You are on page 1of 6

1.

መግቢያ
መምሪያው በ 2010 ዓ.ም ባዘጋጀው አመታዊ እቅድ መሰረት ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ የተለያዩ ሥራዎችን
አከናውኗል፡፡

የመምሪያው የቁልፍ ስራዎች፤አበይት ተግባራት ፤ ያጋጠሙ ችግሮች፤ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችና ቀጣይ ትኩረት
አቅጣጫ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2. የቁልፍ ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ


የመምያው 2010 ዓ.ም የቁልፍ ሥራዎች ዕቅድና አፈጻጸም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የመምሪያውን ዕቅዶች ሠራተኞች የለውጥ ተግባራትን በመምሪያ ደረጃ ለመተግበር በተያዘው ዕቅድ መሰረት በመምሪያው
ያለው የ 1 ለ 5 ቡድን እለታዊ እና ሳምንታዊ እቅድ በማዘጋጀት በየሳምንቱ እየተገናኘ ተወያይቷል፡፡ በ 1 ለ 5 መድረክ
ያጋጠሙ ችግሮች ተነስተው መፍትሄ እንዲሰጥባቸው ተደርጓል፡፡ በ 1 ለ 5 ቱ መፍትሔ ያልተገኘባቸው ሀሳቦች ከመምሪያው
ጋር በመወያየት መፍትሄ አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ከኮርፖሬት ተቋማዊ ለውጥና አቅም ግንባታ መምሪያ የሚመጡ የ ISO
አሰራሮች እና ቅጾች መሰረት ሥራዎች ተከናውኗል፡፡

በሰው ሀብትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ላይ የሚስተዋሉ ቅጥር፤ዝውውርና ደረጃ እድገት ክፍተቶችን ለይቶ እገዛና
ድጋፍ ለማድረግ የአሰራር ሂደት ጥናት ሥራ በማካሄድ ለማናጅመንት ውሳኔ ለማቅረብ እቅድ ተይዞ፤-
የአሰራር ሂደት ጥናቱ 70% ተከናውኖ ቀሪው 30% በ 2011 በጀት ዓመት ለማከናውን ተላልፏል፡፡

አመራሮችና ሰራተኞች በኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት ላይ ያላቸውን አመለካከትና ክህሎትን


እንዲያሳድጉ የስነ-ምግባር መርሆችን በማወያየት ግንዛቤ የማስፋት ሥራ ለማከናወነወ እቅድ ተይዞ፡-

የአመለካከት እና የግንዛቤ እጥረቶችን መሙላት የሚያስችል 2 ስልጠና /በኘርሰናል ሊደርሺኘ የተጀመረውን


መጨረስ/ እንዲሁም በኢቲካል ሊደርሽኘ/ዙሪያ ለከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና መስጠት በሚለው ተግባር
መሰረት ለ 60 ለሚሆኑ የሥራ መሪዎች በኢቲካል ሊደርሽኘ ርዕስ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ የፐርሰናል ሊደርሺፕ
ስልጠና በየዲስትክቶችና ፕሮጀክቶች ያሉ የሥራ መሪዎች ጭምር እንዲወስዱ የታሰበ ስለነበር ከሥራ ጫና እና
ከቦታ ርቀት የተነሳ ሁሉንም ማሰባሰብ አዳገች በመሆኑ በቀጣይ በጀት ምቹ ሁኔታ በማመቻቸት ለመስጠት
ታስቦ ተላልፏል፡፡

1164 የ 1 ለ 5 ቡድን መሪዎች በመጠቀም በተመረጡ ከ 12 ቱ የሥነ-ምግባር መርሆች በማስተማር ከኪራይ


ሰብሳቢነት ጋር የተያያዙ የአመለካከት ክፍተቶችን ለመድፈን ጥረት ማድረግ በሚለው ተግባር መሰረት 1213
የ 1 ለ 5 ቡድኖች በሥራ መሪዎችና በሰራተኞች የሥነ-ምግባር መመሪያ ላይ እንዲወያዩ በማድረግ ሰፊ ግንዛቤ
የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል፡፡

ከካውንስሉ ጋር በመመካከር የኪራይ ሰብሳቢነት እሳቤ በተመለከተ 1 ትምህርታዊ ስልጠና መስጠት በሚለው
ተግባር መሰረት በኪራይ ሰብሳቢነት እሳቤ ዙሪያ Rent Seeking practices በሚል ርዕስ አንድ ትምህርታዊ
ሥልጠና ለ 34 ለሥራ መሪዎችና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

1
የመምሪያው ሥራ በአግባቡ ለማከናወን እንዲቻል የመምሪያውን አደረጃጀት ለማሻሻል 1 ጥናት አዘጋጅቶ
በማፀደቅ የሰው ኃይልና ግብአት እንዲሟላ ለማድረግ በተያዘው ዕቅድ መሰረት ጥናቱን በማጠናቀቅ በጥናቱ
መሰረት ለመምሪያው የሰውኃይልና ግብአት እንዲሟላ ተደርጓል፡፡

3.የዐበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ


የመምሪያው ዐበይት ተግባራት ዕቅድና ክንውን እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሀብት በአግባቡ ለተፈለገው አላማ መዋሉን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊነትን የተላበሰ
ጠንካራ ክትትልና የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ለማድረግ እቅድ ተይዞ

የውስጥና የውጪ ኦዲት ግኝቶችን በመከታተል 2 መረጃዎችን ሰብስቦ ማደራጀት በሚለው ተግባር መሰረት
ለመምሪያው በግልጭ የተላኩ 17 የሚሆኑ የኦዲት ሪፖርቶች ተቀብሎ በማደራጀት አፈፃፀሙን የመከታተል
ሥራ ተከናውኗል፡፡

በኦዲት አስተያየት የተሰጡባቸውን 2 ጉዳዮች ከካውንስሉ ጋር በመሆን በወቅቱ እንዲፈፀሙ በቅርበት


በመከታተል ድጋፍ እና ዕገዛ ማድረግ በሚለው ተግባር መሰረት በተለይ ከሙስና ጋር በተያያዘ በኦዲት አስተያየት
የተሰጡባቸው 2 የሚሆኑ የኦዲት ግኝቶች በወቅቱ እንዲፈፀሙ የመከታተል ሥራ ተከናውኗል፡፡

12 ቱን የሥነ ምግባር መርሆችን በማስተማርና በማወያየት የኮርፖሬሽኑ አመራርና ሠራተኛ በሥነ-ምግባር የታነፀና ሙስናን
የሚፀየፉ እንዲሆኑ መርሆዎችን የማስረጽ ሥራ ለማከናወን እቅድ ተይዞ፡-
የአመለካከትና የግንዛቤ እጥረቶችን ለመሙላት የሚያስችል 1 በስነ-ምግባርና በሙስና ዙሪያ ስልጠና
ለሠራተኞች መስጠት በሚለው ተግባር መሰረት 1500 ለሚሆኑ በኘሮጀክትና ዲስትክቶች ለሚገኙ
ሰራተኞችና የሥራ መሪዎች በሙስና እና ብልሹ አሰራር ማክሰሚያ ስልቶች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ የሥራ
መሪዎችና ሰራተኞች የሥነ-ምግባር መመሪያ በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርታዊ ስልጠና
ተሰጥቷል፡፡

ለዋናው መ/ቤትና በዘርፎች ለሚገኙ ሠራተኞች የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ ምንነትና
አስፈላጊነትን እንዲሁም አፈጻጸምን በሚመለከት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት በሚለው ተግባር
መሰረት በዋናው መ/ቤት ለሚገኙ ሰራተኞች የኮርፖሬሽኑ የስድስት ወር አፈፃፀም በሚቀርብበት ወቅት የተቀናጀ የሙስና
መከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ ምንነትና አስፈላጊነትን እንዲሁም መልካም ሥነ-ምግባር ለሰራተኞች እና ለሥራ መሪዎች ግንዛቤ
ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን በበራሪ ጹሑፍ መልክ በማዘጋጀት ተከናውኖ ለሰራተኛው እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡

የመምሪያው ሠራተኞች ከሙያቸው ጋር የተገናኘና አቅም ለመገንባት የሚያስችል ማኔጂንግ ኦርጋናይዜሽናል


ኤቲክስ፣ ኮንፍሊክት ማኔጅመንት እና ሬንት ሴኪንግ ፕራክቲስ በሚሉ ርዕሶች ስልጠናዎችን እንዲወስዱ
በማድረግ የተሻለ አቅም እንዲፈጥሩ ከማናጅመንት ኢንስቲቱትና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ጋር ግኑኝነት
ተደርጎ በዩንቨርሰቲው የስልጠና ዕቅድ መሰረት ከሚያዚያ 1-3 managinig organizational ethics፤ ከሚያዚያ 3-6
confilict management እና Rent seeking practices በሚሉ ርዕሶች ላይ ቁጥራቸው 34 ለሚሆኑ ከመምያው
ባለሙያዎች፤ ከዋና መ/ቤት፤ከየፕሮጀክትና ከየዲስትሪክት የተወጣጡ የሥራ መሪዎች ስልጠናዎችን እንዲያገኙ
ተደርጓል፡፡

2
በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎችና የስነ-ምግባር ጥሰቶች እንዳይከሰቱ የቅድመ መከላከል ስራ
ለማከናወን በእቅድ ተይዞ፡-

በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ጥሰት እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ስራ ለማከናወን በተያዘው እቅድ
መሰረት የሃብት ምዝገባ ሥራን በተመለከተ ኮሚሽኑ ሀብት ምዝገባ በተመለከተ አዲስ የአፈፃጸም መመሪያ በማዘጋጀት
በላከውና በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ማስመዝገብ የሚመለከታቸው የኮርፖሬሽኑ ነባር ሠራተኞችና አዳዲስ
ሰራተኞች ጨምሮ 250 የሚሆኑ የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች እንዲያስመዘግቡ በእቅድ ተይዞ ማስመዝገብ
የሚገባቸው የሰራተኞች መረጃ ተሰብስቦ 1300 ለሚሆኑ አዲስና ነባር ሰራተኞች ሀብት የማስመዝገብና የማደስ
ሥራ ተከናውኗል፡፡ አፈፃፀሙ ከተያዘው እቅድ በላይ የሆነው በኮሚሽኑ አዲስ የአፈፃፀም መመሪያ እንዲፈፀም
በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተጨማሪ የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች በመካተታቸው ምክንያት ነው፡፡

የተዘጋጀውን የኮርፖሬሽኑን የስነ ምግባር መመሪያ ረቂቅ በማጸደቅ እና በማሳተም ስራ ላይ እንዲውል ማድረግ
በሚለው ተግባር መሰረት የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች የሥነ-ምግባር መመሪያ እንዲፀድቅ ተደርጎ
በ 12 ቱ መርሆች ሰራተኛ እንዲወያዩ እየተደረገ ነው፡፡ መመሪያው ተግብራዊ በመደረጉ መርሆቹን በማስረጽ
የሰራተኛው የግልና የሥራ ባህል መሻሻል እያሳየ ሰለመሆኑ አመላካች ሁኔታዎች መኖራቸውን መጥቀስ
ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ለአመለካከትና ለባህሪ ቀረፃ እንዲሁም ለሥራ ባህል መሻሻል ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ
ሲሆን፤ ብዛቱ 21,000 የሚሆን በፖኬት ሳይዝ ታትሞ መመሪየው ለሰራተኛው እንዲደርስ ለማድረግ በህትመት
ላይ ይገኛል፡፡

በአራቱም አቅጣጫ ከሚገኙ ዲስትሪክቶችና ፕሮጀክቶች እንዲሁም በአካባቢዎች ከሚገኙ ማኀበረሰብና


መንግሥታዊ ተቋማት 4 የውይይት መድረክ በመፍጠር ስለሙስና አስከፊነትና ሙስናን በጋራ በመታገል
የሙስናን ወንጀል መቀነስ የሚቻል መሆኑን በማስገንዘብና መላውን ሠራተኛ በማስተባበር ሙስናን በጋራ
ለመከላከልና ንቅናቄ ለመፍጠር በተያዘው ተግባር መሰረት አመርቂ ሥራዎችን መሥራት ተችሏል፡፡

የሙስና ቅድመ መከላከል ስራ ጋር በተያያዘም ከውስጥ የስራ ክፍሎች ከተባባሪና ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር
እና የውይይት መድረክ በመፍጠር ሙስናን በጋራ ለመከላከል በተያዘው እቅድ መሰረት ከውስጥ
ከኦዲት፤ከህግ፤ከአይቲ፤ከለውጥና ከሰራተኛ ማህበር ጋር በጋራ የመስራት አሰራር ተዘርግቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ ከባለድርሻና
ከተባባሪ አካላት ጋር የጋራ ውይይት ፎረም በማዘጋጀት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ የሥነ-ምግባር ክፍል
ጋር ግንኙነት በማድረግ የሥነ-ምግባር ክፍሉ የውይይት ፎረም እንዲያዘጋጅ በመነጋገር ከስምምነት ተደርሷል፡፡

በተመረጡ 2 የሥራ ክፍሎች ድንገተኛ ፍተሻ(surprise check) በማድረግ ከብልሹ አሠራሮች ራሳቸውን
እንዲጠብቁ በመምከር የማገዝና የመደገፍ ሥራ መስራት በሚለው ተግባር መሰረት በመሳሪያዎችና ማነሪዎች
ዘርፍ እና በመንገድ ኮንስትራክሽን ዘርፍ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በአሰራር ላይ የታዩ ችግሮችን በማንሳትና
ተወያይቶ በመተማመን በቀጣይ እንዲሻሻል የመምከርና የመደገፍ ሥራ ተከናውኗል፡፡

የኮርፖሬሽኑን የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ የተለዩ ችግሮችን በሚመለከት የሥራ ዘርፎች ሞልተው
ባመጡት ቼክ ሊስት እና ዕቅዶቹን ለመተግበር ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እየተከታተሉ የማስፈጸም ስራ ለማከናወን
ታቅዶ፤

በተቀናጀ ሙስና መከላከል ስትራቴጂ በጥናት የተለዩ የኪራይ ሰብሳቢነት ተጋላጭ አከባቢዮች ብዛት 5 የሥራ ዘርፎች
ናቸው፡፡ እነሱም ግዥ፤ንብረት አስተዳደር፤የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና ማሽነሪዎች አስተዳደር፤ፋይናንስና የሰው ሀብት

3
አስተዳደር ሲሆኑ፤ በስትራቴጂ ዕቅዱ ከገጽ 51-81 ላይ በዝርዝር ተለይተዋል፡፡ በጥናቱ ለተለዩ የየዘርፎቹ ችግሮች
መፍትሔ ለመስጠት ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የዕቅዳቸው አካል አድርገው እየፈፀሙ ስለመሆናቸው ክትትል
ማድረግ በሚለው ተግባር መሰረት በተደረገውም ክትትል የሥራ ዘርፎች ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየሰሩ
መሆናቸውን በተደረገው ክትትል ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የተከናወኑ እና ያልተከናወኑ
ሥራዎችን በተመለከተ ለመምሪያ ወቅታዊ ሪፖርት እንዲያደርጉም በደብዳቤ እንዲያውቁት ተደርጎ ወቅታዊ ሪፖርት
በማሰባሰብ የተፈቱና ያልተፈቱ ጉዳዮች ተለይተው ለፌድራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ለሙስና መከላከል
ካውንስል ሪፖርት ተደርጓል፡፡ (ለክትትልና ለመረጃ እንዲመች የተላከው ሪፖርት አባሪ ተደርጎ ቀርቧል፡፡)

ከዚህ ቀደም በ 2 ቱም ተቋማት (ውሃና ህንጻ) በተመረጡ የሥራ ክፍሎች የተከናወኑ የአሰራር ሂደት ጥናቶች የተለዩ ክፍተቶች
ትግበራ በተመለከተ ከፌደራል ሥነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ጋር ግንኙነት በማድረግ አፈፃፀሙን መከታተል በሚለው
ተግባር መሰረት ከኮሚሽኑ ጋር ግንኙነት ተደርጎ በጥናት የተለዩ የአሰራር ክፍተቶችን ከኮሚሽኑ ጋር በተደረገው ውይይት
ጉዳዮቹ ከተቀናጀ ሙስና መከላከል እስትራቴጂ ጋር እንዲታዩ ከስምምነት ተደርሶ ክትትል ተደርጎባቸዋል፡፡

የተቀናጀ የሙስና መከላከል ካውንስል በሙስና መከላከል ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የተሰጠውን ኃላፊነቶች እንዲፈጸሙ
ለማድረግ በሚለው ዕቅድ

የተቀናጀ የሙስና መከላከል ካውንስል ጋር 2 ጊዜ በመገናኘት በስትራቴጂክ ዕቅድ ጥናት በተለዩ ችግሮች
አፈፃፀምና በሌሎች የሙስና ጉዳዬች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫና ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረግ በሚለው
ተግባር መሰረት ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ 2 የሚሆን ጉዳዮች ቀርበው በተሰጠው ውሳኔ መሰረት የእርምት
እርምጃ እንዲወሰድ የመከታተል ሥራ ተከናውኗል፡፡

የተቀናጀ ሙስና መከላከል ስትራቴጂ ዕቅድ አፈፃፀም ለካውንስል በየወሩ ለኮሚሽኑ ደግሞ በየሶስት ወሩ ሪፖርት ማድረግ
በሚለው ተግባር መሰረት የስትራቴጂክ ዕቅድ አፈፃጸም ለኮሚሽኑና ለፕሮሰስ ካውንስል ሪፖርት ተደርጓል፡፡

ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በሚመለከት የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከርና ከኮሚኒኬሽን መምሪያ ጋር


በመመካከር ሠራተኞች እንዲያውቁ ማድረግ በሚለው ተግባር መሰረት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን
በሚመለከት የተገኙ ውጤቶችን የሚያሳይ አጭር ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ለሠራተኞች እንዲሰራጩ የማድረግ ሥራ
ተከናውኗል፡፡

በኮርፖሬሽኑ ውስጥ የሚከሰቱ ከባድ የስነ-ምግባር ጥሰቶችና የሙስና ወንጀሎችን በሚመለከት 6 ጥቆማዎችን በመቀበልና
በማጣራትና መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለማድረግ ታቅዶ

በቅድሚያ የጥቆማ መቀበያና ማስተናገጃ ሥርአት ለመዘርጋት ብሮሸሮች ተዘጋጅቶው በየፕሮጀክቶችና ዲስትሪክቶች
እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት 24 ጥቆማዎች ቀርበው ለ 17 ቱ ምላሽ ተሰጥቷችዋል፡፡ 3 ቱ በአሰራር ሂደት
ጥናት የሚመለሱ ሲሆኑ፤ ለቀሪዎቹ 4 ጥቆማዎች ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡ አፈፃፀሙ ከእቅድ በላይ
የሆነው ቀድሞ የጥቆማ መቀበያና ማስተናገጃ ሥርአት ለመዘርጋት ብሮሸሮች ተዘጋጅተው በየፕሮጀክቶች ዲስትሪክቶች
እንዲደርስ በመደረጉና የጥቆማ መቀበያና ማስተናገጃ ግልፅ ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ በመደረጉ ምክንያት ነው፡፡

4
ከዘህ ጋር በተያያዘም 10 ተጨማሪ የሀሳብ መስጫ ሳጥኖችን አሰርቶ ለየስራ ዘርፎች ለማስቀመጥ በሚለው ተግባር መሰረት
የሀሳብ መስጫ ሳጥኖቹ በቃሊቲ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ እንዲያዘጋጁልን ክትትል በማድረግና በማሰራት
ተገቢው እንዲፈጠም ተደርጓል፡፡

ከፌዴራል የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽንና ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክትሬት መግለጫ
እንዲቀርብበት የሚላኩ ጉዳዩች በሚመለከት እየተከታተሉ ማስፈፀም በሚለው ተግባር መሰረት በቀድሞ የኢትዮጵያ ውሀ
ሥራዎች ድርጅት የኩራዝ ፕሮጀክት በተመለከተ ከደቡብ የወንጀል ምርመራ ዳራክቶሬት መረጃ እንዲሰጥ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ
ተሰጥቷል፡፡

በመልካም ስነ ምግባር ተቋም እንዴት መገንባት እንደሚቻል በሃገር ውስጥ ከሚገኙ 2 ተቋማት የተሻለ ልምድ በመቀመር
ተግባራዊ ለማድረግ በሚለው ተግባር መሰረት አዲስ አበባ ከሚገኙ ሁለት ተቋማት (የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን
እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ልምድ ልውውጥ ተደርጎ ከዚህ በታች የተመለከቱ ልምዶችን መቀመር ተችሏል፡፡

በየፕሮጀክቱና በየዲሰትሪክቱ የሥነ-ምግባር ክበባትን ማቋቋም አስፈላጊነት በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ ካለው የስራ ስፋት
እንዲሁም የፕሮጀክትና ዲስትርክቶች መብዛት ጋር ተያይዞ የሥነ-ምግባር መምሪያው ባለው ውስን የሰው ሀይል በማዕከል
ሆኖ ማዳረስ ስለሚያስቸግር የሥነ-ምግባር እና የሙስና ጉዳይ በጋራ ለመስራትና ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ቀድሞ
ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስለሚኖረው በየፕሮጀክቶችና ዲስትሪክቶች የሥነ-ምግባር ክበባትን ለማቋቋም 2011 ዓ.ም
ዕቅድ ወስጥ አካቶ ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል፡፡

በኮርፖሬሽኑ መረጃን የሚሰጥ እና ጥቆማን የሚቀበል ነፃ የስልክ መስመር እንዲኖር ማድረግን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ
ስለሚሰጠው አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማብራሪያ ለመስጠት እንዲሁም ህብረተሰቡ እና የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ሙስናንና
ብልሹ አሰራርን ለመጠቆም ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ስለሚያስችል በልምድ ልውውጡ የተገኘውን ልምድ በ 2011 ዓ.ም
ላይ የእቅዱ አካል በማድረግ ተግባራዊ ለማድረግ ታስቧል፡፡

ከስትራቴጂክ ዕቅዱ በመነሳት የመምሪያውን የ 2011 ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ይደረጋል
በሚለው ተግባር መሰረት፡-
የ 2011 ዓ.ም ዕቅድ ተዘጋጅቶ ተልኳል፡፡

4. ያገጠሙ ችግሮች የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ

4.1 ያጋጠሙ ችግሮች

 ግብአት በወቅቱ ያለመሟላት

 የሥነምግባር መመሪያው በታቀደለት ጊዜ ጸድቆ ሥራ ላይ ያለመዋሉ

4.2 የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች


 ግብአት እንዲሟላ ክትትል እየተደረገ ነው፡፡

 የሥነምግባር መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ እዲውል ክትትል ተደርጓል፡፡

4.3 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ

5
 በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጸ ኮርሬሽን ለመገንባት የሙስና ወንጀሎችንም በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ
12 ቱን የሥነ ምግባር መርሆችን ለማስረጽ ሰፊ የማስተማርና ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ማከናወን
 መፍትሄ የላገኙ በተቀናጀ ሙስና መከላከል ዕቅድ የተለዩ ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጥ በቅርበት እየተከታተሉ
ማስፈፀም ፣
5. የሥራ ክፍሉ የአፈጻጸም ውጤት
መመሪያው በበጀት ዓመቱ ከያዛቸው እቅዶች መካከል አብዛኞዎቹን አከናውኗል፡፡ ስለሆነም አጠቃላይ የስራ ክፍሉ አፈጻጸም
ውጤትም 99.7 ፐርሰንት ነው፡፡

ማጠቃለያ
በአጠቃላይ መምሪያው በ 2010 ዓ.ም በጀት ዓመት ሊያከናውናቸው ከያዘቸው እቅዶች መካከል የሰው ኃይል
ዝውውርና ቅጥር በተመለከተ የአሰራር ሂደት ጥናት ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ ከመሆኑ በስተቀር መምሪያው
የያዛቸውን እቅዶች ሙሉ በሙሉ ያከናወነ ሲሆን፤ በ 2011 ዓ.ም ከዚህ በበለጠ ለመስራት ቁርጠኛ መሆን
ይጠበቅበታል፡፡

You might also like