You are on page 1of 5

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የሰው ሃብት ሥራ አመራር ባለሙያ የሰው ሃብት ሥራ አመራር
IV ዳይሬክቶሬት

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


ለሰው ሃብት ሥራ አመራር ቡድን መሪ

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 የተቋሙን አደረጃጀትና የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ጥናቶችን በየጊዜው በማጥናት ደንብና መመሪያ
መሠረት በማድረግ የተቋሙን ዕቅድና ዓላማ ሊያሳካ የሚችል የሰው ሀብት እንዲሟሉ ለማድረግ ነው፡፡
2.2.ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡- የሰው ሀብት ሥራ አመራር ጥናቶችን በማጥናትና መመርያዎችን በማዘጋጀት ውጤታማ ማድረግ፣
 አዲስ የሰው ኃይል ፍላጎት ለሚያቀርቡ የሥራ ክፍሎች እንደአስፈላጊነቱ ጥናት በማካሄድና የሥራ ደረጃው
በመወሰን ለሚመለከተው ተቋም ያቀርባል፣ ሲፈቀድም በደንቡ መሠረት ይፈጽማል፡፡
 በተቋሙ አደረጃጀት መሠረት በየሥራ መደቦች ተገቢው የሥራ ዝርዝር እንዲዘጋጅ በማድረግና በመገምገ
የማሻሻያ ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ተፈጻሚነቱንም ይከታተላል፣
 በተቋሙ የተለያዩ የሰው ሀብት ሥራ አመራር መመሪያዎችና ማኑዋሎችን ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነቱን በመከታተ
እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡
 የተቋሙ ድርጅታዊ መዋቅር በሚሻሻልበት ጊዜ ጥናት በማድረግና ለሚመለከተው ያቀርባል ሲፈቀድ ተገቢው
በማሟላት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፡፡
ውጤት 2፡- በተቋሙ ውስጥ የሰው ኃይል እንዲሟላ ማድረግ፣
 ከተቋሙ በሚደርሰው የሰው ኃይል ፍላጎት መጠየቂያ ቅጽ መነሻ በማድረግ ለቅጥር፣ ለደረጃ ዕድገትና ለዝውው
ደንብና መመሪያ መሠረት በማድረግ ማስታወቂያ ያወጣል፣
 በማስታወቂያ መሠረት የተመዘገቡ አመልካቾችን መረጃ ያጣራል፣ምርጫ እንዲከናወን በማድረግ ያጸድቃል፡፡
 ፈተና በማዘጋጀት ወይም እንዲዘጋጅ በማድረግ ተወዳዳሪዎችን በመፈተን የፈተናውን ውጤት ያሳውቃል፣
 የተቀጠሩ ሠራተኞች የተቋሙንና የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣ደንቦችና መመሪያዎችን እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡
ውጤት 3፡- የሰው ሀብት ሥራ አመራር ሥራዎችን በደንብ እና መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ፣
 በተቋሙ የተወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ህግንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረጉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡

1
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

 በተቋሙ ላሉ ሠራተኞች የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ጭማሪ የሚገባችውን ሠራተኞች በመለየትና በጀት እንዲያዝላቸ


በማድረግ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፡፡
 የተቋሙን ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና መረጃ በየ 6 ወር በትክክል መሞላቱን በማረጋገጥ ያጠናቅራል፡፡
 በሥራ አፈጻጸም ውጤት መሠረት ሽልማት ማግኘት የሚገባቸውን በመለየት አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
 ለሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በየወቅቱ ለሚመለከተው ያቀርባል፣
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1 የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው የተቋሙ የሰው ኃይል ፍላጎት ደንብና መመሪያን መሠረት በማድረግ መሟላቱንና ማስፈጸምን፣አስተዳደራ
ጉዳዮችን የማየትና የመከታተል፣ የሰው ሃብትን በሚመለከት የተለያዩ ጥናቶችን የማካሄድና ማንዋሎች
መመሪያዎችን የማዘጋጀት፣ተፈጻሚነታቸውን የመከታተል፣ አዲስ ለሚጠይቁ የሥራ መደቦች የሥራ ዝርዝ
የማዘጋጀት እንዲሁም የሠራተኞችን የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት በመገምገም ተፈጻሚነቱን የመከታተል የመሳሰ
ተግባራትን ማከናወንን የሚጠይቅ ነው፡፡ በሥራ ክንውን ወቅት የሥራ ዘርፎች የሚወስዷቸው አስተዳደራ
እርምጃዎች ደንብና መመሪያን የተከተሉ አለመሆን፣ በሥራ አፈጻጸም ምዘና ወቅት ፍታሃዊ የሆነ ውጤት አለመስጠት
የተወዳዳሪዎችን መረጃ የማጣራት ሂደት አስቸጋሪ መሆን (የትምህርት መረጃ፣ የሥራ ልምድ) እና የሥራ አመራ
ማኑዋሎችንና መመሪያዎችን ለማዘጋጀት ጥናት በሚደረግበት ወቅት ውስብስብ መሆን የሚያጋጥሙ ችግሮች ሲሆ
እነዘህንም ችግሮች በደንብና መመሪያዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለሠራተኛችና ለኃላፊዎች በመስጠት፣የሥ
ዘርፎች የሥራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ተከትለው እንዲሰሩ ድጋፍና ክትትል በማድረግ፣ መረጃዎችን በጥንቃቄ
በአትኩሮት ማየትና ማጣራትን እንዲሁም የተቋሙን የሥራ ዘርፎች በማሳተፍና በመሥራት ይፈታሉ፡፡
3.2 ራስን ችሎ መስራት
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው በተቋሙ ስትራቴጂክ ዕቅድና የሰው ሃብት ሥራ አመራር ደንቦችና የአፈጻጸም መመሪያዎችን በመከተ
የሚከናወን ነው፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው በጥራት መከናወኑን በሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች አማካኝነት ይገመገማል፡፡
3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 በቅጥር፣ በደረጃ ዕድገትና በሠራተኞች ድልድል ወቅት ሥራው ሲከናወን በጥንቃቄ መከናወን አለበት፡፡ ይህ ባይሆ
ብቃት የሌላቸውን ሠራተኞች እንዲቀጠሩ ማድረግ እንዲሁም በሠራተኞች ላይ ቅሬታ ይፈጥራል በተጨማሪ
በሥራ ዘርፉና በተቋሙ ላይ ታዓማኒነትን ያሳጣል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 ሥረው የሠራተኛ ቅጥርና የደረጃ እድገት፣ ፈተናና የፈተና ውጤት፣ የዲስፕሊን ጉዳዮች ይፋ እስከሚደረግ ድረ
በሚስጥር መጠበቅ አለበት፣ ይህም ባይሆን በሠራተኛው፣ በሥራ ዘርፉና በተቋሙ ተዓሚነትን ማሳጣትንና ግጭት

2
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ይፈጥራል፡፡
3.4 ፈጠራ
 የተቋሙን የሰው ሀብት ሥራ አመራር ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ እንዲያስችል የተለያዩ የሰው ሃብት ሥ
አመራር ማንዋሎችን፣ መመሪያዎችን ለማሻሻልና ለማዘጋጀት ጥናት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ሥራው በተቋሙ ውስጥ ካሉ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ ከሥራ ዘርፉ ሠራተኞችና ኃላፊዎች፣ ለቅጥ
ከሚመጡ አመልካቾች፣ ፈተና ከሚሰጡ ተቋማት እንዲሁም ከሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ
ይጠይቃል፡፡
3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 የግንኙነቱ ዓላማው የሰው ሀብት ሥራ አመራር ሥራዎችን ቅጥር፣ የደረጃ እድገት፣ ዝውውር ምደባ፣ ልዩ ልዩ ጥቅ
ጥቅሞችን፣ የአገልግሎት ክፍያዎችን ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የዲስፒሊን ጉዳዮችን ለማየትና ለማጣራት
የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ለመገምገምና ቀጣይ ተግባራትን ለማከናወን እንዲሁም ሥራውን ተበብ
ለመስራትና ውጤታማ ለማድረግ ሲሆን ከውጭ ተወዳዳሪዎች ጋር መረጃ ለመለዋወጥ ፈተና ለመፈተንና ሙያ
ድጋፍ ለማግኛት ነው፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 በውሰጥ ካሉ ሠራተኞችና ኃላፊዎች ጋር 30%፣ ከውጭ ተፈታኞች፣ ፈታኞችና መንግሥታዊ ተቋማት 10
የግንኙነት ድግግሞሽ ያለበት ነው፡፡
3.6 ኃላፊነት
 ሥራው ኃላፊነት ለሰው ሀብት የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 ሥራው ኃላፊነት ለገንዘብ የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ እንደ ኮምፒዩውተር(ዴስክቶፕና ላፕቶፕ)፣ ፕርንተ
ጠረጴዛና ወንበር፣ ሼልፍ፣ የመሳሰሉትን ዋጋቸው እስከ 60000 ብር የሚደርስ በአግባቡ፣ በጥንቃቄ እንዳይበላ
የመጠበቅና የመያዝ ኃላፊነት አለበት፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 የሰው ሀብት ሥራ አመራር ስትራቴጅክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ የሥራ ዘርፉን ዕቅድ ማዘጋጀት(5%)፣ ጥናቶች
ማድረግ (15%)፣ የዲስፒሊን ኬዞችን ማየት (10%)፣ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ትንተና (Analysis
በማድረግ ስታትስቲካል መረጃዎች ማጠናቀር (10%)፣ በሰው ሀብት ሥራ አመራር የቅጥር የደረጃ እድገት
የዝውውር መረጃዎችን ማጣራት (10%)ና ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት (5%)ን የአዕምሮ ስ

3
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ሲሆን ከስራ ሰዓቱ ከ 55% ይወስዳል፡፡


3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 ሥራው በተቋሙ ውስጥና ከተቋሙ ውጭ ካሉ የተለያየ ባህሪ ካላቸው ሠራተኞችና ተወዳዳሪዎች ጋር በሥራ ወቅት
በቅጥር፣ በደረጃ ዕድገት፣ በዝውውር፣ በአስተዳደራዊ ነክ ጉዳዮች መገናኘትን የሚጠይቅ በመሆኑ ይህንን መነ
በማድረግ የተለያዩ አለመግባባቶች ሊነሱ ይችላሉ ይህም በሥነ ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ስለሆነም ሁልጊ
በመቻቻልና በትዕግሥት እንደተገልጋዩ ባህሪይ ራስን ለሥራ በማዘጋጀት ሥራውን ማከናወን ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ሥራው በኮምፒውተር ላይ ለጥናት የሚረዱ የጥናት ሰነዶችንና ጹሁፎችን ከተለያዩ ድረ ገጾች ማንበብን እነዲሁ
የጥናት ሰነዶችንና ሪፖርቶችን መጸፍን የሚጠይቅ በመሆኑ ከመደበኛ የስራ ጊዜው 40% የዕጥታ ጥረት ይጠይቃል፡፡

3.7.4 የአካል ጥረት


 ሥራው በአብዛኛው ጊዜ 85% በመቀመጥ፣5% በመቆም፣ 5% በእግር በመጓዝ እና 5% በመውጣትና በመውረ
የሚከናወን ነው፡፡
3.8. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 ሥራው ሥጋትና አደጋ የለበትም፡፡
3.8.2. የጤና ጠንቅ፣
 ሥራው በሚከናወንበት ወቅት የጤና ጠንቅ የለበትም፣

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


የመጀመሪያ ዲግሪ

የትምህርት ደረጃ የትምህርት ዓይነት


የመጀመርያ ዲግሪ በሥራ አመራር፣ በህዝብ አስተዳደር፣ ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ የአለም አቀፍ
ግንኙነትና ፖለቲካል ሳይንስ
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
7 ዓመት በሰው ሥራ አመራር ሙያ ቀጥታ ግንኙነት ያለው፣

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን


ቡድን 6

4
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like