Professional Documents
Culture Documents
Amharic Press - 2014 EFY Annual Business Performance
Amharic Press - 2014 EFY Annual Business Performance
ይህ ሪፖርት ከሐምሌ 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም ያለውን የኢትዮ ቴሌኮም የአንድ ዓመት
የሥራ አፈጻጸም የሚገልጽ ነው፡፡
ኩባንያችን በበጀት አመቱ 61.3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 87.6 % አሳክቷል፡፡
ይህ ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ8.5% እድገት ያለው ሲሆን በበጀት ዓመቱ
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች
ምክንያት 3,473 የሞባይል ጣቢያዎች አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ከታቀደው የገቢ እቅድ
አኳያ ክፍተት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ የጸጥታ ችግሩን በወቅቱ መቅረፍ ቢቻልና
Page 1 of 5
Page 2 of 5
አገልግሎቱን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል መስጠት ቢቻል ኖሮ ግቡን ሙሉ በሙሉ ማሳካት የሚቻል
እንደነበር ያሳያል፡፡ ሆኖም ካሉት ተግዳሮቶች አንጻር የተመዘገበው የገቢ አፈጻጸም እጅግ አበረታች
ሲሆን ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው የደንበኞች የቴሌኮም አጠቃቀምን ለማሳደግና ተሞክሯቸውን
ለማሻሻል የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያ፣ የአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ እንዲሁም የደንበኞችን
ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ወቅታዊነትን የተላበሱ 67 አዳዲስ እና 77 ነባር የሀገር ውስጥና የዓለም
አቀፍ ምርትና አገልግሎቶችን በማሻሻል ለደንበኞች ለማቅረብ በመንቀሳቀሱ ነው፡፡
የተገኘው የገቢ ድርሻ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የድምጽ አገልግሎት 51% ድርሻ ሲኖረው ዳታና
ኢንተርኔት 27%፣ ዓለም አቀፍ ገቢ 10%፣ እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች የ5.7%፣ እንዲሁም
ሌሎች አገልግሎቶች 6.6% ድርሻ አላቸው፡፡ የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 146.6
ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 82.3% ያሳካ ነው፡፡
ኩባንያችን በበጀት ዓመቱ የገቢ አማራጮችን ለማስፋት ከሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት በተጨማሪ
ወጪን በአግባቡ የመጠቀም እንዲሁም አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስወገድ እና በአጠቃላይ
ኩባንያውን ውጤታማና ምርታማ ለማድረግ የሚያስችል የወጪ መቆጠብ ስትራቴጂ (DO2SAVE
& cost optimization strategy) በመቅረጽና ተግባራዊ በማድረግ 5.4 ቢሊዮን ብር ወጪ በመቀነስ
ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት የተቻለበት ነው፡፡
የአገልግሎታችን ተጠቃሚ ደንበኞች ብዛት 66.59 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን የበጀት አመቱ አፈፃፀም
ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ18.4% እድገት እንዲሁም ከእቅድ አንጻር
የ104% አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት
64.5 ሚሊዮን፣ የመደበኛ ብሮድባንድ (Fixed Broadband) 506.8 ሺህ ፣ የመደበኛ ስልክ ደንበኞች
885.3 ሺህ እንዲሁም የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 26.1 ሚሊዮን ናቸው፡፡
Page 2 of 5
Page 3 of 5
ኢትዮ ቴሌኮም ለሁለንተናዊ ሀገራዊ እድገት ካለው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ለመንግስት በተለያየ
መልክ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገባ ተቋም እንደመሆኑ በበጀት ዓመቱ ወር 18.8 ቢሊዮን ብር ታክስና
500 ሚሊዮን ብር ዲቪደንድ ገቢ በማድረግ የሚጠበቅበትን ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽዖ ለመወጣት
ችሏል፡፡ ባለፉት ሶስት አመታት ከፍተኛ ግብር በመክፈል በተከታታይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ
ሊሆን ችሏል፡፡
Page 3 of 5
Page 4 of 5
Page 4 of 5
Page 5 of 5
ኩባንያችን በበጀት አመቱ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባጋጠመው
የፀጥታ ችግር ምክንያት የአገልግሎት መቋረጥ፣ በኔትዎርክ ሀብት ላይ የሚደርሱ አደጋዎች
እንዲሁም የፋይበርና የኮፐር መስመሮች ስርቆትና መቆራረጥ፣ ቴሌኮም ማጭበርበር፣ የኮረና
ወረርሽኝ በተቋም ንብረት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች፣ የገበያ አለመረጋጋት እንዲሁም የሃይል
አቅርቦት መቆራረጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡
ኩባንያችን በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው አበረታች አፈጻጸም ለበለጠ ስኬት የሚያነሳሳ ሲሆን
በተለይም በወቅቱ ከነበሩ ተግዳሮቶች እና የቴሌኮም አገልግሎትን ለመስጠትና ለማስፋፋት ካለው
ፈታኝ ሁኔታ አንጻር አፈጻጸሙን እጅግ አመርቂ ያደርገዋል፡፡ ይህ ውጤት የተመዘገበው የተቋሙ
የሥራ አመራር ቦርድ ከኩባንያው አመራር ጋር በመናበብና በመደጋገፍ እንዲሁም የኩባንያችን
አመራርና ሠራተኞች የኩባንያችንን ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥና ተመራጭ የቴሌኮም
አገልግሎት ሰጪ እንዲሆን ለማድረግ ካላቸው ህልም፣ ለውጤታማነቱ ባሳዩት ቁርጠኝነት
እንዲሁም በየወቅቱ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአግባቡ በመወጣት ላቀዷቸው ግቦች መሳካት
ባደረጉት ያልተቆጠበ ጥረትና ሰፊ ርብርብ ነው፡፡
Page 5 of 5