Professional Documents
Culture Documents
Cause Effect
Cause Effect
ሽያጭ አፈጻጸም ሲታይ ደግሞ የኤክስፖርት ዘርፍ ሽያጭ በዓመቱ 535,895,472.40 ብር ሽያጭ
ለማከናወን ታቅዶ የብር 223,429,419.17 ሽያጭ በማከናወን የእቅዱን 42% የተፈጸመ ሲሆን
በኢምፖርትና አገር ውስጥ ሸቀጦች ሽያጭ ዘርፍ ደግሞ የብር 2,248,256,041.18 ሽያጭ ለማከናወን እቅድ
የችግሩ ዋና ዋና ምክንያቶች
በስትራቴጅዉ መሰረት አፈጻጸምን እየገመገሙ ባለመሄዱ መሰረት አፈጻጸም ላይ አሉታዊ
ተጽእኖ ሚያሳድሩ የዉጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ስራማስኬጃ ገንዘብ ችግሮችን በወቅቱ መፍታት
አለመቻል
አመራሩ ፈጣን ዉሳኔ መስጠት ላይ ዉስንነት መኖር
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ በእቅድ ይዞ መፍትሄ ማፈላለግ ላይ ዉስንነት
መኖር
ችግሩ የሚያስከትለው ተጽእኖ
ኩባንያዉ በስትራቴጅ ዘመኑ መጨረሻ ሊያሳካ ያሰበዉን ግብ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል
ሊገኝ የታሰበዉ ተጨማሪ ገቢ ባለመሳካቱ የኩባንያዉ ተጨማሪ ማስፋፊያ ስራዎችና ላይ
ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ እንዲሁም የስራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረቱ እንዳይቀረፍ ያደርጋል፡፡
ሊወሰድ የሚገባው የመፍትሄ ሀሳብ
እቅድ በሚዘጋጅበት ወቅት ተጨባጭ አቅምን እና በተጨባጭ ሊፈጸም የሚችል መሆኑን
በማረጋገጥ ወደ ትግበራ መግባት
እቅድ አፈጻጸም ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን አስቀድሞ ለመፍታት አቅዶ
መስራት
የአመራር ዉሳኔ ቅልጥፍና ያለዉ እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም እንቅፋት የሚሆኑ የአሰራር
ስርዓቶችን በፍጥነት ማሻሻል
2. ከደንበኞች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነትን ቅሬታ በማይፈጥር መንገድ እያከናወነ
ስለመሆኑ፤
ኩባንያው በ 2016 በጀት ዓመት ከሲውዲን አገር ካስመጣው 12 ሺህ ሜ/ቶን የቢራ ገብስ ጋር በተያያዘ
የተከሰተውን የመርከብ ዲሜሬጅ USD 664,000 ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ
አገልግሎት ድርጅት ጋር እልባት ባለመስጠቱ ለኮንቴነር ማስያዣ ዲፖዚት የተደረገው ብር
20,220,141.89 የተያዘ መሆኑ፤
ኩባንያው ለአዲስ አበባ ዉሀ ስራዎች ድርጅት ካቀረበው የዲሲአይ ቧንቧና የዉሀ ፓምፕ ጋር በተያያዘ
የተፈጠረውን አለመግባባት በወቅቱ ባለፈታቱ ያልተተሰበሰበ ከ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ቀሪ ክፍያ ያለ
መሆኑ፤
ኩባንያው ከፌቤላ ዘይት ፋብሪካ እንዲያሰራጭ ውክልና የተሰጠው ቢሆንም የተወሰኑ ቦታዎችን ለሌላ
አከፋፋይ የተሰጠ መሆኑ፤
የስሚንቶ ምርት ክምችት መኖሩ ሳይረጋገጥ በባንክ ገቢ ላደረጉ ደንበኞች የሽያጭ ደረሰኝ እየተቆረጠ
የሚሰጥበት ሁኔታ ጎልቶ መታየቱንና በደንበኞች ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩ፤
ኩባንያው ለአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት የአስፋልት ቤትመንት (ሬንጅ) ለማቅረብ ውል የያዘ
ቢሆንም በወቅቱ ባለማቅረቡ በደንበኛው ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ መሆኑ፤
ኩባንያው በ 2021 በጀት ዓመት ከውጭ እያስመጣ ካከፋፈለው የፓልም ዘይት ውስጥ በመንግስት
ከተደረገ 15% የውጭ ምንዛሬ ማስተካካያ ለኩባያው የሚሰጥ የማካካሻ ክፍያ ከ 4 ኛ-6 ኛ ዙር
ለተሰራጨው ብር 98,768,585.64 ያለ ቢሆንም ከንግድ ሚኒስቴር ያልተሰበሰበ መሆኑ፤
ከአማራ ዉሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ባለዉ የጀነሬተር እና የዉሃ መሳቢያ ፓምፕ
ግብይት የተፈጠረ አለመግባባት እልባት አለማግኘቱ፤
ኩባንያው ለአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (ዓመልድ) የግሪን ሀውስ ግንባታ ማቴሪያል ከ 2
ዓመት በፊት ያቀረበ እና ተከላውን ለማሰራት ከቻይና ባለሙያ ያስመጣ ቢሆንም በአመልድ በኩል
የፋውንዴሽን ስራ ባለመጠናቀቁ ስራው ሳይከናወን ባለሙያው መመለሱ፤
ኩባንያው የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ሽያጭ በተመለከተ የደንበኞችን መረጃ አደራጅቱ
ባለመያዙ ኢትዮ ቴሌኮም ጋር በሚፈጠር የመረጃ ክፍተት ውዝፍ የአየር ስዓት ክፍያ በሚል ከ 2017
እስከ ፌብሩዋሪ 2022 ድረስ አጠቃላይ ቫትን ጨምሮ ብር 37,364,342.85 ውዝፍ ክፍያ የተጠየቀ
መሆኑ፤
ኩባንያው በአዋሳና አዳማ ሽያጭ ጣቢያ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ሽያጭ ከ 5 ዓመት በፊት ያቆመ
ቢሆንም ከገቢዎች ሚኒስቴር ጋር ተወያይቶ ያሉትን 703 የደንበኛ ማሽኖች እንዲወግዱ ባለመደረጉ
ለሰራተኛ ደመወዝና ለቤት ኪራ ወጪ የተዳረገ መሆኑ፤
ኩባንያው ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና/መቤት ጀነሬተር ለማቅረብ ዉል የያዘ ቢሆንም የማስረከቢያ
ጊዜው 31 ቀናት ዘግይቶ በማቅረቡ ለብር 140,853.29 መቀጫ የተዳረገ መሆኑ፤
ኩባንያው ለ 2013/2014 የምርት ዘመን የሚውል ጸረ አረም፤ ጸረ ተባይና ጸረ ፈንገስ ኬሚካል የውጭ
ምንዛሬ በልዩ ሁኔታ አስፈቅዶ ያስመጣ ቢሆንም ዩኔኖች፤ መሰረታዊ ማህበራ እና በኤቲኤ በኩል
የተደራጁ አካላት ፍላጎታቸውን ባለማሳወቃቸው ለስርጭት መቸገሩን ለአብክመ ግብርና ቢሮና
ለህ/ስ/ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ማሳወቁ፤
የጥቁር አባይ ትራንስፖርት አሽከርካሪ በሰሌዳ ቁጥሩ 50948/17140 የሆነ መኪና ከደርባ ሲሚንቶ
ፋብሪካ ወደ ጎንደር የጫነውን ፒፒሲ ሲምንቶ ለባለቤቱ ሳያደርስ መንገድ ላይ የሸጠው መሆኑ፤
በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ 1 ባለ 20 ፊት ኮንቴነር ከጅቡቲ ወደ ቃሊቲ በ 23/08/2020 እንዲጭን
የታዘዘ ቢሆንም የኮንቴነሩ መዳረሻ አ/አበባ መባል ሲገባው መቀሌ በመባሉ በበከልቻ ላይ አላስፈላጊ
ወጪ ማስከተሉ፤
ጥቁር አባይ ሌሎች ትራንስፖርት ድርጅቶች ከሚያቀርቡት ዋጋ የተጋነነ ከመሆኑ በተጨማሪ በገባው
ውል መሰረት በወቅቱ ተሸከርካሪ የማያስገባ መሆኑ፤
ቡሬ ከተማ ከሚገኘው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ለሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎች ስርጭት የሚውል ዘይት ወደ
አዲስ አበባ ሲያጓጓዝ በኦሮሚያ ክልል ግራር ጃርሶ ወረዳ ህገወጥ ጭነት ነው በሚል በፖሊስ ተይዞ
ከ 15 ቀን በላይ እንዲጉላላ በመደረጉ በኩባያው ላይ የጊዜና የወጪ ብክነት ማስከተሉ፤
የኩባንያውን ስሚንቶ የሚያጓጉዙ የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶች
በክልሎች መውጫና መግቢያ ኬላዎች የሚከፈሉ የኮቴ ክፍያዎች በአምባሰል እየተተካ የነበረ ቢሆንም
በራሳቸው እንዲሸፍኑ በመወሰኑ ቅሬታ እያቀረቡ መሆኑ፤
የችግሩ ዋና ዋና ምክንያቶች
ኩባንያዉ ከደንበኞች እና አጋር አካላት ጋር ያለዉን ግንኙነት ቅሬታ በማይፈጥር መልኩ
እንዲሆን የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ አለማድረግ
ኩባንያዉ የሸቀጥ አቅርቦትና ስርጭት ከደንበኞች ጋር በገባዉ ስምምነት መሰረት ሆኖ
አለመገኘት
የሚመለከተዉ የስራ ሃላፊና ባለሙያዎች ስራቸዉን በቅልጥፍና እና በሃላፊነት መንፈስ
አለመፈጸም
ሰሊጥ ሲሆን ኮሚቴው በ MTOV ወጪ አድርጎ ወደ ጎንደር ፕሮሰሲንግ የላከው 7,085.97 ኩንታል
በመሆኑ 42.98 ልዩነት ማሳየቱ፤ ጎንደር ሲደርስ በ MTIV የገቢ ሰነድ የተመዘገበው 7,125.91 ኩንታል