You are on page 1of 13

ማውጫ

ርዕስ ገጽ

1. መግቢያ 01

2. የወረዳው ውጫዊ ሁኔታ ትንታኔ


01

3. ውስጣዊ ሁኔታ ትንታኔ


02

4.. የስራ ሂደቱ መርሆች 03

5. የስራ ሂደቱ ዕሴቶች 03

6. የስራ ሂደቱ ራዕይ 04

7. የስራ ሂደቱ ተልዕኮ 04

8. የዕቅድ አጠቃላይ ግብ 04
9. የዕቅድ ዋና ዋና ዓላማዎች 04
10. ግብ አንድ፡- የትምህርት መረጃ ስርዓትን በማጠናከር ተአማኒነት ያለው መረጃ ማዘጋጀትና በወቅቱ ለተጠቃሚዎች

በማቅረብ የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ 05

11. ግብ ሁለት፡- በአገር አቀፍና ፣በክልል ደረጃ የወጡ ፖሊሲዎችን ተመርኩዞ የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ስትራቴጅክ

እቅድ ተዘጋጅቷል 06

12. ግብ ሶስት:- ህ/ሰቡን በት/ቤቶች ጉዳይ ወሳኝና ባለቤት ማድረግ 07

13. ግብ አራት ፡- ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ በቂ የትምህርት ሀብት በማመንጨት

(በማፈላለግ) የሚገኘውን ሀብት ለተማሪዎች ውጤት ማሻሻል ተግባር ላይ ውሏል 08

14. ግብ አምስት፡-በውጤት ላይ የተመሰረተ አንድ ወጥ የሆነ የክትትልና ግምገማ ስርዓት ተዘርግቷል 09

15. ግብ ስድስት፡- የሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ ተከፍሏል የተለያዩ ንብረቶች በመዝገብ ተይዘው ጥቅም ላይ ውለዋል 10

16. ግብ ሰባት፡- የተለያዩ ንብረቶችን ጥቅም ላይ ማዋል 11

2
መግቢያ

3
የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት በአዲሱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ /BPR/ በውስጡ ከተደራጁት 4 ዋና እና 2 ደጋፊ የስራ
ሂደቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የትምህርት መረጃ ስርዓት፤የዕቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ /ማመንጨት/ ስራ አመራር ደጋፊ የስራ
ሂደት ነው ፡፡

በዚህ የስራ ሂደት ከሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አመታዊ የትምህርት ዕቅድና የ 5 ዓመት እስትራቴጅክ እቅድ ማዘጋጀት
የት/ቤቶችን የሥራ ዕንቅስቃሴ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ሩብ አመት እና አመታዊ መሰረታዊ የትምህርት መረጃ ማዘጋጀት፡፡
ህብረተሰቡን በት/ቤቶች ጉዳይ ወሳኝ ባለቤት ማድረግ ሁሉም የህ/ሰብ ክፍል ያሳተፈ በቂ የት/ት ሀብት በማመንጨት
/በማፈላለግ/የሚገኘውን ሀብት ለትምህርት ጥራትና ለተማሪዎች ውጤት ማሻሻል ተግባር ላይ ማዋል&የጽ/ቤቱን በጀት
መከታተል፣ የት/ቤቶች በጀት መደልደልና እንዲጠቀሙበት ማድረግ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ፡፡

የወረዳው ውጫዊ ሁኔታ ትንታኔ


የመተማ ወረዳ በሰሜን ጎንደር ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከርእሰ ከተማ መዲናችን ከሆነችው አዲስ አበባ በ 905
ኪ/ሜ፣ከክልላችን ባህር ዳር ከተማ በ 343 ኪ/ሜ እንዲሁም ከጎንደር በ 158 ኪ/ሜርቃ ትገኛለች፡፡ በአብዛኛው መልክአ ምድሩ
ሜዳማና አልፎ አልፎም ተራሮች ሸለቆዎችና ወንዞች የሚታዩበት አካባቢ ነው፡፡ የአየር ንብረቱም ቆላማ 84.22% ሲሆን
በአማካይ የሙቀት መጠኑ ከ 32-44 ዲግሪ ሴንት ግሬድ ይደርሳል ወይናደጋ 5.88% ነው ፡፡ የመተማ ወረዳ በስተ-ሰሜን
ታች አርማጭሆ፣ በስተ-ደቡብ ቋራ፣በስተ-ምስራቅ ጭልጋና በስተ-ምዕራብ ሱዳን ያዋስኑታል፡፡

የመተማ ወረዳ በ 19 ቀበሌዎች የተከፋፈለች ሲሆን ከዚህም ውስጥ ሦስት ንዑስ ማዘጋጃ ሁለት መሪ መዘጋጃ ቤት ሲሆን ሌሎች
15 ቱ ደግሞ የገጠር ቀበሌዎች ናቸው፡፡ የወረዳውን የህዝብ ብዛት በተመለከተ በገጠር ወ-49308 ሴ-56273 ድ-105581
ሲሆን በከተማ ወ-16988 ሴ-19380 ድ-36368 ነው፡፡ በጠቅላላው የወረዳው የህዝብ ብዛት ወ-73262 ሴ-68687 ድ-
141949 ይገኙበታል፡፡ በዚህም የወረዳው ህዝብ ከ 74.37% በላይ በገጠር ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ወረዳዋም
ጠቅላላ የመሬት ስፋት 440‚085 ሄ/ር ሲሆን የአመቱ የዝናብ መጠን በአማካይ ከ 700-900 ሚ/ሜ ይደርሳል፡፡
አካባቢው ከሱዳን ጋር ድንበር ከመሆኑ የተነሳና ለም መሬትም ስላለው ከሁሉም የአገሪቱ ክፍል የመጡ ህብረተሰቦችን አቅፋ
ይዛለች፡፡ በአካባቢው ከ 5 በላይ ቋንቋ ተናጋሪ ብሔሮች አሏት እነሱም፡- አማርኛ፣አገውኛ፣ጉምዝ ፣ ትግረኛ ፣ ኦሮመኛ ወዘተ
ተናጋሪዎች ይገኙበታል፡፡
የወረዳውን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ስናይ ደግሞ አብዛኛው ህዝብ በግብርና የሚተዳደር ሲሆን፤ጥቂት የማይባለው ህብረተሰብም
በንግድ ይተዳደራል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፈጠረው ምቹ መሰረተ ልማት ሁኔታ ደረቅ ወደብ በመሆን እያገለገለ ላለው
የዩሐንስ ከተማ አስመጪና ላኪዎች በማስተናገድ ከሀገር የሚወጡና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምሮቶችን በማቀባበል ትገኛለች፡፡
በወረዳው የመሰረተ ልማት ግንባታ በኩል ደህና የሚባል እንቅስቃሴ የሚታይበት ሲሆን፤በተለይ የአዘዞ መተማ አስፓልት
መንገድ 5 ቀበሌ በጠጠር 7 ቀበሌ በአጠቃላይ 12 ቀበሌ(63.15%) ዘመናዊ መንገድ አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው ፡፡ በመብራት
አገልግሎት በኩልም የወረዳው 14 ቀበሌዎች(73.68%) 24 ሰዓት አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ ሌሎች ከተሞችን ለማዳረስም የፖል
ተከላው በመሳለጥ ላይ ይገኛል፡፡ የገጠር ከተሞች መንገድ ከወረዳ ጋር ለማገናኘት አቅም በፈቀደ መጠን ደፋ ቀና በመባል ላይ
ይገኛል፡፡
4
በመተማ ወረዳ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ስንመለከት በጤናው በኩል በሁሉም ቀበሌዎች በድምሩ 21 የጤና ኬላ
የተዘረጉ ሲሆን፤5 ጤና ጣቢያዎች፤መካከለኛ ክልኒክ 2 ፤ መለስተኛ ክልኒክ 61 ፤ መዳኒት መደብር 8 ፤ ገጠር መዳኒት ቤት ና
ዲያግኖሲስ ላብራቶሪ 4 ይገኛሉ(100%) ፡፡ የት/ት ተቋማትን ስንመለከት 2 ሀይስኩል 82 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፤42
ሳተላይት እና 05 አፀደ ህፃናት ት/ቤቶች ያሉት ሲሆን ፤የት/ት ሽፋኑን ለሁሉም ለማዳረስ በሁሉም ቀበሌ የት/ት ተቋማት
ተስፋፈተዋል(100%) ፡፡ ውኃ አቅርቦት በኩልም ጥሩ የሚባል ሽፋን ከወረዳው ህዝብ ብዛት 95437 ውሃ ተጠቃሚ ሲሆን
ይህም 79.55% ይሆናል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከበርሀማነቱ አኳያ በአንዳንድ አካባቢዎች የውኃ እጥረት ይስተዋላል፡፡
ወረዳችን በፖለቲካዎ እንቅስቃሴ በኩል ህ/ሰቡን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት በማደራጀትና የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ደፋ
ቀና በማለት ይገኛል፡፡ በተለይ አካባቢው ብዙ ኢንቨስተሮችና ነጋዴዎች የምታስተናግድ ከመሆኗ አንፃር የተቀላጠፈ ስራ ለመስራት
በአዲሱ የስራ ሂደት ለውጥ ሰራተኛው እንዲቃኝና በሁሉም በኩል የማስፋት ስትራቴጅው ተግባራዊ ለማድረግ እና ወደ እድገት ጎዳና
ለማምራት በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

ውስጣዊ ሁኔታ ትንታኔ


በጽ/ቤት 1 ኃላፊ፣2 መ/ ኃላፊ፣4 ዋና ሂደት፣2 ደጋፊ ሂደት፣4 አስተባባሪ(100%) ፣20 (86.95%) ፈፃሚ፣4 ጸሀፊ(80%) ፣ 1 ሹፌር በአጠቃላይ የሰው
ኃይል(87.87%)

8 ኮፒውተር(80%)፣6 ፐሪተር (85.71%)፣ 2 ላፕቶፕ(40%) ፣ 3 መደበኛ ስልክ(75%) ፣ 7 ዘመናዊ ቢሮ ከሞላ ጎደል የተሟላ(73%) ቢሆንም ሙሉ
በሙሉ ተግባራትን በታቀደው መሰረት በተሰጠው የጊዜ መደብ ለማሳካት በሂደታችን መደበኛ ስልክ ፣1 ጠሬጴዛ 1 ኮፔውተር የሚያስፈልገው ነው፡፡

በ 2008 ዓ.ም. የታዩ ጠንካራ ጎኖች ፡- መረጃና ሪፖርት በወቅቱ እየተሰሩ ለሚመለከተው አካል ደርሰዋል፡፡

ደካማ ጎኖች፡- ት/ቤቶች የተጠቀሙ ባቸውን በጀቶች በማጠናከር አስተያየትና ግብረመልስ አለመስጠትና በአካል ተገኝቶ የሂሳብ አስተዳደር
ሥርአታቸውንአለመገምገም፡፡በጠጨማሪ አቋራጭ ተማሪን በአካል በመገኘት ቅስቀሳን አለማስተባበር፡፡ ከነዚህ ድክመቶች በመውጣት የተሻለ
ስራ ለመስራት ይህን ዕቅድ አቅደናል፡፡

የስራ ሂደቱ መርሆች


የትምህርት መረጃ ስርዓት የዕቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ /ማመንጨት /ደጋፊ የስራ ሂደት በአዲስ መልክ ከተደራጀ በኋላ
መሰረታዊ ለውጥ ውጤት ለማምጣት እንዲችል የሚከተሉትን መርሆች እንከተላለን፡፡

ተጠያቂነት /Accountabilty & responsibilty

ተደራሽነት / accessibility/

ሁሉን አቀፍነት /comprehensive/

ተከታታይነት /continuity/

ኢኮኖሚያዊነት /economical/
5
ፍትሀዊነት /equity/

ችግር ፈችነት /problem solving approach /

አሳተፊነት / participatory /

ውጤታማነት /outcome based /

የስራ ሂደቱ ዕሴቶች


ለስነምግባር መርሆች ተገዥ መሆን
ጥራት ያለው ተገልገይ ተኮር አገልግሎት መስጠት
በጋራ የመስራት ባህል ማዳበር
የፈጠራና የምርምር ስራዎች ማበረታታትና ማዳበር
በግልፅና በታማኝነት ላይ የተመሰረተ የቡድን መንፈስ ማጎልበት
አቅምን በማሳደግ በራስ መተማመን
ግልፅነት
ትምህርት መረጃ ስርዓት እቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ /ማመንጨት/ ስራ አመራር ደጋፊ የስራ ሂደት ዓመታዊ እቅድ

የስራ ሂደቱ ራዕይ


ጥራት ያለው የት/ት ልማት መረጃ እና የት/ት ልማት እቅድ ዝግጅት ከማስፈፀሚያው በጀት /ሀብት/ጋር በወቅቱ በደንበኛ እጅ ደርሶ
የት/ት ስርዓቱን በአግባቡ በመደገፍ ብቁ የሆነ የሰው ሀይል ተፈጥሮ ማየት፡፡

የስራ ሂደቱ ተልዕኮ


በት/ት ፖሊሲ ላይ በመመስረት ጥራት ያለውና የህብረተሰቡን ፍላጎት የሚያንፀባርቁ የት/ት ልማት መረጃ ት/ት ልማት እቅድ
በማዘጋጀትና የታቀደውን እቅድ በአግባቡ እንዲተገበር ሀብት በማፈላለግ/በማመንጨት/የት/ት ስርዓቱንና ሂደቱን በመደገፍ የት/ት
ግብዓቶችን እንዲሟሉ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ ውጤታማ በመሆን ሰብአዊ የሆነ ሀብት
ማፍራት ነው፡፡

የዕቅድ አጠቃላይ ግብ
የደንበኞችን ፍላጎት ያረካ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የትምህርት መረጃ ስርዓትና እቅድ ዝግጅት ሀብት ማፈላለግና/ማመንጨት/
በመጠቀም ት/ቤቶች ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ዜጋ በማዳረስ ብቁ ዜጋ ማፍራት ተልዕኮን ማሳካት ነው፡፡
6
የዕቅድ ዋና ዋና ዓላማዎች
የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ለትምህርት ስራ የሚያስፈልጉትን ሀብት ማመንጨትና መመደብ
ሊተገበር የሚችል እቅድ ማቀድና እቅዱን ወደ ተግባር መለወጥ

የደንበኞችን ፍላጎት ያረካ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የት/ት መረጃ ማዘጋጀት

የክትትልና ግምገማ ስራ የአሰራር ስልቶች መጠቀም

በሰፊው የህዝብ 1 ኛ ደረጃ ት/ትን ለሁሉም ማዳረስ

ት/ቤቶች የበቁ ማፍሪያ ማድረግ

በት/ቤቶች ህ/ሰቡን ወሳኝና ባለቤት ማድረግ

የ 2009 ዓ.ም አጠቃላይ እቅድ

ግብ አንድ

የትምህርት መረጃ ስርዓትን በማጠናከር ተአማኒነት ያለው መረጃ ማዘጋጀትና


በወቅቱ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ፡፡

ተግባር 1፡-

ከክልል/ዞን የሚላከውን የትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ቅፅ በተጨማሪ


ሌሎች የመረጃ መሰብሰቢያ ቅፅ በማዘጋጀት ወረዳ አቀፍ የትምህርት
መረጃ መሰብሰቢያ ቅፅን ተዘጋጅቷል፡፡ በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ
ቅፅ መሰረት ስልጠና በመስጠት ከትምህርት ተቋማት እስከ ጽ/ቤት
መረጃዎች በአግባቡ መሰብሰብ

7
ተግባር 2፡-
የወረዳውን ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት በመዘርጋት ወቅታዊና ዓመታዊ
መረጃዎች ተሰብስበው ተተንትነው ተጠናክረው የተጠናከረ አገልግሎት
መስጠት ይቻል ዘንድ ለመረጃ መሰባሰብ የሚያገለግሉ ፎርማቶችን፣
የትንተና የመረጃ ቅንብርና የሪፖርት አቀራረብ ዘዴዎችንና ስልቶችን
በሚመለከት አዳዲስ አሰራሮች ማፍለቅ
ተግባር 3፡-

ዓመታዊ የት/መረጃ ሪፖርቶች ሳምንታዊ የሁለተኛ ና የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች


መረጃ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማድረስ፡፡የትምህርት መረጃዎችን
በማጠናከር ት.ስ.መን ማዘጋጀት

ተግባር 4፡-
ተቋማት የየራሳቸውን መረጃ ለማዘጋጀትና ለመጠቀም እንዲሁም
መረጃውን ለሚፈልጉ አካላት ዝግጁ የሚያደርጉበት ስርዓት በመዘርጋት የፈፃሚዎችን ውሳኔ
ሰጭነት ማጎልበት፡፡

ግብ ሁለት፡-

በአገር አቀፍና ፣በክልል ደረጃ የወጡ ፖሊሲዎችን ተመርኩዞ


የረጅም የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ስትራቴጅክ እቅድ ተዘጋጅቷል

ተግባር 1 ፡-
በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ውስጥ ያሉ ሁሉም የስራ ሂደቶች
በወጣው የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጅ ተመርኩዘው አመታዊ
የፊዚካልና የፋይናንስ እቅድ አውጥተው ወደ ስራ ማስገባት
ተግባር 2-
ለእቅድ ዝግጅት የሚያስፈልጉ የፖሊሲ ስትራቴጅና የረጅም ጊዜ እቅድ
ሰነድና የጥናት ውጤቶችን ማሰባሰብና መረጃ ማደራጀት
8
ተግባር 3 ፡-
የመደበኛና ካፒታል በጀት ዝግጅት ፣ድልድል ፣ስርጭትና ክትትል ማድረግ ተችሏል፡፡
ተግባር 4፡-
በዘመኑ በትምህርት ዘርፍ በወጣው መርሃ ግብር መሰረት ሙሉ
በሙሉ እቅዱ የሚያስፈፅምና ውጤታማ ሊያደርግ የሚችል የበጀት
ሠነድ ተዘጋጅቷል፡፡
ግብ ሶስት ፡

ህ/ሰቡን በት/ቤቶች ጉዳይ ወሳኝና ባለቤት ማድረግ

ተግባር 1 ፡-

በት/ቤቶች አመራር ህዝቡ የሚሳተፉበትን አደረጃጀት መፍጠር

ተችሏል፣ ት/ቤቶች በግንባታ ጥገናና ማስፋፋት ህ/ሰቡ ዋነኛውን ወጪ እንዲሸፍን ማድረግ

ተግባር 2፡-

ት/ቤቶች የውስጥ ገቢ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ጥረት

ተደርጓል፣ተጨማሪ ሀብት የሚመነጩበት የተለያዩ ስልቶች በመጠቀም

በቂ ሀብት እንዲገኝ ጥረት ማድረግ

ተግባር 3፡-

ህ/ሰቡ (ተማሪዎች መምህራን የአካባቢ ኑዋሪ ህዝብ) በት/ቤቶች ጉዳይ

ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በአተገባበርና በግምገማ መሳተፍና መወሰን

መቻላቸውን ማስገንዘብ

ተግባር 4 ፡-

ህ/ሰቡ በት/ቤት የሚተገበረውን ካሪኩለም በሚደግፍ መልኩ

የሚሳተፉበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ት/ቤቶች በሚያዘጋጁት ዓመታዊ

የምክክር መድረኮችና ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ መገኘት

እንዲችሉ ማድረግ፡፡

9
ግብ አራት ፡-

ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ በቂ የትምህርት

ሀብት በማመንጨት (በማፈላለግ) የሚገኘውን ሀብት

ለተማሪዎች ውጤት ማሻሻል ተግባር ላይ ውሏል፡፡

ተግባር 1

ከአካባቢው ማኅበረሰብና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚገኘውን

ሀብት በአግባቡ ት/ቤቶች እንዲጠቀሙ ማድረግ

ተግባር 2

ውጤታማ ፤ብክነትን ያስወገደ ወጭ ቆጣቢ የሆነ ኃላፊነትንና

ተጠያቂነትን ያሰፈነ የሀብት አጠቃቀም ስርዓት ተዘርግቶ የደንበኞችን ፍላጎት ማርካት፡፡

ተግባር 3

ከመያድ የሚቀርቡ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ላይ አስተያየት በመስጠት


በፕሮጀክት ፕሮፖዛል የውል ስምምነት ማድረግ፣ በመያድ ፕሮጀክቶችን
ማሻሻያ የጊዜ ማራዘሚያ ጥያቄዎች ላይ አስተያየት መስጠትና የተጠናቀቁ
መያዶች ፕሮጀክቶችን ንብረት የተሰሩ ስራዎች በአግባቡ ርክክብ መፈፀም
ተግባር 4
ከህብረተሰቡ ከረድኤት ሰጪ ድርጅቶች ከአካባቢ ተወላጆች ወዘተ
ሀብትን በማሰባሰብ ወደ አንድ ቋት ማስገባትና ይህን ከተለያዩ ምንጮች
የተገኘን ሀብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ድልድል መፈፀም

ተግባር 5
በወረዳው ለተማራዎች በቀመር የሚመደበውን የ 2008 ዘመን
መደበኛ በጀት ክትትል በማድረግ ተገቢ የማሻሻያ ሀሳብ ማቅረብ

10
ግብረመልስ ለሚመለከታቸው መስጠት፡፡
ግብ አምስት ፡-

በውጤት ላይ የተመሰረተ አንድ ወጥ የሆነ የክትትልና

ግምገማ ስርዓት ተዘርግቷል፡፡

ተግባር 1፡

 ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የእቅድ አፈፃፀሞች ያላቸውን ተቋማት በመለየት


የሚበረታቱበትና የሚሻሻሉበትን መንገድ መፍጠር

ተግባር 2 ፡-

 ት/ቤቶች ተልዕኮአቸው በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን የት/ቤት


ሀብት ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ

እየተጠቀሙበት መሆኑ ክትትል ማድረግ፣

ተግባር 3 ፡-

 የመስክ ግምገማ ሪፖርት ማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ


መልስ በመስጠት የማሻሻያ ስራ መስራት፡፡

ተግባር 4 ፡-

 የተሰበሰቡ ሪፖርቶችን በማጠናከርና መልክ በማስያዝ በጽ/ቤቱ ስራ


አመራር ማስገምገምና በተሰጠው አስተያየት መሰረት አጠናክሮ

ለሚመለከተው አካል ሪፖርት መላክ ፡፡

ግብ ድስት ፡-

የሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ ተከፍሏል የተለያዩ

11
ንብረቶች በመዝገብ ተይዘው ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

ተግባር 1 ፡-

 በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ የሆነ (የተሰበሰበው ሂሳብ) በትክክል ወደ


ሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ የተወራረሰ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

ተግባር 2፡-

 እያንዳንዱ ወጭ በወጭ ሰነድ መሂ/7 የተከፈለ እንዲሆን የወጪ ተቀጽላ በአግባቡ እንዲያዙና
በሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ የተወራረሰ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ተግባር 3 ፡-

 ሠራተኞች የተፈቀደላቸው ደመወዝ በትክክል በፔሮል እየተመዘገበ


በሰሩበት ቀን ክፍያ እንዲከፈልና ያልሰሩበት ቀን ደመወዝና ከደመወዝ

የሚቀነሱ ክፍያዎች ህጋዊ መሆናቸው በማረጋገጥ ለሚቀነስባቸው

ግለሰቦች በወቅቱ አውቀውታል

ተግባር 4 ፡-

 በግዥና በርዳታ ወይም በስጦታ የተገኙ ንብረቶች በትክክል ወደ


ሚመለከተው አካል ማድረስና በሞዴል 19 ገቢ ተደርገዋል ፡ገቢ

የተደረጉ ንብረቶችም በሞዴል 20 ወጪ እየሆኑ ጥቅም ላይ ማዋል

ተግባር 5 ፡-

 ት/ቤቶች የባንክ ሂሳብ እንዲኖራቸው በማድረግና ሂሳቡን


የሚያንቀሳቅሱ ግለሰቦችም ህጋዊ በመሆናቸው የባንክ ሂሳቡ በትክክል

ለተፈለገው ዓላማ ማዋል

ተግባር 6፡-

 በስራ ሂደቱ ለልዩ ልዩ ተግባራት ማከናወኛ የሚመደቡትን የስራ


መሳሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውንና በእንክብካቤ መያዛቸውን

ማረጋገጥ፡፡ ያልተከናወኑ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰሩ

ማድረግ
12
ግብ ሰባት፡-

የተለያዩ ንብረቶችን ጥቅም ላይ ማዋል

ተግባር 1፡-

 የተጨመረ ወይም የተቀነሰበት በጀት ካለ በየጊዜው በማጣራት የተስተካከለ በጀት በትክክል በመያዝ
ለአስፈላጊ ተግባራት ማዋል

ተግባር 2፡-

 በግዥና በርዳታ የተገኙ ንብረቶችን ( ዩኒፎርም ፣ ደብተር፣ጫማዎች፣እስክርቤቶ ወ.ዘ.ተ) በትክክል ወደ


ሚመለከታቸው አካል እንዲዳረስ ማድረግ

ተግባር 3፡-

 የስራ ሂደቱ አፈፃፀም በወቅቱ በማዘጋጀት ሪፖርት ማቅረብና ላልተከናወኑ ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ
መስራት

መረጃ ሀብት ነው !!!

13

You might also like