You are on page 1of 39

የተሻሻለው የቴሌብር የፓርትነር መተግበሪያ (PARTNER

APP) የአጠቃቀም መመሪያ

ለቴሌብር ወኪሎች (Agents) የተዘጋጀ

Resiliently
መጋቢት 22፣ 2014
MOVING
FORWARD
STRATEGIC THEMES
BRIDGE (ድልድይ)
ማውጫ

1 መግቢያ

2 የአኑቲ ኮሚሽን አከፋፈል

3 የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃን ማሳደግ

4 ለደንበኛ ጥቅል ለመሸጥ

5 ገንዘብ ከወኪል ወደ ወኪል ማስተላለፍ

6 የአገልግሎት ክፍያ

7 ከዋና ወኪሉ ወደ ወኪል ገንዘብ ለማስገባት እና ለማውጣት


መግቢያ
የቴሌብር አገልግሎት

• የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞች በቀላሉ የሞባይል ስልኮቻቸውን በመጠቀም ገንዘብ እንዲያስተላልፉ ፣ ከሃገር ውስጥና
ከሃገር ውጭ ገንዘብ እንዲቀበሉ፣ እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው።

• ደንበኞች የቴሌብርን አገልግሎት በወኪል ወይም በራስ አገዝ የቴሌብር መተግበሪያ አሊያም የአጭር ቁጥር (*127#)
በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ።

• ይህ ሰነድ የተሻሻለውን የፓርትነር የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም የቴሌብር አገልግሎት ለደንበኞች እንዴት
መስጠት እንደሚቻል ያሳያል::

• ይህን የፓርትነር መተግበሪያ መጠቀም የሚችሉት የቴሌብር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለመስጠት ከኢትዮ ቴሌኮም
ጋር ውል የገቡ ወኪሎች ብቻ ናቸው።

• ወኪሎች ለሚሰጡት አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ኮሚሽን ይታሰብላቸዋል።

• የተሻሻለው የፓርትነር የሞባይል መተግበሪያ ቨርዥን V1.0.330 ነው።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 6


የተሻሻሉ እና አዳዲስ የኮሚሽን ክፍያዎች
1. የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች (Utility Payment)
– ወኪሉ ለደንበኛ እንደ መብራት እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን በሚከፍልበት ጊዜ አገልግሎት አቅራቢው እና ኢትዮ ቴሌኮም
የተስማሙበትን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ በሙሉ ወኪሉ እና ዋና ወኪሉ በ80/20 መርህ መሠረት ይካፈላሉ፡፡

– ለምሳሌ፡ ኢትዮ ቴሌኮም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን በቢል 1 ብር የአገልግሎት ክፍያ የሚያስከፍል ከሆነ ወኪሉ ለአንድ ደንበኛ
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በሚከፍልበት ጊዜ ወኪሉ እና ዋና ወኪሉ በ80/20 መርህ መሠረት 1 ብሩን ይካፈላሉ፡፡

2. የኢትዮ ቴሌኮም ቢል ክፍያ (Ethio Telecom Bill)


– ወኪሉ ለደንበኛ የኢትዮ ቴሌኮምን ቢል በሚከፍልበት ጊዜ እንደየቢሉ መጠን በሚከተለው መልኩ የኮሚሽን ክፍያ ያገኛል

የኢትዮ ቴሌኮም ቢል ወኪሉ የሚያገኘው ለምሳሌ፡ አንድ ደንበኛ በወኪል በኩል 1,200 ብር የኢትዮ ቴሌኮም ቢል
መጠን (በብር) ኮሚሽን (በብር)
0 – 50 4 ቢከፍል ወኪሉ 20 ብር ኮሚሽን ያገኛል፡፡ እንዲሁም ደንበኛው ብር 6000
51 – 1000 15 ከከፈል ወኪሉ 6,000*1% = 60 ብር ኮሚሽን ያገኛል ማለት ነው፡፡
1001 - 2000 20
2002 – 5000 30
› 5000 የቢሉን 1%
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 7
የተሻሻሉ እና አዳዲስ የኮሚሽን ክፍያዎች …
3. ለደንበኛ ገንዘብ ገቢ ማድረግ (Cash-In)
– ከዚህ በፊት የነበሩ እስከ 8000 ብር ደረስ ለሚደረግ የደንበኛ ገቢ የሚከፈሉ የኮሚሽን ክፍያ ክፍልፋዮች እንዳሉ ሆነው አሁን
ወኪሉ እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ ከደንበኛ መቀበል ይችላል፡፡ የኮሚሽን ክፍያ መጠኑም በሚከተለው ሠንጠረዥ ተመላክቷል፡፡

ወኪሉ የሚያገኘው
መጠን (በብር) ለምሳሌ፡ አንድ ደንበኛ 18 ሺህ ብር ገቢ ቢያደርግ
ኮሚሽን (በብር)
8000 – 15000 12 ወኪሉ 13 ብር ኮሚሽን ያገኛል ማለት ነው፡፡
15001 – 20000 13
20001 - 30000 15

4. የጥቅል ሽያጭ (Sell Package)


– አንድ ወኪል ለደንበኛ ጥቅል ሲሸጥ የሸጠውን የጥቅል መጠን 5.75 በመቶ ኮሚሽን ያገኛል፡፡

– ለምሳሌ፡ አንድ ወኪል ለደንበኛ ወርሃዊ ያልተገደበ ድምፅ ወይም ዳታ ጥቅል ብር 999 ቢሸጥ ወኪሉ 999*5.75% = 57.44 ብር
ኮሚሽን ያገኛል፡፡ ወኪሉ ዓመታዊ የድምጽ፣ ዳታ እና መልዕክት ጥቅል ለአንድ ደንበኛ ቢሸጥ 10200*5.75% = 586.50 ብር
ኮሚሽን ያገኛል፡፡

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 8


መተግበሪያውን ለማግኘት

በየጊዜዉ እየተሻሻለ የሚመጣው የፓርትነር መተግበርያ የቨርዥን ቁጥር እየጨመረ ስለሚመጣ


የተሻሻለውን የቴሌብር መተግበሪያ ከጉግል ፕሌይ አልያም ከአፕስቶር በማውረድ ይጠቀሙ!

https://play.google.com/store/apps/details?i https://apps.apple.com/al/app/telebirr-
d=cn.tydic.ethiopartner partner/id1553620008

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 9


ወደ ፓርትነር መተግበሪያዉ እንዴት ይገባሉ?
➢ ወደ ፓርትነር መተግበሪያዉ ለመግባት መጀመሪያ የወኪል አጭር ቁጠር (short code), ኦፕሬተር አይዲ እንዲሁም
የሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስፈልጎታል። ይህም በሚያደርጉት ምዝገባ መሰረት ከኢትዮ ቴሌኮም ከ127 በአጭር
የጽሁፍ መልእክት (SMS) የሚላክሎት ይሆናል።

ወደ ፓርትነር መተግበሪያዉ ለመግባት

➢ መጀመሪያ User short code በሚለው ሣጥን ውስጥ የወኪል አጭር ቁጠር
(short code) ያስገቡ

➢ ቀጥሎ User ID በሚለው ሣጥን ውስጥ ኦፕሬተር አይዲ ያስገቡ

➢ በማስከተል PIN በሚለው ሣጥን ውስጥ የምሥጢር ቁጥር ያስገቡ

➢ በመጨረሻ Login የሚለውን ይጫኑ

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 10


የፓርትነር መተግበርያው የፊት ገጽ/HOMEPAGE

ወደ ሞባይል መተግበሪያው እንደገቡ የፊት ገጽ ያገኛሉ። የፊት ገጹ


የሚከተሉትን አገልግሎቶች የያዘ ነው፡፡

በቴሌብር ያለዎትን ቀሪ የኢመኒ መጠን ለማወቅ

ያከናወኑትን ትራንዛክሽን ለማየት

ያለዎትን የኮሚሽን እና የአኑቲ ኮሚሽን መጠን ለማወቅ

እንዲሁም የተለያዩ የቴሌብር ዋንኛ አገልግሎቶችን ያገኛሉ

በቀጣይ የተሻሻለው ፓርትነር መተግበሪያ ላይ የሚገኙ አዳዲስ


አገልግሎቶችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል እንመለከታለን
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 11
የተሻሻለው የፓርትነር መተግበሪያ ምን አዲስ ነገር ይዟል
የተሻሻለው
የቀድሞው

የአኑቲ ኮሚሽን ክፍያ መጠንን የደንበኛን ደረጃ ማሳደግ


ማየት 1 3 (Customer Upgrade)

ከወኪል ወደ ወኪል ገንዘብ


ለደንበኞች ጥቅል መሸጥ (Sell
Package) 2 5 ማስተላለፍ

የቴሌኮም ቢል ክፍያ ቀድሞ


ለዋና ወኪል ገንዘብ ገቢ
የነበረ ሲሆን የተደረገው 7
የኮሚሽን ማሻሻያ ብቻ ነው
4 ማድረግ (Agent Cash-In)

ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን ከዋና ወኪል ገንዘብ ወጪ


መፈጸም (Utility Payment) 6 8 ማድረግ (Agent Cash-Out)

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 12


የተሻሻለው የፓርትነር መተግበሪያ …
ከመጠቀሚያ
አካውንታችንን የሚስጥር የስራ ሰአት እና የሱቃችንን ፎቶ ለማስገባት
ቁጥር ለመቀየር ይህን ማስገባታቸን ደንበኞች የራሳቸውን መተግበሪያ ተተቅመው
በአቅራቢያቸው የሚገኙ ወኪሎችን ለማግኝትና ሱቃቸው ክፍት
• የሚስጠር ቁጥሩ 6 አሃዝ መሆን አለበት።
የሚሆንበትን የስራ ሰአት ላማወቅ ያስችላቸዋል።
• ተከታታይ የሆኑ ቁጥሮችን መጠቅም አይችሉም።
• ከዚ በፊት የተጠቀሙትን የስሚስጥር ቁጠር ➢ change profile የሚለውን እንመርጣለን። ወኪሉ የራሱን ሙሉ
ደግመው መጠቀም አይችሉም መራጃ ቀጥሎ በሚመጣው ገጽ ላይ መመልከት ይችላል።
➢ እነዚህን መረጃዎች ሁሉንም ወኪሎች በራሳቸው መቀየር አይችሉም
ነገር ግን የተሳሳት መረጃ ካለ በኢትዮ ቴሌኮም በኡል ማስቀየር
ይችላሉ።
➢ እዚህ ጋር ከሚመጡት ውስጥ የስራ ሰአት እና የሱቃችንን ፎቶ መቀየር
የመጠቀሚያ ቋንቋ ለመቀየር እንችላለን
➢ የስራ ሰአት ለመቀየር ወይም ደሞ ከዚህ በፊት ካላስገባንና እንደ አዲስ
ለማስገባት Opening hour የሚለውን እንጫናለን።
➢ ከዛም ከሰኞ እስከ እሁድ የሰራ ሰአት ለማስገባት የሚያስችሉ
ምርጫዎችን እናገኛለን።
➢ ማስገባት የምንፈልገው ቀን ላይ ዝግ ከሆነ በቀኛ በኪል ያለውን ቁልፍ
እንጫናለን
➢ ከዛም የስራ ሰአታችንን በአግባቡ እንሞላለን።
የሚጠቀሙበትን የፓርትነር
➢ Working schedule remark በሚለው ባዶ ቦታ ላይ የምንፈልገውን
መተግበሪያ ቨርዥን ለማየት ማስታወሻ ማስቀመጥ እንችላለን።
➢ Picture የሚለው ውስጥ በመግባት የውኪሉን ሱቅ የውስጥና የውጭ
ፎቶ እናስገባለን። ይህን ማድረጋችን ደንበብኛች የወኪሉን ሱቅ በቀላሉ
ለማኝት ይረዳቸዋል።
➢ በመጨረሻም Submit የሚለውን እንጫናለን።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 13


የአኑቲ ኮሚሽን አከፋፈል
(ANNUITY COMMISSION)
የአኑቲ ኮሚሽን አከፋፈል
• ወኪሎች ደንበኛ ሲመዘግቡ እንዲሁም የተለያዩ የቴሌብር አገልግሎቶችን ለደንበኞች ሲሰጡ ኮሚሽን ይታሰብላቸዋል።

• በተጨማሪም ደንበኞች በራስ አገዝ ተጠቅመው በሚያደርጉት የገንዘብ ልውውጥ ወይም የተለያዩ ክፍያዎችን ሲፈጽሙ ኢትዮ
ቴሌኮም ከሚያገኝው የአገልገሎት ከፍያ ላይ ደንበኛውን ለመዘገበው ወኪል እንዲሁም ዋና ዋኪል አኑቲ ኮሚሽን ያስባል።

• አኑቲ ኮሞሽን የሚታሰብባቸው የአገልግሎት አይነቶች ከደንበኛ ወደ ደንበኛ ብር መላክ፣ የአየር ሰአት መሙላት, የቢል ክፍያዎች
እንዲሁም ሌሎች ኢትዮ ቴሌኮም የአገልገሎት ከፍያ የሚያስከፍልባቸው አገልግሎቶችንም ይጨምራል።

• ለምሳሌ አንድ ደንበኛ 6000 ብር ወደሌላ ደንበኛ ገንዘብ ቢልክ ለላከበት 12 ብር ለኢትዮ ቴሌኮም ይከፍላል። ከዚ የክፍያ ላይ
ደንበኛውን ለመዘገበው ወኪሉ 5 ፐርሰንት ማለትም 60 ሳንቲም ክፍያ ይፈጽማል። ለዋና ወኪሉ ደሞ ወኪሉ ያገኘውን 20 ፐርሰንት
ማለትም 12 ሳንቲም ይታሰባል።

• ይህ ክፍያ የሚታሰበው ወኪሎችን የበለጠ ለማበረታታት ነው።

• ወኪሎች ብዙ ደንበኞችን ሲመዘግቡ የተሻለ አኑቲ ኮሚሽን የማግኘት እድል ይኖራቸዋል።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 15


ለደንበኛ ጥቅል
ለመሸጥ
(SELL PACKAGE)
ለደንበኛ ጥቅል ለመሸጥ

➢ ወኪሎች ለደንበኞች ኢትዮ ቴሌኮም የሚያቀርባቸውን የድምጽ፣ የኢንተርኔት እና


የመልዕክት ጥቅሎች መሸጥ ይችላሉ።

➢ ወኪሉ የሞባይል ጥቅል ሲሸጥ 5% ኮሚሽን ሲያገኝ ለዋና ወኪሎች ደግሞ ውኪሉ ያገኝውን
ኮሚሽን 20% የሚያክል ያገኛሉ። ለምሳሌ ውኪሉ ያገኝው ኮሚሽን 10 ብር ከሆነ ዋና ውኪሉ
2 ብር ያገኛል ማለት ነው።

➢ ወኪሉ ጥቅል ሲሸጥ በሸጠው ጥቅል መጠን ከኢ-መኒው ላይ ይቀነሳል፡፡

➢ ወኪሎች ከደንበኛው የሸጡትን የጥቅል መጠን ብቻ በጥሬ ገንዘብ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

➢ ደንበኛው የገዛውን ጥቅል በአግባቡ ማግኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 17


ለደንበኛ ጥቅል ለመሸጥ …

ጥቅል ለመሸጥ Customer service ከታች በቀረቡት አማራጮች መሰረት


መጀመሪያ sell number በሚለው ሳጥን ደንበኛው የሚፈልገውን የጥቅል
01 02 03
package የሚለውን ውስጥ የደንበኛውን ስልክ አይነት መርጠው Next የሚለውን
ይምረጡ። ቁጥር ያስገቡ። ይምረጡ።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 18
ለደንበኛ ጥቅል ለመሸጥ …

የተሳክቷል መልእክት
ከዛም pin code ያስገቡትን መረጃዎች
በመተግበሪያው ላይ እና
04 አስገብተው finish 05 አረጋግጠው confirm 06
በአጭር የጽሁፍ ምልእክት
የሚለውን ይጫኑ። የሚለውን ይጫኑ።
ይላክሎታል።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 19
የቴሌብር
ደንበኝነት
ደረጃን
ማሳደግ
(Customer
Upgrade)
የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃን ማሳደግ (Customer Upgrade)
• አንድ የቴሌብር ደንበኛ በደረጃ 1 ላይ ካለ አስፈላጊውን መረጃ በሟሟላት የደንበኛውን ደረጃ ማሻሻል ይቻላል::
• ደንበኛው የቴሌብር ደንበኛ ደረጃ ሲያሳድግ ማንቀሳቀስ እና ወደ አካውንቱ ማስገባት የሚችለው የገንዘብ መጠን ጣራ
ያድግለታል።
• ነገር ግን መረጃው ቀድሞውኑ የተሟላ እና በደረጃ ሦስት ላይ ያለ ከሆነ ውኪሉ የደንበኛውን መረጃ መለወጥ
አይችልም፡፡

• የደንበኛን ደረጃ በማሳደግ ወኪሉ 10 ብር ኮሚሽን ተከፋይ ሲሆን ዋና ወኪሉ ደግሞ የ2 ብር ኮሚሽን ተከፋይ ይሆናል።

• የደንበኛው ደረጃ ከማደጉ በፊት የተቀየረው የደንበኛው መረጃ በኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር ባለሙያዎች ይጣራል።
• የደንበኛው መረጃ ተጣርቶ ሲጸድቅ ለውኪሉ የደንበኛው መረጃ መጽደቁን የሚገልጽ አጭር የጽሑፍ መልዕክት
ይላካል።
• ደንበኛው የራሱን ደረጃ (level) በከስተመር መተግበሪያ በመጠቀም my account ውስጥ በመግባት መመልከት
ይችላል።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 21


የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃን ማሳደግ …

የሚመዘግቡትን የሞባይል ቁጥር


ማረጋገጫ ቁጥሩ በሚመዘግቡት ደንበኛ ስልክ
Customer Mobile Number
Customer Upgrade ላይ ይላካል። ከደንበኛው የማረጋገጫ ቁጥሩን
01 02 በሚለው ሣጥን ውስጥ በማስገባት 03
የሚለውን ይጫኑ ማረጋገጫ ቁጥር ለማግኘት Get
በመቀበል “Verification Code” በሚለው ባዶ
ቦታ ላይ በማስገባት “Next” የሚለውን ይጫኑ
Code የሚለውን ይጫኑ
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 22
የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃን ማሳደግ …

ይህ የደንበኛ መረጃ አሞላል ደንበኛ


ሲመዘግቡ ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው።
ሁሉንም መረጃ ሞልተው
በሚቀጥለው ገጽ ላይ 05 ደንበኛው በሚያቀርበው የመታወቂያ
ከጨረሱ በኋላ customer
04 ቀድሞ የተሞላውን መረጃ መሰረት ሁሉንም መረጃዎች 06
upgrade የሚለውን
የደንበኛ መረጃ ያገኛሉ። በትክክል ይቀይሩ።
ይጫኑ

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 23


ገንዘብ ከወኪል
ወደ ወኪል
ማስተላለፍ
(AGENT
TRANSFER)
ገንዘብ ከወኪል ወደ ወኪል ማስተላለፍ

➢ የፓርትነርን መተግበርያን በመጠቀም በአንድ ዋና ወኪል ውይም ማስተር


ኤጀንት ስር ያሉ ወኪሎች እርስ በእርስ የገንዘብ ልዉዉጥ ማከናውን ይችላሉ፡፡

➢ ነገር ግን አንድ ወኪል በሌላ ዋና ወኪል ስር ካሉ ወኪሎች የገንዘብ ልዉዉጥ


ማድረግ አይችልም።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 25


ገንዘብ ከወኪል ወደ ወኪል ማስተላለፍ

2 3
1
ከኤጀንት ወደ ኤጀንት ገንዘብ ቀጥሎ የሚያስተላልፉለትን ወኪል ቀጥሎ ፒን ኮድ ያስገቡ ከዛም finish
ማስተላለፍ በምንፈልግበት ግዜ መለያ ቁጥር እና የሚላከዉን የገንዘብ የሚለውን ይጫኑ።
መጀመሪያ Agent Transfer መጠን በማስገባት Next የሚለውን
የሚለውን ይጫኑ። ይጫኑ።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 26
ገንዘብ ከወኪል ወደ ወኪል ማስተላለፍ

4 5
ከዛ በሚመጣው ገጽ ላይ የተሳክቷል መልእክት በመተግበሪያው
መረጃውን አረጋግጠው Confirm ላይ እና በአጭር የጽሁፍ ምልእክት
የሚለውን ይጫኑ። ይላክሎታል።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 27
የአገልግሎት
ክፍያ መክፈል
(UTILITY
PAYMENT)
የአገልግሎት ክፍያ

➢ ደንበኞች በቴሌብር ወኪል በኩል የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም ይችላሉ።


➢ ለአሁኑ እንደምሳሌ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ድርጅትን የአገልግሎት ክፍያ እንዴት እንደምንከፍል
እንመልከት።
➢ የሌሎቹንም ድርጅቶች ክፍያ በተመሳሳይ መልኩ መክፈል እንችላለን።
ማሳሰቢያ፡ ከደንበኛው የሚቀበሉት የክፍያ መጠን የአገልግሉት ክፍያን መጨመር ስላለበት
አጠቃላይ የክፍያ መጠኑን ከሚላክሎት የአጭር የጽሁም መልእክት ላይ ብቻ ይመልከቱ።

4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 29


የአገልግሎት ክፍያ …

ሌሎች አዳዲስ
ድርጅቶችም
በየግዜው
እየተጨመሩ
ይመጣሉ።

ከፓርትነር መተግበሪያው ላይ ከዛም በድጋሜ Utility payment ደንበኞች በኤጀንት በኩል ክፍያ
1 Utility payment የሚለውን 2 የሚለው ላይ እንጫናለን። 3 እንዲፈጽሙ የተፈቀዱ የአገልግሎት
እንመርጣለን ሰጪ ድርጅቶችን እናገኛለን።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 30
የአገልግሎት ክፍያ …

ከዛም Contract account number በሚለው ሳጥን


5 ውስጥ የደንበኛውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክፍያ
የሚፈጽምበትን የደንበኝነት ቁጠር ያስገባሉ።

Mobile number በሚለው ሳጥን ውስጥ የደንበኛውን


6 ስልክ ቁጥር አስገብተው Next የሚለውን ይጫኑ።

ቀጥሎ ባለው ገጽ ላይ የደንበኛውን መረጃ በማረጋገጥ


7 እንዲሁም የሚከፍሉትን ገንዘብ መርጠው Next
የሚለውን ይጫኑ።

8 በመቀጠል ፒን ኮድ አስገብተው finish የሚለውን


ይምረጡ።

9 በመጨረሻም pay የሚለውን ይምረጡ።

Electric utility payment በሚለው


4 ምርጫ ውስጥ Ethiopia Electric 10
ከፍያው ሲጠናቀቅ የተሳክቷል መልእክት በመተግበሪያው ላይ እና በአጭር የጽሁፍ
ምልእክት ይላክሎታል።
utility የሚለውን እንመርጣለን
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 31
ከዋና ወኪሉ ወደ
ወኪል ገንዘብ
ለማስገባት እና
ለማውጣት
(AGENT CASH-IN AND
AGENT CASH-OUT)
ከዋና ወኪሉ ወደ ወኪል ገንዘብ ለማስገባት

1 2

ዋና ውኪል በስሩ ላሉ ወኪሎች ገንዘብ ለመላክ በዋናውን ወኪል መተግበሪያ ላይ የQR Code
ዋናው ወኪሉ የሞባይል መተበሪያውን ወይም short code የሚለውን መርጠው
በመጠቀም Agent Cash-In የሚለውን መጠቀም ይችላል።
ይጫናል፡፡
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 33
ከዋና ወኪሉ ወደ ወኪል ገንዘብ ለማስገባት …
ምርጫዎ በQR ኮድ ከሆነ ምርጫዎ በወኪል ቁጥር ከሆነ

3 4

ወኪሉ ከራሱ መተግበሪያ short code የሚለውን ይመርጣሉ። የገንዘብ መጠኑን set amount
ላይ በመሆን የሚያሳየዉን የወኪሉን አጭር መለያ ቁጠር short code በሚለው ሳጥን ውስጥ በመጻፍ
QR ኮድ ስካን ያደርጋሉ። በሚለው ውስጥ ያስገቡ next የሚለውን ይጫኑ
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 34
ከዋና ወኪሉ ወደ ወኪል ገንዘብ ለማስገባት …

5 6 7

ከዛ በሚመጣው ገጽ ላይ የተሳክቷል መልእክት


ቀጥሎ ፒን ኮድ በማስገባት በመተግበሪያው ላይ እና በአጭር
መረጃውን አረጋግጠው Confirm
finish የሚለውን ይጫኑ። የጽሁፍ ምልእክት ይላክሎታል።
የሚለውን ይጫኑ።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 35
ከዋና ወኪሉ ገንዘብ ለማውጣት
➢ በመቀጠል የQR Code ወይም By short code የሚለውን መርጠው ይጫኑ።

1 ምርጫዎ በQR ኮድ ከሆነ ምርጫዎ በወኪል ቁጥር ከሆነ


2

የመረጡት QR code ከሆነ By short code የሚለውን ከመረጡ


መጀመሪያ Agent Cash Out የዋናውን ወኪል መለያ አጭር ቁጥር
የዋና ወኩሉን QR code ስካን
የሚለውን ይጫኑ short code በሚለው ውስጥ ያስገቡ
ያደርጋሉ
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 36
ከዋና ወኪሉ ገንዘብ ለማውጣት …

3 4 5 6

የገንዘብ መጠኑን set amount በሚመጣው ገጽ ላይ መረጃውን የተሳክቷል መልእክት በመተግበሪያው


ቀጥሎ ፒን ኮድ በማስገባት
በሚለው ውስጥ በመጻፍ next አረጋግጠው Confirm የሚለውን ላይ እና በአጭር የጽሁፍ ምልእክት
finish የሚለውን ይጫኑ።
የሚለውን ይጫኑ። ይጫኑ። ይላክሎታል።
4/5/2022 Prepared by Mobile Money Business Division 37
Resiliently
MOVING
FORWARD
Thank you
Stay Safe!

You might also like