Professional Documents
Culture Documents
የመንግስት ግዥ አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት
ሰኔ /2012 ዓ.ም
Page 1 of 17
መግቢያ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በስሩ ሁለት (2) ቡድኖች ይዞ
እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል፡፡ በስሩ የመንግስት ግዥ አስተዳደር የግዥ አፈፃፀምና ንብረት ማስወገድ አቤቱታ
ማጣራት ቡድን እና የመንግስት ግዥ ኦዲት ቡድን የሚገኝ ሲሆን የከተማውን የመልካም አስተዳደር ስራዎችን
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመቀነስ የመንግስት ውስን ሀብት በቁጠባና ውጤታማ የልማት
እንቅስቃሴ ላይ ለማዋል ለተገልጋዩ ህ/ሰብ ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር መንግስት
የነደፋቸውን የልማት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች እንዲሁም ፖሊሲዎችና ስትራተጂዎች በብቃት ለመፈጸም
እንዲቻል በጋራ የ 2012 ዓ.ም እቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በመሆኑም የ 2012 በጀት ዓመት የ 12
ወራት እቅድ አፈጻጸም በግብና በተግባር ተለይቶ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
በከተማችን ያለውን ውስብስብና መጠነ ሰፊ የአፈፃፀም ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ አስተዳደሩ
ከአጭርና ከረጅም ጊዜ አኳያ የነደፋቸውን የልማት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ተግባራዊ እንዲሆኑ አጋዥ ሚና
የሚጫወት ሴክተር እንደመሆኑ የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመቀነስ ትግልን በማጠናከር
በመንግስት ግዥ አስተዳደር ላይ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ የተጀመረውን የማስፈፀም አቅም ግንባታ ስራ እና
የኦዲት ምርመራ አጠናክሮ በማስቀጠል ያለንን ውስን ሀብት በተገቢው ሁኔታና ስርዓትና ፍትሃዊ በሆነ
መንገድ ተግባራዊ ማድረግና ለልማት እንቅስቃሴ በማዋልና በሴክተር መ/ቤቶች ሥር ነቀል ኢኮኖሚያዊ
ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና መጫዎቱና ለውጡን በሚፈለገው መልኩ ለማረጋገጥ
የሚያስችል የተደራጀ የለውጥ ሠራዊት በመገንባት፣ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የመንግስት ግዥ የህግ
ማእቀፎች (አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ማኑዋሎች ) ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ ዋነኛ ዓላማው
ነው፡፡
Page 2 of 17
ተግባር 1.1 በግዥ አፈጻጸም ሂደት የሚፈጠሩ የአሰራር ግድፈቶች በሴክተር መ/ቤቶችን የኦዲት
ምርመራ በማድረግ አሰራሩ መመሪያን የተከተለ እንዲሆን በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 4 ያቀደ ሲሆን
በዚህ መሰረት በበጀት አመቱ 12 ወራት 8 የኦዲት ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ / ከእቅድ ውጭ
የተሰሩትን 3 የጥቆማ የኦዲት ስራዎች ጨምሮ 11 ተከናወኖ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ የተደረገ
ሲሆን የኦዲት ክንውን አፈፃፀሙም 137.5 % ነው፡፡
በየጊዜው የሚደረጉ የሞርኒንግ ብሪፊንግ / 1 ለ 5 / ውይይት በማጠናከር ተጨባጭ ትግል በማድረግ
በዳይሬክቶሬቱ ውስጥ የሚመጣውን ለውጥ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የስራ ሰዓት አክብሮ መግባትና መውጣት ፣ በስራ ሰዓት በስራ ላይ በመገኘት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
በጀት ዓመቱ 12 ወራት የግዥ ፈፃሚ መ/ቤቶች ባወጡት ጨረታ ላይ ከተሳተፉ 45 አቅራቢዎች
በግዥ አፈፃፀም አካሄዱ ላይ የህግ ማቀፉን ያልተከተለ አሰራር መሆኑን ገልፀው ያቀረቡትን አቤቱታና
Page 3 of 17
ቅሬታ በመመርመር በ 16 አቤቱታና ቅሬታዎች ላይ ቅሬታው ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን ፣ 14 ቱ
አቤቱታና ቅሬታዎች የህግ ማቀፉን ያልተከተለ የግዥ ሂደት በመሆኑ ሙሉ ለሙሉ ጨረታው
እንዲሰረዝ መደረጉና ቀሪው 10 ሩ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች ተቀባይነት አግኝቶ ቅሬታ አቅራቢዎቹ
በጨረታው ሂደት ተካተው ጨረታው እንዲቀጥል ውሳኔ የተሰጠበት፤ እንዲሁም 5 ቱ ደግሞ
ለቅሬታና አቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ ቀርቦ በመታየት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ከአቅራቢዎች በግዥ
አፈፃፀም ዙሪያ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በበጀት አመቱ ዘጠኝ
ወራት 55 ታቅዶ 40 የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 72.72 ፐርሰንት ነው፡፡
በበጀት ዓመቱ 12 ወራት ከቀረቡት የ 115 አቅራቢዎች የጥፋተኝነት ሪፖርት መካከል የ 81
አቅራቢዎች የጥፋተኝነት ሪፖርት ምርመራ ተጠናቆ ከማንኛውም የመንግስት ግዥ ላይ
እንዳይሳተፉ በ 75 ቱ ላይ ለ 6 ወራት የእገዳ ውሳኔ የተላለፈ፤ በ 5 አቅራቢዎች ለ 1 አመት እና በ 1
አቅራቢ ላይ የሁለት ዓመት እግድ የተጣለበት ሲሆን የውሳኔው ግልባጭ የ 64 ቱ አቅራቢዎች
ሰርኩለር የተላለፈ ሲሆን 17 በሂደት ላይ ያለ 25 ቱ ባለበጀት መ/ቤቶች ያቀረቡት የጥፋተኝነት ክስ
አግባብ ባለመሆኑ ውሳኔ ተሰጥቶበት ለተቋማቱ ምላሽ የተሰጠ መሆኑ በተጨማሪም 9 ከአቅራቢዎች
ማስረጃ ባለማቅረባቸው መረጃዎች እንዲሟሉ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝ ነው።
በአጠቃላይ በበጀት አመቱ 90 ለመስራት ታቅዶ 106 የተከናወነ ሲሆን አፈፃፀሙም 117.8%
ተከናውኗል፡፡
የመ/ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት 48 44
Page 4 of 17
የሳምንቱን ስራዎችና ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ያለበት ደረጃ በሚገባ በመገምገም ያልተሰሩ
ስራዎች ያልተሰሩበትን ምክንያቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት ውይይቱን
ውጤታማና አስተማሪ የተሻለ አፈፋፀም እንዲኖር በሚያስችል መልኩ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የ 1 ለ 5 እና የለውጥ ቡድን እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ 12 ወራት ከ 4 ባለበጀት መ/ቤቶች በቀረበ የስልጠና ፍላጎት ጥያቄ መሰረት ለ 130
ባለሙያዎች በመንግስት ግዥ አስተዳደር ስርዓቱ ላይ የተሻለ አቅም እንዲኖር ለማድረግ ስልጠና
ተሰጥቷል።
Page 5 of 17
በበጀት አመቱ 12 ወራት በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ፣ ክ/ከተሞች እና ወረዳዎች
ስር ለሚገኙ ተቋማት በመንግስት ግዥ አስተዳደር ዙሪያ ተቋማዊ ስልጠና ለ 270 ፈፃሚዎችና አመራሮች
ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዚህ መሰረት በበጀት አመቱ ለ 300 አመራርና ፈፃሚ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ
ለ 270 የተሰጠ ሲሆን አፈፃፀሙም 90 ፐርሰንት ነው፡፡
የክትትልና ድጋፍን በተመለከተ በበጀት አመቱ 12 ወራት 90 ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ
ታቅዶ በ 110 ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ ተደርጎ ግብረመልስ የተሰጠ ሲሆን አፈፃፈሙም 122
ፐርሰንት ነው፡፡
ለ 10 ክፍለ ከተሞች በተጨማሪም ከእቅድ ውጪ ማእከል እና ክፍለ ከተማን ጨምሮ ለ 102 የግዥና
ንብረት የስራ ክፍሎ ላይ ምዘና በማካሄድ ምዘናው በአግባቡ ለተከናወነበት የስራ ክፍል ግብረ መልስ
የመጠመር ስራ ተሰርቷል፡፡
በተዘጋጀው የሴክተር መ/ቤቶች እና የክፍለ ከተማ የ 2012 በጀት አመት የ BSC እቅድ /እስኳር ካርድ/ ላይ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለ 1 ቀን ተሰጥቷል
በበጀት ዓመቱ ባለሙያው ራስን ለማብቃት ባቀደው እቅድ መሰረት አንድ /1 / የዳይሬክቶሬቱ ባለሙያ
በአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ለ 8 ቀናት የፌደራል የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ባዘጋጀው በከፍተኛ
ደረጃ ሙያዊ ስልጠና አቅሙን እንዲገነባ ተደርጓል፡፡
1. ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ፡- የጀነሬተር ግዥ ከግዥ አፈጻጸም መመሪያ
ውጪ የተፈጸመ በመሆኑ ችግሩን በፈጠሩት ላይ የማስተካከያ እርምጃ ተወስዶ እንድናውቀው
በአካልና በስልክ ከተደረገው ውጭ መጋቢት 25 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ጭምር
አሳውቀናል፡፡
Page 6 of 17
3. የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ኦዲት አድርጎ ለላከልን ግኝት በኦዲት ግኝቶቹ
መሰረት ማስተካካያ እርምጃ መወሰዱ እንዲረጋገጥ ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ
ግብረ መልስ ተልኳል፡፡
4. ከየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ፣ ከኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት፣ ከጉለሌ
ክ/ከተማ ፋናንስ ጽ/ቤት ፣ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፋናንሽ ጽ/ቤጽ እና ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ
ፋይናንስ ጽ/ቤት የተላከልንን ኦዲት ሪፖርት በመቀበል በኦዲት ሪፖርቱ ዙሪያ የታትን ጠንካራና
ደካማ ጎኖችን በመለየት እና በመገምገም ግብረ- መልስ በድብዳቤ ተሰጥቷል፡፡
5. ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ፡-
ጤና ጣቢያው CBC Machine ለመግዛት ባወጣው ውስን ጨረታ በግዥ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ
ችግር እዳለበት ለቢሮአችን ጥቆማ በመድረሱ ምክንያት የግዥ አፈጻጸሙን ኦዲት አድርገን
በተገኘው ግኝት መሰረት እርምጃ እንዲወሰድ መጋቢት 01 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥር
ፋ/ቢ 25/8/64/1481 በተጻፈ ደብዳቤ ችግሩ የተፈጠረው በጤና ጣቢያው የአሰራር ስህተት
በመሆኑ ችግሩን በፈጸሙት ላይ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ እና የመንግስት ሃብት ያለ
አግባብ ለወጪ ከመዳረጉ በፊት መፍትሄ ተሰጥቶ ይህ ደብዳቤ በደረሰ በ 10 ቀናት ውስጥ
እንድታሳውቁን ቢጠየቅም በወቅቱ መልስ ባለመሰጠቱ በተደረገው ክትትል በድጋሚ የማስተካከያ
እርምጃ ተወስዶ እንድናውቀው መጋቢት 25 2012 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ጠይቀናል፡፡ በተላከው
ሪፖርት መሰረት ጤና ጣቢያው ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥር ን/ስ/ላ/ወ 11/ጤ/ጣ/12 በተጻፈ
ደብዳቤ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዳቸውን በግብረ መልስ አሳውቀዋል ፡፡
6. የተፋሰስ አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት እና አስተዳደር ኤጀንሲ የባሻ ወልዴ ችሎት ፕላዛ ህንጻ
ግንባታ የኦዲት ግኝት ኮንስትራክሽን ቢሮንም ስለሚመለከት በግኘቱ ላይ ምላሽ እንዲሰጥና
መረጃ እንዲላክል ሚያዚያ 05 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ እንድናውቀው ለቀረበ ጥያቄ
ግብረ -መልስ የተሰጠ ቢሆንም በህንጻው መፍረስ ላይ ውሳኔ የሰጠው የኮንስትራክሽን ቢሮ በአስር
ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁን ደብዳቤ ቢጻፍም እስካሁን ምላሽ አልተሰጠም፡፡
7. የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና መኔጅመንት ጽ/ቤት ፡- የክፍለ ከተማው መሬት ልማትና
ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ/ም በጨረታ ቁጥር መ/ል/ማ/ግ/0001/2012 ዓ/ም
የተለያዩ የጽህፈት እና የጽዳት እቃዎችን ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው ግልጽ ጨረታ
ላይ የግዥ ውል አፈጻጸሙ ችግር እንዳለበት የተሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ግዥው
የመንግስት የግዥ መመሪያን ፣ ህግና ደንብን ተከትሎ የተፈጸመ ስለመሆኑ በኦዲት ለማረጋገጥ
Page 7 of 17
እና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ ኦዲት አድርገን ግብረ-መልስ መስጠታችንን መነሻ
በማድረግ ጽ/ቤታችሁ በቁጥር ቂ/ክ /ከ/መ/ል/ማ/17/ን/አስ/ጠ/5799/12 በቀን ሚያዚያ 01 ቀን
2012 ዓም በተጻፈ ደብዳቤ የተላከልን ምላሽ ጽ/ቤቱ የተፈጸመውን የግዥ ጥሰት ላለመቀበል
የተሰጠ ምላሽ በመሆኑና ከችግራቸው ለመውጣት ዝግጁ መሆናቸውን ባለማሳየታቸው የችግሩ
ባለቤት በሆኑት አመራርና የጥራት ኮሚቴ ላይ የማስተካከያ እርምጃ ተወስዶ እንድናውቀው
ሚያዚያ 08 ቀን 2012 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ተጠይቆ ጽ/ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2012 በቁጥር
ቂ/ክ/ከ/መ/ል/ማ/ጽ/ቤት/17/6026/2012 በተጻፈ ደብዳቤ በእቃው በጥራት ኮሚቴ ምዘና የተፈጠረ ስህተት
በመሆኑ ውል ሲሰጥ የገንዘብ መጠኑ ከዋናው ግዥ ጋር ልዩነት የነበረውና በመንግስት ሀብት ላይ ሊደርስ
የነበረው የብር 716,671.80 ልዩነት በኦዲት ተገኝቶ ማዳን የተቻለ ሲሆን ጽ/ቤቱ ችግሩን አምኖና
ማስተካከያ በማድረግ ለተፈፀረው ስህተት ይቅራታ ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም የግዥ ክፍሉና የንብረት ክፍል
ተናበው ባለመስራታቸው ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ስህተቱ እንዲታረም በማድረግ ለቢሮአችን
ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
8. የጎፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የጥቆማ ኦዲት ተሰጥቶ ኮሌጁ ባወጣው ጨረታ የግዥ ስርዓትን
ያልተከተለ አካሄድ የነበረ በመሆኑ ጉዳዩን ከኮሌጁ ዲን እና ከሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጋር
በመሆን ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ እና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በተሰጠው አስተያየት
ኮሌጁ ግዥውን በውስጥ ኦዲት ክፍል ኦዲት እየተደረገ መሆኑንና ችግሩን በፈጸሙት ላይ
የዲሲፕሊን እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ሚያዚያ 19 ቀን 2012 በቁጥር ጎ/ኢ/ኮ/1853/25/35
በተጻፈ ደብዳቤ ያሳወቁ ቢሆንም ተጨባጭ ማስረጃ እንዲያቀርቡ በድጋሚ ተጠይቆ ምላሽ
እየተጠባበቅን ነው፡፡
ተግባር 2. የክትትልና ድጋፍን በተመለከተ በበጀት አመቱ 12 ወራት 90 ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ
ለማድረግ ታቅዶ በ 110 ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ ተደርጎ ግብረመልስ የተሰጠ ሲሆን አፈፃፈሙም
122 ፐርሰንት ነው፡፡
ተግባር 3. የክትትልና ድጋፍ ቼክ ሊስት በመከለስ የማዘጋጀት ስራ ተከናውኗል፡፡
3 በመወዳደሪያ 3,865,184.70 0%
5 ዋጋ ማቅረቢያ 141,623,254.47 1%
Page 9 of 17
የ2011 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀምም የ62 ተቋማት
12,000,000,000.00
10,000,000,000.00
8,000,000,000.00
0.00 292,844,711.16
4,331,199.153,865,184.70 141,623,254.47
ግልፅ አፈፃ ሁለት ደረጃ በመወዳደሪያ ውስን ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ አንድ አቅራቢ ድምር
Page 10 of 17
የ 48 ባለበጀት መ/ቤቶች የ 2012 በጀት ዓመት የግዥ ዕቅድ ማጠቃለያ
986,228,888.9
ዕቅድ በብር 6,581,439,073.76 0.00 0.00 180,932,331.00 0.00 4 7,748,600,293.7
0
986228888.94
85% 0.00
1.00 2.00
0% 0.00180932331.00
0% 4.002% 0.00
3.00 5.00 13% 7.00
0% 6.00 100%
ያ ያ ር
ረታ ረታ የቂ ረታ ረ ቢ ራ
ቢ
ም
ጨ ጨ ጠ ጨ ቅ አ ቅ ድ
ጽ ጃ መ ስን ማ ድ ላ
ግል ደረ ብ ው ጋ አ ን ቅላ
ለት ሃሳ ዋ ጠ
ሁ ሪያ
ዳደ
ወ
መ
ይህ የዕቅድ ማጠቃለያ የ 48 ባለበጀት መ/ቤቶች ብቻ ሲሆን የ 2012 በጀት ዓመት የግዥ ዕቅድ ካላመጡ መ/ቤቶች መካከል
ለአብነት ከፍተኛ በጀት ከሚያንቀሳቅሱ ተቋማት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ መንገድ
ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ጤና ቢሮ የመሳሰሉት ይገኙበታል፤
በህትመት ስርጭትና ቁጥጥር ክፍል በአጠቃላይ 2012 ዓ/ም የ 12 ወራት ሪፖርት በተመለከተ 856,987 የተለያዩ
ህትመቶች ተሰራጭተዋል፡፡
Page 11 of 17
የምንገለገልባቸውን ቋሚና አላቂ ንብረቶች በደንብና መመሪያ መሰረት በአግባቡ በመጠቀም፣ የዳይሬክቶሬቱን በጀት፣
ሃብትና ንብረት በቁጠባና በተገቢው ሁኔታ ለታለመለት አላማ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት ተደርጓል፣
ግብ 8 የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት አሰራርን ማጠናከርን በተመለከተ
የባሻ ወልዴ የአረንጓዴና ፕላዛ ግንባታ ግዥ በውሉ መሰረትና በተቀመጠው የስራ ዝርዝር እና ስፔክ Quantity
(BOQ) መሰረት የተገነባ መሆኑ ተረጋግጦ ርክክብ ሳይደረግ ባልታወቀ ምክንያት ከንቲባ ጽ/ቤት አዟል በማለት
እንዲፈርስ የተደረገ በመሆኑ በተደረገው ክትትል የኮንስትራክሽን ቢሮ ባቋቋመው ኮሚቴ ህንጻው ባለበት ዲዛይን
ተስተካክሎ (As Built Design) ይሰራ ብሎ ወስኖ እያለ ህንጻው ያለበት ደረጃ ሳይታወቅ ከአሰራር ውጭ ፈርሶ
ተገኝቷል፡፡
ኤጀንሲው በብር 260,819.18 (ሁለት መቶ ስልሳ ሺ ስምንት መቶ አስራ ዘጠኝ ከ አስራ ስምንትሳንቲም)
የተሽከርካሪ ጥገና ሲያደርግ በወቅቱ በደብዳቤ ቁጥር ው/መ/80/53/11 በቀን 11/01/2011 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ
ቢሾፍቱ ብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ከመለስ ኪዳነ ማረያም ጋራዥ በቀጥታ እንዲጠገን ተወስኗል
ተብሎ ተሽከርካሪ በቀጥታ ግዥ መጠገኑ ፤
Page 12 of 17
የት/ቤቱ አሸናፊ ተደርጎ የመረጠው አቅራቢ ዲ.ኤል.ኤፍ ጠቅላላ የንግድ ስራ በቀረበለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ
ምን አይነት ኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር ፣ ላፕቶፕ ፣ ዲጅታል የፎቶ ኮፒ ማባዣ ማሽን ጀስትነር እና ኤል.ሲ.ዲ
(LCD Projector) እንደሚያቀርብ ግልጽ ሳያደርግ በተለይም የፍላጎት መግለጫ Specification ሳይዘጋጅ
ከቀረቡት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ስላቀረበ ብቻ ከግዥ መመሪያ ደንብ እና አሰራር ውጪ እቃዎቹ
ከመገዛታቸውም በላይ በውሉ እና አቅራቢው (ዲ.ኤል.ኤፍ ጠቅላላ የንግድ ስራ ድርጅት) ለክፍያ ባቀረበው ገንዘብ
መቀበያ ደረሰኝ እና ገቢ ደረሰኝ (ሞዴል 19 ) ላይ ጭምር የእቃው ሙሉ ስፔሲፊኬሽን (Specification) ሳይገለጽ
እቃዎቹ ንብረት ክፍል ገቢ መደረጋቸው እና ክፍያ ተፈጽሞ መገኘቱ የግዥ ህግን የተከተለ አስራር አለመሆኑ እና
የመንግስትን ጥቅም ያሳጣ መሆኑ ፤
የተሰጠው ጥቆማ ኤጀንሲው የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ የመንግስት ገንዘብ ያለአግባብ እንዲወጣ እና ከግዥ አፈጻጸም ውጭ
ግዥ ለመፈጸም ተሞክሯል የሚል ሲሆን ነገር ግን ኤጀንሲው በሸተው የመደበኛ ጨረታ ሰነድ ክፍል ሶስት የዋጋ ማስተካከያን
Page 13 of 17
አስመለክቶ ስህተት ሲኖር የነጠላ ዋጋ ለውጥ ሳይደረግ አጠቃላይ ወደ ጎን ብዜት እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ትክክለኛውን
የነጠላ ዋጋ መሰረት በማድረግ ጨረታው ይፋ ከመሆኑ በፊት ማስተካከል እንደሚቻል እና ኤጀንሲውም ለሁሉም
ተጨራቾች ተደራሽ ያደረገውን በመደበኛ ጨረታ ሰነድ ውስጥ በክፍል ሶስት ላይ በተቀመጠው ህግ መሰረት
እንዲሁም በግዥ መመሪያው
አንቀጽ 34 ተራ ቁጥር 34.1 ከ ሀ-ሐ የተገለጹትን ስለአጠራጣሪ የዋጋ ማስተካከያ አሰስመልክቶ የተጠቀሱትን ነጥቦች
ተከትሎ የተሰራ መሆኑን በኦዲት አረጋገጠናል ፡፡ እንዲሁም በመደበኛ የግዥ ኦዲት በእቅድ የተያዘው ስራ ጨረታ
የሚከፈትበትን ጊዜ ለአቅራቢዎች ሳያሳውቁ በሌሉበት በመክፈት በግኝቱ ላይ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥበት ሪፖርት
ተልኮ ምላሹን እየተጠባበቅን ነው፡፡
6. የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በስሩ ለሚገኙ ትምህርት ቤ/ቶች
4,800 ኮምባይን ዴስኮችን ለመግዛት ባወጣው ግልጽ ጨረታ ከስፔሲፊኬሽን ውጭ ግዥ መፈጸሙን በተመለከተ እና
የወረዳ 08 ህብረተሰብ ተሳትፎ የልማት ገቢ አሰባሰብና በቼኮች ወጭ ላይ ምዝበራ ስለፈጸሙ የማራጋገጥ ስራ
ተሰርቷል። በመሆኑም 4,800 ኮምባይንድ ዴስኮች ከስፔሲፊኬሽን ውጭ መገዛታቸውንና በራሪ ቼክና ጉርድ ቼክ ላይ
የገንዘብ መጠን አበላልጦ በመጻፍ ፈራሚዎች ባዶ ቼክ ላይ በመፈረም መንግስት ላይ የብር 1,771,703.84 ኪሳራ
እንዲደርስበት ተደርጓል ይህም ፡፡
7. የትራፊክ ማኔጅመንት በእቅድ የተያዘ ኦዲት 100 % ተጠናቆ ሪፖርት ተልኮ ምላሽ
እየተጠበቀ ሲሆን፡-
በረካታ ግዥዎች የጨረታ ሂደቶች ህጋዊ የግዥ አፈጻጸም ስርዓትን የተከተሉ ባለመሆኑ የማስተካከያ
እርምጃ እንዲወሰድ ለኤጀንቺው ሪፖርት ተልኳል፡፡
8. የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንትጽ/ቤት የጥቆማ ኦዲት 100%
ተጠናቆ በድጋሚ ግብረመልስ ጭምር ተጠናቆ የተላከ ሲሆን ፡-
ጽ/ቤቱ ሚያዚያ 28 ቀን 2012 በቁጥር ቂ/ክ/ከ/መ/ል/ማ/ጽ/ቤት/17/6026
/2012 በተጻፈ ደብዳቤ በእቃው በጥራት ኮሚቴ ምዘና የተፈጠረ ስህተት በመሆኑ ውል ሲሰጥ የገንዘብ መጠኑ ከዋናው
ግዥ ጋር ልዩነት የነበረውና በመንግስት ሀብት ላይ ሊደርስ የነበረው የብር 716671.80 ልዩነት በኦዲት ተገኝቶ ማዳን
የተቻለ ሲሆን ጽ/ቤቱ ችግሩን አምኖና ማስተካከያ በማድረግ ለተፈፀረው ስህተት ይቅራታ ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም የግዥ
ክፍሉና የንብረት ክፍል ተናበው ባለመስራታቸው ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ በመጠየቅ ስህተቱ እንዲታረም በማድረግ
ለቢሮአችን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
Page 14 of 17
9. የጎፋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የጥቆማ ኦዲት ተሰጥቶ ጉዳዩን ከኮሌጁ ዲን እና ከሚመለከታቸው ሃላፊዎች ጋር
በመሆን ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የማማከር ስራ ተሰርቷል ፡፡
ያጋጠሙ ችግሮች
የተወሰዱ መፍትሔዎች
Page 15 of 17
የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል፤
የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለመቀነስ የተጀመረውን የተለያዩ የአቅም መገንቢያ
ስልጠናዎች መስጠት፣
በአዲሱ አደረጃጀት የሰው ሀይል እንዲሟላ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ጥረት ማድረግ
በጂ.ኤ.ጂ ኮንቨርሽን ላይ የተነሱት ቅሬታዎች እንዲፈቱ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ክትትል
ማድረግ
Page 16 of 17
Page 17 of 17