You are on page 1of 4

በኤልሀመር 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ 2014 ዓ.

ም ትምህርት ዘመን
የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ

ሀሎ ቡሰ 1ኛ /
ደረጃ ት ቤት ለ 2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን

/
የቅድመ መደበኛ የኦ ክፍል ትምህርት

ዓመታዊ እቅድ

በእቅዱ የተካተቱ ርዕሰ ጉዳዮች ዝርዝር

1. መግቢያ

2. የእቅዱ ዋናዋና ዓላማዎች

3. የእቅዱ ዝርዝር ዓላማዎች

4. የእቅዱ አስፈላጊነት

5. የእቅዱ ቅድመ ትኩረት ነጥቦች ዝርዝር

6. የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት

7. የድርጊት መርሃግብር

8. እቅዱን ያፀደቁ ባለድርሻ አካላት ስም ዝርዝር

‹‹ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም››

ሀሎ ቡሰ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት

ሰኔ 2014 ዓ.ም

1
በኤልሀመር 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን
የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ

1. መግቢያ

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ለህፃናት ሁለንተናዊ ስብዕና እድገት ከፍተኛ እገዛ ያለው፣ለወደፊት ህይወታቸው መሰረት
የሚጥልና ህጻናት ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚዘጋጁበት የትምህርት ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮግራም ሁሉንም
ህፃናት በፍትሀዊነት ተጠቃሚ በማድረግ በየትምህርት እርከኑ የሚታዩ የትምህርት ውስጣዊ ብቃት፣ ተገቢነት እና ጥራት
ችግሮችን ከማሻሻል አንፃር ጥቅሙ የላቀ ሲሆን በረጅም ጊዜ ውስጥ የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድም የሚጫወተው
ሚና የጎላ ነው።
የሀገራችን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የቅድመ መደበኛ ትምህርት የመጀመሪያው የትምህርት ፕሮግራም መሆኑን
በግልፅ ቢያመላክትም በመንግስት የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ሀገራዊም ሆነ በትምህርት ቤታችን ደረጃ ሽፋኑ
እጅግ ከፍተኛ ሲሆን አሀዛዊ ከሆኑት ግቦች ባሻገር ለኦ ክፍል ትምህርት ተመጣጣኝ የሆኑ ጥራትን የሚያረጋግጡ ግቦች
በበቂ ሁኔታ አ።ተቀመጡወል።በመሆኑም መርሀ ግብሩ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ፣ የሰለጠኑ መምህራን መኖር፣የግብዐት ፣
የፋሲሊቲዎች ተሞላቶ፣ የተለያየ እድሜ ያላቸው ህጻናት በአንድ ላይ መማር፣ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ህጻናት
ተደራሽነት አነስተኛ መሆንና መሰል ችግሮች በዋነኛት ይንፀባረቁበታል።
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን እና መሰል ችግሮችን ለመቀነስ ለኦ ክፍል ትምህርት ስታንድርድ በማዘጋጀት ህጻናት
ለደረጃው የተቀመጠውን ትምህርት አጠናቀው ለመደበኛው ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ ለማስቻል በትምህርት ቤታችን
የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

በዚህም መሰረት በትምህርት ቤታችን በተመደቡ የሰለጠኑ ሁለት/2 ሴትየኦ ክፍል መምህራን በመታገዝና ሰለሰ አንድ/31
ወንድና ሀያስምንት/28 በድምሩ ሀምሰ ዜጠኝ/59 ህፃናትን በመመዝገብ የ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን መማር
ማስተማር ሂደትን ማስጀመር ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በትምህርት ቤታችንን የኦ ክፍል አፈፃፀም ከቅድመ መደበኛ ትምህርት
ስታንዳርድ አንፃር በተደረገው የአፈፃፀም ኢንስፔክሽንና ግምገማ መሰረት ትምህርት ቤታችን

ነጥብ በማስመዝገብ በደረጃ ሶስት/3 የግምገማ ውጤት ላይ የምንገኝ መሆኑን በአስተዳደራችን ትምህርት ቢሮ
በተገለፀልን ግብረመልስ መድረክ ላይ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ይህ የኢንስፔክሽን ሂደት ውጤት እንደሚያሳየው በኦ ክፍል
ትምህርት አፈፃፀም ትምህርት ቤታችን የተሻለ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ቢሆንም በሌላ መልኩ ሊሻሻሉ የሚጠበቁ ብዙ
ክፍተቶች መኖራቸውንም ጭምር በግልፅ የሚጠቁምና በተጨማሪ ጥረቶች መታገዝ እንዳለበት አመላካች ነው፡፡

ስለዚህም የትምህርት ቤታችንን የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ትግበራና አፈፃፀም ማሻሻል የሚቻልባቸው
መልካም አጋጣሚዎች እንዳሉ ሁሉ ስጋቶች ያሉ መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ባለን አቅምና ግብዓት እንዲሁም
አካባቢያዊ የመፍትሄ አቅጣጫዎች በመታገዝ የትምህርት ቤታችንን ደረጃ ሶስት/3 አፈፃፀም ወደ ደረጃ አረት/4 ማሻሻል
ይጠበቅብናል፡፡

በዚህም መሰረት ይህ የ 2015 ዓ.ም ት/ት ዘመን የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ ከግብዓት፤ከሂደትና
ውጤት ቁልፍ ርዕሰ ጉዳዮች አንፃር አፈፃፀምን ማሻሻል በሚያስችል መልኩ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባና
ለስኬቱም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረት እንደሚጠይቅ ከመርሃግብሩ ቁልፍ የት/ቤቱ ማህበረሰብ ጋር
ከስምምነት ተደርሶ ይህ ሀሎ ቡሰ

1 ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ 2015 ዓ.ም ት/ት ዘመን የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ እንደሚከተለው
ተዘጋጅቷል፡፡

2. የእቅዱ ዋና ዓላማ

በት/ቤታችን ሀሎ ቡሰ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ስታንዳርዱን የጠበቀ እንዲሆን
በማስቻልና ያለንበትን ደረጃ ሶስት/3 አፈፃፀምን ወደ ደረጃ አረት/4 በማሻሻል የት/ቤታችን ህፃናት

2
በኤልሀመር 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን
የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ
አካላዊ፤አዕምሮዓዊ፤ማህበራዊና ስነልቦናዊ እድገቶችን አዳብረው ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል የእቅዱ
ዋና ዓላማ ሲሆን የሚከተሉትን ዝርዝር ዓላማዎችም በውስጡ ያካተተ ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡

3. የእቅዱ ዝርዝር ዓላማዎች

የዚህ ለ 2015 ዓ.ም ት/ት ዘመን ሀሎ ቡሰ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ
እቅድ ዝርዝር ዓላማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፤-

 የኦ ክፍል ትምህርት ከተቀመጠው ስታንዳርድ አንፃር ተግባራዊ መደረጉን ማረጋገጥ


 ለደረጃው የተቀመጠውን ዝቅተኛ የሰው ሀይልና መምህራን አሟልቶ መተግበሩን ማረጋገጥ
 ለልዩ ፍላጎት ያላቸውና አካል ጉዳተኛ እንዲሁም ለሁሉም ህፃናት ጨምሮ ምቹ የትምህርት ሁኔታና
አካባቢን መፍጠር
 የኦ ክፍል የውስጥና የውጪ የትምህርትና የመጫዎቻ ቁሳቁሶችን የተሟሉ እንዲሆኑ ማስቻል
 በየደረጃው ያሉ ባላድርሻ አካላት ለኦ ክፍል ትምህርት መሻሻል ተግባርና ሀላፊነታቸውን ተረድተው
የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ
4. የእቅዱ አስፈላጊነት

በት/ቤታችን ሀሎ ቡሰ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት አሰጣጥና ትግበራን


ከግብዓት፤ከሂደትና ከውጤት አንፃር ያለበትን ደረጃ በማሻሻል ህፃናቱ ለደረጃው የተቀመጠውን ትምርት
አጠናቀው ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራትን/ስራዎችን ወጥ በሆነና በባለቤትነት የመምራት
ስርዓትን ማረጋገጥ ለዚህ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ዓመታዊ እቅድ አስፈላጊነቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው
ነው፡፡

5. የእቅዱ ቅድመ ትኩረት ነጥቦች ዝርዝር


5.1. የኦ ክፍል መማሪያና አገልግሎት መስጫ ክፍሎችና ፋሲሊቲዎችን ማሟላት
5.2. የኦ ክፍል ስርዓተ ት/ት አሰጣጥ ሂደትን ማሻሻል
5.3. የኦ ክፍል ት/ት ማስተግበሪያ የስርዓተ ት/ት መሳሪያዎችንና ሰነዶችን የተሟሉ ማድረግ
5.4. የኦ ክፍል ተማሪዎች ቅበላ፤ስለማጠናቀቅና የማበረታቻ እንዲሁም የት/ት ማስረጃ አሰጣጥ
ስርዓትን መዘርጋት
5.5. የፋይናንስ አጠቃቀምና ሀብት ማጎልበት ስርዓትን ሰርግቶ ተግባራዊ ማድረግ
5.6. የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ለኦ ክፍል ትምህርት አሰጣጥ ሂደት አጋርነትን ማሳደግ
6. የሚከናወኑ ዋናና ዝርዝር ተግባራት
6.1. የኦ ክፍል መማሪያና አገልግሎት መስጫ ክፍሎችና ፋሲሊቲዎችን ማሟላት
6.1.1. የኦ ክፍል መማሪያ ክፍል ግድግዳና ወለል በቀለም በማስዋብ ማራኪ ማድረግ
6.1.2. በኦ ክፍል መማሪያ ክፍል ውስጥ መገኘት ያለባቸው ቁሳቁሶችን ማሟላት
6.1.3. የኦ ክፍል መማሪያ ክፍል በአጥር መለየት
6.1.4. የመማሪያ ክፍልና ጨዋታ ቦታዎች መግቢያና መውጫ በሮችን ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት
ምቹ ማድረግ
6.1.5. የኦ ክፍል ህፃናት ማረፊያና መመገቢያ ክፍል ማዘጋጀት
6.1.6. የኦ ክፍል ህፃናትን ማዕከል ያደረገ/ያማከለ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማሟላት
6.1.7. የእጅ መታጠቢያ አገልግሎት ያለው የመፀዳጃ ቤት ለኦ ክፍል ህፃናት ለብቻ መለየት
6.1.8. ለኦ ክፍል ህፃናት ጤና አጠባበቅና ለመምህራን የመጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ ግንዛቤ በጤና
ባለሞያ እንዲሰጥ ማድረግ

3
በኤልሀመር 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ 2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን
የቅድመ መደበኛ/የኦ ክፍል ትምህርት ዓመታዊ እቅድ

6.1.9. የመጀመሪያ እርዳት መስጫ ኪት አሟልቶ በክፍል ውስጥ በማቅረብ ህፃናት አገልግሎቱን
እንዲያገኙ ማስቻል
6.2. የኦ ክፍል ስርዓተ ትምህርት አሰጣጥ ሂደትን ማሻሻል
6.2.1. የኦ ክፍል ት/ት አሰጣጥ ክፍለጊዜ ድልድልና ፕሮግራም ማዘጋጀት
6.2.2. የኦ ክፍል እለታዊ የትምህርት መርሃግብር ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ
6.2.3. የኦ ክፍልን በተለያዩ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች የተሟሉ እንዲሆኑ ማስቻል
6.2.4. የኦ ክፍል የተለያዩ የት/ት ጥጎች/ማዕዘኖች በማዘጋጀት የተሟሉ ማድረግ
6.2.5. የኦ ክፍል ውጪያዊ መጫዎቻ ቁሳቁሶች ማዘጋጀት
6.3. የኦ ክፍል ት/ት ማስተግበሪያ የስርዓተ ት/ት መሳሪያዎችንና ሰነዶችን የተሟሉ ማድረግ
6.3.1. የስርዓተ ትምህርት መሳሪያዎችና ሰነዶች ማሟላት
6.3.2. የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሰነዶች አዘጋጅቶ ማቅረብ
6.3.3. የኦ ክፍል ኢንስፔክሽን ማዕቀፍ በክፍል ውስጥ እንዲኖር ማድረግ
6.4. የኦ ክፍል ተማሪዎች ቅበላ፤ስለማጠናቀቅና የማበረታቻ እንዲሁም የት/ት ማስረጃ አሰጣጥ
ስርዓትን መዘርጋት
6.4.1. የኦ ክፍል ህፃናት ቅበላ ትክክለኛ እድሜን(5 እና 6 ዓመት) ያማከለ እነዲሆን ማስቻል
6.4.2. የኦ ክፍል ህፃናት ሙሉ መረጃ፤በአደጋ ጊዜ ተጠሪ የሆኑ ሙሉ አድራሻ ጋር ማዘጋጀት
6.4.3. ለኦ ክፍል ህፃናት የት/ት ማጠናቀቅ ምስክር ወረቀት አዘጋጅቶ ወላጆች ባሉበት በመስጠት
ማስመረቅ
6.4.4. የኦ ክፍል ህፃናት ፖርቲፎሊዮ መረጃ በማዘጋጀት የህፃናት ለውጥ ሂደትን
የመከታተል፤የመደገፍና የመገምገም ስርዓትን መዘርጋት
6.5. የፋይናንስ አጠቃቀምና ሀብት ማጎልበት ስርዓትን ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ
6.5.1. የኦ ክፍልን ትምህርት መሰረት ያደረገ የበጀት አጠቃቀም ተግባራዊ ማድረግ
6.5.2. የኦ ክፍል በጀት አጠቃቀምን የሚያሳይ የገቢና ወጪ ሂሳብ መዝገብ በማዘጋጀት ተግባራዊ
ማድረግ
6.5.3. ለኦ ክፍል ትምህርት ተጨማሪ የሙያ፤የገንዘብ፤የቁሳቁስ፤የጉልበትና የመሳሰሉት ሀብት
የሚገኝበትንና ስራ ላይ የሚውልበትን ስልት ቀይሶ ተግባራዊ ማድረግ
6.6. የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ለኦ ክፍል ትምህርት አሰጣጥ ሂደት አጋርነትን ማሳደግ
6.6.1. ወላጆች የኦ ክፍል ት/ት አሰጣጥ ሂደትን እንዲጎበኙ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ
6.6.2. ወላጆች በህፃናት ት/ት አሰጣጥና አቀባበል ሂደትና ሁኔታ ላይ ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ
ማስቻል
6.6.3. ወላጆች ለልጆቻቸው ትምህርት አሰጣጥ ሂደት የአስተያየትና ቅሬታ ግብረመልሶች
የሚሰጡበት ስርዓት መዘርጋት
6.6.4. ለኦ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ድጋፎች በአካባቢው ህብረተሰብ ተሳትፎና አጋርነት
ተግባራዊ መደረጉን ማረጋገጥ
6.6.5. በኦ ክፍል በሚደራጀው ኮሚቴ ውስጥ ወላጆች እንዲሳተፉ ማስቻል
6.6.6. በኦ ክፍል እቅድ ዝግጅት ላይ የወላጆች ተወካይ እንዲሳተፉ ማድረግ

You might also like