You are on page 1of 16

በኢ.ኮ.ሥ.

ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

Company Name: Document No.:


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን OF/ECWC/006
ETHIOPIAN CONSTRUCTION WORKS CORPORATION

Issue No: 2 Document Title: Page No.:


የኦፕሬሽናል እና የመደበኛ ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትማቅረቢያ(Narrative Page 1 of 1
Summary Report)ቅጽ

ማውጫ
1. መግቢያ...................................................................................................................................................2
2. የአቅም ግንባታ ሥራዎች..............................................................................................................................5
2.1 ስልጠና፣..........................................................................................................................................5
2.2 ተሞከሮዎች ቅመራ፣............................................................................................................................5
2.3 የአሰራርስርዓት፣.................................................................................................................................5
2.4 ማኑዋሎችና የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት......................................................................................................5
3. የዓበይት ተግባራት የ 12 ወር ዕቅድ አፈጻጸም፤...................................................................................................6
3.1 የፕሮጀክቶች ዝርዝር የ 12 ወር አፈጻጸም ሪፖርት.......................................................................................7
4. የማዕከሉ ተቋማዊ ለውጥዕቅድ አፈጻጸም፤.......................................................................................................14
4.1 የወርክ ፋሲሊቴሽ (የ 1 ለ 5 ውይይት)...................................................................................................14
4.2 ካይዘንና ትግበራው፣/ Kaisen Training /..........................................................................................14
4.3 የሴቶች ጉዳይና ተሳትፎ.....................................................................................................................14
የአፕሬይዛልና ሪስክ ማኔጅመንት ዕቅድ አፈፃፀም...................................................................................................15
5. ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ፤.......................................................15
5.1 ያጋጠሙ ችግሮች.............................................................................................................................15
5.1.1 የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ማሟላት.............................................................................................................15
5.1.2 የሰዉ ሐይል ማሟላት...................................................................................................................15
5.2 የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች...........................................................................................................17
6. በአባሪገፅ፡..............................................................................................................................................18
7. ማጠቃለያ፤.............................................................................................................................................18

1
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

1. መግቢያ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል
ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ተጠሪ በመሆን በአዲስ መልክ በመደራጀት ቀደም ሲል ያልነበሩ አዳዲስ ተግባራት እና
ኃላፊነቶች ማለትም የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት፣የፕሮጀክት አፕሬይዛልና ምህንድስና፣ የፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ
እንዲሁም ፐርፎርማንስ ማኔጅመንት፣ ኮንትራት ፎርሙሌሽን እና ሪስክ ማኔጅመንት ኃለፊነቶችን እንዲወጣ ሀላፊነት
ተሰጥቶታል፡፡ ማዕከሉ እራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ሆኖ በ 2010 በጀት ዓመት ስራ እንዲጀምር ተደርጓል፡፡ ይህ
ማዕከል በቀጣይ ኮርፖሬሽኑ የሚገነባቸውን እንዲሁም በሌሎች አካላት የሚገነቡ የግንባታ ፕሮጀክቶችን የባለቤትነት ድርሻ
ውል (ኮንትራት) እየወሰደ ያስተዳድራል፤ የፕሮጀክት አመራር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በ 2010 በጀት ዓመት ማዕከሉ ዋና ዋና ግቦችን እና ዝርዝር ተግባራትን ያካተተ የ 12 ወር ክንዉኖችን


እንዲሁም በማዕከሉ ስር በተደራጀው የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት በኩል በባለቤትነት ተረክቦ
የሚያስተዳድራቸዉን መንግስታዊ ፕሮጀክቶችን በዕቅዳቸው መሠረት ያከናወነ ሲሆን፤ የ 12 ወር አፈፃፀም
መርሃ-ግብሩም ከስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዕቅድ መምሪያ ለማዕከሉ ከተሰጡት ከወቅታዊነትና ከጥራት
አኳያ መነሻ በማድረግና በመገምገም የተሠጡትን ግብረመልሶች መነሻ በማድረግ ማዕከሉ የ 2 ዐ 10
በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ደካማ እና ጠንካራ ጐኖቹን ለይቷል፡፡ እንዲሁም በሥሩ
በሚገኙት መምሪያዎች እና ቡድኖች የሚከናወኑ ሥራዎች በመደበኛ ዕቅድ ክለሳ ላይ ታርመውና ተሻሽለው
ተፈፅመዋል፡፡

ሥለሆነም በቀጣይ በዚህ ማዕከልአማካኝነት እየተከናወነ ያለዉን አፈፃፀም በላቀ ደረጃ በማሳደግ ለኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ
ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ሚና መጫወት የሚጠበቅበት ሲሆን፤ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከሉም ይህንኑ
በመገንዘብ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት የሚያስችለው አደረጃጀት በመፍጠር፤ የ 12 ወር ዕቅድ ስራዎችን ማከናወኑ
ይታወቃል፡፡

በ 2010 በጀት ዓመት ማዕከሉ ዋና ዋና ግቦችን እና ዝርዝር ተግባራትን ያካተተ ዕቅድ እና ክንዉኖችን እንዲሁም በማዕከሉ
ስር በተደራጀው የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት በኩል በባለቤትነት ተረክቦ የሚያስተዳድራቸዉን መንግስታዊ
ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጀ ሲሆን፤ የዕቅድ አፈፃፀም መርሃ-ግብሩም በዚሁ መሠረት በዝርዝር ቀርቧል፡፡ ይህ
ሪፖርት የበጀት ዓመቱን የ 12 ወርዕቅድ አፈፃፀም የሚያሳይ ነው፡፡

2
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

በዚህም መሰረት በኮርፖሬሽኑ ሥር የሚገኘው የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከልና በሥሩ በሚገኙት መምሪያዎች እና
ቡድኖች የሚከናወኑ ሥራዎችን በመደበኛዕቅድክለሳ መሰረት የ 12 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ስለሆነም
በዕቅዱ ከተያዙት የግንባታ ፕሮጀክቶች ዉስጥ፡

ሀ). ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት ውል ስምምነት ተመስርቶባቸው እየተከናወኑ
ከሚገኙ መንግስታዊ ፕሮጀክቶች መካከል፡-

1. የአራቱ ዘመናዊ የአዉቶቢስ ማቆሚያና መጠገኛ ዴፖዎች ዲዛይንና ግንባታ ስራ፤


2. የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ዋና መ/ቤት ህንጻ ግንባታ የአዋጭነት ጥናት ስራ፤
3. የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የቢሮ የማስፋፊያ ህንጻ ስራ፤
4. የኢ.ፌ.ድ.ሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፈዴሬሽን ም/ቤት አዲስ ህንጻ ዲዛይንና ግንባታ ስራ፤
5. በኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘው የባስኬት ቦልና የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ
ሜዳ ግንባታ፤
ለ.በኮርፖሬሽኑ በጀት ሊከናወኑ የታቀዱ የሕንጻ ፕሮጀክቶች

1. አዲሱ G+20 የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንጻ የዲዛይን እና ግንባታ ስራ ፕሮጀክት፤


2. የኮርፖሬሽኑ የመሳሪያዎችና የማሽነሪዎች መጠገኛ ማዕከል የዲዛይንና ግንባታ ስራ ፕሮጀክት፤
3. የኮርፖሬሽኑ አዲስ የቢሮ ማስፋፊያ ስራ(G+5) በዋናው መ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚከናወን፤
4. ከዚህ ቀደም ተጀምረው የነበሩ የኮርፖርሽኑ የቢሮ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች (4 ብሎኮች)
5. የኮርፖሬሽኑ የቃሊቲ አሮጌ ህንጻ እድሳት ስራ ፕሮጀክት፤
6. የኮርፖሬሽኑ የሞጆ ማሰልጠኛ ማዕከል ማስፋፊያ ፕሮጀክት፤
7. የኮርፖሬሽኑ የዳታ ሴንተር ግንባታ ፕሮጀክት ዲዛይን ስራ፤

በጥቅሉ በ 12 ወር ግዜ ዉስጥ በዕቅዱ ከተያዙት ተግባራት መከካል የተከናወኑቱ በሪፖርቱ ውስጥ እንዲካተቱ
ተደርጓል፡፡

2. የአቅም ግንባታ ሥራዎች


2.1 ስልጠና፣
- በማዕከሉ ያሉ ሞያተኞች በ ’’BSC- Balance Score Card Trianining” በሰው ኃብት ልማት
መምሪያ በኩል በተዘጋጁ ስልጠናዎች ባለሙያዎች አማካኝነት ለ 3 ቀን ያህል በአዲስ አበባ
ገነት ሆቴል ስልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ ተችሏል፡፡

3
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

- በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በተዘጋጀው የሶስት ቀን


የምህንድስና ክህሎት ማዳበሪያ ስልጠና ላይ 3 የማዕከሉን ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
- የማዕከሉን ሳኒተሪ መሀንዲስ በ ‘’Hydraulic modeling on Flood forcasting” ከካሊፎሪኒያ
ዩኒቨርሲቲ በመጡ ባለሙያዎች ለ 5 ቀን ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ችሏል፡፡
- በጥቅሉ ከወርክ ፋሲሊቴሽን አደረጃጀትና አተገባበር ጋር በተያያዘ ለማእከሉ ሰራተኞች በሙሉ
የአንድ ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም በባለሙያዎች ዘንድ የሚታየውን የክህሎት
ክፍተት በትክክል በመለየት በማዕከሉ ውስጥ ላሉት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን
ለማመቻቸት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

2.2 ተሞከሮዎች ቅመራ፣


ከየመምሪያው ሊገኙ የሚችሉ መልካም ተሞክሮዎችን በማጥናት፤ በመቅሰምና ከማዕከሉ ዕቅድና
ተልዕኮ ጋር በማጣጣም በስፋት በማዕከሉ ውስጥ ለመተግበር ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ይህ ሂደት ወደ
ፊትም ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ከዚሁ ጋር በማያያዝ በማዕከሉ ስር አዲስ በተቋቋመው የፕሮጀክት አፕሬይዛል መምሪያ ስር የዲዛይን


ስራ ክህሎት እየተስተዋለ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለዚህ መምሪያ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በቀጣይ
በኮርፖሬት ደረጃ በሙሉ ሀይልና በስፋት የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን ሁኔታ
ለማመቻቸት እየተሰራ ይገኛል፡፡

2.3 የአሰራር ስርዓት፣


በማዕከሉ ውስጥ ሀላፊነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ግልጽ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት ሰራተኛው
በተዘረጋው የአሰራር ስርአት መሰረት ስራውን በብቃትና በሃላፊነት መንፈስበማከናወን ውጤታማ
እንዲሆን ለማድረግእንደተተለመደው በዚህ ወር ጊዜ ውስጥም ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡

2.4 ማኑዋሎችና የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት


በማዕከሉ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በኮርፖሬሽኑ በኩል በየጊዜው እየተዘጋጁ በሚሰራጩ ማኑዋሎችና
መመሪያዎች ላይ በቂ መረጃና ግንዛቤ እንዲኖራቸውመረጃዎችን ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት ለማድረግ
ተሞክሯል፡፡ ከዚህም ባለፈ ከማእከሉ ሃላፊነት ጋር የሚያያዙና በሀገር አቀፍ ደረጃ እየወጡ በሚገኙ
ህጎች፤ኮዶችና መመሪያዎች ላይ ሰራተኞች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት
ተደርጓል፡፡

4
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

በተጨማሪም የግንባታና የማማከር የጨረታ ትንተና አቀራረብ ስርአቱን ለማዘመንና ወጥ


(Standardize) ለማድረግ የሚያግዙ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት ማኑዋሎችን በድራፍት ደረጃ
የማዘጋጀት ሂደት በዚህ ወር ተጀምሯል፡፡

3. የዓበይት ተግባራት የ 12 ወር ዕቅድ አፈጻጸም፤


የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከሉ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት፣የፕሮጀክት አፕሬይዛልና
ምህንድስና፣የፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ፤ፐርፎርማንስ ማኔጅመንት፣ኮንትራት ፎርሙሌሽን፣ወዘተ
ኃለፊነቶች የተጣለበት ማዕከል እንደመሆኑ መጠን ይህንን ሀላፊነት በብቃት ከመወጣት አንጻር በዚህ
12 ወር ጊዜ ውስጥ የሚከተሉትን አበይት ስራዎች ሲያከናውን ቆይቷል፡-

 ኮርፖሬሽኑ በአማካሪ መሀንዲሶች ዲዛይን በማሰራት ግንባታቸውን ሊያከናውን ላቀዳቸው


የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጨረታን በማውጣትና አሸናፊ አማካሪ ድርጅቶችን ለይቶ ውል በማሰር
በአማካሪ ድርጅቶቹበኩል ተዘጋጅተው በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ግምገማ በማድረግ ሙያዊ
ግብረ-መልስ ተሰጥቷል (ምሳሌ በቃሊቲ መሳሪያዎች መገጣጠሚያ፤ በፐብሊክ ሰርቪስ ዋና
መ/ቤት የአዋጭነት ጥናት ላይ እና በ 4 ቱ ዴፖቶች ጥናት ላይ)
 ኮርፖሬሽኑ በውስጥና በውጭ በጀት ከሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በተቋራጭ
ድርጅቶች በኩል የሚቀርበውን ዋጋ በመመርመርና ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር በማመዛዘን
ፕሮጀክቶች በተቻለ መጠን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲከናወኑ ለማድረግ
ከፍተኛ የድጋፍና የማማከር ስራበዚህ ወር ጊዜውስጥምቀጣይነት ባለው መልኩ ተከናውኗል፡፡
 የኮርፖሬሽኑን የሞጆ ማሰልጠኛ ተቋም ለማስፋፋት ከተያዘው እቅድ አኳያም ከህንጻ
ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፉ ጋርየግንባታ ውል ሰነድ ተፈርሞ የሳይት ርክክብ ተከናውኗል፡፡
በቀጣይ አጭር ጊዜ ውስጥ የግንባታ ሥራው እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
 ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ጋር በተፈረመው የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት ውል
ስምምነት መሰረትም ለየተቋማቱ ተገቢው የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት በ 12 ወር
ጊዜ ውስጥም ያለማቋረጥ ተሰጥቷል፡፡

3.1 የፕሮጀክቶች ዝርዝር የ 12 ወር አፈጻጸም ሪፖርት


3.1.1 የአራቱ ዘመናዊ የአዉቶቢስ ማቆሚያና መጠገኛ ዴፖዎች፡

የፕሮጀክቶቹን ዲዛይንና ግንባታ ስራ ለማከናወን ይቻል ዘንድ፤ የዲዛይንና supervision ስራው አሸናፊ
ድርጅት (ዮሐንስ አባይ አማካሪ አርኪቴክቶችና መሐንዲሶች ድርጅት) ስራውን ከየካቲት ወር

5
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

2010 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት በ 6 ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቅ በታሰረው ውል መሰረት የዲዛይን
ስራው የተጀመረ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመጀመሪያው/inception report/ ተጠናቆ ቀጣዩ የ/Schematic
Design Report/ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ይህም ሪፖርት በማዕከሉ ባለሙያዎች ተገምግሞና ተተችቶ
አስፈላጊው ግብረ መልስ ለአማካሪ ድርጅቱ በተሠጠው መሠረት በአሁኑ ወቅት ሪፖርቱ ተስተካክሎ
የተመለሰ ሲሆን ይህንኑም ተከትሎ በተደረገው የጋራ ውይይት መሰረት ቀጣይ የዲዛይን ሥራውን
ለማጠናቀቅ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

3.1.2 የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ዋና መ/ቤት ህንጻ የአዋጭነት ጥናት፡

ጥናቱን ለማጥናት ውል ያሰረው አማካሪ ድርጅት (ብሬቭ ኮንሰልታንት ኃ/የተ.የግ.ማህ) በገባው ውል


ሰነድ መሰረት የአዋጭነት ጥናት ስራውን በ 4 /አራት/ ወር ግዜ ውስጥ (ከጥር ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ)
ሰርቶ ለማጠናቀቅ በገባው ውለታ መሠረት ስራውን አጠናቅቆ የመጨረሻ ሪፖርት /Final report/
ያቀረበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ይሄው ሪፖርት በማዕከሉ ባለሙያዎች በኩል በጥልቀት ተገምግም
ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን በቀጣይ ለአሰሪዉ ድርጅት በመላክ እንዲፀድቅ በማድረግ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

3.1.3 የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ቢሮ የማስፋፊያ ህንጻ ግንባታ፡

በኮርፖሬሽኑና በጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት መካከል በተፈረመው የግንባታ ውል ስምምነት መሰረት የቦታ
ርክክቡ ቢፈጸምም ፕሮጀክቱ የሚከናወነው ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ቁጥጥር በሚደረግበት አካባቢ
ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በፕሮጀከቱ ባለቤት በኩል አንዳንድ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ አጥር ከማጠርና
በአንዱ ህንጻ ላይ ስራዎችን ከማከናወን በዘለለ አሁንም ድረስ መሰረታዊ በሆነ መልኩ ፕሮጀክቱን
በሙሉ ኃይል ለመጀመር ያልተቻለበት ሁኔታ እንዳለ ይታያል፡፡

ሥለሆነም እስካሁን ድረስ ሊከናወኑ ከሚገባቸው የስራ ክፍሎች ማለትም (Office Building,
Waiting Area, Parking Building, Guard Post, Inspection, Check Point, Fence, Site
Sanitary, Site Electrical, Civil Work) መካከል በሙሉ ሀይል መጀመር የተቻለው የዋናውን ህንጻ
ብቻ ሲሆን ይህም ህንጻ በአሁኑ ወቅት የመሰረት ስራው (Substructure work) እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡

3.1.4 የአዲሱ የህዝብ ተወካዮች እና የፈዴሬሽን ም/ቤት የዲዛይንና ግንባታ፡-

6
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ይህንን ፕሮጀክት በተለመደው የዲዛይን-ቢድ-ቢዩልድ የፕሮጀክት ትግበራ ዘዴ ለማከናወን ታቅዶ


የነበረው ሀሳብ በኋላ ላይ በዲዛይን-ቢዩልድ የትግበራ ዘዴ እንዲቀየር ተደርጎ የጨረታ ማስታወቂያው
በአለም-አቀፍ የጨረታ ሂደት መስፈርት መሰረት በጨረታ ላይ ውሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ የቤተ-መንግስቱን ጋራዥ መልሶ የማልማት ስራው
እንዲካተት በመንግስት በኩል ውሳኔ ተሰጠቷል፡፡ በመሆኑም ይህንን ተጨማሪ ስራ ለማካተት ይቻል
ዘንድ ለተወዳዳሪዎች ሰፊ የጊዜ ማራዘሚያ በመስጠት ጨረታው መጋቢት 7 ቀን 2010 ዓ.ም
ተከፍቷል፡፡

በጨረታው ላይም 7/ሰባት/ አለም አቀፍ ድርጅቶች ሰነድ ማስገባታቸው ተከትሎ የቴክኒክ ሰነድ
ግምገማው ተከናውኗል፡፡ ከቴክኒክ ግምገማ ውጤቱ ለመገንዘብ እንደተቻለውም 3 ድርጅቶች ብቻ
ዝቅተኛ የቴክኒክ ምዘና መስፈርቱን አሟልተው ወደ ቀጣዩ ዙር ውድድር አልፈዋል፡፡ ይህም ውጤት
ለሁሉም ተወዳዳሪዎች በጽሁፍ ተገልጿል፡፡ ይህንኑም ተከትሎ 2 ድርጅቶች በተሰጣቸው ውጤት ላይ
ቅሬታ እንዳላቸው በመግለጽ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ለ 2 ቱም
ድርጅቶች በቂ ማብራሪያ በጽሁፍ ተዘጋጅቶ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡

በግዢ ህጉ መሰረት ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ የ 3 ቱ ስኬታማ (Responsive) ተወዳዳሪዎች የፋይናንስ


ሰነድ ተከፍቶ የተገመገመ ሲሆን አሸናፊውን ድርጅት ለመለየትና ለማፀደቅ ለዋና ሥራ አስፈፃሚ
የቦርድ ኮሚቴ ለውሳኔ ቀርቧል፡፡

3.1.5 በጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተከናወነ የሚገኘው የባስኬት ቦልና የሜዳ ቴኒስ
መጫወቻ ሜዳ ግንባታ፡

ፕሮጀክቱ እንዳይጠናቀቅ ምክንያት ሆኖ የነበረው ከውጪ ሀገር ሊገባየሚገባው “Impermeable


HERCULAN COURTS” የውጪ ምንዛሪ ካለማግኘት ጋር በተያያዘ ረጅም ጊዜ የወሰደ በመሆኑ ምክንያት
ስራው ሊጠናቀቅ ሳይችል ለረጅም ጊዜ ያህል ቆሟል፡፡ ይሁንና በስተመጨረሻ የጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት በጉዳዩ
ላይ ጣልቃ በመግባትና ድጋፍ በማድረጉ እቃው ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ስራው በአሁኑ ወቅት እየተገባደደ
ይገኛል፡፡

3.1.6 አዲሱ G+20 የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንጻ የዲዛይን እና ግንባታ፡

የፕሮጀክቱን ዲዛይን ለማስጀመር ታቅዶ በተደረገው የተወዳዳሪዎች ግብዣ ላይ የቀረቡትን የአማካሪ


መሀንዲሶች የቴክኒክ ሰነድ ግምገማ ተጠናቅቆ ቀጣዩ የፋይናንስ ሰነድ ግምገማ በሚደረግበት ወቅት

7
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

በተለይም ሁለት አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የፋይናንስ ሰነድ በግልጽ ዋጋቸውን ለመገምገም እጅግ
አሻሚና አስቸጋሪ ሆኖ በመገኘቱና ከጨረታ ውድድር ውጪ ለማድረግም የህግ አግባብ ባለመኖሩ
ምክንያት ውድድሩን ማጠናቀቅ አልተቻለም፡፡

ሥለሆነም ይህንኑ በመገንዘብ የቴክኒክ ኮሚቴው የጨረታ ሂደቱ ውድቅ ተደርጎ ጨረታው በድጋሚ
ይወጣ ዘንድ ለምህንድስና ጉዳዮች ጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴው ባቀረበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት
ጨረታው ተሰርዞ ድጋሚ ሌላ ጨረታ እንዲወጣ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የጨረታ ሰነዱና
ማስታወቂያው ተዘጋጅቶ ለኮርፖሬት ግዢና ንብረት አስተዳደር ዋና መምሪያ ተልኳል፡፡ ሥለሆነም
ጨረታው እደተሸጠና ከተጫራቾች ለሚቀርቡ ማብራሪያዎች መልስ እየተሠጠ ይገኛል፡፡

3.1.7 የኮርፖሬሽኑ የመሳሪያዎችና የማሽነሪዎች መጠገኛ ማዕከል የዲዛይንና ግንባታ፡

የዚህን ፕሮጀክትየዲዛይን ስራ ለማስጀመር በማቀድ የአማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር


የተሻለውን ድርጅት የመምረጡ ስራ ተጠናቅቆ ከአሸናፊው አማካሪ ድርጅት (አት ኮን አማካሪ
መሐንዲሶች ድርጅት) ድርጅት ጋር በተፈረመው ውል መሰረት አማካሪው ያቀረበውን የ (”Feasibility
and Environmental Impact Assessmentreport”) ሪፖርት ከኮንስትራክሽን መሳሪያዎችና ማሽነሪ ዘርፍ
ጋር በጋራ በመገምገምእና ግብረ-መልስ በመስጠት በቀጣይ ሪፖርቱ ተጠናቅሮ ለኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት
ኮሚቴ ለውይይት እንዲቀርብና እንዲተች ጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ አማካሪው ለዚሁ የሚሆን የቅድመ-
ዝግጅት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

3.1.8 ኮርፖሬሽናችን በዋና መ/ቤት ሊገነባ የታቀደው G+5 ህንጻ፡

ለስራው የሚያስፈልገው ዲዛይንና የስራ ዝርዝር በህንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በኩል
ተከናውኖ ቀርቧል፡፡ ይህንኑም ተከትሎ ለስራው የሚያስፈልገው የዋጋ ዝርዝር በዘርፉ በኩል ተዘጋጅቶ
የቀረበ ሲሆን የቀረበውን ዋጋም በማእከሉ ባለሙያዎች አማካኝነት በመገምገምና ከወቅቱ የገበያ ዋጋ
አንጻር የዋጋ ማስተካከያ ሊደረግባቸው ይገባል ተብለው በተለዩ የስራ አይነቶች ላይ ተገቢው የዋጋ
ማስተካከያ ተደርጎና ከስምምነት ላይ ተደርሶየመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ለሚመለከተው አካል
ተላልፏል፡፡

3.1.9 የኮርፖርሽኑ የቢሮ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች (4 ብሎኮች) ግንባታ፡

8
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ለዚህ ግንባታ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ግንባታ ሥራውን ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ በአሁኑ ወቅት
ግንባታው ከውሃና ከመጸዳጃ አገልግሎት ውጪ ያሉት ስራዎች በሙሉ መሰረታዊ ሊባል በሚችል ደረጃ
የተጠናቀቁ ስለሆነ ፕሮጀክቱን በከፊል በመረከብ ህንጻዎቹን ለአገልግሎት ማዋል ተችሏል፡፡
የህንጻው የሴፕቲክ ታንክ ግንባታ ስራም በአሁኑ ወቅት በተወሰነ ደረጃ ተጀምሯል፡፡

3.1.10 በቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን ሕንጻ ጥገና ፕሮጀክት፡

ፕሮጀክቱን በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማስፈጸም ከህንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር ውል


በማሰርበጥቅሉ የእድሳት ሥራው እየተከናወን ሲሆን በዚህም መሰረት የቀለም ቅብ ሥራው ሙሉ
በሙሉ ተከናውኗል፤የኤሌክትሪካልና ሳኒተሪ ዕቃዎች ገጠማ ስራው እተጀመረ ነው፡፡ የመጀመሪያ ክፍያ
ከህንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የተጠየቀ በመሆኑ ይህንም ለማጣራት ሞያተኞች ሳይት ላይ
የተሰራውን ለማረጋገጥ የጥገና ሸነዶች እየገመገሙ ይገኛል፡፡

3.1.11 የኮርፖሬሽኑ የሞጆ ማሰልጠኛ ማዕከል ማስፋፊያ ፕሮጀክት፡

የፕሮጀክቱ የዲዛይንና የስራ ዝርዝር ስራው ተጠናቅቆ ለሕንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን


ዘርፍተልኮዘርፉ የመስሪያ ዋጋውን ያቀረበ ሲሆን በቀረበው ዋጋ ላይ አስፈላጊውን ጥናትና ግምገማ
በማድረግና የዋጋ ማሻሻያ እንደ ሚያስፈልጋቸው በተለዩት የስራ አይነቶች ላይ ማሻሻያ
እንዲደረግባቸው ለዘርፉ ተልኮ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ በመሆኑ የውል ሰነድ ተፈርሞ የግንባታ
ቦታ ርክክብ ሥራ ተከናውኗል፡፡ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር የዲዛይን የማፀደቅ ሂደት
ላይ ይገኛል፡፡

3.1.12 የኮርፖሬሽኑ የዳታ ሴንተር ዲዛይንና ግንባታ


/ ECWC-Secured Modular Data Center /

በዚህ አመት የኮርፖሬት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ዳታ ቤዝ ልማት መምሪያ የዳታ ሴንተር ዲዛይን
እንዲሰራለት ለማእከሉ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍላጎቱን በማጥናት በማዕከሉ ሥር በሚገኘው
የፕሮጀክት አፕሬይዛልና ምህንድስና መምሪያ፣የምህንድስና እና ኮንትራት ፎርሙሌሽን ቡድን የዳታ
ሴንተር ዲዛይንና የግንባታ ዝርዝር ስራ ከዋጋ ትመና አገልግሎት ጋር ሙሉ በሙሉ በማከናወን የጥናት
ሰነዱን ፍላጎቱን ላቀረበው መምሪያ መላክ ተችሏል፡፡ በመምሪያው በኩል ግንባታው እንዲ ጀመር
ውሳኔ ሲሰጥ የዋጋ ድርድር ተደርጎ ውል የሚታሰር ይሆናል፡፡
3.1.13. የ 5 የግድብ አስተዳደርማዕከላትሕንፃ ሰነድን በተመለከተ

9
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

በ 2010 የበጀት አመት የ 5 የግድብ አስተዳደደር ማዕከላት ለመገንበት በታቀደው እቅድ መሰረት የሰነድ
ዝግጅቱ ተጠናቅቋል፡፡ የሕንፃ ቴክኖሎጂና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የመስሪያ ዋጋውን እንዲያቀርብ ተደርጎ
የቀረበው ዋጋም በባለሙያዎች ተገምግሞ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡

ይህንኑም መሰረት በማድረግ ቀጣይ ውል ከመታሰሩ በፊትበግድብና መስኖ ኮ/ፕ/ፕ/ማ ዘርፍ፡ የግድብ
ኦፕሬሽን ጥገናና የተፋሰስ ሪሃብሌሽን መምሪያ የአስተዳደደር ማዕከላቱ የዲዛይን ይዘትካለው ፍላጎት
ጋር ስለ መጣጣሙና ለግንባታው በቂ በጀት ስለመያዙ ማረጋገጫ እንዲሰጥ በጽሁፍ ተጠይቋል፡፡
ሥለሆነም ይህ ሂደት ሲጠናቀቅ ውል ታስሮ ግንባታው የሚጀመር ይሆናል፡፡

3.1.14 በማዕከሉ ሥር እየተሰጡያሉ ሌሎች የማኔጅመንት አገልግሎት ስራዎች፡

የ 12 ወር ገቢ የማሰባሰብ ስራዎች

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሜጋ ፕሮጀክቶች፡-

ኮርፖሬሽኑለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጥ በሁለቱ ተቋማት መካከል የጋራ
መግባባት ላይ ተደርሶ ለጊዜው በሁለት ፕሮጀክቶችላይ ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ፕሮጀክት ለሆነው ለሴካ እርሻ የግድብ ግንባታ ወጪ ግምት ሙያዊ
አገልግሎት ለመስጠት በኮርፖሬሽኑ በኩል ለአገልግሎቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ ብር 502,632.31 ውስጥ
ለጊዜው የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ብር 251,316.10 (ሁለት መቶ ሀምሳ አንድ ሺህ ሦስት መቶ አስራ
ስድስት ሺህ ብር ከ 10 ሳንቲም) በኮርፖሬሽኑ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ስለመደረጉ መረጃ መገኘቱን ተከትሎ
ለስራው ባለሙያዎችን ወደ ፕሮጀክቱ በመላክ በፕሮጀክቱ አስፈላጊውን የልኬት ሥራ /as-built
reading / መውሰድ ተችሏል፡፡ በመሆኑ ይሄው የተጠናቆ የመጀመሪያ ሪፖርት / Draft
report /ተዘጋጅቷል፡፡ ይሄው ይበልጥ ተገምግሞና ዳብሮ ለባንኩ በቅርቡ የሚላክ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ መልኩም ባንኩ በአንድ አልሚ የቀረበለትን አንድ የአለም አቀፍ የጨረታ ሰነድ
(የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት) በኮርፖሬሽኑ በኩል እንዲገመገምለት በጠየቀው መሰረትኮርፖሬሽኑ
ለአገልግሎቱ የጠየቀው ገንዘብ ብር 83,211.70 (ሰማኒያ ሶስት ሺ ሁለት መቶ አስራ አንድ ብር ከ 70
ሳንቲም) በኮርፖሬሽኑ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ስለመደረጉ መረጃ በመገኘቱ ምክንያት ስራውን በማከናወን
ውጤቱ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

10
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሽከርካሪ ግዢ፡-

የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክለተለያዩ ተሽከርካሪዎች /ሁለት ቫኖች (ትልቅ እና ትንሽ) ፣ሃያ/20/


አውቶሞቢል እና አንድ ፎክሊፍት/ግዢ የሚሆን የጨረታ ሰነድና የመመዘኛ መስፈርት ዝግጅትና፣
ተያያዥ አገልግሎት ከኮርፖሬሽኑ ለማግኘት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከመሳሪያዎች ዘርፍ ጋር
በቅንጅት በመሆን አገልግሎቱን መስጠት እንደሚቻል የጋራ ግንዛቤ ተይዞ አገልግሎቱን ለመስጠት
የሚያስፈልገው አጠቃላይ ገንዘብ ብር 225,283.66 በኮርፖሬሽኑ የሂሳብ ቁጥር ገቢ እንዲደረግ ለባንኩ
ተገልጿል፡፡ በዚህም መሰረት የባንኩ ውሳኔ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ሥለሆነም ባንኩ ተስማምቶ ገንዘቡን
ገቢ የሚያደርግ ከሆነ አገልግሎቱ በቀጣይ ወራት ጊዜ ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የኢፌድሪ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአርባ ምንጭ ፈጥኖ ደራሽ መንገድ ስራ ፕሮጀክት፡

የፌዴራል ፖሊስ በአርባምንጭ ከተማ የ 1.154 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለማከናወን በስራ
ተቋራጮች የቀረበለትን ዋጋ ተገቢነት ኮርፖሬሽኑ እንዲገመግምለት በጠየቀው ሙያዊ ትብብር መሰረት
አስፈላጊው ሙያዊ ድጋፍና ትብብር በሙሉእጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደርጎለታል፡፡

ከኢ.ፌ.ድ.ሪ. የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የተያያዘ ስራ

የኢ.ፌ.ድ.ሪ. የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአይሲቲ ፓርክ እያከናወነ ለሚገኘው የዋና
መ/ቤቱ ህንጻ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት ለማግኘት ባቀረበው ጥያቄ መነሻነት ወርሃዊ
የአገልግሎት ክፍያችንን በጽሁፍ አሳውቀናል፡፡ ሥለሆነም ከሚ/ር መ/ቤቱ ጋር በወርሃዊ የአገልግሎት
ክፍያው ተመን ላይ ከስምምነት ከተደረሰ በቀጣይ አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ማዕከሉ ለሚሰጠው ሙያዊ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ገቢ
ከተደረገለት ጠቅላላ ገንዘብ ብር 334,527.8 (ሶስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሀያ ሰባት
ብር ከ 80 ሳንቲም) በተጨማሪ ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ከተሰጠ የፕሮጀክት ማኔጅመንት
አገልግሎት ማለትም ፡-

i. ለጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት ህንጻ ግንባታበዲዛይን “Phase” ከተሰጠው የፕሮጀክት


ማኔጅመንት አገልግሎት በውሉ መሰረትብር 180,665.00 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺ ስድስት
መቶ ስድሳ አምስት ብር) ገቢ ሆኗል፡፡
ii. ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዲዛይን “Phase” ከተሰጠው አገልግሎት በውሉ መሰረት
ሊገኝ የሚገባው ብር 703,800 (ሰባት መቶ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ገቢ ሆኗል፡፡
የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት

11
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ማዕከሉ እንደ አዲስ በመደራጀት ላይያለ እንደመሆኑ መጠን በስሩ ለሚደራጁት የስራ ክፍሎች የሰዉ
ሐይል፤የቢሮዎች እና የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፍላጎት በ 2011 ዕቅድ ለበጀት ዓመቱ ደረጃ በደረጃ
ለማሟላት ዝግጅቱ ተጠናቆ ለሚመለከታቸው ክፍሎች ሪፖርት ተደርጓል፡፡

4. የማዕከሉ ተቋማዊ ለውጥዕቅድ አፈጻጸም፤


4.1 የወርክ ፋሲሊቴሽ (የ 1 ለ 5 ውይይት)

በማዕከሉ ስር በሚገኙት ሁለት መምሪያዎች ማለትም በፕሮጀክት አፕሬይዛልና ምህንድስና


መምሪያስር ሁለት የ 1 ለ 5 ቡድን እና በፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት መምሪያ ሥር ሁለት የ 1 ለ
5 ቡድን በድምሩ በማዕከሉ ስር 4 የወርክ ፋሲሊቴሽን ቡድን ተቋቁሞ ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ
ውይይቱ በቋሚነት የቀጠለበትና ወራዊ ሪፖርት እየቀረበ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

4.2 ካይዘንና ትግበራው፣/ Kaisen Training /

የካይዘንን ፍልስፍና በመተግበር በስራ ላይ ውጤታማ ከመሆን አንጻር በተለይምየስራ ቦታን ለሰራተኞች
ምቹ ከማድረግ አንጻር በጥቅሉ አበረታች ሊባሉ የሚችሉ ስራዎች በዚህም ግዜ ውስጥ ተሰርተዋል፡፡

4.3 የሴቶች ጉዳይና ተሳትፎ

የፕሮጀክት ልማት ማዕከሉ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሁሉ በማዕከሉ ስር ያሉት ሴት


ባለሙያዎች የበኩላቸውን ተሳትፎና ሚና እንዲያ በረክቱ ከማበረታታትና ከመደገፍ አኳያ የተለያዩ
ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን ለአብነትም ያህል በሚቋቋሙ የተለያዩ ሙያዊ የኮሚቴ ስራዎች ውስጥ
በሰብሳቢነትና በጸሀፊነት ጭምር የመሪነት ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

የአፕሬይዛልና ሪስክ ማኔጅመንት ዕቅድ አፈፃፀም

በአጠቃላይ ከፕሮጀክት አፈጻጸምና ትግበራ አኳያ በዋናነት የስጋትና ሪስክ ተጋላጭ የሆኑት ጉዳዮች
ከፕሮጀክት መተግበሪያ ጊዜ (Project Schedule)፤ከስራ ደህንነት (Project Safety) ከፕሮጀክት ስኮፕ
(Project Scope)እና ፕሮጀክት ዋጋ(Project Cost) እንዲሁም ውጫዊ ሁኔታዎች (External factors)ጋር
የተያያዙት ጉዳዮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሳቢ በማድረግ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ “ Focused” ሆኖ
በጥልቀት ለመስራት ጥረት ተደርጓል፡፡

12
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

5. ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ፤


5.1 ያጋጠሙ ችግሮች

5.1.1 የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ማሟላት

በበጀት ዓመቱ በማዕከሉ ስር ለተመደቡ አዳዲስ ባለሙያዎች የሚሆን የቢሮ መገልገያ እቃዎችን ደረጃ
በደረጃ በግዥ ለመሟላት ጥረት የተደረገ መሆኑ ባይካድም በተለይም ለማዕከሉ ስራ እጅግ አንገብጋቢ
ከሆኑት የቢሮ መገልገያ እቃዎች መካከል እንደ ዴስክ
ቶፕኮምፒውተር፣ላፕቶፕ፣ፕሪንተር፣ፕሮጀክተር፣ፎቶኮፒ ማሽንና የተለያዩ ጠረዼዛዎችና
ወንበሮችንአሁንም ድረስ በቂ በሆነ ደረጃ ለማሟላት አልተቻለም፡፡ይህም በመሆኑ ምክንያት በጥቅሉ
በማዕከሉ የስራ እንቅስቃሴ ላይ ጫናን ፈጥሯል፡፡
ይህን ችግር ለማስተካካል በማቀድም የማቴሪያልና አገልግሎት ፍላጎት ክፍተቱን በመለየት በ 2011
በጀት ዓመት እቅድ ውስጥ ምላሽ እንዲያገኝ ጥያቄውን ከወዲሁ ለሚመለከተው የስራ ክፍል
ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

5.1.2 የሰዉ ሐይል ማሟላት


ማዕከሉ በሙሉ ሀይል ወደ ስራ ይገባ ዘንድ የሚያስፈልገዉን የሰዉ ሐይል ብዛት እና አይነት በጥንቃቄ
በመለየት ያዘጋጀውን የ 2010 በጀት ዓመት ዕቅድ መነሻ በማድረግ በበጀት ዓመቱ እንዲሟላለት
ለሚመለከተው ክፍል ጥያቄ በማቅረብ ባለፉት 12 ወራት ጊዜ ውስጥ ደረጃ በደረጃ የባለሙያዎች
ቅጥር ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ በዚህም መሰረት

 ለማዕከሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተመድቦለት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም አንድ የፕሮጀክት


ማኔጅመንት አገልግሎት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ በሃላፊነት ተመድበው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ለማዕከሉ ከሚያስፈልጉ ባለሙያዎች መካከልም፡-

በፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት መምሪያና በፕሮጀክት አፕሬይዛል መምሪያ ስር

 አንድ /1/ የኮንትራት መሀንዲስ፣ 4 /አራት/ ሊድ ሲቪል መሀንዲሶች፣2 / ሁለት/ ሲኒየር


አርክቴክቶች፣1/አንድ/ ስትራክቸራል መሓንዲስ፣1/አንድ/ ኤሌክትሪካል መሓንዲስ፣ 1/አንድ/ ሳኒተሪ
መሓንዲስ፣ ሶስት /3/ ኳንቲቲ ሰርቬየርስ፣1/አንድ/ ካድ ቴክኒሺያን፣ እንዲሁም 1/አንድ/ ጸሀፊና
1/አንድ/ ኦፊስ አሲስታንት፣ በቅጥርና በምደባ ተደልድለው በማዕከሉ ውስጥ በመስራት ላይ
ይገኛሉ፡፡

13
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

 የሌሎች ባለሙያዎች ፍላጎትን በቅጥርና በምደባ ለማሟላት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በማዕከሉ


የሚፈለገውን የሰዉ ሐይል የማሟላት ስራ በእቅዱ መሰረት በሚፈለገው የሙያ ስብጥር ዓይነትና
ብዛት ሊሟላ ስላልቻለ በማዕከሉ ስር መከናወን ያለባቸውን ስራዎች በማዕከሉ ላሉት ሰራተኞች
በማከፋፈል ያጋጠመውን የሰዉ ሐይል ክፍተት ለመሸፈን ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
 አንድ የህግ ባለሞያ ከሥራ መደቡ ከዚህ ወር ጀምሮ በራሱ ፈቃድ በመልቀቁና በሌሎች 2
ሞያተኞች ዝውውር (ወደ ሌላ ዘርፍ) ምክንያት፣ ስራዎችን በተሻለ ቅልጥፍናና በጥራት ለመፈጸም
ይቻል ዘንድ ክፍተቱን በቀጣይ በቅጥር ለመሸፈን ጥረት የሚደረግ ይሆናል፡፡

5.1.3 የተሽከርካሪ ግብዓት ማሟላት

በማዕከሉ ስር ላሉት ሁለት ሃላፊዎች ከተመደቡት ሁለት ተሸከርካሪዎች ውጪ ለማዕከሉ የተመደበ


ሌላ ተሸከርካሪ የለም ስለሆነም ስራዎችን ለማከናወን የግድብ ዘርፉን ውሱን ተሸከርካሪዎች በጋራ
መጠቀም የግድ ሆኗል፡፡ ሥለሆነም በቀጣይ የፕሮጀክት ማኔጅመንት አገልግሎት በሚሰጥባቸው የግንባታ
ፕሮጀክቶች ላይ ሰፊ የመስክ ክትትል ለማድረግ፤መረጃዎችን ለማሰባሰብና ፕሮጀክቶችን በአግባቡ
ለመምራትአስቸጋሪ ሁኔታ እንዳይፈጥር ለማእከሉ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ሊመደቡለት ያስፈልጋል፡፡

በዚህ 12 ወር ጊዜ ውስጥ ማዕከሉ ስራዎቹን በዕቅዱ መሰረት እንዳያከናውን ተግዳሮት ከነበሩት


ሁኔታዎች መካከል አንዱ የጨረታ ሂደቶች ከሚጠበቀው በላይ ረጅም ጊዜን መፍጀታቸው ሲሆን
ለዚህም ከውስጥ የአሰራር መንጠባጠብ ባለፈ በዋናነት ተወዳዳሪዎች ተደጋጋሚ የሆነ የጊዜ ማራዘሚያ
ጥያቄን ከማቅረባቸው ጋር በተያያዘ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ያህል የጨረታ መመለሻ ጊዜያትን ለማራዘም
ግድ ከመሆኑ ጋር የተያያዘና ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በፕሮጀክት ባለቤት መ/ቤቶች አካባቢ ከሚነሳ የፍላጎት መለዋወጥ ጋር ተያይዞ
ፕሮጀክቶችን አስቀድሞ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ለማከናወን አስቸጋሪ የሆነበት ሁኔታም ይታያል፡፡

5.2 የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች


የቢሮ መገልገያዎችን ችግር ለመቅረፍ በአስቸኳይ የግዥ ሂደት እንዲገዙ ጥያቄ በማቅረብና በማስፈቀድ
እንዲሁም የቅርብ ክትትል በመደረግ ላይ ቢሆንም ብዙም ውጤታማ መሆን አልተቻለም፡፡

ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ

14
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ማዕከሉ በዋነኛነት የእያንዳንዱን ፕሮጀክት መረጃ የማሰባሰብ፤ የፕሮጀክት ኮንትራት አስተዳደር


ስራዎችን እና የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስራዎችን አጠናክሮ ለማከናወን እንዲሁም የፕሮጀክት
አፕሬይዛል ስራዎችን በቀጣይ በትኩረት ለመስራት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በዚህም መሰረት የኮርፖሽኑን የዳታ ሴንተር ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል ዝርዝርና የተሟላ ዲዛይን
እንዲሁም “Specification & Bill of quantities” የተዘጋጀ ስለሆነ ቀጣይ የትግበራ ውሳኔን ተከትሎ
ለትግበራ ምዕራፉ ዝግጁ የማድረግ ስራ በዕቅድ ተይዟል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ መለስተኛ መሰብሰቢያ አዳራሽና ወላድ እናት ሰራተኞች በስራ ላይ በሚሆኑበት
ጊዜ ህጻናቶቻቸውን የሚያቆዩበት ጊዜያዊ ማረፊያ ሕንጻ በዋና መ/ቤታችን ቅጥር ጊቢ ውስጥ
ለመገንባት የሚያስችል የዲዛይንና የስራ ዝርዝር በማዘጋጀት ለቀጣይ ትግበራ ዝግጁ ለማድረግ
አንዳንድ ቅድመ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩም የሞጆ ማሰልጠኛ ማዕከሉን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ትኩረት
ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር-ቤት ህንጻ ግንባታ ሂደትንም የማስጀመር ስራው ትኩረት ተሰጥቶት
የሚከናወን ይሆናል፡፡

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በተያያዘም የቀረውን የአንድ ፕሮጀክት ውጤት በማጠናቀቅ ለባንኩ
ሪፖርት ለማድረግ ጥረት የሚደረግ ይሆናል፤ በተመሳሳይ መልኩም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክና
ለኢ.ፌ.ድ.ሪ. የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተሰጠው የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል ላይ
በጎ ምላሽ ከተገኘ ይህንንም ስራ በፍጥነት ለመጀመር ተገቢው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

6. አባሪ ገፅ፡
የማዕከሉ የ 12 ወር የአፈጻጸም ውጤት፤
የመደበኛ ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረቢያ ቅፅ ተያይዟል፡፡

Annex as per Plan review report.xls

15
በኢ.ኮ.ሥ.ኮ የፕሮጀክት ዴቨሎፕመንት ማዕከል የ 2010 በጀት አመት የ 12 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

7. ማጠቃለያ፤
በማዕከሉ በኩል በ 2010 የበጀት አመት ዕቅድ ውስጥ የተያዙት የመንግስታዊ የግንባታ ፕሮጀክቶች ከላይ
በዝርዝር የተቀመጡት ናቸዉ፡፡ ይሁን እንጂ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ወደ ፊት ወደ ማዕከሉ
በሚመጡት ተጨማሪ ፕሮጀክቶች መሰረት አፈፃፀሙ እያደገ የሚሔድ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ሥለሆነም በጥቅሉ ባለፉት 12 ወራት ጊዜ ውስጥ በማዕከሉ በኩል በመደበኛነት ሊከናወኑ የታቀዱ ዋና
ዋና ስራዎች የፕሮጀክቶቹን የኮንትራት አስተዳደር ስራዎችን መስራት፤ የዲዛይንና የግንባታ ነባራዊ
መረጃ የማሰባሰብ እንዱሁም የፕሮጀክቶቹን የፕሮጀክት ማኔጅመንት 2011 በጀት ዓመት ዝርዝር
መርሃ ግብር ዕቅድ መሰረትና ከዚህ በፊት የታዩትን ክፍተቶች በማስወገድ መፈጸምና የፕሮጀክት
አፕሬይዛል ስራዎችን ማከናወን ሲሆን ይህም ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ የሚከናወን ይሆናል፡፡

16

You might also like