You are on page 1of 8

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ

ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

የ 2016 በጀት ዓመት ለወረዳ 10 ካስኬድ


የተደረገ ዕቅድ

Table of Contents
ነሐሴ
23፤
1
ክፍል ሶስት......................................................................................................................................................2
3.ዋና ዋና ስትራቴጂክ ግቦች እና ዓላማዎች................................................................................................................2
3.1.ዋና ዋና ግቦች እና የየዙት ዒላማ ብዛት.......................................................................................................2
3.2.የአበይት ግቦች ዒላማ እና ዝርዝር ተግባራት.................................................................................................3

ክፍል ሶስት
3.ዋና ዋና ስትራቴጂክ ግቦች እና ዓላማዎች
3.1.ዋና ዋና ግቦች እና የየዙት ዒላማ ብዛት

ግብ-1.ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፣የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበት፤(15%)

 የዒላማ ብዛት 5

2
ግብ-2. ደንብ መተላለፍን የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር የንድፈ ሃሳብ ስልጠና መስጠትና የህብረተሰቡን ግንዛቤ
ማሳደግ፤(35%)

 የዒላማ ብዛት 3

ግብ-3.የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን መከታተል፣መቆጣጠርና እርምጃ መውሰድ፤(45%)


 የዒላማ ብዛት 4

ግብ-4.የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት፤(3%)

 የዒላማ ብዛት 1

ግብ-5.የአገልግሎት አሰጣጡን ሽፋን፣ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ የተገልጋይ እርካታን ውጤታማነት


ማሻሻል፤(2%)

 የዒላማ ብዛት 1

አጠቃላይ እንደ ክፍለ ከተማችን የ 2016 ዓ.ም ዕቅድ 5 ዋና ዋና ግቦች እና 14 ዒላማዎች አሉት፡፡

3.2.የአበይት ግቦች ዒላማ እና ዝርዝር ተግባራት


ግብ 1.ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፣የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበት፤(15%)

ዓላማ 1.የዕቅድ ዝግጅት፣ የክትትልና ግምገማ እና የስታቲስቲክስ መረጃ አስተዳደር አሰራር ማሻሻል፤ (1%)

ተግባር 1፡-12 ጊዜ ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ ሪፖርት ማዘጋጅት፤

ተግባር 2፡-365 ጊዜ እለታዊ ሪፖርት ማዘጋጀት፤

ተግባር 3፡-የእቅድ ዝግጅትና የአፈፃፀም ግምገማ ዙሪያ 4 መድረክ በማዘጋጀት 6 አደረጀጃቶችን፣23 ባለድርሻ
አካላትን፣የተቋሙን አመራሮችና ሰራተኞች በድምሩ 170 አካላትን ማሳተፍ፤

3
ዓላማ 3.የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር አሰራርንና ውጤታማነትን ማሻሻል፤(3%)

ተግባር 1፡-የመንግስት ሀብት እና ንብረት አያያዝን 100% ማሳደግ፤


ተግባር 2፡-ከደንብ ተላላፊዎች ከቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ 4 ጊዜ ኦዲት መደረጉን ክትትል ማድረግ፤
ተግባር 3፡-ከደንብ ተላላፊዎች ከቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ የተገኘ ብር ወደ ፋይናንስ ገቢ መሆኑን 100%
ማረጋገጥ፤
ተግባር 4፡-ህግና ስርአትን በመከተል የተወረሱ ንብረቶችን 100% በጨረታ እንዲሸጡ ማድረግ እና የማይሸጡ
መሆናቸው የተረጋጋጡትን እንዲወገዱ ማድረግ፤
ዓላማ 4.የኢንፎርሜሽን፣ኮሙኒኬሽን እና ቴክኖሎጂ አሰራርንና ውጤታማነትን ማሻሻል፤(2.5%)
ተግባር 1፡-በፅ/ቤቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ መረጃዎችን በሀርድና በሶፍት ኮፒ 100% ማደራጀት፤

ተግባር 2፡-የደንብ መተላለፎችን ለመቆጣጠርና እርምጃ ለመውሰድ እንዲያስችል በሁሉም ወረዳዎች በመገናኛ በሬድዮ
የታገዘ ቁጥጥር 100% ማድረግ፤(የመገናኛ ሬድዮ ሲሰጥ የሚሰራ)

ዓላማ 7.የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና የክትትል ሥራዎችን ማሻሻል፤(1%)


ተግባር 1፡-ለብልሹ አሰራርና ለስነ-ምግባር ጉድለት የሚያጋልጡ ችግሮችን በመለየት 1 ማክሰሚያ ሰነድ ማዘጋጀት፤
ተግባር 2፡-የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን ፈጻሚና አመራሮች በመለየት 100% ተገቢውን እርምጃ መውሰድ፣
ዓላማ 9.የበጎ አድራጎት እና የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን ማሻሻል፤(2%)
ተግባር 1፡-5 የሚሆኑ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን መደገፍ፤
ግብ 2.ደንብ መተላለፍን የሚጸየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር የንድፈ ሃሳብ ስልጠና መስጠትና የህብረተሰቡን
ግንዛቤ ማሳደግ፤(35%)
ዓላማ 1.ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት ደንብ መተላለፍን የመከላከል ተሳትፎውን ማሳደግ፤(%)

ተግባር 1፡-በቅድመ መከላከል ደንብ መተላለፍ ላይ የሚሰሩ የበጎ ፈቃደኞችን ቁጥር በ 16 መጨመር፡፡
ተግባር 2፡-2 ጊዜ ለበጎ ፍቃደኞች ግንዛቤ መፍጠር፤
ተግባር 3፡-በደንብ መተላለፍ ዙሪያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚረዳ 2 ሰነድ ማዘጋጀት፤
ተግባር 4፡-በባለስልጣኑ አዋጅ፣ደንብ፣መመሪያዎች ለ 380 የህብረተሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት በመድረክ ግንዛቤ
መፍጠር፤
ተግባር 5፡-ለ 4,303 የተለያዩ አደረጃጀቶችን እና የብሎክ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ በባለስልጣኑ
አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ግንዛቤ መስጠት፤

4
ተግባር 6፡-በቤት ለቤት እና በቡና ጠጡ በባለስልጣኑ አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ለ 2,435 የህብረተሰብ ክፍል
ግንዛቤ መስጠት፤
ተግባር 7፡-የንቅናቄ መድረኮችን በመጠቀም በባለስልጣኑ አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ለ 8,715 የህብረተሰብ ክፍል
ግንዛቤ መስጠት፤
ተግባር 8፡-10 ጊዜ በሞንታርቦ በአደባባይ ሁነቶች ላይ ለህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር፤
ተግባር 9፡-በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች አዲስና ነባር ክበባትን በመጠቀም ለ 7,119 በደንብ መተላለፍ በተለይም
በአዋኪ ድርጊት ዙሪያና በተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ዙሪያ ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር፤
ተግባር 10፡-በባስለልጣኑ አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎች ላይ 11,753 ብሮሸርና በራሪ ጹሁፍ በማዘጋጀት ማሰራጨት፤
ተግባር 11፡-1 ጊዜ የግንዛቤ ማስጨበጫ የፋይዳ ግምገማ ማድረግ፤
ዓላማ 2.የድጋፍ፣የክትትል እና የሱፐርቪዥን ስራዎችን በመስራት የግብረ መልስ ሽፋንን ማሳደግ፤(%)
ተግባር 1፡-ከበጎ ፍቃደኞች የሚመጡ ጥቆማዎችን በመቀበል ለሚመለከተው አካል በማስተላለፍ ተፈፃሚነቱን ክትትል
ማድረግ፤

ዓላማ 3.የንድፈ ሀሳብና የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የመፈፀምና የማስፈፀምን አቅም ማሳደግ፤(%)
ተግባር 1፡-1 ጊዜ የስልጠና ፍላጎት ዳሳሳዊ ጥናት ማድረግ፤
ተግባር 2፡-2 ጊዜ በወረዳ ለሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች የእውቀትና የክህሎት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፤
ግብ 3.የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን መከታተል፣መቆጣጠርና እርምጃ መውሰድ፤(45%)
ዓላማ 1.የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተል፣በመቆጣጠርና እርምጃ በመውሰድ የደንብ
መተላለፍን መቀነስ፤(25%)
ተግባር 1፡-በቦታ ----- በካሬ ------ መሬት ባንክ የገቡ እና ርክክብ የተደረገባቸዉን ቦታዎች 100% መጠበቅ፤
ተግባር 2፡-በ 46 ህገ-ወጥ ግንባታን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 3፡-በ 9 በህገ-ወጥ የመሬት ማስፋፋትን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 4፡-በ 1800 ህገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 5፡-በ 47 ህገ-ወጥ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 6፡-በ 10 ህገ-ወጥ የእንስሳት ዝውውር፣እርድና ሽያጭን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 7፡-በ 151 ህገ-ወጥ መንገድ አጠቃቀምን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 8፡-በ 22 አዋኪ ድርጊቶችን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 9፡-በ 2458 ህገ-ወጥ ማስታወቂያን በመቆጣጠር እርምጃ መውሰድ፤
ተግባር 10.10 ጊዜ የመስክ ስምሪት፣ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ተግባራት አሰራሩን ተከትሎ መፈፀሙን በመከታተል
የታዩ ችግሮችን በመለየት ለችግሮቹ የመፍትሄ ስልት መንደፍ፤

5
ተግባር 11፡-10 ጊዜ በመፍትሄዎቹ ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተግባራዊ መደረጉን መከታተል፤
ተግባር 12፡-4 ጊዜ ውጤቱን መገምገም፤
ተግባር 13፡-10 ጊዜ ኦፕሬሽን የሚደረግበትን ቦታ በመለየትና በማረጋገጥ በደንብ መተላለፍ የተሳተፉ ግለሰቦችና
ድርጅቶችን መረጃ በልዩ ሁኔታ እና በሚስጥር በማደራጀት ኦፕሬሽኑን ለመፈፀም የሚያስችል የሰው
ኃይልና ሎጀስቲክ ዝግጅት ማድረግ፤
ተግባር 14፡-10 ጊዜ የኦፕሬሽኑን ሂደት በመምራት በኦፕሬሽን ወቅት የሚወረሱ ንብረቶችን ወደ ሚመለከተው ክፍል
ገቢ ማድረግ፤
ተግባር 15፡-10 ጊዜ የኦፕሬሽኑን አፈፃፀም መገምገም፤

ዓላማ 3.የእጩ ኦፊሰሮች ምልመላና መረጣን በማስተቸት ብቃታቸው የተረጋገጠ ኦፊሰሮችን መመልመል፤(2%)

ተግባር 1፡-1 ጊዜ ለዕጩ ኦፊሰሮች በምልመላና መረጣ መስፈርት መሰረት እንዲከናወን ኦሬንቴሽን በመስጠት
ተግባራዊነቱን በመስክ ማረጋገጥ፤
ተግባር 2፡-1 ጊዜ ለዕጩ ኦፊሰሮች የመስተቸት ተግባር መከናወኑን ማረጋገጥ፤
ተግባር 3፡-1 ጊዜ የምልመላው፣መረጣና ማስተቸት ሂደት ሪፖርት ማዘጋጀት፤

ዓላማ 4.በሰርቪላንስ የደንብ መተላለፍ ቅድመ ልይታ እና ጥናት በማካሄድ የእርምጃ አወሳሰድን አቅም ማሳደግ፤(5%)
ተግባር 3፡-በደንብ መተላለፍ የተሳተፉ ግለሰቦችና ድርጂቶችን መረጃ 100% በማደራጀት ለሚመለከተው አካል
ማስተላለፍ፤
ግብ 4.የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት፤(3%)

ዓላማ 1.ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራና በትብብር መስራት፤(3%)

ተግባር 1፡-ከ 23 ባለድርሻ አካላት ጋር የትስስር ሰነድ በመፈራረም በትብብር መስራትና በየሩብ አመቱ መገምገም፤
ተግባር 2፡-ከፀጥታ ተቋማት ጋር በየሩብ ዓመቱ በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን መገምገም፣
ተግባር 3፡-ከአጎራባች ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ጋር በየወሩ በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን መገምገም፤
ተግባር 4፡-የተጣለባቸውን ቅጣት በማይፈጽሙ ደንብ ተላላፊዎች ላይ 100% መረጃ በማደራጀት ለፍትህ ጽ/ቤት
ማቅረብ፤
ተግባር 5፡-ለፍትህ ጽ/ቤት የቀረቡ ፋይሎች ውሳኔ ማግኘታቸውን 100% መከታታል፤
ተግባር 6፡-በመሬት ወረራ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን መረጃ በማደራጀ ለሚመለከተው አካል በመላክ በሊዝ አዋጁ
100% ተጠያቂ እንዲሆኑ ማስደረግ፤
ተግባር 7፡-የመንገድ ላይ ልመናን ለመከላከል ከሴቶች፣ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጋር 100% በቅንጅት መስራት፤
ተግባር 8፡-የአደጋ መከላከል ስጋት ቅነሳና ቁጥጥር ስራዎችን ከሚመለከተዉ አካል ጋር 100% በቅንጅት መስራት፤

6
ተግባር 9፡-10 የአደባባይ ኩነቶች እና በአላት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የድንብ መተላለፍ
እንዳይሳፋፋ በጋራ መስራት፤
ግብ 5.የአገልግሎት አሰጣጡን ሽፋን፣ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ የተገልጋይ እርካታን ውጤታማነት
ማሻሻል፤(2%)
ዓላማ 1.የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን ማሳደግ፤(2%)
ተግባር 1፡-2 ዋና ዋና እና 9 ዝርዝር አገልግሎቶችን በስታንዳርዱ መሰረት በመስጠት፤
ተግባር 2፡-የህብረተሰብ እርካታ ከ 64% ወደ 66% ማድረስ፤
ተግባር 3፡-በተሰጡ አገልግሎቶች የተገልጋይ እርካታ 66% ማድረስ፤
ተግባር 4፡-1 ምርጥ ተሞክሮ መለየት፣መቀመር እና ማስፋፋት፤
ተግባር 5፡-1 ጊዜ የልምድ ልውውጥ ማድረግ፤
ተግባር 6፡-ከህብተሰቡ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን 100% መቀበልና መፍታት፤
ተግባር 7፡-ከህብተሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን 100% መቀበልና መፍታት፤

7
/
በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለ ስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ ቤት

የ 2016 በጀት ዓመት ከመሪ ዕቅድ ውስጥ ለወረዳ 10 ካስኬድ ተደርጎ የተሰጠ በበጀት ዓመቱ በክፍለ ከተማው የሚተገበሩ ግቦች ፤አላማዎችናዝርዝር ተግባራት

ዕቅዱን ያወረደው ኃላፊ፡-አቶ ዳኜ ሂርጳሳ ዕቅዱ የወረደለት ኃላፊ፡-አቶ ሳጅን ንጉሴ ገመቹ

ኃላፊነት፡-የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ኃላፊነት፡-የወረዳ 10 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ

ፊርማ፡…………………………………. ፊርማ፡………………………………….
ቀን፡ 23/12/2015 ዓ.ም ቀን፡ 23/12/2015 ዓ.ም

You might also like