ለሰልጣኞች በወቅቱ ማሳወቅ፣

ግብ አራት፡-

በወረዳው ከሚገኙ ት/ቤቶች በማስተማር ላይ ከተሰማሩት መ/ራን በት/ት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ኘሮግራሞች
በማሳተፍ ተገቢውን አካዳሚያዊ እውቀት፣ሙያዊ ስነ-ምግባርና አወንታዊ አመለካት ያላቸው መ/ራንን
ማፍራት፡፡

ተግባር 1፡- በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች በማስተማር ላይ ያሉ የዲፕሎማ መ/ራን ከዞን ትም/መምሪያ በሚሰጠን ኮታ መሰረት
በመመልመል በዲኘሎማ ደረጃ በሊኔየርና በክላስተር እንዲሁም በዲግሪ ኘሮግራም እንዲከታተሉ ማድረግ፣

ግብ አምስት፡-

መ/ራን በተግባር መሳሪያዎች ቋት የሙያ ማሻሻያ ኘሮግራም ስልጠና ሂደት በማሳተፍ አካዳሚያዊ
እውቀታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸውን በማሻሻል ሀላፊነታቸውን የሚወጡና በራሳቸው እንዲተማመኑ
ማስቻል፡፡

ተግባር 1፡- በኘሮግራሙ አተገባበር ላይ የነበሩ ችገሮችን በመፍታት መ/ራን የተግባር መሳሪያ ሙያ ማሻሻያ ኘሮግራም
ተግባራት በት/ቤትና በጉድኝት ማዕከላት በአግባቡ ፈፅመው የተማሪዎችን ውጤት የማሻሻል ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ማድረግ፣

ተግባር 2፡- አዲስ ለሚቀጠሩና ለነባር መ/ራን በተመደቡበት ት/ቤት የሙያ ትውውቅ ኮርስና

የተግባር መሳሪያዎች ቋት ስልጠና መጀመር ወይም መቀጠል እንዲችሉ ማድረግ፣

ተግባር 3፡- አዲስ ለሚከፈቱ ት/ቤቶች ለተግባር መሳሪያዎች ቋት ስልጠና አጋዥ የሚሆኑ የስልጠና ቁሳቁሶችን ለት/ቤቶች
አባዝቶ እንዲዳረሱ ማድረግ፣

ተግባር 4፡- ስልጠናው በአግባቡ እንዲካሔድ ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ ተደርጐ ጠንካራና ደካማ

ጐኖችን በመለየትና ከት/ቤቶች የሚመጡ ሪፖርቶችን በማጠናከር ግብረ-መልስ

እንዲሰጥባቸውና የተሞክሮዎች ልውውጥ ማድረግ፣

ተግባር 5፡- ስልጠናዎች በትክክል በተዘጋጀው መርሀ-ግብር መሰረት እየተካሔዱ መሆናቸውን

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 12


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

እንዲረጋገጡ ማድረግ፣

ተግባር 6፡- የኘሮግራሙ የሩብ አመት፣የ 6 ወርና ዓመታዊ የመረጃ አያያዝና ሪፖርት

የተጠናከረ መሆኑ እንዲረጋገጥ ማድረግ፣

ግብ ስድስት፡-

በወረዳው ውስጥ ያሉ መ/ራን የስልጠና ፍላጐታቸውንና ያሉባቸው የአቅም ክፍተት ተለይቶ ወቅታዊ አጫጭር
ስልጠና በመሰጠት ተጨማሪ አቅም መፍጠር፡፡

ተግባር 1፡- የስልጠና ፍላጐት ከልዩ ልዩ መረጃዎች መ/ራን ካለባቸው የአቅም ክፍተት

በመለየት ተጨማሪ አቅም ሊፈጠርላቸው የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ለመስጠትና ከወቅታዊ

ለውጦች ጋር በማስተሳሰር እንዲሰጥ ማድረግ፣

ተግባር 2፡- በተለየው የስልጠና ፍላጐት መሰረት ስልጠናው መቼ፣የት፣ለማን፣በምን ያህል ጊዜ

እንደሚሰጥ ኘሮጀክት እንዲቀረፅ ማድረግ፣

ተግባር 3፡- ስልጠናውን ለመስጠት ሞጁሎችን ማዘጋጀትና አጋዥ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት፣

ተግባር 4፡- ስልጠናው ያመጣውን ለውጥ በመገምገም ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት

የማስተካከያ ስራዎችን መስራት፣

ግብ ሰባት፡-

የመ/ራን፣ር/መ/ራንና ሱፐርቫይዘሮችን ጥቅማጥቅሞች በማስጠበቅ መብቶቻቸውን


ማክበር፤ግዴታቸውን እንዲወጡ ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- የመርሱ ዝውውርን ለመስራት ወቅቱን ጠብቆ የዝውውር መሙያ ቅፅ ለት/ቤቶች

መላክና በመመሪያው መሰረት ማስሞላት፣

ተግባር 2፡- ተሞልቶ የሚመጣውን የዝውውር መረጃ ማጠናከርና ወደ ዞን የሚላከውን በወቅቱ መላክ፣

ተግባር 3፡- ዝውውሩን በወቅቱ፣ግልፅ በሆነ መንገድና አግባብ ያለው ቅሬታ በማያስነሳ ሁኔታ መስራት፣

ተግባር 4፡- የትምህርት ደረጃቸውን የሚያሻሽሉና የቆይታ ጊዜያቸውን አሟልተው የደረጃ እድገት

ተጠቃሚ የሚሆኑ መ/ራን፣ር/መ/ራንና ሱፐርቫይዘሮችን መረጃ በማጠናከር በወረዳ

አስተዳደሩ በጀት በማስያዝ ተጠቃሚ ማድረግ፣

ተግባር 5፡- በስራ ቦታ ላይ ያለ ምክንያት በማይገኙና የስራ ሰዓትን በሚያባክኑ መርሱዎች ላይ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 13


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ፣

ተግባር 6፡- መ/ራን፣ር/መ/ራንና ሱፐርቫዘሮች በሚሰጡት አስተያየት መሰረት የተገልጋይ ፍላጎትን እንዲሻሻል ማድረግ፣

ተግባር 7፡- አግባብነት ያለቸውን ቅሬታዎች በመቀበልና በመመርመር አፋጣኝ ምላሽ መስጠት፣

ግብ ስምንት
በሁሉም ደረጃ የሚገኙ መለስተኛና በመምህር ደረጃ ያሉ መምህራንን መመዘን፡፡

ተግባር 1፡- በሁሉም ደረጃ ያሉ፣በመለስተኛ ደረጃና በመምህር ደረጃ የሚገኙ መምህራንን መለየት፣

ተግባር 2፡- ለተለዩት መምህራን ምዘና የሚሰጥ መዛኝ መለየትና ለስልጠና መላክ፣

ተግባር 3፡- ለተለዩት የተመዛኝ መምህራን የሚያበቃ የምዘና መሳሪያዎችንና የበጀት ዝግጅት ማከናወን፣

ተግባር 4፡- የምዘና ማስተዳደርና ውጤት ገለፃ ተግባራትን ማከናወን፣

ተግባር 5፡- በስታንዳርዱ መሠረት ምዘናውን ላለፉ መምህራን የሙያ ፈቃድ መስጠት፣የሚጠበቅ ውጤት ተማሪዎች
ብቃታቸው በተረጋገጠ መምህራን ይማራሉ፣መምህራን ለስራቸው ይተጋሉ፣ለሙያቸው ክብር ይሰጣሉ፣

ግብ ዘጠኝ የይዘትና የፔዳጎጅ ምዘና ለወሰዱ ጀማሪ መምህራን የተግባር ምዘና ይሰጣል፡፡
ተግባር 1፡-
የይዘትና የተግባር ምዘና የተመዘኑ መምህራንን የስምሪት መረጃ ማደራጀት፣

ተግባር 2፡- ለተመዛኞች በቂ ሊሆን የሚችል መዛኝ መለየትና ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ፣

ተግባር 3፡- ለተመዛኞች የተዘጋጀውን ሩብሪክስ ለተመዛኞች ቀድሞ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ፣

ተግባር 4፡- የተመዛኝ ስምሪት፣የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን መስራት፣

ተግባር 5፡- የተመዛኞችን ውጤት ከመዛኞች መቀበልና የማጠናከር ስራ መስራት፣

ተግባር 6፡- በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ውጤት ላመጡ መምህራን የሙያ ፈቃድ እንዲያገኙ ማድረግ፣የሚጠበቅ
ውጤት፡-ተማሪዎች ብቃታቸው በተረጋገጠ መምህራን ይማራሉ፣መምህራን ለስራቸው ይተጋሉ ለሙያቸው ክብር ይሰጣሉ፣

.የትምህርት ቤት ማሻሻያ መርሃ-ግብር


ግብ አስር
በትምህርት ቤት መሻሻል መርሀ ግብር ላይ ያለውን የአመለካከት የክህሎትና የግብዓት ችግሮችን ለመቅረፍ
የሚያስችል በየደረጃው ላሉ አካላት ግምገማ ነክ ስልጠና በመስጠት የተሻለ ፈፃሚና አስፈፃሚ ሀይል
መፍጠር፡፡

ተግባር 1 ፡- በወረዳው ውስጥ በአጠቃላይ ትምህርት በተለይም በትምህርት ቤት መሻሻል ላይ ባለድርሻ ለሆኑት
አካላት ተካታታይ ስልጠና መስጠት፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 14


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 2 ፡- ከወረዳ እስከ ት/ቤት ድረስ አዲስ ተመድበው፣ተቀጥረው ወይም ተዛውረው ለሚመጡ
ር/መ/ራን፣ሱ/ቫይዘሮችንና መምህራን የፅንስ ሀሳብና ተግባር ተኮር ስልጠና መስጠት፣

ግብ አስራ አንድ
የወረዳው ት/ቤቶች የመማር-ማስተማር ሂደቱንና የሁሉንም ተማሪዎች ውጤት እያሻሻሉ የሚያስችል
ዓመታዊ የትምህርት ቤት መሻሻል ዕቅድን በአሳታፊነት ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ፡፡

ተግባር 1 ፡- ሁሉም የወረዳው ት/ቤቶች በዕቅድ ዘመኑ ያጠናቀቁትን ዓመታዊ የት/ቤት መሻሻል እቅድ
አዘገጃጀት፣አተገባበርንና ውጤት ግምገማ በማድረግ የቀጣዩን የሦስተኛ ዓመት ዕቅድ በአሳታፊነት
አዘጋጅተው ማፅደቅ፣

 የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ ግምገማ ማካሄድ


 በተደረገው ግምገማ ት/ቤቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ መለየት
 በተማሪዎች ውጤት መማር-ማስተማሩ የተገኘ ለውጥ ካለ ለተሞክሮ መጠቀም

ተግባር 2 ፡- የት/ቤት ማሻሻያ መርሀ-ግብር ሂደት በመሆኑ የትምህርት ተቋማት ካለፉት አንድ ዓመት የዕቅድ ዝግጅት
ሂደት፣አተገባበር፣ከተገኝው የግብ ስኬት ግምገማ፣ውጤትና ለግምገማው ከተፈጠረው የግንዛቤ ለውጥ
መነሻ በማድረግ የስትራቴጅክ እቅድ ዋና ዋና ግቦችና ተግባራትን ክለሳ ማድረግ፣

2..1 በወረዳና በቀበሌ የተካሄዱትን መድረኮችና በአገር አቀፍ ደረጃ በታቀደው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅድ የ 2010 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድን መከለስ

2..2 እቅዱን ለባለድርሻ አካላት ትውውቅ ማድረግና ወደ ስራ መግባት

2..3 በእቅድ ትውውቅ ላይ የተገኙ ባለድርሻ አካላትን በየደረጃው በቃለ-ጉባኤ አስደግፎ መያዝ

2..4 በእቅድ ትውውቅ በባለድርሻ አካላት የተነሱ ዋናዋና ጉዳዮችንና እቅዱን ለመተግበር የሚያጋጥሙ
ችግሮችና ለችግሮች የተሰጠ መፍትሄ የተፈጠረ መነሳሳትን ቀምሮ መያዝ

ተግባር 3 ፡- የት/ቤት ዓመታዊ የት/ቤት መሻሻል ዕቅድ በአራቱ አብይ ርዕስ ጉዳዮች በአስራ ሁለት ንዑሳን ርዕስ
ጉዳዮችና ሁሉንም ስታንዳርዶች መሰረት በማድረግና የግምገማ ትግበራውንና ሪፖርቱም ይህን አግባብ
የተከተለ ማድረግ፣

3.1 በት/ቤት ማሻሻያ አብይ ርዕስ ጉዳዮችንና ስታንዳርዶችን መምህራን በንቃትና በውጤታማነት ስለመሳተፋቸው
በየወሩ ግምገማ ማካሄድ

ተግባር 4 ፡- ዓመታዊ ዕቅድን ከአዲስ ት/ቤት ማሻሻያ ዕቅድ ግብ ጋር በማያያዝ ማለትም የመምህራንን ግብ
ከተማሪዎች ግብ ጋር ማስተሳሰር፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 15


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 5 ፡-በተጣለው የተማሪዎች ማሻሻያ ግብ ላይ የት/ቤቱ መምህራን፣ሰራተኞች፣ተማሪዎች፣ልዩ ልዩ


አደረጃጀቶችና ወላጆች በልዩ ልዩ መድረኮች ላይ ግልፅነት እንዲኖራቸው ማድረግና በአተገባበሩ ላይ
የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ማድረግ፣

5.1 በተጣለው የተማሪዎች ግብ ላይ የት/ቤቱ ማህበረሰብና ወላጆች፣እንዲሁም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ግልጽ


እንዲሆኑ ማድረግ

5.2 በተጣለው የተማሪዎች ግብ ላይ ለመወያየት ልዩ ልዩ መድረኮችን መፍጠር

5.3 የተፈጠሩ መድረኮችን ውጤት በመገምገም ለቀጣይ በግብዓትነት መጠቀም

5.4 የመምህራን ሰራተኞች፣ተማሪዎች ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና ወላጆች በተጣለው የተማሪዎች ማሻሻያ ግብ ላይ


ተከታታይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማገዝ

ተግባር 6፡-በትምህርት የሚገኙ የልዩ ልዩ አደረጃጄቶች የመምህራን፣የወላጆች፣የአመራሩና የሲፐርቫይዘሮች ተወካዮች


የተሳተፉበት የት/ቤት ማሻሻያ እድገትና የተማሪዎች ውጤት ላይ በት/ቤት ደረጃ በዓመት 2 ጊዜ
የት/ቤት መሻሻል አጠቃላይ የምክክር ጉባኤ ማድረግና ቀጣይ ሊሻሻሉና ሊጠናከሩ በሚገባቸው
ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ አስቀምጠው ሁሉም ባለድርሻዎች የራሳቸውን እንዲወጡ ማድረግ፣

6.1 የት/ቤት ማሻሻያ አጠቃላይ የምክክር ጊዜውን ጠብቆ ማካሄድ

6.2 በምክክር ጉባኤው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦችን ቀምሮ መያዝና በግብዓትነት መጠቀም

6.3 የምክክር ጉባኤው ያመጣውን ለውጥ መከታተልና ለሚመለተው አካል ማሳወቅ

ተግባር 7፡- በት/ቤት ደረጃ በየወሩ፣በጉድኝት ደረጃ 3 (በየሩብ አመቱ) በወረዳ ደረጃ 2 ጊዜ በትምህርት ሴሚስተር
መጨረሻ ላይ በትምህርት ቤቱ ማሻሻያ ውጤት ላይ ያለበትን ሁኔታ አጀንዳ አድርጎ መወያየት፣

7.1 በየደረጃው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መከናወኑን ማረጋገጥና በየጊዜው በግብረ-መልስ ማሳወቅ

ግብ አስራሁለት

የትምህርት ቤት ማሻሻያ ፕሮግራም በወረዳው ውስጥ ተቋማዊ የሆነ የአሰራር ስርዓት


እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

ተግባር 1 ፡- 50/90 የት/ቤት ኮሌጅ ግንኙነት ውስጥ በሆነ መንገድ በት/ቤት ማሻሻያ መርሀ- ግብር እንዲሆን ማድረግ፣

1.1 የት/ቤት ማሻሻያ መርሀ-ግብር በውጤታማነት ለመፈፀም ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 16


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 2 ፡- በት/ቤት ውስጥ ያሉ መምህራንና ሰራተኞች በዘመኑ በት/ቤት ማሻሻል ኮሚቴ በአባልነት ይህንም ከአራቱ አብይ
ርዕስ ጉዳዮች በአንደኛ ንቁ ተሳትፎ የማድረግ ተቋማዊ ባህል መፍጠር፣

ተግባር 3 ፡- በወረዳችን ያለፉት ዓመታት የትምህርት ቅበላ የሶስት ዓመት ት/ቤት ማሻሻል የውጤት ጥናት በመስራት
ለማሻሻያ ግብዓትነት መጠቀም፣

ተግባር 4 ፡-የት/ቤት ማሻሻያ ዕቅድ ውጤትን ማደረጃጀትና በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ ማዋል፣

ተግባር 5 ፡- ትምህርታዊ የጥናትና ምርምር ፅሁፎችን ውጤት ማሳተም፣ግብረ-መልስ መስጠት ፣ማሰራጨትና


ከሚመለከታቸው አካላት /መምህራን፣ወላጆች፣ተማሪዎችና የትምህርት ባለሙያዎች ጋር ተገቢውን ውይይት
ማካሄድ፣

ግብ አስራ ሶስት የት/ቤትና ህብረተሰብ ግንኙነት በታቀደና በተደራጃ መልኩ በማጠናከር


ህብረተሰቡም የተማሪዎች ውጤት የማሻሻሉን ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ
ማድረግ፡፡
ተግባር 1 ፡- ሁሉም የወረዳው ት/ቤቶች ህብረተሰቡ የተለያዩ ግብዓቶችን ለሟሟላት በገንዘብና ፣በጉልበትና በቁሳቁስ
ለተቋሙ በመደበኛውና በካፒታል በጀት 80 % እንዲሸፍን ማድረግ፣

ተግባር 2 ፡- ወላጆች በዓመት ውስጥ በየ 2 ወሩ ለ 5 ጊዜ በመገኘት በት/ቤት ዕቅድ አፈፃፀምና በተማሪዎች ውጤት ላይ
እንዲወያዩና የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ፣

ተግባር 3 ፡- ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉት የህዝብ ም/ቤቶችና የወረዳው አስተዳደር አካላት በዕቅድ ዘመኑ በፓኬጅ አተገባበር
ሪፖርት ቀርቦለት እንዲመክርና የድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ፣

ተግባር 3 ፡- ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ህዝባዊ ማህበራትና አደረጃጀቶች በየደረጃው ባሉ ተቋማት በፓኬጅ አተገባበር ሪፖርት
እንዲያመጡና ሚናቸውን እንዲጫወቱ ማድረግ፣

ግብ አስራ አራት በክፍል ውስጥ መማር-ማስተማር ሂደቱን በአዲስ የትምህርት ቤት ማሻሻል ማዕቀፍ
መሰረት እያሻሻሉ በመሄድ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፡፡

ተግባር 1 ፡- በወረዳው ውስጥ ያሉት ሁሉም የመጀመሪያ ሳይክል /1-4/ የክፍል ውስጥ አደረጃጀት ከነባር ዘዴ ወጥተው
አዲሱን ተማሪ ተኮር አማራጮች በሙሉ እንዲተገበሩ ማድረግ ፣

1.1 የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አደረጃጄቶችን በሁሉም የመጀመሪያ ሳይክል /ከ 1-4/ ት/ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ፣

ተግባር 2 ፡- በወረዳው የሚገኙ የአንደኛ ክፍል አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በአዲስ የክላስተር ክረምት ባጠናቀቁ መምህራን
እንዲማሩ ማድረግ፣

2.1 የክላስተር ክረምት ስልጠና የጀመሩ መምህራንን ለይቶ መያዝ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 17


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

2፣2 ስልጠና ያጠናቀቁ የክለስተር ሰልጣኝ መምህራንን ከ 1 ኛ ክፍል ጀምሮ ወደላይ መመደብ

ተግባር 3፡- በወረዳው የሚገኙ የ 1 ኛ ክፍል ሴክሽኖች ውስጥ የክላስተር ቋንቋ ስልጠና የወሰዱ መምህራን እንዲመደቡ
በማድረግ በመንፈቅ ዓመቱ መጨረሻ የተማሪዎች የቋንቋ ክህሎት የሚጠብቀው ፕሮፋይል ላይ
እንዲደርስ ማድረግ፣

3.1 በመንፈቅ ዓመቱ መጨረሻ የተማሪዎች የቋንቋ ከህሎት የሚጠበቀው ፕሮፋይል ላይ እንዲደርስ
ከመምህራን ጋር ስምምነት ላይ ማድረስ፣

ተግባር 4 ፡-ተማሪዎች በየ ሩብ ዓመቱ መጨረሻ በተጣለው ግብ የተከናወኑ ተግባራትንና


በተገኘው ውጤት ላይ ውይይት ማድረግ፣

ተግባር 5 ፡- ተማሪዎች በዓመቱ ውስጥ በሙሉቀን የሚማሩት 1 ,075 ,30 ሰዓት በፈረቃ
የሚማሩበት ደግሞ 820 ሰዓታት ትምህርት ያገኙ መሆኑን ማረጋገጥ በበቂ ምክንያት ለሚቀሩ መምህራን
የተተኪ መምህራንን ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድርግ፣

5.1 ከት/ቤቱ ማህብረሰብ ጋር በመነጋገርና በመተማመን የሙሉቀን ትምህርት መጀመር

5.2 የክፍለ ጊዜ ብክነት እንዳይፈጠር የተተኪ መምህራንን ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ፣

ተግባር 6፡- በአጠቃላይ በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤቶች የቤተ-ሙከራ አጠቃቀም በአግባቡ
ተቃኝቶና ተጠንቶ የሳይንስ ትምህርት ቤቶች የቤተ-ሙከራ አጠቃቀም በአግባቡ ተቃኝቶና ተጠንቶ
የሳይንስ ትምህርት በተሸለ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ስልት ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ

6.1 የሳይንስ ኪትን በአግባቡ መጠቀም

6.2 የሳይንስ ቤተ-ሙከራ / በሶስቱም ሳይንሶች / በሁሉም ሙሉ ሳይክል ት/ቤቶች በአግባቡ የሚጠቀሙበትን ስልት ቀይሶ
መንቀሳቀስ፣

ተግባር 7፡- ለመጀመሪያ ደረጃ 2 ኛ ሳይክል የቤተ-ሙከራ ስታንዳርድና አደረጃጀት ማንዋል በአሳታፊነት
አግባብ በማዘጋጀት ተገቢውን ትውውቅ በማድረግ ትምህርት ቤቶችን ማደራጀት፣

ተግባር 8፡- በወረዳው በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ መጀመሪያ ሳይክልና ንባብን የሚያሻሽሉ ስነ- ዘዴዎችን በመጠቀም ሁሉም
ህፃናት እንዲያነቡ ማድረግ፣

8.1 በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ማንበብና መፃፍ ባለመቻላቸው ድጋፍ ለማድረግ የተለዩ ተማሪዎችን መረጃ
በአግባቡ መያዝና ለውጡን እየተከታተሉ ሪፖርት ማድረግ

ተግባር 9፡- በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች የሳይንስና የሂሳብ ትምህርት አሰጣጥን በማሻሻል የተማሪውን ውጤት
ማሻሻል፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 18


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

9.1 የሳይንስና የሂሳብ ትምህርት አሰጣጥን ለማሻሻልና የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ ከመምህራን ጋር በመወያየትና
ስምምነት በመድረስ እንዲሁም ልዩ ልዩ እቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ

9.2 በአተገባበሩ የተገኙ ተጨባጭ ለውጦችና ያጋጠሙ ችግሮችን በግብዓትነት መጠቀም

ተግባር 10፡- የመማር-ማስተማሩን ስራ ለማጠናከር የሚያስችል ጥናታዊ ፅሁፎችንና የፅንስ ሀሳብ ፅሁፎችን
እያንዳንዱን የትምህርት አይነት ሊያጠናከር በሚችል መልኩ ዝግጅት ማድረግና ማጠንከር

1.1 የመማር-ማስተማርን ስራ ለማጠናከር ጥናታዊና የፅንሰ ሀሳብ ፅሁፎችን ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ
1.2 በጥናታዊ ፅሁፎች ውይይት /ሲፖዚየም / በት/ቤት ደረጃ፣በጉድኝትና በወረዳ ደረጃ ማካሄድ
1.3 በተማሪዎች ውጤትና የሳይንስ ሂሳብ ትምህርት ላይ የተገኙ ተጨባጭ ለውጦች

ተግባር 11 ፡- የሳይንስ መምህራን መድረክ በትምህርት ቤትና በወረዳ ደረጃ ማዘጋጄትና እንዲዘጋጁ
በማድረግ ተማሪዎች በሳይንስ ትምህርት ውጤታማ የሚሆኑበትን አግባብ መሞከር፣

ግብ አስራ አምስት
በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት በአዲሱ ክልላዊ ስታንዳርድ ወሳኝ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት
ምቹና ማራኪ በማድረግ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል፡፡

ተግባር 1፡- ሁሉም ተቋማት የመማር-ማስተማር ዘዴዎችንና የተማሪዎችን አያያዝ እንዲሁም የትምህርት
ቤቶች አካባቢ ተማሪዎችን የሚማርኩ፣የሚያበረታቱና ከስጋት ነፃ እንዲሆኑ ማድረግ፣

ተግባር 2 ፡- በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙ መማሪያ ክፍሎች ሳቢ፣ማራኪና ምቹ እንዲሆኑ


ማድረግ / ሞዴል/ ማድረግ፣

2.1 በአዲስ የሚሰሩ ክፍሎችን እስታንደርዱን የጠበቁ እንዲሆኑ ማድረግ

ተግባር 3 ፡- ተጨማሪ ክፍሎችን በመገንባት የተማሪ ክፍል ጥምርታን 1-4 1፡50 ና 5-8 1 ለ 45 ማድረስ፣

ተግባር 4 ፡- የተማሪ መምህር ጥምርታን 1-4 1፡50 ና 5-8 1 ለ 45 ማድረስ፣

4.1 በት/ቤቶች የሌሉ መማሪያ፣ማስተማሪያ መፅሀፍትና መርሀ ስርዓት ትምህርቶችን ማሟላት

ተግባር 5 ፡- የተማሪዎችን የማንበብ ልምድ በማዳበር ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ፣

5.1 ከ 1—4 የመማሪያ ክፍል ደረጃ ሞባይል ቤተ-መፅሀፍት ማዘጋጀት

5.2 ከ 1-4 ት/ቤት ንባብ ቤቶችን ማዘጋጀት

5.3 ከ 5—8 ና ከ 9—10 ቤተ-መፅሀፍት 100% እንዲኖራቸው ማድረግ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 19


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 6 ፡- ትምህርት ቤቶች ቤተ-ሙከራ (ከ 5—8)፣አይሲቲ ማዕከል(ከ 9—10)ና በ 10 (ከ 5—8) ት/ቤቶች ፣የመጠጥ
ውሀ፣የሁለቱም ፆታ መፀዳጃ ቤት፣የትም/ማበልፀጊያ ማዕከላት(በሁሉም)፣የስፖርት ሜዳዎች(በሁሉም) 100% ያላቸው
እንዲሆኑ ማድረግ
ተግባር 7፡- ሁሉም ተማሪዎች 100% ደረጃቸውን በጠበቁ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ዴስክ መቀመጥና መማር
መቻላቸውን ማረጋገጥ፣
ግብ አስራ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ የትም/ት ተቋማት ግንባታን ጥያቄ ከየቀበሌዎች በቀረበው
መሠረት ተለይቶ አመች ሁኔታ መፍጠር፡፡
ተግባር 1፡- የተፈቀደ በጀት መኖሩን
በማረጋገጥ የተገኘውን መረጃ በማጠናከር የግንባታና የግዥ ዕቅድ በማዘጋጀት በዕቅድ ላይ ውይይት ማድረግ፣
ተግባር 2፡- ከወረዳ እስከ ት/ቤት ድረስ ከውይይቱ በተገኘው ግብዓት ዕቅዱን በማሻሻልና በማፅደቅ የዕቅድ መከታተያ ቸክሊስት
በማዘጋጀት በየ 15 ቀኑ ክትትል ማድረግ፣
ግብ አስራ ሰባት
ሁሉም የተገነቡት የትም/ት ተቋማት በበቂ መጠንና ጥራታቸውን የጠበቁ በስታንዳርዱ መሠረት የክፍል
ተማሪ ጥምርታ እንዲኖር በማድረግ የደንበኞችን እርካታ መጨመር፡፡

ተግባር 1፡- የትም/ት ተቋማትን ለመገንባት የተዘጋጀውን የህንፃ ዲዛይንና የስራ ዝርዝር በባለሙያዎች ቡድን እንዲታይና
እንዲረጋገጥ ክትትል ማድረግ፣
ተግባር 2፡- የተሰጠውን ማረጋገጫ መሠረት በማድረግ በስራ ሂደቱ የበላይነት በማፅደቅ የግዥ ዘዴውን በመለየት ግዥ
እንዲፈፀም የጨረታውን ሰነድና ማስታወቂያ በማዘጋጀት የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣት፣የጨረታ ሰነድ አባዝቶ ለመሸጥ
በሰነዱ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ማመቻቸት፣(ከወረዳው ገ/ፕ/ልማት ትብብር ጽ/ቤት ጋር)
ተግባር 3፡- የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ማሸግ፣እንዲሁም በወቅቱ በተያዘለት ፕሮግራም ሳጥኑን በመክፈት የተጫራጨቾችን
ዋጋ በንባብ ማሰማትና የጨረታ ማስከበሪያ በመረከብ የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ በማዘጋጀት የቴክኒክ ግምገማ
ማከናወን፣የጨረታውን ውጤት ማሳወቅና ሰነድ በማዘጋጀት እንዲፈፀም የውል ማስከበሪያ በመረከብ ስራን የመፈፀም ብቃት
መፍጠር፣(ከወረዳው ገ/ፕ/ልማት ትብብር ጽ/ቤት ጋር)

ተግባር 4፡- የሚገነቡት ተቋማት ደረጃቸውንና ጥራታቸውን እንዲጠብቁ የተሟላ ቤተ-መፅሀፍ፣ቤተ-ሙከራ፣መፀዳጃ


ቤቶች፣የስፖርት ሜዳ ወ.ዘ.ተ ያላቸው እንዲሆኑና የአካል ጉዳተኞችን ችግር ያገናዘቡ እንዲሆኑ ጥረት ማድረግ፣

ተግባር 5፡- የሚገነቡት ተቋማት ስርጭት ፍትሀዊ እንዲሆኑ የተቋማቱ ግንባታ በወቅቱ ተጠናቆ ለተፈለገው የትም/ት መስጫ
አገልግሎት እንዲውል ማድረግ፣

ግብ አስራ ስምንት
በወረዳችን በሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን የጠበቁ የት/ት መሳሪያዎችን ማቅረብ

ተግባር 1፡- የት/ት መሳሪያዎችን አቅርቦት አስመልክቶ ረቂቅ ስታንዳርድና የመረጃ መሰብሰቢያ

ፎርማት በማዘጋጀት መረጃውን በመሰብሰብ በማጠናከርና የመነሻ ሃሳብ በማዘጋጀት

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 20


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ
በሃሳቡ ላይ በስራ ሂደቱ ውይይት በማድረግ ማፅደቅና ስታንዳርድ ማዘጋጀት፣

ተግባር 2፡- በተዘጋጀው ረቂቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የተፈጥሮ ሳይንስ፣

የሂሳብ፣የህብረሰተብ ሳይንስ፣የሰ.ማ.ጎ የትም/መሳሪያዎች በየዓይነቱ በየትም/ት

ሳብጀክቱ የስራ ዝርዝር አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባት፣

ተግባር 3፡- በማንኛውም መንገድ ማለትም በግዥ ወይም በዕርዳታ የሚገኙ የት/ት

መሳሪያዎችን በፍትሃዊነት በወቅቱ በየተቋማቱ እንዲደርስ ማድረግ፣

ግብ አስራ ዘጠኝ
በወረዳችን ባሉ የት/ት ተቋማት ወቅቱን የጠበቀ የት/ት መሳሪያዎች ጥገናና ዕድሳት ጥያቄ ወቅታዊ
ምላሽ እንዲያገኝ ማድረግ፡፡
ተግባር 1፡- ጉዳት የደረሰባቸውን ህንፃዎች በየአካባቢው የጉዳት መጠናቸው ምን እንደሆነ

ተለይተው ተጠግነው አገልግሎት ላይ እንዲዉሉ ማድረግ፣

ተግባር 2፡- በየት/ት ተቋማቱ የት/ት መሳሪያዎችን ጥገና ፍላጎት በማሰባሰብ በተቋሙ መጠገን

የሚችልና የማይችለውን በመለየት በትም/ት ልማት ሰራዊት /ልማት ቡድን/ በማስጠገን አገልግሎት ላይ እንዲውል ማስቻል፣

ተግባር 3፡- ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡትን የት/ት መሳሪያዎች በአሰራሩ መሰረት

እንዲወገዱ ማድረግ፣

ግብ ሀያ
የክፍል፣የጉድኝነትና የወረዳ እንዲሁም የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ትንተና ለተማሪዎች ውጤት ማሻሻያነት
በግብዓትነት የመጠቀም የአሰራር ስርዓት ተጠናክሮ ተግባር ላይ እንዲውል ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- በትምህርት ዘመኑ ከመጀመሪያ ደረጃ 1 ኛ ሳይክልና 1 ኛ ደረጃ 2 ኛ ሳይክል እና ከዚያም ዝቅተኛ
የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ በ 10 ጥሬ ማርክ መነሻ ማሻሻል፣
ተግባር 2፡- ሁሉም ት/ቤቶች በ 2010 ዓ.ም የፈተና ውጤታቸው በመተንተን ችግር ያሉባቸው የትምህርት
አይነቶች ልዩ ዕቅድ አዘጋጅቶ መተግበር መምህራን የሚያስተምሩት የትምህርት አይነት ዓመታዊ
የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ግብ አቅደው እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ፣
ተግባር 3፡- ት/ቤቶች በትምህርት መሻሻያ ዕቅዳቸው መሰረት የ 2010 ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና በመነሳት ዓመታዊ የተማሪዎች ውጤት የማሻሻያ
ግብ ላይ የጋራ ስምምነት ማድረግ፣በግቡ ስኬትና መንስኤዎች ላይ ወርሀዊ ውይይት ማድረግ፣
3.1 የፈተና ውጤቶችን በመተንተንና ችግር ላለባቸው የት/አይነቶች ልዩ እቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ
3.2 ት/ቤቱ በጣለው የተማሪዎች ውጤት ማሻሻያ ግብ ለተማሪዎችንም ማወያየትና ተማሪዎችም የራሳቸውን ግብ እንዲጥሉ ማድረግ
3.3 ስለውጤቱ መሻሻል ተከታታይነት ያለው ወርሀዊ ውይይት ማካሄድ
ተግባር 4 ፡- የ 4 ኛ፣የ 8 ኛና 10 ኛ ክፍል ውጤት ትንተና በማድረግ ከተገኘው ውጤት አንፃር ለውጤታማነቱ
የእቅድ መነሻ ሀሳብ እንዲሆን ማስቻል፣
4.1 የ 8 ኛ ክፍልና የ 10 ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ትንተና በማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ
ተግባር 5 ፡- የ 4 ኛ ከፍል የንባብ ብቃት መለኪያ በጉድኝት ደረጃ ማዘጋጀትና ፈተና ማካሄድ፣
4. የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት መርሃ-ግብር
ግብ ሃያ አንድ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 21


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

የስነ--ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ከምንግዜውም በላይ በተሻለ ሁኔታ የሚሰጥበትን ስርዓት


አጠናክሮ በመቀጠል የሀገራችን ማህበራዊ እሴቶች በትምህርት ቤት ውስጥና ውጭ ማስረፅ፡፡

ተግባር 1፡- ትምህርቱ ከት/ቤቶች ግቢ ውጭ ለህብረተሰቡ የሚሰጥበትን ስልት ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ፣
 ትምህርቱን ወደውጭ ለማውጣት የሚያስችል ስልት በመቀየስና ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ
 በት/ቤት ደረጃ ተግባራዊ የሆኑና ተግባራዊ ያልሆኑ እሴቶችን ለይቶ መያዝና ተግባራዊ ያልተደረጉ
እሴቶችን ተግባራዊ ማድረግ
ተግባር 2 ፡- ከት/ቤት ውጭ ያሉ ልዩ ልዩ ባለሙያዎችን በት/ቤት ተገኝተው ትምህርትን የማጠናከር ተግባር እንዲያበረክቱ
ማድረግ፣
ተግባር 3 ፡- ትምህርቱ በሁሉም የወረዳው ት/ቤቶች (ከ 5—10 ኛ) ክፍል ውስጥ በተሻሻለው አዲስ ስርዓተ ትምህርትና
በሰለጠኑ መምህራን መሰጠቱን ማረጋገጥ፣
ተግባር 4 ፡- ከ 1 ኛ-4 ኛ ክፍል ለሚያስተምሩ መምህራን ተገቢና ተከታታይ ስልጠና መስጠት፣ ትምህርቱን የሚያስተምሩ
መምህራን ከአካባቢ ሳይንስ ት/ት በተለይም ደግሞ የስነ-ምግባር እሴቶችንችን ለይተው ምን ያህል
እንሚያስረዱ በየወሩ በክፍልና በሳይክል ደረጃ እንዲወያዩ ማድረግ፣

ግብ ሀያ ሁለት

ትምህርቱን በይበልጥ ለማስረፅ ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራትን አጠናክሮ ተማሪዎች ላይ በመስራት


የትምህርት አሰጣጥን በማጠንከርና በበቂ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ክፍል በመመሪያው መሰረት ማቋቋም፣

ተግባር 2፡- የት/ቤቱን ተማሪዎችና መምህራን በእሴቶች አካባቢያዊ አተገባበር ችግር ዙሪያ የተደራጀ ልዩ ልዩ መድረኮችን ፈጥሮ ውይይት
በማድረግ ግንዘቤ መፍጠር፣

ተግባር 3 ፡- ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በመመሪያዉ መሰረት ከየድርሻው በተጨማሪ የጋራ ፎረም በመፍጠር በዓመቱ በአጠቃላይ በት/ቤታቸው
ልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ አራት ጊዜ መክረው ለችግሮች መፍትሄ ማስቀመጥ፣

ተግባር 4፡- የስነ-ምግባር መኮነኖች ክበብ በየት/ቤቱ በመመሪያው መሰረት ተቋቁሞ ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ማድረግ፣

ተግባር 5፡- የተማሪዎች ካውንስል ፓርላማ ም/ቤት የምርጫ ሂደቶችን ተከትሎ እንዲመረጡ በማድረግ ተግባራዊ ልምምድ ማድረግ፣

ግብ ሀያ ሶስት
የተጠናከሩ የክፍል ውስጥ የክበባትና የአደረጃጀት ስርዓቶች ተከታታይነት ባለው መልኩ መዘርጋትና ተግባር
ላይ በማዋል የተማሪዎችን ዲሲሰፕሊን ማሻሻል፡፡

ተግባር 1፡- በየሴክሽኑና ት/ቤት ደረጃ አሳታፊ በሆነ መንገድ የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ በወቅቱ ወጥቶ ተግባራዊ ማድረግ፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 22


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

-ሁሉም ሴክሽኖች መተዳደሪያ ደንብ አውጥተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ማድረግ

ተግባር 2፡- የልዩ ልዩ የተማሪዎች አደረጃጀቶችን ባረጋገጠ መልኩ የአለቆች ህብረት፣የጎበዝ ተማሪዎች ህብረት፣የተማሪዎች ካውንስል፣የሴት
ተማሪዎች አማካሪ ኮሚቴ ወ.ዘ.ተ በወቅቱ በአግባቡ ማደራጀት፣

ተግባር 3፡- የት/ቤቱ ተማሪዎች ከሀገሪቱ ራዕይ በመነሳት የወደ ፊት ራዕያቸውን እንዲለዩ መዝግቦ በራዕያቸው ላይ የተደራጀ ውይይት
እንዲያደርጉና የባለሙያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲያገኙ ማድረግ፣

1.1 ተማሪዎች ራዕያቸውን እንዲለዩ ማድረግ


1.2 ተማሪዎች በራዕያቸው ዙሪያ ውይይት እንዲያደርጉ ማገዝ፣ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

ተግባር 4፡- ልዩ ልዩ በሆኑ ብሔራዊ ዓለም አቀፍ የበዓል ቀናት / የባንዴራ ቀን፤አድዋ ድል፣የሰማዕታት ቀን፣የፀረ-ሙስና ቀን፣የኤች አይቪ
ቀን፣የሴቶች ቀን፣የግንቦት 20፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ከእሴቶች ጋር በማያያዝ የት/ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን ከልዩ ልዩ
ከግብዓት ጋር በቅንጅት የፓናል ውይይት በማድረግ ትምህርቱን የበለጠ የማስረፅ ስራ መስራት፣

ተግባር 5፡- የፌድራሉና የክልል ህገ-መንግስትና ሌሎች ወሳኝ የሆኑ ድንጋጊዎችንና ተጨማሪ ልዩ ልዩ ፅሑፎችን በት/ቤቶች እንዲሟሉ
በማድረግ እሴቶችን በሚሞሪ፣በበራሪ ፁሑፎች፣ፓስተሮችና ልዩ ልዩ ህትመቶችን ማሰራጨትና እንዲሰርፅ ማድረግ፣

ግብ ሀያ አራት
በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሰንደቅ ዓላማና መዝሙር ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከበር በማድረግ የተማሪዎችን የሀገር ፍቅር
ስሜት ማጎልበት፡፡

ተግባር 1፡- የሰንደቅ ዓላማ መዝሙርን ለዜጎችም ሆነ ለሀገር ያለውን ትርጉም በስነ- ስርዓት ላይ ከዜጎች ስለሚጠበቅ ስነ-ስርዓት ለተማሪዎች
የማስተዋወቅ ስራ መስራት፣

ተግባር 2፡- ሁሉም የወረዳው ት/ቤቶች ስታንዳርዱን የጠበቁ ሁለቱን ባንዴራዎች እንዲያውለበለቡ ማድረግ፣

ተግባር 3፡- መምህራን የሰንደቅ ዓላማም ሆነ የመዝሙር ስነ-ስርዓትን እንዲማሩት ማድረግ፣

ተግባር 4፡- የሰንደቅ ዓላማ ስርዓቱ በሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተገቢው መንገድ እንዲፈፀም የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ክበብና ት/ቤቱ
ከየወረዳቸው፣ቀበሌ አፈ-ጉባኤዎች ጋር በማቀናጀት ተግባራዊ ማድረግ፣

ተግባር 5፡- የሰንደቅ ዓላማ ቀንን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ማክበር፣

ግብ ሀያ አምስት
ተማሪዎች በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጭ በንድፈ ሀሰብ የቀሰሟቸውን እሴቶች የተላበሱ መሆኑን የሚያረግጡባቸው
ተግባራዊ ስራዎች በማከናወን ተጨባጭ ውጤታማ ለውጥ ማሳየት፡፡

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 23


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 1፡- እሴቶች ት/ቤት ባሉበት ደረጃና አካባቢያዊ ሁኔታ ከህ/ሰብ ባህል፤ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች አንፃር ወዘተ በመነሳት
ተማሪዎች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ ስራዎችን ተግባራት ለይቶ ማቀድ፤ የአሰራርና ስምሪት አፈፃፀም ስርዓት መዘርጋት፤ ባደረጉት ተግባራዊ
እንቅስቃሴ ግምገማና ውይይት እንዲያደርጉ ማድረግ፣

ተግባር 2፡- ተማሪዎች በተግባር የተሳተፉባቸውን ስራዎች እንደየስሜታቸው በመለየት ተሞክሮ እንዲለዋወጡ፣ ከውጤቱም ምን እንደተገኘ
በጋራ እንዲመከሩ ማድረግ፣ በግልና በቤተሰብ የዕለት ተዕለት ኑሮ መተግበር የሚገባቸውን ለይተው ወደ ተግባር እንዲገቡ
የማነሳሳት ስራ መስራት፣

ተግባር 3፡- የሀገሪቱን ራዕይና እሴቶች ከት/ቤቶች ግቢ ውስጥ በጉልህ ቦታ ተፅፈው የት/ቤቱ ማህበረሰብ ሲወጡና ሲገቡ እያዩ የበለጠ
እንዳይረሷቸው ማድረግ፣

ተግባር 4፡- የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህራን በዘመኑ ውስጥ አራት ጊዜ /በየሩብ ዓመቱ /በመገኘት በ 2010 ዓ.ም ትምህርት ዘመን መጨረሻ
ያደርጉትን ምክክር ውሳኔ መነሻ በማድረግ ልምድ በመለዋወጥ ትምህርቱን ማጠናከር፣

ተግባር 5፡- የመምህራን ህብረትን አጠናክሮ በማቋቋም በትምህርት ይዘቶች፣በክበብ እንቅስቃሴዎች ከት/ቤት ውጭ እሴቶን ከማስረፅ አኳያ
በተማሪዎች ዲሲፒሊን ችግሮች አጠቃላይ በመማር-ማስተማሩ በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ ተከታታይ ምክክር ማድረግ፣

ተግባር 6፡- በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የቀስሟቸውን እሴቶች ከት/ቤት ውጭ በማህበረሰብ ውስጥ ተግባራዊ
በሚደረግባቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ውስጥ ማሰማራት፣

ተግባር 7፡- በወረዳው የትምህርት ተቋማት ውስጥ እሴቶችን በይበልጥ ለማስረፅ የሚያስችሉ ተጓዳኝ ተግባራትን በተጠናከረ መልኩ ተግባር
ላይ ማዋል፣

ተግባር 8፡- የህፃናት ፓርላማ ስርዓትን በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተግባራዊ ማድረግና እሴቶችን በተሻለ መልኩ ማስረፅ፣

ተግባር 9፡- የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ባለፉት ዓመታት ያመጣውን ለውጥ ዳሰሳ በማካሄድ ለቀጣይ ማሻሻያነት እንደ ግብዓት
መጠቀም፣

5 .የስርዓተ-ትምሀርት ማሻሻያ መርሃ-ግብር


ግብ ሀያ ስድስት
የስርዓተ ትምህርቱን ትግበራ ለመደገፍ መካተት የሚገባቸውን ወሳኝ ተጓዳኝ ተግባራት በየትምህርት ቤቱ
ማስፈፀም፡፡

ተግባር 1፡- ከት/ቤት መሻሻል ማዕቀፍ ውስጥ ትኩረት የተሰጣቸው ሁለገብ ጉዳዮች አካባቢ እንክብካቤ፣ስርዓተ ፆታ፣ኤች አይ ቪ
ኤድስ፣ሀይጅንና ሳንቴሽንን ማስተግበሪያ አቅጣጫ ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ፣

ተግባር 2፡- በየደረጃው ያለ የትምህርት ዘርፍም ሆነ ህብረተሰብና የትምህርት ባለድርሻዎች ስርዓተ ትምህርቱ የሚገመገምበት፣ግብረ-መልስ
የሚሰጥበት ቋሚ ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድርግ፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 24


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ተግባር 3 ፡- ተጨማሪ የንባብና የፅህፈት ክህሎት ማስተማሪያ የተማሪዎች ተግባር ተኮር ፣የቤተ-ሙከራ ማንዋሎች ተባዝተው ለአዲስና
ለሌሎች ት/ቤቶች ማሰራጨት እንዲሁም በየደረጃው ባሉ በሁሉም ጉዳዮች (any matter) አማካኝነት የሱፐር
ቪዢን ድጋፍ ማድረግ፣

ተግባር 4 ፡- በክፍል ውስጥ እስከ ወረዳ ያሉ ልዩ ልዩ የተማሪዎች አደረጃጀትና የአሰራር ስርዓቶችን በተጠናከረ
የተቀናጀና ተከታታይነት ባለው መልኩ አደራጅቶና የአሰራር ስረዓቶችን በማጠናከር ወደ ስራ በማስገባት
የወረዳውን ተማሪዎች ስነ-ምግባር ማሻሻል፣

 ግብ ሃያ ሰባት

በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣውን የስርዓተ ትምህርት መነሻ በማድረግ ክልላዊ ስትራቴዎች
ተዘጋጅተው በዝግጅትና ትግበራ ሂደት በስኬታማነት መፈፀም፡፡

ተግባር 1፡- በአዲሱ የመሰረታዊ የክልሉ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት ለመማሪያና ማስተማሪያ መፅሀፍት
ስርጭት በዝርዝር በማቀድ ተግባራዊ ማድረግ፣ለት/ቤቶች መፅሀፍት ስርጭት ብዛት በአይነትና በክፍል
ደረጃ ለይቶ ማቀድ፣

ተግባር 2 ፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁትን የተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ትም/ት መምሪያ ማስተማሪያ ማሳወቅ፣

ተግባር 3፡- በሀገር አቀፍ ደረጃ ተዘጋጅተውና ታትመው የሚሰራጩትን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ
ማስተማሪያ መፅሀፍትን ለሁሉም የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች በነፃ መታደላቸውን ማረጋገጥ፣

ተግባር 4፡- ተግባር-ተኮር የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ስርዓት ትምህርት ማተሪያሎች / መርሀ ትምህርት
የአመቻቾች ማንዋልና የተሳታፊዎችን የተግባር መልመጃዎች መፅሐፍ ማሰራጨት፣

ተግባር 5፡- የቅድመ-መደበኛ ትምህርት የማስተማሪያ መፅሐፍት/ደረጃ አንድ፣ሁለትና ሶስት/ማሰራጨት፣

ግብ ሃያ ስምንት
የክልሉን የአጠቃላይ ትምህርት አፈፃፀም በቀጣይነት እያሻሻሉ ለመሄድ እንዲቻል የትምህርት
ጥናትና ምርምር ባህልን አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- መምህራን በት/ቤት ደረጃ በሰለጠኑበት የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መሰረት በተለያዩ ችግሮች ላይ ተግባራዊ
ጥናትና ምርምር እንዲያካሂዱ ማድረግ ውጤቱን በትምህርት ቤት ጉባኤ ቀርቦ የፓናል ውይይት
ማካሄድ፣ምርጦችን እስከ ክልል ማቅረብና መፍትሔዎችን ለችግር መፍቻነት መጠቀም፣

ተግባር 2፡- አዲስ የተሸሻለውን ስርዓተ ትምህርት ትግበራ አሳታፊ በሆነ ሂደት መገምገምና የማሻሻያ ግብዓቶችን
ማሰባሰብ፣

ተግባር 3፡- ከተቋማት እስከ ወረዳ ባሉ የትምህርት ባለሙያዎች በሴቶች ትምህርት ተሳትፎ ዙሪያ የጉድኝት
ማዕከላት በትምህርት ስራ ያለውን አስተዋፅኦ በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ዙሪያ በትምህርት ውስጣዊ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 25


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ብቃት ዙሪያ በሳይንስና ሂሳብ አሰጣጥ ዙሪያና በተከታታይ ምዘናና ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ
ዙሪያ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣

ግብ ሃያ ዘጠኝ

የስርዓተ ትምህርትን ለማሻሻልና ለማጎልበት የሚያስችሉ ምዘናና


ተግባርን በውጤታማነት መፈፀም፡፡

ተግባር 1፡- የመጀመሪ ደረጃ ትምህርት ማጠናከሪያ ትምህርት፣የመጀመሪያ ትምህርት ማጠናከሪያ ፈተና፣የተማሪዎች
ምዝገባ፣የፈተና ህትመት ስርጭት፣የፈተና አስተዳደርና ውጤትን ማሳወቅ፣

1.1. በ 2010 ዓ.ም በትም/ቤቶች የተፈታኞች ብዛትን መለየትና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግና
በጀት መያዙን ማረጋገጥ

ተግባር 2፡- የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ትምህርት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና የተማሪዎች
ምዘገባ የፈተና ህትመት፣ስርጭት የፈተና አስተዳደርና ውጤትን ማሳወቅ

1.1. በ 2010 የትም/ቤቶች የተፈታኞች ብዛት መለየትና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ

ተግባር 3፡- በተከታታይ ምዘና ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ ክትትል በማድረግና አፈፃፀሙን በማየት ቀጣይ የመፍትሔ
አቅጣጫ ማስቀመጥ፣

2.1. ክትትል ማድረግና አፈፃፀሙን በማየትና የመፍትሔ አቅጣጫ አስቀምጠው ተግባራዊ ማድረግ፣

ተግባር 4፡- የቀለም ትምህርትና የስፖርት ውድድር የሚካሄድበትን አግባብ ማስቀመጥና መተግበር፣

-የቀለም ትምህርት ውድድር ፕሮግራም በማውጣት በተከታታይነት ተግባራዊ ማድረግ

-የስፖርት ውድድር ፕሮግራም /ከሴክሽን፣ከክፍል ክፍል/ በማውጣጣት በተከታታይ ተግባራዊ ማድረግ

-የስፖርት ውድድር ፕሮግራም /በጉድኝት፣ከት/ቤት ት/ቤትና በወረዳ/በማውጣት በተከታታይ ተግባራዊ ማድረግ

ተግባር 5፡- በክልል አቀፍ ፈተናዎች አስተዳደር ላይ የተከሰቱ ችግሮች ተለይተው በ 2010 ዓ.ም እንዳይከሰት
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄድ፣
ተግባር 6፡- የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ለሚጠይቁ ተገልጋዮች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት፣
1.1. በድጋሜ ካርድ የተሰጣቸውን ተገልጋዮች ብዛት ለይቶ መያዝ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 26


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

6. የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ አገልግሎትን


የማስፋፋት መርሃ-ግብር
ግብ ሰላሳ
የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት የማስፋፋት ፕሮግራምን ተቋማዊ የሆነ
አሰራር ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፡፡

ተግባር 1፡- በወረዳው ውስጥ የሚገኙ 1 ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክልና በ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዋና ዋና ግብዓቶች
እንዲሟሉና እንዲደራጁ በማድረግ የመማር-ማስተማርና ስልጠና ሂደቱን በተጠናከረ መልኩ መደገፍ፣

ግብ ሰላሳ አንድ
አዲስ በተሸሻለው መደበኛና መደበኛ ያልሆውን ትምህርት በመደገፍ የትምህርት ጥራትን
ማስጠበቅ፡፡

ተግባር 1፡- የሬዲዮ ስርጭት ለማይደርስባቸው ት/ቤቶች ሚሞሪ አስጭነዉ ት/ቤቶች እንዲጠቀሙ ማድረግ፣
ተግባር 2፡- የት/ቤት ሚኒ-ሚዲያ ክበባትን ለማጠናከር ለ 124 መምህራንና ተማሪዎች በሚኒ-ሚዲያ አጠቃቀም ላይ
ስልጠና መስጠት፣
ተግባር 3፡- የሬዲዮ ፕሮግራም የጊዜ ሰሌዳ ተዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፣
አብይ ተግባር
የትምህርት ሽፋንን ማሳደግ 25%
ግብ አንድ
በወረዳው ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት በሙሉ ትምህርት ቤት ገብተው
እንዲማሩ ማስቻል፡፡
ተግባር አንድ
 በወረዳው እድሜያቸው ሰባት ዓመት የሞላቸው ሁሉም ህፃናት ትምህርት ቤት የሚገቡበት ቅድመ ሁኔታዎችን
ማመቻቸት፣
 ወ 2344 ሴ 2086 ድ 4430 ተማሪዎች እድሜያቸው ሰባት ዓመት የሞላቸውን መቀበልና የአንደኛ ክፍል ጥቅል
ቅበላን ወ 2691 ሴ 2308 ድ 4999 ማድረስ
 የአንደኛ ደረጃ ጥቅል የትምህርት ሽፋንን ወ 14448 ሴ 14923 ድ 29371 ማድረስ
 በሁለቱ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችን የትምህርት ሽፋንን ወ 719 ሴ 995 ድ 1714 ማድረስ
 በ 4 የአፀደ-ህፃናት ተቋም የትምህርት ሽፋንን ወ 306 ሴ 275 ድ 581 ማድረስ
 የልዩ ፍላጎት ትምህርት ተሳትፎ ሽፋንን በማሻሻል ወ 93 ሴ 81 ድ 174 ተማሪዎችን ማስተናገድ
 የ 2010 ዓ.ም ህብረተሰብ አቀፍ የቅድመ-መደበኛ የት/ት ተሳትፎን ወ 2891 ሴ 2757 ድ 5648 ማድረስ
 የ 2010 ዓ.ም የቅድመ-መደበኛ የት/ት ተሳትፎን ወ 3197 ሴ 3032 ድ 6229 ማድረስ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 27


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 በመሰናዶ ት/ቤቶች ወ 98 ሴ 152 ድ 250 ማድረስ

ተግባር ሁለት
በየደረጃው የሚሰጠውን የትምህርት አቅርቦትና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ግብዓቶች እንዲሟሉ ማድረግ፡፡
ለዚህም የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ፡፡

 በ 19 ት/ቤቶች ተጨማሪ መማሪያ ክፍሎችን መገንባት፣በ 28 ት/ቤቶች 84 መማሪያ ክፍሎች ጥገና፣8 ት/ቤቶች ፈፅሞ
የተጎዱትን 16 ክፍሎች አፍርሶ የመገንባት ስራ ማካሄድ
 በወረዳ ደረጃ 4 የልዩ ፍላጎት ዩኒት ማዕከል መገንባት
 በዚሁ የት/ት ዘመን በሁሉም የክፍል ደረጃዎችና የትምህርት አይነቶች የመማሪያ መፃህፍትን ለሁሉም ተማሪዎች
በነፍስ ወከፍ ማዳረስ
 በወረዳው ለተማሪዎች በቀመር የሚመደበውን የ 2010 ዓ.ም መደበኛ በጀት ክትትል በማድረግ ተገቢ የማሻሻያ ሀሳብ
በማቅረብ ግብረ-መልስ ለሚመለከታቸው አካላት መስጠት
 ከህብረተሰቡ፣ከረድዔት ሰጭ ድርጅቶችና ከአካባቢው ተወላጆች ወዘተ ሀብትን በማሰባሰብ ወደ አንድ ቋት
ማስገባትና ይህን ከተለያዩ ምንጮች የተገኘን ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ድልድል መፈፀም
ተግባር ሶስት

 የአካቶ ትምህርትን በየደረጃው በመስጠት የትምህርት አቅርቦትን ማስፋፋት፣


ተግባር አራት

 በወረዳው የአካቶ ት/ት ባሉት ት/ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች ጥናት በማካሄድ ፕሮጀክት በማዘጋጀት የሃብት
ማፈላለግ ማመንጨት ተግባር መፈፀም፣
ግብ ሁለት
መሠረታዊ የጎልማሶች ትምህርት በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ፕሮግራሙን
ማጠናከር፡፡

ተግባር አንድ
 መሠረታዊ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም በሁሉም የወረዳው ቀበሌዎች በመጀመር የጎልማሳውን አቅም
ማጠንከር፣
 ወ 1861 ሴ 1433 ድ 3294 አዲስና ወ 2495 ሴ 1937 ድ 4432 ነባር በጠቅላላው ወ 4356 ሴ 3370 ድ 7726
ጎልማሶችን መመዝገብ
 በ 135 ጣቢያዎችና በ 135 አመቻቾች ትምህርቱን መስጠት(በሁሉም ቀበሌዎች)፡፡ይህን የሚያስተባብሩ 2
ባለሙያዎችም ተቀጥረዋል፡፡
ተግባር ሁለት
 ወረዳዊ የተቀናጀ ተግባር-ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ፕሮግራሙን በሁሉም ቀበሌዎች
ተጠናክሮ መስጠት መጀመር፣
ተግባር ሶስት

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 28


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ወረዳዊ የህዝብ ንቅናቄ ሰነድ በማዘጋጀትና ከወረዳ እስከ ቀበሌ በማስተዋወቅ ግንዛቤ

መፍጠር፣
ተግባር አራት
 ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የማይችሉ ወጣቶችና ጎልማሶችን መረጃ በየደረጃው አጠናቅሮ
መያዝና ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ፣
ግብ ሶስት
የትምህርት ፍትሀዊነትን ማስጠበቅ፡፡

ተግባር አንድ፡-
o ስርዓተ-ፆታን በትምህርት ስራ ውስጥ ማካተት
በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ፕሮግራሞች የስነ-ፆታዊ ክፍተትን/Gender Disparity/ የሚያጠቡ ተግባራትን መፈፀም፡፡
ለዚህም ለ 2010 ዓ.ም የሴቶችን የት/ት ተሳትፎ ለማጎልበት 14923 ለማድረስ ዕቅድ ተይዟል፡፡
 ህ/ሰቡ ስለሴት ልጅ ያለውን አስተሳሰብ ስለ ሴቶች ትምህርት አስፈላጊነትና ችግሮች የግንዛቤ ማጎልበቻ በተለያዩ
መድረኮች መፍጠር
 በት/ቤት ዙሪያ የሚገኙ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ያለ እድሜ ጋብቻንና ጠለፋን ለማስቀረት ጥረት ማድረግ
 በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች ማበረታቻ ማለትም የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ
የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር
 በየት/ቤቶች የሴት ተማሪዎች የተጨማሪ ትምህርት ድጋፍ ማድረግ
ተግባር ሁለት
 በከተሞችና በገጠር መካከል ያለውን የትምህርት አቅርቦት ልዩነት/urban-Rural inequity/ ለማጥበብ በገጠርና
በኋላቀር አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት በተጠናና በተጠናከረ ሁኔታ ማስፋፋት፣
ተግባር ሶስት
 ዝቅተኛ የተማሪ ተሳትፎ ባላቸው ቀበሌዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተሳትፎን የሚያጎለብቱ የተለያዩ
ተግባራትን መፈፀም፣
 የሳተላይት ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት መክፈትና የት/ት ዕድል ያላገኙትን ዕንዲያገኙ ማድረግ
 እንደ አከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ማህበረሰብ አቀፍ አፀደ-ህፃናት ተቋም ማቋቋም
ግብ አራት
የትምህርት ብቃትን ማሻሻል፡፡
ተግባር አንድ
 በ 2010 ዓ.ም በጀት ዓመት በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች የመማሪያ ሴክሽን ተማሪ ጥምርታ በስታንዳርዱ መሠረት
ማድረግ፣
ተግባር ሁለት
 በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን መድገምና ማቋረጥ ምጣኔን የሚያሻሽሉ ተግባራትን
በውጤታማነት መፈፀም፣
 የመድገም ምጣኔን 2% በታች ማድረስ
 የማቋረጥ ምጣኔን ከ 2% በታች ማድረስ
 የየእርከኑን ማጠናቀቂያ ምጣኔ ማሻሻል

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 29


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

ግብ አምስት
በወረዳችን በሚገኙ በሁሉም ት/ቤቶች ደረጃቸውንና ጥራታቸውን የጠበቁ
የትም/መሳሪያዎች ማቅረብ፡፡
ተግባር አንድ
 የትም/መሳሪያዎች አቅርቦትን አስመልክቶ ረቂቅ ስታንዳርድና የመረጃ መሠብሠቢያ ፎርማት በማዘጋጀት መረጃውን
በመሰብሰብ፣በማጠናከርና የመነሻ ሀሳብ በማዘጋጀት በሀሳቡ ላይ በስራ ሂደቱ ውይይት በማድረግ ማፅደቅና ስታንዳርድ
ማዘጋጀት፣
ተግባር ሁለት
 በተዘጋጀው ረቂቅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የተፈጥሮ ሳይንስ፣የሂሳብ፣የህብረተሰብ ሳይንስ፣የሰ.ማ.ጎ
የትም/መሳሪያዎችን በየዓይነቱ በየትም/ት ሳብጀክቱ የስራ ዝርዝር አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባት፣
ተግባር ሶስት
 በማንኛውም መንገድ ማለትም በግዥ ወይም በዕርዳታ የሚገኙ የትም/መሳሪያዎችን በፍትሀዊነት በወቅቱ በየተቋማቱ
እንዲደርስ ማድረግ፣

ንዑስ ተግባር፡-የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም (5%)


ግብ አንድ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራምን በትምህርት ተቋማት አጠናክሮ ተግባራዊ
ማድረግ፡፡
ዓላማ፡- የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራምን በመተግበር ውጤታማ አሰራሮችን መፍጠር ነው፡፡
የሚከናወኑ ተግባራት
- ተቋማት ራዕይና ተልዕኳቸውን በግልፅ እንዲያሳውቁ ማድረግ
- የአግልግሎት አሰጣጥን በት/ት ተቋማት ማሻሻል
- አቅጣጫ ጠቋሚ እንዲኖር ማድረግ
- ሰራተኞች የደረት ባጅ መጠቀምና መምህራን ጋዎን እንዲለብሱ ማስተባበር
- የማስተነጋጃ ሰዓት ለይቶ ማስቀመጥ
- ለአግልግሎቱ ሰዓት መጥኖ በማስቀመጥ አግልጋሎት መስጠት
- የውጭ አስተዳደርን በተመለከተ ት/ቤቶች የፋይናንስ አሰራራቸውን በባንክ አካውንት እንዲጠቀሙ ማድረግ
- ትም/ቤቶች የግዢ ስርዓት፣ደንብና መመርያውን ተከትለው እንዲገዙ ማድረግ
- የውጤት ተኮር እቅድ ሁሉም ት/ቤቶች እንዲያዘጋጁ ማድረግ
- ውል የወሰዱና ያልወሰዱ መምህራን እና ሰራተኞችን መረጃ በተገቢው ሁኔታ በመያዝ እንዲያሟሉ ማድረግ
- የ 6 ወር የስራ አፈፃፀም በወቅቱ ተሞልቶ እንዲቀርብ ማድረግ
- የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓትን ማሻሻልና ቅሬታን በፅሁፍ ተቀብሎ ምላሽ በደብዳቤ መስጠት
- የስራ መከታተያ ቸክሊስት አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባት
- ከአጋር መ/ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ መስራት
ግብ ሁለት

የዕቅድ ክንውን የስራ ግምገማ ማካሄድናለቀጣይ እቅድም መሰረት መጣል፡፡

ዓላማ ፡-በየዕለቱ የዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ችግሮችን ፈጥኖ ለማስተካከል እንዲቻል ነው፡፡
የሚከናወኑ ተግባራት
- አስተዳደሩ በየሳምንቱ ስራዎችን ይገመግማል
- ሱፐርቫይዘርና የትምህርት ባለሙያዎች በየ 15 ቀኑ ይገመገማሉ
- ር/መምህራን፣ሱፐርቫይዘርና ጽ/ቤቱ በየሩብ ዓመቱ ይገማገማል

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 30


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

- የጉድኝት ማዕከላት በየወሩ እየተገናኙ ግምገማ ያካሂዳሉ


- የተማሪ ቁጥር መረጃ ት/ቤቶች በየሳምንቱ ለወረዳ ይልካሉ፤ወረዳ ለዞን በማጠናከር ያስተላልፋል
- የየሩብ አመቱና ወርሃዊ ሪፖርቶች ከስራ ግምገማዎች በመነሳት ይዘጋጃሉ
ክፍል 4
( )
ዕቅዱን ለመፈፀም ያሉ መልካም አጋጣሚዎች፣ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ስጋቶች ፣መፍትሄዎችና የምንከተላቸው አቅጣጫዎች፣
4.1 ዕቅዱን ለመፈፀም የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎች
 የሀገራችን ኢኮኖሚ ቀጣይነት እያደገ መምጣት፣
 በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጅ ላይ እየተፈጠረ የመጣው የግንዛቤ ለውጥ፣
 ለትምህርት አመራሩ፣ለር/መምህራን፣ሱፐርቫይዘሮችና የስራ ሂደት ፈፃሚዎች የተሰጠው የመካከለኛ አመራር ስልጠናና
ክትትል፣
 በሁሉም ተቋማት ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች መሟላታቸው፣
 ለ 2010 ዓ.ም የመምህራን የእርከን ጭማሪ
 መንግስት ለተመራቂ ተማሪዎች ከፍተኛ የስራ እድል መፍጠሩ
 የመምህራን የደረጃ እድገት መቀጠል፣
 ህብረተሰቡ ለትምህርት ስራ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሸለ መምጣትና ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች
መከፈታቸውና ህብረተሰቡ ተቋማትን ለመደገፍ ያለው ተነሳሽነት፣
 በክረምት መምህራንና ር/መ/ራን የደረጃ ማሳደጊያ ስልጠና መጀመራቸው፣
 በገጠርም ሆነ በከተማ የመልካም አስተዳደር ፓኬጅ ተግባራዊ መደረጉ፣
 በገጠር ቀበሌዎች የመገናኛ ቴጅኖሎጅ እየተስፋፋ መሄድ፣
 ተግባር-ተኮር የጎልማሶችን ት/ት ለማጠናከር በቂ ጨራሽ ተማሪዎች መኖራቸውና
 ጥሩ በሚባል ደረጃ መምህራንና ርዕሠ-መምህራን በክረምቱ የት/ት መርሃ-ግብር እየተከታተሉ መሆናቸው፣
4.2 ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች/ስጋቶች
 የአጠቃላይ ትም/ፓኬጁን በታቀደው ዕቅድና በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተደራጀ የልማት ሰራዊት ፈጥሮ
ያለመንቀሳቀስ፣
 የሚደራጁት የልማት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመሆን
 በየደረጃው ያለው አመራርና ፈፃሚ ከጠባቂነት ሙሉ በሙሉ ያለመላቀቅ፣
 መልካም ተሞክሮን የማስፋት ስትራቴጂ በአግባቡ ተግባራዊ ያለማድረግ፣
 እቅዱን በአግባቡ አቅዶ ተገቢ ኦረንቴሽን ሰጥቶ ወደ ለውጡ ያለመግባት፣
 የክትትል፣ድጋፍና ሪፖርት ችግሮች፣
 ተግባራትን ለማከናወን የበጀት እጥረት መኖሩ፣
 የተመደበውን በጀት ለተፍለገው አለማ በመመሪያው መሰረት ተግባር ላይ አለማዋል
 ጤና፣ፖሊስና ግብርና ከትምህርት ጋር በመቀናጀት ተግባር-ተኮር ጎልማሶችን ያለመርዳት ችግር፣
 ህብረተሰቡ ለጎልማሳ ትምህርት ያለው አመለካከት አናሳ መሆን
4.3 የመፍትሄ አቅጣጫዎች

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 31


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 የንቅናቄውን ዕቅድ በአግባቡ በተቀመጠው ፕላን መሰረት መፈፀም፣መከታተል፣መደገፍ መገምገምና ተገቢ እርምጃ
መውሰድ፣
 በወረዳው ያለውን የፖለቲካ አመራሩ ክትትል ኮሚቴ አደራጅቶ ማንቀሳቀስ
 ሁሉም አካል የማስፋት ተልዕኮ መፈፀሙን በተጠያቂነት ማረጋገጥ
 የክረምቱን ስልጠና ከኮሌጅ አመራሮች ጋር ተገቢ ዝግጅት ማድረግ፣መሰናዶዎችን መጠቀም፣
 የተጠናከረ የእቅድ ትውውቅና ዝግጅትን በተለያዩ መድረኮች ማድረግ፣
 የትምህርት ሀብት አጠቃቀምን /የመምህራን ትም/መሳሪያና ሌሎች ሀብቶችን /ማሻሻልና የህብረተሰብ ተሳትፎን
ማሳደግ፣
 በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ አጭር ስልጠና መስጠት
 በተቻለ መጠን ሁሉንም ሴክተሮች አጣምሮ ለመስራት መሞከር፣
 ለህብረተሰቡ የጎልማሳ ትምህርት አስፈላጊነት ግንዛቤ መፍጠር
4.4 ዕቅዱን ለመፈፀም የምንከተላቸው አቅጣጫዎች
 የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጁን በበላይት የፖለቲካ አመራር እንዲሰጥ የሚጠበቀውን ኮሚቴ ከወረዳ እስከ ቀበሌ
ድረስ እንዲቋቋም በማድረግ በየወሩ የአፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበለት ድጋፍና ክትትል እንዲያደርግ ማድረግ፣
 በየደረጃው በአመራሩ በባላሙያዉና በልዩ ልዩ ባለድርሻዎች ውስጥ ያለውን የዕውቀት ፣ክህሎትና ግንዛቤ ችግሮች በተለያዩ
የአጭርና ረጅም ጊዜ ስልጠና በማዘጋጀት የተሻለ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሄድና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ፣
 የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጅም ሆነ የምዕተ-ዓመቱ ግብ የተቀናጀ ወረዳዊ የትምህርት ልማት ሰራዊትን ፈጥሮ
ማደራጀት፣ማብቃት፣መደገፍና ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ይህን አግባብ መከተል፣
 ዓመታዊ ዕቅድ ዝግጅታችን በሶስት ምዕራፍ በመክፈል/በቅድመ ዝግጅት፣በትግበራና በግምገማ/ መስራት ያለብንን ለይቶ
ወቅታዊ ተግባራትን መፈፀም፡፡በተለይም ደግሞ ከክልል ት/ቤት የተናበበ፣በፓኬጁ ስታንዳርዶች መነሻነትና ለአካባቢያዊ
ሁኔታዎች ሁሉ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የማስፋት ስትራቴጅውን ከውስጥ ተቋም፣ግለሰብ አፈፃፀም ውስጥ ፕሮግራም በማውጣት ሁሉንም ተቋማት እንዲሸፍን
አድርጎ መፈፀም፣
 መሰረታዊ የስራ ሂደት ጥናት ውጤቶችን የለውጥ ማራመጃና ማስተግበሪያ መሳሪያነት በውል በመረዳት ለአጠቃላይ
ትምህርት ጥራት ፓኬጅ መርሃ-ግብሮች ማስፈፀሚያነት እንዲውል ማድረግ፣
 በወረዳው በየደረጃው ያሉ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን ወመህ፣ቀትስቦ፣የተማሪዎች ልዩ ልዩ አደረጃጀት….ወዘተ/በአግባቡ
አደራጅቶና አንቀሳቅሶ በፓኬጁ ትግበራ የየድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ፣

ወሳኝ የሆኑ የሀምሌና የነሀሴ ወር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በወቅቱና በአግባቡ መፈፀም

 የመምህራን ቅጥር፣ምደባና ዝውውርን ከሰኔ 10 ቀን 2010 ዓ.ም በፊት ማጠናቀቅ፣


 አዲስ የሚከፈቱ፣ደረጃቸውን የሚያሳድጉ ሳተላይት ትምህርት ቤቶች በሰኔና በሀምሌ ወር ማጠናቀቅ፣
 እስከ ነሀሴ 27/2009 ሰባት ዓመት የሞላቸውን ህፃናት ትምህርት ቤት ማስገባት ባህል ማድረግ

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 32


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 መምህራን በወቅቱ በትምህርት ቤት ተገኝተው የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አከናውነው ትምህርት በወቅቱ እንዲጀመር
ማድረግ ፣ከክረምት ኮርስ ተመላሾች በወቅቱ በትምህርት ቤት እንዲገኙ ማድረግ፣
 የ 8 ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤትን ለተማሪዎች ወዲያውኑ እንደደረሰ ወደ ትምህርት ቤቶች ማድረስ፣

 የትምህርት ቤቶች አከፋፈት በወቅቱ የቀበሌው አመራርና ወላጆች በተገኙበት በደመቀ ስነ-ስርዓት
እንዲፈፀም ማድረግ

 በስነ-ስርዓቱ ላይ የትምህርት ቤቱን ዕቅድና ከወላጆች የሚጠበቀውን ተሳትፎ በማስተዋወቅና ሌሎችንም ወሳኝ ተግባራት
በማከናወን መፈፀም፣
 ህብረተሰቡ የጊዜ ሰሌዳውን ጠብቆ በየ ወሩ በመወያየት በተማሪዎች ውጤትና ዲሲፕሊን መሻሻል እንዲያመጣና
ተቋሙንም በፋይናንስ የማገዝ ስራ እንዲሰራ መግባባት፣

 ለትምህርት ተቋማት መሪ እንዲኖራቸው ማድረግ

 በአዲሱ የመርሱ መመልመያ መመሪያ መሰረት ለሁለቱ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 6 ድጋፍ ሰጭ፣ 11 መምህራንን
በመመደብ ማሰማራትእንዲሁም፣ 5 ድጋፍ የ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት 1 የ 1 ኛ ደረጃ ሱፐርቫይዘሮችን፣9 የ 1 ኛ ደረጃ ር/መ/ራን
መመደብ፣
 የስራ ሂደት ፀሀፊዎችንና ፈፃሚዎችን/ባለሙያዎችን ማሟላት፣

 መልካም አስተዳደርን በየደረጃው ለማስፈን ጥረት ማድረግ

 የመምህራንን ዝውውር በወቅቱና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መፈፀም/እሰከ ሰኔ አጋማሽ ማጠናቀቅ


 ፍትሃዊ የሆነ የስልጠና ዕድል መምህራን፣ሱፕቫይዘሮች፣ር/መ/ራንና የጽ/ቤት ፈፃሚዎች እንዲያገኙ ማድረግ፣
 ተገቢና ፈጣን አገልገሎት በጽ/ቤት ውስጥ በየስራ ሂደቱ መስጠት፣
 ከመምህራን ማህበር ጋር በቅንጅት መስራት፣
 ከየ ስራ ሂደቶች ጋር ተቀናጅቶ መስራት፣
 የህብረተሰብና ትምህርት ቤት ግንኙነት በተለያዩ መንገዶች በማጠናከር በአመራሩ የበላይነቱን እያረጋገጡ
መሄድ

 የህብረሰብ ተሳትፎን በአግባቡ በጥራትም ሆነ በሽፋን ለይቶ መያዝና ማነሳሳት፣


 አጠቃላይ ህ/ሰቡን የተሳትፎ ዕቅድ ማስተዋወቅና በዕቅዱ መሰረት እንዲሳተፍ ማድረግ፣
 የተሳትፎውን መረጃና ሪፖርት በአግባቡ መያዝና ማስተላለፍ …ወዘተ
 ጠባቂነትን አስወግዶ በስልጠናና በልምድ የተገኘን ተሞክሮና የትምህርት ቤት ማህበረሰብ አቅም አሟጦ መጠቀም፣
 ዓመታዊ የትምህርት ቀን በዓል በማክበር የፓኬጁን አፈፃፀም መዘከርና ለውጤታማ ተቋማት፣ግለሰቦች፣አደረጃጀቶች
ወዘተ የማበረታቻ ሽልማት መስጠትና መልካም ተሞክሮዎችን ለሌሎች በማስተላለፍ የስራ ተነሳሽነትን አጠናክሮ
ማስቀጠል፣
 በየደረጃው ተገቢ የክትትል ድጋፍና ሪፖርት ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ

 ትርጉም ያለው ከተቆጣጣሪነት መረጃ ከመልቀምና ከማቀባበል ያለፈ የሱፐርቪዥን ድጋፍ መስጠት፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 33


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 ስራዎችን በቼክሊስት ቆጥሮ ለየስራ ሂደቱና በየደረጃው ላሉ ተቋማት ማስረከብ፣


 ወቅታዊ፣ታማኝና ተከታታይነት ያለው የሪፖርትና ግብረ-መልስን ስርዓት አጠናክሮ ተግባራዊ ማድረግ፡፡ከሁሉም በላይ
ደግሞ ከሪፖርት ጥንቅር በኋላ ለበታችኛው አካል የሚሰጠው ግብረ-መልስ በራሱ አስተማሪ የስልጠናና ማስተካከያ
መሳሪያ መሆኑን በመረዳት በአግባቡ መተግበር፡፡

ክፍል 5
5. የዕቅዱ አተገባበር፣የግንኙነትና የሪፖርት አደራረግ ስርዓት
5.1 በትምህርት ቤት ደረጃ ፡-

 በትምህርት ቤቶች ያሉት ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በየሳምንቱ የፓኬጁን አፈፃፀም ይገመግማሉ፣ለጉድኝት ማዕከላት ሪፖርት
ያደርጋሉ፣በየሳምንቱ የተማሪ ቁጥር በፆታ፣ በእድሜና በክፍል ደረጃ ለይተው እንዲሁም የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል
ከጣሉት ግብ አኳያ አፈፃፀሙ እንዲሁም የመምህራን ተከታታይ ስልጠና፣የስነ-ዜጋ ትምህርት እንቅስቃሴ በስርዓተ-
ትምህርቱ ተግባራት ዙሪያ ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግመው ለጉድኝት ማዕከል ያስተላልፋሉ፣
 ሞዴል መምህርና ክፍል መርጠው ሌሎች መምህራንና ክፍሎች ወደዚህ ስታንዳርድ እንዲደርሱ ያደርጋሉ፣
 ሁሉም የወረዳው ት/ቤቶች የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ለየስራ ሂደቶች ይልካሉ፣
5.2 በጉድኝት ደረጃ ፡-
 ሱፐርቫይዘሮች በተመደቡበት ጉድኝት ማዕከላት የሚገኙ ት/ቤቶችን ር/መምህራን በማዕከሉ በማሰባሰብ ዘወትር በየአስራ
አምስት ቀኑ ስራ እንዲገመግሙ ማድረግ፣
 የጉድኝት አባል መምህራን በወር አንድ ጊዜ እየተገናኙ በሚያስተምሩት የት/ዓይነት በተናጠልና በጋራ ተሞክሮና ልምድ
ይለዋወጣሉ፣
 የጉድኝት ሱፐርቫይዘሮች ር/መምህራንን ከመደገፍ ባለፈ የጉድኝታቸውን መምህራን ተገቢ የሆነ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል
ይደረጋል፣
 የጉድኝቱ የተማሪ መረጃ ሪፖርትና ሌሎች ዋና ዋና አፈፃፀሞች በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለወረዳ እንዲደርስ
ይደረጋል፣
 የጉድኝቱ ት/ቤቶች መምህራን የ 1 ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማብቃት ፎረም በማቋቋምና ልምድ በመለዋወጥ ደረጃ
እየሰጡ ለወረዳ ሪፖርት ያደርጋሉ፣
 ሁሉም በጉድኝቱ ያሉ መምህራን የጎልማሶችን ትምህርት በትኩረት ይዘው ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ይንቀሳቀሳሉ፣
 በት/ቤቶች ያለውን አፈፃፀም ገምግመው በውጤታቸው መሰረት በየወሩ ደረጃ ያወጣሉ፣ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፣
 ሞዴል ርዕሰ-መምህር፣ት/ቤትና ክፍል ተመርጠው ሌሎቹ ወደዚያ ስታንዳርድ እንዲደርሱ ጥረት ይደረጋል፣
5.3 በወረዳ ደረጃ:-
 የወረዳ ማኔጅመንት ኮሚቴ በየሳምንቱ እየተገናኘ የዕቅድ አፈፃፀሙን ይገመግማል፣በወር አንድ ጊዜ ወደ ቀበሌ እየሄደ
ይገመግማል፣ይደግፋል የአንድን ት/ቤት የተሻለ ተሞክሮ ወደ ሌላ ያስተላልፋል እንዲሁም ርዕሳነ-መምህራንና
መምህራንን በማንቀሳቀስ የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋል፣
 በየወሩ ለጉድኝት ማዕከላትና ለት/ቤቶች በጥራት ማስጠበቂያ ፓኬጅ አፈፃፀም ደረጃ እያወጣ መረጃ ይይዛል፣ግብረ-
መልስ ይሰጣል፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 34


የመተማ ወረዳ ትም/ጽ/ቤት የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ

 የተቀናጁት ተግባር-ተኮር ጎልማሶችን ትምህርት ትኩረት ሰጥቶ መስራትና ይህንንም በተግባር ያረጋገጠ ግምገማ በዕቅድ
በተመራ አግባብ ማካሄድ፣
 በአራቱም ሩብ ዓመታት በወረዳ ደረጃ የሱፐርቫይዘርና ር/መ/ራን ግምገማና ክትትል ይካሄዳል፣
 ወረዳዎች በወር አንድ ጊዜ ሱፐርቫይዘሮችን በመያዝ የጋራ ግምገማ ያካሂዳሉ፣
 ወረዳዎች የየወሩን አፈፃፀም አንድ ጊዜ እንዲሁም የሩብ ዓመት ሪፖርትን ለዞን ያቀርባሉ፣
የወረዳው ስትሪንግ ኮሚቴ የፓኬጁን አተገባበር መደበኛ በሆነ አግባብ በየወሩ እየገመገመ አቅጣጫ ይሰጣል፣

ለዕቅድ ተግባራዊነትና ስኬት በጋራ እንረባረብ !! Page 35

You might also like