You are on page 1of 3

የክረምት ስራዎች ቼክ ሊስት

ሰኔ 30/2015 ዓ.ም

መግቢያ

ከሀገራዊ ለውጡ ማግስት የአማራ ክልል ኢኮኖሚ በመሰረታዊነት ከነበሩበት ስብራቶች በተገቢው
ለመጠገንና የህዝባችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ልማቶችን በማከናወን በኩል የ 10 አመትን ስትራቴጅክ
ዕቅድ አቅደን ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ይሁን እንጅ በዕቅዱ መፈፀሚያ የመጀመሪያ አመታት ያጋጠመው
የኮቪድ-19 አለማቀፍ ወረርሽኝ እንዲሁም ሀገራዊ የእርስ በርስ ጦርነት ከለውጡ በፊትና በኋላም
ከተፈጠሩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ጋር ተዳምረው ሁኔታውን ፈታኝ አድርጓል፡፡ የክልላችንን የኢኮኖሚ
መዋቅራዊ ሽግግር ከማረጋገጥና ዘላቂ የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማምጣት አንፃር ከግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ
ባልተናነሰ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ላይ ርብርብ ማድረግ አስገዳጅ ስለነበር የክልሉ መንግስት ከላይ

0
በጠቀስናቸው ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥም ሆኖ ባለፉት አመታት በክልሉ ኢንቨስትመንት እዲስፋፋና
የኢንዱስትሪ ልማት እንዲፋጠን ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ቢሮም የ 2015 በጀት ዓመት እቅድን የ 10 ዓመቱን የልማትና መ/አስተዳደር
እቅድ እንደመነሻ፣ የፌደራል ተቋማትን ዕቅድ እንደመነሻ፣ በክልሉ ያሉ አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎች
ትንታኔ እንደመነሻ በማድረግ ዓመታዊ እቅድን በማዘጋጀት ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም
በየደረጃው ላለው የቢሮ ፈፃሚና አስፈፃሚ የዕቅድ ኦረንቴሽን በመስጠት፤ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሞ
ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ በዚህም በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ታይቷል።ስለሆነም መልካም ጅምሮችን
አጠናክረን ለመቀጠልና ጉለታችንን አርመን በ 2016 የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከወዲሁ በቂ ቅድመ
ዝግጅት ማድረግና በክረምቱ ትኩረት ሰጥተን መስራት ያለብንን የትኩረት መስኮች በሚከተለው መልኩ
ቀርበዋል::

@ከ 2015 በጀት ዓመት ማጠቃለያና የ 2016 በጀት አመት ዝግጅት አኳያ

 የ 2015 በጀት አመት እቅድ አፈፃጸም ሁሉንም ፈጻሚ ባሳተፈና ለቀጣይ ትምህርት በሚወሰድበት መልኩ
በሁሉም የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤቶች፣ መምሪያችና በቢሮ ደረጃ እስከ ሀምሌ 30/2015 ዓ.ም
መገምገም ይኖርበታል፡፡
 የተቋምና የስራ ክፍል አፈጻጸምን መሰረት በማድረግ የ BSC ውጤት ለፈጻሚዎች መሙላት፣
ውጤት አሰጣጡ ስራንና ስነ ምግባርን መሰረት ያደረገና ሁሉንም ፈጻሚ በይሉኝታ በአንድ ቋት
ከማስቀመጥ የወጣ መሆኑን መረጋገጥ
 የ 2016 በጀት አመት የተቋም ዕቅድ የበላይ አካል መነሻና የአካባቢን ፖቴንሽያል መሰረት በማድረግ
በጥራት ማቀድና ሁሉም ፈፃሚ በእቅዱ ላይ በቂ ተሳትፎ እንዲኖራቸውና የአቅዱ ባለቤት
ማድረግ
 ከተቋሙ ግብ ተኮር እቅድ በመነሳት ለፈጻሚዎች የሚለካና የተቋሙን ግቦች ማሳካት የሚስችል
የግል እቅድ ውል መስጠትና የአጋርና ባለድርሻ አካላት አቅድ አዘጋጅቶ በእቅዱ ላይ መግባባት
 የ 2015 ዓ.ም ተግባራት ከመምሪያዎች ጋር በተወሰደው የውል ስምምነት መሰረት አፈጻጸምን
መሰረት ያደረገ ተግባራትን መለካት እና ሁሉንም ጽ/ቤቶች በመምሪያ ደረጃ በደረጃ ማሰቀመጥ
እንዲሁም የሁሉንም መምሪያዎች ደረጃ በክልል ደረጃ መለየት፤ እንደ አፈጻጸም ደረጃቸው
ለመምሪያዎች በክልል፤ ለወረዳ ጽ/ቤቶች በመምሪያ ደረጃ ማበረታቻ እና እውቅና መስጠት፤

@ከዝግጅት ተግባራት በትይዩ የሚከናወኑ ተግባራት


 የሀገር ውሥጥና የውጭ ባለሀብቶች ወደ ክልሉ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የየአካባቢውን
የኢንቨስትመንት ፖቴንሽያል መሰረት አድርጎ ማሰተዋወቅና የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያወጡ
ማድረግ፣ የአገልግሎት አሰጣጣችን ከተገልጋይ እይታ አኳያ ገምግሞ መስተካከል

1
 ቀልጣፋና አስተማማኝ የመረጃ ስርአት መዘርጋት፤ ሁሉንም የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች
የተሟላ ፕሮፋይል በየዘርፉና ባሉበት የአፈጻጸም ደረጃ በማደራጀት ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት
እንዲሁም ወደፊት የሚሻሻሉ መረጃዎች ሲመጡ የሚደራጁበት ሲስተም ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ
ጋር የተጀመረውን የመረጃ ቋት የማልማት ስራን ማጠናቀቅ
 አዲስ በወጣው የኢንዱስትሪዎች ማቋቋሚያ ደንብ መሰረት በክልሉ ያሉትን 3624
ኢንዱስትሪዎች ደረጃ በአዲስ መልክ ማደራጀት(ማስተካከል)
 የአምራች ኢንዱስትሪዎችም ሆነ ሌሎች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በተጨባጭ መረጃ ላይ ሆኖ
ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንዲቻል በሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች ያሉባቸውን ችግሮች መለየት /
የብድር፣የመሰረተ ልማት፣የውጭ ምንዛሬ፣ የግብአት፣ የገበያ ትስስር ወዘተ…/ እንዴትና መቼ ፣
በማን ሊፈቱ እንደሚችሉ በእቅድ ማመላከት
 የአምራች ኢንዱስትሪዎችም ሆነ ሌሎች ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ምርታማነት የሚሻሻልበት
እና የሚያድግበት ሁኔታን መከተል፤ያሉባቸውን ማነቆዎች ተከታትሎ መፍታት፡፡
 ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በኢንዱስትሪ መንደርና ከኢንዱስትሪ መንደር ውጭ እንዲሁም
ለሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች የለማ መሬት እንዲቀርብ መሬት አቅራቢ ተቋማት ማለትም
መሬት ቢሮ እና ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮዎች ጋር በቅንጅት ማቀድ(መስራት)
 አምራች ኢንዱስትሪዎችና ሌሎች የግብርና ኢንቨስትመንቶች ምርታቸውን ወደ ውጭ እንዲልኩ
መደገፍ፣ የኢክስፖርት የጠራ መረጃ መያዝ እንዲሁም በሁሉም ከተሞች አምራቾች
ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት የኢግዚቢሽንና ባዛር በእቅድ ተይዞ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት
ስራዎችን መስራት
 በክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ወደ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተላኩ
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የአፈጻጸም ደረጀ መገምገምና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ
 አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ያሉባቸውን የፋይናንስ ችግር
በዘላቂነት ለመፍታት በክልላችን ካሉ ሁሉም የፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ጋር በክልል ፤በዞን እና
በከተማ አስተዳደር ደረጃ የጋራ የምክክር መድረክ ማካሄድ
 ክልላችን ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ በሚዲያ እና በሌሎች
የማስተዋወቂያ መንገዶች የሚከናውነው የፕሮሞሽን ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ በክልሉ ገብተው
በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከተሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች ጋር በክልል ደረጃ ውይይት
ማድረግ እሰከ ሀምሌ 30/2015
 ቀደም ሲል ስምምነት ላይ በተደረሰው መሰረት በሁሉም ዞኖችና ከተሞች ወደ ምርትና
አገልግሎት በአዲስ መልክ የሚገቡ የኢንዱስትሪ እና ሌሎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ለቀጣይ
ስራችን በሚያነሳሳ መልኩ እስከ ሐምሌ ከሀምሌ 5_20/2015 ማስመረቅ እና ንቅናቄ መፍጠር
 ″ነገን ዛሬ እንትከል″ በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የ 2015 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር
በአንድ በተመረጠ የኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ ከተቋማችን ሰራተኞች እና ከሌሎች የባለድርሻ
አካላት ጋር በክልል ደረጃ የችግኝ ተከላ ስራን ማከናወን፤ በተመሳሳይ በየደረጃው ባለው
መምሪያዎቻችን ያሉ ሰራተኞችም በተመሳሳይ ደረጃ በተቋማቸው ስም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ
ግብር እንዲያከናውኑ ይደረጋል፡፡

You might also like