Professional Documents
Culture Documents
የተማሪዎች ምግብ አደራሽ
የተማሪዎች ምግብ አደራሽ
በደ ብ ብ ህ ክ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ግንቦት 2014 ዓም
አርባምንጭ
ማውጫ
ርዕስ ገጽ
2
የፕሮጀክቱ ስም-------------------------------------------------------------------------------------------------3
የፕሮጀክቱ ባለቤት---------------------------------------------------------------------------------------------3
የፕሮጀክቱ ሁኔታ---------------------------------------------------------------------------------------------3
የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት--------------------------------------------------------------------------------------5
ፕሮጀክቱ የሚገኝበት ቦታ -----------------------------------------------------------------------------------6
ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚያስፈልገው ጠቅላላ በጀት-----------------------------------------------6
የፕሮጀክቱ ቆይታ ጊዜ----------------------------------------------------------------------------------------7
-የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች-------------------------------------------------------------------------------------7
የፕሮጀክቱ ዓላማ፣ አስፈላጊነትና የሴክተሩን የልማት ፖሊሲ ለማስፈጸም የሚኖረው ድርሻ:-------------------------9
የፕሮጀክቱ ግቦችና በፕሮጀክቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት-------------------------------------10
የዚህ ፕሮጀክት ባለቤት በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ ሲሆን የተለያዩ
ባለድርሻ አካላትም በፕሮጀክቱ አተገባበር ላይ የጋራ ሚና ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል::
የአርባ ምንጭ ትም/ኮሌጅ በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ ውስጥ እያደገ የመጣውን የአንደኛ ደረጃ መምህራን ፍላጎት
ለማሟላት ታስቦ በ 1980 ዓ.ም የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ሆኖ የተመሠረተ ሲሆን በ 1996 ዓ.ም የክልሉ
መንግስት በአዋጅ ቁጥር 74/1996 በአንቀጽ 37 እና አስፈጻሚና ፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን
በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/1995 አንቀጽ 56 ንዑስ አንቀጽ 1 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ወደ መምህራን ትምህርት
ኮሌጅ ያደገ ተቋም ነዉ::
3
በመሆኑም ይህ ፕሮጀክት ከላይ የተጠቀሱ ችግር በመቅረፍ ሠልጣኞች ውጤታማ ሆነው እንዲዘልቁ ለማስቻል
ወሳኝነቱ አጠያይቅ ጉዳይ ባለመሆኑ ኮሌጁ ራዕውንና ተልዕኮውን በብቃት ለመፈፀም እንዲያስችለው ወሳኝ ግብዓት
ከመሆኑ አኳያ የክልሉ መንግስትም ፕሮጀክቱን በጥንቃቄ ገምግሞ ምላሽ ይሰጣል የሚል እምነት አለን::
በተጨማሪም የተማሪዎችን በኮሌጁ ግቢ የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያገኛሉ ተብሎ ሲታሰብ የተማሪዎች
የሚመገቡበትን የምግብ አደራሽ አብሮ የሚታሰብ በመሆኑ ለተማሪዎች መመገቢያ አገልግሎት በተገቢውን
ማስተናገድ የሚችል አደራሽ በጊዜ ወቅቱን ጠብቆ መገንባት የተማሪዎች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመፍታት በፍኖቴ
ካርታው ከተያዙ ችግሮች ውስጥ የሚካተት ስለሆነ ኮሌጁም ለዚህ አገልግሎት የሚሆን ህንፃ ባለመኖሩ የዚህ ፕሮጀክት
ግንባታ ወሳኝ ነው::
በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ይህ ፕሮጀክት ኮሌጁ ራዕውንና ተልዕኮውን በብቃት ለመፈፀም እንዲያስችለው ወሳኝ ግብዓት
ከመሆኑ አኳያ የክልሉ መንግስትም ፕሮጀክቱን በጥንቃቄ ገምግሞ ተግባራዊ ያደርጋል የሚል ጽኑ እምነት አለን::
4
ከጤና አኳያ
ንፁህ ለመመገቢያ የተመቸ የምግብ አደራሽ መኖር ለአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተ n ም የመማር
ማስተማሩን ሂደትን ጤናማና ሰላማዊ አከባቢ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ንጽህናው የተጠበቀ
ምግብ አደራሽ መኖር ተማሪዎች ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ እጅግ በጣም
አስፈላጊ ነው:: በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በአለማችንና በአገራችን የተከሰተውን የኮሮና ወረርሽኝ ሆነ
ሌሎች ምግብና ውሃ ወለድ በሽታዎች በመከላከል የመማር ማስትማሩን ስራ ለማድከድ አስፈላጊ
ነው::
ከመማር ማስተማር አኳያ
ተማሪዎች ሙሉ ጊዜያቸውን ለመማር ማስተማሩ ስራ በማዋል በትኩረት መማር ሲገባቸው የምግብ
መመገቢያ አደራሽ ያለመኖር ምግብ ላይዘጋጅ ይችላል በዚህ መነሻ ምግብ ፍለጋ ከግቢ ይወጣሉ በዛው
ምክንያት የትምህርት ጊዜ ብክነት ብሎም የተሟላ መስተንግዶ በማጣት ፍለጋ ላልተፈለገ ችግሮች
ልጋለጡ ይችላሉ:: ይህም በአንድ በኩል ለትም/ት ማዋል የሚገባቸውን ጊዜ ያባክናሉ:: በሌላ በኩል
ደግሞ የተሟላ ምግብ ላይገኝ በሚችልበት ወቅት ጥያቄ በማንሳት የመማር ማስተማሩ ሥራ ላይ ጫና
ያሳድራሉ በዚህና በመሰል ምክንያት ፕሮጀክቱ አስፈላጊ ነው::
ከፖሊሲ ለውጥ አንጻር
ቀደም ስል ተማሪዎች ወርሃዊ የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸው ከግቢ ውጭ የሚኖሩ ሲሆን በአዲሱ የትምህርትና
ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሠረት በኮሌጁ ግቢ ውስጥ እየኖሩ የምግብና የመኝታ አገልግሎትን ከግቢ እያገኙ
ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተወሰነ በመሆኑ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የተማሪዎች ምግብ አደራሽ
ወሳኝ ነው::
በተጨማሪም ተ n ሙ ከዚህ ቀደም የተፈቀዱለት ውስን ካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት
በአግባቡ ተጠናቀው አገልግሎ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ተ n ሙ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ከፍተኛ ልምድ
እና ተሞክሮ ያለው ነው:: ይህም የኮሌጁ አመራር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት
እና ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከፍተኛ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ድጋፍ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ልምድ
ያለው ነው:: በመሆኑም ይህ ፕሮጀክት ብጸድቅና ተግባራዊ ብደረግ ጊዜና ውስን የሆነውን ሀብት በአግባቡ
በመጠቀም ለማስፈጸም የሚያስችል በቂ አቅም አለው::
V. ፕሮጀክቱ የሚገኝበት ቦታ :-
ይህ ፕሮጀክት በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት በአ/ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኝ ነው::
የአ/ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በጋሞ ዞን አ/ምንጭ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ከአገሪቱ መዲና አዲስ አበባ በስተ ደቡብ አቅጣጫ
5
505 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከክልሉ መቀመጫ ሐዋሳ ከተማ ደግሞ በ 275 ኪሎ ሜትር በስተደቡብ ምዕራብ
ሆኖ በምስራቅ ኩልፎ ወንዝ በደቡብ የነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በሰሜን ወደ አርባ ምንጭ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
የሚውስደው አስፋልት መንገድ እና በምዕራብ ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ የሚወስደው መንገድ የሚያዋስኑትና ግቢው የቦታ
ስፋትም 119,312.5 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ተቋም ነው::ተቋሙም ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተፈጥሮ ቁሳቁሶች
በከተማ አቅራቢያ የሚገኝ መሆኑ ሌላው እድል ነው፡፡በሌላ በኩል ተቋሙ ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ የሆነ አካባቢ ያለው
ስሆን የአካባቢው ማህበረሰብም ከኮሌጁ ጋር መልካም መስተጋብር ያለው እና ለትምህርትና ስልጠና ሂደት የራሱን
አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም ባሻገር በሀገር ደረጃ የሰላም ተምሳሌት አከባቢ በመሆኑ ተማሪዎች ያለምንም ችግር
ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙበት ተቋም ነው::በተጨማሪም ኮሌጁ በሚገኝበት አከባቢ የሚገኙ አምስት ዞኖችና
ሶስት ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የመምህር እጥረት የሚታይባቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ አርብቶ
አደር አካባቢ የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ትምህርትና ስልጠና የሚያገኙበት ተቋም ነው፡፡
ለዚህ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን በጀት የወቅቱን ተለዋዋጭ የገበያ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ
በቀጣይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት በባለሙያዎች የሚዘጋጅ ሆኖ
አጠቃላይ ፕሮጀክቱ እስከ 50 ሚሊዮን ብር ሊደርስ እንደሚችል የሚገመት ሲሆን በ 2015 ዓ.ም
ተጠናቅቆ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል::
የዚህ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰብ ክፍሎች ሲሆኑ ተጠቃሚዎቹን በጥቅሉ በሁለት ከፍሎ
ማየት ይቻላል:: ይህም
6
በመሆኑም ኮሌጁን በተለየ መልኩ በመሰረት ልማት በኩል ጎድቷል፡፡ነገር ግን በባለፉት ዓመታት ቢሆን ኮሌጁን
በሚለውጥ መልኩ መሰረተ ልማቶች ማስፋፊያ በጀት ተመድቦ በልዩ ሁኔታ መታየት ሲገባው ይህ አልተደረገም፡፡
በመሆኑም ይህ በእንድዳለ ኮሌጁ የመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር መምህራንን እንዲያሰልጥን በአዋጅ የተደገፈ
ኃላፊነት የተሰጠ ሲሆን ይህንን ተልዕኮ በመወጣት የሀገራዊ እራይ ለማሳካት የተጓደሉ መሰረተ ልማቶችን
በማሟላት የትምህርትና ሥልጠናውን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑና ለኮሌጁ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች
አንዱ የሆነውን የተማሪዎች መመገቢያ አደራሽ መገንባት አስፈልጓል፡፡
ስሆነም የመማር ማስተማሩን ስራ ውጤታማ ለማድረግና ብቁ ዜጋ ለማፍራት ለማሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ
ግብዓቶችን በኮሌጁ ውስጥ ማሟላት እንዳለበት የሚታመን ሲሆን በዚሁ መነሻ ይህ ችግር ለመቅረፍ ታስቦ
የተማሪዎች ምግብ አደራሽ ግንባታ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡
የዕቅድ ዝግጅት
የሳይት ዝግጅት ስራ
የኮሌጁ ዲን
6. ታሳቢዎች(Assumption)
ሠልጣኞች ከ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማደሪያ ተሰጥቷቸው ግቢ መኖር የሚጀምሩ መሆናቸው ፣
በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ላይ እንደተመለከተው ትምህርት ኮሌጁ በድግሪ መርሃ
ግብር እንዲያሰለጥኑ መደረጉ፣
ኮሌጁ የተሻለ የፕሮጀክት አፈጻጸም ክትትል ልምድ ያለው መሆኑ፣
የአካባቢው ማህበረሰብና አስተዳደር ጋር ከኮሌጁ ጤናማ የሥራ ግንኙነት በመኖሩ ፕሮጀክቱን
በባለቤትነት ስሜት የሚደግፈው/የሚያየው /መሆኑ፣
ከፋብርካ ዕቃዎች ውጪ ያሉ የግንባታ እቃዎች ቦሌጁ አከባቢ በቅርበት መኖሩ፣
7. ስጋቶች(Risk)
የግንባታ ቁሳቁሶች የዋጋ ንረት መኖር፣
የመንግስት የበጀት አቅም ውስንነት፣
የቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር፣
በተቋራጮች በኩል የሚስተዋል የቁርጠኝነት እና የአፈጻጸም ውስንነት፣
8. የክትትልና ግምገማ ስርዓት(Monitoring & Evaluation)
የኮንስትራክሽን ዘርፍ በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ያለ እና ውስብስብ ሲሆን የተለያዩ ብልሹ አሰራሮችና
ማጭበርበሮች ያሉበት እንደሆነ ይታመናል:: በመሆኑም ተ n ሙ ይህንን ጉዳይ ታሳቢ በማድረግ ከፍተኛ የሆነና
ስልታዊ የክትትልና ግምገማ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ የሚያደርግ ይሆናል:: በተጨማሪም በግምገማው ሂደት
12
የሚገኙ ክፍተቶችን እያረመና አስፈላጊውን የእርምት እርምጃዎች እየወሰደ ዝርዝር እቅድ ተዘጋጅተው
በጥንቃቄ የሚመራ ይሆናል::