You are on page 1of 5

ብሉናይል ፋርማሲውቲካልስ ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን

ማህበር/ብሉፋር

እ.ኤ.አ የ 2019 ዓመታዊ አፈፃጸም ሪፖርት

ጥር 12 ፣ 2020 እ.ኤ.አ

አዲስ አበባ
አጭር መግለጫ

ብሉ ናይል ፋርማሲውቲካልስ ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ ፕሮጀክት የአዋጪነት ጥናቱ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2018
የተጠናቀቀ ቢሆንም ፕሮጄክቱ ግዙፍና ከፍተኛ የኢንቬስትመንት ወጪ የሚጠይቅ ሆኖ በመገኘቱና አሁን ባለው
ነባራዊ የካፒታል እጥረት ምክንያት ያለ አጋር ፕሮጄክቱን ወደ ትግበራ ለማሸጋገር አዳጋች ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም
የጥረት የበላይ አመራር በ 2019 እ.ኤ.አ ይህንን ፕሮጄክት በተመለከተ አጋር እና የፕሮጀክት ፋይናንስ ከማፈላለግ
ውጪ ሌላ ተግባር እንደማይኖር በመወሰኑ ምክንያት በዚህ ባሳለፍነው የስራ ዘመን አጋርና ፋይናንስ ከማፈላለግ ውጪ
በፕሮጄክት ጽ/ቤቱ የታቀደም ሆነ የተከናወነ ሌላ ስራ አልነበረም፡፡

አጋር በማፈላለጉ ረገድ ከአሜሪካ ከተገኙ ባለሀብቶች ጋር በተደረገ ግንኙነት ተስፋ ሰጪ ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡

የፕሮጀክት ጽ/ቤትን በተመለከተ ፕሮጄክቱ ደሴ ይገኝ የነበረውን ቢሮ በመዝጋት ወደ ጥረት አዲስ አበባ ጽህፈት ቤት
ተዛውሯል፡፡ እንደዚሁም ፕሮጀክቱ ብዙም የስራ እንቅስቃሴ ስላልነበረው ሰራተኞች በጥረት ኮርፖሬት አማካኝነት ሌላ
መስራያ ቤቶች ላይ እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡

I. በ 2019 የተሰሩ ዋና ዋና ዋና ስራዎች

1. የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ቢሮ ፕሮጄክቱ ከተቋቋመበት ከደሴ ከተማ ወደ ጥረት ኮርፖሬት አዲስ አበባ ማስተባበሪያ
ጽ/ቤት ተዛውሯል

Page 1 of 5
ፕሮጅክት ጽ/ቤቱን በሰው ሃይልና በቁሳቁስ ለማደራጀት ከጥረት በተሰጠው መመሪያ መሰረት እ.ኤ አ በ ጥር 2018
ፕሮጄክቱ በተቋቋመበት በደሴ ከተማ ሶስት ተጨማሪ የሰው ሀይል በመቅጠር የራሱን ቢሮ በማደራጀት ለአንድ ዓመት
ሲንቀሳቀስ ከቆየ በኋላ በድጋሚ ወደ ጥረት አዲስ አበባ ጽ/ቤት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ጽ/ቤቱ ወደ አዲስ አበባ
ከመመለሱ በፊት የፕሮጀክቱ የሂሳብ ሰነድ ከፕሮጀክቱ የሂሳብ ሰራተኛ ወደ ጥረት አዲስ አበባ ጽ/ቤት ሂሳብ ሰራተኛ
ርክክብ ተደርጓል፡፡

የሰው ሀይልን በተመለከተ ፕሮጀክቱ በ 2018 በአጠቃላይ 5 ሰራተኞች የነበረው ሲሆን አሁን ግን ከስራ አስኪያጁ
በስተቀር ሁሉም በተለያየ ምክንያት ለቀዋል፡፡

2. እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2018 በ እስፔክትረም ፋርማቴክ ኮንሰልታንትስ ፕራይቬት ሊሚትድ ካምፓኒ ተጠናቆ
የቀረበውን የፕሮጄክቱን አዋጪነት ጥናት መገምገም

የአዋጪነት ጥናቱ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2019 የፕሮጄክት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፤ የጥረት ተወካዮች እና ሌሎች
ባለሙያዎች ባሉበት በአማካሪው ድርጅት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ በዚሁ መሰረት ጥናቱ በዋና ዋና የአዋጪነት ጥናት
መለኪያዎች ተገምግሞ አዋጪ ሆኖ በመገኘቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቱ ጥናቱን ከአማካሪዎቹ ተረክቧል፡፡ በመቀጠል
ጥናቱን ለጥረት ማኔጅመንት በማቅረብና በማጸደቅ ለጥረት ቦርድ ሊቀርብ ችሏል፡፡ በመጨረሻም ቦርዱ
የአዋጪነት ጥናቱን ገምግሞ በባንክ ተቀባይነት እንዲኖረው/ባንኬብል/ ማድረግ እንደሚኖርበት አቅጣጫ
አስቀምጧል፡፡

የፕሮጀክት ትግበራን በተመለከተ ቦርዱ ፕሮጀክቱ በምእራፍ ተከፋፍሎ ሚተገበርበትን አቅጣጫም ሰቷል፡፡

3. አጋር የማፈላለግ ስራ
ፕሮጄክታችን ብሉናይል ፋርማሲውቲካልስ ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ 2018 የዋጪነት ጥናቱ የተጠናቀቀ ቢሆንም
ፕሮጄክቱ ከፍተኛ የካፒታል አቅም ስለሚጠይቅ ወደትግበራ መግባት አልተቻለም፡፡

ፕሮጄክቱን ለመተግበር ከ 246 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይንም 7 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን ይህንን የሚያህል
ትልቅ ፕሮጄክት በጥረት አቅም ለመተግበር አዳጋች ሆኖ ተግኝቷል፡፡ በመሆኑም አቅም ያለው አጋር እስኪገኝ ወደ
ትግበራ መግባት እንደማይቻል በበላይ አካል በመወሰኑ ምክንያት ባሳለፍነው የ 2019 የስራ ዘመን አጋር
ከማፈላለግ ዉጪ በብሉ ናይል ፋርማሲውቲካልስ ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ. ሌላ የታቀደ ስራ አልነበረም፡፡

Page 2 of 5
አጋር ማፈላለግን በተመለከተ፤ ለተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ተቋማት ጥያቄ በማቅረብ እና በተለያየ
መንግድ ግንኙነት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ ከሀገር ውስጥ ፣ ለአብክመ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ድጋፍና፤ክትትል
ባለስልጣን፣ ለ ዓባይ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማህበር፣ እና ለአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የፕሮጀክቱን አክሲዮን በመግዛት
አብረውን እንዲሰሩ ጥያቄ ቀርቦ መልሳቸውን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን፡፡

የውጪ ሀገር አጋር ከማፈላለግ አንጻር በተለያየዩ ጊዜያት በልየልዩ አጋጣሚ ከተገኙ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር
አጋር ለማድረግ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ይሁንና የአንዳንዶቹ ድርጅቶች ፍላጎት ከኛ ፍላጎት እና ከሀገራችን የኢንቨስትመንት ህግ ጋር የሚጣጣም ስላልነበረ


በሂደቱ መቀጠል አልተቻለም፡፡ ከነዚህ ውሥጥ በዋናነት Alves Group of companies የተባለ የእስፔይን ሀገር
የመደሃኒት አምራች ካባኒያ ተጠቃሽ ነው፡፡

እስካሁን ግንኙነቱ እንደቀጠለ ያለውና ተስፋ ሰጪ ደረጃ ላይ የሚገኘው አሜሪካ ሀገር የመገኙ Stalwart Green
Global International አና TREEJ International LLC (TREEJI) የተባሉ ጥምር አለም አቀፍ የኢንቬስትመንት
ተቋም ጋር ያለን ግንኙነት ሲሆን ተቋማቱ የብሉፋር እና የጣና ፐልፕ ፕሮጄክቶችን 80%(800 ሚሊዮን የአሜሪካን
ዶላር) የኢንቬስትመንት ወጪ የሚሸፍኑበትን የኢንቬስትመንት አግባብ ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የተቀረው
20% የጥረት ድርሻ ሲሆን በብር ተመንዝሮ የሚዋጣ ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ ስምመነቱን ለመቋጨት በጥረት በኩል
የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ባለመቻሉ ምክንያት ስምምነቱ ቢዘገይም በስተመጨረሻ የባንክ ጋራንቲው የፕሮጀክቱን
ግንባታ የሚያከናውነው China State Construction Engineering Ethiopia PLC የተባለ አለም አቀፍ የግንባታ
ተቋራጭ እንደሚያቀርብ ከስምምነት ላይ ተደርሶ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ሌላው በአምባሰል የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ ኩባኒያ በኩል የተገኘና Beacons Pharmaceuticals Pte Ltd
የተባለ የሲንጋፖር የመድኃኒት አምራች ኩባኒያ ጋር መግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም ዝግጅት ላይ ነን፡፡

እንንደዚሁም የአጋርነት ግብዠ ያቀርብንላቸውና መልስ በመጠባበቅ ላይ ምንገኝበት የፈረንሳይ፤ የሰሜን


አፍሪካ፤ወዘተ ኩባኒያዎች ይገኙበታል፡፡

4. የፕሮጀክት ፋይናንስ የማፈላለግ ስራ


ፋይናንስ ከማፈላለግ አንጻርም ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ለፕሮጄክቱ የብድር አገልግሎት መረጃ ለማገኘት የሀገር
ውስጥና የውጪ ሀገር የፋይናንስ ተቋማትን ለማነጋገር ተሞክሯል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በዋናነት የኢትዮጵያ ልማት
ባንክ፤ የኢትየጵያ ንግድ ባንክ፤ ይገኙበታል፡፡

ሆኖም ግን ሁሉም ተቋማት የብድር ጥያቄያችንን የሚያስተናግዱት ያስቀመጡትን የብድር መስፈርት ስናቀርብ
ብቻ ሲሆን ፕሮጄክታችን አሁን ባለበት ደረጃ ማቅረብ የሚችለው የአዋጪነት ጥናት እና የአከባቢ ተጽእኖ ጥናት
Page 3 of 5
ሰርተፊኬት ብቻ ነው፡፡ የመሬት ካርታ/ባለቤትን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፤የፕሮጄክት ዲዛይን/ብሉ ፐሪነት/፤ቢል ኦፍ
ኳንቲቲ፣ እና የመሳሰሉትን ሌሎች የብድር መስፈርቶች ይጎድሉናል፡፡

ከአለም አቀፍ ተቋማት የአፍሪካ ልማት ባንክንና የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬይሽንን የብድር ጥያቄ ያቀረብን
ሲሆነ፡ የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬይሽን ጥረት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመሆኑ ምክንያት የብድር ጣያቄውን
አልተቀበለውም፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክ ግን ያቀረብነውን ጥያቄ ተቀብል በማየት ላይ ይገኛል፡፡

I. ያጋጠሙ ችግሮች
 በደሴ ከተማ መስተዳድር አዘጋጅቶ ባቀረበው 10 ሄክታር መሬት የአፈርና ውሃ ምርመራ እንደዚሁም
የአከባባ እና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ ተሰርቶለት የይሁንታ ሰርተፊኬት የተገኘ ቢሆን
የአርሶአደሮች ካሳ ባለመክፈሉ ምክንያት እስካሁን መሬቱን መረከብ አልተቻለም፡፡

 በዚህ በተገባደደው የስራ ዘመን የአማካሪ የአገልግሎት ክፍያ በውጪ ሀገር ምንዛሪ እጥረት
ምክንያት እስካሁን ሳይከፈል መቆየቱ በዋናነት ሊነሱ የሚችል ችግር አንዱ ነው፡፡
II. ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

 የአዋጪነት ጥናቱ የመተግበሪያ ጊዜው እያለፈ ስለሆነ በውስጥ አቅም ለመከለስ ታቅዷል፡፡
 በጅማሮ ላይ ያሉትን አጋር የማፈላለግና ፋይናንስ የማፈላለጉን ሂደት አጠናክሮ መቀጠል
 ካሳ በማስከፈል የፕሮጄክቱን መሬት የምንረከብበትን ሁኔታ ማፋጠን
 የአዋጪነት ጥናቱን በባንክ ማጸደቅ ይቻል ዘንድ የፕሮጄክቱ ዲዛይን ከየሚዘጋጅበትን ሁኔታ
ማመቻቸት፡፡ ባንክ የአዋጪነት ጥናትን ለማጽደቅ ከሚያስፈልጉት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ
ዲዛይን ስለሆነ ነው፡፡
 የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የዘገየውን የአማካሪ የገልግሎት ክፍያ በፍጥነት እንዲከፈል
ማድረግ

Page 4 of 5

You might also like