You are on page 1of 14

መግቢያ

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 66/1989 የተቋቋመ' ከመንግስት' ከክልሎችና ከመንገድ ተጠቃሚዎች የሚወከሉ
አባላት ባሉት ቦርድ የበላይነት የሚተዳደር እና ተጠሪነቱ ለትራንስፖርት ሚኒስቴር የሆነ ተቋም ነው፡፡ ጽ/ቤቱ በአዋጁ
የተሰጡት ሥልጣንና ኃላፊነቶች በዚህ ሠነድ (ቻርተር) የወደፊት ገጾች በዝርዝር የሚመላከት ሲሆን በጥቅሉ ሲታይ ግን
ጽ/ቤቱ በአዋጅ በተደነገጉት እና በመንግስት ውሳኔ የፈንዱ የገቢ ምንጮች እንዲሆኑ ከተወሰኑት የገቢ ዓይነቶች (በፈንዱ
ማቋቋሚያ አዋጅ ከተዘረዘሩት ማለትም በመንግስት ከሚመደብ በጀት' ለመንገድ ጥገና ከተጣለ የነዳጅ ታሪፍ' በክብደት
ላይ ከተመሰረተ ዓመታዊ የተሸከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ' ከተፈቀደው ክብደት በላይ በመጫን ከሚጣል ቅጣት'
እንደአስፈላጊነቱ ከሚጣል ከማናቸውም ሌላ የመንገድ ታሪፍ) ገቢ መሰብሰብ' በየበጀት ዓመቱ ለፈንዱ ተጠቃሚዎች
በጀት መደልደልና በተደለደለ በጀት መሰረትም ገንዘብ በማስተላለፍ የተላለፈው ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ
ሥራ ላይ መዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም ነው፡፡

የፈንዱ ተጠቃሚዎች የፌዴራል መንገዶችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን' 9 የክልል መንገድ
ባለሥልጣኖች' ይህ የዜጎች ቻርተር በተዘጋጀበት ወቅት የፈንዱ ተጠቃሚ የሆኑ 60 የከተማ አስተዳደሮች እና የብሄራዊ
የመንገድ ደህንነት ካውንስል ጽ/ቤት ሲሆኑ በድምሩ 71 ተቋማት ናቸው፡፡ ጽ/ቤቱ ለእነዚህ ተቋማት የሚመድበው በጀት
የሚውለው ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት ለሚሰጡ የመንገድ መስመሮች እና ድልድዮች ጥገና እና ለመንገድ ደህንነት
ሥራዎች ነው፡፡

የፈንድ ጽ/ቤቱ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማስፈፀም የሚያስችለው አደረጃጀት ያለው ሲሆን በዚህም መሰረት በሶስት
ዓላማ አስፈፃሚ ቡድኖች ማለትም ፕላን ዝግጅት' ክትትልና ግምገማ& ፋይናንስ እና ኦዲት ቡድኖች እንዲሁም በድጋፍ
ሠጪ እና በህዝብ ግንኙነት የሥራ ዘርፎች ተደራጅቷል፡፡ ጽ/ቤቱ ለደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና
ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን ይቻለው ዘንድ የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት (BPR) በማድረግ እና
የውጤት ተኮር ሥርዓትን (BSC) በመዘርጋት በተግባር ላይ ያዋለ ሲሆን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ጥራት ያላቸው'
የደንበኞችን እርካታ የሚያስገኙ' ግልፅነትንና ተጠያቂነትን የተላበሱ እንዲሆኑ ለማስቻል ዜጎች ከጽ/ቤቱ ማግኘት
የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች' የአገልግሎት አሠጣጥ
ስታንዳርዶች እና መብቶቻቸውን እንዲሁም በአገልግሎት አሠጣጡ ቅሬታ ያላቸው የሚስተናገዱበትን ሥርዓት በዚህ
ቻርተር ውስጥ በማካተት ለአገልግሎቱ መሻሻል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል ይህ የዜጎች ቻርተር
የተዘጋጀ ሲሆን በሠነዱም የተቋሙ ራዕይ' ተልዕኮ' ዕሴቶች እና በአዋጅ የተሰጡት ሥልጣንና ኃላፊነቶች እንዲካተቱ
ተደርጓል፡፡

1. የመስሪያ ቤቱ ስም፡- የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት

2. የቻርተሩ ዓላማ፡-

 ግልፅነትንና ተጠያቂነትን የተላበሰ አሠራር ማስፈን'

 ዜጎች ጥራትና ወቅቱን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል'

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 1


 ተቋሙ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነቶች' የመፈፀሚያ ጊዜ እና አገልግሎቶቹን ለማግኘት
መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ዜጎች እንዲያውቋቸው ማድረግ'

 ዜጎች ለመንገዶች የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸውና ለደህንነታቸው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ


እንዲያበረክቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባሮችን ማከናወን'

 በጽ/ቤቱ እና በዜጎች (ደንበኞች' ባለድርሻ አካላት' ተባባሪ አካላት' ወዘተ…) መካከል የተጠናከረ
ግንኙነት እንዲኖር ማስቻል'

3. የተቋሙ ራዕይ

“በ 2015 የራሱን መንገድ በራሱ አቅም የሚንከባከብ ህብረተሰብ መፍጠር”

4. የተቋሙ ተልዕኮ

“የመንገድ ፈንድ አስተዳደር ሥርዓትን በማሟላት የታቀዱ የመንገድ ጥገናና የመንገድ ደህንነት ሥራዎችን ለማከናወን
የሚያስችል ፈንድ በማፈላለግ' በመሰብሰብና ለመንገድ ኤጀንሲዎች በማከፋፈል ከመንገድ ተጠቃሚው የመክፈል
አቅምና ፍላጎት ጋር የተመጣጠነ የመንገድ ጥገና ሥራ ጥራቱን ጠብቆ እንዲከናወን በማድረግ አፈፃፀሙን በመከታተልና
በመገምገም መንገድ ተጠቃሚው ህብረተሰብ ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ማግኘቱን ማረጋገጥ”

5. ዕሴቶች

 የመንገድ ተጠቃሚውን እርካታ ለማስገኘት አንተጋለን


 ሥራችን አለቃችን ነው
 ሙስናን እንዋጋለን
 ለለውጥ ዝግጁ ነን
 ቁጠባን ባህላችን እናደርጋለን
 ለነገ የምናሳድረው ሥራ አይኖረንም

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 2


 በውይይት ችግሮቻችንን እንፈታለን
 መስራት ያለብንን ያለቀስቃሽ እንሰራለን

6. ስትራተጂያዊ የትኩረት መስኮች

 የላቀ የመንገድ ፈንድ ማመንጨትና ማስተዳደር (በፈንድ ጽ/ቤቱ ማቋቋሚያ አዋጅ የገቢ ምንጮች
እንዲሆኑ ከተወሰኑት የገቢ ዓይነቶች ገቢ ለማሰባሰብ እና ተጨማሪ ፈንድ ሊገኝ የሚችልበትን ሁኔታ
ለማመቻቸት የሚያስችሉ ደንቦችን እና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ለመንግስት የውሳኔ ሀሳብ
ማቅረብን ያካተተ ነው)፡፡

 የላቀ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት፡፡

 የላቀ ስትራተጂያዊ ግንኙነት መፍጠር፡፡

7. የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ሥልጣንና ተግባሮች

 የቦርዱ ውሳኔዎችና መመሪያዎች በትክከል ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል' ያረጋግጣል፤

 የፈንዱን ሂሣብና ሪኮርድ ይይዛል፤

 የቦርዱን ሥራ አመራር ስብሰባዎች ሪኮርዶች ይይዛል፤

 ለፈንዱ መግባት የሚገባው ገንዘብ ሁሉ በወቅቱ በፈንዱ ሂሣብ ገቢ መደረጉን ይከታተላል፤

 የፈንዱን የሒሣብ መግለጫዎች እያዘጋጀ በየዓመቱ ለቦርዱ ያቀርባል፤

 ስለፈንዱ ገቢዎችና አጠቃቀም' ስለመንገድ ጥገና ጠቀሜታ' መንገድን አለመጠገን


ስለሚያስከትላቸው ውጤቶች' ጥራት ያለው መንገድ ለተጠቃሚዎች ስለሚያስገኘው ቁጠባና
ስለመሳሰሉት የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችንና ወቅታዊ ሕትመቶችን ያመነጫል' ያሠራጫል፤

 የንብረት ባለቤት ይሆናል' ውል ይዋዋላል' በስሙ ይከሳል' ይከሰሳል፤

8. ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት

8.1. ደንበኞች

 የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን&


 የክልል ገጠር መንገድ ባለሥልጣኖች&
 የፈንዱ ተጠቃሚ የሆኑ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች&

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 3


 ብሄራዊ የመንገድ ደህንነት ካውንስል ጽ/ቤት&

8.2. ባለድርሻ አካላት


 የመንገድ ተጠቃሚው ህብረተሰብ&
 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት&
 ትራንስፖርት ሚኒስቴር&
 ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር&
 የፌዴራልና የክልል መንግስታት&
 የፌዴራልና የክልል ትራንስፖርት ባለሥልጣኖችና ቢሮዎች&
 የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅትና ነዳጅ ኩባንያዎች&
 የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት&

9. አጠቃላይ የጥራት (አሠራር) መርሆዎች

 የፈንዱን ገቢ በወቅቱና ሙሉ በሙሉ መሰብሰብ&

 በተጨባጭ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ እና ፍትሃዊ የበጀት ድልድል ለፈንዱ ተጠቃሚዎች ማድረግ&

 ፈጣን የክፍያ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ&

 የፈንዱ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማስቻል&

 ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሠራር ሥርዓት ማስፈን&

 ለዜጎች (ደንበኞች' ባለድርሻ አካላት' ተባባሪ አካላት' ወዘተ…) ጥያቄዎችና አስተያየቶች ፈጣን
ምላሽ መስጠት&

 በዕቅድ መመራትና ለውጤት መስራት&

 የሲቪል ሠርቪሱን ህጎች' ደንቦችና መመሪያዎች ማክበር&

10. የደንበኞችና ባለድርሻ አካላት መብቶች

10.1. የደንበኞች መብቶች

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 4


 የፈንዱን አስተዳደር አስመልክቶ የወጡ ህጎችን' ደንቦችንና መመሪያዎችን ማወቅ&

 የበጀት ድልድል መስፈርቶችንና ታሳቢዎችን ማወቅ&

 በየበጀት ዓመቱ የፍትሃዊ በጀት ድልድል ተጠቃሚ መሆን&

 በቻርተሩ በተቀመጡ የአገልግሎት ስታንዳርዶች መሰረት አገልግሎት ማግኘት&

 ሁሉንም አገልግሎቶች በእኩልነትና በፍትሃዊነት ማግኘትና መጠቀም&

 ተፈላጊ መረጃዎችን በተፈለገው መጠንና ወቅት ማግኘት&

 ከፈንድ ጽ/ቤቱ እና በስሩ ከተዋቀሩ የሥራ ዘርፎች ጋር በጋራም ሆነ በተናጠል መመካከር&

 ቅሬታና አስተያየት በማንኛውም ወቅት ማቅረብ&

 ለሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ተገቢውን ምላሽ በወቅቱ ማግኘት&

 በፈንዱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ የሚያስችሉ አስተያየቶችን ማቅረብ&

10.2. የባለድርሻ አካላት መብቶች

 ለፈንዱ ተጠቃሚዎች በየበጀት ዓመቱ የሚደለደል የበጀት መጠንን ማወቅ&

 ወቅታዊ እና የተሟላ መረጃዎችን የያዙ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶች ማግኘት&

 ተፈላጊ መረጃዎችን በተፈለገው መጠንና ወቅት ማግኘት&

 በዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችና መረጃዎች ላይ አስተያየትና ግብረ መልስ መስጠት&

 በፈንዱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ የሚያስችሉ አስተያየቶችን ማቅረብ&

 ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ወቅታዊና በቂ ምላሽ ማግኘት&

11. በመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የሚሰጡ አገልግሎቶች

የፈንድ ጽ/ቤቱ የሚሠጣቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት ጉዳዮች ታሳቢ ያደረጉት
የጽ/ቤቱን ደንበኞች' ባለድርሻ አካላት እና ተባባሪዎችን ሲሆን ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦችን የዳሰሱ እንዲሆኑ
ተደርጓል፡፡

 የፈንዱን ገቢ ማሰባሰብና ፋይናንሱን ማስተዳደር&

 የመንገድ ጥገና እና መንገድ ደህንነት እርምጃ ማስፈፀሚያ ሥራዎችን ፋይናንስ ማድረግ&

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 5


 በፈንዱ የፋይናንስ አስተዳደር ላይ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝና ማሠራጨት&

 በፈንዱ በጀት የሚከናወኑ ሥራዎች ላይ የክትትልና ድጋፍ ሥራዎችን ማከናወን&

 ከአማካሪ ድርጅቶች የሚቀርቡ የመንገድ ጥገና ሪፖርቶችን በመገምገም ግብረ መልስ መስጠት&

 የሚቀርቡ የአፈፃፀም ሪፖርቶችን በመገምገም እና በመስክ ላይ የተደገፈ የክትትልና የድጋፍ


ሥራዎችን በማከናወን የፈንዱ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ'

 ከፈንዱ አስተዳደር ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎችን ማከናወን'

 የፈንዱንና የመደበኛ በጀትን የሂሣብ መዛግብቶችን በአግባቡ በመያዝ የሂሣብ መግለጫዎችን


ማዘጋጀት'

 የፈንዱን ገንዘብ በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ሠነድ በማዕከላዊነት አሳትሞ ለደንበኞች


ማሠራጨት'

 ከደንበኞች የሚቀርቡ የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅዶችን በመፈተሽ ግብረ መልስ መስጠት'

 ደንበኞችን ያሳተፈ የፈንድ አስተዳደር መመሪያ በማውጣት ሥራ ላይ እንዲውል ማድረግ'

 ለፈንዱ ተጠቃሚዎች የተፈቀዱ ክፍያዎችን መፈፀም'

 ከፈንዱ ተጠቃሚዎች የሚቀርቡ ሪፖርቶችን በመገምገም ግብረ መልስ መስጠት'

 ለደንበኞች ወቅታዊና ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ድጋፍ መስጠት'

 የመንገድ ኤጀንሲዎችን ሂሣብ በየበጀት ዓመቱ መመርመርና ቴክኒካል ኦዲት ማከናወን'

 የፈንዱን ማዕከላዊና የመንገድ ኤጀንሲዎችን ሂሣብ በየበጀት ዓመቱ በውጭ ኦዲት ማስመርመር'

 ለደንበኞች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ'

 የጽ/ቤቱን ህጎች' ደንቦችና መመሪያዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማሠራጨት'

12. በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ቡድኖችና የሥራ ዘርፎች የተቋቋሙበት ዓላማ

12.1. የፕላን ዝግጅት' ክትትልና ግምገማ ቡድን

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 6


 የፈንዱን ስትራተጂያዊና ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት'

 የፈንዱ ተጠቃሚዎችን የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ ከዕቅድ ማቅረቢያ መስፈርቶች አኳያ


በመፈተሸ ግብረ መልስ መስጠት'

 ለመንገድ ጥገናና ለመንገድ ደህንነት እርምጃዎች ማስፈፀሚያ የበጀት ድልድል ማከናወን'

 የዕቅድ አፈፃፀምን መከታተል' መገምገም' ግብረ መልስ መስጠትና ሪፖርት ማቅረብ'

 የተጠቃለለ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ'

 በፈንዱ አፈፃፀም ላይ የክትትልና ግምገማ ሥራዎች ማከናወን'

 ከአማካሪ ድርጅቶች የሚቀርቡ የመንገድ ጥገና ሪፖርቶችን በመገምገም ግብረ መልስ


መስጠት'

 የሚቀርቡ የአፈፃፀም ሪፖርቶችን በመገምገም እና በመስክ ላይ የተደገፈ የክትትልና


የድጋፍ ሥራዎችን በማከናወን የፈንዱ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ'

 ከፈንዱ አሠራር ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን የማሰባሰብ'


ማደራጀትና ማሠራጨት ሥራዎችን ማከናወን'

12.2. የፋይናንስ ቡድን

 የፈንዱን ገቢዎች ማሰባሰብ'

 የፈንዱንና መደበኛ በጀትን ማስተዳደርና ክፍያዎችን መፈፀም'

 የፈንዱንና የመደበኛ በጀት የሂሣብ መዛግብት መያዝ'

 የሂሣብ ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከታች አካላት ማሠራጨትና ማስመርመር'

 የፈንዱን የፋይናንስ አሠራር መመሪያዎችን ማውጣት' ማሻሻልና ለሚመለከታቸው


አካላት ማሠራጨት'

12.3. የኦዲት ቡድን

 የፈንዱ ገንዘብ በፋይናንስ ህግና ሥርዓት መሰረት ሥራ ላይ መዋሉን መከታተልና


ሪፖርት ማቅረብ'

 የፈንዱ የማዕከላዊ እና የመንገድ ኤጀንሲዎች ሂሣብ በተገቢው መንገድ ተዘግቶ ለኦዲት


ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ'

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 7


 በኦዲት ግኝት መሰረት ተገቢው የእርምት እና የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን
መከታተልና ማረጋገጥ እንዲሁም ችግር ባለባቸው መንገድ ኤጀንሲዎች በመገኘት
የማጣራት ሥራዎችን በማከናወን የመፍትሄ አስተያየት ማቅረብ'

 የመንገድ ኤጀንሲዎችን ሂሣብ በየበጀት ዓመቱ መመርመር'

 በፋይናንስ ኦዲት ላይ የተጠናቀረ ሪፖርት ማዘጋጀትና ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ


መልስ መስጠት'

 በመደበኛ በጀት ላይ የውስጥ ኦዲት ሥራዎችን ማከናወን'

 የተዘረጋ የቁጥጥር ሥርዓትን በመገምገምና የስጋት ዳሰሳ በማከናወን አስተያየት


ማቅረብ'

 ለኦዲት ግኝት ምክንያት የሆኑ የአሠራር ሥርዓቶችን በመፈተሽ የማስተካከያ እርምጃ


ለመውሰድ የሚያስችል አስተያየት ማቅረብ'

1.2.4. የህዝብ ግንኙነት

 በጽ/ቤቱ በተለዩት የትኩረት መስኮች የስራ ክንውን ዙሪያ ዶክመንተሪ ፊልም እንዲዘጋጅ
ማድረግ'

 በተቋሙ የትኩረት መስኮችና ተያያዥ ርዕሶች ዙሪያ መጽሔት አዘጋጅቶ ማሠራጨት'

 በዘርፉ የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያጎለብቱና የሚያነሳሱ መልዕክቶች' ብሮሸሮች' በራሪ


ወረቀቶች' ፖስት ካርዶች' የቀን መቁጠሪያዎች (ካላንደር)' ባነሮች እና
ማስታወቂያዎችን አሳትሞ ማሠራጨት'

 የጽ/ቤቱን የሥራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ልዩ ልዩ መረጃዎችን በተቋሙ ድረ ገጽ በመጫን


የውስጥና የውጭ አካላት በተቋሙ ተልዕኮና ተግባር አፈጻጸም ዙሪያ ግንዛቤ እንዲጨብጡ
ማድረግ'

 የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴዎች ከሀገር አቀፍና ከዓለም አቀፍ ሁነቶች ጋር በማያያዝ


እንዲከበሩ ማድረግ'

 ከፈንድ ጽ/ቤቱ ጋር የተያያዙ ወቅታዊ ክንውኖችን አስመልክቶ የፅሁፍ መግለጫ (ፕሬስ


ሪሊዝ) በማዘጋጀትና ለመገናኛ ብዙሃን በመስጠት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ
ማድረግ'

1.2.5. የድጋፍ ሠጪ

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 8


 የጽ/ቤቱን ኃብትና ንብረት ማስተዳደር'

 የዕቃና የአገልግሎት ግዥዎችን በመፈጸም አቅርቦቶችን ማሟላት'

 የሠው ኃብት ልማትና አስተዳደር ሥራዎችን ማከናወን'

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 9


13. በተቋሙ የሚሠጡ አገልግሎቶች የመፈፀሚያ ጊዜ እና ቅድመ ሁኔታዎች

ተራ አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ


የአገልግሎት ዓይነት የመፈፀሚያ ጊዜ
ቁጥር ሁኔታዎች

1 ለፈንዱ ተጠቃሚዎች የበጀት ድልድል በማድረግ ማሳወቅ ከግንቦት 1 - ሰኔ 30 ዓመታዊ የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ

የቅድሚያ ክፍያ ጥያቄ' ዓመታዊ የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ'


የክፍያ ጥያቄ በቀረበ በ 3
2 ለፈንዱ ተጠቃሚዎች የ 20% ቅድሚያ ክፍያ መፈፀም ዓመታዊ የፊዚካልና ፋይናንሻ ዕቅድ ክንውን ሪፖርት' የሂሣብ
ቀን ውሰጥ
ሪፖርት' የክፍያ ጥያቄ

3 ከፈንዱ ተጠቃሚ የሚቀርብ የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ ገምግሞ ግብረ መልስ መስጠት ከ 1 እስከ 3 ቀን ዓመታዊ የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ

ከፈንዱ ተጠቃሚ የሚቀርብ የፊዚካልና ፋይናንሻ ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ገምግሞ ግብረ
4 3 ቀን ዓመታዊ የፊዚካልና ፋይናንሻ ዕቅድ ክንውን ሪፖርት
መልስ መስጠት

የሂሣብ ሪፖርት (ዓመታዊ የሂሣብ ሪፖርት ሲቀርብ የሰኔና


5 ከፈንዱ ተጠቃሚ የሚቀርብ የፋይናንስ ሪፖርት ገምግሞ ግብረ መልስ መስጠት 5 ቀን የሐምሌ የባንክ መግለጫ /Bank Statement/ መያያዝ
ይኖርበታል)

6 ለሚቀርቡ የዕቅድ ማሻሻያ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ከ 1 እስከ 3 ቀን የተሻሻለ ዕቅድ

7 ለሚቀርቡ የበጀት ዝውውር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እስከ 1 ሳምንት የበጀት ዝውውር ጥያቄ

በቂ በጀት' የሩብ ዓመትና ዓመታዊ የሂሣብ ሪፖርት' የፀደቀ


ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ' ለተከናወነ ሥራ በአማካሪ ድርጅት የፀደቀ
8 የተሟላ ደጋፊ የሠነድ ማስረጃ ለቀረበባቸው የክፍያ ጥያቄዎች ክፍያ መፈፀም 3 ቀን
የክፍያ ሠርተፊኬት' ከውል ጋር የተጣጣመ የክፍያ ጥያቄ''
በተፈቀደላቸው የሥራ ኃላፊዎች የፀደቀ የክፍያ ጥያቄ

9 ለደንበኞችና ባለድርሻ አካላት መረጃዎችን መስጠት እስከ 1 ሳምንት አግባብነት ያለው የመረጃ ጥያቄ

የሠነዱ (ሠነዶቹ) ተጠቃሚ አካል መሆን እንዲሁም


10 የታተሙ የሂሣብ ሠነዶችን ለፈንዱ ተጠቃሚዎች መስጠት 4 ሠዓት የሚፈለጉ ሠነዶችን ዝርዝር (ዓይነትና ብዛት) እና
የተረካቢውን ማንነት በሚገልፅ ደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ

ለሙያዊ ድጋፍ የሚያበቃ የአሠራር ክፍተት መኖሩን


11 ለደንበኞች ወቅታዊና ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ድጋፍ መስጠት እንደ አስፈላጊነቱ
ማረጋገጥ' የሙያዊ ድጋፍ ጥያቄ

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 10


ተራ አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ
የአገልግሎት ዓይነት የመፈፀሚያ ጊዜ
ቁጥር ሁኔታዎች

ለበጀት ዓመቱ ከተመደበ በጀት 80 በመቶውን እስከ


12 የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ተቀብሎ ግብረ መልስ መስጠት ከ 1 እስከ 3 ቀን ሚያዝያ 30 ሥራ ላይ ማዋልና በተጨማሪው በጀት
የሚሰሩ ሥራዎች የፊዚካልና ፋይናንሻል ዕቅድ

ለበጀት ዓመቱ ከተመደበ በጀት 80 በመቶውን እስከ


13 በተገቢው መንገድ ለሚቀርቡ የተጨማሪ በጀት ጥያቄዎች ክፍያ መፈፀም 3 ቀን
ሚያዝያ 30 ሥራ ላይ ማዋልና የተጨማሪ በጀት ጥያቄ

ለሙያዊ ሥልጠና የማሽን ኦፕሬታሮችን ዝርዝር በወቅቱ


14 ለፈንዱ ተጠቃሚዎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማከናወን እንደ አስፈላጊነቱ ማቅረብና ተፈላጊ ማስረጃዎች ማያያዝ' ለአቅም ግንባታ
ሥራዎች የሚያበቁ ቅድመ ሁኔታዎች

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 11


14. ለደንበኞች የምንገባው ቃል

 በተዘጋጀው ቻርተር መሰረት ለዜጎች ቀልጣፋ' ግልፅና ፍትሃዊ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡

 ደንበኞች ለሚያቀርቧቸው ቅሬታዎች ወቅታዊና አግባብነት ያላቸው ምላሽ እንሰጣለን፡፡

15. አስተያየትና ተሳትፎ

ዜጎች ያላቸውን አስተያየት' ቅሬታ' ጥቆማ እንዲሁም ጥያቄዎችን በጽ/ቤቱ ዌብሳይት' በሀሳብ መስጫ ሳጥን'
በሀሳብ መስጫ መዝገብ' በስልክ' በፋክስ' በኢ-ሜይል ወይም በጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት በቃል' በፅሁፍ ወይም
በሁለቱም ማቅረብ ይችላሉ፡፡

16. የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት

በቻርተሩ በተቀመጠው መሰረት አገልግሎት ያላገኘ ዜጋ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ በዚህም መሰረት
ከላይ በተራ ቁጥር 15 ላይ በተገለፁት ዘዴዎች፡-

 ቅሬታ ያጋጠመው ዜጋ ቅሬታውን አገልግሎት ለሰጠው ፈፃሚ ያቀርባል& ፈፃሚውም ቅሬታ


በቀረበለት በግማሽ ቀን ውስጥ ለቅሬታ አቅራቢው ምላሽ መስጠት ይኖርበታል'

 በፈፃሚዎች ምላሽ ያልረካ ቅሬታ አቅራቢ ቅሬታውን ለሥራ ክፍሉ ያቀርባል የሥራ ክፍሉም
ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ቅሬታ በቀረበለት በ 1 (አንድ) ቀን ውስጥ ለቅሬታ
አቅራቢው ምላሽ መስጠት ይኖርበታል'

 በሥራ ክፍሉ ምላሽ ያልረካ ከሆነ መስሪያ ቤቱ ለሰየመው ቅሬታ አጣሪ አካል ቅሬታውን ያቀርባል&
ቅሬታ አጣሪው አካል ቅሬታ በቀረበለት በ 2 (ሁለት) ቀን ውስጥ ለቅሬታ አቅራቢው ምላሽ መስጠት
ይኖርበታል'

 ቅሬታ ያቀረበ ዜጋ በቅሬታ አጣሪው አካል ምላሽ ያልረካ ከሆነ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፤
የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊም በዜጋው የቀረበውን ጥያቄ እንዲጣራ በማድረግ ከሶስት ቀን ባልበለጠ
ጊዜ ውስጥ ለቅሬታ አቅራቢው የመጨረሻ መልስ ይሰጣል፡፡

 የቀረቡ ቅሬታዎችን ይዘት' ቅሬታዎቹ የቀረቡበትን ቀን' የተሰጡ ምላሾችን (መፍትሄዎችን)'


ለቅሬታዎቹ ምላሽ የተሰጠበትን ጊዜ' ወዘተ…በዝርዝር በማመላከት (በመግለፅ) በየ 15 (አስራ
አምስት) ቀን በማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ እንዲገለፅ ይደረጋል፡፡

17. የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት

ጽ/ቤቱ በቻርተሩ መሰረት ዜጎች አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥበት የክትትልና ድጋፍ
ሥርዓት ይኖረዋል፡፡

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 12


የተቋሙ የሥራ ክፍሎች' አመራሮችና ፈፃሚዎች በስታንዳርዱ መሰረት የሚጠበቅባቸውን
ስለመፈፀማቸው በውጤት ተኮር የአፈፃፀም መመሪያ አግባብ በየሳምንቱ' በየአስራ አምስት ቀን እና
በየወሩ በመገምገም ለተቋሙ የበላይ አመራር ሪፖርት ይቀርባል፡፡

ጽ/ቤቱ የምክክር መድረኮችን በማዘጋጀት ከደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ጋር የአገልግሎት አሠጣጡን


ይገመግማል፤ በሚደረስባቸው የስምምነት ነጥቦች መሰረትም የማሻሻያ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡

የቅሬታ ማቅረቢያ እና አፈታት ሥርዓቱ በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል፡፡

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 13


18. የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የሥራ ዘርፎችና ኃላፊዎች ስምና አድራሻ

ተ. የሥራው ዘርፍ ኃላፊ ስልክ ቁጥር


የሥራ ዘርፍ ፋክስ
ቁ ስም ኃላፊነት የቢሮ ተንቀሳቃሽ

011-470-2932
1 ጽ/ቤት አቶ ራሺድ መሐመድ ዋና ዳይሬክተር 0911-20-08-24 011-553-44-07
011-470-2662

2 ፕላንዝግጅት'ክትትልናግምገማ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቡድን መሪ ተወካይ 011-470-2935 0911-871727

3 ቴክኒካል ክትትልና ግምገማ ቡድን አቶ አለባቸው አህመድ ቡድን መሪ 011-470-1439 0923-25-60-87

3 ፋይናንስ ወ/ሮ አባይነሽ ከበደ ቡድን መሪ 011-470-2467 0911-41-49-32

4 ኦዲት ወ/ሮ ዘነበች ጤናው ቡድን መሪ 011-470-2468 0911-17-08-19

የህዝብ ግንኙነት ረዳት


5 ህዝብ ግንኙነት አቶ አብደላ ጉዲ 0911-54-95-42
ሀላፊ

የሠው ኃብት አስተዳደርና ጠቅላላ


6 ወ/ት ሃይማኖት ገ/ኪዳን ቡድን መሪ 011-470-2933 0914-73-48-87
አገልግሎት

7 የሥነ ምግባር ክትትል ክፍል አቶ ደረጀ ኪሮስ የስነ ምግባር መኮንን 0912115817

የመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት የዜጎች ቻርተር Page 14

You might also like