You are on page 1of 12

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ወረዳ 10

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10

ስር የሚገኙ ዕድሮች

ጋር የተደረገ የቅንጅታዊ አሰራር የትስስር ስምምነት ሰነድ


ማውጫ

መግቢያ................................................................................................................................................1
ዓላማ...................................................................................................................................................1
ዝርዝር ዓለማዎች.............................................................................................................................................1
የቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነት....................................................................................................................1
የቅንጅታዊ አሰራር ትስስር አሰራር ሁኔታ እና መርህ.........................................................................................2
የውጪ ትስስር (External interface)..........................................................................................................2
የቅንጅታዊ አሰራር ክትትል እና ድጋፍ ስራዎች................................................................................................3
የትስስሩ ወሰን........................................................................................................................................3
ከትስስር የሚጠበቅ ውጤት........................................................................................................................3
የወረዳዉ ሲ/ም/ነ/አ/ ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራት........................................................................................................3
የትስስር ሰነድ ስለማሻሻል..........................................................................................................................3
ልዩነቶች ስለሚፈቱበት ሁኔታ......................................................................................................................3
የትስስሩ የቆይታ ጊዜ................................................................................................................................4
በቅንጅታዊ አሰራር ሂደት ለሚገጥሙ ችግሮች የተቀመጡ የመፍትሄ ሀሳቦች.............................................................4
የክትትትል፣ ድጋፍ እና ግምገማ ስርዓት.........................................................................................................4
በውል ሰጪ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እና በውል ተቀባይ በስሩ የሚገኙ የሲቪል
ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት መካከል የሚጠበቁ ሚናዎች እና ውጤቶች........................................................5
የድርጊት መርሐ-ግብር...............................................................................................................................7
የሁለቱ ባለድርሻ አካላት የስምምነት ፊርማ........................................................................................................8
መግቢያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የሚታዩትን የመልካም
አስተዳደር ችግሮች ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም ለውጥ የበለጠ
ውጤታማ ለማድረግ የሚመለከታቸው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኙ ዕድሮች ጋር ትስስር
ፈጥረው በተቀናጀ ሁኔታ የድርሻቸውን በመወጣት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በጋራ ሲፈቱ ይሆናል፡፡

ለውጥ እና ችግሮች የሚፈተቱት ደግሞ በአንድ አካል ጥረት ብቻ አለመሆኑን በመገንዘብ ጽ/ቤቶች እና የስራ
ከፍሎች የውስጥ እና የውጪ ትስስር በመፍጠር የጋራ በሚያደርጋቸው ግቦች እና ተግባራት ላይ የጋራ መግባባት
በመፍጠር የድርጊት መርሐ-ግብር በማዘጋጀት በጋራ በመስራት እና በመገምገም የታቀዱ ተግባራትን በቅንጅት
ውጤታማ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በመሆኑም የጽ/ቤቶች እና የስራ ከፍሎች ቅንጅታዊ አሰራር የበጀት ዓመቱን
እቅድ ውጤታማ ለማድረግ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ስር የሚገኙ ዕድሮች ጋር ይህ የትስስር
ስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

ዓላማ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት
ለመወጣት በወረዳዉ ስር ባሉ ዕድሮች መካከል የሥራ ትስስር እና ቅንጅት በመፍጠር የጽ/ቤቱን ውጤታማነት
ከፍ ማድረግ ነው፡፡

ዝርዝር ዓለማዎች
 ከወቅታዊ ሞት ምዝገባ ጋር ከ ዕድሮች ጋር በትስስር መስራት መቻል
 በጽቤቶች ውስጥ በተናጠል ማከናወን የማይችሏቸውን ሰትራቴጂክ ግቦች እና ተግባራትን በመለየት የጋራ
መግባባት በመፍጠር የዕቅድ አካል በማድረግ በጋራ በቅንጅት በመስራት ማስቻል
 በጽቤቶች ውስጥ የቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጠናከር እና ያላቸውን የማስፈጸም አቅም በማሳደግ
የራሳቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት

የቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊነት


በቅንጅታዊ አሰራር የረጅም እና የአጭር ጊዜ እቅዱን በጽ/ቤት፤ በስራ ክፍሎች በመናበብ በጥራት በማዘጋጀት
የትስስር ቅንጅታዊ አሰራር ትስስር ሰነድ አስፈላጊነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 በቅንጅት የሚከናወኑ ግቦች እና ተግባራቶች የእቅድ አካል አድርገው እንዲሰሩ ለማድረግ


 በቅንጅት የሚከናወኑ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ከጋራ መግባባት እስከ ውጤት መገምገም ድረስ
በጋራ መስራት እንዲቻል
 የጋራ የሆነ ለውጥን ለማስመዝገብ
 በቅንጅት አሰራር ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮችን በጋራ መፍትሄ ለመስጠት
 በዕድሮች መካከል አስተማማኝ፤ ወቅታዊ እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እና አሰራር ለመፍጠር
 በዕድሮች መካከል በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ የመተባበር እና የመከባበር ባህልን ለማዳበር
 ስራዎችን በትስስር ስምምነት ሰነዱ መሰረት በድርጊት እና መርሀ ግብሩ መሰረት ለመተግበር

1|Page
የቅንጅታዊ አሰራር ትስስር አሰራር ሁኔታ እና መርህ
በየደረጃው የሚገኙ ጽ/ቤት በራሱ በተቋሙ ውስጥ እና ከሚመለከታቸው ሌሎች አቻ ጽ/ቤት ጋር ስራን ቆጥሮ
ሀላፊነት በመውሰድ እና ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር እየተደረገ የነበረው
አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም፡፡ በመሆኑም የሚታየውን አንዳንድ የአመለካከት እና የግንዛቤ ችግሮችን በማስወገድ
የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ስራዎችን ከእቅድ ጀምሮ አስከ ፍጻሜ ድረስ ማከናወን ከሁሉም ባለድርሻ
አካላት የሚጠበቅ በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት በጋራ በሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ላይ ተመስርተው አቅድ
አውጥተው እና የስምምነት ሰነድ ተፈራርመው በቁርጠኝነት ወደ ስራ መግባት ይገባል፡፡

በመሆኑም የቅንጅታዊ ስራርን ተግባራዊ ለማድረግ የቅንጅት ስራዎችን በተገቢው ሁኔታ የሚከተሉትን የአሰራር
ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት።

 በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን ከማን ከማን ጋር ትስስሩ መከናወን እንዳለበት መለየት።


 የተለዩ ግቦች እና ተግባራት የጋራ መግባባት በመፍጠር የጋራ ሊለካ የሚችል የድርጊት መርሀ ግብር
ያለው የማስፈጸሚያ መርሐ-ግብር ወይም ዕቅድ ማዘጋጀት
 በተዘጋጀው የቅንጅት የትስስር ሰነድ ላይ በጋራ መፈራረም
 በስምምነት ሰነዱ መሰረት በድርጊት መርሀ ግብሩ መሰረት በቋሚነት ስራዎችን በጋራ ከጽ/ቤት ጋር
መከታተል፤አፈጻጸሙን መገምገም
 በስምምነት ሰነዱ መሰረት ቋሚ የግኝኑነት ጊዜን በድርጊት መርሐ-ግብሩ በማስቀመጥ ተግባራዊ
ማድረግ፤
 የባለድርሻ አከላትን ተሳትፎ ማረጋገጥ፤
 ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ያለውን አሰራር ማስፈን፤
 መተማመን እና መከባርን ማዳበር፤

ከላይ የተዘረዘሩ ተግባራትን በመፈጸም ውጤታማ ማድረግ የሚቻል ሲሆን በአመለካከት እና በግንዛቤ የሚታዩ
ችግሮችን መፍታት፤ ባለድርሻ አካላትን በተገቢው መንገድ የተጠያቂነት ስርዓትን ማስፈን ወሳኝ ነው፡፡

የውጪ ትስስር (External interface)


በወረዳዉ ስር የሚገኙ ዕድሮች ጋር በሚመለከታቸው ግቦች ተግባራት ላይ የጋራ አሰራር በመዘርጋት ለተገልጋዩ
ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት እና የተቀመጡትን ሰትራቴጂካዊ ግቦች ለማሳካት የሚያስችል የትስስር ዓይነት
ነው፡፡

በተናጠል በአንድ ጽ/ቤት ተልእኮ ብቻ አድርጎ ከመውሰድ ይልቅ ሁሉም ባለድርሻ አካለት/ዕድሮች
በሚመለከታቸው መስክ የድርሻቸውን በመውሰድ መስራቱ የሚጠበቀውን የልማት እና የመልካም አስተዳደር
ለውጥ በአስተማማኝ እና ዘላቂ መሰረት ላይ ለመጣል የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር የጽ/ቤቱን
ራይይ ተልእኮ እሴቶች ሰትራቴጂካዊ የትኩረት መስኮችን ከመጋራት ከማካፋል አኳያ ከፍተኛ አስተዋእጾ
ይኖረዋል፡፡

2|Page
የቅንጅታዊ አሰራር ክትትል እና ድጋፍ ስራዎች
ሁሉንም የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት/ዕድሮች በማሳተፍ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት
በመፍጠር እና እቅድ አዘጋጅቶ በትስስር ሰነዱ ላይ መፈራረም፤ በተቀመጠው የትስስር ሰነድ መሰረት ቅንጅታዊ
አሰራር ውስጥ የተቀመጡ ግቦች እና ተግባራት በታቀደላቸው የጊዜ ሰሌዳ እና ጥራት ደረጃ መፈጸማቸውን
ክትትል ያደርጋል፤ ይገመግማል፤ በእቅዱ መሰረት የሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረት ያደርጋል፡፡

የትስስሩ ወሰን
የቅንጅታዊ አሰራር ትስስሩ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
በወረዳዉ ስር ከሚገኙ ዕድሮች ጋር ሲሆን በትስስር ሰነድ ውስጥ የተዘረዘሩ ተግባራት ላይ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ከትስስር የሚጠበቅ ውጤት


በትስስሩ ሰነዱ መሰረት ተግባራትን በቅንጅት በመፈጸም የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ፡፡

በስሩ ላሉት የወረዳ ጽ/ቤቶች የሚጠበቁ ተግባራት


 ተቀናጅቶ ባለመስራት ምክንያት የሚፈጠሩ ጉዳዮችን ለይቶ በቅንጅት መፍታት እና የተፈቱበትን
አግባብ በሪፖርት ማሳወቅ
 የክትትል፣ የድጋፍ፣ የሱፐርቪዥን እና የኢንስፕክሽን ስራዎችን በትብብር መስራት
 የጽ/ቤት ዕቅድና ሪፖርት በወቅቱ እና በጥራት ጠምሮ ማቅረብ
 የአፈጻጸም ምዘና የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በወቅቱና በጥራት ማቅረብ
 ተቀናጅቶ ባለመስራት የሚታዩ ችግሮችን እንዲሁም በእቅድ እና ሪፖርት የሚስተዋሉ ተግዳሮችቶችን
በመለየት ተግባራዊ ማድረግ
 የሚሰጡ ተጨማሪ ተግባራቶችን በወቅቱ ማከናወንና የክንዉን ሪፖርት ማቅረብ

የትስስር ሰነድ ስለማሻሻል


ይህ የትስስር ስምምነት ሰነድ የጽ/ቤት ኃላፊዎች የጋራ ውይይት ወይም በአንዱ ወገን የጽሁፍ ጥያቄ በማቅረብ
በማናቸውም ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

ልዩነቶች ስለሚፈቱበት ሁኔታ


በዚህ የመግባቢያ ሰነድ በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ቢኖሩ በዘርፉ እና በወረዳዉ ሲቪል ምዝገባና
ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በውይይት እና በመግባባት መንፈስ እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡

የትስስሩ የቆይታ ጊዜ
ይህ የተግባር ትስስር የሁለቱም አካላት የሚመለከታቸው አካላት ሀላፊዎች ወይም ተወካዮች በፊርማቸው
ካጸደቁበት ቀን ከዛሬ ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ/ም የሚቆይ
ይሆናል፡፡

3|Page
በቅንጅታዊ አሰራር ሂደት ለሚገጥሙ ችግሮች የተቀመጡ የመፍትሄ ሀሳቦች
በቅንጅታዊ አሰራር ለሚገጥሙ ችግሮች ሁለቱ አካላት በወርሀዊ የግንኙነት ጊዜያቸው ቀርበው ተነጋግረው
መፍታት ይገባቸዋል፡፡

የክትትትል፣ ድጋፍ እና ግምገማ ስርዓት


በስምምነት ሰነዱ ላይ የተቀመጡትን ዓላማ እና ተግባራት ለማሳካት የትስስሩን አፈጻጸም የክትትል እና ድጋፍ
አግባብ እንደሚከተለው ይሆናል።

 የትስስር ሰነዱ ላይ በየወሩ በተለያዩ የክትትል ዘዴዎች በጽሁፍ፣ በስልክ፣ መረጃዎችን መለዋወጥ
 በየሩብ ዓመቱ በትስስር ሰነዱ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎች እና ተግባራት ስለመፈጸማቸውን፣ ይወያያሉ፣
ይገመግማሉ፣ በግምገማው ውጤት መነሻ መሰረት አስፈላጊውን የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ
 በትስስሩ የተገኙ መልካም ውጤቶችን፣ ልምዶችን እና ጥረቶችን በየሩብ ዓመት አንድ ጊዜ ይገመግማሉ
 በትስስር የተካተቱ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በየሩብ ዓመቱ የጽሁፍ ሪፖርት ይቀርባል፡፡

በውል ሰጪ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት እና
በውል ተቀባይ በስሩ የሚገኙ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት መካከል የሚጠበቁ
ሚናዎች እና ውጤቶች
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ማሳደግ፤

ዓላማ 1፡- ወቅታዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማለትም የሞት ምዝገባ ሽፋንን ከ 60% ወደ 70% ማሳደግ፤

4|Page
ተግባር 1፡-በዕድሮች ከ 30% ወደ 65% ሽፋን ማሳደግ፤

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃና ማስረጃ አሰጣጥ ቅብብሎሽ፤አቅርቦት እና አጠቃቀምን ማሳደግ

ተግባር 1፡ ለ 50 ተገልጋዮች የሞት ምዝገባ እና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት፤

 ለ 10 ተገልጋዮች በወቅቱ ሞት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት

 ለ 10 ተገልጋዮች በዘገየ ሞት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት፤

 ለ 30 ተገልጋዮች ጊዜ ገደቡ ባለፈ ሞት ምዝገባና ማስረጃ አገልግሎት መስጠት፤

ጊዜ ገደቡ
ተ.ቁ ወረዳ 10 ሲ/ም/ነ/አ/ጽ/ቤት በወቅቱ በዘገየ ድምር
ባለፈ

ድምር 10 10 30 50

5|Page
ተ/ቁ በቅንጅት እንዲሳካ የሚፈለገው ተግባር ውል የተቀባይ (የውል ተቀባይ) ተግባር የተቋሙ (የውል ሰጪ) ተግባር ከትስስሩ የሚጠበቅ ውጤት
ስም

1 ዕቅድና ሪፖርት በወቅቱ እና በጥራት ዕቅድና ሪፖርት በወቅቱ እና በጥራት ጠምሮ ማቅረብ በወረዳዉ ስር ያሉ ዕድሮችን እቅድና በወቅቱ እና በጥራት ተደራሽ የሆነ
ጠምሮ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ጥራት ያለው እቅድ እና ሪፖርት
ሪፖርት ወጥ ተናባቢ እና ወቅታዊ
መሆኑን ይከታተላል፤ ይጠምራል፤
ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ያደርጋል
.2. የተቀናጀ ወቅታዊ ክትትል እና ድጋፍ ለክትትል እና ድጋፍ ስራዎች፤ መሳተፍ፣ መረጃ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ የተቀናጀ ክትትል እና ድጋፍን
መስጠት፤ በማድረግ የጽ/ቤትን አፈጻጸም
በአዲስ ከተማ ማሻሻል
3 የተቀናጀ ወቅታዊ ሱፐርቪዝን ማድረግ ክፍለ ከተማ በሱፐርቪዥን ስራዎች ላይ መሳተፍ፣ መተባበር፣ መረጃ ወቅታዊ ሱፐርቪዝን ማከናወን ጠንካራ የሱፐርቪዥን በማከናወን
ጽ/ቤትን ማጠናከር እና
ወረዳ 10 ስር መስጠት፣ የተሰጡ ግብረ-መልሶችን ማረም አፈፃፀማቸውን ማሻሻል
4 የኢንስፕክሽን ስራዎችን በትብብር የሚገኙ ዕድሮች ለኢንስፕክሽን ስራዎችን የሚጠቅሙ መረረጃዎችን በትብብር የኢንስፔክሽን ስራዎችን በአሰራር ችግር የፈጠሩ ግለሰቦችና
በመስራት አሰራሮችን ማረም ማስተካከል፤ ያከናውናል ጽ/ቤትን ተጠያቂ ማድረግ
መስጠት፣ ትብብር ማድረግ፣ ግኝቱን በፍጥነት ማረም፣
አጥፊውን አካል በአሰራር መሥር ተጠያቂ ማድረግ
5 በጽ/ቤት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ ተቀናጅቶ ባለመስራት ምክንያት የሚፈጠሩ ጉዳዮችን ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፤ በተደረገ የቅንጅታዊ አሰራር ክትትል
አስራር ለመሻሻል የተጠናከረ ክትትል እና እና ድጋፍ በቅንጅት የተሳኩ ጉዳዮች
ድጋፍ ማድረግ ለይቶ በቅንጅት መፍታት እና የተፈቱበትን አግባብ
በሪፖርት ማሳወቅ፣
6 ወጥ፣ ወቅታዊ እና የጠራ እቅድና ሪፖርት በጥናት ስራዎች ላይ መሳተፍ፣ መረጃ መስጠት፤ በጥናት ያሳትፋል፣ ውጤቱን ያሰራጫል፣ ተጠንተው ተግባራዊ የተደረጉ
ለማቅረብ አሰራሮችን በጥናት ማሻሻል የጥናት ውጤቶች
የጥናቱን ውጤት ተግባራዊ ማድረግ ክትትል ያደርጋል

7 በቅንጅታዊ አሰራር የሚስተዋሉ ተቀናጅቶ ባለመስራት የሚታዩ ተግዳሮችቶችን በጥናት የተጠናውን ውጤት ለወረዳዎች ተጠንተው ተግባራዊ የተደረጉ
ተግደሮቶችን በጥናት ለይቶ መፍታት መለየት የጥናት ውጤቶ
ያሰራጫል፤ ክትትል ያደርጋል
8 በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ ካሉት ባለድርሻ አካላት ጋር ግንዘቤ መፈጠሩን ክትትል እና ድጋፍ የተፈጠረ ግንዘቤ
ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ያደርጋል
የግንዛቤ ማስጨበጫ መደረኮች ማዘጋጀት፣
9 በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የሲቪል ምዝገባ የአፈጻጸም ምዘና የሚያስፈልጉ መረጃዎችን በወቅቱና ዕድሮችን መመዘን በምዘና እና ፍረጃ በውድድር
እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤቶችን መንፈስ አፈፃፀማቸው የተሻሻለ
አፈጻጸም መመዘን፣ መፈረጅ በጥራት ማቅረብ ጽ/ቤቶች
10 ከዘርፉ የሚሰጡ ተጨመሪ ተግባራትን ከዘርፉ የሚሰጡ ተጨማሪ ተግባራቶችን በወቅቱ ከጽ/ቤቱ በሚሰጠው በወቅቱ የተከናወኑ ውጤታማ

6|Page
ተ/ቁ በቅንጅት እንዲሳካ የሚፈለገው ተግባር ውል የተቀባይ (የውል ተቀባይ) ተግባር የተቋሙ (የውል ሰጪ) ተግባር ከትስስሩ የሚጠበቅ ውጤት
ስም

ማከናወን ማከናወንና የክንዉን ሪፖርት ማቅረብ ስራዎች

የድርጊት መርሐ-ግብር
ተ/ በቅንጅት ለመስራት የታቀዱ ተግባራት ዝርዝር መለኪያ ዒላማ የድርጊት መርሐ-ግብር የግንኙነት ጊዜ ፈጻሚ የሚጠበቅ ውጤት
ቁ 1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ
ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
1. ዕቅድና ሪፖርት በወቅቱ እና በጥራት ጠምሮ ለሚመለከተው በቁጥር 4 1 2 3 4 በየሩብ ዓመቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቁጥር 4 በጥራት ተዘጋጅቶ
አካል ማቅረብ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና ተደራሽ የሆነ መረጃዎች
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
3 ወቅታዊ የሱፐርቪዢ በማካሄድ ጽ/ቤትን ማጠናከር በቁጥር 4 1 2 3 4 በየሩብ ዓመቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተደረገው ድጋፍ
ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና አፈጻጸማቸው የተሻሻሉ
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ጽ/ቤት
4 የኢንስፔክሽን ስራዎችን በትብብር በመስራት አሰራሮችን በመቶኛ 100% 100% 100% 100% 100% በየሩብ ዓመቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተጠያቂ የሆኑ ጽ/ቤት
ማረም ማስተካከል፤ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና እናግለሰቦች
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
5 በዕድሮች መካከል ያለዉን ቅንጅታዊ አስራር ለመሻሻል በቁጥር 4 1 2 3 4 በየሩብ ዓመቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተደረገው ክትትል እና
የተጠናከረ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና ድጋፍ በቅንጅት የተከናዉ
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስራዎች
6 ወጥ፣ ወቅታዊ እና የጠራ እቅድና ሪፖርት ለማቅረብ በቁጥር 1 1 በዓመቱ 1 ጊዜ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተጠንቶ ተግባራዊ የሆነ 1
አሰራሮችን በጥናት ማሻሻል ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና ጥናት
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
7 በቅንጅታዊ አሰራር የሚስተዋሉ ተግደሮቶችን በጥናት ለይቶ በቁጥር 1 1 በዓመቱ 1 ጊዜ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ተጠንቶ ተግባራዊ የሆነ 1
መፍታት ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና ጥናት
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
8 በቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቁጥር 1 1 በዓመቱ 1 ጊዜ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተፈጠረ ግንዛቤ
መስጠት ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
9 በወረዳ ደረጃ የሚገኙ ዕድሮችን አፈጻጸም መመዘን፣ በቁጥር 2 ጊዜ - 1 2 በየ 6 ወር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተሸሻለ አፈጻጸም
መፈረጅ ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና

7|Page
ተ/ በቅንጅት ለመስራት የታቀዱ ተግባራት ዝርዝር መለኪያ ዒላማ የድርጊት መርሐ-ግብር የግንኙነት ጊዜ ፈጻሚ የሚጠበቅ ውጤት
ቁ 1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ
ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት
10 ከዘርፉ የሚሰጡ ተጨማሪ ተግባራትን ማከናወን በመቶኛ 100% 100% 100% 100% 100% በየሩብ ዓመቱ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በጥራት እና በወቅቱ
ወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የተከናወኑ ስራዎች
የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት

8|Page
የሁለቱ ባለድርሻ አካላት የስምምነት ፊርማ
በትስስር ስምምነት ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን የስራ ድርሻዎች ሙሉ በሙሉ በመውሰድ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት
አድርገናል፡፡

1. የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ

የኃላፊ ስም:-

ፊርማ:-

ቀን :-

2. ዊንጌት አካባቢ መረዳጃ ዕድር

የዕድሩ ዳኛ /ተወካይ ስም:-

ፊርማ:-

ቀን :-

9|Page
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲ/ም/ነ/አ/ኤ

የሚከሰቱ ኩነቶችን ለማስመዝገብ ከእድር ማህበራት ለወረዳ ሲ/ም/ነ/አ/ጽ/ቤት የሚሰጥ

ማሳወቂያ ቅጽ

1. የሟች ሙሉ ስም የአባት ስም የአያት ስም


2. የሟች አድራሻ ክ/ከተማ ወረዳ ነባር ቀበሌ የቤት ቁጥር
3. የሟች የትዉልድ ወር ቀን ዓ.ም
4. ሞቱ የተከሰተበት ወር ቀን ዓ.ም
5. ሞቱ የተከሰተበት ክልል ክ/ከተማ ወረዳ ቤ.ቁ
6. ከሟች ጋር ያለዉ ዝምድና
7. ሞቱን ያስመዘገበዉ የእድር ዳኛ ስም ፊርማ ቀን
ማሳሰቢያ:-

 ይህ የማሳወቂያ ቅጽ ዕድሩ ከሚጽፈዉ ደብዳቤ ጋር አብሮ የሚላክ ይሆናል


 ደብዳቤዉ ሲጻፍ መሟላት ያለባቸዉ ሟች የሞተበት ቀን/ወር/ዓ.ም ፣ የደብዳቤ ቁጥር፣ቀን፣ የዕድሩ ዳኛ ስም
እና ፊርማ እና የስራ ድርሻ ማለትም የዕድሩ ዳኛ ወይም ተወካይ ተብሎ መገለጽ አለበት
 የዕድሩ ማህተም
--------------------------------------------------------------------------------------

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲ/ም/ነ/አ/ኤ

የሚከሰቱ ኩነቶችን ለማስመዝገብ ከእድር ማህበራት ለወረዳ ሲ/ም/ነ/አ/ጽ/ቤት የሚሰጥ

ማሳወቂያ ቅጽ

1. የሟች ሙሉ ስም የአባት ስም የአያት ስም


2. የሟች አድራሻ ክ/ከተማ ወረዳ ነባር ቀበሌ የቤት ቁጥር
3. የሟች የትዉልድ ወር ቀን ዓ.ም
4. ሞቱ የተከሰተበት ወር ቀን ዓ.ም
5. ሞቱ የተከሰተበት ክልል ክ/ከተማ ወረዳ ቤ.ቁ
6. ከሟች ጋር ያለዉ ዝምድና
7. ሞቱን ያስመዘገበዉ የእድር ዳኛ ስም ፊርማ ቀን
ማሳሰቢያ:-

 ይህ የማሳወቂያ ቅጽ ዕድሩ ከሚጽፈዉ ደብዳቤ ጋር አብሮ የሚላክ ይሆናል


 ደብዳቤዉ ሲጻፍ መሟላት ያለባቸዉ ሟች የሞተበት ቀን/ወር/ዓ.ም ፣ የደብዳቤ ቁጥር፣ቀን፣ የዕድሩ ዳኛ ስም
እና ፊርማ እና የስራ ድርሻ ማለትም የዕድሩ ዳኛ ወይም ተወካይ ተብሎ መገለጽ አለበት
 የዕድሩ ማህተም

10 | P a g e

You might also like