You are on page 1of 1

አይታብ ድጋፍ መስመር

ስልክ. 011 666 32 37

ከአይታብ ጋር የተያያዙ - ተደጋግመው የሚቀርቡ ጥያቄዎች (ተ.የ.ጥ.)

ጥያቄ 1፡ የ JV ሪፖርቱን Print ማረግ ፈልጌ አላመጣ አለኝ?

መልስ፡ JV ሪፖርት እንዳይወጣ የሚያረጉ ምክንያቶች

1. ደሞዝ ካልተዘጋጀ JV ልናይ አንችልም ስለዚህ ደሞዝ JV ለተፈለገበት ወር መሰራቱን እናረጋግጥ


2. ለመስሪያ ቤቱ የወጪ ክፍል ካልተመዘገበ JV አያወጣም። ይሄን ለማስተካከል በግራ በኩል ካሉት መምረጫ ውስጥ
ማቀናበሪያ > ድርጅት ውስጥ መዋቅር የሚለውን ከፍተው የስራ ሂደቱን ይምረጡ በመቀጠል የወጪ ክፍል የሚለውን ሳጥን
ይመጡ፡፡

ጥያቄ 2፡ የ JV ተቀናናሽ code (ተቀፅላ) መቀየር ፈልጌ ነበር?

መልስ ፡ የተቀናናሽ code(ተቀፅላ) ለመቀየር ማቀናበሪያ ውስጥ ይግቡ በመቀጠል የክፍያ ማጣመሪያ የሚለውን ይክፈቱት የተቀናሹን
አይነት ከፍተነው ተቀፅላውን ይቀይሩለት ሲጨርሱ መዝግብ ብለው ይውጡ፡፡

ጥያቄ 3፡ የኋላ ክፍያ print ለማረግ ፈልጌ ነበር?

መልስ፡ ሪፖርት ውስጥ ይግቡ በመቀጠል የደሞዝ መክፈያ ሪፖርትን ሲከፍቱ ከታች ያልተከፈለ ክፍያ የሚል ያገኛሉ እሱን ከፍተው
የተዘጋጀውን ደሞዝ ሪፖርት አዘጋጅ በማለት print ማረግ ይችላሉ፡፡

ጥያቄ 4፡ የትርፍ ሰዓት ስራ print ለማረግ ፈልጌ ነበር?

መልስ፡ ሪፖርት ውስጥ ይግቡ በመቀጠል የደሞዝ መክፈያ ሪፖርትን ሲከፍቱ ከታች የትርፍ ሰዓት ስራ የሚል ያገኛሉ እሱን ከፍተው
የተዘጋጀውን ደሞዝ ሪፖርት አዘጋጅ በማለት print ማረግ ይችላሉ፡፡

ጥያቄ 5፡ የዓመት ፍቃድ ወደ ክፍያ print ለማረግ ፈልጌ ነበር?

መልስ፡ ሪፖርት ውስጥ ይግቡ በመቀጠል የደሞዝ መክፈያ ሪፖርትን ሲከፍቱ ከታች የዓመት ፍቃድ ወደ ክፍያ የሚል ያገኛሉ እሱን
ከፍተው የተዘጋጀውን ደሞዝ ሪፖርት አዘጋጅ በማለት print ማረግ ይችላሉ፡፡

ጥያቄ 6፡ ቀሪ ያላቸው ሰራተኞችን እንዴት አርጌ አቴንዳንሱን መቀነስ እችላለሁ?

መልስ፡ የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይክፈቱ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይግቡ ቀሪ ያለበትን ሰራተኛ ይክፈቱ (አሳይ) የሚለውን ይንኩት
በመቀጠል ጠዋት ማታ የሚለውን ቲክ በማረግ የቀረበትን ቀን ቀንሰን መዝግብ የሚለውን በተን ይጫኑት ከመዘገበ በኋላ ወደ ዋናው
አቴንዳንስ ይመልሶታል ከጎን box ቲክ ያርጉትና ባለበት አፅድቅ የሚለውን ይቻኑት፡፡

ጥያቄ 7: ምልክቱን ተጠቅሜ አይታፕን ለማስጀመር ብሞክርም ሥርዓቱ ሳይጀምር ይቀርና ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር የስህተት ምልክት
ያሳያል። ይህንን ስህተት ለማስተካከል ምን ማድረግ እችላለሁ?

መልስ: ይህ ሁኔታ የተፈጠረው ኮምፒውተርዎን ልክ እንዳስነሱ ከሆነ ትንሽ ደቂቃዎች ጠብቀው አይታብን ከእንደገና ለማስጀመር
ይሞክሩ። ይህ ካልሰራ የኔትዎርክ ገመዶች እንዳልተነቀሉ እንዲሁም ኮምፒውተሮ ኔትዎርክ እንዳለው ያረጋግጡ ።ይህ ካልሰራ
ኮምፒውተርዎን ከእንደገና አስነስተው አሁንም ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ አይታብን ለማስጀመር ይሞክሩ። ሁለቱም መንገዶች
ካላስተካከሉት ላለመስራቱ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ የአይታፕ ድጋፍ መስመርን ደውለው ያማክሩ።

You might also like