You are on page 1of 4

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ለሚደረግ የመስክ ምልከታ

-
የተዘጋጀ ቼክ ሊስት

ሚያዚያ/ 2016 ዓ.ም

አዲስ አበባ

1.መግቢያ

0
6 ኛ ዙር የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3 ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለጋምቤላ
ዩኒቨርስቲ ከፌዴራል መንግሥት በ 2016 በጀት ዓመት የተመደበው በጀት በፕሮግራም በጀት አሰራርና መመሪያ መሰረት

የበጀት ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እየተሰሩ ካሉ ሥራዎች በተለይም በብድርና እርዳታ የሚከናወኑ

ፕሮጀክቶች አፈጻጸም በዩኒቨርስቲ በመገኘት ቋሚ ኮሚቴው ከተሰጠው ሀላፊነትና ተግባር መሰረት በመስክ ምልከታ

አፈጻጸሙ ያለበት ሁኔታ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ነው፡፡

በመሆኑም በመስክ ምልከታ ወቅት የተገኙ ግኝቶች በጥንካሬ፣ በጉድለት እና ቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ

ጉዳዮችን በመለየት እና ከሚመለከተው አካል ጋር የውይይት መድረክ ለማድረግ ይህንን የመስክ ምልከታ ቼክ-ሊስት

እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

2.ዓላማ

ከፌዴራል መንግስት ለጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የ 2016 ዓ/ም የተመደበው በጀት በዕቅዱ መሰረት ለታለመለት ዓላማ እየዋለ

እንደሆነ ለማረጋገጥ በመስክ ምልከታ በቦታው በመገኘት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ነው።

3. በመስክ ምልከታ የሚሳተፉ የቋሚ ኮሚቴ የቡድን አባላት

1. 5 የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣

2. 1 ባለሙያ ፣ 1 ሪፖርተር ፤ 1 ካሜራ ማን እና 2 ሹፌሮች ናቸው።

4. የመስኩ ምልከታ የሚካሄድበት ሂደት

 ቋሚ ኮሚቴው ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ዩንቨርስቲው ከፌዴራል መንግስት በተመደበው በጀት እየተሠሩ ስላሉ

ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች መነሻ በማድረግ በግማሽ ዓመት የተከናወኑ አፈፃፀምን በተላከው ቼክሊስቱ መሰረት

ሪፖርት በዩኒቨርስቲው ይቀርባል፤

 በዩኒቨርስቲው በተመረጡ ፕሮጀክቶች አፈጻጸማቸውን በመስክ ምልከታ ጉብኝት ማረጋገጥ፡፡

 በመስክ ምልከታ ወቅት ከሚመለከተው አካል ማብራሪያ ይሰጥበታል፤

 በመስክ ምልከታ ወቅት የሚታዩ ጠንካራ፤ እጥረትና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በየፈርጁ ተለይተው በማጠቃለያ

ውይይት መድረክ የቃል ግብረ-መልስ ይሰጥባቸዋል፤

5. በመስክ ምልከታ በዋናነት ትኩረት የሚደረግባቸዉ

5.1.በፋይናንስ አጠቃቀም ተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ

1
 የፌደራል መንግስት የተመደበዉ በጀት በተቀመጠዉ ጊዜ እየደረሰ መሆኑን ማረጋገጥ

 በዩንቨርሲቲው የ 2016 በጀት ዓመት ከተመደበዉ በጀት 9 ወር የበጀት አጠቃቀም ፤


 የበጀት ግልፀኝነትን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከማሳወቅ አንፃር የተሰራ ስራ
 የተያዘው በጀት በየሩብ ዓመት ተከፋፍለው የተዘጋጀ እና የየሩብ ዓመቱ አፈጻጻም ምን ላይ ይገኛል?
 የውስጥ ገቢን ከማስተዳደር አንጸር ምን ይመስላል?
 በጀትን በቁጠባ ለማስተዳደር በውስጥ አቅም በመጠቀም የተሰሩ ስራዎች ምን ይመስላል?

5.2. የግዥ ስርዓትን የተከተለ ተግባራትን ስለመከናወኑ

 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ አፈጻፀም ምን ደረጃ ላይ ነው

 በማዕቀፍ የሚገዙ እቃዎች የግዥ እቅድ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ወቅቱን ጠብቆ ከማቅረብ ምን

ይመስላል?
 በግዥ ህግና መመሪያ መሰረት በወቅቱ ግዥን ከመፈጸም አንጻር የተሰሩ ሥራዎችን መገምገም
 ለተማሪዎች ካፊቴሪያ የሚውሉ ግዥዎች በተለይም የምግብ ፊጆታዎችን ከማቅረብ አንጻር የተሰራ ሥራ
ምን ይመስለል ?
 የግዥ የስራ ክፍሉን በቂ የሰው ኃይልና የትምህርት ደረጃ የተደራጀ ስለመሆኑ ማየት

5.3.የመንግስት ንብረት ከማስተዳደር ፣

 አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በተቀመጠው ደንብና አሰራር መሰረት ለማስወገድ የተሰራ ስራ

 የንብረት ቆጠራ በንብረት አስተዳደር ስርዓት መሰረት ስለመከናወኑ በመረጃ የተደገፈ ምልከታ ማየት

 በንብረት አስተዳደር በቂ የሰው ኃይል እና ችሎታ ተደራጅቶ እየተሰራ ነው?

 በቂ የንብረት ማስቀመጫ መጋዘን መኖሩና ለንብረቱ አያያዝ የተደረገው ትኩረት?

5.4.የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በተለይ ነባር ፕሮጀክቶችንም ከማጠናቀቅ

 የፕሮጀክቱ ዓይነት

 መቼ ተጀመረ ?

 አፈጻጸሙ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

 የፋይናንስ አፈጻጸሙስ?

5.5.በብድር እና እርዳታ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች አፈጻጸም

2
 ፕሮጀክቶች መቼ ተጀመረ ?

 አፈጻጸሙ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

 የፋይናንስ አፈጻጸሙስ ምን ይመስላል?

5.6.የኦዲት ተግባራትን ከማከናወን አንጻር

 ለውስጥ ኦዲት የተሰጠው ሀላፈነትና ተግባር ከመወጣት አንጻር


 በውጭ ኦዲት የተገኘው ግኝትና የማሰተካኪያ እርምጃ የተወሰደው ካለ ምን ይመስላል?

5.7. ከበጀት አጠቃቀም አንጸር ለትምህርት ጥራት አጋዥ የሆኑ ፋሲሊቲዎች ለማሟላት የተሰሩ ስራዎች

 ወርክሾፕን ከማደራጀት አንጻር የተሰሩ ሥራዎች መገምገም

 ላብራቶሪዎችን
 በአጠቃላይ ለመማር ማስተማር የሚረዱ ግብዓቶችን ከማሟላት የተሰሩ ስራዎች ምን ይመስላል?

5.8. ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢን ከማመንጨት አንጻር የተከናወኑ ስራዎች ምን ይመስላል?

በመስክ በተግባር ጉብኝት በማድረግ በቂ መረጃ መዉሰድ

You might also like