You are on page 1of 4

የክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግብረ መልስ ቁጥር ሁለት

1. መግቢያ

በበጀት አመቱ ከተሞች በፕላን የሚመሩ፣ ጽዱና ለኑሮ የተመቹ እንዲሁም የኢኮኖሚ ማሳለጫ ማእከል እንዲሆኑ
የሚያስችሉ ግቦች ተነድፈዋል፡፡ ከዚህ አኳያ በ 2015 በጀት አመት የታቀዱ ግቦቻችን ላይ በየደረጃዉ ያለ አመራር፣
ሙያተኛና ህዝብ ግንጽነት ይዞባቸዉ ወደ ስራ መግባት ወሳኝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ባለፈዉ ሳምንት በአብዛኛዉ ዞኖችና ከተሞች
የዝግጅት ስራ ላይ አተኩረዉ እየሰሩ እንደሆነ ዉስን ዞኖችና ከተሞች ደግሞ የእቅድ ኦሬንቴሽን መስጠት እንደጀመሩና
በሂደቱ የተስተዋሉ ዝንባሌዎች፣ ተሞክሮወችና የቀጣይ ትኩረት ጉዳዮች ላይ አተኩረን ግብረ መልስ መላካችን
ይታወቃል፡፡

የሁለተኛዉ ግብረ መልስም ካለፈዉ ሳምንት የቀጠለና በመድረኮች የተነሱ ሀሳቦችን፣ መስተካከል ያለባቸዉን
ጉድለቶች፣ ትምህርት የሚወሰድባቸዉን ተሞክሮች እንዲሁም የቀጣይ ትኩረት ጉዳዮችን ባመላከተ ሁኔታ
ተዘጋጅቶ ተልኳል፡፡ በመሆኑም በዚህ ግብረ መልስ ላይ የዞን እና የሪጅዎ ከተሞች ከተማና መሰረተ ልማት
መመሪያ የማኔጅመት አባላት በጋራ ተወያተዉበትና ዳብሮ ወደ ወረዳዎችና ከተሞች በማዉረድ በሂደቱ
የመዋቅራችን አቅም የሚጠናከርበትን እድል መስፋት ይገባል፡፡

2. የእቅድ ኦሬንቴሽን ማካሄድ

በዚህ ሳምንት በርከት ያሉ ከተሞችና ዞኖች የእቅድ ኦሬንቴሽን መድረኮቻዉን በበቂ ዝግጅት ማካሄድ ችለዋል፡፡
በመድረኩ ከዞን አስተዳዳሪዎችና የድርጅት አመራሮች ጀምሮ እስከ ታዳጊ ከተሞች የስራ ሀላፊዎች ተገኝነተዉ
በእቅዶቻችን ላይ መግባባትና መነሳሳት ለመፍጠር እድል የሰጠ ሲሆን በመድረኮች የተሳተፈ ጠሰዉ ሀይል ሰሜን ሸዋ
(271)፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን (360)፣ ደቡብ ጎንደር ዞን (320)፣ ማእከላዊ ጎንደር ዞን (250) እንዲሁም ደብረ ማርቆስ
ከተማ (137) ከተማ በድምሩ 1338 አመራር እንደሆነ የዞኖች ሪፖርት ያመላክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደሴ ከተማ
ቀድመዉ ካካሄዱት መድረክ በተጨማሪ ከባለድርሻ አካላት፣ ከልማት ኮሚቴዎች፣ ከክፍለ ከተማ ቡድን
መሪዎች.ከመመሪያ ሰራተኞች ጋር በድምሩ 585 የሰዉ ሀይል በማሳተፍ መድረኮችን አካሂደዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የከተማ
ልማት ስራን ሁሉም አመራር አዉቆ እንዲመራ የተደረገዉ ጥረት የሚበረታታ ሲሆን በቀጣይ ማሳተፍ ካለብን የሰዉ
አኳያ እየተነጻጸር ማቅረብ የበለጠ ትምህርት ይወሰድበታል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የሚታየዉ በመድኩ ሀሳቦች እየተነሱና ዉይይት እየተደረገባቸዉ መግባባት በመፍጠር ወደ ስራ ማስገባት
ነዉ፡፡ ከዚህ አኳያ በመድረኩ ጠቃሚ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዉ ዉይይት ተደርጓል፡፡

 የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሰፊ መሆናቸዉንና ይልቁንም እኛ ባለመስራታችን ችግሮች እየተባባሱ የመጡ እንደሆነ በስፋ
የተነሳ ሲሆን በቀጣይ በየደረጃዉ ያለ አካል በትኩረት መስራት እንደሚገባ መነሻ መግባባት ተፈጥሯል፡፡
 ህገ ወጥነትን ከመታገ፤ አኳያ ባንድ በኩል በተቋሙ አመራርና ሙያተኛ ትኩረት ሰጥቶ ችግር ፈች ርምጃ አለመዉሰድ
እንደተጠበቀ ሆኖ በሌላ በኩል ህገወጥነትን ለመታገድ ሌሎች የሚመለከታዉ አካላት ትኩረት ሰጥተዉ እያገዙን አይደለም
እንዲያዉም በተደጋጋሚ እየተከሰስን መዋያችን ፍርድ ቤት ሆኗል፣ ማከጃ በመጻፍ ስራዉን እንዳናሳልጥ እቅፋት እየሆነ ነዉ፣
በዚህ ሂደትም በቀጣይ ስራዉን ዉጤታማ ለማድረግ ችግር ይገጥመናል የሚል ዉይይት ተደርጓል፡፡ አንዳንድ አካባቢ በዚሁ
ምክንያት ለምን ጠበቃ አይመደብልንም በሚል ሃሳቦቻቸዉን አንስተዋል፡፡ ህገወጥነት የሁሉም አካል ርብርብ የሚያስፈልገዉ
መሆኑን ተገንዝበን ከወዲሁ እዚህ ላይ መስራ ይገባል፡፡
 ከህዝብ ተሳታፎ አኳያ በሁሉም አካባቢ ትኩረት ተሰጥቶት ዉይይት ተደርጎበታል፡፡ ባንድ በኩል የህዝብ ተሳትፎዉን በማጠናከር
የከተሞችን የመሰረተ ልማት እቅዶቻችን እናሳካለን በሚል መግባባት የተፈጠረ ሲሆን በሌላ በኩል አንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ
ህዝቡ በተለያየ መንገድ መዋጮ ስላለበት በዚህ ልክ ተሳትፎ ላያደርግ ይችላል፣ እቅዱም የተጋነነ ነዉ በሚል ተነስቶ ዉይይት
ተደርጎበት በአጠቃላይ ባለን ሀብት ልክ ከህብረተሰቡ ጋር በተገቢዉ ተወያይተንና ተማምነን ወደ ስራ ከገባን ማሳካት እንችላለን
የሚል መነሻ መግባባት ተፈጥሯል፡፡ ከዚህ ተግባር አኳያ የተፈጠረዉን መነሻ መግባባት እንደ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እስከ ህዝቡ
የምናደርገዉን መድረክ በአግባቡ መምራትና ወደ ተሟላ ስራ መግባት እንደሚገባ መገንዘብ ይገባል፡፡ በዚህ አመት ለሁሉም
የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባሮቻችንን እንደ ዋና መግቢያ መሳሪያ የምንጠቀምበት ህዝቡ ጋር በተገቢዉ መግባባትና
ይህንኑ አቅም አድርጎ መጠቀም ወሳኝ መሆኑን በሁሉም አመራርና ሙያተኛ ግልጽነት ሊያዝበት ይገባል፡፡ ህገ ወጥነትን
በመታገል፣ የህዝብ ርካታን በማሳደግ እና በመሰረተ ልማት ስራዎቻችን በጥራትና በወቅቱ ለመፈጸም የህዝብ ባለቤትነትና
ተሳትፎ ቁልፍ ጉዳይ አድረገን እንሰራለን፡፡
 ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ አኳያ ባንድ በኩል የመንግስት ግንባታዎችን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ሴክተር መስሪያ ቤቶች
መመሪያዉን አያዉቁትም በሚል የተነሳ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አዊ ዞን ችግሩን ቀድሞ ተገንዝቦ የሚመለከታቸዉን አካላትን
በመመሪያዉ ዙሪያ መደረክ ፈጥሮ በማወያየት ግንዛቤ ፈጥረዉ ወደ ስራ ለመግባት የጀመሩት እንቅስቃሴ ሌሎችም ትምህርት
ልትወስዱበት ይገባል፡፡
 ከአደረጃጀት አኳያ አንዳንድ የወረዱ መደቦች ከተቋሙ ተግባርና ሃላፊነት ጋር የሚጣጣም አይደለም ይህ ደግሞ የባለሙያዉን
የስራ ስሜት የሚጎዳ ስለሆን ማስተካከያ ቢደረግ በሚል ተነስቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የወረዳ ከከማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤቶች
ተግባርና ሃላፊነት በዉል ስላልተገለጸ ሪፖርት ከመቀበል የዘለለ ዉጤታማ ስራ እየተሰራ አለመሆኑ ቀርቧል፡፡ ከዚህ ተግባር አኳያ

በእቅድ ኦሬንቴሽን እንደተግባባነዉ የወረዳ ጸ/ቤት ሃላፊዎች ከከተማና መሰረተ ልማት መምሪያዉ የወረደዉን የከተማ ልማት
እቅድ ወደ መሪ፣ ንኡስ ማዘጋጃ ቤቶችና ታዳጊ ከተሞች ሸንሽኖ በማዉረድ፣ እንዲሁም ቀጣይነት ባለዉ መልኩ ግንዛቤ
በመፍጠርና የህዝብ ተሳትፎዉ እንዲያድግ በትኩረት በመስራት የታቀዱ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን ዉጤታማት
በማሳደግ ከተሞች ለኑሮ ምቹ ማድረግና እንደየ ሀብት ይዞታቸዉ የኢኮኖሚ ማሳለጫ ማእከልነታቸዉ እንዲያድግ ማድረግ ላይ
ማተኮር ይገባል፡፡

በሌላ በኩል እስካሁን የዞንና የሪጅዎ ከተማ የአመራር መድረኮቻችሁን ያላካሄዳችሁ በፍጥነት እንድታካሂዱና ቀድመዉ
ካካሄዱ ዞኖችና ከተሞች ትምህርት መዉሰድ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ደብረታቦርና ወልደያ ከተሞች የሪጅዎ ከተማ
አደረጃጀታቸዉን በአዲስ እያደራጁና የሰዉ ሀይል ስምሪትም ለማድረግ ከሲቭል ሰርቪስ ጋር እየሰሩ መሆናቸዉን
አንስተዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ተግባሮች በጥራት መፈጸም አንድ ጉዳይ ሆኖ የእቅድ ኦሬንቴሽን ለመስጠት የሚያስችል
ግምገማዎችንና የቀጣይ የእቅድ ጭብጦችን ከተሞችን የሚመጥንና ለቀጣይ መሰረት የሚጥል አድርጎ ከወዲሁ
ዝግታችሁን ማጠናቀቅና በቀጣይ ወደ ኦሬንቴሽን መድረክ መግባት ተገቢ ነዉ፡፡ በዚህ ወቅት አመራሩና ሙያተኛዉ
ተዘናግቶ እንዳይቀመጥ በዋና ዋና ተግባራት ላይ ተመስርቶ ወደ ስራ የሚያስገባ ግልጽ የስራ ስምሪት፣ ክትትልና ድጋፍ
ማጠናከር ይገባል፡፡ ከአደረጃጀት አኳያም የሚሰሩ ስራዎችን ከክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ አመራር ጋር በቅርበት
በመስራት ዉጤታማ ስራ ማከናወን ይጠይቃል፡፡ በክልል ደረጃ የሚፈቱ ችግሮችን በሪፖርታችሁ ማመላከትና በትስስር
መፍታት ይገባል፡፡

3. ተሞክሮ የሚወሰድባቸዉ ጉዳዮች

 የዞን መድረኮቻቸዉን ያካሄዱ ዞኖች በሰነዶች ዝግጅትና ተሞክሮዎችን ቀምረዉ ለመድረኩ በማቅረብ በቂ ዝግጅት
በማድረግ፣ ከታዳጊ ከተሞች ጀምሮ እስዞን አመራሮች እንዲገኙ በማድረግ፣ አጋር አካላት በማካተት እና የዞን ኮር
አመራሮች በመድረኩ ተገኝተዉ የስራ አቅጣጫዎችን እንዲሰጡ በማድረግ ያደገ የስራ መነሳሳት ለመፍጠር የተደረገዉ
ጥረት መልካም ጅምር ሆኖ ታይቷል፡፡ በመሆኑም ይህን መነሳሳት ተከትሎ ወደ ስራ ማስገባት በትኩረት መሰራት ያለበት
መሆኑን ትምህርት መዉሰድ ይገባል፡፡
 ሰሜን ሸዋ እና አዊ ዞኖች ከዞን መድረክ በተጨማሪ ወደ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮችና ህዝቡ እንዲሁም ደሴ ከተማ
ወደ ክፍለ ከተሞች፣ ቀበሌዎችና የልማት ቡድን መሪዎች የደረሰ ዉይይት ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የእቅድ
ኦሬንቴሽኑን ወደ ከተሞች፣ ክፍለ ከተሞች፣ መሪና ንኡስ ማዘጋጃ ቤቶች እንዲሁም ታዳጊ ከተሞችና ህዝቡ ማዉረድና
በአመቱ ስራዎቻችን ላይ መተማመን መፍጠር አጠናክሮ መስራት የዝግጅት ስራዎችን በወቅቱና በጥራት አጠናቆ ወደ
ተግባር ምእራፍ ለመግባት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነዉ፡፡
 አዊ ዞን በዚህ ሳምንት ከአማካሪዎች፣ ተቋራጮችና ህንፃ ሹሞች ጋር በአሰራሮችና በተግባራት አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት
ማካሄድ ተችሏል። በመድረኩ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዕደገት ዙሪያ ያሉ መልካም አጋጣሚዎች፣ ተግዳሮቶችና

መፍትሄዎቻቸው በሚል ሰነድ እና ተሻሽሎ በወጣው የአማካሪና ተቋራጮች መመሪያ ቁጥር 648/2013 ዙሪያ መልካም
ውይይት ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ አዊ ዞን አጋር አካላት ጋር ማለትም ከሁሉም ፍትህ አካላት አመራሮች ዞን እስከ

ወረዳ እና የአቃቢ ህግ ዳኞች እንዲሁም የሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች አመራሮች እስከ ታዳጊ ወንድ 81 ሴት 4 ድምር
85 በተገኙበት በመሬትና በተለያዩየ ጉዳዮች ዙሪያ በቀጣይ ተቀራርቦ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

4. የቀጣይ ትኩረት ጉዳዮች

የተጀማመሩ ተግባራት ጥራት ያላቸዉና ለቀጣይ ስራ መሰረት የሚጥሉ ማድረግ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ
መሆኑን የተገነዘበ የአመራር ሚናን መወጣት ይገባል፡፡ አመራር የአመቱ ዋና ዋና ግቦች ላይ በራሱ ግልጽ
መሆን፣ ተግቡ ስኬት ሌሎችን በተሟላ መንገድ ማስገንዘብ፣ ማነሳሳትና ማስተባር፤ ጠንካራ ድጋፍ
በመስጠት ግቦችን ዉጤታማ ማድረግ በሂደቱም አመራር መገንባት ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡
በመሆኑም የዞንና የከተማ አመራሩ ቀዳሚዉ ጉዳይ በዙሪያዉ የአመራ አቅም እየገነቡ ስምሪቱን
እያጠናከሩ መሄድ ይገባል፡፡
 ከዚህ አኳያ በዓመቱ የተያዙ የከተማ ልማት ግቦቻችን ቆጥሮ ማስጨበጥ ላይ መተኮር አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ በክልሉ
እቅድ በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት እስከ ህዝቡ የሚደርሱ መድረኮችን በብቁ ዝግጅት መምራትና ግንዛቤ መፍጠር
በሁሉም ዞኖችና ከተሞች በጥራ መፈጸም እንዲሁም በሂደቱ የሚስተዋሉ ዝንባሌዎችን በመለየት በዝግጅት ምእራፍ
የሚደረገዉን ርብርብ እነዚህን ችግሮች እየፈታን መሄድ፣ ሌሎች እንደወቅቱ ሁኔታ የሚያጋጥሙ አዳዲስ
ማነቆዎችን ወቅታዊ መፍትሄ እየሰጡ ለዉጤት የሚያበቃ ያገናዘበ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ይገባል፡፡
 እንደ ክልል ማስተካከል ያለብን ድጋፍ የምንሰጥ አመራሮችና የእቅድና ክትትል ዳይሬክቶሬት አበላት
በየምድባችን ሁሉንም ዞኖችና ከተሞች ያሉበትን ሁኔታ በዝርዝር እየተከታተልን አፈጻጸሙን እንዲሻሻል
መፍትሄ መስጠት እንዲሁም የተብራራና የተጠቃለለ ሪፖርት ማቅረብ ይገባል፡፡
 ከዞኖችና ሪጅዎ ከተሞች አኳያ እስከ ህዝቡ የሚደርስ ግንዛቤ መፍጠር ላይ በቂ ትኩረት ማድረግ የሚገባ
ሲሆን በሂደቱ የታችኛዉ መዋቅር ያለበትን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተሉ የተሸለ መነሳሳት እድፈጠር
ማድረግ ይገባል፡፡ የተብራራና ገላጭ ሪፖርት ለክልል በመድረስ ረገድ ያሚስተዋሉ ክፍተቶችን መሙላት
ይገባል፡፡ ከጥቂት ዞኖች በስተቀር ወቅታዊና ገላጭ ሪፖርት አልተላከም፡፡ በመሆኑም ወቅቱ የጠበቀ፣

የተገመገመ ሪፖርት የዞንና የሪጅዎ ከተማ መምሪያ ሃላፊዎች በየሳምንቱ አርብ አርብ እስከ ቀኑ 6፡30
ድረስ በተዘጋጀዉ አዲስ የቴሌግራም አድረሻ መላክ ይገባል፡፡
 የእቅድ ኦሬንቴሽን መድረኮች ጎን ለጎን የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባሮቻችን በትኩረት መደገፍ፣
መከታልና ችግሮች እየፈቱ አፈጻጸማቸዉ እንዲሻሻል ማድረግ ይገባል፡፡ የሪፖርቱ ይዘትም በእቅድ የተመላከቱ ግቦች
ላይ ማተኮር አለበት፡፡ የምንመራበት እቅድ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
 ከፕሮጀክቶቻችን አኳያ (UIIDP እና ከተማ ሴፍቲኔት) በዚህ ወቅት የሚከናወኑ ተግባራትን ለይተን አንዲፈጸሙ
ድጋፍ ማድረግ ለፈጻሚ አካላት በቂ ግንዛቤ መፍጠር አፈጻጸሙንም ሪፖርት ማድረግ ይገባል፡፡ በተለይም በእቅድ
የተያዙ ፕሮጀክቶች ዲዛይን ጨርሰዉ ዉል አጸድቀዉና የጨረታ ስራዉን አጠናቀዉ እንዲሁም ለተቋራጮችና
ኢንተርፕራይዞች በፕሮጀክት አመራር ዲስፕሊን ላይ ግንዛቤ ፈጥሮ ማሰማራትና አፈጻጸሙን መከታተል ከወዲሁ
ታስቦ የሚሰራ ተግባር ይሆናል፡፡ ከከተማ ሴፍቲኔት አኳም የሰዉ ሀይል ልየታ ስራዉ የከተማ ግብርናና ግሪነሪ ስራዎች
ላይ ተሳታፊዎችን አሰልጥኖ ጥራት ያለዉ ስራ እንዲሰራ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቅ ይገባል፡፡ የክልል የፕሮግራም
አስተባባሪዎችም በተያዘዉ እቅድ መሰረት እነዚህ ተግባሮች መፈጸማቸዉን የተለመደዉን ድጋፍና ክትትል
በማጠናከር ጥራት ያለዉ ሪፖርት ለዘርፍ ማቅረብ ይገባል፡፡ በየዘርፉም በቂ ክትትል ይደረጋል፡፡

በመሆኑም የአመራ ስምሪችን በዋናነት በእቅድ የተመላከቱ ግቦቻችን መሰረት በማድረግ አመራር መስጠት ላይ
እናተኩር፡፡

የአመራር ብቃታችን በማሳደግ ከተሞችን የብልጽግና ማእከል እናደርጋለን!!

መስከረም 28/2015

You might also like