You are on page 1of 31

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት

ጽ/ቤት የ 2016 በጀት ዓመት የ 2 ኛ ሩብ ዓመት


የካፒታል
ፕሮጀክት ሪፖርት

መግቢያ
መንግስት ካስቀመጣቸው ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች መካካል ለሀገሪቷ ያለው ውስን ሃብት ፍትሐዊ በሆነ
መንገድ ለህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማት ጥያቄዎች
ለመፍታት በከተማ አስተዳደሩ በ 2016 በመሠረት ላይ የሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች መስክ ድረስ በመሄድ
ከተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያሉበትን ደረጃ በመየት ለሚመለከተው አካል የተገኘ ውጤት
በጥንካሬ ሆነ በጉድለት በማስተላለፍ ለቀጣይ የታዩ ጥንካሬዎችን በማበረታታት እና ጉድለቶችን እንዲቀርፉ
ለማድረግ የተቋቋመው ቡድን ቦታው ድረስ በመሄድ የተለዩ ካፒታል-ፕሮጀክቶችን ያሉበትን ደረጃ በዝርዝር
በማየት ለቀጣይ መታረም ያለበት እንዲታረም በጥንካሬ መቀጠል ያለበትን እንዲያስቀጥሉ የመስክ ግብረ-
መልስ እንደሚከተለው መስጠት ተችሏል፡፡
ክፍል 1.

I.የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች በተመለከተ

1. ከለውጥ ሰራዊት ግንባታ አኳያ የተሰሩ ተግባራት


 የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች በተመለከተ ፡- ለ 2016 በጀት ዓመት ዕቅድ የፈፃሚ ዝግጅት መድረኮች ስራ
ተሰርቷል ፡፡ በመሆኑም የ 2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ከሴክተሩ ፈፃሚዎች ማጠቃለያ መድረክ በመፍጠር
አመታዊ የተግባር አፈፃፀም በማቅረብ በሂደቱ የነበሩ ጥንካሬዎች እንዲሁም የታዩ ጉድለቶች በአጠቃላይ ሰራተኛና
ማኔጅመት በመገምገም የነበሩ ጉድለቶች የ 2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አካል በማድረግ ጥንካሬዎችን በተሻለ ደረጃ
አቅቦ በመያዝ እና በማስፋት በማኔጅመንት አካላትና ከጠቃላይ ሰራተኛ መድረክ በማዘጋጀት የመገምገም ስራ
ተሰርቷል፡፡
 በመሆኑም ከማጠቃለያው መድረክ ምዕራፍ ግምገማው ለዕቅድ ዝግጅት በግብዓትነት ከተወሰዱ ዋና ዋና ጉዳዮች
ውስጥ በጉድለት ፡- ሴክተሮች እና ቀበሌዎች አካባቢ የሚሰጡ አገልግሎቶች ፈጣን ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ
አገልግሎትን ባለመስጠት በተገልጋዩ መሐበረሰብ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ሴክተሮች አካባቢ የተለያዩ
የሪፎርም ስራዎችን እንዲሰሩ ውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል ጉድለት መነሻ ማነቆዎችን አስቀድሞ
የመፍታት ስራ በመስራትና የሰው ሐይል በመመደብ በኩል የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም የአገልግሎት
አሰጣጡን ፈጣን ፤ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ ስታንዳርዱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት በኩል
የተገልጋይ እርካታን አሁንም ያረጋገጠን ባለመሆኑ ከውድቀታችን የምንማርበት እንደሆነ በመገምገም
የ 2016 ዕቅድ አካል ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
 በጥንካሬ የተለዩና ለቀጣይም በማጠናከር የሚናስቀጥላቸው ፤- ሴክተሩ ምንም እንኳን አድስ እና በርካታ
ጉድለቶች የሉበት ቢሆን ከሴክተር እስከ ዳይሮክቶሬት ሁሉም አደረጃጀቶችና እስከ ግለሰብ የደረሰና
ከተቋሙ ጋር የተናበበ ግቦች መሰረት ያደረገ የዕቅድ ዝግጅት በማድረግ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ
ለአፈፃፀሙም የግብ ስምምነት በመፍጠር ወደ ትግበራ የተገባበት አግባብ በጥንካሬ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡
 የግብዓት ማነቆን ከመፍታት አንፃር ምንም እንኳን የሰው ሀይል ፣ የሎጀስቲክ ችግሮች በስፋት የነበሩበት
ቢሆንም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የተኬደበት ርቀት በጥንካሬ ሊወሰድ የምችል ነው ፡፡
 የክትትልና ድጋፍ አግባብ ፡- በዳይሮክቶሬቶች የዕቅድ አፈጻጸምና የለዉጥ ስራዎች ላይ ምንም እንኳን
ጉድለት ቢኖርበትም የሰው ኃይል ምደባና ስምሪት አካባቢ ተግባራትን በቼ-ክሊስት መሰረት ቆጥሮ ሰቶ
ቆጥሮ ለመቀበል የተደረገዉ ጥረት በመልካምነት ተወስዶዋል ፡፡
 የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም የመገንባት ችግሮችን በመፍታት ረገድ በየደረጃው የሚገኘውን አስፈፃሚና
ፈፃሚ አካል የማስፈፀም አቅሙን በተሻለ ደረጃ ለማጎልበት የግንዛቤ እና የአስተሳሰብ ክፈተቱን
ለመሙላት በምያስችል ደረጃ የበተለያዩ ስልጠናዎች ክህሎቱን ለማሳደግ ባሳለፈነው በጀት ዓመት
የተሰራው ስራ ቀላል ነው ባይባልም ከተቋሙ አጠቃላይ ተልኮ አንፃር ሲታይ ባለሙያው አድስ ከመሆኑ
መነሻ የመፈፀም አቅም የበለጠ እንዲያድግ ተደጋጋሚ ስልጠናዎች እንደሚያስፈልጉት በተግባር ሂደት
በነበረው አፍፃፀም ለመረደት ተችሎዋል ፡፡ ሌላው እና መሰረታዊ ጉዳይ የመንግስት የማስፈፀም አቅም
ስንል የመንግስት ተቀጣሪውን ብቻ ወይም በሴክተራችን ውስጥ ያለውን ፈፃሚ ሰራተኛ ፣ የቲም
አደረጃጀት እና ማኔጅመንት አካለትን መሆኑ ሊያዝ ይገባል ፡፡ ይሁን እንጂ በሴክተራችን የለውጥ ሰራዊት
ግንባታ ስራችንን ማሳኪያና የተግባራት ሁሉ ማዕከል አድርጎ የተዘረጉ አደረጃጀቶች ውጤትን ሊያመጡና
የሴክተሩን መሰረታዊ ችግሮች በሚፈለገው ደረጃ ለመፍታትና ተግባራትን ለማሳለጥ ፈፃሚ በቲም ደረጃ
እንዲሁም በማኔጅመንት እና በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ ሰራተኛ መድረኮች እየተፈጠሩ የተቋሙን
ውጤታማነት መልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ ለማድረቅ በተቀመጠው አሰራር መሰረት
በየጊዜው እየገመገሙ ጉድለቶችን እና ክፍተቶችን በመለየት እንዲሁም ጉድለቶችን ጭምር በመሙለት
የግንባታና የቀጣይ አቅጣጫ በጋራ እያስቀመጡ ወደ ዕቅድ ቀይሮ በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ እንደ ቁልፍ
መሳሪያ ይወሰዳል ፡፡ በመሆኑም በጽ/ቤታችን የማስፈፀም አቅሙን ለማጠናከር በአንድ ቲም አንዲሁም
በአንድ የለውጥ አመራር በመደራጀት ተልዕኮ ለመፈፀም ካሉ ፈፃሚዎች የተሟላ እቅድ ተዘጋጅቶ የጋራ
ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሶ በመፈራረም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡
2.ከመልካም አስተዳደር ስራዎችን በተመለከተ

የተለዩ ዋና ዋና የመልካም አስተዳደር ውስጣዊ ችግሮች 1 ኛ/የሞተር ፎቶ ኮፒ ሲሆኑ ሌላኛው በክትትልና ድጋፍ ወቅት
እንዲሁም በግምገማ በተለዩ ጉድለቶች ወቅቱን የጠበቀ ግብረ-መልስ በተከታታይ ከመስጠትና ግብረ-መልሱ
የሚያመጣቸውን ለውጦችን በመከታተል ረገድ ውስንነቶች መኖራቸው በባለፈው ሪፖርታችን የገለጽ እንደነበር
ይታወቃል በመሆኑም በሩብ አመቱ መጨረሻ ጉድለቶችን ለማረም የተሻለ ርቀት መሄድ መቻሉ መገምገም ተችሎዋል፡፡
ሌለዉ ከዉስጥ ከተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዉስጥ 1፡- አቅጠጫ ጦቃሚ ተፔላ፣አዲሱን የማዕካለዊ ኢትዮጵያ
ክልል የራስጌ እና የእግርጌ ማህታም አሁን ላይ ተጠነቆ የታስታካከለበት ሂደት አንዱና ዋነኛ ተፈቱ ከዉስጥ የመልካም
አስተዳደር ችግሮች ነበሩ፡፡

 ውጫዊ ችግሮች ፡- ለመሰረተ ልማት የሚመደበውን ካፒታል በጀት ለታቀደለት ዓላማ በትክክል ስራ ላይ
እንዲውል የሚደረገው የክትትልና ግምገማ ስራ ውጤታማነት አነስተኛ መሆን፣የካፒታል ፕሮጀክቶች
ጥራትና ዘላቂነት ባለው መልኩ እንዲገነቡ ተገቢውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ ስራ
ከመስራት አንፃር ውስንነት ያለው መሆኑ፣ በሁሉም መዋቅሮች የስነ ህዝብን ጉዳይ የልማት አካል አድርጎ
ከመሄድ አንፃር በአንዳንድ መዋቅሮች ጉድለት ያለ መሆኑ፣ የስነ-ህዝብ ም/ቤት ስብሰባዎችን ወቅቱን
ጠብቆ በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን እየወሰኑ ማስተላለፍ ያለመቻል እና አንዳንድ ተቋማት
አካባቢ በየጊዜው የሚጠበቅባቸውን መረጃ በወቅቱና በጥራት ለሚመለከተው ኣካል ያለማቅረብ ችግር
አሁንም ያልተሸገርነው ችግር እንደሆነ ለመገምገም ተችሎዋል ፡፡ ሌላው በተቋሙ በአፈፃፀም ሂደት ላይ
ሊፈጠሩ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት የ 2016 በጀት አመት የተቋሙን የመልካም
አስተዳደር ችግር መፍቻ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ለመግባት በታቀደው መሰረት እቅዱን የማዘጋጃት
ስራ ተሰርቷል ፡፡ በዚህም መሰረት

ከውጫዊ አምስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውስጥ ፡- ለመሰረተ ልማት የሚመደበውን ካፒታል በጀት
ለታቀደለት ዓላማ በትክክል ስራ ላይ እንዲውል የሚደረገው የክትትልና ግምገማ ስራ ውጤታማነት አነስተኛ
መሆን አስመለክቶ በተለይ የዘንድሮው በጀት አካባቢ በተለየ ሁኔታ እንዲታይ እና በካቢኔ ችግሩን ጭምር
በዝርዝር በማስረዳት ለዚህ ዘርፍ የተለየ ትኩረት መስጠት የሚቻልበትሁኔታ በቅርበት ግፊት በማድረግ
በአንፃሩ የተለየ ትኩረት እንዲሰጠው ማድረግ ተችሎዋል ፡፡ ከዉጭ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እስከዚ ግዜ
ከተፈቱት ዉስጥ ከትምህርት መስረጃ ማጠራት ጋር በተያያዘ በዚ አመት እስከዚ ወር የ 03 ባለሙያ የትምህርት መስረጃ
የጠራንበት ሂደት አንዱና ዋነኛዉ የተፈታ የዉጭ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ነበሩና የተፈታበት ሂደት አለ፡፡

 የካፒታል ፕሮጀክቶች ጥራትና ዘላቂነት ባለው መልኩ እንዲገነቡ ተገቢውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ
ውጤታማ ስራ ከመስራት አንፃር ውስንነት ያለው መሆኑ፣ ምንም እንኳን በዘንድሮ በጀት የተጀመረ ነገር
ባይኖርም ባደሩ ፕሮጀክቶች በተለይ ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ተገቢውን ቼክ-ሊስት
ጭምር በማዘጋጀት ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ ፕሮጀክቶች ከተቀመጠው እና ከተዋዋሉት ስታንዳርድ
ውጪ ለመስራት በሞከሩ መሐበራት ድጋሚ ስራውን እንዲሰሩ ማድረግ ተችሎዋል ፡፡
 የመንግስት መ/ቤቶች በካፒታል ፕሮጀክቶች አስተዳደር ዙሪያ በቅንጅት ከመስራት አንፃር ጉድለቶች
መኖራቸው ፣ ከዚህ ችግርም አንፃር በተለይ ዘንድሮ ፕላን ፣ ማዘጋጃ ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ሕዝብ ክንፍ እና
ፋይናስ ሳይነጣጠሉ በተግባር በቅንጅት ፕሮጀክቶችን በመስክ ድጋፍ እና ክትትል አድረጎ ከመሄድ አንፃር
ሙሉ ለሙሉ ተቀርፎዋል በሚል ደረጃ አይደለም ኮንስትራክሽን አካባቢ ሊፈቱ የሚገቡ ቅንጅታዊ
አሰራሮች መኖራቸውን ማንሳት ይቻላል ፡፡
 ተቋማትን በውጤታማነት እየመዘኑ ከመሄድ ጋር የባለሙያው ክህሎት እና ብቃት ግዜው ከሚፈልገው
የቴክኖሎጂ እድል ጋር ተወዳዳሪ መሆን ያለመቻል ውስንነት በሁሉም ተቋማትና መስክ የታየ ነው

 የስነ-ህዝብ ም/ቤት ስብሰባዎችን ወቅቱን ጠብቆ በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችን እየወሰኑ
ማስተላለፍ ያለመቻል፣ከዚህ ችግር አንፃር ምንም እንኳን ውሳኔ የምይሹ ጉዳዮች ያጋጠሙን ባይሆኑም
የስነ-ህዝብ ምክር ቤት ጉባዔ እና ቀን በወቅቱ በማክበር የተቻለና ችግሩንም በአጭር ጊዜ መፍታት የተቻለ
ሲሆን በተለይ ከባለሙያዎች ጋር ያለው ግንኙነት የተሸለ ተብሎ የሚወሰድ ነው ፡፡
 በክልል ማዕከል ደረጃና በዞን እንዲሁም በከተማ ደረጃ ያለው የመረጃ ተነባቢነት ችግር መኖሩ፣በተለይ
ከመረጃ ጋር በተያያዘ ወደላይም ወደጎንም አሁንም የመናበብ መሰረታዊ ችግር ያለና ያልተሻገር ነው ችግር
ሆኖ ነገር ግን በወሩ ማጠቃለያ አካባቢ መሻሻሎችን ያሳየ ሲሆን በተለይ ከመረጃ ወቅታዊነት ችግር
እየተሸሻለ የመጠ ቢሆንም አሁንም ስራ መሰራት እንዳለበት የሚያሳይ ጉድለት አለ ፡፡ የክልሉን ከፌደራል
እስታቲስቲክስ ጋር ማንበብ የተቻለበት መንገድ በጥሩ እየተገመገመ ነው
 ተቋማት በየጊዜው የሚጠበቅባቸውን መረጃ በወቅቱና በጥራት ለሚመለከተው አካል ያለማቅረብ ችግር
ያለ መሆኑ፣ ከነችግሩም ቢሆን በዚኘው ወር መሻሻሎች የሉ ቢሆንም ነገር ጊን የመረጃ ወቅታዊነት
ችግሮች በተቀመጠው ጊዜ ለሚመለከተው ባለድርሻ አካላት አለማድረሱ ቀሪ ስራ አሁንም መኖሩ ታውቆ
መሰራት እንዳለበት ለመገምገም ተችሎዋል ፡፡
 የዕቅድ ዝግጅትን በተመለከተ ፡- የከተማ አስተዳደሩን የ 10 ዓመቱን መሪ የልማት እቅድ በተዋቀሩ ቴክኒካል
ቡድን የደረሰበትን ደረጃ ማትሪክስ እንዲሁም በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማስተቸት ስራ
በመስራት ተችሎዋል ፡፡ ከ 10 ዓመት ዕቅዱ መነሻም ሁሉም መዋቅሮች ካስኬድ አድርገው የ 2016 ዕቅድን
እንዲያቅዱ ተደርጓል ፡፡ የከተማ አስተዳደሩን መሪ ዕቅድ መነሻ በማድረግም የከተማ አስተዳደር ሴክተሮች
የራሳቸውን ዓመት ዕቅድ እንዲያቅዱ አቅጣጫ በተቀመጠው አግባብ ሁሉም እንዲያቅዱ ተደርጓል ፡፡
በመሆኑም የተቋሙን የ 2016 በጀት አመት ፊዚካልና ፋይናንሻል እቅድ በማቀድ ወደ ተግባር ለመግባት
ታቅዶ በእቅዱ መሰረት አቅደን ወደ ተግባር ለመግባት ተችሏል ፡፡ የ 2016 በጀት ዓመት ሁሉም ዓይነት
ዕቅድ በመከለስ በተለይ ከተቋም ጀምሮ እስከ ፈፃሚ ድረስ የውጤት ተኮር እቅድ በማቀድ ወደ ተግባር
ለመግባት በታቀደው መሰረት የተቋሙን ውጤት ተኮር እቅድ በማቀድ ካስኬድ አድርገን
ለዳይሬክቶሬትና ለፈፃሚ በማውረድ የመፈራረም ስራ ተሰርቶዋል ፡፡
 ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አንፃር ፡- የበታች መዋቅሮችን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የ 2015
ማጠቃለያ ምዕራፍ ስራዎችና የ 2016 የዕቅድ ዝግጅት ምዕራፉን በማጠናከር የቀጣይ የተግባር
ስራዎችን በተገቢው እንዲፈፅሙ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎ ግብረ መልስ የማውረድ ስራ ተሰርቷል
፡፡
 የተቋም ባለሙያዎንች እስታንደርዱን በጠበቃ መልኩ የአንደኛ ሩብ ዓመት የቢኤስሲ እና የግብ ስኮት
ምዘና በመሰብሰብ ተጠቃሎ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ተሰደርጎዋል፡፡
 በልማት ዕቅድና ዝግጅት ስራችን በተመለከተ፡- ስለ ልማት ዕቅድ ምንነትና ስለ ጠቃሜታዉን
በማስመልከት በራሪ ወራቀት በማዘጋጀት ተሰራጭቷል፡፡
 ለከተማ ሴክተር መስራቤቶች ለልማት ዕቅድ ባለሙያዎች ወክታዊ በሆና የልማትስራዎች ስልጠና
ለመስጠት ተቅዶ ተከነዉኖዋል፡፡
 የፕሮጀክቶ ፕሮፈይል አፈጻጸማቸውንና ያለባቸውን ችግር ሊግጽ በሚችል መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡
 ከተማዊ የ 60 ቀን እቅድ ታቅዶ ለዞን ተልኳል፡፡
 የሰው ኃይል አደረጃጀትን በተመለከተ
 የተቋማችን የትምህርት ማስረጃ የተጣራለቸዉ እና የልተጣራለቸዉ ባለሙያዎች በመለያት ለይተን
ሞልታን ለስልጤ ዞን ፕላን መምሪያ ና ለከተማ ፐ/ሰ/ጽ/ቤት ለመላክ ተቅዶ ተከናውኖዋል፡፡ ከስራ ሂደቱ
ሪፖርት አንፃር እስከዚ ሩብ ዓመት ሪፖርት በተገቢዉ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ተደርጎዋል፡፡
የትምህርት ማስረጃን በተመለከተ ለ 05 ወንድ እና ለ 02 ሴትም ማጣራት ተችሏል፡፡ የ 02 ሴት ሲዮሲ
ለማጣራት ፕሮሰስ በተጀማረበት ሂደት የትምህርት ቢሮ ወደዚ ለመምጠት ሽግግር እያደረጋ ስለነበራና
የስምሪት ቦታዉም ስለተከፋፈላ በቅርብ ግዜ የምንጨርስ ይሆናል፡፡ የ 2016 የዜጎች ቻርተር ሰነድ እና የኪራይ
ሰብሳቢነት ሰነድ መረጃ በጠየቁት መሰረት ተደራሽ ተደርጎዋል፡፡ እስከዚህ ሩብ ዓመት የሰው ሃይል መረጃ ለዞን ፕላን
መምሪያ ተደራሽ ለማድረግ ተቅዶ ማከናወን ተችሎዋል ፡፡ ዬተኛዉም የመንግስት ሠራተኛ በስራ ቀናቶች የራሱ
የሆነ መግቢያና መዉጫ ሰዓት መኖሩ ሚታወቅ ነዉ ስለሆናም በወሩ ዉስጥ የሚባክን የሰዓት መሸራረፍ ስላለ በየወሩ
እና በየሳምንቱ ግብረ መልስ ተዘጋጅቶ ይወርደል፡፡ ከዚ ጋር በተያያዘ የመርፈዱና ሰያስፈቅዱ የማቅረቱ ነገር
አስካሁንም መቅራፍ የልቻልነዉ አንድ የልተፈተ የዉስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑ የሚስተዋል ነዉ፡፡

ተ/ቁ የዳይሮክቶሬቶች ስም የተፈቀደ የሰው ሀይል የተቀጠረ ቀሪ ቅጥር በመ


1 ልማት ዕቅድ 04 03 01 75
2 መረጃ 03 02 01 66
3 ስነ-ህዝብ 03 01 02 33
4 የሰው ሀብት 05 02 03 40
ሴክተራል አማካይ 8 7 53

II.የተግባር አፈፃፀምን በተመለከተ

1. በፕላን ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና የዕቅድ ግቦች አፈፃፀም

 በያዝነው በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም በተገቢው ለመከታተልና ውጤታማነት


ለማረጋገጥ ተገቢውን መረጃ ማደራጀት የ 2016 በጀት አመት የዳይሮክቶሬቱ ዋና ተግባር ሲሆን የካፒታል
ያሳለፍነውን በጀት ዘመን ፕሮጀክት ዝርዝር መረጃ የያዘ ፕሮፋይል ለማዘጋጀት ታቅዶ በእቅዱ መሰረት
በፌድራል ፣ በክልል፣ በዞን ና በከተማ አስተዳር ደረጃ የሚሰሩ ካፒታል ፕሮጀክቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ
ፕሮፋይል የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል ፡፡ የተዘጋጀውን ፕሮፋይል ፕሮጀክቶችን የበጀት ምደባ ግብዓት
እንዲሆን ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ተደርጓል ፡፡ እንደ ከተማ አስተዳደር ስንመለከተው ካፒታል
ፕሮጀክቶችን የሚያሰሩ ሁሉም ሴክተር የካፒታል ፕሮጀክት ፕሮፋይል የማዘጋጀት ስራ የሰሩ ሲሆን
የእስከዚህ ወር ካፒታል ፕሮጀክት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገብ
ጉድለት በታየባቸው ፕሮጀክቶች አካባቢ ማስተካከያ ኢንዲደረግ ተደርጎዋል ፡፡
 የሴክተር መ/ቤቶችን እቅድ አፈፃፀም ለመከታተልና ለመደገፍ እንዲሁም አፈፃፀማቸው ግብ ተኮር
መሆኑን ለመከታተል ያመቸን ዘንድ የተቋማትን የተግባራት ስኬት ማሳያ ዘርፎችና አመልካቾችን
/ኢንዲኬተር/ ለማዘጋጀት በታቀደው መሰረት የሁሉንም ሴክተር መ/ቤቶች የግብ ስኬት ማሳያ ዘርፎችና
አመልካቾችን የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል፡፡ የከተማ አስተዳር ሴክተር ሴክተር መ/ቤቶችን የ 2016 በጀት ዓመት
እቅድ በመሰብሰብና በተገቢው በሶፍትና ሃርድ በማደራጀት የመጠቅለል ስራ ተሰርቶ ተጠናቆዋል ፡፡የ 2015
የሴክተሮችን እቅድ አፈፃፀም ከ 10 ዓመቱ እቅድ ጋር በማነፃፀር ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ በእቅዱ መሰረት
ተሰርቷል ግ/መልስም ተሰቶዋል ፡፡
 ተቋማትን በእውቀት እና ባደገ አስተሳሰብ ለመደግፈ እና ለመምራት ያስችል ዘንድ የከተማ አስተዳር ሴክተር
መ/ቤቶችን ፖሊሲ ሰነድ ለማደራጀትና ትንተና ለማድረግ ይረዳ ዘንድ የከተማ አስተዳር ተቋማትን
በሃርድና በሶፍት ኮፒ እንዲልኩ የመጠየቅ እና የማደራጀት ስራ በመሰራት ለይ እንገኛለን ፡፡ በዚህም
መሰረት በስካሁኑ ሂደት ለጅምር የ 01 ሴክተር መ/ቤት ፖሊሲ የማደራጀት ስራ ተጀምሮዋል ፡፡
በተጨማሪም እንደ ከተማ አስተዳር ወደ ተግባር ላደሩ ካፒታል ፕሮጀክቶች የግንባታና የኮብልስቶን
መንገድ ንጣፍ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ ሲከናወን በተጨማሪም በክልል ማቺንግ ፈንድ
ለሚሰራው የወራቤ ከተማ አስተዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ግንባታም ድጋፍ ለማድረግ ተቅዶ በድጋፍ
ወቅት አሁንም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ አለመገባቱ መገምገም ተችሎዋል ፡፡ በሴክተር ደረጃ
በሚከናወኑ በአራቱም ዳይሮክቶሬቶች ተግባር በጥንካሬና በጉድለት ደረጃ የታዩ ጉዳዮችን በመገምገም
የጽሁፍ ግ/መልስ ለማስጠት ተቅዶ ተከናውኖዋል ፡፡
 ሌላው በፕሮጀክቶች ጥራት እና ፍጥነት ዙሪያ ከባለድርሻ ጋር ከአመራሩ ፣ ከመሀበራት እና ከሌሎች
ባለድርሻ አካላት የግምገማ ሰነድ እና ማስፈፀሚያ ዕቅድ በማዘጋጀት ምክክር ለማድረግ ተቅዶ
ተከናዉኖዋል፡፡
 በከተማ አስተዳደሩ በያዝነው በጀት አመት ለሚሰሩ ካፒታል ፕሮጀክቶች እንደ ከተማ አስተዳር በተደራጀ
የባለሙያ ቡድን 04 ጊዜ ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ግ/መልስ ለመስጠት ታቅዶ 02 ዙር ማከናወን
ተችሎዋል ፡፡
 ለሴክትር መስራቤቶች በያዝነው በጀት አመት 04 ዙር በዋና ዋና ተግባራት ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ
ግ/መልስ ለመስጠት ተቅዶ 02 ዙር ተከናዉኖዋል፡፡
 በ 100 ቀኑ 2016 በጀት ዓመት የተሸለ አፈፃፀም ላሳዩ ባለሙያዎች የማትጊያ ፕሮግራም በማዘጋጀት
ማትጋት የተቻለ መሆኑን ተረጋገውጦዋል፡፡
 የተቋም ባለሙያዎንች እስታንደርዱን በጠበቃ መልኩ የአንደኛ ሩብ ዓመት የቢኤስሲ እና የግብ ስኮት
ምዘና በመሰብሰብ ተጠቃሎ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ተሰደርጎዋል፡፡
 በልማት ዕቅድና ዝግጅት ስራችን በተመለከተ፡- ስለ ልማት ዕቅድ ምንነትና ስለ ጠቃሜታዉን
በማስመልከት በራሪ ወራቀት በማዘጋጀት ተሰራጭቷል፡፡
 ለከተማ ሴክተር መስራቤቶች ለልማት ዕቅድ ባለሙያዎች ወክታዊ በሆና የልማትስራዎች ስልጠና
ለመስጠት ተቅዶ ተከነዉኖዋል፡፡
 የፕሮጀክቶ ፕሮፈይል አፈጻጸማቸውንና ያለባቸውን ችግር ሊግጽ በሚችል መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡
 ከተማዊ የ 60 ቀን እቅድ ታቅዶ ለዞን ተልኳል፡፡
 በተቋም የሪፎርም፣ህዋስ ውይይቶች በተያዘላቸው ግዜ ውይይት ተደርጓል፡፡
2. በመረጃ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና የእቅድ ግቦች አፈፃፀም በተመለከተ
 በግማሽ ዓመቱ 06 ጊዜ ወርሃዊ መረጃን ከሴክተሮች ሰብስቦ ለዞን ማዕከል ለመላክ ታቅዶ 06 ጊዜ
በሃርድና በሶፍት ኮፒ ተልኳል፡፡ ከወርሃዊ ሪፖርት ጋር በተያየዘ በተቀመጠው አስተንዳርድ መሰረት
ጥራትና ወቅቱን የጠበቀ የወርሃዊ መረጃ ሀምሌ 2015 አስከ ታህሳስ 2016 ድረስ ወር በገባ 02
ቀን ከመድረስ አንፃር ሁሉም ሴክተሮች የግዜ ገደቡን በጠበቀ መልኩ መረጃውን ሳያቆራርጡ
ወጥነት፣ተከታታይነት ባለዉ መልኩ መላክ ችለዋል፡፡ የ 2015 በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩን
ዓመታዊ የሶሾ ኢኮኖሚ መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት 01 ጊዜ ለማዘጋጀት ታቅዶ መረጃው
ተሞልቷል በከቢኔ ተጋምግሞ ለዞን ተደረሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ከተለያዩ በለድርሸ አከላት መረጀ
ፈልጎ ለሚመጡ ባለጉደዮች በጠየቁን ደብዳቤ መሰረት መረጀ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡
በግማሽ ዓመቱ የተለያዩ ዓይነት መረጃዎችን የያዘ ብሮሸሮችን 05 ግዜ ለማዘጋጀት ታቅዶ 05 ግዜ
ተዘጋጅቶ ለበለድርሻ አከላት ተሰራጭቷል፡፡ የስራ ሂደቱን መረጃ በሶፍትና በሃርድ ኮፒ የማደራጀት
ስራ ተሰርቷል፡፡በ 2016 በጀት ዓመቱ በ 1 ኛው ሩብ ዓመት መረጃ አያያዝናአደረጃጀት ለሴክተር
መረጀ ባለሙያዎችና ለቀበሌዎች በቼክ ሊስት እና ፕሮፖዛል በማዘጋጃት ድጋፍና ክትትል
ለማድረግ ተቅዶ በእቅዱ መሰረት ድጋፍ ማድረግ ሪፖርትና ግብረ-መልስ መስጠት ተችሏል፡፡የ 2015
በጀት ዓመት ፕሮፈይል ለመዘገጀት ለሴክተሮች መረጀ መጠየቂያ ፎርመት የመበተን ስራ በመስረት
መረጀ በማሰበሰብ ፕሮፈይሉን ተዘገጀቷል ተሰራጭታል ለዞንም ተደራሽ ተደርጋል፡፡ ለሴክተር
መረጀ ባለሙያዎች ስለ መረጀ ጥራት፣ታማኝናት እና በአስተደርዱ መሰረት ተደረሽ እንዲሆንና
የመረጃ አያያዝና አደረጃጀታች ምቹ እንዲሆን ስልጠና ተሰጥታል፡፡በከተማ አስተዳደር ደረጃ
የስታስቲክስ መረጃና የካርታ መረጃ በቀረበው ጥያቄ መሰረት ለተገልጋዮች ፈጣን አገልግሎት
መስጠት ተችሏል፡፡ የእርካታ ደረጃ የለበትን ደረጃ ለማወቅ መጠይቅ በመበተን የተገልጋይ ዝርካት
ተሰርታል፡፡የ 2015 መረጃ ወደ ዳታ ቤዝ የመመዝገብ ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡የከተማ አስተዳደሩን
የ 2015 በጀት ዓመት የአብስትራክት አናሊሲስ ትንተና 1 ግዜ ለማዘጋጀት ታቅዶ በእቅዱ መሰረት
ተዘጋጅቷል 2014 ለተደረገው የዉሃ፣የማብራት፣ የት/ት፣ ተቋማት፣የጤና ተቐዋማት
የትራንስፎርመሮች ጥናት ትንተና ተሰርቶ ለዞን ተደራሽ ተደርገዋል ፡

3.በስነ-ህዝብ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና የዕቅድ ግቦች አፈፃፀም በተመለከተ


 ለሴክተር ስነ-ህዝብ ቴክኒክ ኮሚቴዎች የስነ-ህዝብን ተግባር በልማት እቅዳቸው ውስጥ እንዲያካቱ
የ 2016 መነሻ እቅድ ታቅዶ በማሰራጨት ሴክተሮችም በተሰጠው መነሻ እቅድ መሰረት እቅዳቸውን
አቅደው ገቢ እንዲያደርጉ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ፡፡ የህዝብ ቁጥር እድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር ተመጣጣኝ
እንዲሆን የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግ አንፃር የአድቮኬሲ ስራን በተመለከተ በወሩ 01 ዙር በመድረኮች
በመገኘት ለመጠቀምታቅዶ 01 ዙር ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተተሰርቷል። ለከተማ ሴክተር መ/ቤቶች 01
ዙር ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ታቅዶ በእቅዱ መሰረት ድጋፍና ክትትል ተደርጓል ፡፡ አመታዊ 2016 የስነ
ህዝብ ፕሮፋይል ለማዘጋጀት ታቅዶ በእቅዱ መሰረት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል የማሰራጨት ስራ
ተሰርቷል፡፡ የቴክኒክ ኮሚቴ ውይይት ለማረግ ታቅዶ በእቅዱ መሰረት በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የስነ ህዝብ ምክር
ቤት ጉባዔ 1 ዙር ለማድረግ ታቅዶ በእቅዱ መሰረት የተለያዩ የኢኮኖሚ የአቅም ችግር ላለባቸው አካላት
ድጋፍ በማድረግ ማከናወን ተችሎዋል ፡፡

 የ 2016 በጀት ዓመት የስነ-ህዝብ/ጉ/ የስራ ሂዳትን አመታዊ ዕቅድን 01 ዙር ጊዜ ለማዛገጀት ታቅዶ
በዕቅዱ መሠረት 01 ዙር ዕቅዱን አዛገጅተን ለሚመለከተው አከል ተዳራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ የ 2016
በጀት ዓመትን ለሴክተሮች መናሸ ዕቅድ በማዛጋጀት ተድራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ የ 2016 በጀት ዓመትን
የሴክተሮችን የስነ-ህዝብ የቴክኒክ ኮሚቴዎችን ዕቅድ 01 ዙር ጊዜ ዕቅዳቸውን ለመሰባሰብ ታቅዶ
በዕቅዱ መሠረት ዕቅዱን ከሴ/መ አሰባስበን ማደራጀት ተችሏል፡፡ የ 2016 በጀት ዓመት የስነ-ህዝብ ቀን
እና የ 1 ኛውን ዙር የስነ-ህዝብ የምክር ቤት ጉባኤ ለማካሄድ የጉባኤ ሰነድ በማዛጋጀትወ 47 ሴ 13 ድ 60
ታሳታፊ በማድረግ በለድርሻ አካለትን ተሳታፊ በማድረግ ጉባኤውን በተለያዩ በፓናል ውይይት
በማድረግሁሉም ሴክተር መ/ቤቶችን የ 10 ዓመቱ ስራቴጂክ መሪ ዕቅድ በመገምጋም ና ብሮሸሮችን
በመሰራጨት ግንዛቤ በመፍጠር በተጨማሪም የቀጣይ አቅጠጫዎችን በመስቀመጥ ጉባኤውን
አስመልክቶ ለ 3 አቅማ ደካማዎች መዓድ በማጋራት ና የከተማ ጽዳትን በመስራት ጉባኤውን ማካሄድ
ተችሏል፡፡ 200 ችግኝ BDS ቦተ ላይ ችግን በመትከል ጉባኤውን ማካሄድ ተችሏል፡፡ ለሴ/መቤቶች የስነ-
ህዝብ የቴክኒክ ኮሚቴዎች በ 1 ኛውን ሩብ ዓመት ላይ ቼክሊስት አዛጋጅቶ 01 ዙር ድጋፍ ና ክትትል
ለማድረግ ታቅዶ 01 ዙር ተከናውኗል ፡፡ በጉባኤ መድረክ በመጠቀም በድምሩ 01 ዙር በስነ-ህዝብ
ዙሪያ የአድቮኬሲ ሰናድ በማዛጋጃት ና ብሮሸር በመሰራጫት የአድቮኬሲ ግንዛቤ መፍጣር
ተችሏል፡፡ 2016 በጀት ዓመት የ BSC ዕቅድን 01 ዙር ጊዜ ለማዘጋጀት ታቅዶ 01 በዕቅዱ መሠረት ዕቅዱን
ከሃለፊ ጋር ተፋራርማን ዕቅዱን ለሚመለከው አከል ተዳራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡
 3.በስነ-ህዝብ ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና የዕቅድ ግቦች አፈፃፀም በተመለከተ
 የመቀጣጠያ ሰነድ በመዘጋጃት ለሁሉም ቀበሌዎች ተደረሽ ማድረግ ተችሏል፡፡ለት/ቤቶች ቼክ-ሊስት በማዘጋጃት ድጋፍና
ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለኝ፡፡ ለቀበሌዎች የመቃጠጠያ በሰነዱ ዙሪያ በአለማ ግቡ ምን እንዳሆነ በአጠቃለይ
በተግበር ሂዳቱን ጭምር አድቮኬሲ መፍጠር ተችሏል፡፡
 ለት/ቤቶች ድጋፍ ና ክትትል የማድረግ ስራ እየተሰረ የለበት ሂዳት መሆኑን፡፡
 ለት/ቤቶች የጥያቄና መልስ ውድድር እንዲያካሄዱ የጥያቄና መልስ ሰነድ ጭምር ለት/ቤቶች ተደረሽ ማድረግ አድቮኬሲ
መፍጠር ተችሏል፡፡
 የዞን ፕላን ለማት መምሪያ እና የዞን ፋይናንስ መምሪያ በማስመልከት በስነ-ህዝብ ፅንሳ ሃሰብ ዙሪያ በረሪ ፅሁፎችን
በማሰረጫት ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡
 የሴክተሮችን የ 100 ቀን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ቼክ-ሊስት ተዘጋጅቷል፡፡

4.የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዘርፍ ስራዎች


፨ በዉል የስራ መደቦችና በአላማ አስፋጻሚ የሥራ መደብ እስከ ቀበሌ የተያዘና የልተያዘ መደብ በመለያት፤የተቋማችን
የዴስክ ኦዲት በማድረግ፤የተቋማችን የጡረታ መለያ ቁጥር የመጠላቸዉ ባለሙያዎች በመለያት እንዲሁም የተቋማችን
የ COC ማስረጃ የልተጣራለቸዉ ባለሙያዎች እና የተቋማችን የትምህርት ማስረጃ የተጣራለቸዉ እና የልተጣራለቸዉ
ባለሙያዎች በመለያት ለይታን ሞልተን ለከተማ ፐ/ሰ/ጽ/ቤት በመላክ ተደራሽ አድርገናል ፡፡ ለፐብሊክ ሰርቪስ እስታቲካል
የሰዉ ሃይል መረጃ እና ፐርሶኔል መረጃ በጥራት ተዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ተደርጎዋል ፡፡

 የተቋማችን የትምህርት ማስረጃ የተጣራለቸዉ እና የልተጣራለቸዉ ባለሙያዎች በመለያት ለይተን ሞልተን ለስልጤ ዞን
ፕላን መምሪያ ና ለከተማ ፐ/ሰ/ጽ/ቤት ለመላክ ተቅዶ ተከናውኖዋል፡፡ የትምህር ማስረጃን በተመለከተ ለ 05 ወንድ
እና ለ 02 ሴትም ማጣራት ተችሏል፡፡ የ 02 ሴት ሲዮሲ ለማጣራት ፕሮሰስ በተጀማረበት ሂደት የትምህርት ቢሮ ወደዚ
ለመምጠት ሽግግር እያደረጋ ስለነበራና የስምሪት ቦታዉም ስለተከፋፈላ በቅርብ ግዜ የምንጨርስ ይሆናል ፡፡ ዬተኛዉም
የመንግስት ሠራተኛ በስራ ቀናቶች የራሱ የሆነ መግቢያና መዉጫ ሰዓት መኖሩ ሚታወቅ ነዉ ስለሆናም በወሩ ዉስጥ
የሚባክን የሰዓት መሸራረፍ ስላለ በየወሩ እና በየሳምንቱ ግብረ መልስ ተዘጋጅቶ ይወርደል፡፡
5.ስነ-ምግባር ስራዎች በተመለከተ
 በየዝነዉ በጀት ዓመት እስከዚ ጊዜ እከ ወደ 14 በህብረተሰብ እና በመንግት እያተሰሩ የሉና ተሰርቶ የተጠነቀቁ
እንደሉ እስከዚ ወር መከታተል የተቻለ ሲሆን በሂደቱ ወጠ የለ ነገር እንደለገጠመ መገምገም ተችሏል ፡፡
የዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በዓል በመስማልከት በፅ/ቤት ደረጃ በማክበር ሪፓርት ተሰርቶ ለሚመለካተዉ
አካል ተደራሽ ተደርጎዋል፡፡ የ 2015 የዞን ማትጊያን በመጠቀም ለተለያዩ የ/ህ/ሰብ ክፍሎችና ከተለያዩ
ተቋማት ለመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች ስለ ስነ-ምግባር ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ብሮሸር በማዘጋጀት
ተሰራጭቷል፡፡በተቋም ደረጃ ለባለሙያዎች የአሰራር መመሪያዎችን እንዳይጥሱ በስነ-ምግባር ዙሪያ ምክር
ለማድረግ ተቅዶ ተከናውኖዋል ፡፡እንደ ማንኛውም ተግባር ተግባሩ በማኔጅመንት እና በህዝብ ክንፍ ሪፖርት
በማቅረብ ለማስገምገም ተቅዶ ማከናወን ተችሎዋል ፡፡ የካፒታል ፕሮጀክት ክትትልና ጥቆማ ከመስጠትና
ከማረጋገጥ አንፃር በስነ-ምግባር ዙሪያ ወጠ ያለ የገጠመን ነገር አለመኖሩን በድጋፍና ክትትል ወክት
መለያት ተችሎዋል፡፡ በአንደንድ በልተግባበነበቸዉ ጫፍ በወጡ በስነ-ምግባር ጉዳዮች ላይ ቁጭ ብለን
ዉይይት በማድረግ የተፈተበት ሂደት አለ ፡፡የ 2016 ዓመታዊ የስነ-ምግባር ዕቅድ በማቀድ ለሚመለከተዉ
አካል ተደራሽ ተደርጎዋል፡፡የአደሩ የካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ የሚስተዋሉ የሲሚንቶ ሬሾ
እንዲሁም ክረምቱን ተከትሎ የሚስተዋሉ የጥራት ጉድላት በሚፈጥሩ የግንባታ መሀበራት ላይ
ማስተካከያ እንድያደርጉ ማድረግ ተችሎዋል ፡፡
6.ስራተ ፆታን በተመለከተ

 የ 2016 ዓ.ም አመታዊ እቅድ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ተደረሽ ተደርጓል፡፡የሴክተር መ/ቤቶችን
2016 ዓመታዊ ዕቅድ ሰብስበን ሴቶችና ህፃናትን አከተው የቀዱ ሴክተሮች ስንመለከት
እንተርፕራይዝና ልማት ፅ/ቤት፣ግብርና ፅ/ቤት ፣ባልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ፣ህብራት ስራ ዩኒት ፣ሰላምና
ፀጥታ ፅ/ቤት፣ወጠቶችና ስፖርት ፅ/ቤት፣ ጤና ፅ/ቤት፣ ሴቶችና ህፀናት ፅ/ቤት፣ ትራንስፖርት
ፅ/ቤት፣ት/ት ፅ/ቤት ና ሠረተኛና ማህባራዊ ፅ/ቤት ነቸው ፡፡በመስራቤተችን ውስጥ የሉ ሰረተኞች 4
ወንድ እና 4 ሴት ውስጥ 2 ሴት እና 2 ወንድ መኔጅመንት አባለት ነቸው፡፡ የስነ-ህዝብ ቀንና የስነ-ህዝብ
የምክር ቤት ጉባኤ በመክበር በተመለከተ ወንድ 50 እና ሴት 50 ተቅዶ ወንድ 47 ሴት 13 በድምሩ 60
ተሰተፊ በማድረግ መከሄድ ተችሏል፡፡የስነ-ህዝብ ቀንና የስነ-ህዝብ የምክር ቤት ጉባኤ በመስመልከ ለ 3
ለአቅማ ደካማዎች 30 ኪሎ ሩዝ እና 9 ሊትር ዘይት ድጋፍ በማድረግና ፅዳት በማፅዳት የእለቱን
ፕሮግራም ማከነወን ተችሏል፡፡የአቅማ ደካማን አንድ ልጅ 1|(አንድ) ለደብተር ና ለእስኪሪብቶ ወጪ የሚሆን
በወላጁ እጅ 4032 ብር በጽ/ቤቱ ወጪ ተደርጎለታል፡፡ሴክተር መስራቤቶች የ 2 ኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል
ለማድረግ ቼክ-ሊስትና ፕሮፖዛል ተዘጋጅቷል፡፡የስራታ ፆታውን ፈይል በተገቢው መደረጃት ተችሏል፡፡
ስራታ ፆታን በተመለከተ 03 ብሮሻር ተዘጋጅቷል፡፡

#ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ በተመለከተ


1. የኮብል ስቶን እና ድች ግንባታ በተመለከተ፡- ከመሊቅ እስከ ሲያም ጁስ ድረስ ሲሆን አክቾት የኮብል አስቶን
ንጠፍ ማህባር በብር 3,909,757.17 አሸንፎ ስራውን በመስራት ላይ ስሆን አፈጻጸሙም 100% ነው፡፡
2. የከተማው የውሃ ግንባታ በተመለከተ፡- ገርማማ ሲሆን GTB የግንባታ ተቋራጭ በማሸነፍ በብር
345,221,988.16 አሸንፎ ስራውን መስረት የጀመረ ሲሆን የተከፈለ ክፍያ 103,566,596 ውል የተገባበት ቀን
09/02/2021 ስራው የሚጠናቀቅበት ቀን 09/08/2022 ሲሆን ስራው በ 03 ቱም ሰይቶች የጀነሬተር ቤት
ግንባታ መሰረት ወቶዋልና መጸዳጃ ግንባታ በ 03 ሳይት ተቆፍሮዋል፣ ፓምፓ ሃውሱ ተቆፍሮዋል፣ ሰርቪስ
ፓምፕ ቁፋሮ ተጀምሮዋል ለነዚህ የሚሆን ድንጋይና አዋዋ ቀርቧል፣ 26 ሜትር ስፋት ያለው ሪዘርቫየሩ
ተቆፍሮ ቢን ኮንክሪት ተሰርቷል፣መናሃሪያ ውስጥ ያለው መጸዳጃ መሰረቱ ወቶዋል እና ሻወር ቤቱ መሰረቱ
ወቶዋል፡፡ ይህ የከተማችን 80 ኪ/ሜ የሚሸፍን ውሃ በተያዘለት ወቅት ወደ ተግባር ከመግባት አንጻር ጉድለት
ስላለበት የሚመለከተው አካል ክትትል ቢያደርግለት የተሸለ ነው አፈጻጸሙም 22% ነው፡፡
ስራው የቆመ ስለሆና የሚመለከተው አካል ድገፍ ብያደርግለት ጥሩ ነው፡፡
3. የፕሮጀክቱ ስም የትምህርት ጽ/ቤት የቤተ-መጽሀፈት ግንባታ በተመለከተ፡- ለመሰረት ጨረታ ወጥቶ ሲ 4
ፎር የግንባታ ማህበር በማሸነፍ ውል የተገባበት ገንዘብ መጠን 2,597,464.25 ሲሆን አፈጻጸሙም 100% ላይ
ይገኛል፡፡
4. የፕሮጀክቱ ስም አስተዳደር የቢሮ ግንባታ በተመለከተ፡- ለመሰረት ጨረታ ወጥቶ ደሪር የግንባታ ተቋራጭ
በማሸነፍ ውል የገበበት በብር 165, 940,560.6 ስሆን አፈጻጸሙም 30% መሆኑ ተቋራጩ ውል ከገባበት ቀን
አንጻር ጥሩ ስለሆነ ክትትልና ድጋፍ በዝህ ሊክ ቢደረግ የተሸለ ነው፡፡
5. የፕሮጀክቱ ስም የፖሊስ ጽ/ቤት ተጠርጣሪ ቢሮ ግንባታ በተመለከተ፡- ለመሰረት ጨረታ ወጥቶ ኤግል
የግንባታ ማህበር በማሸነፍ ውል የተገባበት ገንዘብ መጠን 354,563.23 እስካሁን የተከፈለ ገንዘብ መጠን
93,198.44 ቀሪ ብር 261,36479 ስሆን አፈጻጸሙም 78% መሆኑ ተቋራጩ ውል ከገባበት ቀን አንጻር የዘገያ
ስለሆነ ክትትልና ድጋፍ ቢደረግት አሁን ላይ ውልተቋርጧል፡፡

6. የፓርክ ግንባታ በተመለከተ፡- አቴንቲክ ጠቅላለ ተቋራጭ በማሸነፍ በብር 5,949,600 አሸንፎ ስራውን
የጀመረ ሲሆን የተከፈለ ክፍያ 1,784 ,880 ሲሆን ስራውን በተያዘለት የግዜ ገደብ ከመሰረት አንጻር ውስንነት
ስላለበት ክትትልና ድጋፍ ቢደረግለትና አፈጻጸም 100%፡፡
7. የፓርክ ግንባታ ፌዝ ሁለትን በተመለከተ፡- አበራ አብዲ ጠቅላለ ተቋራጭ በማሸነፍ በብር 23,960,378
አሸንፎ ስራውን የጀመረ ሲሆን የተከፈለ ክፍያ 7,188 ,113.4 ሲሆን ስራውን በመስረት ብሞችንመቆምና
ዲች እንድሁም ኢስለቨ ከቨር መስረት ችሏል፡፡ አፈፃፀሙ 95% ላይ ይገኛል፡፡
8. የመማሪያ ክፍል ግንባታ በተመለከተ፡- አምልግጥ የግንባታ ማህበር በማሸነፍ በብር 2,824,961 አሸንፎ
ስራውን በመስራት ላይ ሲሆን ስራው በጥሩ ሁኔታ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡ አፈጻጸም 100%ነው፡፡
9.የአናስተኛ ድልድይ ግንባታ ዛሞ የከብት እርባታ ሼድ አከበቢ የሚገነበውን በተመለከተ፡- ሞሃ የግንባታ
ማህበር በማሸነፍ በብር 2,691,827.54 አሸንፎ ስራውን በመስራት ላይ ሲሆን አፈጻጸም ፊዝካል 100%
ስሆን ፋይናሻል 100%ነው፡፡
10.የውሃሪዘርቫይር ግንባታ ፡- ሀይራንዚ ግቢ ውስጥ የሚሰረ ስሆን ስረውን ለመሰረት ጨረታ ወጥቶለት ስራውን
የሸነፈው ማህበር ፐርፌክት የግንባታ ማህበር በብር 579,138.22 አሸንፎ ስራውን መጠናቀቅ ችሏል፡፡
11.የኢትርፒራይዝ ሼድ ግንባታ ፡- ኢንድስትሪ መንደር ውስጥ የሚሰረ ስሆን ስረውን ለመሰረት ጨረታ
ወጥቶለት ስራውን የሸነፈው ማህበር አምልግጥ የግንባታ ማህበር በብር 5,333,080.28 አሸንፎ ስራውን በመስራት
ላይ ነው፡፡
13. የፕሮጀክቱ ስም የማዘጋጃ ቤት አጥር ግንባታ በተመለከተ፡- ለመሰረት ጨረታ ወጥቶ መርከቡ የግንባታ
ተቋረጭ በማሸነፍ ውል የተገባበት ገንዘብ መጠን 2,083,315 እስካሁን የተከፈለ ገንዘብ መጠን 1,383,391.34
ቀሪ ብር 699,923.36 ስሆን ፊዝካል አፈጻጸሙም 75% ፈይናሻል አፈጻጸሙም 64.4% መሆኑና የተቋራጠ
ስለሆና አስፈለጊ ክትትልና ድፍ ብደረግለት፡፡
 በተጨማሪም ወራቤ ከተማ አስተዳደር ውኃ ጽ/ቤት ፡- በዚህ ተቋም በክልል ፣ በዞን እና በከተማ በተውጣጣ በጀት
ከሚሰሩ ፕሮጀክቶች ውስጥ የዋሽ ውሃ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን እነዚህ ፕሮጀክቶች በከታማም ይሁን በዞን በጀት
ይሰሩ ኢንጂ ዋነው ቁም ነገር የከተማውን የንጹሁ መጠጥ ውኃ ሽፋናችንን ከማሳደግም ባለፈ በዚህ ዘርፍ በየግዜው
የሚነሳውን የከተማውን ነዋሪ የንጹ መጠጥ ውኃ የመልካም አስታደደር ችግርን ለመፍታት የሚያስችል ነው በሚል
አሻግሮ በማየት አስተሳሰብ ተቋሙ ፕሮጀክቱን እየተከታተለ የለበትን ሁኔታ እየገመገመ ለቦርድ እና ለከንቲባ
ጉድለቶችን እና ጥንካሬዎችን እየለዩ ባጋጠሙ ጉድለቶች መፍትሄ ኢንዲሰጣቸው ከማድረግ አንፃር ያለበትን ደረጃ
ከዚህ በታች ለማየት እንሞክራለን ፡፡ ከውኃ ሴክተር አንፃር ከዋሽ ፕሮጀክት ጋር በተያዘ ለፕሮጀክቱ ከተያዘለት
345,221,988.16 በጀት አንፃር እንዲሁም እስከ ዛሬ ግንባታቸው መጀመር ከነበረባቸው እና የፕሮጀክቱ አካል ከሆኑ
ግንባታ አንፃር ጋፋት ለይ 2000 ሜትር ኪዩብ ፣ አልባዘር ለይ 500 ሜትር ኪዩብ ፣ ገርማማ ላይ 300 ሜትር ኪዩብ
ሪዘርቨየር ፣ 35 የህዝብ ፋውንቴን ፣ 10 የህዝብ መጸዳጃና ገላ መታጠቢያ ወራቤ ከተማ ውስጥ ፣ 02 ዘመናዊ ሽንት
ቤት ግንባታ ገርማማ ላይ ፣ 04 ቪ አይ ፒ ሽንት ቤት ግንባታ ገርማማ ለይ ፣ የውኃውን ደህንነት ወይም ክሎሪ
መጨመሪያ ክፍል ገርማማ ላይ እና ኤለክትሪካል እና ሌሎች መቆጣጣሪያ ክፍሎች ግንባታ ገርማማ ለይ እስከ ዛሬ
ድረስ ውል ተገብቶባቸው የተጀመሩ የፕሮጀክቱ አካላት እንደሆኑ ተውቆ ተግባሩ በዕውቀት ፣ በፍጥነት እና
በጥንቃቄ ተቋሙ አውቆ በተለየ መንገድ ሊመረው እንደሚገባ መታወቅ ያለበት ሲሆን በተለይ ለግንባታው ውል
ከተገባበት ጊዜ አንፃር ሲታይ ደግሞ ፕሮጀክቱ በ 16 ወር ተጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት ይታወቃል
ነገርግን በተለያዩ ምክንያት ፕሮጀክቱ እየተቋረጠ እንድሁም በሚደረግ እንቅስቃሴ እየተጀመረ የሚሄድበት ሁኔታ
በዘላቂነት የፕሮጀክቱን ጠቀሜታ ከግንዛቤ በማስገባት ትኩርት ሰቶ አሁን በተያዘው ልክ የሚያልቅበትን ሁኔታ
መከተል ቢቻል ፡፡ ምክኒያቱም ከኮንተራክተሩ በቅርበት በመነጋገር ተቋሙ መፍትሄ መምጣት ይኖርበታል
ምክንያቱም በኛ ድጋፍ እና ክትትል እጦት እና መዘንጋት ምክኒያት ልናጣው የሚገባ ልማት መኖር የለበትም ፡፡
 ትምህር ጽ/ቤት ፡- አንሸቤሶ 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይብራሪ ግንባታ በወራቤ ከተማ አስተዳደር በ 2015 ከሚሰሩ

ፕሮጀክቶች አንዱ እንደነበረና ፕሮጀክቱ እስከ ዛሬ ድረስ ላለመጠናቀቁ በጉድለት ከታዩ ጉዳዮች አንፃር ፡-

ግንባታው የዲዛይንና እንዲሁም አንዳንድ የጥራት ችግር ያለበት መሆኑ ፣ ለግንባታው ተገቢው ክትትል እየተደረገ

አለመሆኑ ፣ ግንባታው ከውል ጊዜ አንፀፃር የዘገየ መሆኑና አፈፃፀሙም እጅግ ዘገምተኛ መሆኑ ፣ የኮንትራክተሩ

የአቅም ውስንነት መኖሩ ሲሆን በአጠቃላይ ትምህርት ተቋም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ግንባታው አሁን

ከቆመበት ደረጃ መነሻ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ቀርቦ በመነጋገር ለግንባተው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጠው

በማድረግ የዘርፉን የመልካም አስተዳደር ችግር በፍጥነት መፍታት ያስፈልጋል ፡፡ በሌላ መልኩ የመጀመሪያውን

ተቋራጭ ውል አቋጦ በአድስመልክ የስራ ዝርዝር ተዘጋጅቶ ጨረታ እንዲወጣ መደረጉነ በጥንካሬ ተወስዶ ነገርግን

ከፕሮጀክቱ ቆይታ አንፃር መፍጠን ቢቻል ፡፡ ሌላው የአልከሶ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በፍጥነት ማስጀመር ቢቻል ፡፡
 ሌላው ከማዛጋጃ ቤት ጋር ፡- ከባለፈው አመት በያዝነው ስራ ዘመን የተሸገሩ በከተማ አስተዳደር ደረጃ ማዘጋጃ ቤቱ
በ 02 ቀበሌ ኮብልስቶን መንገድ ንጣፍ ፣ እንዲሁም የከንቲባ ጽቤት እና አዳራሽ ግንባታ በመውሰድ ወደ ተግባር
መግባታቸው ከፕሮጀክቶች ስፋት አንፃር በጥንካሬ ረገድ የሚወሰድ ሲሆን ነገርግን በተመሳሳይ ሁኔታ እንጂ ሊሻሻሉ
ከሚገባቸው ጉዳዮች ስንነሳ ፡- አሁንም የከንቲባ ጽቤት ግንባታ ፍጥነት ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል ፡፡
 ሌላው ከኮንስትራክሽንም ዘርፍ አንፃር ፡- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ
እስካለ ድረስ ግንባታዎችን ለግንባታ ጥራታቸው ብቻ ሳይሆን ለከተሜነት እድገት እና ድይዛይን ጭምር በማሰብ
በተገቢው ጥናትና ወቅቱ የደረሰበትን የግንባታ ቴክኖሎጂ እና ድዛይን ጥራት ላይ መሆናቸውን ቀጣይ በልዩ ትኩረት
እንደ ዘርፉ ተልእኮ አንፃር ወጣ ባለ ሁኔታና ወቅቱን የሚመጥን ድጋፍ በማድረግ ብክነት እና ጥራትን በማስቀረት

ከወዲሁ በአሰራር መአቀፍ ውስጥ ሆኖ መምራት ተቀዳሚ ተግባር ነው ፡፡

እንደ አጠቃላይ በፕሮጀክት በድጋፉ የታዩ ዋና ዋና ችግሮች

 ሌላው በአጠቃላይ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ያሉ ሴክተር መስራቤቶች በዞንና በክልል የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን በኔነት
ስሜት ክትትል አድርጎ አፈፃፀማቸው ከመከታተልና ከመቆጣጠር አንጻር ጉድለት ያለባቸው መሆኑ፣
 ግንባታ እየሰሩ ያሉ አንዳንድ ኮንትራክተሮች ውል የገቡባቸውን ግንባታዎች በወቅታቸውና በጥራት ከመስራት
አንፃር ችግር ሰፋ ያለ ችግር ያለባቸው መሆኑ፣
 ካፒታል ፕሮጀክቶችን በቅንጀት ክትትል እያደረጉ አለመሄድ ችግር ከከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ጀምሮ
ችግር መስተዋሉ በተለይ መረጃ ይዞ ተገቢውን ክትትል ከማድረግ አንፃር ክፍተት ያለ መሆኑ፣
 አሰሪ መ/ቤቱና ክትትል የሚያደርገው አካል ችግር ያለባቸውን ፕሮጀክቶች ተገቢውን ክትትል በማድረግ በወቅቱ
ተከታትሎ ለውሳኔ ሰጪ አካል ከማቅረብ አንፃር ክፍተት ያለ መሆኑ፣
 ካፒታል ፕሮጀክቶች ከውል ጊዜ አንፃር እየዘገዩ በመሆኑ በወቅቱ አልቆ አገልግሎት መስጠት ሲገባው ለመልካም
አስተዳደር ችግር መነሻ እየሆኑ መሆኑ፣
 ግንባታዎችን ክትትል/ሱፐርቫይዝ በማድረግ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትል ከማድረግ አንፃር ጉድለት ያለ
መሆኑ/ ተገቢውን ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎች ባሉበት ሳይት ግንባታው የሚፈጥንበትና ከጥራትም አንፃር
የተሻለ መሆኑን መታዘብ የተቻለበት መሆኑ/፣
የፕሮጀክቶችን ውጤታማነት ለማሻሻል የቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎች
 በከተማ አስተዳደሩ በሶስቱም ቀበሌዎች እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ውጤታማነታቸውን በሚያረጋግጥ አግባብ

መረጃዎችን በማደራጀት ከሚመለከተው አካል በመቀናጀት ተገቢውን ክትትል በማድረግ ሁሉም ፕሮጀክቶች

በዕቅዱ አግባብ መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

 እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በየወቅቱ ተገቢውን ክትትል በማድረግ ግብረ መልስ እየሰጡ በተግባር እያረሙ ቢኬድ

 ፕሮጀክቱን የሚሰሩ አካላት ላይ በተገቢው ጥራትና በውል ጊዜያቸው እየፈፀሙ መሆኑን እየተከታተለ

በማይፈጽሙት ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እየወሰዱ ቢመራ


 ከከተማ አስተዳደሩ ውጪ በዞንና በክልል የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን ችግር በሚገጥም ወቅት ለሚመለከተው አካል

በማሳወቅ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ቢቻል

 ፕሮጀክቶችን የሚያሰራው ሴክተር መ/ቤትና ፕላን ጽ/ቤት እንዲሁም ፋይናንስ ተቋም በመናበብ ፕሮጀክቶችን

በወቅታቸውና በጥራት እንዲሰሩ ማድረግ ቢቻል


 በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች ምንም እንኳን ይታረሙ ተብለው አቅጣጫ ቢቀመጥም አለመታረማቸው
እየቆየ ሲሄድ የሚፈጠረውን ችግር መገመት አያዳግትም ፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ባለብን ከፍጠኛ የመሰረተ ልማት
ፍለጎት ባልተጣጣመ የከተማ ዕድገት እንዲሁም የበጀት ውስንነት ከብዙ ጥረት ቦኋላ በተገኛ የአለም ባንክ ድጋፍ
ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች የሚስተዋሉብንን የልምድ እጥረቶችን ባረምንበት ወቅት በመሰረተ ልማቶች እያጋጠሙን
ያሉ ብክነቶችን እና የጥራት ችግሮችን ሪፎርሙ በፈጠረው መነሳሳት ውስጥ ሆነን ስናያቸው እጅጉኑ የኛን ተግባር
የሚመጥኑ እንዳልሆኑ በመረዳት የተቀመጠላቸውን የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ጭምር እያስታወሱ በተለየ ሁኔታ
አሁንም ፕሮጀክቶችን መምራት አማራጭ የለውም ፡፡
 በተጨማሪም 2016 ዓ/ም የተቀዱ ካፕታል ፕሮጀክት በተመለከተ፡-
 የአልከሶ 2 ኛ ደረጀ ት/ቤት 02 ቱም ብሎክ ጨረታው ተከፍቶ ለአጽደቂ ደርሷል፡፡
 የጤና ጣባያ ካርድ ክፍል ግንባታ ጨረታው ተከፍቷል፡፡
 የፖሊስ ግንባታ በተመሣሰይ ጨረታው ተከፍቷል፡፡
 የግብርና እንሳሰት ክልንክ ግንባታ ሰነዱ ተገምግሞ ለግዥ ክፍል ደርሷል፡፡
 የመንገድ ደር መብረት ሰነዱ ተገምግሞ ለግዥ ክፍል ደርሷል፡፡
 የ 02 ቀበሌ ጤና ጣብያ ግንባታ ቦታ አልተወሰነም በምል ሰነዱን አለመጠም ተቋሙ፡፡
 ለገቢ አሰባሰብ ባለሙያ የመስክ ቢሮ ግንባታ ከጽ/ቤቱ ሰነዱም አልመጠም፡፡
 ለህብረት ስራ መጋዘን ግንባታ አልባዘር ላይ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
 የኢንተርፒራይዝ የክለስተር ማእከል ግንባታ በመጠነቀቅላይ ይገኛል፡፡
 የኢንተርፒራይዝ የ 01 ቀበሌ ቢሮ ኢድሳት ተጠነቋል፡፡
 የኢንተርፒራይዝ የዶሮ ቤት መስሪያ ተቋሙ ሰነድ አለመጠም፡፡

በ 2016 ዓ/ም የተቀዱ በካፕታል ፕሮጀክትየተቀዱ ግዥዎችን በተመለከተ፡-

 02 አፓች ሞተር አሸነፊ ተሸነፊ በመለያት እንድያቀርብ ተእዘዝ ተሰቷል፡፡


 05 100 ሲሲ ሞተር ለምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ 01፣ለፕላን ጽ/ቤት 01፣ለገቢዎች 02 እና ለኢንተርፒራዝ
01 ሞተር አሸነፊ ተሸነፊ በመለያት እንድያቀርብ ተእዘዝ ተሰቷል፡፡
 የከንቲባ መኪናና ማሽን ግዥ ከክልልፍቃድ በመምጣት ለዞን ደብደቤ መጸፍ ተችሏል፡፡
 የፋርንቻርና ኮምፒታር ግዥ ኦርደር ጠብቆ ይወጠል፡፡
 የጤና ጣቢያ መድሃኒት ግዥ ለ 02 ጤና ጣብያዎች ተላልፏል፡፡

ቁጥር ወከ/አስ/ፕላን 830/2016 ዓ.ም

ቀን 19/04/2016 ዓ.ም

ለስልጤ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ

ወራቤ

ጉዳዩ ፡- የካፒታል ፕሮጀከት 2 ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ያለበት ደረጃ ፣የድጋፍ ግ/መልስ ፣ ምረቃ እና የቀጣይ
አቅጣጫ የሚያሳይ ሪፖርት ስለመላክ ፡-
ከላይ ለመግልጽ እንደተሞከርው በተቋማችን እስከዚህ 2 ኛ ሩብ ዓመት ድረስ የተሰሩ ፣በድጋፍ እና ክትትል
የታዩ ፣ የተመረቁ እንዲሁም ለቀጣይ የታሰቡ የካፒታል ፕሮጀክት ያሉበት ደረጃ የሚያሳይ ተግባራት በዝርዝር
በማጠቃለል ከዚህ ሸኚ ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርገን ሪፖርት መላካችን በአክብሮት እንገልፃለን ፡፡

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

 ለፕላን ጽ/ቤት
 ለልማት ዕቅድ
ወራቤ
0

You might also like