You are on page 1of 21

ግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር

ለገበሬዎች ማሠልጠኛ ማዕከላት የተዘጋጀ የስርዓተ ትምህርት መመሪያ

የስራ አይነት፡ - ግመል አርቢ


-
የትምህርት አይነት፡ ግመል ርባታ
ሞዲዩል፡- 3

ግብርና ኤክስቴንሽን ቴ/ሙ/ት/ሥ/መምሪያ


ሰኔ 1996
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

ማ ው ጫ
ይዘት ርዕስ ገጽ

ዋና ሥራ 1 የግመል ርባታ ዓላማዎችን ማስቀመጥ

0
ዝርዝር ሥራ 1 ለግመል ርባታ ወሣኝ የሆኑ ነገሮችን መለየት
ዝርዝር ሥራ 2 የርባታውን አላማ መዘርዘር
ዋና ሥራ 2 ተስማሚ የሆኑ የግመል አያያዝ ስልትን መወሰን
ዝርዝር ሥራ 1 በመካሄድ ላይ ያለውን የግመሎችን የአያያዝ ስልት መለየት
ዝርዝር ሥራ 2 በአካባቢው የሚገኙትን ለግመሎች የሚሆኑ የመኖ ምንጮችን ማሠስና
መከተል የሚገባንን የአያያዝ ስልት መወሰን
ዋና ሥራ 3 የግመሎችን ስነ-ተዋልዶ መከታተል
ዝርዝር ሥራ 1 የግመሎችን የስነ-ተዋልዶ ስልቶችን መለየት
ዝርዝር ሥራ 2
ዝርዝር ሥራ 3 ተስማሚ የሆነ የጥቂ ስልትንና የርቢ ወቅትን መወሰን
ዝርዝር ሥራ 4 እርጉዝ ግመል መንከባከብና ወሊድን ማገዝ
ዝርዝር ሥራ 5 የወተት ግመሎችን መንከባከብ
ዋና ሥራ 4 መንጋን መንከባከብ
ዝርዝር ሥራ 1 ማኮላሸት /መቀጥቀጥ/
ዝርዝር ሥራ 2 የግመልን ዕድሜና ክብደት መገመት
ዝርዝር ሥራ 3 የአርብቶ አደሩን የመንጋ እንክብካቤ የሚጎዱ ነገሮችን መለየት
ዋና ሥራ 5 ግመሎችን መመገብ
ዝርዝር ሥራ 1 የግመል መኖ ምንጮችን መለየትና በተለያዩ የዕድሜ ክልል ለሚገኙ
ግመሎች መኖ ማዘጋጀት
ዝርዝር ሥራ 2 ግመሎችን ለግጦሽ /ለቅንጣባ/ ማሠማራትና ተጨማሪ መኖ
መመገብ
ዝርዝር ሥራ 3 የመጠጥ ውሃ የፍላጐት መጠንን ማወቅ
ዋና ሥራ 6 የግመልን የወተት ምርት የመስጠት አቅም መለየትና የወተት አያያዝን
ማወቅ
ዝርዝር ሥራ 1 የግመልን የወተት ምርት ምርት የመስጠት አቅም መለየት
ዝርዝር ሥራ 2 ማለብ
ዝርዝር ሥራ 3 የወተት አያያዝና ወተትን ማቀነባበር
ዋና ሥራ 7 ግመልን ማድለብ
ዝርዝር ሥራ 1 ለማድለብ የሚሆኑ ግመሎችን መምረጥ
ዝርዝር ሥራ 2 የግመልን የሥጋ ምርት የመስጠት አቅም መለየት
ዝርዝር ሥራ 3 የማድለብ ሥራን ማካሄድ
ዋና ሥራ 8 የግመል በሽታዎችን ማገናዘብ
ዝርዝር ሥራ 1 በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን መለየት
ዝርዝር ሥራ 2 በኘሮቶዞዋ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን መለየት
ዝርዝር ሥራ 3 የግመል ጥገኞችን መለየት
ዝርዝር ሥራ በሽታዎችን መከላከል

ዋና ሥራ 1 የግመል ርባታ ዓላማዎችን ማስቀመጥ


ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል ርባታ ዓላማዎችን መዘርዘር ይችላሉ
ዝርዝር ሥራ 1- ለግመል ርባታ ወሣኝ የሆኑ ነገሮችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል ርባታ ወሣኝ ነገሮችን ይለያሉ

1
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘቶች
 የመሬት ስፋት
 የአየር ፀባይ
 የግብዓቶች መገኘት
 የገበያ ሁኔታ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 ስኬታማ የሆኑና ስኬታማ ያልሆኑ የርባታ ጣቢያዎችን ታሪክ በማውራት
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 የመኖ ምንጮች
 የዓየር ንብረት መረጃ
 ግመሎች
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይት መገምገም
 በዋና ዋና ነጥቦች አጠቃላይ ገለፃ እንዲያደርጉ መጋበዝ
ዝርዝር ሥራ 2 የርባታውን ዓላማ መዘርዘር
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል ርባታ ዓላማዎችን መወሠን ይችላሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ለወተት፣ ለስጋ ወይም ለጉልበት የሚሆኑ ግመሎችን መለየት
 ለግመል ውጤቶች ጥሩ ገበያ መኖሩን ማጥናት
 ለሚፈለገው የርባታ ዓላማ ግመሎች መኖራቸውን ማረጋገጥ

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 ገለፃና ውይይት
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት
ሐ/ የማሰልጠኛ ቁሳቁስ
 የገበያ ጥናት መረጃ

2
 ለተለያየ ምርት የሚያገለግሉ የግመል ዝርያዎች
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በግሩኘ ውይይት መገምገም
ዋና ሥራ 1 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በጥያቄና መልስ መገምገም
ዋና ሥራ 2 ተስማሚ የሆነ የግመል አያያዝ ስልቶችን መወሠን
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ተስማሚ የሆነ የግመል አያያዝ ስልቶችን
ይወስናሉ
ዝርዝር ሥራ 1 በመካሄድ ላይ ያለውን የግመሎችን የአያያዝ ስልቶች መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል አያያዝ ስልቶች ይለያሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 የልምድ ልውውጥ
 በአካባቢያቸው ተስማሚ የሆነውን የአያያዝ ስልት መለየት
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት
 የግመልና መንጋ መጎብኘት
ሐ/ የማሠልጠ ኛ ቁሳቁስ
 መጽሐፍት
 የርባታ ጣቢያ /የግመል መንጋ
 በተለያዩ የርባታ ስልቶች የሚጠቀሙ የመኖ ምንጮች
 ስላድና ፎቶግራፍ
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 የግሩኘ ስራ በመስጠትና በውይይት የሠልጣኞችን ክህሎት መፈተሽ
ዝርዝር ሥራ 2 በአካባቢው የሚገኙትን ለግመል የሚሆኑ የመኖ ምንጮች ማሠስና
መከተል የሚገባንን የአያያዝ ስልት መወሰን
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች በአካባቢያቸው የሚገኙትን የመኖ ምንጮች
ማሠስ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ተስማሚ የሆነ የአያያዝ ስልትን ይወስናሉ፡፡
የስልጠና ይዘቾች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት

3
 የመኖ ምንጮች መገኘትና ወቅታዊ ስርጭታቸው
 በአካባቢው መሬት የማግኘት ዕድል መኖር
 የንፁህ ውሃ መገኘት
 የግጦሽ መሬት አካባቢዎች
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃ
 የልምድ ልውውጥ
 ቪዲዬ ፊልም ማሣየት
 የግጦሽ መሬት ጉብኝት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 የተለያዩ የአያያዝ ስልቶች ስዕላዊ መግለጫ
 መጽሐፍት /የማገናዘቢያ ጹህፍ
 ቪደዬ
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 ተስማሚ የአያያዝ ስልት መምረጥ መቻላቸውን በውይይት መገምገም
 በቪዲዮ ፊልሙ ላይ ያላቸውን አመለካከት በመገምገም
 የግጦሽ መሬት አሠሣ ሲደረግ የሠልጣኞችን ብቃት መገምገም
ዋና ሥራ 2 ግምገማ
 ተስማሚ የአያያዝ ስልት የመምረጥ ክህሎትና ዕውቀታቸውን በተግባርና በጹህፍ መፈተን

ዋና ሥራ 3 የግመሎችን ስነ-ተዋልዶ መከታተል


ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን ስነ-ተዋልዶ መከታተል ይችላሉ
ዝርዝር ሥራ 1፡- የግመሎችን የስነ-ተዋልዶ ስልቶችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን ስነ-ተዋልዶ ስልት ይለያዩ
የስልጠና ይዘቶች ፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የወንድ የመራቢያ አካላት
 የሴት የመራቢያ አካላት
ለ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 ገለፃና ውይይት
 የልምድ ልውውጥ

4
 ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማጠቃለያ ማድረግ
 በመራቢያ አካላትን በቪዲዬ ማሣየት
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 መፃህፍት
 የተጠናከረ ጹህፍ
 የወንድና ሴት ግመል ስዕል
 ፎቶግራፍ
 የቪዲዬ ፊልም
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይት መገምገም
 በቪዲዬ ፊልሙ ምን እንደተገነዘቡ መገምገም

ዝርዝር ሥራ 2
ዓላማ፡- ኪዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ ይዘት
 ለርቢ የሚደርሱበት ዕድሜ
 ለርቢ ዕድሜያቸው ሲደርስ የሚያሣዩዋቸው ምልክቶች /ወንድና ሴት ግመሎች/
 የድሪ ሰዓት መጀመር /ለሴትና ለወንዱ/
 የድሪ ሰዓት ምልክቶች
 የወንዱ የድሪ ሰዓት ርዝመት
 የድሪ ሰዓት ርዝመትና ድግግሞሽ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 ልምድ ልውውጥ ማድረግ

5
 ቪዲዬ ፊልም ማሣየት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ስዕሎች
 ወንድና ሴት ግመሎች
 መጽሐፍት
 ቪዲዬ
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይትና በተግባር ሥራ መገምገም
 ከቪዲዬ ፊልሙ ምን እንደተገነዘቡ በመገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- ተስማሚ የሆነ የጥቂ ስልትንና የርቢ ወቅትን መወሰን
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ተስማሚ የሆነ የጥቂ ስልትንና የርቢ ወቅትን
ይወስናሉ፡፡
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ለርቢ የሚሆን ኮርማ መምረጥ /አቋምና ብቃትን መለየት
 ለርቢ የሚሆኑ ሴት ግመሎችን መምረጥ
 የወንድና የሴት ጥንቅርን መወሰን
 የሚወገዱ ዕድሜ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃ
 ማብራሪያና ውይይት
 ተፈላጊ ግመሎች አመራረጥ የተግባር ሥልጠና
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 ስዕሎች
 የግመል ርባታ ጣቢያ
 መጽሐፍት
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ክትትል በውይይትና በተግባር ሥራ መገምገም
ዝርዝር ሥራ 4፡- እርጉዝ ግመል መንከባከብና ወሊድን ማገዝ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች እርጉዝ ግመል መንከባከብና ወሊድን ማገዝ
ይችላሉ፡፡

6
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የዕርግዝና ምልክቶች
 የዕርግዝና ጊዜ ርዝመት
 በዕርግዝና ወቅት የሚደረግ እንክብካቤ
 የወሊድ ጊዜ መቃረብን አመልካች ሁኔታዎች
 የወሊድ ምልክቶች
 ትክክለኛ ውልጃ
 ወሊድን ማገዝ
 አዲስ በተወለደ ጥጃ አያያዝ
 የእናቶችና ጥጆች አያያዝ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 የዕርጉዝ ግመል ተከለ ቁመናን በማየት
 ዕርግዝናን ስለመለየት በተግባር ማስተማር
 ወሊድን እንዲያግዙ በተግባር ማለማመድ
ሐ/ የማሠልኛ ቁሳቁሶች
 የርባታ ጣቢያ
 የስላይድ ፎቶግራፍ
 የትክክለኛና ትክክለኛ ያልሆነ ውልጃ በስዕላዊ መግለጫ
 መጽሐፍት
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ግንዛቤ በውይይትና በፈተና መገምገም
 የሠልጣኞችን ተግባር በስራና በሪፖርታቸው መገምገም
ዝርዝር ሥራ 5- የወተት ግመሎችን መንከባከብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የወተት ግመሎችን መንከባከብ ይችላሉ፡፡
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የወተት ግመሎች እንክብካቤ
 የወተት ግመሎች አመጋገብ
 አስተሳሰብ

7
 ማንጠፍ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራራትና ውይይት
 በይዘቶች በሙሉ የተግባር ሥራ ማሠራት
 የልምድ ልውውጥ
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት

ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 የሚታለቡ ግመሎች
 መኖ
 መጽሐፍት

ዝርዝር ሥራ 4 ግምገማ
 በውይይትና በተግባር ሥራ ላይ ሠልጣኞችን መገምገም
ዋና ሥራ 3 ግምገማ
 ሠልጣኞች የጨበጡትን ክህሎትና ዕውቀት በተግባርና በጹህፍ መፈተን
ዋና ሥራ 4፡- መንጋን መንከባከብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች መንጋን መንከባከብ ይችላሉ፡፡
ዝርዝር ሥራ 1፡- ማኮላሸት /መቀጥቀጥ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ግመሎችን ማኮላሽት ይችላሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና የማሠልጠኛ ቁሳቁስች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 በማኮላሸት ጊዜ የግመሎች አያያዝ
 የማኮላሸት ዕድሜና ዘዴን መወሰን
 በተገቢው መሣሪያ ማኮላሸት
 ከተኮላሹ በኋላ የሚደረግ እንክብካቤ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራሪያ ውይይት
 የልምድ ልውውጥ
 ስዕሎችን መስጠት
 በርባታ ጣቢያ የተግባር ሥራ ማሠራትና ሪፖርት እንዲቀርቡ ማድረግ

8
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ወንድ ግመሎች
 የማኮላሸት ቁሳቁሶች
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 የማኮላሸት የተግባር ሥራ በማሠራት ክህሎታቸውን መገምገም
 የሚቀርበውን ሪፖርት በመገምገም
ዝርዝር ሥራ 2- የግመልን ዕድሜና ክብደት መገመት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን ዕድሜና ክብደት ይገምታሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች

ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ጥርስን በማየት ዕድሜን መገመት
 ዕድሜን ለመገመት የሚያስፈልጉ መረጃዎች
 በክብደት መለኪያና በደረት መጠነ ዙሪያ መለኪያ ሜትር ክብደትን የመለካት ስልቶችን ማሣየት
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገላፃና ውይይት
 የርባታ ጣቢያ ጉብኝት
 የግሩኘ ሪፖርት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 የተለያየ ዕድሜ ያላቸው ግመሎች
 የክብደት መለኪያ ቁሳቁሶች
 የማጣቀሻ ጹህፎች
 የማገናዘቢያ ጹህፍ
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን የዕድሜና ክብደትን መገመት ክህሎታቸውን መገምገም
 የግሩኘ ሪፖርቱን በመገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- የአርብቶ አደሩን የመንጋ እንክብካቤ የሚጎዱ ነገሮችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የአርብቶ አደሩን የመንጋ አንክብካቤ የሚጎዱ
ነገሮችን ይለያሉ፡፡
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት

9
 የመንጋ ስብጥር
 የግጦሽ መሬት ሁኔታ
 የውሃ ፍላጎት
 የሠው ጉልበት መገኘት
 ግመሎች የሚረቡበት ዓላማና በእነርሱ ላይ ያላቸው የጥገኝነት መጠን

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 ከላይ በተዘረዘሩት ይዘቶች ላይ የተግባር ሥራ ማሠራት
 የልምድ ልውውጥ
 የተጠናከረ ጹህፍ
 የቪዲዮ ፊልም

ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 መጽሐፍት
 የማገናዘቢያ ፉህፍ
 ቪዲዮ
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይትና በጹህፍ መገምገም
 የተግባር ክህሎታቸውን መገምገም
 በቪዲዮ ፊልሙ የተገነዘቡትን መገምገም
ዋና ሥራ 4 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ክህሎትና ዕውቀት፣ በውይይትና በመስክ የተግባር ሥራና በጹህፍ ፈተና መገምገም
ዋና ሥራ 5 ግመሎችን መመገብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች በአካባቢያቸው የሚገኙ የግመል መኖ
ምንጮችን ይለያሉ፣ የአመጋገብ ዘዴያቸውንም ያውቃሉ
ዝርዝር ሥራ 1፡- የግመል መኖ ምንጮችን መለየትና በተለያዩ የዕድሜ ክልል
ለሚገኙ ግመሎች መኖ ማዞጋጀት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የመኖ ምንጮችን መከፋፈል በተለያየ የዕድሜ
ክልል ላሉ ግመሎች መኖ ማደባለቅና እንደ ንጥረ ነገር የፍላጐት መጠናቸው

10
መመገብ ይችላሉ

የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች

ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ግመል ቀንጣቢ እንስሳ
 የግመል የምግብ ዓይነቶች /ሣር፣ ቁጥቋጦ
 በአካባቢው የመኖ ዓይነቶች መገኘታቸውን ማረጋገጥ
 የግመሎችን የንጥረ ነገር ፍላጎት መለየት
 ምግቦችን ማሠባሰብ
 ድብልቅ መኖ ማዘጋጀት
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 የምግቦችን ክፍፍል ማሠራት
 በተግባር የምግብ ዝግጅት ማሠራት
 የግሩኘ ሪፖርት እንዲቀርቡ ማድረግ
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ምግቦች ናሙና
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 ለግመል መኖ የሚሆኑ ምግቦችን የመለየት ክህሎታቸውን በተግባር መፈተን
 ለግመል መኖ የሚሆኑ መኖ ምንጮችን የማዘጋጀት ክህሎታቸውን በተግባር መፈተን
 የተለያዩ ዕድሜ ላላቸው ግመሎች መኖ የማዘጋጀት ክህሎታቸውን በተግባር መፈተን
 በግሩኘ ሪፖርት አቀራረባቸው ላይ ዕውቀታቸው መገምገም
ዝርዝር ሥራ 2፡- ግመሎችን ለግጦሽ /ለቅንጣቢ/ ማሠማራትና ተጨማሪ መኖ
መመገብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ግጦሽን /ቅንጣቢን/እንዴት መጠቀም
እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ ግመሎች ለሚሰጡት ምርት ተመጣጣኝ የሆነ ተጨማሪ
መኖ ይመገባሉ፡፡

11
የስልጠና ይዘት፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች

ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ግጦሽን /ቅንጣቢን/ መቆጣጠር
 የመንጋ አያያዝ /መንጋን መከፋፈል/
 የውሃ አያያዝ
 የግጦሽ መሬት አያያዝ
 አመጋገብ

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 ልምድ ልውውጥና ውይይት
 በግጦሽ መሬት አያያዝና ተጨማሪ መኖ ዝግጅትና አመጋገብ የተግባር ሥራ ማሠራት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 የግጦሽ መሬት
 ተጨማሪ መኖዎች
 ግመሎች
 የተመጠነ መኖ ድብልቅ ሠንጠረዥ
 ስዕሎች
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ክህሎት በውይይትና በተግባር ሥራ መገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- የመጠጥ ውሃ ፍላጎት መጠንን ማወቅ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን የመጠጥ ውሃ ፍላጎት መጠን
ያውቃሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ውሃ የመጠጣት አቅምና የውሃ ምንጮች
 የውሃ የማጠጣር አቅምና የውሃ ምንጮች
 ውሃን ማሰባሰብ
 የውሃ አጠቃቀም

12
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት
 በአካባቢው በሚገኙ የውሃ ምንጮች የተግባር ሥራ ማሠራት
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት

ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁስ
 የውሃ ምንጮች መረጃ
 በአካባቢው የአየር ፀባይ ሁኔታ ካርታ
 የሠልጣ ኞች ብቃት በውይይትና በቡድን ሥራ መገምገም
ዋና ሥራ 5 ግምገማ
 የሠልጣኞችን አቅም በተግባርና በጹህፍ ፈተና መገምገም
ዋና ሥራ 6፡- የግመልን ወተት ምርት የመስጠት አቅም መለየትና
የወተትና የወተት አያያዝን ማወቅ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን የወተት ምርት የመስጠት
አቅማቸውን መለየትና የወተት አያያዝን ያውቃሉ
ዝርዝር ሥራ 1፡- የግመል ወተት የመስጠት አቅም መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን ወተት የመስጠት አቅም ይለያሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 በአንድ የመታለቢያ ወቅት የሚሰጡት የወተት መጠን
 ማለብና የወተት ፍጆታ
 የወተት ምርትን የሚያዛቡ ነጥቦች
 የግመል የወተት ፊዚካልና ኬሚካላዊ ባህሪያት

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት ማድረግ
 ሠልጣኞች የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ማነሣሣት
 የወተት ምርትን ማገናዘቢያ የተግባር ሥራ ማሠራት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች

13
 የምትታለብ ግመል
 የወተት ምርት መረጃ
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይትና በልምድ ልውውጥ ጊዜ መገምገም
ዝርዝር ሥራ 2 ማለብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የማለብ ቅደም ተከተሎችንና ማለብ ያውቃሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች

ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የማለቢያ ዕቃዎችን ማዘጋጀት
 የሚታለቡ ግመሎችን መቆጣጠር
 እናት ያገለለችውን ጥጃ እንድታጠባ ማስገደድ
 ማለብ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራሪያና ውይይት ማድረግ
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 የተግባር ሥራ ማሠራትና የቡድን ውይይት እንዲያደርጉ ማነሣሣት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 የማሠሪያ ገመድ
 የማለቢያ ዕቃ
 የሚታለቡ ግመሎች
 መጽሐፍት

ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ችሎታ በአለባ ሰዓት መገምገም
 በቡድን ውይይት ላይ ዕውቀታቸውን መገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- የወተት አያያዝና ወተትን ማቀነባበር
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የወተት አያያዝና ወተትን ማቀነባበር ይችላሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት

14
 ትኩስ ወተትን የማከማቸት ቅደም ተከተሎች
 ወተትን የማቀነባበር ቅደም ተከተሎች
 የማቀነባበሪያ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት ማድረግ
 የተጠናከረ ጹህፍ መስጠት ቡድን በመስራት ትኩስና የመረረ ወተትን እንዲያቀነባብሩ ማድረግ

ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 የወተት ማከማቻ ዕቃ
 የማቀነባበሪያ ቁሳቁሶች /መናጫ፣ የክሬም መለያ/
 ወተት
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 በወተት ማከማቸትና የማቀነባበር ስልቶች የሠልጣኞችን ችሎታ መገምገም
 በቡድን ያቀነባበሩትን ወተት ውጤት በማየት መገምገም
ዋና ሥራ 6 ግምገማ
 በመስክ የተግባር ሥራና በክፍል ተሳትፎ የሠልጣኞችን ዕውቀትና ክህሎት መገምገም

ዋና ሥራ 7 ግመል ማድለብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞችን የግመል ማድለቢያ ጣቢያ ሥራን ማካሄድ
ይችላሉ
ዝርዝር ሥራ 1፡- ለማድለብ የሚሆኑ ግመሎችን መምረጥ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ለማድለብ የሚሆኑ ግመሎችን ይመርጣሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ዕድሜ
 የሠውነት አቋም
 ጤና

15
ለ/ የማሠልጠ ኛዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት ማድረግ
 ገበያዎችን ወይም የርባታ ጣቢያዎችን መጎብኘት
 የቡድን ውይይት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ግመሎች
 የግመሎችን ጥርስና የሠውነት አቋም የሚገልጹ ስዕሎች
ዝርዝር ሥራ 1 ግምገማ
 ለማድለብ የሚሆኑ ግመሎችን እንዲመረጡ በማድረግ ክህሎታቸውን መገምገም
ዝርዝር ሥራ 2፡- የግመሎች የስጋ ምርት የመስጠት አቅም መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመሎችን የስጋ ምርት የመስጠት
አቅማቸውን ይለያሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የፍላጎትና አቅርቦት መጠንን ማወቅ
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራሪያና ውይይት ማድረግ
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 የቪዲዬ ፊልም ማሣየት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ግመል
 ቪዲዮ፣ ፎቶግራፍ
 የግመል ሥራ ፍጆታ መረጃ
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 የሠልጣኞችን አቅም በውይይትና በተግባር ሥራ መገምገም
 በቪዲዬ ፊልሙ ያዳበሩትን ዕውቀት መገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- የማድለብ ሥራን ማካሄድ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል የማድለብ ሥራን ያካሂዳሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የማድለቢያ ዘዴዎችን መምረጥ

16
 የሚደልቡ ግመሎችን ማዘጋጀት
 ተስማሚ የሆነ የአመጋገብ ስርዓትን መምረጥ
 የማድለቢያ ጊዜን መወሰን
 ለገበያ ማቅረብ /መሸጥ/
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት ማድረግ
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 ጥሩ የርባታ ጣቢያዎችን ማስጎብኘትና የቡድን ሪፖርት እንዲያቀርቡ ማድረግ
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ግመሎች
 የተለያዩ የመኖ ዓይነቶች
 ሚዛን
 መመገቢያና መጠጫ ገንዳዎች
 መጽሐፍት
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 በበቂ ሁኔታ የግመል ማድለብ ስራ ማካሄድ መቻላቸውን መፈተን
 በቡድን ሪፖርትና ውይይት ዕውቀታቸውን መገምገም
ዋና ሥራ 7 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በተግባርና በንድፈ ሃሳብ ፈተና መገምገም
ዋና ሥራ 8 የግመሎች በሽታዎችን ማገናዘብ
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል በሽታዎችን ያገናዝባሉ
ዝርዝር ሥራ 1፡- በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን
ይለያዩ

የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች


ሀ/ የስልጠና ይዘት
 አባ ሠንጋ

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ገለፃና ውይይት ማድረግ

17
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 ቪዲዬ ፊልሙ ቁሳቁሶች
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 መጽሐፍት
 ግመሎች
 ቪዲዬ
ዝርዘር ሥራ 1 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት በውይይት መገምገም
 በቪዲዬ ፊልሙ ያዳበሩትን ዕውቀት በመገምገም
ዝርዝር ሥራ 2፡- በኘሮቶዞዋ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች በኘሮቶዞዋ አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን
ይለያሉ
የስልጠና ይዘቾች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የስነ-ተዋልዶ በሽታዎች
ለ/ የማሠልጠኛ ዘሪዴዎች
 ገለፃና ውይይት በማድረግ
 የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ ማድረግ
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ማጽሐፍት
 የታመሙ ግመል ስዕላዊ መግለጫ
ዝርዝር ሥራ 2 ግምገማ
 ጥያቄና መልስ በማድረግ የሠልጣኞችን ብቃት መገምገም
ዝርዝር ሥራ 3፡- የግመል ጥገኞችን መለየት
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች የግመል ጥገኞችን ይለያሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 የ ውስጥ ጥገኛ
 የውጭ ጥገኛ

18
ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራሪያና ውይይት ማድረግ
 የልምድ ልውውጥ
 ጥገኞች ያሉባቸውን አካባቢዎች መጎብኘት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 መጽሐፍት
 ስዕሎች
 ፎቶግራፍ
ዝርዝር ሥራ 3 ግምገማ
 የሠልጣኞችን ብቃት ጥገኞችን እንዲለዩ በማድረግ መገምገም
ዝርዝር ሥራ 4፡- በሽታዎችን መከላከል
ዓላማ፡- ከዚህ ስልጠና በኋላ ሠልጣኞች ተገቢውን ጥንቃቄና እርምጃ በመወሰድ
በሽታዎችን መከላከል ይችላሉ
የስልጠና ይዘቶች፣ የማሠልጠኛ ዘዴዎችና ቁሳቁሶች
ሀ/ የስልጠና ይዘት
 ተመጣጣኝ ንጥረ ነገር ያለው መኖ መመገብ
 የታመሙ ግመሎች እንክብካቤ
 ንፅህናን መጠበቅ
 ተገቢ የሆነ የግጦሽ አስተዳደር

ለ/ የማሠልጠኛ ዘዴዎች
 ማብራሪያና ውይይት ማድረግ
 የልምድ ልውውጥ ማድረግ
 ዋና ዋና ነጥቦችን ማጠቃለያ መስጠት
ሐ/ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች
 ግመሎች
 መጽሐፈት
 የፅዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶች

19
ዝርዝር ሥራ 4 ግምገማ
 በውይይትና በተግባርና የንድፈ ሃሳብ ፈተና በመስጠት የሠልጣኞችን ብቃት መገምገም

ዋና ሥራ 8 ግምገማ
 በተግባርና በንድፈ ሃሳብ የሠልጣኞችን ዕውቀትና ክህሎት መገምገም

20

You might also like