You are on page 1of 8

የትምህርት ሴክተር የእስካሁን አፈጻጸም ሪፖርት

1.ትምህርት ቤቶችን ለመማር - ማስተማር ስራዉ ዝግጁ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ

የ2016 ዓ/ም የሥራ ቅድመ ዝግጅት በክረምት ወራት በ23ቱም መወቅሮች የትም/ቤቱ ባለድረሻ አካላት
በተገኙበት የክረምት አቅድ ተነድፈዉ በአግባቡ ትም/ቤቱ ለ2016 ዓ/ም ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ
እንዲሆን ከግብ ሳር የተበላሹ ወንበሮችና ደስኮች ጥገና፤ጥቁር ሠሌዳ ቀለም መቀባት፤የመማሪያ ክፍሎች
እድሳትና አድስ ግንባታ እና የሌሎች መሰረተ-ልማት በመስራት ትም/ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ
ዝግጁ የማድረግ ሥራ ተሰርተዋል፡፡

ከዚህ አንጻር በክረምት ዝግጅት ወቅት አዲስ ተጨማሪ የክፍል ግንባታ 308 ፣የነባር ክፍል ጥገና 243
፣አዲስ የተማሪ ዴስክ አቅርቦት 889 ፣የተማሪ ዴስክ ጥገና 1724 ፣አዲስ የጥቁር ሰሌዳ አቅርቦት 155
፣የጥቁር ሰሌዳ ጥገና 784 ተደርጓል፡፡ በተጨማርም የማጣቀሻ መጻሓፍትና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁስ
ለተማሪዎች የማቅረብ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
የቀጠለ………….
2. የ2016 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ በተመለከተ

አጠቃላይ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የምዝገባ ዕቅድ ወንድ 327982 ሴት 307531 ድምር
635513 ክንዉን ወንድ 298212 ሴት 284192 ድምር 582404 አፈጻጸማችን ዞናዊ 91.6
% ነዉ፡፡የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ቅበላ ዕቅድ ወንድ 6094 ሴት 5400 ድምር 11494
ክንዉን ወንድ 2979 ሴት 2780 ድምር 5759 አፈጻጸማችን 50.1% ነዉ፡፡

የቅድመ-አንደኛ ተማሪዎች ቅበላ ዕቅድ ወንድ 68458 ሴት 63851 ድምር 132309


ክንዉን ወንድ 63627 ሴት 60007 ድምር 123634 አፈጻጸማ2. የ2016 የትምህርት ዘመን
የተማሪዎች ቅበላ በተመለከተ

አጠቃላይ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የምዝገባ ዕቅድ ወንድ 327982 ሴት 307531 ድምር
635513 ችን 93.44% ነዉ፡፡
3. የልዩ ፍላጎት ርሶርስ ማዕከላትንና ቂድመ አንደኛ ት/ቤቶችን በተመለከተ
 በ2015 አስራ ሦስት /13/ የርሶርስ ማዕከላት ከነበረበት 3/ሦስት/ ተጨማሪ ርሶርስ ማዕከላት ማለትም

በሁመቦ፤አበላ አባያ እና በድጉና ፋንጎ ወረዳ ርሶርስ ማዕከላትን በማቋቋም የሚያሰፈልጉትን ኮምፒዩተር
ለእያንዳንዱ ትም/ቤት 20 እና ሌሎች ግብአቶችን ጨምሮ 1.2 ሚልዮን የሚገመት ንብሬት ተዳርሰዋል፡፡

4. የህብረተሰብ ተሳትፎን በተመለከተ

በዞናችን ከህብረተሰቡ፣ ከመንግስትና ከአጋር ድርጅቶች የተሰበሰበበ ገንዘብ፣በአይነትና በቁሳቁስ ከክረምት


ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ዕቅድ ወጥቶ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተመለከተ አጠቃላይ
ዕቅድ 14,1996,236 ይህም በገንዘብ እቅድ 56,000,000 ክንዉን 31,274,970 ፣በጉልበት እቅድ
21,990,036 ክንዉን 16,700,000 ፣በአየነት ዕቅድ 64,006,200 ክንዉን 45,620,150 ሆኖ፤
በአጠቃላይ ዕቅድ 141,996,236 ክንዉን 93,595,120 (65%) ደርሰዋል፡፡
5. ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ተቋማት ደረጃ ብቃት በመገምገም የዕዉቅና ፈቃድ በተመለከተ

በዞኑ በሁሉም የትምህርት ዕርከኖች የቅድመ ዕዉቅና ለመስጠት ዕቅድ 6 ክንዉን 4 (66.6%)፤ሙሉ ዕዉቅና
ዕቅድ 3 ክንዉን 1 (33%) ሆነዋል።የግል ቅድመ-አንደኛ ቅድመ ዕዉቅና ዕቅድ 4 ክንዉን 5 ፤ሙሉ
ዕዉቅናዕቅድ 11 ክንዉን 8 ናቸዉ፡፡

6.ከመምህራን የትምህርት አመራርና አስተዳደር አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ

የመምህራን ምደባ/ቅጥር በተመለከተ የዲፕሎማ ወንድ 45 ሴት 30 ድምር 75 ድግሪ ወንድ 42 ሴት10


ድምር 52 ናቸዉ፡፡

የመምህራን ዝዉዉር በተመለከተ በዞን ዉስጥ ከወረዳ/ከተማ ትም/ጽ/ቤቶቸ ወደ ወረዳ/ከተማ ት/ጽ/ቤቶቸ


ዝውውር ያገኙ ዲግሪ ወ 87 ሴ 16 ድ 103 ድፕሎማ ወ 106 ሴ 62 ደ 168 እንድሁም በተለያዩ
ምክንያቶች መነሻ በድጋፍ ደብዳቤ የተዛወሩ በአጠቃላያ ወ 30 ሴ10 ድ 40 በተጨማሪ ከሌላ ዞን ወደ
ዞናችን የተዛወሩ መ/ራን ወ 26 ሴ 7 ድ 33

በጊዜያዊ ህክምና ዝውውር የወጡ መ/ራን ወ 7 ሴ 10 ድ 17

የትምህርት ማስረጃ ህጋዊነት የተረጋገጠላችው መ/ራን ወ 26 ሴ10 ድ 36 ሀስት ሆኖ የተገኘ ወ 5 ሴ 3 ድ 8


7. ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ሥራን በተመለከተ
ከ1-6ኛ ክፍል የግብረገብ ትምህርት ለተማሪዎች እንዲሰጥ በተወሰነው መሰረት በአገር ደረጃ የመጽሃፍ
ዝግጅት የተደረገ ሲሆን ተጠናቅቆ እንደ ዞን በወላይትኛ የማስማማት ሥራ ተሠርተው ወደ ትግበራ
ተገብተዋል፡፡ በተጨማሪም ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ከአድሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር
የትዉዉቅ ሥልጠና ተሰጥቶ የማስተማር ሥራ እንድቀጥል ተደርገዋል፡፡ በተያያዘም በሁሉም የትምህርት
አይነትና የትምህርት እርከን የተማሪ መጽሃፍ ጥምርታ 1፡1 ለማድረስ እና የተማሪ መፅሃፍ አጠቃቀም
ጥምርታ ለማሻሻል ታቅዶ ፣ በሁለተኛ ደረጃ 1፤5 እና በመካከለኛ ደረጃ 1፤4 የተዳረሰ ስሆን ከ1ኛ-6ኛ ክፍል
ደረጃ ባለው የችግሩ አሳሳብነት እንደቀጠለ ነው፡፡

8. የፈተና እና ምዘና አስተዳደር ተግባራትን በተመለከተ


በ2015 ትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከተፈተኑ ወንድ 15,626 ሴት 15,028 ድምር 30,554
ተፈታኞች መካከል ወደ ዘጠነኛ ክፍል ከተዛወሩት ተማሪዎች ወንድ 2,407 ሴት 1,971 ድምር 4,378
(14.3%) ሲሆን ከእነዚህ መካከል የግል/የመያድ ት/ቤቶች ካስፈተናቸዉ ወንድ 915 ሴት 799 ድምር
1,714 ሲሆን ወደ ዘጠነኛ ክፍል የተዛወሩት ወንድ 621 ሴት 658 ድምር 1,279 (74.6%) ሲሆን
በመንግሥት ት/ቤቶች ወንድ 15,011 ሴት 13,057 ድምር 28,068 ከተፈተኑት ደግሞ ወንድ 1,786 ሴት
1,313 ድምር 3,099 (11%) ብቻ ተዛዉረዋል፡፡
በ2015 የትም/ ዘመን በዞኑ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስፈታኝ ት/ቤቶች ብዛት 79 ሲሆን ፈተና
ከተፈተኑ ወንድ 11186 ሴት 9767 ድምር 20953 ተፈታኞች መካከል ከ50% በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች
ወንድ 299 ሴት 48 ድምር 347 (1.66%)

ካስፈተኑ 79 ትም/ቤቶች መካከል አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ት/ቤቶች ብዛት 36(45%) ናቸዉ፤ አንድ ተማሪና
በላይ ያሳለፉ ት/ቤቶች ደግሞ 43 (64%) ናቸዉ፡፡

9. የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትም/ቤቶች ደረጃ የማስጠበቅ ሥራ በተመለከተ

ለአጠቃላይ የትምህርት ሥራ ውጠታማነት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤትን ደረጃ ማስጠበቅና


የትምህርት አከባቢውን እጅግ ማራክ፣ ሳብ እና ምቹ እንድሆን በማድረግ የህፃናትን የትምህርት አጀማመር
ማስተካከል ተኪ የለውም፡፡ በመሆኑም እንደ ዞናችን “ዘመቻ ቅድመ አንደኛ” በሚል መሪ ቃል በሁሉም
ከተሞችና የወረዳ አስተዳደሮች የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶችን ደረጃቸውን የማስጠበቅ ሥራ
ለመስራት በተደረገዉ ርብርብ እንደ ዞን በቁጥር 388 ቅ.አ ደረጃ ት/ቤቶችን ደረጃ ለማስጠበቅና ዕውቅና
ለመስጠት መቻላችን ይታወሳል፡፡
 በመሆኑም የተግባሩን አንገብጋብነት በምመጥን መልኩና እጅግ በምያስደምም ዘመቻ

ወደ ተግባር የገቡ መዋቅሮች ከመኖራቸው የተነሳ በ2015 የትምህርት ዘመን እንደ ዞን


የተጣለውን ዕቅድ (262) ያሳካን የምመስል ነገር ብኖርም እንኩዋን ከጠቄሜታው
አኩዋያ ገና ብዙ መስራት ይጠበቅብናል፤ ከመዋቅር ወደ መዋቅር ያለውን ልዩነትንም
ማጥበብ ይገባናል፡፡
 ከዚህ አኩዋያ አጠቃላይ የትምህርቱን ማህበረሰብ በማነቃነቅ የተጣለውን ዕቅድ

ከማሳካት ባሻገር ያላቸውን ት/ ቤቶች በሙሉ ሞዴል በማድረግ ለዕውቅና አሰጣጥ


ሥነሥርዓት ያበቁ መዋቅሮች ኪ/ኮይሻ፣ ባይራ ኮይሻ፣ ገሱባ፤በሌ፤ ዳ/ሶሬ እና ጠበላ
ከተማ ሲሆኑ ፤ ሌሎች ግን የተግባሩን አንገብጋብነትና ጠቄሜታ በሚመጥን መልኩ
እንድተጉ ይጠበቃል፡፡
ያጋጠሙ ችግሮች

1.በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ሙሉ ትግበራ ላይ የመጽሐፍት አቅርቦት ችግር፣

2.በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ሙሉ ትግበራ ላይ አዲስ በተካተቱ ትምህርት ዓይነቶች የመምህራን


እጥረት፣

3.የትምህርት ቤቶች የድጎማ በጀት ያለመመደብ፣ የመደቡ መዋቅሮችም ቢሆኑ ሙሉ በሙሉ ያለ


ማውረድ፣

4.የመምህራን የትምህርት ለውጥ እና የደረጃ ዕድገት ክፍያን በወቅቱ ያለመክፈል፣ ካፒታል በጀት ተመድቦ
በጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ያለመዋል ችግር፣

You might also like